telebirr
📈 Telegram kanali telebirr analitikasi
telebirr (@telebirr) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 324 990 obunachidan iborat bo'lib, Texnologiyalar & Aralashmalar toifasida 270-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 17-o'rinni egallagan.
📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika
невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 324 990 obunachiga ega bo‘ldi.
05 Sentabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 4 347 ga, so‘nggi 24 soatda esa -54 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.
- Tasdiqlash holati: Tasdiqlangan (Telegram tomonidan rasmiy tasdiq)
- Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 8.11% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 3.96% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
- Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 26 371 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 12 872 ta ko‘rish yig‘iladi.
- Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 49 ta reaksiya keladi.
📝 Tavsif va kontent siyosati
Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“https://t.me/EthiotelecomChatBot”
Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 06 Sentabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Texnologiyalar & Aralashmalar toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.
Ma'lumot yuklanmoqda...
| Sana | Obunachilarni jalb qilish | Esdaliklar | Kanallar | |
| 06 Sentabr | 0 | |||
| 05 Sentabr | +47 | |||
| 04 Sentabr | +119 | |||
| 03 Sentabr | +267 | |||
| 02 Sentabr | +158 | |||
| 01 Sentabr | +201 |
| 2 | #ከግንኙነት_ባሻገር_ለወገን_አጋር!
በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ በዛሬው ዕለት በይፋ የተጀመረው አገራዊ የበጎ አድራጎት መርሃ-ግብር፤ በአዲስ አበባ ዞኖች እና በመላው ሀገራችን በሚገኙ ሪጅኖች በኩባንያችን አመራሮች አማካኝነት ለበጎ አድራጎት ተቋማት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በአዲስ ጅማሮና በአዲስ ተስፋ ወደ አዲሱ ዓመት ስንሸጋገር፣ ወገኖቻችንን በመደገፍና አብሮነታችንን በማረጋገጥ ጭምር ነው።
🌼 አዲስ ጅማሮ
🌼 አዲስ ተስፋ
🌼 አዲስ ዕይታ
#በበጎነት!
#በአዲስ_ጅማሮ_በአዲስ_ተስፋ_በአዲስ_ዕይታ_2019አዲስ_ዓመት! | 7 565 |
| 3 | ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ፤ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በመርዳት ከግንኙነት ባሻገር ለወገን አጋርነትን ለማረጋገጥ ያለመውን ዓመታዊ የአዲስ ዓመት የበጎ አድራጎት መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።
በዚሁ መሠረት ዛሬ ባካሄድነው መርሐ-ግብር፤ በመላ ሀገራችን በሚገኙ 50 የበጎ አድራጎት ተቋማት ለሚረዱ 22,212 አረጋውያን፣ ሕፃናት፣ እናቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርገናል።
ባለፉት 5 ተከታታይ ዓመታት ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንጻር ከ117 በላይ ለሚሆኑ የበጎ አድራጎት ማዕከላት አጋር በመሆን፣ ድጋፍ የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ስንደግፍ ቆይተናል።
በ"ቀጣዩ አድማስ" ሰው-ተኮር ስትራቴጂያችንም የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ከማፋጠን ባሻገር፣ ሰብአዊነት የተሞላባቸው ተግባራትን በማከናወን የወገን አጋርነታችንን በቁርጠኝነት እናጠናክራለን።
#በበጎነት!
#ከግንኙነት_ባሻገር_ለወገን_አጋር!
#በአዲስ_ጅማሮ_በአዲስ_ተስፋ_በአዲስ_ዕይታ_2019አዲስ_ዓመት! | 10 445 |
| 4 | ኩባንያችን ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ነገ እሑድ ዻጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የበዓል ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡
በዕለቱ “ቴሌ ቀለማት” የተሰኘ ልዩ የአዲስ ዓመት የቴሌቪዥን ፕሮግራም የሚተላለፍ በመሆኑ ሙሉ ዝግጅቱን እንድትከታተሉ ከወዲሁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል፡፡
#Ethiotelecom #FMC #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia | 10 379 |
| 5 | ‘’ወደ አዲስ ዓመት፣ በበጎነት!’’ ብለን በያዝነው መሪ ቃል መሠረት የአዲስ ዓመት ጉዟችንን በደም ልገሳ አሐዱ ብለናል!
🩸በኩባንያችን ዋና መ/ቤት፣ በዞን እና በሪጅን ጽ/ቤቶቻችን የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናውነናል።
ተጨማሪ ምስሎች 👉 https://bit.ly/4gMII7n
በአዲስ ጅማሮ፣ በአዲስ ተስፋና በአዲስ ዕይታ ወደ አዲስ ዓመት፣ በበጎነት!
#InternationalDayOfCharity #BloodDonation
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia | 12 615 |
| 6 | ወደ አዲስ ዓመት...
በበጎነት!
🌼 አዲስ ጅማሮ
🌼 አዲስ ተስፋ
🌼 አዲስ ዕይታ
ሁሌም በየዓመቱ እንደምናደርገው ከዛሬ ጀምሮ የዻጉሜ ቀናትን በበጎነት እናሳልፋለን።
በኩባንያችን ዋና መ/ቤት፣ በዞንና በሁሉም ሪጅን ጽ/ቤቶቻችን የደም ልገሳ መርሐ ግብር በመካሔድ ላይ ነው፤ ዛሬ 22 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ላይ የገንዘብ ድጋፍ እናደርጋለን፤ በቀጣዮቹ የዻጉሜ ቀናት የደብተር ልገሳን ጨምሮ በልዩ ልዩ የበጎነት ተግባራት እንሳተፉለን።
መልካም ዓለም አቀፍ የበጎነት ቀን!
ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም
#InternationalDayOfCharity
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia | 12 998 |
| 7 | በ2019 በጀት ዓመት ኩባንያችን ሰፊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኢንቨስትመንቶችን በማድረግ የሀገራችንን ዕድገት ለማፋጠንና የዜጎችን ሕይወት ለመቀየር በርካታ ቁልፍ ስትራቴጂያዊ ሥራዎችን ለማከናወን አቅዷል፡፡
በዚህም መሠረት በበጀት ዓመቱ ከ644,000 በላይ ለሚሆኑ የምህዳር አጋሮቻችን (ወኪሎች፣ አቅራቢዎችና የVAS አጋሮች) የገቢ ምንጭ የሚፈጥር ሲሆን፤ ከ49,200 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞችም አስተማማኝ የሥራ ዕድል እንዲቀጥል ያደርጋል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል የተፈጠሩ 2.4 ሚሊዮን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የገቢ ምንጮችን በማስቀጠል፣ ተጨማሪ 163,375 አዳዲስ ቀጥተኛ የሥራ እና የገቢ ዕድሎችን ለመፍጠር ግብ ይዟል።
ኩባንያችን አገራዊ የፋይናንስ አቅምን ለማጠናከር 43.1 ቢሊዮን ብር የትርፍ ክፍፍል (Dividend) ያለመ ሲሆን፤ 83.8 ቢሊዮን ብር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ የግብር ገቢ ለሀገራችን ለማበርከት አቅዷል።
በማኅበረሰብ ድጋፍና በጎ አድራጎት ረገድም 8.1 ቢሊዮን ብር ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ እንዲሁም ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክት ድጋፎችን ሳይጨምር 533 ሚሊዮን ብር ለተለያዩ የማኅበራዊ ኃላፊነት (CSR) ፕሮጀክቶች ያውላል።
በዘላቂ አረንጓዴ ኦፕሬሽን ልማት ረገድም በአረንጓዴ ኃይል አጠቃቀም፣ በካርበን ቅነሳ፣ በፋይናንስ አካታችነት እና በሳይበር ደኅንነት ላይ ትኩረት በማድረግ አገራዊ ተልዕኮውን በቁርጠኝነት ለመወጣት ይሠራል።
ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3UvAR5j
#Ethiotelecom #telebirr #NextHorizon #NationalDevelopment #CSR #ESG #GSMA #ITU | 11 787 |
| 8 | በ2019 በጀት ዓመት ኩባንያችን ሰፊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኢንቨስትመንቶችን በማድረግ የሀገራችንን ዕድገት ለማፋጠንና የዜጎችን ሕይወት ለመቀየር በርካታ ቁልፍ ስትራቴጂያዊ ሥራዎችን ለማከናወን አቅዷል፡፡
በዚህም መሠረት በበጀት ዓመቱ ከ644,000 በላይ ለሚሆኑ የምህዳር አጋሮቻችን (ወኪሎች፣ አቅራቢዎችና የVAS አጋሮች) የገቢ ምንጭ የሚፈጥር ሲሆን፤ ከ49,200 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞችም አስተማማኝ የሥራ ዕድል እንዲቀጥል ያደርጋል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል የተፈጠሩ 2.4 ሚሊዮን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የገቢ ምንጮችን በማስቀጠል፣ ተጨማሪ 163,375 አዳዲስ ቀጥተኛ የሥራ እና የገቢ ዕድሎችን ለመፍጠር ግብ ይዟል።
ኩባንያችን አገራዊ የፋይናንስ አቅምን ለማጠናከር 43.1 ቢሊዮን ብር የትርፍ ክፍፍል (Dividend) ያለመ ሲሆን፤ 83.8 ቢሊዮን ብር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ የግብር ገቢ ለሀገራችን ለማበርከት አቅዷል።
በማኅበረሰብ ድጋፍና በጎ አድራጎት ረገድም 8.1 ቢሊዮን ብር ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ እንዲሁም ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክት ድጋፎችን ሳይጨምር 533 ሚሊዮን ብር ለተለያዩ የማኅበራዊ ኃላፊነት (CSR) ፕሮጀክቶች ያውላል።
በዘላቂ አረንጓዴ ኦፕሬሽን ልማት ረገድም በአረንጓዴ ኃይል አጠቃቀም፣ በካርበን ቅነሳ፣ በፋይናንስ አካታችነት እና በሳይበር ደኅንነት ላይ ትኩረት በማድረግ አገራዊ ተልዕኮውን በቁርጠኝነት ለመወጣት ይሠራል።
ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3UvAR5j
#Ethiotelecom #telebirr #NextHorizon #NationalDevelopment #CSR #ESG #GSMA #ITU | 1 |
| 9 | ኩባንያችን በ2019 በጀት ዓመት የሞባይል ኔትወርክ ጣቢያዎችን ወደ 12,238 እና የ4ጂ ሽፋንን ወደ 95% ለማድረስ አቅዷል
ኩባንያችን በ“ቀጣዩ አድማስ” ስትራቴጂ ሁለተኛ ዓመት የአገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራ ሲሆን፤ የሞባይል ኔትወርክ ጣቢያዎችን ብዛት ከ10,613 ወደ 12,238 ለማድረስ አቅዷል፡፡
በአዲሱ 2019 በጀት ዓመት 1,625 ተጨማሪ የሞባይል ጣቢያዎች (605ቱ በገጠር አካባቢዎች የሚገነቡ) ለመገንባት የታቀደ ሲሆን፤ ይህም የደንበኞች የማስተናገድ አቅም ከ115.1 ሚሊዮን ወደ 135.7 ሚሊዮን ከፍ እንዲል ያደርጋል።
በበጀት ዓመቱ 5,417 አዳዲስ የ4ጂ ጣቢያዎችን በመገንባት የ4ጂ ተጠቃሚ ከተሞችን ቁጥር ከ1,200 ወደ 1,500 ከፍ ለማድረግ የታቀደ ሲሆን፤ ይህም የሕዝብ ቁጥር ሽፋን 95% እንዲደርስ ያስችላልል።
በተጨማሪም የ5ጂ ጣቢያዎችን ቁጥር ከ340 ወደ 648 በማሳደግ፣ አገልግሎቱ የሚዳረስባቸውን ከተሞች ቁጥር ወደ 73 ለማድረስ ታቅዷል።
በሌላ በኩል የመደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎትን ለማሻሻል ከ150 ሺህ በላይ ደንበኞች መስመር ከኮፐር ወደ ፋይበር የመቀየር ሥራ የሚከናወን ይሆናል፡፡
እነዚህ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች ለሀገራችን የዲጂታል ሽግግር ጠንካራ መሠረትና አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥሩ ናቸው።
ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3UvAR5j | 15 828 |
| 10 | በበጀት ዓመቱ ከ17.18 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የቴሌብር ደንበኞች እስከ 35.04 ቢሊዮን ብር የአነስተኛ ብድር አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷል
ኩባንያችን በ“ቀጣዩ አድማስ” ስትራቴጂ ሁለተኛ ዓመት በቴሌብር አማካኝነት የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የዲጂታል ኢኮኖሚ ሥነ-ምህዳሩን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን ያከናውናል።
በአዲሱ 2019 በጀት ዓመት የቴሌብር ደንበኞች ቁጥርን በ11.7 በመቶ በማሳደግ 67.69 ሚሊዮን ለማድረስ አቅዷል።
የቴሌብር አጠቃላይ የግብይት ብዛት (Transaction Volume) 4.99 ቢሊዮን ለማድረስ የታቀደ ሲሆን፣ ይህም 7.4 ትሪሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብ ፍሰት በዲጂታል ሥርዓቱ ውስጥ ለማንቀሳቀስ ያስችላል።
የአነስተኛ ብድር አገልግሎት ከ17.18 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች 35.04 ቢሊዮን ብር ለመስጠት ታቅዷል። ይህም ለግለሰቦችና ለአነስተኛ ንግዶች የዲጂታል ብድር አገልግሎቶች ተደራሽነት መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
የዲጂታል ቁጠባ መጠን ወደ 29.39 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ የታቀደ ሲሆን፤ ይህም ለ3.88 ሚሊዮን ደንበኞች የፋይናንስ ደኅንነትን የሚፈጥርና የቁጠባ ባህልን የሚያሳድግ ነው።
ቴሌብር የሀገራችንን ዲጂታል ፋይናንስ አካታችነት እና የዲጂታል ሥነ-ምህዳር አንቀሳቃሽ ሞተር በመሆን የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ማፋጠኑን አጠናክሮ ይቀጥላል።
ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3UvAR5j
#Ethiotelecom #telebirr #NextHorizon #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF | 17 331 |
| 11 | ኩባንያችን የ“ቀጣዩ አድማስ” ስትራቴጂ ሁለተኛ ዓመት የቢዝነስ እቅዱን ለህዝብ ይፋ አደረገ
ኩባንያችን በ“ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂው ሁለተኛ ዓመት ማለትም በ2019 በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚያደርገውን ዓመታዊ የቢዝነስ እቅዱን ይፋ አድርጓል።
በ2019 በጀት ዓመቱ የ4G የህዝብ ሽፋንን ወደ 95% ለማድረስ፣ የ4G አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞችን ቁጥር ከ1,200 ወደ 1,500 ከፍ ለማድረግ እንዲሁም የ5G አገልግሎት የሚሰጡ ከተሞችን ቁጥር ከ33 ወደ 73 ለማድረስ ታቅዷል።
በአጠቃላይ በጀት ዓመቱ የደንበኞችን ቁጥር 96.2 ሚሊዮን እንዲሁም የቴሌብር ተጠቃሚ ደንበኞችን ብዛት 67.69 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዷል።
በበጀት ዓመቱ 312 አዳዲስና የተሻሻሉ ምርትና አገልግሎቶችን ለግለሰብ እና ድርጅት ደንበኞች ወደ ገበያ በማቅረብ፣ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢን ወደ 295 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል።
ኩባንያችን በስትራቴጂው የመጀመሪያ ዓመት በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ፤ በተለይም ከቁጥር ዕድገት ባሻገር ለሀገራችን ሁለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለዜጎች ትርጉም ያለው የአኗኗር ዘይቤ መሻሻል የላቀ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3UvAR5j
#Ethiotelecom #telebirr #NextHorizon #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries | 17 166 |
| 12 | “ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂ ሁለተኛ ዓመት ዓመታዊ የቢዝነስ ዕቅድ መርሐ ግብር!
NEXT HORIZON - DIGITAL & BEYOND STRATEGY 2028
YEAR II 2019 EFY (2026/27) ANNUAL BUSINESS PLAN
#Ethiotelecom
#NextHorizon #BusinessPlan
#telebirr #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia | 16 523 |
| 13 | ከባሕርማዶ በቴሌብር ሬሚት እንዲሁም በአጋሮቻችን ከወዳጅ ዘመድ የተላከልዎን ዓለም አቀፍ ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ ምቾትና ቅልጥፍና ሳይጓድልብዎ 9% ተጨማሪ ስጦታ ያገኛሉ፡፡
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
*127# ደውለን ወይም ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ስንቀበል እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን | 20 830 |
| 14 | ለጥሪ መለያ አገልግሎት በቀላሉ እንዴት መመዝገብ እንችላለን?
#callSignature
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia | 20 821 |
| 15 | 🌼📞 ከባሕር ማዶ የዘመድ ጥየቃዎን በኢትዮ ኮል!!
ማንኛውንም የሞባይል ወይም የመደበኛ ስልክ ላይ በታላቅ ቅናሽ መደወል ያስችላል።
🇨🇦 Canada | 🇩🇪 Germany | 🇮🇳 India | 🇮🇱 Israel | 🇮🇹 Italy | 🇰🇪 Kenya | 🇷🇼 Rwanda | 🇸🇦 Saudi Arabia | 🇸🇴 Somalia | 🇿🇦 South Africa | 🇬🇧 United Kingdom | 🇺🇸 USA | 🇾🇪 Yemen
📲መተግበሪያውን ያውርዱ: https://onelink.to/ethiocall
ወደ አገርቤት በቅናሽ ይደውሉ፤ በገዙት ጥቅል ደዋዮች ሳይቆጥርባቸው በነፃ ይቀበሉ!
#ethioCall
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia | 21 174 |
| 16 | 🌟🌍 በዓለም አቀፍ የድምፅ ጥቅሎቻችን በቀጥታ ይገናኙ!!
እስከ 51% ቅናሽ በተደረገባቸው በዓለም አቀፍ የድምፅ ጥቅሎቻችን በርቀት ሳይገደቡ ባሕር ማዶ ከሚገኙ ወዳጆችዎና የሥራ አጋሮችዎ ጋር በቀጥታ ይገናኙ!
❇️ በዕለታዊ
❇️ ሳምንታዊ እና
❇️ ወርኃዊ አማራጮች!
በ*999#፣ በማይ ኢትዮቴል፣ እንዲሁም በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp መግዛት ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ 👉 https://bit.ly/4sqxw42
#InternationalPackage
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia | 19 730 |
| 17 | 🌼 አዲሱን ዓመት ከሰራተኞችዎና ከደንበኞችዎ ጋር በኢትዮ ቴሌኮም የአደይ አበባ ኢንተርፕራይዝ የበዓል ፓኬጅ ያክብሩ።
🎁 ለድርጅቶች ስጦታና ለሰራተኞች እውቅና መስጫ ተደርጎ የተዘጋጀው እያንዳንዱ ፕላን ቅናሽ የተደረገባቸውን የድምፅ፣ የዳታና የአጭር መልእክት (SMS) ጥቅሎች እንዲሁም የ25% ተጨማሪ ስጦታ ያካትታል።
📍 በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የድርጅት አገልግሎት ማዕከል ጎራ ይበሉ ወይም
📥 Corporate.Enterprise@ethiotelecom.et ያግኙን!
ለተጨማሪ መረጃ: bit.ly/4gRFD5E
#EnterpriseSolutions
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia | 18 659 |
| 18 | ዘመን ገበያ 2019 አዲስ ዓመት ኤክስፖ!
የዘመን ገበያ ኤክስፖ ትኬትዎን በቴሌብር ይቁረጡ፤ በየቀኑ በሚወጡ ዕጣዎች ፓወር ባንክ፣ ኤርፖድ፣ ኢንተርኔት ፓኬጅ እና ሌሎች በርካታ ሽልማቶችን ያሸንፉ!
በተጨማሪም ትኬት ሲቆርጡም ሆነ በኤክስፖው ግብይት ሲፈጽሙ በቀን እስከ 3 ጊዜ የእድለኛ ዕጣ እድሎችን ያገኛሉ!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ስንሸልም እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን | 21 671 |
| 19 | 📲 የሞባይል ስልክ ቁጥር በራስዎ ምርጫ!
✨ በጊዜና ቦታ ሳይገደቡ እጅዎ ላይ ባለው ስማርት ስልክ የወደዱትን የሞባይል ስልክ ቁጥር በቀላሉ መርጠው ከሚቀርብዎት የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመውሰድ ራስዎ በመረጡት ቁጥር መጠቀም ይችላሉ!
👉 ቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/tele-sim ላይ ወይም በ https://telesim.ethiotelecom.et/ ያገኙታል!
እገዛ ካሻዎት ኢሜይል ያድርጉልን: Onlinesales@ethiotelecom.et
#teleSIM
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia | 20 456 |
| 20 | ለጥቅሉ ይከፍላሉ፤ ከነስልኩ ይወስዳሉ!
የማይረሱ ትዝታዎችን በዘኔክሰስ ስልኮች ይፍጠሩ!
znexus L131- በ3,189 ብር ቅድሚያ ክፍያ: በወር 50 ብር፤ 4ጊባ ዳታ፤ 80 ደቂቃ ድምፅ፤ 50 ብዛት መልዕክት - ለ12 ወራት!
znexus L2028- በ3,395 ብር ቅድሚያ ክፍያ: በወር 70 ብር፤ 5ጊባ ዳታ፤ 50 ደቂቃ ድምፅ፤ 20 ብዛት መልዕክት - ለ12 ወራት!
ቀድመው ይምጡ - ያሻዎን ይምረጡ!
#ትዝታዎችን_በዘኔክሰስ_ስልኮች_ይፍጠሩ
#znexus #ዘኔክሰስ #Ethiotelecom #telebirr #ለጥቅሉ_ይከፍላሉ_ከነስልኩ_ይወስዳሉ | 21 966 |
