Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
@telemetr_io_bot
Telegram analytics bot

The bot can:

  • analyze channel audience
  • channels intersections
Channel location and language
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። .  #ዝማሬ_ዳዊት  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት  @zmaredawit_messengerbot  ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል 
Show more
179 5330
~25 323
~65
14.09%
Telegram general rating
Globally
5 687place
of 3 850 983
44place
of 10 453
In category
1place
of 1 320

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

#የአንተ_ሥራ የአንተ ሥራ የአንተ ሥራ የአንተ ሥራ ለዓለም ይወራ (፪) በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት መጻጉዕ ተብሎ ተኝቶ ባዐራት ዘመን ያስቆጠረ ሠላሳ ስምንት ተነሳ ተባለ አገኘ ምህረት #አዝ ሰውነቱ ደቆ እጅግ የታመመ (፪) በሱ ድንቅ ስራ አልጋ ተሸከመ (፪) #አዝ ወገን ያልነበረው ወድቆ የተረሳ (፪) ምሕረት አገኘና በድንገት ተነሳ (፪) #አዝ ያዳነው ኢየሱስ መሆኑን ሲናገር ያልተፈቀደውን ይሄው ሰንበት ሲሽር አየነው ሰማነው አያሻም ምስክር ብለው ተነሱበት በጠማማ ምክር መዝሙር ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ "ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ" ዮሐ፭፥፰ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

406245552.mp3

9 586
77
#አቡነ_ሃብተ_ማርያም_ጻድቅ እኒህ ጻድቅ ደግሞ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል:: ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ: እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ: ምጽዋትን ወዳጅ: ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር:: ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች:: ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር:: የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል:: ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው: መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም:: ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ:: በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው) በ40 ቀናት: ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ:: ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው:: በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና) ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ: ክቡር ደሙን ይጠጣሉ:: በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን: መከፋትን አላሳደሩም:: በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው:: "ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::" "በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው:: ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት:: #የናግራን_ሰማዕታት በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ናግራን (የአሁኗ የመን) የክርስቲያኖች ሃገር ነበረች:: የሳባ ግዛትን የእኛ ነገሥታት ሲተዋት የተተካው ፊንሐስ ደግሞ ጨካኝ አይሁዳዊ ነበርና ናግራንን ሊያጠፋት ተመኘ:: ቀጥሎም "ሃገራችሁን ልጐብኝ" ብሎ በማታለል ገባ:: ወዲያውም ሕዝቡንና ካህናትን ሰብስቦ "ክርስቶስን ካዱ" አላቸው:: ጽኑ ክርስቲያኖች ግን "አይደረግም" አሉት:: እርሱም ሊያስፈራራቸው አስቦ 4,000 ያህል ካህናት: ዲያቆናትና ምሑራንን ጨፈጨፋቸው:: ይሕንን አድርጐ "አሁንሳ?" አላቸው:: ሕዝቡ ግን አሁንም "ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን የለም" አሉት:: (ሮሜ. 8:5) ጨካኙ ፊንሐስም እንደ ገና ከሕዝቡ መካከል ከ4,100 በላይ የሚሆኑትን ጨፈጨፈ:: ታላቁን ቅዱስ ሒሩትንም (የሕዝቡ መሪ ነው) ብዙ አሰቃይቶ ሰየፈው:: ሚስቱን ቅድስት ድማሕንም 2 ሴት ልጆቿን ሰይፈው የልጆቿን ደም አጠጧት:: ከዚያም ሰየፏት:: ይሕንን የተመለከቱ የናግራን ክርስቲያኖች ግን ስለ መፍራት ፈንታ በፈቃዳቸው እየተሯሯጡ ወደ እሳትና ሰይፍ ተሽቀዳደሙ:: ከተማዋም እየነደደችና ደም እየፈሰሰባት ለ40 ቀናት ቆየች:: ይሕንን የሰማው ቅዱሱ አፄ ካሌብም ደርሶ የተረፉትን ሲታደግ ፊንሐስን ከነ ወታደሮቹ አጥፍቶታል:: አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን:: #ኅዳር 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ 2.አቡነ ሃብተ ማርያም ንጹሕ 3.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን 4.ቅዱስ ሒሩት አረጋዊ 5.ቅዱሳን ቢላርያኖስ: ኪልቅያና ታቱስብያ (ሰማዕታት) 6.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘደሴተ ሰንሲላ 7.ቅድስት ዮስቴና ቡርክት #ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን " እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" (መዝ. 36:28-31) ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞ ✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞ ✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞ ዝክረ ቅዱሳን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
11 697
106
ለገጠር ቤተክርስቲያን መርጃ ይሆን ዘንድ የተለገሰው ቲሸርት በመግዛት አገልግሎት ይደግፉ! ቅዱስ ቂርቆስ ሰንበት ትምህርት ቤት ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ያገኛሉ ዋጋው 200 ብር ብቻ ነው (ጨርቆስ)። ለበለጠ 251927707000 ይደውሉልኝ በቴሌግራም አድራሻ @BeGood16 ላይ ማናገር ይችላሉ። በተጨማሪም ቲሸርቱን ለማግኝት አዲስ አበባ 251927707000 ወላይታ 251910005860 አዳማ 251964356337 እግዚአብሔር ይስጥልኝ ሼር በማድረግ ይተባበሩ! እዚህ ላይ ይቀላቀሉ 👇👇👇👇 https://t.me/KeAbawandebet https://t.me/KeAbawandebet https://t.me/KeAbawandebet
9 290
24
​​✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ #ኅዳር ፳፮ #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ_ዘሐይቅ እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው:: እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር: የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል:: ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ:: አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት: የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ: ሲፈጩ: ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ:: በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ: ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው:: በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ: በስብከተ ወንጌል: በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ:: ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ:: በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው:: ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ:: ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል:: እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ: በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም:: "እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ:: መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል:: ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: <<ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው!!>> ዝክረ ቅዱሳን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
10 735
36

file

10 852
18
10 687
6
​​✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ እንኳን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር)" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ኃያል ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው:: ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር:: አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: 2 ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር:: እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል:: እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው:: ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው:: "ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ 2ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት:: ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና 2ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ:: አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው:: ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ:: ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ:: በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ5 ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው:: እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ:: በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት:: በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ:: ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቁዋቁዋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት:: እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም:: ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ:: በ3ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው:: "ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: (ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ)" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው:: ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት:- "አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም:: እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም:: አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት:: ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር 25 ቀን አንገቱን ሰይፈውታል:: እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ200 ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ220 ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ225 ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል:: <<የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው>> አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን:: #ኅዳር_25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት 2. ቅዱሳን ታቦትና ኖኅ (ወላጆቹ) 3. ቅዱስ ሮማኖስ ዝክረ ቅዱሳን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
12 776
67
ለገጠር ቤተክርስቲያን መርጃ ይሆን ዘንድ የተለገሰው ቲሸርት በመግዛት አገልግሎት ይደግፉ! ቅዱስ ቂርቆስ ሰንበት ትምህርት ቤት ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ያገኛሉ ዋጋው 200 ብር ብቻ ነው (ጨርቆስ)። ለበለጠ (092) 770-7000 ይደውሉልኝ በቴሌግራም አድራሻ @BeGood16 ላይ ማናገር ይችላሉ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ ሼር በማድረግ ይተባበሩ! እዚህ ላይ ይቀላቀሉ 👇👇👇👇 https://t.me/KeAbawandebet https://t.me/KeAbawandebet https://t.me/KeAbawandebet
7 605
23
ለገጠር ቤተክርስቲያን መርጃ ይሆን ዘንድ የተለገሰው ቲሸርት በመግዛት አገልግሎት ይደግፉ! ቅዱስ ቂርቆስ ሰንበት ትምህርት ቤት ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ያገኛሉ ዋጋው 200 ብር ብቻ ነው (ጨርቆስ)። ለበለጠ (092) 770-7000 ይደውሉልኝ በቴሌግራም አድራሻ @BeGood16 ላይ ማናገር ይችላሉ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ ሼር በማድረግ ይተባበሩ! እዚህ ላይ ይቀላቀሉ 👇👇👇👇 https://t.me/KeAbawandebet https://t.me/KeAbawandebet https://t.me/KeAbawandebet
10 091
37
#እናታችን_ጽዮን እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምስጋና መጠጊያ ማረፊያ ጥላችን ነሽና ከገነት ብንወጣ ማረፊያ ሆንሽን የምሕረት ደመና ውኃ ሰጠሽን የሕይወት እንጀራ አመጣሽልን በአስራትም በአደራም ለአንቺ ተሰጠን #አዝ የኤልጣቤጥ አጽናኝ የጭንቅ ቀን ደራሽ የኃጢአታችን ብዛት ዳገት ሳይሆንብሽ ምሥራችን ደስታን ይዘሽልን መጣሽ ማርያም ስንልሽ ደረስሽልን ፈጥነሽ #አዝ ውለታሽ ብዙ ነው ለልብ የማይጠፋ ስምሽ መጽናኛ ነው አዝኖ ለተከፋ በእንተ ማርያም ብሎ ለለመነ የሰማይ የምድሩም ማንም አልጨከነ #አዝ በትራችን አንቺ ነሽ የምትደግፊን ባሕረ እሳትን የምታሳልፊን ጽርሐ ሥላሴ ነሽ ማኀደረ መለኮት ሁልጊዜ አንጠግብሽም እንላለን ብጽዕት 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ነይ ነይ ማርያም ዝማሬ ዳዊት

26 501
289
#የናቁሽ_ሁሉ የናቁሽ ሁሉ ወደእግሮችሽ ጫማ ይሰግዳሉ የካዱሽ ሁሉ ይፀፀታሉ እኛ ግን አንቺን እናከብራለን}2 እናታችነን ፅዮን አንልሻለን} እናቴ እመቤቴ እኔም እልሻለው ጌታዬ ባደራ የሰጠኝ አንቺን ነው ከእግረ መስቀሉ ስር አንቺን አጊኝቻለው ትውልድ ነኝና ብፅዕት እልሻለው በድል ነሺዎች ዘንድ በፃድቃን ሰማዕታት በቅዱሳኑ ና በትጉሃን መላዕክት የሰለጠነ ነው ስምሽ በእግዚአብሔር ዘንድ በፍጥረታት ሁሉ እጅግ የሚወደድ እናቴ ማርያም ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ ያልሽኝን እንዳልፈፅም የሚከለክለኝ ብሏልና ልጅሽ በቤተ ዶኪማስ ለምኝልን ድንግል እንባችን ይታበስ የጌድዮን ፀምር ዳግማዊቷ ሰማይ ሕይወትን ያስገኘሽ ወላዲተ ፀሐይ የሕወትን መና ያገኘነው እኛ ካንቺ ተወልዶ ነው የአለሙ እረኛ ዘማሪት መብራት ድርብሣ (አብ-ሳላት) 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

406245552.mp3

22 073
208
#የልቤን_በልቤ_ይዤ የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጅኝ እላለሁ ግራኝ ቀኝ ህይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል በፊት በኋላዬ መሰናክል በዝቷል እኔስ ያለ ምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል እመ አምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል(2) #አዝ ቆሜ ስራመድ ጤነኛ እመስላለሁ የውስጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ(2) #አዝ እናት ያለው ሰው ፍጹም አይተክዝም አንድ ቀን ይስቃል አልቅሶም አይቀርም ሀዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ በደስታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ(2) #አዝ አሁን ጎዶሎ በውስጤ አለና ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና ለዚች ለትንሿ ለጥቂቷ እድሜ እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ(2) 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

Hdbdu - __ g1aTY0UtbnM.m4a

16 760
254
#እናቴ_እመቤቴ እናቴ እመቤቴ የማትጠፊው ከአፌ /2/ በረከቴ አንቺ ነሽ የመስቀል ስር ትርፌ /2/ አምላኬ ሸልሞኝ ለዘለአለም ያዝኩሽ ጌታን የማይብሽ ብሌኔ አደረኩሽ በልቤ ላይ ይፍሰስ የፍቅርሽ ጸዳሉ የሚጣፍጥ ስምሽ መድኃኒት ለሁሉ ተወዳጁን ልጅሽ ጸጋውን ያብዛልኝ እድሜ እስኪፈጸም ለክብርሽ እንድቀኝ #አዝ ነፍሴ እንዳትጎዳ እንዳትቀር ባክና ብርታት ሆኖልኛል የስምሽ ምስጋና እኖራለው ገና ንኢ ንኢ ስልሽ ክብሬ ነሽ ጌጤ ነሽ ከአፍ የማልነጥልሽ #አዝ ሲነጋም ጠራሁሽ ሲመሽም ጠራሁሽ ስዕልሽ ፊት ቆሜ ሰአሊ ለነ እያልኩሽ አሜን የምልብሽ መነጋገሪያዬ የአማኑኤል እናት አንቺ ነሽ ቋንቋዬ #አዝ መች በስጋ ጥበብ ሰው ላንቺ ይቀኛል ከአምላክ ካልተላከ ከፊትሽ ይቆማል አንቺን ማመስገኔ አንቺን ማወደሴ በልቡ ያሰበሽ ፈቅዶ ነው ሥላሴ #አዝ ብዙ ተቀብዬ ጥቂት አልዘምርም ለእናትነት ፍቅርሽ ከቶ ዝም አልልም እኔን በእደ ፍቁርሽ የምትባርኪ ኦ ምልይተ ጸጋ ድንግል ሰላም እለኪ በሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

ማኅቶት_ቲዩብ_Mahtot_Tube_አዲስ_ዝማሬ_እናቴ_እመቤቴ_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.m4a

17 465
351

AnimatedSticker.tgs

18 365
10
ሕዳር 21/03/2014 ዓ.ም የሕዳር ጽዮን ማርያም ✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ። ዲያቆን፦ 2ቆሮ 7÷12-ፍ.ም ንፍቅ ዲያቆን፦ 1ጴጥ 2÷5-11 ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 7÷44-59 ምስባክ ፦ መዝ 131÷13-15 እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን ወአብደራ ከመትኩኖ ማህደሮ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም ትርጉም ፦ እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና ማደርያውም ትሆነው ዘንድ ወዷታልና እንዲህም ብሎ ይህች የዘለዓለም ማረፊያዬ ናት ወንጌል ፦ ማቴ 21÷42-ፍ.ም ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

ነይ ነይ ማርያም ዝማሬ ዳዊት

19 601
125
Share 'ህዳር 21.pdf'

ህዳር 21.pdf

18 120
115
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች ሼር 👉 @ortodoxmezmur
18 243
45
​​እንኳን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ "ጽዮን ማርያም" "ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል:: እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች:: ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን:: ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም:: ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው:: "ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19) #በመጨረሻም_ኅዳር_21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን:- 1. ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19) 2. በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1) 3. በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል:: "ሰላም ለኪ ማርያም እምነ:: ዘሰመይናኪ ጸወነ:: ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ:: ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ:: ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: (አርኬ ዘኅዳር 21) 4. በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1) 5. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል:: 6. በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል:: 7. በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል:: 8. በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው:: " አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን " "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና:: ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና:: #እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው:: 1. "ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት:: "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም) 2. "ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: ¤ "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ¤ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ) 3. ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና:: 4. እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና:: #ሼር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
24 283
406
የምነና ቅዱስ ሚካኤል ቤተልሔም በዚህ መልኩ ተጠናቋል። አስጀምሮ ላስጨረሰን ቸሩ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው። በገጠር ስላለቸው ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ መረጃ እና የአገልግሎት ማነቃቂያ ለመስጠት የተከፈተ መንፈሳዊ የዘገባ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቻናል ነው ለበለጠ ስራዎችን ከስር ባለው ቻናል መመልከት ይችላሉ 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/+qs_zcXBArtAxOTJk https://t.me/+qs_zcXBArtAxOTJk
17 140
7
​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞ እንኳን ለቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ: ለቅዱስ ኤላውትሮስ እና ለደናግል አጥራስስ ወዮና ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ " ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ " እንደ አባቶቻችን ትርጉም 'ፊልጶስ' ማለት 'መፍቀሬ አኃው - ወንድሞችን የሚወድ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ነው:: (ማቴ. 10:3) በዚህ ስም የሚጠራ ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት ውስጥ ነበር:: እርሱም ጃንደረባውን ባኮስን ያጠመቀው ነው:: አንዳንዴ የ2ቱ ታሪክ ሲቀላቀል እንሰማለን:: ለሁሉም ይህኛው ቅዱስ ፊልዾስ ቁጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት ሆኖ ምሑራነ ኦሪት ከሚባሉትም አንዱ ነበር:: በወቅቱ ገማልያል የሚሉት ክቡርና ምሑረ ኦሪት በርካታ ምሑራነ ኦሪትን አፍርቶ ነበር:: እንደ ምሳሌም ቅዱሳኑን "ጶውሎስን: ኒቆዲሞስን: ናትናኤልን: እስጢፋኖስንና የዛሬውን ሐዋርያ ቅዱስ ፊልዾስን" መጥቀስ እንችላለን:: ቅዱስ ፊልዾስ ነገዱ ከእሥራኤል ሲሆን ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ ነው:: ኦሪትን ተምሮ በመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ 'መሲሕ ቀረ' እያለ ሲተክዝ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ ደረሰ:: ትክ ብሎ አይቶት "ተከተለኝ" አለው። (ዮሐ. 1:44) ቅዱስ ፊልዾስም ያለ ማመንታት: ሁሉን ትቶ በመንኖ ጥሪት ተከተለው:: በዚህ ዓይነት ጥሪ መድኃኒታችን ቅዱስ ማቴዎስንም ጠርቶታል:: (ማቴ. 9:9) ቅዱስ ፊልዾስ ጌታን ከተከተለ በሁዋላ ሥራ አልፈታም:: ወዲያውኑ ሒዶ ለናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) ሰበከለት እንጂ:: "ሙሴ በኦሪት: ነቢያትም የተነበዩለትን መሲሕን አግኝቸዋለሁ" አለው:: ይሕ አነጋገሩም ምሑረ ኦሪት እንደ ነበር በእርግጥ ያሳያል:: (ዮሐ. 1:46) ቅዱስ ናትናኤልም ምሑር ነውና "ከናዝሬት ደግ እንዴት ይወጣል?" ቢለው ቅዱስ ፊልጶስም መልሶ "ነዐ ትርአይ-ታይ ዘንድ ና" አለው:: ናትናኤልም ሒዶ በጌታ አመነ:: ቅዱስ ፊልዾስ አገልጋይ እንደ መሆኑ መጠን በዮሐንስ ወንጌል ተደጋግሞ ስሙ ተጠቅሷል:: በተለይ ደግሞ ጌታ የ5 ገበያ ሕዝብን አበርክቶ ሲመግብ አስቀድሞ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር:: እርሱ ግን "ጌታ ሆይ! የ200 ዲናር እንጀራ ብንገዛም አንዘልቀውም" ብሎ ነበር:: በሁዋላ ግን የጌታን ድንቅ ተአምር ተመለከተ:: (ዮሐ. 6:5) በተለይ ደግሞ በሐዋርያት አበው መካከል ለጌታ እንደ እንደራሴ ሆኖ ያገለግል እንደ ነበርም ተጠቅሷል:: ሰዎች ጌታን ማግኘት ሲፈልጉ እሱና እንድርያስን ያናግሩ ነበር። (ዮሐ. 12:20) አንድ ጊዜ ግን እስካሁን ሊቃውንትን የምታስደምም ጥያቄ ጠይቆ ነበር:: አጠያየቁ ደግሞ ፍጹም የዋሕ እንደ ሆነ ያሳያል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ባሕርይ አባቱ አብ እየነገራቸው ሳለ ቅዱስ ፊልዾስ ከመካከል ተነስቶ "እግዚኦ አርእነሁ ለአብ ወየአክለነ": ልክ ወልድን በዐይኑ እንዳየ ሁሉ አብን ሊያይ ቸኩሎ "አቤቱ ስለ አብ የሰማነው ይበቃልና አሳየን" ብሎታል:: (ዮሐ. 14:8) ጌታችን ግን "ዘርእየ ኪያየ ርዕዮ ለአብ-እኔን ያየ አብን አይቷል" (ዮሐ.14:9) ብሎ ምሥጢረ ባሕርዩን: አንድነቱን ሦስትነቱን አስረድቶታል:: ቅዱስ ፊልዾስም ጌታን እስከ ሕማሙ አገልግሎ: ቅድስት ትንሳኤውን አይቶ: ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ: ቅዱስ መንፈሱን ከ72 ልሳን ጋር ነስቶ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለምን በእጣ ሲካፈሉ ለእርሱ አፍራቅያ (አፍሪካ) ደርሳዋለች:: ስለዚህም በምድረ አፍሪካ ወንጌልን ከሰበኩ ሐዋርያት አንዱ ነው:: በአፍራቅያና በቀድሞው የኃምስቱ አሕጉር ግዛት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጐ ብዙዎችን ወደ መንጋው (ወደ ክርስትና በረት) ቀላቀለ:: ለበርካታ ዓመታትም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲሰብክ: ብርሃነ ክርስቶስን ሲያበራ: ነፍሳትንም ሲማርክ ቆየ:: ገድለ ሐዋርያት እንደሚለው የቅዱስ ፊልዾስ ፍጻሜው በሰማዕትነት እንደ ሆነ ቢታወቅም የትኛው ሃገር ውስጥ እንደ ሆነ መለየት አልተቻለም:: ዜናው ግን እንዲህ ነው:- በአንዲት ሃገር ውስጥ ገብቶ ሰበከ:: ብዙዎችንም አሳመነ:: ያላመኑት ግን ይዘው አሰቃዩት: ገረፉት:: "በክርስቶስ እመኑ እባካችሁ!" እያለ እየለመናቸው ዘቅዝቀው ሰቅለው ገደሉት:: ከዚያም በእሳት እናቃጥላለን ሲሉ ቅዱስ መልአክ ከእጃቸው ነጥቆ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው:: በዚህ የደነገጡት ገዳዮቹ ለ3 ቀናት ጾሙ: ተማለሉ:: በዚህ ምክንያት የቅዱሱ ሥጋ ተመልሶላቸው: ገንዘው ቀብረውት በክርስቶስ አምነዋል:: ©ዝክረ ቅዱሳን ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur
Show more ...
photo
30 446
118
አዲስ አበባ ለምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ህዳር ጽዮንን በብርብር ማርያም ታከብሩ ዘንድ የጉዞ መርኃግብር ተዘጋጅቷል። ~~~~~~~~~~~ ዚጊቲ አቡዬ፤ቦረዳ ገዳም ፤አጆራ ተክልዬ፤ዶርዜ ጊዮርጊስ፤ሆሳዕና ማርያም በጉዞው ላይ ተይዘዋል ~~~~~~~~ ከአምስቱ ስርዓተ ኦሪት ከተፈጸመባቸው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን ቅዱሳን መካናት መሐከል አንዷ በሆነችው የደቡቧ ኮከብ ተብላ በምትጠራው ብርብር ማርያም ገዳም ህዳር ጽዮንን ያከብሩ ዘንድ መንፈሳዊ ጉዞ ከአዲስ አበባ ተዘጋጅቷል። በጉዞ መርኃግብሩ ላይ ታላቁ የፈውስ ማዕከል የሆነው ዝጊቱ አቡዬ፤ ጥንታዊ የዶርዜ ጊዮርጊስ እና ዘፍኔ ሚካኤል እንዲሁም ሆሳዕና ማርያም ፣ጩንቾ መድኃኒዓለም ፣ወራቤ ሩፋኤልን እንሳለማለን። እንዲሁም የደቡብ ክልል ግዙፉን ህንፃ መቅደስ የሆነውን የአርባ ምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኒዓለም ካቴዴራልን እና የአቡነ አረጋዊ ገቢረ ታምራት ድንቅ ሥራ የሆነውን የአርባምንጭ ጫካ እና አርባ ምንጮች ይጎበኛሉ። ይምጡ እና ብርብርን ይሳለሙ። ህዳር ጽዮንንም በሰማያዊት ጽዮን ብርብር ማርያም ገዳም ያክብሩ። ትኬቱ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን አከባቢ ይገኛል። የጉዞ ዋጋ ትራንስፖርት እና መስተንግዶን ጨምሮ 2000 ብር። ለበለጠ መረጃ (092) 770-7000 ወይም በቴሌግራም አድራሻ @BeGood16 ላይ ማናገር ይችላሉ / ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰሯት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን // የቴሌግራፍ አድራሻ https://t.me/KeAbawandebet
Show more ...
8 333
11
​​​​#ዝም_ብዬ_አልሞትም #አስተማሪ_ታሪክ በጥንት ዘመን አንድ ንጉሥ በሁለት ሰዎች ላይ ሞት ፈርዶ ሲያበቃ ለመጨረሻ ጊዜ የምትናገሩት ሐሳብ ካለ ይዛችሁት ከምትሞቱ ሐሳባችሁን ግለጹ አላቸው። አንደኛው የሞት ፍርዱ ላይነሳልኝ ምን አደከመኝ ብሎ ያስብና ምንም የምናገረው ነገር የለኝም የለኝም ይላል። ሌላኛው ግን ዝም ብዬ ከምሞት ብሎ ያስብና አንድ መላ ያመጣል። ንጉሱ አንድ በጣም የሚወዳት ምርጥ ፈረስ እንዳላቸው ስለሚያውቅ "ንጉስ ሆይ ሺ ዓመት ይንገሡ! እኔ የሚወዱትን ፈረስዎ ለአንድ ዓመት መብረር ላለማምውደ እችላለሁ" ይህ የሚሆነው ግን የአንድ ዓመት ዕድሜ ከተሰጠኝ ብቻ ነው ይላል። ንጉሡም አባባሉ ቢያስገርመውም "የሚበር ፈረስ ያለው በዓለም ላይ ብቸኛ ንጉሥ" መባሉን ውስጡ ስለወደደው በነገሩ ተስማምቶ የአንድ ዓመት ዕድሜ እንዲሰጠው ፈቀደ ። ከችሎቱ መልስ ያ ዝም ያለው ባልንጀራው በዚህኛው ላይ ስላቅ ተናገረበት "ወፈፍ ያረግሃል ልበል? አሁን በየት ሀገር ነው ፈረስ የሚበረው? አንድ ዓመት ረዥም መስሎህ ነው ይህን የማይሆን ነገር የምትናገረው? ምናለ ጣርህን ባታበዛው" አለው። ብልሁ ሰው ግን ተኩራርቶ እኔ እንዳንተ ዝም ብዬ አልሞትም ይህን ሃሳብ ሳቀርብ ነጻ ለመውጣት አራት አማራጮች አሉኝ እነርሱም፡- ፩ኛ. በዚህ አንድ ዓመት ንጉስ ሊሞቱ ይችላሉ ፪ኛ. እኔ እራሴ ልሞት እችላለሁ ፫ኛ. ፈረሱ ሊሞት ይችላል ፬ኛ. ማን ያውቃል ምንአልባት ፈረሱን መብረር #አስተምረው ይሆናል። አለው ይባላል። #ጭብጥ - እኛም ዛሬ ለመናገር የሚከብድ ለማየት የሚቀፍ ሀጥያት ሰርቻለው ስለዚህ እግዚአብሔር ይቅር አይለኝም እያልን ሳንሞት እንደሞተ ሰው አንኑር በንስሐ የማይጠፋ ሀጥያት የለም። ወደ ንስሐ እንዳንቀርብ የምናስበው ስበብ የምናመጣው ሰበብ ሁለ የሰይጣን እንጂ የእኛ አይደለም እግዚአብሔር ሀጥያትን እንጂ ሀጥያተኛል አይጠላም። እናም ዝም ብለን ከነኃጥያታችን ልንሞት አይገባም ንስሐ ገብተን ሥጋ ወደሙን ተቀብለን ነጻ ወጥተን መንግስቱን ብንጠባበቅ ይሻለናል ይሻለናል። ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur
Show more ...
photo
30 691
379
#እናት_አለኝ እናት አለኝ የምታብስ እንባ አያታለሁ ስወጣ ስገባ ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ ራቁቴን ብቆምም አፍሬ ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት #አዝ ለዘላለም ንፅሕት በመሆኗ ከእኔ ጋር ነው ሕያው ቃልኪዳኗ ደስተኛ ነኝ ሐዘኔን አልፌ አፅናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት #አዝ ከጥፋት ውሃ ማረፊያዬ መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት #አዝ በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታ ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ ሰንሰለቴ ከእግሬ ተቆረጠ መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት #አዝ ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ ራቁቴን ብቆምም አፍሬ ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

convert_1592873492728.mp3

26 372
626
#ኪዳነ_ምህረት_ልዩ_ነሽ_ለኔ ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪) #አዝ የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ #አዝ የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ #አዝ የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ #አዝ የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

convert_1592891023949.mp3

24 540
369
የፍቅር እጦት ቂም እና ጥላቻን ይፈጥራል ይህ ደግሞ በኃጢአት ሐሴት ማድረግን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ ፤ በመሰናከሉም ልብህ ሐሴት አያድርግ፤.. ሌላው የፍቅር እጦት ውጤት ቁጣ እና ክፍት ነው። እንዲህ ያለው ሁኔታ ስድብን፣ ጠብን ፣ ግድያን፣ ነቀፋን፣ ማዋረድንና ስም ማጥፋትን ማስፋፋትን ያስከትላል። ከዚህ በተጨማሪ የፍቅር እጦት ወይም ጉድለት ወደ ቅንዓት ፣ ወደ አላዋቂነት ፣ ወደ ኩራት፣ ወደ ጽናት ማጣትና ወደ ጭካኔ ይመራል። 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
26 492
124
አዲስ አበባ ለምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ህዳር ጽዮንን በብርብር ማርያም ታከብሩ ዘንድ የጉዞ መርኃግብር ተዘጋጅቷል። ~~~~~~~~~~~ ዚጊቲ አቡዬ፤ቦረዳ ገዳም ፤አጆራ ተክልዬ፤ዶርዜ ጊዮርጊስ፤ሆሳዕና ማርያም በጉዞው ላይ ተይዘዋል ~~~~~~~~ ከአምስቱ ስርዓተ ኦሪት ከተፈጸመባቸው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን ቅዱሳን መካናት መሐከል አንዷ በሆነችው የደቡቧ ኮከብ ተብላ በምትጠራው ብርብር ማርያም ገዳም ህዳር ጽዮንን ያከብሩ ዘንድ መንፈሳዊ ጉዞ ከአዲስ አበባ ተዘጋጅቷል። በጉዞ መርኃግብሩ ላይ ታላቁ የፈውስ ማዕከል የሆነው ዝጊቱ አቡዬ፤ ጥንታዊ የዶርዜ ጊዮርጊስ እና ዘፍኔ ሚካኤል እንዲሁም ሆሳዕና ማርያም ፣ጩንቾ መድኃኒዓለም ፣ወራቤ ሩፋኤልን እንሳለማለን። እንዲሁም የደቡብ ክልል ግዙፉን ህንፃ መቅደስ የሆነውን የአርባ ምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኒዓለም ካቴዴራልን እና የአቡነ አረጋዊ ገቢረ ታምራት ድንቅ ሥራ የሆነውን የአርባምንጭ ጫካ እና አርባ ምንጮች ይጎበኛሉ። ይምጡ እና ብርብርን ይሳለሙ። ህዳር ጽዮንንም በሰማያዊት ጽዮን ብርብር ማርያም ገዳም ያክብሩ። ትኬቱ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን አከባቢ ይገኛል። የጉዞ ዋጋ ትራንስፖርት እና መስተንግዶን ጨምሮ 2000 ብር። ለበለጠ መረጃ (092) 770-7000 ወይም በቴሌግራም አድራሻ @BeGood16 ላይ ማናገር ይችላሉ / ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰሯት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን // የቴሌግራፍ አድራሻ https://t.me/KeAbawandebet
Show more ...
16 235
24
​​#ጾመ_ነቢያት (የገና ጾም) ኅዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ #ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም: ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡ ምንጭ፡- ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡ ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
35 986
615
#የሚጠብቀኝ_አይተኛም የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/ አያንቀላፋም ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም ቀን እና ለሊት ከኔ አይርቅም ድምጸ አራዊት የለሊት ግርማ ወደኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ አዝ መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም አዝ ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ መውጣት መግባቴን እየጠበቀ ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ አዝ የሰማዩን ጠል እታገሳለው ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው ለሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ አዝ እንቅልፌን ባርኮ ለሰጠኝ የጌታ በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም መዝሙር ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ "እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም።" 👉 መዝሙረ ዳዊት 121:4 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

406245552.mp3

25 944
547
#ማረኝ ማረኝ /3/ መመኪያዬ አርጅቻለሁ እኔስ በኃጢያት ጎስቁዬ/2/ ከፊቴ ናትና ኃጢያቴ ሁል ጊዜ ተዉጫለሁ እኔስ በሐዘን በትካዜ በፊትህ ክፋትን አድርጌያለሁ እኔ ምንም ጽድቅ አልሰራሁ በሕይወት ዘመኔ #አዝ ከፊትህ መቅበዝበዝ መሰደድ ፈለኩኝ ኃጢያት ከኋላዬ እያሳደደችኝ ወዴት እሄዳለሁ መሸሸጊያም የለኝ ምህረትህ መጠጊያ ዋሻ ካልሆነችኝ #አዝ የተሰባበረዉ አጥንቴ እንዲጠገን በምህረት እና በቸርነት ዳሰኝ የቀና መንፈስን አድስ በልቤ ዉስጥ ነፍሴ በእልልታ በተስፋ ትለወጥ #አዝ ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትዉሰድ በንስሐ ድኜ በተስፋ እንድራመድ አቤቱ ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ እና በደስታ ልስገድ በፍቅርህ ልፅናና ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

406245552.mp3

25 815
606
​​​​👆 #የቀጠለ የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ “በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..” (ዳን.12፡1) በማለት ተናግሮለታል ፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው። ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡ (ዘኁል.12፡3፤ዘጸአ.32፡32)በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲያግዛቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.7፡35) እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው (ይሁዳ.12) ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡ እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው” መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን፡፡ #ምንጭ፦ የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መልአከ ሠላም ሰንበት ትምህርት ቤት ገጽ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
34 228
386
​​#ሕዳር_ሚካኤል ! #እንኳን_ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #በዓለ_ሲመት_በሠላም_አደረሰን ! በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (ሕዳር 12) (አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE_SHARE_SHARE ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡) ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡ በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ #ይቀጥላል ....... 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
31 126
422
#ቅዱስ_ሚካኤል ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች ሼር 👉 @ortodoxmezmur
27 272
143
📖 የፈለጉትን አማርኛ መጽሐፍት (1) 15% ቅናሽ (2) ነፃ ዴሊቨሪ, ቤቶ ድረስ ያግኙት እዚህ ይጎብኙን 👇👇👇 shewaberr.com Join Us On Telegram https://t.me/joinchat/kqrzH6PP8nVkMzg0
20 879
14
በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን በመሎ ጋዳ ወረዳ የሚገኘው የአሊዛ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከ120 ዓመታት በላይ ታሪክ እንዳለው ነገር ግን በታሪኩ ልክ ከፍ ብሎ መታየት ሲገባው በተቃራኒው የቁልቁል ተጉዞ ምዕመናን እስከማጣት እንዲሁም የካህናት ልብሰተክህኖ እና የተለያዩ የንዋየ ቅድሳት እጦት ለአገልግሎቱ መሰናክል ስለሆነበት የአቅማችንን መለመኔ ይታወሳል። ከላይ በፎቶ የሚታዩትን ተገስቶ ተልኳል። ______________________ ለሰጣቸው እግዚአብሔር ይስጥልኝ ቁጭ በላቸው ደሞ ለምታሙት ደሞ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ እያልን ሥራችንን ቀጥለናል በቴሌግራም አድራሻ @BeGood16 ላይ ማናገር ይችላሉ #ማስታወሻ የሌሎችንም እንደዚህ እየገዛን እናሳውቃለን (092) 770-7000
26 363
11
📖 የፈለጉትን አማርኛ መጽሐፍት (1) 15% ቅናሽ (2) ነፃ ዴሊቨሪ, ቤቶ ድረስ ያግኙት እዚህ ይጎብኙን 👇👇👇 shewaberr.com Join Us On Telegram https://t.me/joinchat/kqrzH6PP8nVkMzg0
11 963
6
#ኦ_ሚካኤል ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል/2/ ስንጠራህ ድረስልን ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል ዘንዶው ጠላታችን ከፊታችን ቆሟል ከባህር ሊጥለን አድፍጦ ያደባል የመላዕክት አለቃ እርዳን በፀሎትህ ጥበቃህ አይራቀን በቀን በሌሊት/2/ ክርስትና ኑሮ እጅጉን ከብዶናል የጌታን ውለታ ፍቅሩን ዘንግተናል አፅናኙ መልዐክ ከፊታችን ቅደም በመንገድህ ምራን እንድንሆን ሰላም/2/ የጌታ ባለሟል የህዝብ እረኛ ባህሩን አሻግረን ቅረበን ወደ እኛ ከጌታህ አማልደን መልዐከ ራማ የልጆችህን ቃል ድምፃችንን ስማ በሚያስፈራው ዘመን ሰላም በሌለበት ባስጨናቂው ጊዜ ፍቅር በጠፋበት የፍቅርን ወንጌል ቃሉንም ስበከን ሚካኤል ተራዳን ድረስም አፅናናን ዘ/ዲ ሱራፌል ስዩም 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️

መዝሙር ዝማሬ ዳዊት

28 374
525
#ናና_ሚካኤል_ናና ናና ሚካኤል ናና /2/ አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና ናና ሚካኤል ናና የረዳህ አፎምያን ሚካኤል ናና ሰይጣን ሲፈትናት ሚካኤል ናና አንተነህ ያዳንከው ሚካኤል ናና ባሕራንን ከሞት ሚካኤል ናና ለእነርሱ እንደመጣህ ሚካኤል ናና እኔንም ተራዳኝ ሚካኤል ናና ሚካኤል ደግፈህ ሚካኤል ናና ለመንግሥቱ አብቃኝ ሚካኤል ናና ናና ሚካኤል ናና /2/ አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና አዝ------------- ናና ገብርኤል ናና /2/ አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና ናና ገብርኤል ናና ዘመኑ ሲፈፀም ገብርኤል ናና አምላክ መምጫው ሲደርስ ገብርኤል ናና ገብርኤል አንተ ነህ ገብርኤል ናና ያልካት ደስ ይበልሽ ገብርኤል ናና ድምጽህን አሰማኝ ገብርኤል ናና ነፍሴ ጽድቅን ትልበስ ገብርኤል ናና አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና ናና ገብርኤል ናና አዝ------------- ናና ዑራኤል ናና /2/ አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና ናና ዑራኤል ናና ቆመህ ጽዋ ይዘህ ዑራኤል ናና ለእዝራ ሱቱኤል ዑራኤል ናና ጥበብ አጠጥተህ ዑራኤል ናና ዕውቀት ስታድል ዑራኤል ናና ተገለጠ ክብርህ ዑራኤል ናና መልአኩ ዑራኤል ዑራኤል ናና ድኜ በፀበልህ ዑራኤል ናና በአውደ ምህረትህ ላይ ዑራኤል ናና እኔም ዘመርኩልህ ዑራኤል ናና አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና ናና ዑራኤል ናና 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

ነይ ነይ ማርያም ዝማሬ ዳዊት

25 943
570
📖 የፈለጉትን አማርኛ መጽሐፍት (1) 15% ቅናሽ (2) ነፃ ዴሊቨሪ, ቤቶ ድረስ ያግኙት እዚህ ይጎብኙን 👇👇👇 shewaberr.com Join Us On Telegram https://t.me/joinchat/kqrzH6PP8nVkMzg0
10 736
9
​​በመንፈሳዊ ሕይወትህ/ሽ ለውጥ እንዲኖሮት ከፈለጉ ✝#1ኛ የፀሎትን ህይወት ተለማመድ ተጠቀምበትም፣ ✝#2ኛ ከመንፈሳዊ አባቶችና ሊቃውንት መ/ራን ምክርና ትምህርት አትራቅ ✝#3ኛ ከቅዱሳት መፃህፍት ጋር ያለህን ግንኙነት አዘውትር፣ ✝#4ኛ የምትውልባቸውን ቦታዎች ፥የምታነባቸውን መፃህፍት፥ የምትመርጣቸውን ባልጀሮችህን ምረጥ፤ለመንፈሳዊ ህይወትህና ለሌሎች ወንድሞችህና እህቶችህ የሚያሰናክሉ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ፣ ✝#5ኛ የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ መሆንህን ዘወትር አትዘንጋ፣ ✝#6ኛ ሃፍረትንና ፍርሃትን አስወግድ፥በራስህ ማስተዋልም አትደገፍ፣ ✝#7ኛ አላዋቂነትህን ተቀበል 'እኔ ብቻ'፦ አትበል ውዳሴ ከንቱንም አትፈልግ፣ ✝#8ኛ ለሰራሃው ሃጢአት ሳትዘገይ ንስሃ ግባ፣ ✝#9ኛ ልበ ደንዳናነትንና አመፀኛነትን ከአንተ አርቃቸው፣ ✝#10ኛ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ለመኖርና የቃሉ ሙላት በውስጥህ ኖሮ ከክርስቶስ ጋር መኖርን ተለማመድ በቃሉም ፀንተህ ተገኝ፣ ✝#11ኛ የቅዱሳንን ተጋድሎና ፍቅር በመመልከት እነርሱን ለመምሰል ትጋ፣ ✝#12ኛ ከዚህ በፊት የነበርክበትን የሃጢአት ህይወት ኮንነው ✝#13ኛ ሰዎችን/ባልንጀራህን አፍቅር ከጥላቻም ራቅ፣ ✝#14ኛ ነገርን ሁሉ ለበጎነው ብለህ ተቀበል። ጌታ ሆይ ይህን እንድናደርግ እርዳን አሜን ይቆየን። #ሼር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
33 393
679
📖 የፈለጉትን አማርኛ መጽሐፍት (1) 15% ቅናሽ (2) ነፃ ዴሊቨሪ, ቤቶ ድረስ ያግኙት እዚህ ይጎብኙን 👇👇👇 shewaberr.com Join Us On Telegram https://t.me/joinchat/kqrzH6PP8nVkMzg0
15 082
12
​​#ፍቅር_ይበልጣል #አስተማሪ_ታሪክ ባልና ሚስት በሚኖሩበት አንድ ቤት ውስጥ ከመሸ በራቸው ይንኳኳል ። ሚስት ለመክፈት ትሄዳለች ከዛም ባየችው ነገር በጣም ተገረማለች ። ሶስት ነጫጭ ሽበት ያለባቸው የሚያማምሩ ባለግርማ ሞገስ ሽማግሌዎች ነበሩ ። አቤት ግቡ ምን ፈልጋቹ ነው አለቻቸው ፈራ ተባ ባለ የአነጋገር ድምፀት ። ሶስታችንም አንገባም አንዳችን ነን የምንገባው እራሳችን እናስተዋውቅሽ አሉና ራሳቸውን ማስተዋወቅ ጀመሩ ። 1ኛው ስኬት እባላለው እኔ ቤትሽ ከገባሁ አሳብሽ ሁሉ ይሳካል አላት ፣ 2ተኛው ገንዘብ እባላለው እኔ ቤትሽ ከገባሁ ችግር የሚባል አይኖርም አላት ፣ 3ተኛው ፦ ፍቅር እባላለው ፍቅር ማብራሪያ የለውም አላት። ከዛ ሚስት ባለቤቴን ላማክር ብላ ወድ ውስጥ ገባችና ልክ ለባለቤቷ ስትነግረው በነገሩ ተደንቆ እንዲህ አለ። በእውነቱ ይሄ እድል ሊያመልጠን አይገባም ገንዘብን የሚያክል ነገር ደጅ ቆሞ መወያየት ግፍ ነው ሰርቼ ከሰው በታች የሆንኩት ገንዘብ ሰለሌለኝ ነው እና ፈጠን በይ ገንዘብን ወደቤታችን እንዲገባ ንገሪው አላት ሚስትየውም በሀሳቡ ተስማምታ ገንዘብን ልትጠራው ስትል ልጇ እንዲ አላት እማዬ ገንዘብ ገብቶ አባዬ እንደለመደው ማታ ማታ ከሚደበድብሽ ፍቅር ገብቶ ሰላምሽን ብታገኚ አይሻልም ? አላት ። እሷም በልጇ ሀሳብ ተደስታ ባልየውን ፍቅር ካልገባ ብላ ሞገተቹ በመጨረሻም ፍቅር እንዲገባ ወስነው ወደ ሽማግሌዎች ሄዱና ፍቅር የተባልከው ሰው ወደቤታችን ግባ ይሉታል። እሱም ተከትሏቸው ይገባል። ባልና ሚስቱም ዞር ብለው ሲያዩ 3ቱም። ሰዎች ቤት ገብተው ቆመዋል ባልየው ደንግጦ እኛ በቤታችን እንዲገባ ያልነው ፍቅርን እኮ ነው አለ ከሽማግሌዎቹም አንዱ ዞር አለና ልክ ብለሀል ። ነገር ግን ፍቅር ካለ ስኬት አለ ፍቅር ካለ ገንዘብ አለ ። በማለት 3ቱም ወደቤታቸው ገቡ ፍቅር የሆነው ፈጣሪ ወደቤታችን ሲገባ መልካም የሆኑ በሙሉ አብረው ይገባሉ። #ጭብጥ - አሁን ዓለማችን ከኮሮና በላይ ፍቅር ማጣት እያሰቃያት ነው ወንድም ወንድሙን እየገደለ ነው። አንተ የገደልከው ሰው እኮ ትላንት ኢየሱስ ክርስቶስ በፍቅር ደሙን ከፍሎለታል። ወንድሙን የሚገድል ሁሉ እርሱ የሰይጣንን ስራ እየሰራ ነው እና የሰይጣን ልጅ ይባላል ፈጽሞ ክርስቶስን ከሕይወቱ አውጥቶታል እና አሁንም ግን ለንስሐ እድሜ ተሰጥቶታል። ፍቅር ከሁሉም ይበልጣል "፤ ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። " (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4: 8) ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur
Show more ...
photo
35 746
558
📖 የፈለጉትን አማርኛ መጽሐፍት (1) 15% ቅናሽ (2) ነፃ ዴሊቨሪ, ቤቶ ድረስ ያግኙት እዚህ ይጎብኙን 👇👇👇 shewaberr.com Join Us On Telegram https://t.me/joinchat/kqrzH6PP8nVkMzg0
12 125
14
ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ፤ የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ ኅዳር 6 ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና:: ‹‹አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ›› ልንልም ይገባል፡፡
31 801
135
የመጀመሪያ 10 የገጠር ቤተክርስቲያን ከአዲስ አበባ 750ኪሎ ሜትር ይርቃል ዛሬ ወደ ደቡብ እምንልክ ይሆናል። ደቡብ አሞ (ወደ ጅንካ አከባቢ ከከተማው በተጨማሪ ከ100 ኪሎ ሚትር ይርቃል) 1. ባኮ ቅዱስ ጊዮርጊስ 2. ጴልጳ ቁስቋም ማርያም 3. የትነበርሽ ቅድስት ማርያም 4. ቴንቤል ቅዱስ ገብርኤል 5. ኮመር ቅድስት አርሴማ 6. አርኪ ቅዱስ ገብርኤል 7. ሸንጋማ ቅዱስ ጊዮርጊስ 8. ጎይረተር ክዳነምህረት 9. ዘመር ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርሲቲያን 10. ወሰት ቅዱስ ሚካኤል የትራንስፖርት ለእንደዚህ 10 ቤተክርስቲያን በርግጥ ከጅንካ በኋላ በሞተር ነው የሚከፋፈለው ከአዲስ አበባ ጀንካ ድረስ 400 ብር እቃውን ማድረሻሃ በተጨማሪ በሞተር ሁሉንም አከባቢ ለመድረስ 1000 ብር ይፈልጋል በተጨማሪ እቃው ከተሰበሰቡት ወደ ጅንካ ተራ ለመሰድ 230 ብር አጠቃላይ 1730 ብር ለትራንስፖርት ውሏል ማስታወሻ ፈቅርተ ማርያም፤ ሀብተ ስላሴ፣ አስራተ ሚካኤል፤ ፈቅረ ሂወት እና አጸደ ማርያም በ Hirut Getachew ከተላከው 2500 ብር -1630 ብር በቀረው ማለትም በ 840 ብር ደሞ ፍሬያለው ዘቢብ ተገስታል
Show more ...
30 392
18
29 392
74
#ገሊላ_እትዊ እመቤቴ እሰከ መቼ በባዕደ ሀገር ትኖርያለሽ /2/ ገሊላ ግቢ/4/ ሐገርሽ ገሊላ ግቢ/2/ ገሊላ እትዊ/4/ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/ እመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ ሰደቱ ይበቃሽል ገሊላ እትዊ ሄሮድስ ሞቷልብሎ ገሊላ እትዊ ገብርኤል ነገሮሽል ገሊላ እትዊ በእሳት ሰርገላ ገሊላ እትዊ ዑራኤል ይመራሻል ገሊላ እትዊ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/ የዝናቡን ጌታ ገሊላ እትዊ እናቱ ሁነሽ ሳለ ገሊላ እትዊ ሰይጣን በሰው አድሮ ገሊላ እትዊ ውሃ ጥም ጸንቶብሽ ገሊላ እትዊ አፈሽ ደርቆ ዋለ ገሊላ እትዊ ይበቃል እናቴ ገሊላ እትዊ ረሀብ ጥማትሽ ገሊላ እትዊ ሂጅ ወደ ገሊላ ገሊላ እትዊ ወደ ዘመድችሽ ገሊላ እትዊ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/ የሰማዕታት አክሊል ገሊላ እትዊ የፃድቃን እናት ገሊላ እትዊ ባርከሽ ሰጠሻቸው ገሊላ እትዊ መከራን ስድት ገሊላ እትዊ እኛም ይታደለን ገሊላ እትዊ የአንቺው በረከት ገሊላ እትዊ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/ ገጽሽ ብሩህ መልካም ገሊላ እትዊ ልክ እንደ ፀሐይ ገሊላ እትዊ እግዝእትነ ማርያም ገሊላ እትዊ እሙ ለአዶናይ ገሊላ እትዊ አይገባም ለአንቺ ገሊላ እትዊ መከራ ስቃይ ገሊላ እትዊ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ /2/ ገሊላ ግቢ /4/ አገርሽ ገሊላ ግቢ/2/ ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

convert_1603936436042.mp3

28 992
357
6ኛ የመጨረሻው ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ወረብ ቀጥታ ስርጭት https://youtu.be/bk2Ly_UBWlo
6ኛ የመጨረሻው ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ወረብ 2
25 712
36
ሥድስተኛ ሳምንት 💚ተ💛ፈ❤️ፀ💙መ ነግሥ ሰምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያእመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡ ነግስ፦ ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም። ዚቅ ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት። ማኅሌተ ጽጌ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡ ወረብ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ/2/ ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ/2/ ዚቅ እለትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፤ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል ፤መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡ ወረብ እለ ትነብሩ ተንስኡ ወእለ ተረምሙ አውስዑ ማርያምሀ በቃለ ስብሐት ፀውኡ/2/ ጸልዩ ቅድመ ስዕል ለቅድስት ድንግል እመ በግ ወመርዓተ አብ/2/ ማኅሌተ ጽጌ፦ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ። ወረብ፦ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/2/ ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/2/ ዚቅ ይዌድስዋ ትጉሃን፤ይቄድስዋ ቅዱሳን፤ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርይዪ ወአጽምዒ ዕዝንኪ ማኅሌተ ጽጌ፦ ሶበ ዴገነኪ አረዌ በሊዓ ሕፃንኪ ዘኀለየ፤በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጎይየ፤አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ ጸገየ፤ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሐየ፤ተአምርኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ ወረብ፦ ዚቅ፦ በሊዓ ሕፃናት ሶበ ኀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ፤ምስለ ዮሴፍ አረጋ፤ነገደት ቁስቋመ ናዛዚት ኃዘን ወብካይ ማኅሌተ ጽጌ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡ ወረብ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/2/ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ ለተክለ ሃይማኖት/2/ ዚቅ፦ አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት፤ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት ማኅሌተ ጽጌ፦ ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡ ወረብ ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/2/ አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት/2/ ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ይግበሩ ለኪ ኰሰኰሰ ወርቅ፡፡ ሰቆቃወ ድንግል ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡ ወረብ ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/2/ ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/2/ ዚቅ ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር፤ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ። መዝሙር ፦ በ6 ሃሌታ- ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት፤ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት ወጸገወነ ዕረፍት ከመ ንትፌሳሕ ኅቡረ።አዕፃዳተ ወይን ጸገዩ ቀንሞስ ፈረይ፤ማ- ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ፤ከመ አሐዱ እምእሉ አመላለስ፦ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ/2/ ከመ አሐዱ እምእሉ/4 ምስባክ ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙሐዘ ማይ እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ ወቈጽላኒ ኢይትነገፍ የተወደደች ማኅሌተ ጽጌ እነኆ 💚ተ💛ፈ❤️ፀ💙መ💜
Show more ...
32 854
458
ማስታወቂያ አዲስ አበባ እና ለአዲስ አበባ አከባቢዎች አገልግሎት እንሰጣለን
16 543
13
አክሊሉ እሸቱ 2448 ብር አብርሃም ሞላ በቀር ብር 840 ብር ሚልኪያስ ዳምጠው 1000 ብር የሺዓለም ጫላ 1000 ብር ዓመተ ማርያም 1540ብር እግዚአብሔር ይስጥልኝ የ6540 ሺ ብር ጧፍ ተገዝቷል እግዚአብሔር ይስጥልን _________ ፆመ ገና ማስቀደሻን ምክንያት በማድረግ የ3 ወር መባ (ዕጣን፥ዘቢብ፥ጧፍ፥ሻማ፣) በ6 ሀገረስብከቶች ለሚገኙ 100 የገጠር አጥቢያዎች በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን ። __________ ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም በውስጥ መስመር ያናግሩን።በ251927707000 ይደውሉልን ! በተጨማሪ ከላይ ባለው ቁጥር በዋትስአፕ ፣ ማናገር ይችላሉ። በቴሌግራም አድራሻ @BeGood16 ላይ ማናገር ይችላሉ
3 029
2
Watch "የአምስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ" on YouTube https://youtu.be/A-euuFseLew
የአምስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ
12 349
17
የአምስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ወረብ https://www.youtube.com/channel/UC8iS8VUpEphoIVnfhsC2WdQ
351
0
🌹🌹🌹የአምስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ሥርአተ ማኅሌት እነሆ🌹🌹🌹 ነግሥ ሰምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ እመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡ መልክአ ሥላሴ፦ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። ዚቅ አሠርገወ ገዳማት ስን፤በመንክር ኪን አርአያሁ ዘገብረ፤ሰሎሞን ጥቀ ኢለበሰ በኩሉ ክብሩ፤ከመ ኢሎን ጽጌያት፤ኢቀደምት ወኢደኃርት፤አራዛተ ሠርጕ ነሢኦሙ፤ኢክህሉ ከመ ክርስቶስ መዊዓ ማህሌተ ጽጌ፦ ዘብኪ ተባረኩ ወተቀደሱ አሕዛብ፤ትእምርተ ግዝረቱ ወዘርዑ ለአብርሃም አብ፤ጽጌ ድንግልናኪ በግዕ ለቤዛ ይስሐቅ ውሁብ፤ማርያም ዕፀ ሳቤቅ ወምስራቅ ዘያዕቆብ፤ወላዲቱ ለሥርግው ኮከብ ወረብ፦ ዕፀ ሳቤቅ ዕፀ ሳቤቅ ማርያም ወምስራቅ ዘያዕቆብ/2/ ወላዲቱ ወላዲቱ ወላዲቱ ለሥርግው ኮከብ/2/ ዚቅ ቡራኬሁ ለሴም ወክፍል ሎቱ፤ተናግዶቱ ለአብርሃም፤መዓዛሁ ለይስሐቅ ወሰዋስዊሁ ለያዕቆብ፤ወናዛዚቱ ለዮሴፍ ማኅሌተ ፅጌ፦ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ። ወረብ፦ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/2/ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት/2/ ዚቅ በሰላም ንዒ ማርያም፤ ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም። ማኅሌተ ፅጌ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ። ወረብ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘይኀቱ እምዕንቄ ባሕርይ/2/ አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/2/ ዚቅ፦ አክሊል ዘእምጳዝዮን ተደለወ ጌራ ባሕርይ ወቀጸላ ወርቅ ጽሩይ በቤተልሔም ተወልደ እምድንግል ብሥራትክሙ መሃይምናን እምአፈ ዮሐንስ ሥርግው ተቀስመ አፈው ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማዕከለ አኃው፡፡ ማኅሌተ ፅጌ፦ ዘንተ(ዘኒ) ስብሐተ ወዘንተ(ወዘኒ) ማኅሌተ፤ተአምርኪ ጸገየ ወፈረየ ሊተ፤ከመ እሰብሕ ዳግመ እንዘ እጸውር ፀበርተ፤ምስለ እለ ሐፀቡ ኣልባሲሆሙ በደመ በግዑ ድርገተ፤ውስተ ባሕረ ማኅው ድንግል ክፍልኒ ቁመተ። ወረብ ምስለ እለ ሐጸቡ አልባሲሆሙ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ/2/ ክፍልኒ ቁመተ ድንግል ድንግል ውስተ ባህረ ማኅው/2/ ዚቅ ማህሌተ ነዓርግ ወስብሐተ ዘነግህ፤ንፌኑ ለኪ እግዝእትነ ማርያም ዓዲ ዚቅ፦ ዮም ሠርፁ ጽጌ በረከት፤ወበዝኁ ውሉደ ጥምቀት፤ትእምርተ መድኃኒት ቆመ ማዕከለ አህዛብ፤እስመ ቤዘወነ ክርስቶስ በዕፀ መስቀሉ፤ወተሣየጠነ በክዕወተነ ደሙ፤ገብረ ሕይወተ ማዕከሌነ ሰቆቃወ ድንግል ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤ኢየሱስ ግፉዕ ምስካዮሙ ለግፉዓን፤እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን፤ ኢየሱስ ነግድ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን፤ወልደ አብ ፍቁር በኀበ ሰብእ ምኑን፤መኃልየ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን። ወረብ ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን/2/ መኃልየ ብካይ ኮነኒ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን/2/ ዚቅ፦ አንተ ውእቱ ምርጕዞሙ ለጻድቃን፤ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤መርሶሙ ለእለ ይትሀወኩ፤ብርሃነ ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው መዝሙር በ5- ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፤ወፈረዩ ኩሉ ዕጽወ ገዳም ቀንሞስ ዕቁረ ማየ ልብን፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ጸገዩ ደንጎላት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ምሕረት፤ማ፦ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ አመላለስ፦ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ/2/ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ወለመድኃኒት/2/ © ሥርዓተ ቤተክርስቲያን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
15 678
175
​​ጥቅምት ፳፯ በዚህች ዕለት የታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባ መባዓጽዮን መታሰቢያ ነው። አቡነ መብዓጽዮን ለቸሩ አምላካችን ለመድኃኔ ዓለም ባላቸው ጽኑዕ ፍቅር የሚታወቁ ግሩም አባት ናቸው። ገና ልጅ እያሉ ሥዕለ አድኅኖ ተለይቷቸው አያውቅም። የመድኃኒታችንን ጽኑዕ መከራ በማሰብ በራሳቸው ላይ ያላደረጉት ምን አለ? ችንጋሮችን ራሳቸው ላይ ይቸነክሩ ነበር፣ ድንጋይ ተሸክመው ብዙ ይሰግዱና ከልቅሶ ጋር ይጸልዩ ነበር፣ ሥጋቸውንም በጽኑዕ ቅጣት ይቀጡት ነበር። ጌታችንን ይወዱትም ስለነበር በቅዱስ ስሙ ዝክር ይዘክሩ ነበር። ዝክራቸውም በንጽሕና የኾነ ነበርና ከዚያ ዝክራቸው የቀመሰ ኹሉ ካለበት ደዌ ይፈወሳል። ጌታችንም የሚያስደንቁ ቃልኪዳናትን የገባላቸውና በዚህች እለት ብዙ ነፍሳትን ከሲዖል ያወጡበትም እለት ነው። ዕረፍታቸውም ከጌታችን ዕረፍት ጋራ አንድ እምደሚኾንላቸው ተነግሯቸው ነበር። ከጽኑዕ ገድልም በኋላ በዚህች ቡርክት ቀን ዐርፈዋል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በአባታችን በአባ መባዓ ጽዮን ጸሎት ይማረን ! 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
14 996
72
​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞ ✞ ጥቅምት ፳፯ (27) ✞ ✞✞✞ እንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል:: ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: 7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: +በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: 11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው:: ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም:: በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል:: © ዝክረ ቅዱሳን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
18 125
342
​​ውርጃ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ ምድሪቱ (የሴቲቱ ማኅፀን) ዘር ከዘራንባት በኃላ ፍሬ እንዳታፈራ የምናደርገው ስለ ምንድን ነው? ውርጃን የምናካሒደው ስለ ምንድን ነው? እናንተ ዘማውያን ሆይ! ዝሙት መፈጸማችሁ ሳይበቃ ሰውን መግደል ትጨምሩበታላችሁን? እንግዲህ ስካር እንደ ምን ሴተኛ አዳሪን እንደሚያደርግ፣ ሴተኛ አዳሪነትም ዘማዊ፣ ዝሙትም እንደ ምን ነፍሰ ገዳይ እንደሚያደርግ ታስተውላላችሁን? ይህን ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም ምክንያቱም ይህን ሕፃን ከተወለደ በኃላ ከቤት አስወጥተን አይደለም ያባረርነው፤ እንዳይወለድ ከለከልነው እንጂ ወዮ! ስለምን የእግዚአብሔርን ስጦታ ታቃልላላችሁ? ስለምን ሕጉን ትተላለፋላችሁ? ስለምን ርጉም የሆነን ተግባርን እንደ በረከት ትቆጥሩታላችሁ? ስለምን እግዚአብሔር ሰውን ለመፍጠር ያዘጋጀውን መንገድ መግደያ ታደርጉታላችሁ? ስለምን ልጅን አቅፋ እንድትስም የተፈጠረችውን ሴት ነፍሰ ገዳይ እንድትሆን ታደርጓታላችሁ? እህቴ ሆይ! ፍቅረ ንዋይ ዐይንሽን አሳውሮት፣ ዳግመኛም በፍትወት ከሚመስሉሽ ጋር ዝሙትን ለመሥራት ስትዪ ፍምን በራስሽ ላይ አታከማቺ ወንድሜ ሆይ! ምንም እንኳን ይህን አሰቃቂ ግድያ የምትፈጽመው እርሷ ብትሆንም አንተም ከእርሷ ጋር ተባባሪ ነህ። 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
17 745
145

📝 ከሚከተሉት ውስጥ ትክክለኛው አጻጻፍ የቱ ነው?

ሀ. እግዚያብሄር
ለ. እግዚአብሄር
ሐ. እግዚአብሔር
መ. እግዛቤር
ሠ. እግዚያብሔር
ረ. እግዚሐብሔር
3.6k
Anonymous voting
19 525
153
​​ፋሽን የምትወድ ሚስት ላለችው ኦርቶዶክሳዊ ባል የተሰጠ ምክር “ሚስትህ ውጫዊና ውድ የኾኑ ጌጦችን፣ ጊዜ አመጣሽ ልብሶችን፣ ብዙ መናገርን እንደዚሁም መጀነንን ልትወድ ትችላለች፡፡ በርግጥ እነዚህን ኹሉ ችግሮች በአንድ ሰው ውስጥ ይገኛሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ይኾን ይኾናል፡፡ ነገር ግን እንደው እንደዚህ ያለች ሴት (ሚስት) አለችህ እንበል፡፡ ባል እንግዲህ ማድረግ ያለበት ሚስቱን የተቻለውን ያህል እንድታስተካክል ማድረግ ነው፡፡ ባል ሚስቱ እንድትስተካከል ማድረግ የሚችለውስ እንዴት ነው? በሚስቱ ዘንድ ያሉትን ስሕተቶች ውጤታማ በኾነ መንገድ ሊቀርፋቸው ቢፈልግ በአንድ ጊዜ ኹሉንም ነገር አይከልክላት፡፡ ይህን ከማድረግ ይልቅ ከቀላሉና ከሌሎቹ ይልቅ አነስተኛ ግምት ከምትሰጠው ነገር ይጀምር፡፡ ትዕግሥት የለሽ ከኾንህና ኹሉንም በአንድ ጊዜ ካልተውሽ ካልሃት ግን ማስወገድ የምትችለው እጅግ ጥቂቱን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ጌጦችዋን በመውሰድ አትጀምር፤ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ እንድታደርገውም ፍቀድላት፡፡ ይልቅ አብዝታ ስትቀባባና ስትኳኳል ይህን እንደማትወድላት በመንገር ጀምር፡፡ ይህን ስትነግራት ግን በማሳመንና በቀና መንፈስ እንጂ በማስፈራራትና በመዛት ወይም አሉታዊ በኾነ አገላለፅ አይኹን፡፡ ይህን በማድረግዋ መንፈሳውያን ወንድሞችና እኅቶች ደስ እንደማይሰኙባት ንገራት፡፡ የአንተ ምርጫ ምን እንደ ኾነ ንገራት፡፡ ፊቷን አብዝታ ስትቀባባና ስትኳኳል እንደማትወድላት ብቻ ሳይኾን ደስታን እንደማይፈጥርልህ ንገራት፡፡ ይልቅ ይህ ቅር እንደሚያሰኝህ ግለፅላት፡፡ በተፈጥሮአቸው እጅግ መልከ መልካም የኾኑ ሴቶች ይህን ሲያበዙ ማራኪነታቸውን እንደሚቀንስ በቀና መንፈስ ንገራት፡፡ “በዚህ መንገድ ለዚህ ነገር ያላትን ፍቅር እንድትቀንስ አስረዳት፡፡ ይህን ስትነግራት ግን እስከ ጊዜው ጊዜ ከእሳተ ገሃነም ወይም ከመንግሥተ ሰማያት ጋር አያይዘህ አትንገራት፡፡ ይህ ጊዜ እንድታጠፋ ያደርግሃልና፡፡ ከዚህ ይልቅ ባልዋ የምትኾን አንተ ደስ የምትልህ እግዚአብሔር በሰጣት ውበት ውብ ስትኾን እንደ ኾነ፣ ሌሎች መንፈሳውያን ወንድሞችና እኅቶችም ይህን ተፈጥሮአዊ ውበትዋን እንደሚወዱላት ንገራት፡፡ “ይህን ለብዙ ጊዜ ነግረሃት ባትሰማህ አንተም መንገርህን አታቋርጥ፡፡ ጠብ ክርክር በሚፈጥር መልኩ ሳይኾን በብልሐትና በፍቅር ንገራት፡፡ ያን አድርጋ ስታያት ደስ አለመሰኘትህን አንዳንድ ጊዜ በፊትህ ገጽታ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ለእርስዋ በመጠንቀቅና በማሳመን ንገራት፡፡ ይህን ደጋግመህ ስታሳያትና ስትነግራትም አንድ ቀን አብዝታ ከንፈርዋን በቀይ ቀለም መቀባባቱን፣ ቅንድቦችዋን መኳኳሉን ትተዋለች፡፡… “ይህን ችግር እንዲህ አድረገህ ካስተካከልህ በኋላ ሌሎቹም በቀላሉ ይስተካከላሉ፡፡ አሁን ወደምታደርገው የወርቅ ጌጥና ብዙ መናገርዋን ወደ ማስተካከል መሸጋገር ትችላለህ፡፡ ከላይ በነገርኩህ መንገድም ማስተካከል ትችላለህ፡፡” (#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ) ገብረ እግዚአብሔር ኪደ እንደተረጎመው 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
21 157
182
ምን ያስጨንቃችኋል? በተለያየ አጋጣሚ፣ በተለያየ ሁኔታ ውስጣችን የሚጨነቅበት፣ ለዘመናት አምቀነው የቆየናቸው እና ለማን አወራዋለሁ ብለን የተሰቃየንባቸው ምሥጢሮች፣ ራሳችንን መግዛት፣ ራሳችንን ማሸነፍ እየፈለግን አቅም ያጣንባቸው ዓመታት። እነዚህን ሁሉ ማሸነፍ የምንችልበት የሥነ-ልቡና የምክክር አገልግሎት አዘጋጅተን ወደ እናንተ የመጣን ሲሆን እረፍት፣ሠላም፣ብርታት እና አሸናፊነትን መላበስ ከወደዳችሁ። 👉በ(091) 208-5085 በመደወል ወደ ቢሮአችን መምጣት ትችላላችሁ። 🌕ንጹሕ ህሊና ለሠላማዊ ማንነት🌕
20 969
36
21 881
20
​​ኦ ፍጡነ ረድኤት እምሩጸተ ነፋስ ወዓውሎ ለዘይጼውዐከ በተወክሎ ጊዮርጊስ ቅረብ ለምሕረት ወለተሣህሎ ተወከፍ ወትረ ጸሎትየ ወቃለ ጽራኅየ ኵሎ እስመ ልበ አምላከ ርኅሩኅ በኀቤከ ሐሎ ለቤሩታዊት የደረሰ ሰማቱ ጊወርጊስ ገሰገሰ ፈጥኖ ሊወጣኝ ከመከራ ቆሟል ከጎኔ ከእኔ ጋራ/፪/ #አዝ ሥጋው ሲመተር አልፈራም እርሱ ሠባት አክሊላት ጭኗል በራሱ በደብረ ይድራስ በዛ ተራራ የልዳው ጸሐይ ተብሎ ተጠራ #አዝ ዓለምን ስትዞር በነጭ ፈረስ አንድግዜ እርዳኝ ጊዮርጊስ ድረስ ሥሙን ለጠራ አምላከ ጊዮርጊስ ሲደርስ ይፈጥናል ከዓውሎ ንፍስ #አዝ ለእሣት ለግለት ሥጋውን ሲሰጥ ፍርሐት የለበት ወይም መደንገጥ ኡዲያኖስ አፍሮ ጣዖት ወደቀ በጊዮርጊስ ጽናት ጌታ ታወቀ #አዝ ከሹመት ይልቅ መርጠኽ መከራ ወንጌሉን ሰበክ አንዳች ሳትፈራ በጭንቀት ሆነ የአንተ ንግሥና ብድራትኽን አይተሃልና #አዝ መስተጋድል ነኽ ሐያል ገናና መክብበ ሠማያት የዕምነት ጀግና ሥምኽን ስጠራ ከቤትኽ ቆሜ ይቀልልኛል የሐጢዓት ሸክሜ። 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

ኦ_ፍጡነ_ረድኤት_ለቤሩታዊት_የደረሰ_ሰማእቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ዘማሪት_መቅደስ_ማርዬ_16k.m4a

24 089
420
#አካሉ እሸቱ #አብርሀም ሞላ (3392 ብር ቀሪ አለ ነገ ጧፍ ሲመጣሃ እንጨምራለን ማለትም አብርሀም 3392 ብር ደረሰኝ ይቀርሃል) #ፍቅር ዘውድ #ቃልኪዳን አሸናፊ #ድርሰ አያሌው #አያልነሽ ድርስ #አጠቃላይ 5004 ብር ጧፍ ተገዝቷል ___________ ለፆመ ገና ማስቀደሻን ምክንያት በማድረግ የ3 ወር መባ (ዕጣን፥ዘቢብ፥ጧፍ፥ሻማ፣) በ6 ሀገረስብከቶች ለሚገኙ 100 የገጠር አጥቢያዎች በማሰባሰብ ላይ ነን በማሰባሰብ ላይ ነን :: መግዛት ለምትፈልጉ በቴሌግራም በውስጥ መስመር ያናግሩን። በ251927707000 ይደውሉልን ! በተጨማሪ ከላይ ባለው ቁጥር በዋትስአፕ ፣ ማናገር ይችላሉ በቴሌግራም @BeGood16 #ማስታወሻ የሌሎችንም እንደዚህ እየገዛን እናሳውቃለን
19 956
6
​​ስለጸሎት ምክር 👉 "መልካም ነገሮች ከሚባሉት መካከል ተጠቃሽ የሚሆነው አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ መያዙ እና መጠበቁ ነው። እግዚአብሔር ብዙ ቃል ገብቷል እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ግልፅና ታማኝ ነው። እናም ቃሉን አያጥፍም። የእርሱን ቃል ይዛችሁ ከእርሱ ጋር ተነጋገሩ። " ቃል የገባህልንን መች ነው የምትፈፅምልን" በሉት። 👉 ቃልህን ይዤ እጠይቅሀለው “አዲስ ልብን እሰጣችኋለው” ብለሃል ፣ ታዲያ የታለ አዲሱ ልብ? እኔ ራሴን ስመለከተው የድሮ ልቤ እንዳለ ነው። የትናንትናው መጥፎ ጠባይ ልክ እንደ ትናንትናው ነው። የታለ ታዲያ አዲስ ልብ እሰጥሃለሁ ያልከኝ? እኔ ማወቅ እፈልጋለው፣ ከውስጥ እንድትቀይረው እንድትሰማው እፈልጋለው፣ እኔ አስቸገርኩህ አንተ አስተካክለኝ፣ ሥራብኝ፣ ደረቅ መሆኔን አስተካክልልኝ። ስህተት አለብኝና ስህተቴን አስወግደው። ድርቅና አለብኝና ድርቅናዬን አስወግደው። ኃጢያአት አለብኝና ኃጢአቴን አስወግደው። ጌታ ሆይ እኔ ውስጥ ሥራ እናም ውስጤን አንጻው። መጋዙን መዶሻውን አንሳው ሥራብኝ ይህ መጥፎ እንጨት የተባለውን ላንተ ወንበር አርገው" በሉት። 👉 አንዳንድ ሰዎች ደካማ መሆናቸውን ሲያውቁ አለመቻላቸውን እና መውደቃቸውን ሲያረጋግጡ እግዚአብሔር ወደ ሕይወታቸው እንዲገባ ከመለመን ይልቅ እግዚአብሔርን ይቀየሙታል እና ይጮሀሉ" ለምንድን ነው እግዚአብሔር ብቻዬን የተወኝ? በቃ ከአሁን በኋላ እግዚአብሔርን አላቅም! ቤተክርስቲያን አልሄድም ! ንስሐ አልገባም ! አልቆርብም !" ይላሉ ። ይህ ምንድን ነው? ጌታን ከመለመን ይልቅ መቃወም ይሻላልን? እስቲ አስተዋይ ሰው እንሁን! 👉 ከእግዚአብሔር ጋር ሆነህ ተፋለም ፣ ታሸንፋለህ እና ታልፋለህም። እግዚአብሔርን እንዲህ ብለህ ጠይቀው... "ጌታ ሆይ አጋዥ ትባላለህ ፤ አጋዥነትህ የት አለ? ና አግዘኝ። አዳኝ ትባላለህ፤ የት አለ ማዳንህ? ና አድነኝ። ምንም ነገር አይሳንህም ትባላለህ እኔን ማዳን አይሳንህም፥ ያለምክንያት ‘ምንም የማይሳነው’ አንልህምና። ጌታ ሆይ፥ እኔ አንድ ችግር ነኝ። ፊት ለፊትህ ቀርቤያለው መንፈስህን አኑርብኝ። ምንም አይሳንህም እና እኔን ሥራኝ እምነትህ ደካማ ነው ካልከኝ ፥ ጠንካራ አድርገው። ልቤ ቆሽሿል እና አፅዳልኝ። ሙሴ ጸሊምን እና ማርያም መግደላዊትን እንዳስተካከልካቸው እኔንም አስተካክለኝ። አንተ የምትለው "ወደ እኔ የመጣውን ወደ ውጪ አላስወጣውም " ነው ... ይኸው ወደ አንተ መጥቻለው ባዶ እጄን አትላከኝ። ጌታ ሆይ የበጎ ነገር ፈጣሪ ትባላለህ እንዲ ከሆነ በእኔ ውስጥ በጎ ነገርን ስራ ። ከብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ስብከት የተቀነጨበ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...
photo
27 169
435
#የልቤን_በልቤ_ይዤ የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጅኝ እላለሁ ግራኝ ቀኝ ህይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል በፊት በኋላዬ መሰናክል በዝቷል እኔስ ያለ ምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል እመ አምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል(2) #አዝ ቆሜ ስራመድ ጤነኛ እመስላለሁ የውስጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ(2) #አዝ እናት ያለው ሰው ፍጹም አይተክዝም አንድ ቀን ይስቃል አልቅሶም አይቀርም ሀዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ በደስታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ(2) #አዝ አሁን ጎዶሎ በውስጤ አለና ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና ለዚች ለትንሿ ለጥቂቷ እድሜ እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ(2) 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show more ...

Hdbdu - __ g1aTY0UtbnM.m4a

23 953
638
Last updated: 06.12.21
Privacy Policy