TIKVAH-ETHIOPIA
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
Ko'proq ko'rsatish1 530 453
Obunachilar
+29324 soatlar
+2 0357 kunlar
+2 19030 kunlar
Ma'lumot yuklanmoqda...
O'xshash kanallar
Taglar buluti
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Kirish va chiqish esdaliklari
---
---
---
---
---
---
Obunachilarni jalb qilish
June '25
June '25
+5 375
1 547
146 kanaldaMay '25
+7 124
3 603
327 kanalda Get PRO
April '25
+3 904
3 049
315 kanalda Get PRO
March '25
+7 492
2 353
221 kanalda Get PRO
February '25
+3 535
1 999
237 kanalda Get PRO
January '25
+9 238
2 901
288 kanalda Get PRO
December '24
+7 427
2 834
277 kanalda Get PRO
November '24
+17 973
2 344
207 kanalda Get PRO
October '24
+47 299
3 426
462 kanalda Get PRO
September '24
+48 401
3 022
469 kanalda Get PRO
August '24
+41 009
3 079
323 kanalda Get PRO
July '24
+40 425
2 479
334 kanalda Get PRO
June '24
+23 811
1 315
172 kanalda Get PRO
May '24
+18 463
2 895
317 kanalda Get PRO
April '24
+26 173
3 356
376 kanalda Get PRO
March '24
+29 994
2 294
255 kanalda Get PRO
February '24
+11 084
1 712
215 kanalda Get PRO
January '24
+7 577
1 901
245 kanalda Get PRO
December '23
+6 532
1 232
176 kanalda Get PRO
November '23
+5 216
1 289
295 kanalda Get PRO
October '23
+55 878
1 150
256 kanalda Get PRO
September '23
+5 756
@0
0 kanalda Get PRO
August '23
+7 223
@0
0 kanalda Get PRO
July '23
+16 059
@0
0 kanalda Get PRO
June '23
+5 249
@0
0 kanalda Get PRO
May '23
+5 980
@0
0 kanalda Get PRO
April '23
+6 824
@0
0 kanalda Get PRO
March '23
+3 206
@0
0 kanalda Get PRO
February '23
+16 807
@0
0 kanalda Get PRO
January '23
+34 420
@0
0 kanalda Get PRO
December '22
+4 616
@0
0 kanalda Get PRO
November '22
+19 825
@0
0 kanalda Get PRO
October '22
+8 681
@0
0 kanalda Get PRO
September '22
+10 002
@0
0 kanalda Get PRO
August '22
+11 933
@0
0 kanalda Get PRO
July '22
+13 816
@0
0 kanalda Get PRO
June '22
+3 415
@0
0 kanalda Get PRO
May '22
+3 368
@0
0 kanalda Get PRO
April '22
+6 840
@0
0 kanalda Get PRO
March '22
+20 879
@0
0 kanalda Get PRO
February '22
+4 094
@0
0 kanalda Get PRO
January '22
+2 335
@0
0 kanalda Get PRO
December '21
+8 033
@0
0 kanalda Get PRO
November '21
+18 586
@0
0 kanalda Get PRO
October '21
+17 499
@0
0 kanalda Get PRO
September '21
+9 945
@0
0 kanalda Get PRO
August '21
+16 184
@0
0 kanalda Get PRO
July '21
+20 920
@0
0 kanalda Get PRO
June '21
+17 590
@0
0 kanalda Get PRO
May '21
+16 302
@0
0 kanalda Get PRO
April '21
+10 933
@0
0 kanalda Get PRO
March '21
+19 995
@0
0 kanalda Get PRO
February '21
+3 343
@0
0 kanalda Get PRO
January '21
+8 547
@0
0 kanalda Get PRO
December '20
+1 156 877
@0
0 kanaldaSana | Obunachilarni jalb qilish | Esdaliklar | Kanallar | |
20 June | +190 | 27 | ||
19 June | +330 | 80 | ||
18 June | +227 | 74 | ||
17 June | +324 | 100 | ||
16 June | +394 | 27 | ||
15 June | +398 | 81 | ||
14 June | +319 | 89 | ||
13 June | +491 | 56 | ||
12 June | +351 | 92 | ||
11 June | +354 | 69 | ||
10 June | +119 | 85 | ||
09 June | +114 | 31 | ||
08 June | +331 | 122 | ||
07 June | +354 | 74 | ||
06 June | +132 | 95 | ||
05 June | +330 | 103 | ||
04 June | +295 | 75 | ||
03 June | +166 | 62 | ||
02 June | +44 | 84 | ||
01 June | +112 | 121 |
Kanal postlari
#ETHIOPIA #USA
ዛሬ ጥዋት ላይ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ ማሪን ኮርፕስ ጄኔራል እና አፍሪኮም አዛዥ ከሆኑት ጄነራል ማይክል ላንግሌይ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል።
ውይይቱ የጋራ ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንዳተኮረ አመልክተዋል።
አሜሪካም ጄነራሏ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት ማድረጉን አሳውቃለች።
ውይይቱ በአፍሪካ ቀንድ የአልሸባብ እና የአይኤስ የሽብር ስጋትን መከላከል ላይ ያተኮረ እንደነበረም ጠቁማለች።
በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ (AFRICOM) ጀነራል ማይክል ላንግሌይ ኢትዮጵያን እንደጎበኙ አሜሪካ አሳውቃለች።
በዚህም ወቅት ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ጋር መምከራቸውን ገልጻለች።
ምክክራቸው ፦
- ቀጠናዊ ሰላምና ደህንነት፣
- በቀጠናው ላይ ያሉ ችግሮችን በጋራ የመፍታት ጥረት፣
- በሱማሊያ ያለውን ሽብርተኝነት መዋጋት ላይ፣
- በአፍሪካ ቀንድ የረዥም ጊዜ መረጋጋትን ስለ መደገፍ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ አሜሪካ አሳውቃለች።
የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ምን አለ ?
ሀገር መከላከያ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ (አፍሪኮም) ጀነራል ሚካሄል ላንግሌይ የተመራ ልዑክን ተቀብለው እንዳነጋገሩ ገልጿል።
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ " አሜሪካና ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመት በላይ ግንኙነት አላቸው " ያሉ ሲሆን " ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በመከላከያ ዘርፉ በቀጣይም በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል " ሲሉ ገልፀዋል።
በውይይቱ በቀጠናው ባለው ሁኔታ የጋራ መግባባት የተያዘበትና በተለይም በቀይ ባህር ፣ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በሚታዩ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን አመልክተዋል።
የአፍሪኮም አዛዥ ጀነራል ሚካኤል ላንግለይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ከፍተኛ ሚና ያላት ሀገር መሆኗን እንደተናገሩ መከላከያ አሳውቋል።
በቀጣይ በወታደራዊና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን እንደተናገሩም አክሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
Photo ፦ PM Office & US Embassy
@tikvahethiopia
96 780340
2 | " የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል ! "
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የ8 ዓመቷ ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በመፈጸምና በመግደል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የግብረስጋ ድፍረት ወእና ግድያ ወንጀል መዝገብ ተከፍቶባቸዉ በሰውና በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ የቅጣት ዉሳኔ እንደተላለፈባቸው የሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰረድተዋል።
ዳዊት ሻንቆ እና ታምራት ኦሳ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በሶዶ ከተማ ' ፋና ዎንባ ' ተብሎ ከሚጠራዉ አከባቢ ሰኔ 16/ 2016 ዓ/ም የ8 ዓመት ልጅን ከቤት አታለው ወደ ጫካ በመውሰድ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ከፈጸሙ በኋላ ወዲያዉኑ ሕይወቷ ያልፋል።
በዚህም ጊዜ እራሷን ያጠፋች ለማስመሰል በአከባቢዉ በሚገኝ አንድ ኦና ቤት በማስገባት አስክሬኗን በማንጠልጠል ከአከባቢው መሠወራቸው በፖሊስ ምርመራ መረጋገጡን አዛዡ ገልፀዋል።
የወንጀል ድርጊቱ ጥቆማ የደረሰዉ የሶዶ ከተማ ፖሊስ ግለሰቦቹን በጠንካራ ክትትል ይይዛቸዋል።
የምርመራ መዝገብ በማደራጀት ለዐቃቤ ሕግ ያቀርባል።
ጉዳያን የተከታተለው የወላይታ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ግለሰቦቹን በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ም/ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahEthiopia | 113 839 |
3 | #Tigray
" የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " - አቶ አማኒኤል አሰፋ
በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የተገኙበት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል።
ዛሬ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም ለሦስተኛ ቀን የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ውሳኔ መሰረት የመንግስት ሠራተኞች ስራቸውን በማቆም የታደሙበት ነው።
በሰልፉ ማጠቃለያ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቁ በርካታ መልእክቶች ተደምጠውበታል።
በሰልፉ መልእክት ያስተላለፉት የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አማኒኤል አሰፋ " የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ብለዋል።
" ከተፈረመ ሦስት ዓመት ሊሞላ ወራት የቀሩት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተኩስ ከማቆም በዘለለ የተፈናቃዮች ደህንነት ማረጋገጥ አቅቶታል " ሲሉ ተደምጠዋል።
" የትግራይ ህዝብ ሉአላዊ ግዛቱ ተቀምቶ ፣ ከቄዩ ተፈናቅሎ ተሰዶ በማያቋርጥ መከራ ተዘፍቆ ይገኛል " ያሉት ምክትል ፕሬዜዳንቱ " የፌደራል መንግስት በጦርነት ያላሳካው ድል በፕሪቶሪያ ውል ስምምነት ስም የተከፋፈለች ትግራይ እንድትኖር የዲሞግራፊ ለውጥ ለመቀየር እየተጠቀመበት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
" የፌደራል መንግስት ለሰላም ዋጋ ሰጥቶ እንዲሰራ ደጋሜ ጥሪ እናቀርባለን " ያሉት አቶ አማኒኤል " የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች የኩርድ ህዝቦች ዕጣ ፈንታ እንዲደርሳቸው የሚፈቅድ ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር መቆም አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።
ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ የሦስት ቀናት ማጠቃለያ ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት
- የሁሉም የሃይማኖት ተቋማት አመራርና ምእመናንና ምእመናት
- የሚድያ ባለሙያዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች
- ተማሪዎች
- መምህራንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸው ተነግሯል።
የፌዴራል መንግሥት ሁሉም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ፅና ፍላጎ እንዳለው በተደጋጋሚ መግለጹ አይዘነጋም።
የቀድሞ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳም አሁን ላይ በትግራይ ትርምስ እንዲፈጠር እየሰራ ያለው የህወሓት አንጃ ተፈናቃዮችን ለፖለቲካ ፍጆታ በመጠቀም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዳይመለሱ እየሰራ መሆኑን አስገንዝበው ነበር።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትላንት በስቲያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት የትግራይ ተፈናቃዮችን ጉዳይ አንስተው ነበር።
" የተፈናቀሉ ሰዎች መመለስ በሚመለከት 100% ዝግጁ ነን እኛ 100% ፤ ነበርን ነን ፤ ራያ እኮ መልሰናል ፤ ራያ ተመልሰዋል የተፈናቀሉ ሰዎች ወልቃይትም እንደዛ አይነት ፍላጎት ነው ያለን። ከጊዜያዊ መንግሥቱ ጋር እየተነጋገርን ነው በእኛ በኩል እነኚያ ዜጎች ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ሳይሆኑ ቦታቸው ቢመለሱ ከማንም በላይ ኢትዮጵያ ታተርፋለች " ብለዋል።
" በእኛ በኩል አንዴ አይደለም 10 ጊዜ እቅድ ያወጣነው ፤ የትግራይ ጉዳይ ብዙ የማይገደን ፣ የማያሳስበን አይመሳላችሁ " ሲሉ ገልጸዋል።
" ያስጨነቀንን ጉዳይ በግልጽ እንድታውቁት ግን ትንሽ ዘመን ተቀይሯል የዛሬ 4 አመት 5 አመት የነበረን የውጊያ አቅም የነበረን ቴክኖሎጂ እና ዛሬ ትንሽ ይለያያል። በተቻለ መጠን maximum ውጊያ ብናስቀር ይሻላል ለምን ? እንደምታውቁት በባለፈው ውጊያ ያኔም ተናግሪያለሁ ከትግራይ ወጣቶች ከትግራይ እናቶች በላይ የተጎዳ ሰው የለም ፤ የሚያስገድሉ ሰዎች ይፎክራሉ አስገዳዮች ይፎክራሉ ሟቾች ግን ጉዳዩን ሳያውቁ ይጠፋሉ ያ እንዳይፈጠር ነው maximum ትዕግስት የምናደርገው " ብለዋል።
" ትግራይ ውስጥ ሊመጣ የሚገባው ልማት ፤ ሊሰራ የሚገባው ስራ በበቂ ተሰርቷል ብለን አናምንም እንጂ የሚደረጉ ሙከራዎች unconstitutional ልምምዶች እንዳሉ ስለማናውቅ አይደለም በደምብ ነው የምናየው " ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia | 113 594 |
4 | በነፃ ይመዝገቡ !
Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo
ከመስመር እስከ ከባድ መሳሪያ፣ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ እስከ የስልጣን መፍትሄዎች፣ ለየትኛውም የኮንስትራክሽን እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችዎ የሚፈልጉትን ሁሉ በአንድ ቦታ ያግኙ። Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo የሚያስተናግዱት እዚህ ነው።ከየትኛውም ዓለም አቀፍ አገር የመጡ 180+ ባለስልጣን ብራንዶችን በአንድ ጣቢያ ይያዙ፤ ፕሮጀክቶችዎን ለማንቃት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችንና መፍትሄዎችን ያግኙ።አሁኑኑ በነፃ ይመዝገቡ:👉 https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia📅 ሰኔ 19–21፣ 2017 ዓ.ም (26–28 June 2025)📍 ሚሊኒየም አዳራሽ፣ አዲስ አበባ | 107 331 |
5 | #ExitExamResult
“ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” - ኤባ መጂና (ዶ/ር)
በዘንድሮው መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።
የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ መጂና (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽም “ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ስንት ተማሪዎች አለፉ ? ስንት ተማሪዎች ወደቁ ? የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ አናላይሲሱ እየተሰራ እንደሆነ፣ ነገ ማብራሪያ እንደሚሰጡን መሪ ሥራ አስፈጻሚው የገለጹ ሲሆን፣ ነገር ግን ውጤቱ ስለተለቀቀ ተማሪዎች ማየት እንደሚችሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ከዚህ ቀደም ውጤት በሚለቀቅበት በተለመደው ድረ ገጽ ውጤት ማየት እንደሚቻል መሆኑን ጠቁመዋል። “ ውጤት የሚታየው ያው ከዚህ በፊት በነበረው ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት በበኩሉ፣ ተማሪዎች እያዩ መሆኑን፣ ማለፊያው 50% መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል። ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ መረጃው እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።
https://result.ethernet.edu.et
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia | 271 786 |
6 | “ ካሜራ ይዛ አንገቷን በመስኮት አውጥታ ነበር ”- የኮንታ ዞን ጸጥታ መምሪያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንታ ዞን ዛሬ በደረሰ የመኪና አደጋ የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን የካሜራ ባለሙያ ሕይወት መቀጠፉን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
አንድ ዞኑ ጸጥታ መምሪያ አካል በሰጡን ቃል፣ “ አንዲት ካሜራ ማን ለመግስታዊ የሥራ ጉዳይ ከዞን ወደ ወረዳ እየሄደች በአጋጣሚ ቀረጻ ላይ እያለች መኪና ተገልብጦ ነው የሞተችው ” ብለዋል።
የአደጋው ምክንያት ምን እንደሆነና ከሟቿ ባሻገር ምን ያህል ሰዎች እንደተጎዱ ሲጠየቁ፣ “ የቴክኒክ ችግር ይመስለኛል። የመንገድ፣ የቦታ ችግር አይደለም። የቴክኒክ ችግር ሳይሆን አይቀርም የሚል ስጋት አለ። ሌላ ሰው ብዙ የተጎዳ የለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ካሜራ ይዛ አንገቷን በመስኮት አውጥታ ነበር ” ብለው፣ አደጋው ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ እንደደረሰም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ “ዛሬ ረፋድ እህታችን ወ/ሮ ቃልኪዳን መለሰ የኮንታ ዞን የመንግስት ኮሚኒዩኬሽን የሚዲያ ባለሙያ ለመንግስት ሥራ በሚታደርገው ጉዞ በደረሳት ድንገተኛ የመኪና እደጋ ሕይወቷ አልፏል ” ሲሉ አስታውቀዋል።
“ አደጋው ሲያጋጥም በቅርብ ርቀት ለነበርን ሐዘኑ በጣም ጥልቅ ነው። ፈጣሪ ነፍሷን በአፀደ ገነት ያኑርልን ” ብለው ለሟች ቤተሰብ መጽናናትን ተመኝተዋል። “ በአደጋው የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የሥራ ባልደርቦቻችንም ፈጣሪ ፈጥንነው እንዲያገግሙ ብርታቱን ይስጣችው ”ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia | 241 337 |
7 | " ከማረሚያ ወጥተዉ ወደ ቤታቸዉ ገብተዋል " - ቤተሰቦች
የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እና አብሯቸዉ ታስረዉ የነበሩት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ታርኩ ታመነ ከማረሚያ ተለቀዉ ወደ ቤታቸው መግባታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የቆዩትና ከሁለት ወራት በፊትም የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለት የክስ 13 ዓመት ፅኑ እስራት ዉሳኔ አስተላልፎባቸዉ የነበሩት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ይግባኝ ጠይቀዉ ዛሬ በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነፃ መሰናበታቸውን ተከትሎ ከሀዋሳ ከተማ ማረሚያ ቤት ወጥተው ቤተሰቦቻቸውን ተቀላቅለዋል።
ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ከማረሚያ ቤት ወጥተዉ ወደ ቤታቸዉ ሲሄዱ በርከት ሰዎች በሞተር ሳይክሎችና በመኪና አጅቧቸዉ ደስታቸዉን ሲገልፁ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia | 229 285 |
8 | "ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነው የጥላቻ ንግግር የተሰራጨው በታዋቂ ሰዎች/በፐብሊክ ፊገርስ መሆኑን ጥናቱ ያረጋግጣል”- ጥናት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት የሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ስለመድረሱ በጥናት ማረጋገጡን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
"በሀገራችን የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር አሳሳቢ ደርጃ ላይ መድረሱ በጥናት ተረጋግጧል” ሲልም ተናግሯል።
በጥናቱ ግኝት መሠረት፣ “አብዛኛው የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ የተሰራጨው ባብዛኛው በጽሑፍ እና በተንቀሳቃሽ ምስል፤ በአብዛኛው የተሰራጨውም በፌስቡክ፣ ቲክቲቶክና በቴሌግራም እንደሆነ ጥናቱ ያመለክታል” ብሏል።
ባለስልጣኑ በመግለጫው፣ ተጠቃሚዎቹ የተሳሳተ መረጃ ሲያገኙ ሪፖርት እንደሚያደርጉና ለማን ሪፖርት እንደሚደረግ እንደማያውቁ ተናግሯል።
ይህን ሁሉ ያሉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ታምራት ደጀኔ፣ “ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆኑ የጥላቻ ንግግር የተሰራጨው በታዋቂ ሰዎች/ፐብሊክ ፊገርስ በሚባሉት መሆኑን ጥናቱ ያረጋግጣል” ብለዋል።
በግኝቱ መሠረት፣ “የጥላቻ ንግግር ያነጣጠረው የፖለቲካ አመለካካት ላይ ነው፡፡ ቀሪዎቹ በብሔርና ሃይማኖት ናቸው፤ (ብሔር 15%፣ ሃይማት 6%”) ብለው፣ “ሀሰተኛ መረጃው የተሰራጨባቸው ዋና ዋና መንገዶች በግኝቱ መሠረት የሐሰት አውድ በመጠቀም፣ በተሳሳቱ መረጃዎች (በእንዝላልነት)፣ አሳሳች በሆኑ ይዘቶች..." መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ለማሰራጨት የተፈለገው፣ “ማሕበራዊ አለመረጋጋት እንዲፈጠር፣ በማህበረሰብ መካከል ግጭት የመቀስቀስ አላማ፤ የመግስት ተቋማትና መንግስት ሥራቸውን ተረግተው እንዳያከናውኑ ለማድረግና የማስተባበል፣ የግለሰብና የቡድኖችን ሥም ለማጠልሸት..” መሆኑን የጥናቱ ዳሰሳ እንደሚያስረዳ ገልጸዋል።
"ዜጎችን ለአመጽና ለጥቃት እንዲነሳሱ መቀስቀም 15% ይዟል፣ የማህበረሰቡን አብሮ የመኖር እሴት በመሸርሸርም ወደ 11% ታርጌት እንደተደረገ መረጃው ያመለክታል" ነው ያሉት።
“እንደ ኢትዮጵያ ቴሌ ኮሚዩኒኬሽን መረጃ በአገራችን ከ44 ሚሊዮን በላይ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ይገኛሉ፡፡ ለብቻው የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ደግሞ ወደ 4 ሚሊዮን ይጠጋሉ፡፡ ይህ ቀላል ቁጥር አይደለም” ሲሉም ተናግረዋል።
ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አንጻር፣ “የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም በአንጀንዳ ሴቲንግ ከፍተኛ ሚና አላቸው፣ ኮንተንት እስከመወሰን ራሱ የሚደርስ አቅም እንዳላቻው”ም የጥናቱ ግኝት እንደሚያስረዳ አብራርተዋል።
የጥናቱ መረጃ ምንጭ በአምስት ዋና ዋና ማለትም ሜታ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክና ቲዊተር ማህበራዊ ሚዲያዎችን መሠረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም፣ ከ500 ሺሕ ባላይ ተከታዮች ያላቸው ተጸዕኖ ፈጣሪ፣ ግለሰቦችን መሠረት ያደረገ እንደሆነ እና ወደ 1700 ከሚሆኑ ተጽዕኖ ፈታጣሪ ግለሰቦችም በጉዳዩ ዙሪያ የህዝብ አስተያየት እንደተሰበሰበ ገልጸው፣ “ከ2000 በላይ ይዘቶች በባለሙያዎቻችን ሞኒተር ተደርገዋል” ተብሏል።
የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ለሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ስርጭት ምክንያት እንደሆነ፣ በዚህም ታዋቂ ሰዎች 56%፣ መገናኛ ብዙኃን 26%፣ ግለሰቦች 17% አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ተነግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia | 214 466 |
9 | የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!
SAMSUNG S24 ULTRA !
ዛሬ የቶምቦላ ሎተሪ ለቆረጠ 1 እድለኛ SAMSUNG S24 ULTRA ስልክ ይሸለማል!
ቶምቦላው ባለ 3 እና 2 መኝታቤት አፓርትመንት ፣ ID6 እና BYD SUV መኪና ሽልማቶችን ይዞ መጥቷል
ቶምቦላ ሎተሪን በ ethiolottery.et እና በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ ይግዙ ፡፡
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት! | 217 278 |
10 | የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በነፃ ተሰናበቱ።
የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነፃ አሰናበታቸው።
13 ዓመት ተፈርዶባቸዉ በማረሚያ ቤት የነበሩት የቀድሞው ከንቲባ በዛሬዉ ዕለት በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነበራቸው ችሎት የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰነባቸው የፍርድ ዉሳኔ በነፃ መሰናበታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተነግረዋል።
የቀድሞው ከንቲባ በአጠቃላይ ከቀረበባቸዉ 7 የክስ መዝገቦች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው 2 ክሶች በነፃ ተሰናብተው የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ3 ክሶች ነፃ በ2 ክሶች ደግሞ 13 ዓመት እስራት ፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
ከፍርዱ በኃላ ባለቤታቸው ወ/ሮ ዜናዬ ተሰማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " ፀጋዬ ቱኬ የፖለቲካ እስረኛ እንጂ ጥፋተኛ እንዳልሆነ፣ ለሁለት ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ያለ አግባብ በእስር ቤት እንደተንገላታ ፣ጉዳዩን የያዙ ዳኞች በባለስልጣን ጫና ሲቀያየሩ እንደነበር፣ በአጠቃላይ የፍርድ ዉሳኔዉ ጣልቃገብነት የታየበት እንደነበርና ይግባኝ እንደጀመሩ " ተናግረው ነበር።
የቀድሞው ከንቲባ በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነጻ ተሰናብተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የችሎት ሂደቱን ቦታዉ ላይ በመገኘት የተከታተለ ሲሆን የዉሳኔዉን አፈፃፀም የክልሉ ማረሚያ ተቋም የወሰደ ሲሆን ከምሳ ሰዓት በኋላ ከእስር እንደሚለቀቁ ከስፍራዉ ማረጋገጥ ተችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia | 289 386 |
11 | የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ በነፃ ተሰናበቱ።
የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነፃ አሰናበታቸው።
13 ዓመት ተፈርዶባቸዉ በማረሚያ ቤት የነበሩት የቀድሞው ከንቲባ በዛሬዉ ዕለት በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነበራቸው ችሎት የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰነባቸው የፍርድ ዉሳኔ በነፃ መሰናበታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተነግረዋል።
የቀድሞው ከንቲባ በአጠቃላይ ከቀረበባቸዉ 7 የክስ መዝገቦች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው 2 ክሶች በነፃ ተሰናብተው የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ3 ክሶች ነፃ በ2 ክሶች ደግሞ 13 ዓመት እስራት ፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
ከፍርዱ በኃላ ባለቤታቸው ወ/ሮ ዜናዬ ተሰማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " ፀጋዬ ቱኬ የፖለቲካ እስረኛ እንጂ ጥፋተኛ እንዳልሆነ፣ ለሁለት ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ያለ አግባብ በእስር ቤት እንደተንገላታ ፣ጉዳዩን የያዙ ዳኞች በባለስልጣን ጫና ሲቀያየሩ እንደነበር፣ በአጠቃላይ የፍርድ ዉሳኔዉ ጣልቃገብነት የታየበት እንደነበርና ይግባኝ እንደጀመሩ " ተናግረው ነበር።
የቀድሞው ከንቲባ በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነጻ ተሰናብተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የችሎት ሂደቱን ቦታዉ ላይ በመገኘት የተከታተለ ሲሆን የዉሳኔዉን አፈፃፀም የክልሉ ማረሚያ ተቋም የወሰደ ሲሆን ከምሳ ሰዓት በኋላ ከእስር እንደሚለቀቁ ከስፍራዉ ማረጋገጥ ተችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia | 2 730 |
12 | #ExitExam
የ2017 ዓ/ም የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች እየተላከ ይገኛል።
ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ውጤት ለተቋማት እየላከ እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋማቱ ያገኘው መረጃ ያሳያል።
ውጤቱ የደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸው ውጤታቸውን በሬጅስትራር በኩል እንዲያዩ መልዕክት እያስተላለፉ ናቸው።
ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከልም ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንዳለፉም ይፋ ማድረግ ጀምረዋል።
የመውጫ ፈተናው ውጤት እስካሁን ሁሉም ተማሪ ባለበት ሆኖ እንዲያይ ከዚህ በፊት ውጤት በሚታይበት ድረ-ገጽ https://result.ethernet.edu.et ላይ አልተለቀቀም።
ውጤት በድረ-ገጽ ማየት ሲጀመር ተከታትለን መረጃ እናደርሳለን።
በሌላ በኩል ፥ በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች በሳምንቱ መጨረሻ ያስመርቃሉ።
ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ቅዳሜ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች እሑድ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ያካሒዳሉ።
🎓 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ራያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መቱ ዩኒቨርሲቲ እና
🎓 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia @tikvahuniversity | 289 633 |
13 | " ይህንን በተመለከተ ምንም ነገር የለም ፌስታልን እንዲተኩ እንደአማራጭ ይሆናሉ ተብለው የሚነገሩ መሬት ላይ ይወርዳሉ ብለን የማንገምታቸው ነገሮችም አሉ " -የፕላስቲክ እና ጎማ አምራቾች ማህበር
የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ከመጽደቁ ቀደም ብሎ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር።
ሚኒስትሩ ከፕላስቲክ ስናገኝ የነበረውን አገልግሎት በምን አማራጭ ምርቶች ለመተካት ታስቧል ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ።
" በኬሚካል ምርምር ማዕከሎቻችን ያሉ ተመራማሪዎች ፕላስቲክን የሚተኩ አካባቢ ተስማሚ የሆኑ ምርቶችን አግኝተው ሰርተፍኬት ወስደዋል።
ይህንን ምርት ወደ ኢንዱስትሪዎች እያስተዋወቅን ስለሆነ በቀጣይ በስፋት እያመረቱ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን አገልግሎት እንዲያገኝ መጪው ትውልድ ያልተበከለ አካባቢ እንዲረከብ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ማለታቸው ይታወቃል።
ተገኘ የተባለው ፕላስቲክን የሚተካ ምርት በሚመለከት ወደ ኢንዱስትሪዎች የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ እና ጎማ አምራቾች ማህበርን ጠይቋል።
የማህበሩ አባል አቶ በረከት ገ/ህይወት " ይህንን በተመለከተ ምንም ነገር የለም ፌስታልን እንዲተኩ እንደአማራጭ ይሆናሉ ተብለው የሚነገሩ መሬት ላይ ይወርዳሉ ብለን የማንገምታቸው ነገሮችም አሉ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ወደ መሬት ይወርዳሉ ብለን አንገምትም ሲሉ ከዘረዘሯቸው ውስጥ አንደኛው " የወረቀት ማሸጊያዎች " ናቸው።
" የወረቀት ማሸጊያዎች ከሚያስወጡት የውጭ ምንዛሬ አንጻር ፣ለሁሉም አይነት ማሸጊያዎች ጥቅም ላይ የሚውሉ ባለመሆናቸው፣ ለእርጥበት እና ለተለያዩ ነገሮች ተጋላጭ በመሆናቸው እንዲሁም እነዚህን ምርቶች በበቂ ሁኔታ የሚያመርት የወረቀት ኢንዱስትሪ በሃገር ውስጥ ባለመኖሩ ይህንን ክፍተት ይሙሉ ቢባል አስቸጋሪ ይሆናል " ብለዋል።
በተጨማሪም " እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ገብተው ክፍተቱን ለመሙላትም በጣም በርካታ አመት ያስፈልጋቸዋል" ሲሉ አክለዋል።
አቶ በረከት ገ/ህይወት በዝርዝር ምን አሉ?
" የፌስታል ፋብሪካዎች በቀን ከመቶ ሺ በላይ ያመርታሉ ወረቀት ከባህሪው አንጻር ይህን ያህል በቀን ተመርቶ ፍላጎትን ማሟላት አይችልም ከተጣለም በኋላም መልሶ መጠቀም የማይቻል በመሆኑ የማያቋርጥ የውጭ ምንዛሬ ይጠይቃል።
ወረቀት ሃገር ውስጥ ይመረት ቢባል እንኳን ኢትዮጵያ ያላት የእንጨት ሃብት በቂ አይደለም አንድ ኪሎ ግራም ወረቀት ለማምረት የሚፈልገው አቅም አንድ ኪሎ ግራም ፌስታል ለማምረት ከሚወጣው ጉልበት ጋር ሲነጻጸር አራት እና አምስት እጥፍ ነው።
ገበያ ላይም ሰቀርብ ዋጋው ውድ በመሆኑ ትክክለኛ ምትክ ምርት ነው አንለውም።
በሁለተኛነት እንደ እማራጭ የቀረበው የጨረቅ ወይም Non woven ማሸጊያዎች ናቸው እነዚህም እንደጨርቅ የተሸመኑ የፕላስቲክ ምርቶች ናቸው ውድ ናቸው በሃገራችንም ይህንን የሚያመርት ባለመኖሩ የዋጋ ክፍተት መፍጠሩ አይቀርም።
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አለኝ የሚለው ነገር ለማን እንደሆነ ያወቅነው ነገር የለም አለም ከተባለ ለእኛ ለአምራቾች ሊቀርብልን ይገባል " ብለዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አምራቾች በተወሰነ ማስተካከያ ሪፕርፕዝ (Repurpose) በማድረግ በኮቪድ ወቅት የመጠጥ፣ የውሃ እና የአልኮን ፋብሪካዎች ሳኒታይዘር እንዲያመርቱ የተደረገበት አጋጣሚ እንደነበር በመግለጽ የፕላስቲክ ኢንዱስትሪዎችን ተመመሳሳይ ሂደት እንዲከተሉ ይደረጋል ማለታቸው ይታወሳል።
በዚህ ሂደት ላይ ምክክር አላቹ ወይ ? ስንል ሃሳባቸውን የጠየቅናቸው አቶ በረከት " ምክክር የለንም ያንን እና ይሄንን ማነጻጸር ተገቢ አይደለም " ብለዋል።
" የአልኮል እና የኬሚካል ኢንዱስትሪዎችን ለወጥ አድርጎ ሳኒታይዘር እንዲያመርቱ ማድረግ የማሽኖቹን መሰረታዊ ባህሪ መቀየር አያስፈልገውም በእኛ መንገድ ግን ማሽኖቹን repurpose ማድረግ የሚቻልበት እድል የለም የአመራረት ሂደቱ ፕላስቲክ እና ወረቀት አብረው የሚሄዱ ስላልሆኑ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የማህበሩ አባል አቶ በረከት በሰጡት ምክረ ሃሳብም "አዋጁ ጸድቋል በረቂቅ ሂደቱ ላይ የነበሩ ያሳታፊነት ስህተቶች መደገም የለባቸውም ከእኛ ጋር በትክክል ምክክር ያስፈልጋል " ያሉ ሲሆን ኢንዱስትሪ በምንም ሁኔታ በስድስት ወር ውስጥ ስራ አቁም ሊባል አይገባም የሌላ ሃገራት ልምድም ይህንን አያሳይም ሲሉ ተናግረዋል።
" በየትኛውም ሃገር ያልተፈጸመ ተግባር ለምን በእኛ ሃገር ይፈጸማል ? " ሲሉም ጠይቀዋል።
" እነዚህ ኢንዱስትሪዎች በተከራይዋቸው ዌር ሃውስ ውስጥ የሚሰሩ ናቸው ሲከራዩም የ6 ወር እና የ1 አመት ክፍያ ነው የሚፈጽሙት በዚህ ምክንያት ቀድመው በከፈሉት ክፍያ ብቻ ኪሳራ ይደርስባቸዋል " " ሲሉ ገልጸዋል።
" ማሽኖቹም ከጥቅም ውጪ ነው የሚሆኑት ለማጓጓዝም ሰፊ ቦታ እና መሽነሪዎች የሚፈልጉ ናቸው በእነዚህ እና ሌሎች ምክንያቶች የሽግግር ጊዜው ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ አይደለም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia | 252 052 |
Boshqa reja tanlang
Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.