cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
29 295
المشتركون
+8424 ساعات
+4067 أيام
+81730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ ከሕይወት ይልቅ፡ ሞት፡ ይገባሃል፤ እያሉ፡ ያንን ሊቀ ካህናት፡ ይዘልፉት፡ ነበር። በአንድነት፡ ከዘለፉትም፡ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ፡ ይዘውት፡ ሄዱ፤ ወደ ንጉሥም ይወስዱት፡ ዘንድ፡ ተስማሙ። የድንግል፡ ማርያም፡ በረከት የተወዳጅ ልጅዋም፡ ምሕረት፡ ከእኛ፡ ጋራ፡ ለዘላለም ይደርብን፤ አሜን። (#ግብረ_ሕማማት)
إظهار الكل...
👍 18🙏 13 8
#የማርያም_ሐዘን - ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት የሚነበብ ልመናዋ፡ ክብሯ፡ ለዘላለሙ፡ ከእኛ ጋር ይኑርና፡ አንድ፡ አምላክ፡ በሆነ በአብ በወልድ፡ በመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ስም አምኖ የብህንሳ፡ ኤጲስቆጶስ፡ አባ ሕርያቆስ ድንግል፡ ማርያም፡ እመቤታችን ስላለቀሰችው፡ ልቅሶ፡ በዛሬው፡ ቀን የደረሰው ይህ ነው፤ አሜን። ወደ ዮሐንስ ቤትም በደረሰች ጊዜ አልዘገየችም። ወደ ቀራንዮ፡ ተመልሳ፡ ልትሄድ፡ የተወዳጅ፡ ልጅዋን፡ የመከራውን፡ ፍጸሜ፡ ታይ፡ ዘንድ፡ ቸኰለች፡ እንጂ። በመስቀል፡ ላይ፡ ነፍሱን፡ በፈቃዱ፡ ሰጥቶ፡ ዝም፡ በአለ፡ ጊዜ፣ በምድር፡ ላይ፡ ስለሆነው፡ ንውጽውጽታና፡ በሰማይም፡ ስለተደረጉ፡ አስደናቂ፡ ተአምራቶች፡ ሀገሪቱ፡ ሁሉ፡ ተሸበረች። ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ምድር፡ ስትናወጽ፡ ጨለማ፡ በምድር፡ ሁሉ፡ ስትሰለጥን፡ አይታ፡ እነሆ፡ እነዚህ፡ ተአምራቶች፡ የልጄ፡ የሞቱ፡ ምልክቶች፡ ናቸው፡ ብላ፡ ጮኸች። እንዲህ፡ ስትልም፡ ዳግመኛ፡ ዮሐንስ፡ ደርሶ፡ እያለቀሰ፡ ከእርሷ፡ ዘንድ፡ ቆመ። ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ዮሐንስ፡ ሆይ፡ በመስቀል፡ ላይ፡ ልጄ፡ በእውነት፡ ሞተን፡ አለችው። እርሱም፡ ራሱን፡ ዝቅ፡ አድርጎ፡ እናቴ፡ ሆይ፡ አዎን፡ ሞተ፡ አላት። ፮፤ ከዚህም፡ በኋላ፡ ታላቅ፡ ልቅሶ፡ ሆነ። በዚያችም፡ ሰዓት፡ ድንግል እመቤታችንን፡ ፍጹም፡ ጩኸትና፡ ልቅሶ፡ ጸናባት፤ በመረረ፡ ልቅሶም፡ እየጮኸች፡ ልጄ፡ ሆይ ከዚህ፡ ካገኘህ፡ የሞት፡ ፃዕር፡ የተነሣ፡ ግፌን የሚመለከትልኝ፡ ሹም፡ ወይም፡ በሐዘን፡ የተሰበረውን፡ ልቤን፡ አይቶ፡ በማስተዋል፡ የሚፈርድልኝ፡ ዳኛ፡ አላገኘሁም፡ አለች። መኰንን፡ ሆይ፡ እንደ፡ ሕጉ፡ የምትፈርድስ፡ ቢሆን፡ ኖሮ፡ ንጉሥ፡ ልጄን፡ እንደራበው፡ እንደጠማው፡ የአይሁድ፡ ወገኖች፡ ባልሰቀሉትም፡ ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ ፈራጅ፡ ብትሆን፡ ባርያ፡ በጌታው፡ ፈንታ፡ መሞት፡ በተገባው፡ ነበር። በበርባን፡ ፈንታ፤ ሹም፡ ሆይ፡ በቅን፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ልጄን፡ ባልሰቀልከውም፡ ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ከልጄ፡ ይልቅ፡ ይሁዳ፡ ለሞት፡ የተገባው፡ በሆነ፡ ነበር። ሹም፡ ሆይ፡ ፍርድን፡ የምታውቅ፡ ቢሆን፡ ልጄን፡ ሥጋውን፡ አራቁተህ፡ መስቀል፡ ባልተገባህም፡ ነበር። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ ወንበዴውን፡ አድነህ፡ ጻድቁን ባልገደልከውም፡ ነበር። ዳኛ፡ ሆይ፡ መልካም፡ ፍርድን፡ የምታውቅ ብትሆን፡ ኑሮ፡ ጦሮች፡ በላይህ ላይ ሲያንዣብቡ፡ ጽኑዕ፡ የሆነውን፡ ባልገደልከውም ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ የጌታህን፡ ፊት፡ ባፈርክ ነበር። እኔ፡ ስለጦርነት፡ ሰልፍ፡ ስሰማ፡ የንጉሥ፡ ልጅ፡ በጦርነቱ፡ ውስጥ፡ የተያዘ፡ እንደሆን፡ እንዳይሞት፡ ስለእርሱ፡ እጅግ፡ በርትተው፡ እየተዋጉ፡ ወደ፡ አባቱ፡ በፍጹም፡ ጌትነትና፡ ክብር፡ እስከ፡ አደረሱት፡ ድረስ፡ ይጠብቁታል ። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ፡ ለምን፡ እንዲህ፡ ሆነ፡ በጠየቅኸው፡ ጊዜ፡ ዕውነቱን፡ አስረዳህ፣ ግን፡ በአንተ፡ ዘንድ፡ የተጠላ፡ ሆነ፡ ሐሰትን፡ ወደድክ፤ እምነትህንም፡ በሐሰቱ፡ ላይ፡ አጸናህ፤ እንግዲህ፡ ከእውነተኛው፡ ከእርሱ፡ በቀር፡ ማንን፡ ትጠይቃለህ። በፊትህ፡ የቆመው፡ እርሱ፡ እውነተኛ፡ እንደሆነ፡ አታውቅምን፡ እርሱም፡ በዕውነት፡ ሕይወት፡ ነው። ንጽሕት፡ ድንግል፡ ሆይ፡ በኢየሩሳሌም፡ ከተማ፡ በዚች፡ ትውልድ፡ መካከል የሆነውን፡ ታላቅ፡ ግፍ፡ እዪ፣ እነሆ፡ ከእነርሱ በሚበልጠው፡ ላይ፡ ተሰብስበው፡ ስም ለሞት ፍርድ፡ ሰጥተውታልና። ከዚህ፡ ሁሉ፡ በኋላ፡ ክርስቶስ፡ በመስቀል ላይ፡ እንደሆነ፡ ነበር፣ የመቶ፡ አለቃውን በዕውነት፡ ይህ፡ ሰው፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡ ብሎ፡ አመነ፤ እሊህ፡ ተአምራቶቹ በሁሉ፡ ዘንድ፡ ታመኑ። ፳፣ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ሳለ ምዕመናን ሁሉ፡ በአንድነት፡ አለቀሱለት። ስለጌታ፡ ስቅለት፡ ከሄሮድስ፡ ዘንድ ወደ መጣው፡ የመቶ፡ አለቃ፡ ጲላጦስ ልኮ አስመጥቶ፡ ወደ፡ ቤቱ፡ አስገብቶ፡ ወንድሜ ሆይ፡ ይህን፡ ጸድቅ፡ ሰው፡ አይሁድና ሄሮድስ ያደረጉትን፡ አየህን? ይህ፡ ሁሉ ተአምራት በምድር፡ እስኪሆን፡ ድረስ፡ በግፍ ሰቀሉት። ወንድሜ፡ ሆይ፡ በእውነት፡ እነግርሃለሁ፤ እነዚህ፡ ከፋቶች፡ ሁሉ፡ የተፈጸሙት፡ በሄሮድስ፡ ምክር፡ እንጂ፡ በእኔ፡ ፈቃድ፡ አይደለም፤ እኔ፡ እንዳይሞት፡ ልተወው፡ ወደድኩ፤ ነገር፡ ግን፡ ሄሮድስ፡ በዚህ፡ ደስ፡ እንደማይለው፡ ባየሁ፡ ጊዜ፡ ይሰቅሉት፡ ዘንድ፡ ለአይሁድ፡ ሰጠኋቸው፡ እንጂ። ተመልከት፡ አሁን፡ ለእግዚአብሔር፡ ስለ፡ ሰቀልነው፡ ልጄ፡ ምን፡ ብድርን፡ እንከፍላዋለን፡ አለው፣ የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ፡ ከጲላጦስ፡ ጋር፡ ደሙ፡ በሄሮድስና፡ በካህናት፡ አለቆች፡ ላይ፡ ነው፣ እያሉ፡ መራራ፡ ልቅሶ፡ አለቀሱ። በዚያን፡ ጊዜ፡ ጲላጦስ፡ ልኮ፡ የካህናት፡ አለቆች፡ ቀያፋና፡ ሐናን፡ ወደ፡ ጉባዔው አስጠርቶ፡ እናንተ፡ በግፍ፡ ደምን፡ የምትጠጡ፡ ተኵላዎችና፡ ቀበሮዎች፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ወደ፡ ሞተው፡ የናዝሬት፡ ሰው፡ አሁን፡ ተመልከቱ፣ ደሙም፡ በእናንተና፡ በልጆቻችሁ፡ ላይ፡ ይሁን፡ አላቸው። እነርሱግን፡ ደስ፡ በመሰኘት፡ እያፌዙ፡ ደረታቸውን፡ እየደቁ ፊታቸውንም፡ እየነጩ፡ እስከ፡ ሽህ፡ ትውልድ፡ በእኛና፡ በልጆቻችን፡ ላይ፡ ይሁን፡ ኣሉ። እነርሱም፡ እንደ፡ ሕጋችን፡ ፈጽመናል፡ ስለምን፡ እንፈራለን? እንደነግጣለን፡ አሉት። ጲላጦስም፡ የሐሰት፡ ሕግ፡ ፈጸማችሁ፡ እንጂ፡ ይህ፡ ሕግ አይደለም፡ ኣለ፤ አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባልከው፡ እነሆ፡ ልብሶችሁ፡ ተቀደዋል። ሕጉም፡ ሊቀ፡ ካህናቱ፡ ልብሶቹን፡ በቀደደ፡ ጊዜ፡ ከክህነት፡ አገልግሎት፡ ይከልከል፡ ይላል። ቀያፋም፡ እኔ፡ ልብሴን፡ የቀደድኩት፡ እርሱ፡ በእግዚአብሔርና፡ በሕጋችን፡ ላይ፡ የስድብ፡ ቃል፡ ስለ፡ ተናገረ፡ ነው፡ ብሎ፡ መለሰለት። ጲላጦስ፡ እንግዲህ፡ በሊቀ፡ ካህናት፡ ሥርዓት፡ ወደ፡ መቅደስ፡ ኣንተ፡ እንድትገባ አልፈቅድልህም፡ እንደ፡ ሕግ፡ አፍራሽ፡ እንጂ ። አንተ፡ ወደ፡ መቅደስ፡ እንደገባህ ሌላው ቢነግረኝ፡ ቸብቸቦህን፡ ከአንተ ላይ እቆጣለሁ፡ አለው። ቀያፋም፡ ከአንተ፡ በፊት፡ ብዙ ጊዜ አልፎአል፤ ብዙዎችም፡ ሹማምንት የሚቀድሙህ፡ አሉ፤ እስከ፡ ዛሬ፡ የካህናት አለቆችን፡ ወደ፡ መቅደስ መግባትን፡ የከለከላቸው፡ አለን፡ ብሎ፡ መለሰለት። ይህንም፡ ያለ፡ የሄሮድስን፡ ሥልጣን በመተማመን፡ ነበር፤ ጲላጦስም፡ ይህን፡ ሁሉ ተአምር፡ ስታይ፡ ከሕዝቡ፡ ሁሉ፡ ጋር፡ አሁንም፡ ልብህ፡ አያምንምን፡ አለው። ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባለ፡ ቀያፋም፡ አንተስ፡ በዚች፡ አገር፡ አዲስ፡ ተክል፡ ነህ፣ ይህ፡ ምልክት፡ የሆነበትን፡ ነገርና፡ የተደረገውን፡ ኣታውቅም። ይህ፡ ይቅርታ፡ የሚደረግበት፡ የመጋቢት ወር፡ ፀሐይና፡ ጨረቃ፡ ዑደታቸውን፡ ፈጽመው፡ ተራክቦ፡ የሚያደርጉበት፡ ሲሆን፡ በዚሁ፡ ወር፡ መሠርያኖች፡ ጨረቃን፡ እንደ፡ ደም፡ የሚሆንበትን፡ ያደርጋሉ፤ የፀሐይንም፡ ብርሃን፡ በሥራይ፡ ኃይል፡ ይስባሉ። የአግዓዝያንን፡ ተግባር፡ ይመረምራሉ፤ የሥንዴውን፡ የወይንንና፡ የዘይትን፡ ፍሬዎች፡ በማዘጋጀት፡ ይህን፡ የመሰለውን፡ ቀያፋ፣ በሐሰት፡ ይናገር ነበር። ጲላጦስም፡ ከወንበሩ፡ ላይ፡ ተነሥቶ፡ አንተ እርሱን፡ ከመጥላትህ፡ የተነሣ፡ በዓለም ሁሉ፡ ላይ፡ መዐትን፡ ልታመጣ፡ ትወዳለህ ብሎ፡ ከቆዳ፡ በተሠራ፡ በደረቅ፡ በትር ደበደበው፤ ጽሕሙንም፡ ነጨው።
إظهار الكل...
👍 12🙏 5 2
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡ ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡ ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" /ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
إظهار الكل...
26🙏 7👍 3💔 1
#ዓርብ_ስድስት_ሰዓት_የሚነበብ (የስምዖን ዐምዳዊ ጸሎት) ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ በዕንጨት መስቀል፡ ላይ፡ ራቁትህን፡ የሆንክ፡ ጨለማን ከለበሰና፡ ስሕተትን፡ ከሚያመጣ፡ ሰይጣን መንፈስ፡ ለየኝ። በኃይልህ፡ እታደስ፡ ዘንድ፡ በጥበብህም፡ እመገብ፡ ዘንድ፡ የሕይወት፡ ሐር፡ ልብስን፡ አልብሰኝ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን፡ የብርሃን፡ መጐናጸፊያ፡ የምታጐናጽፋቸው ኃይልንም የምታስታጥቃቸው በመስቀል፣ ላይ፡ ራቁትህን፡ ቆምክ። ልቡናዬን፡ ከፍጹም፡ ድንቁርና፡ ጨለማ፡ አርቅ፣ (አንፃ)፣ በልቤና፡ በሕዋሳቴ፡ ውስጥም፡ የጌትነትህን፡ ብርሃን፡ አብራ፤ ከምድራዊ፡ ሀሳብና፡ ጠባይ፡ ተለውጠው፡ ከሰማያውያን መላእክት፡ ጋራ፡ ያመሰግኑህ፡ ዘንድ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ የከበሩ፡ እጆችህን፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ የዘረጋህ፡ ፍቅርህ፡ በውስጡ፡ ያድርበት ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ እንዲከፈት፡ አድርገው። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን ከእሳት፡ የፈጠርካቸው፡ ሰማይንም፡ እንደ ድንኳን፡ የዘረጋህ፡ የምድርንም፡ ስፋቷን ያበዛህ። በበላይዋም፡ ዓለማተ፡ ሰማይን፡ እጅግ፡ ከፍ አድርገህ፡ የፈጠርክ፡ ከበታችዋም፡ እጅግ ጥልቅ ያደረግህ፡ ዙሪያዋንም፡ በባህር፡ የከበብህ ትእዛዝህም፡ ምድርን፡ በባሕር፡ ላይ፡ ጸንታ እንድትኖር፡ ያደረጋት፡ በውስጥዋ፡ ያለውንም ሁሉ። በመስቀል፡ ላይ፡ እንዴት፡ እጅህን ዘረጋህ? እንዴትስ፡ በቀኖት፡ ተቸነከርክ፡ ወዴትስ ወረድክ? ለሞት፡ እስክትደርስ፡ ድረስ፡ የአዳምን፡ ማዳን፡ እንደምን፡ ወደድክ። አፍና፡ አንደበት፡ ካላቸው፡ ለጌትነትህ፡ ምስጋና፡ ማቅረብ፡ የሚችል፡ ማን፡ ነው። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ፍቅርህን፡፡ በልቤ፡ ውስጥ፡ ቅረጽ፤ ከክፉ፡ ማሰሪያ፡ ፍታኝ፤ ለዘላለም፡ ጸንቶ፡ በሚኖር፡ ፍቅርህም፡ እሰረኝ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ማሕየዊ፡ መስቀልህን፡ አቅፌ፡ ከእርሱ፡ የሕይወትና፡ የመድኃኒት፡ መዐዛ፣ አሸት፡ ዘንድ፡ ስጠኝ። በልቡናዬም፡ ውስጥ፡ ንጹሕ፡ ደምህ፡ ይውረድ፤ ንጹሕ፡ መሠዊያ፡ ይሆን፡ ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ ያክብረው፤ በውስጡም፡ የሕይወትን፡ መንፈስ፡ ያንቀሳቅስ፤ የሕይወት፡ መንፈስ፡ አንተን፡ ይቀበል። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ በመስቀል ላይ፡ መጻጻንና፡ ሐሞትን፡ የጠጣህ ከታላቁ፡ ንጹሕ፡ ፍቅርህ፡ አጠጣኝ፤ ከመራራው፡ ሞተ፡ ነፍስም፡ አድነኝ። (#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ)
إظهار الكل...
29🙏 10👍 5
ጴጥሮስ ሆይ እስከ ፈራህና ፈጥነህ እስከ ካድክ ድረስ ለእኔ ነው ትል ዘንድ በድጋሚ ሌላ መስቀል አላየህ፣ እንደ ብረትም የተሳለ አንደበት ሰጥቶህ ነበር። ጴጥሮስ ሆይ አንተስ ያለ እሳትና ያለእንጥረኛም ፈጽመህ አቀለጥከው። ጴጥሮስ ሆይ ከሰው ሁሉ ለገጽህ ግርማ ሰጥቶህ ነበር፤ ብርሃናቸው የማይጠፋ ዓይኖችን የሰጠህ ሲሆን ስለጌታህ አንዲት ጥፊ ትቀበል ዘንድ ዛሬ አልታገሥክም። ጴጥሮስ ሆይ የመንግሥት ሰማያትን መክፈቻ የሰጠህን ልጄን በካድከው ጊዜ አልፈራህም፤ በሊቀ  ካህናቱም ግቢ አልታገሥክም፤ በእርሱ ፈንታም ለዓለሙ ሁሉ የታመነ ጠባቂ አድርጎ ሾመህ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ ጌታህ አንድ ጊዜ እንኳ ጥቂት መከራ አልተቀበልክም። ጴጥሮስ ሆይ ለዓለሙ ሁሉ አባት ትሆን ዘንድ ሾመህ፤ አንተ ግን ለልጄ የወንድማማችነት ፍቅርን አላደረግህም። ጴጥሮስ ሆይ አምላካዊ እጁን በራስህ ላይ ጫነ፤ አንተ ግን ከመካድህ በፊት ዛሬ በራስህ ላይ የእሾህ አክሊል ይጭኑብህ ዘንድ አልፈቀድክም። ጴጥሮስ ሆይ ልጄ ለአንተ ወዳጅህ እንጅ እንደ ጌታህ እንዳልሆነ አስብ። ልጄን እንደዚህ ትክደው ዘንድ ለአንተ አግባብ ኣይደለም። ጴጥሮስ ሆይ ከእኛ ጋራ ይህ ሁሉ ድካም እንዳገኘው እንደ አባቴ ዮሴፍ ብትሆን ኖሮ። ጴጥሮስ ሆይ እንደ እርሱ ወደ ኄሮድስ ቢጎትቱህ በግብጽ ምድርም ከእኛ ጋራ መከራ ተቀባይ ብትሆን እንደ እርሱ መታገሥ ባልቻልክም ነበር እንጃ። አባቴ ጸድቁ ዮሴፍ ሆይ በአጥንቶችህ ላይ የሰማይ ጠል ይውረድ። ነፍስህም ዕፀ ሕይወትን ትመገብ፤ ከእኛ ጋራ ታግሠህ መከራ፡ ስትቀበል እንደ ጴጥሮስ ልጄን አልካድከውምና። ጴጥሮስ ሆይ ወደ ፍርድ አደባባይ አልወሰዱህ በባለ ሥልጣኖችም ፊት አላቆሙህ ፈጥነህ ጌታህን ካድከው። ድንግል በዮሐንስ ቤት እንደዚህ ስታለቅስ ሳለ ዮሐንስ እያለቀሰ መጣ እርሷንም እያለቀሰች አገኛት። ድንግል እመቤታችንና ዮሐንስም ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርስ በርሳቸው እየተላቀሱ ሁለቱም አብረው ነበሩ። ዮሐንስም ድንግልን እናቴ ሆይ ጌታችንን ጴጥሮስ ስለካደው አታልቅሺ አላት፣ አሳልፎ እንደ ሰጠው እንደ ይሁዳ ነውር የለበትምና። በእራት ጊዜ ጴጥሮስ ሆይ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ሲለው መምህሬን ሰምቻለሁና። ጴጥሮስም እንደዚህ በአንተ ላይ ይደረግ ዘንድ አይገባም፤ ጌታዬ ፈጣሪዬም እስከ ዘላለሙ ድረስ እልክድህም መሞት ይሻለኛል፤ እንደዚህም በእኔ ላይ አይሆንም፤ ስለ አንተ ነፍሴን አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ። ከዚህ ቀደምም መምህራችን ጌታ መምህሬ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ሲገሥፀው ሰምቻለሁ። ሰይጣን ባለጋራዬ ወግድ ከኋላዬ ዕንቅፋት ሁነህብኛልና ሰው ሰውኛውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና አለው። አሁንም እመቤቴ እናቴ ሆይ ስለ አባቴ ጴጥሮስ መካድ አታልቅሽ ለኃጢአተኞች ሁሉ ለንስሐ ምሳሌ ነውና። በቃሉ ያመነውን የጌታችንን ቃል አስተባብሎ ነበርና። በሐዘኗ የሚገኝ በረከት ከዐይንዋ የፈሰሰ የዕንባ ውኃ ጸጋ ለዘላለሙ ከእኛ ጋራ ይኑር አሜን። (#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ_ሦስት_ሰዓት)
إظهار الكل...
20👍 3🙏 3
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: #የማርያም_ሐዘን (#ዓርብ_በሦስት_ስዓት_የሚነበብ አባ፡ ሕርያቆስ፡ የደረሰው፡ ድርሳን፡ ይህ፡ ነው።) ወዳጆቼ ሆይ የአባቶች አለቃ የያዕቆብ ልቅሶ፤ ዛሬ ታደሰ አለ። በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ለወለደችው ለተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። መከራ ስለተቀበለችበት ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። የድንግልና ጡቷን ለእጠባችው ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በቤተልሔም በበረት ስለወለደችው ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በማኅፀንዋ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ለተሸከመችው ተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ ወልዳ ላልሳመቻቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ፤ እንደ ሰው ሁሉ በብብቷ ለተሸከመችው ልጇ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቦታ ወደቦታ ይዛ ላልተሰደደችባቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። ከሀገር ወደ ሀገር አዝላ ለተሰደደችበት ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ መቃብራቸውን ላላአየች ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። በአንድ ልጅዋ መቃብር ደጃፍ ላይ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። የባለ መልካም ጽሕም ሽማግሌ የያዕቆብ ልቅሶ በብላቴናይቱ ድንግል ዘንድ ዛሬ ታደሰ። ወንድሞቹ ባሰሩት ጊዜ ያዕቆብ ወደ ዮሴፍ አልተመለከተም። ድንግል ግን ልጅዋን በዕንጨት መስቀል ላይ ተቸንክሮ አየችው። ዮሴፍ በሰፊ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ያዕቆብ በላዩ፡ ያለቅስ ዘንድ ወደ ዮሴፍ አላየም። ድንግል ግን በአይሁድ ጉባዔ መካከል ተሰቅሎ ልጅዋን አየችው። ዮሴፍን ወንድሞቹ ልብሱን ገፈው ሲያራቁቱት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን በጎ ምክር በሌላት በአይሁድ መካከል ልብሱን ተገፎ ራቁቱን ሁኖ አየችው። ወንድሞቹ ዮሴፍን በሃያ ብር ሲሸጡት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን ይሁዳ ልጅዋን በሠላሳ ብር ሲሸጠው አየች። አራዊት ባልቀደዱት ልብስና በሌላ ደም ላይ ያዕቆብ አለቀሰ። አምላካዊ ደም ግን ድንግል ማርያም ስለእርሱ በላዩ የምታለቅስበት በቀራንዮ አለት ላይ የፈሰሰው ነው። ድንግል ግን ዛሬ ያየችው ልጅዋን ያለበሱትን ሌላ ልብስ ነበረ፤ የራሱን ልብስ ግን እርስ በርሳቸው ተካፈሉት። የዮሴፍ ወንድሞች ወንድማቸው ዮሴፍን በሸጡት ጊዜ አለቀሱ ተጸጸቱ። የእስራኤል ልጆች ግን ጌታቸውን በሸጡት ጊዜ አላለቀሱም፤ አልተጸጸቱም። የያዕቆብ ልጆች ወንድማቸው በነገሠ ጊዜ ተደሰቱ። አይሁድ ግን ጌታቸው ከሙታን ተለይቶ በተነሣ ጊዜ ደስ አላላቸውም። ድንግል ሆይ፤ በእውነት በልጅሽ መቃብር ላይ ልቅሶሽ ጣዕም ያለው አሳዛኝ ነበረ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምን ታደርጊያለሽ? ብለው የልጅሽን መሰቀሉን በነገሩሽ ጊዜ በመላእክት መካከልም ቃልሽ ያማረ ነበር። እነሆ ልጅሽን በመኰንኑ ፊት አቁመውታል፤ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትም ያሰቃዩታል፣ ያቃልሉታል፣ ማርያም ሆይ ምን ታደርጊያለሽ? እነሆ ልጅሽን በፍርድ አደባባይ መካከል ልብሱን ገፈው እያራቆቱት ነው። የኢያቄም ልጅ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምንስ ታደርጊያለሽ? እነሆ በኢየሩሳሌም ሜዳ የሚሰቀልበትን ግንድ ብቻውን ተሸክሞአል፤ አንድ እንኳ ወደ እርሱ የሚቀርብ የለም። የሐና ርግብ ሆይ ለምን ተቀመጥሽ? የምትሰሪውስ ምንድን ነው? እነሆ ልጅሽን ሰቅለውት በቀራንዮ ቦታ ቁሞአል። የዳዊት ዘር ሆይ ልጅሽን በመስቀል ላይ ለምን ከፍ ከፍ አደረጉት? እመቤት ድንግል ሆይ በዮሐንስ ቤት ዛሬ ልቅሶሽ በእውነት ጣዕም ያለው ነበረ እንዲህ ስትዪ። ወዮ ለዚህ መራራ ወሬ ነጋሪ ለኢዮብና እስራኤል ለተባለ ያዕቆብ ከአረዷቸው መርዶ የመረረ ነው። ዛሬ ወደእኔ ለሚመጣ ለዚህ ለክፉ ወሬ ወዮ። ልጄ ሆይ አገሩን በኢቃጠሉ ጊዜ ለሎጥ ከአረዱት መርዶ ያስጨንቃል። በእኔ ላይ ለደረሰው ለዚህ አስጨናቂ ስብከት ወዮ። ልጄ ሆይ ስለ ኃያላነ እስራኤል ሞት ከአረዱአቸው መርዶ ይበልጣል። በዚህ በክፉ ወሬ ወደእኔ ለመጣው ለዚህ ወሬ ነጋሪ ወዮ። ልጄ ሆይ እነሆ ስታረጋጋኝ ሠላሳ ዓመት ይሆናል፤ ልገሥጽህም አልተቻለኝም። ዛሬ ወደ እኔ ወሬህ እስከመጣ ድረስ ወጥተህ እስከምትገባ አንዲት ሰዓት እንኳ አላመንኩህም። ልጄ ሆይ ለሐዘኔ ሁሉ ጥንቱ ሰሎሜ ናት፤ እኔ ዳኛውን አየው ዘንድ ከቤቴ አልወጣም፤ በፈራጁም ፊት አልቆምም። ሌባውን ራሱን ሲቆርጡት ሽፍታውንም ይገድሉት ዘንድ ሲፈርዱበት አላየሁም። ከቶ ቀራንዮን አላየሁትም፤ የጎልጎታንም ቦታ አላውቅም፤ ሁል ጊዜም በሚጣሉበት ቦታ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ክፉ የሆነ ፍርድ አላየሁም፤ በፍርድ አደባባይም ከቶ ለዘላለሙ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ያደረኩብህን ግፍ አላውቅም እኔም በዮሐንስ ቤት ነበርኩ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በሊቀ ካህናቱ በሐና ግቢ የተቀበልከው ግፍ ወሬው መራራ ነው። ልጄ ወዳጄ ሆይ ዛሬ ከእኔ ላይ ነጻነቴን አስወገድክ፤ ስለልደትህ በናዝሬት መልካም የምስራች ነገሩኝ። ዛሬ ግን በኢየሩሳሌም ይህችን ክፉ መርዶ አረዱኝ። በዮሴፍ ቤት መልካም ዜና በዮሐንስ ቤት ግን የሞት ዜና መጣልኝ ። ልጄ ወዳጄ ሆይ እኔ በልቤ ደስ እያለኝ ተቀምጨ ነበር። በየዕለቱ ፋሲካ ደርሶአል በዓሉን እናከብር ዘንድ ወደሀገራችንም እንመለሳለን እያልኩ ነበር፤ የዚህ ዓይነት ፋሲካም ደረሰኝ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በእንባና በሐዘን በዓሌ ወደ ልቅሶ ተመለሰ፤ ፋሲካየም ወደልብ ሐዘን። በዮሐንስ ቤት ሳለች ስለ ልጅዋ የመከራ ወሬ በመጣበት ጊዜ ድንግል እመቤታችን ይኸንን ልቅሶ ታለቅስ ነበር። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ከንጹሐን ሐዋርያት አንድ ፈለገች አላገኘችም፤ አይሁድን ከመፍራት የተነሳ ሁሉም ትተውት ሸሽተዋልና። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ስለ ጴጥሮስ መረመረች፤ እርሱማ የካህናት አለቆችን ከመፍራቱ የተነሳ ልጅሽን ከቶ አላውቀውም አለ፤ ሒዶም ተሸሽጓል አልዋት። ዳግመኛም ስለ ጌታችን ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ ለያዙት ሰዎች በተራራ ላይ ልብሱን ትቶ እንደ ሸሸ ነገርዋት። እንድርያስንም ፈለገችው፤ እርሱስ ወደ ከተማ አብሮት አልመጣም አልዋት፤ እንደዚሁ ቶማስም ሽሽቶ ሔደ። ስለ በርተሎሜዎስም ጠየቀች፤ እርሱም ከወንድሞቹ አስቀድሞ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ፊልጶስም ጠየቀች፤ እርሱም የፋናዎችን ውጋገንና መብራቶችን ባየ ጊዜ ፈርቶ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ዮሐንስ ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ አንድ ጊዜ ስንኳ እንዳልቆመ ነገርዋት። ስለ ማቴዎስም መረመረች፤ እርሱም ግብር ስለሚቀበላቸው አይሁድንና የካህናት አለቆችን እጅግ ስለፈራ እነርሱም ስለሚጠሉት በሌሊት ጨለማ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ሁሉም መረመረች፤ አብሮ ወደ ቀራንዮና ወደጎልጎታ ከሔደው ዮሐንስ በቀር አንድም አላገኘችም። ድንግልም ከልጅዋ ደቀ መዛሙርቶች ከዮሐንስ በቀር አንድ እንኳ ባለማግኘቷ እንደገና ዳግም ወደ ጽኑ ልቅሶና ሐዘን ተመለሰች። እንዲህ እያለችም አለቀሰች፦ ልጄ ወዳጄ ሆይ ወዮልኝ ወንድሞችህ ሸሹ ትተውህም ተሸሸጉ። አባቴ ጴጥሮስ ሆይ ጌታህን እንዳትክድ ሁልቀን እጠራጠርህ ነበር፤ ስለ እርሱ ወርቅ ብር አልሰጠህ ለምን ጌታህን ፈጥነህ ካድከው? ስለርሱ መርከብ ወይም ቀዛፊ አልሰጠህም፤ መምህርህንና ጌታህን ዛሬ ለምን ካድከው? ስለርሱ ምንም አልሰጠህም ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ እርሱ ወንድምን ወይም ወዳጅን አልሰጠህም። ልጄን ለምን ካድከው? በዚህ ሁሉ ልብህ ለምን ቀላል ሆነ?
إظهار الكل...
👍 7 6🙏 1💯 1
#የሰሙነ_ሕማማት_ዓርብ ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያን ልዩ ቀን ነው፡፡ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁ ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግብር ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት፣ ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን፤ አሳዳጅ አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡ #የስቅለት_ዓርብ ይባላል የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለ ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል።  (ማቴ 27፡35) #መልካሙ_ዓርብ ይባላል ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ሲያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ። በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይር ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርአያ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ ስላደረገውና በዕለተ ዓርብ በሞቱ ሕይወትን ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡ በዚህ ዕለትም ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱ ፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ ተአምራት አሳይቷል፦ 1. ፀሐይ ጨልማለች 2. ጨረቃ ደም ሆናለች 3. ከዋክብት ረግፈዋል 4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዷል 5. ምድር ተናወጣለች (ተንቀጥቅጣለች) 6. መቃብሮች ተከፍተዋል 7. ሙታን ተነስተዋል በዓመት አንድ ጊዜ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን የምንውልበትና በዋዛ ፈዛዛ ልናሳልፈው አይገባም፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
إظهار الكل...
53👍 26🙏 9
🙏 2 1
#የሰሙነ_ህማማት_ሐሙስ #ጸሎተ_ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡  የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ (ማቴ. 26፥36-46 ዮሐ.17) #ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡ #የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡ #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል (ሉቃ. 22፥20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡ #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
إظهار الكل...
14👍 4
#በእንተ_ጸሎት_ሐሙስ "ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ  ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ዠመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡"  (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ) "በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው" (ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ) @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
إظهار الكل...
87👍 14🙏 8😍 5