uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Hasen Injamo

Hasen Injamo

Kanalga Telegram’da o‘tish

Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው:: https://telega.io/c/Haseniye

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Hasen Injamo analitikasi

Hasen Injamo (@haseniye) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 010 obunachidan iborat bo'lib, Iqtisodiyot & Moliya toifasida 7 906-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 359-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 010 obunachiga ega bo‘ldi.

22 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 47 ga, so‘nggi 24 soatda esa -1 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 31.15% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 12.60% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 675 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 892 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 31 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው:: https://telega.io/c/Haseniye”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 23 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Iqtisodiyot & Moliya toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 010
Obunachilar
-124 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
+4730 kun
Postlar arxiv
የወረቀት መገበያያ በዓይን ይታይ ስለነበረ እንደውም ብልጭልጭ ቀለም ስለነበረው ... የድሮ ወርቅና ብርን ተክቷል የሚል አመለካከት የነበራቸው ሰዎች ነበሩ:: አሁን ላይ በዓይን የማይታይ, በእጅ የማይዳሰስ, በምላስ የማይቀመስ, በሚዛን የማይመዘን, በኩባያ የማይሰፈር, በሬዲዮ ሞገድ እንኳ የማይለካ ቁጥር ሲሆን ምን ብለው ይሆን? የሌለን ገንዘብ አትፈልጉ:: ሲስተሙ ሌላ ነው:: ንብረት ላይ አተኩሩ:: በተለይ የ Ai ዘመን ሀብት የ K ቅርጽ አስይዞታል:: ንብረት የያዘ ሲመነደግ ገንዘብ ያለ መስሎት የሚቆጥብ እንጦሮ-ጦስ ይሰምጣል::

የባንክ ወለድን ሀላል ለማድረግ ከተኬደባቸው መንገዶች አንዱ ስያሜን መቀየር ነው:: ኢንተረስት የሚባለውን ማርክአፕ ማለት, ብድር የሚባለውን ፋይናንሲንግ በማለት መቀየር ይቻላል የሚል አስቂኝ መከራከሪያ ይቀርባል:: ለዚህም በሬን በስመኣብ ብለህ ብታር^ደው ስጋው የክርስቲያን ሲሆን ቢስሚላህ ብለህ ብታር^ደው የሙስሊም ይሆናል የሚለውን ሎጂክ በማቅረብ:: ወለድ እንደ በሬ ሳይሆን እንደ አሳማ ነው:: አሳማን ቢስሚላሂ ብታርደ^ው ሀላል አይሆንም:: ቢራን ራህማ ወይም ዘምዘም ወይም መካ ብትለው ማስከሩን አይተውም:: ባንክ ብር ከማከራየት ውጭ በፍጹም እቃ ገዝቶ ሊሸጥ አይችልም:: ምክንያቱም የሕዝቡ ሁሉ ብር ባንክ ስለሚቀመጥ ባንክ እቃ ገዝቶ መሸጥ ውስጥ ከገባ ያልተገባ ውድድር ይፈጠራል:: ንግድ ይበጠበጣል:: መሸፋፈን አያስፈልግም:: ብድርን ንግድ ለማስመሰል መሄድ ፈጣሪን ልሸውድህ እንደማለት ነው::

ሀቻምና 57 ብር የነበረ ዶላር ዘንድሮ 163 ብር ገብቷል:: የጤፍ ወይም የስጋ ነጋዴ በሀቻምናው ዋጋ ይሽጥ እንዴ? ጤፍ ሲወደድ ገበሬው ወደ እርሻ ይገባል:: ክብሪት ሲወደድ ነጋዴው ወደ ማምረት ይገባል:: አቅርቦትና ፍላጎት ብዙ ጊዜ በራሳቸው እየተናበቡ ይሄዳሉ:: ለምርት እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች እንዲቀረፉ መሥራት ነው::

ስጋ መርከስ አለበት የሚል ሰው ስጋ ቤት ከፍቶ በርካሽ ለምን አያቀርብም? የሰነፍ እዬዬ!

መንግሥት መሬት ይስጠን ማለት ጀግንነት ነው:: መፍትሔው እዚያ ጋር ነው:: ቤት በርካሽ እና በተመጣጣኝ ኪራይ መከራየት አለበት ብሎ የሚያምን ሰው ... ቤት ሠርቶ በርካሽ እና በተመጣጣኝ የማከራየት መብት አለው:: ይህንን የምለው ችግሩ የግለሰብ ንብረት ላይ መጮኽ መፍትሔ ስለማያመጣ ነው:: ሀብታሞች ግቢያቸው ውስጥ ብዙ ባዶ ክፍሎች አሉዋቸው:: እነርሱን ማን ደፍሮ አከራዩ ብሎ ይጠይቃል? የፈረደበት ደሃውን ነው:: ማንም ቢመቸው ቤቱን ማከራየት አይፈልግም:: በዚያች በኪራይ ነው ልጆቹን የሚያስተዳድረው:: ማከራየትን እንደ ቢዝነስ የያዙን ትቼ ነው:: በግሌ ወላጆቼ በጊዜያቸው ያልያዙትን እና የሌላው አባት ለልጆቹ በያዘላቸው ሀብት ላይ መጮኽ አግባብ አይደለም:: ልጆቼም እኔ ባልያዝኩላቸው ንብረት ላይ መጮኽ የለባቸውም:: ለረጅም ዓመታት በኪራይ ኖሬያለሁ:: ጥሩም መጥፎም አከራይ ገጥሞኛል:: ተከራይነቴ የመጣው በአባትና በአያት ስህተት እንጂ በአከራዮቼ መጥፎነት አይደለም:: በገቢዬ አቅም ነው የምከራየው:: ምሳም የምበላው በኪሴ ልክ ነው:: የሸራተን አቅም ከሌለኝ ሸራ ተራ ሄጄ ጮርናቄ በሻይ ተፈውሼ ተፍ ተፍ ማለት እንጂ ሸራተን የምሳ ሒሳብ ይቀንስ ብሎ መጮኽ አግባብ አይደለም:: ተከራይ ሆኖ ኮተታ ኮተት የሚሰበስብ ሞልቷል:: አባቱ ቤት ሳይዙለት ያንኑ ስህተት በኪራይ ቤት የሚደግም ብዙ ሰው አለ:: በኪራይ ቤት ስምንት ልጅ ይደረድራል:: ግሽበት በሌለ ዘመን አስኪዷል:: አሁን እኮ ኑሮ ጦዟል:: በዚህ ዘመን ኑሮ ያላስታረቃቸው ባለትዳሮች ሽማግሌም ፍርድ ቤትም አያስታርቃቸውም:: ሲጠቃለል:- የቤት ልማት ፕሮግራም እና የመሬት ጉዳይ ትልቅ ለውጥ ይፈልጋል:: የትውልድ ቁጥር እየጨመረ, ምእመኑ መንታ መንታ እየወለደ ውሱን የግለሰብ ቤቶች ላይ ኪራይ ተመን ከተገባ ጭራሽ እጥረት ተፈጥሮ ... የሚከራይ ቤት ማግኘት ሎተሪ እንደመጠባበቅ ይሆናል::

Ai ከመጠቀምህ በፊት ደ^ደደብ ከነበርክ Ai ድ^ድብናህን ያፈጥነዋል እንጂ ጎበዝ አትሆንም:: በ በኮምፒውተር ዘመን ሀብታም የነበሩት መሴጅ እንኳ መጻፍ የማይችሉት እንደነበሩ አትዘንጋ:: ስለዚህ Ai ፈጣን ደደ^ብ ቢያደርግህ ነው:: ስለዚህ እጅህ ላይ ያለውን መሳሪያ አፍጥነህ ተለወጥበት::

ለገሃር ጃእፈር ጋር ጠይቁ +251 91 112 5324
ለገሃር ጃእፈር ጋር ጠይቁ +251 91 112 5324

ዕውነተኛ መረጃ ከሕዝቡ በቀላሉ ከሚሰበሰብባቸው መንገዶች አንዱ ኢ-መደበኛ ነፋስ በመልቀቅ ነው:: የሆነ ጊዜ መንግሥት የሊዝ አዋጁን በተመለከተ አጥኚ በተነ:: ሁሉም ምእመናን ተመችቶናል ብለው መለሱ
ዕውነተኛ መረጃ ከሕዝቡ በቀላሉ ከሚሰበሰብባቸው መንገዶች አንዱ ኢ-መደበኛ ነፋስ በመልቀቅ ነው:: የሆነ ጊዜ መንግሥት የሊዝ አዋጁን በተመለከተ አጥኚ በተነ:: ሁሉም ምእመናን ተመችቶናል ብለው መለሱ:: በቀጣይ ጎረቤትህ ስለሊዝ አዋጁ ምን ይላል? የሚል መጠይቅ ሲበተን ምእመኑ ለመልስ ተጨማሪ ወረቀት ይሰጠን አለ::

ቅን አሳቢ ሞልቷል እኮ
ቅን አሳቢ ሞልቷል እኮ

አንዳንድ ሕግ አስከባሪ ለ50 ሰከንድ እንኳ አደብ የለውም:: በአደባባይ, ትራፊክ ፖሊስ ባለበት, በርካታ መኪናዎች ተደርድረው ለሕግ ተገዢ ሆነው በሚጠባበቁበት ወለል ባለ ሜዳ V8 የያዙ most likely ባለሥልጣናት ወይም ልጆቻቸው በጥቁር ስቲከር ተነቅበው በ2 ቁጥር ታርጋ .. መብራት ይጥሳሉ:: ዝም ብለን ስናሰላው ቢሮኣቸው ውስጥ ምን ጉድ እየሠሩ ይሆን? ትራፊክ ፖሊሱን እንኳ አያስፈቅዱም:: ትራፊክ ፖሊሶችም ይፈራሉ:: ዘወር ብለው አሮጌ መኪና, የራይድና የጭነት መኪኖችን ያሳድዳሉ:: ያመናጭቃሉ:: የበላይ ሕግ አስከባሪ የሚባሉት ለሰከንዶች መታገስ እያቃታቸው ሀያና ሠላሳ ዓመታት በችግር የታገሱ ሰዎች ግን መመሪያና ዱ^ላ ይበዛባቸዋል:: ምእመኑ ከማን ምን ይማር? በለውጡ ሰሞን ባለሥልጣናት ከእንግዲህ ላንድ ክሩዘር አይዙም ተብሎ አሁን ግን ጭራሽ ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ መብራቱን እንዳሻቸው እየጣሱ ይረግጡታል:: ይህ ጥ^ጋብ መቸም ከላይ የወረደ እንዳልሆነ እንገምታለን:: ታዲያ የታችኞቹን ማስታገስ እንዴት ተሳነ? ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ቸኩለው ነው ካልክ ይብሳል:: ምክንያቱም ያለእቅድ ነው የሚጠዳደፉት ማለት ነው::

ይልቃል ጌትነት በሰማያዊ ፓርቲ ይሁን በግራጫ ፓርቲ ምክንያት ታስሮ የረሃብ አድማ መታ:: ከዚያ ሊሞት ሲል ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በነፍሱ ደረሱና:- ይልቅስ ይልቃል አሉት ... ድፍን ሀገሩ ረሃብተኛ በሆነበት ሀገር የረሃብ አድማ ብትመታ መሳቂያ ነው የምትሆነው:: ዜና እንድትሆን ከፈለግህ የጥጋብ አድማ መተህ ሰውነትህ መለስ ብሎልህ ስትወዛ እነተፈራ ዋልዋ እነደብረ ጽዮን እርሱ ይፈታና እኛን እሰሩን ብለው እጣ ይጣጣሉብሃል ብለውት መብላት ጀመረ ይባላል:: ብቻ ስጋ ያለመብላት አድማ የጠሩት የኤአይ በሬዎችና ጅቦች ይሆኑ እንዴ? ዛሬ በሄድኩበት ሁሉ ኤስ ኤች ዩ RO ሆነብኝ::

ሁሉንም ፈትኑ:: የተመቻችሁን ያዙ:: ===== 1. ኤቲስት (Atheist - ኢ-አማኝ) አመለካከት: "አምላክ ወይም ፈጣሪ የለም" ብሎ ያምናል። መግለጫ: ማንኛውንም የተፈጥሮ በላይ ኃይል ወይም አምላክ አይቀበልም። የዓለምን መፈጠር እና መንቀሳቀስ በተፈጥሮ ሕጎች እና በሳይንሳዊ መረጃዎች ብቻ ይረዳል:: 2. ቴይስት (Theist - አምላክ አምላኪ / አማኝ) አመለካከት: "ዓለምን የፈጠረ እና አሁንም የሚመራ አምላክ አለ" ብሎ ያምናል። መግለጫ: አምላክ ከፍጥረቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው (ጸሎት ይሰማል፣ ተአምራትን ያደርጋል፣ ነቢያትን ይልካል) ብሎ ያምናል። 3. አግኖስቲክ (Agnostic - ተጠራጣሪ / ያልወሰነ) አመለካከት: "የአምላክ መኖር ወይም አለመኖር በሰው ልጅ አእምሮ ሊታወቅ አይችልም" ይላል። መግለጫ: አምላክ ለመኖሩም ሆነ ላለመኖሩ በቂ እና አሳማኝ ማስረጃ የለም ብሎ ስለሚያስብ "አምላክ አለ" ወይም "የለም" ብሎ እርግጠኛ ከመሆን ይቆጠባል። 4. ዲይስት (Deist - የተፈጥሮ አምላክ አማኝ) አመለካከት: "አምላክ ዓለምን ፈጥሯል፤ ነገር ግን አሁን ጣልቃ አይገባም" ብሎ ያምናል። መግለጫ: ፈጣሪ ዓለምን እና የተፈጥሮ ሕጎችን ፈጥሮ እንደ ሰዓት ካስኬደ በኋላ ትቷታል። ጸሎት፣ ተአምራት ወይም ሃይማኖታዊ መጻሕፍት አያስፈልጉም ብሎ ያምናል። 5. ፓንቴይስት (Pantheist - ተፈጥሮ-አምላኪ) አመለካከት: "ዓለም/ተፈጥሮ እና አምላክ አንድ ናቸው" ብሎ ያምናል። መግለጫ: አምላክ ከዓለም ተለይቶ የሚኖር አካል ሳይሆን፣ አጽናፈ ዓለም (Universe) እና ተፈጥሮ በሙሉ እራሱ አምላክ ነው ብሎ ያምናል። 6. ሚሶቴይስት (Misotheist - አምላክ ጠሊ) አመለካከት: "አምላክ አለ፤ ነገር ግን ክፉ/ጨካኝ ስለሆነ እጠላዋለሁ" ይላል። መግለጫ: በአለም ላይ ያለውን መከራ እና ስቃይ በማየት አምላክ እንዳለ ቢያምንም፣ አምላክን እንደ አፍቃሪ ሳይሆን እንደ ጨካኝ ወይም ኢ-ፍትሐዊ አካል አድርጎ ይመለከተዋል፤ ስለዚህም ይጠላዋል። 7. ሄኖቴይስት (Henotheist - ከአንድ በላይ አማልክት ባሉበት አንዱን አብልጦ አምላኪ) አመለካከት: "ብዙ አማልክት እንዳሉ ይቀበላል፤ ነገር ግን አንዱን ዋና አምላክ አድርጎ ያመልካል"። መግለጫ: የሌሎችን አማልክት ህልውና ሳይክድ፣ ለእሱ ወይም ለወገኑ ግን አንዱን የተወሰነ አምላክ ብቻ የላቀ አድርጎ ያመልካል። 8. ፖሊቴይስት (Polytheist - ብዙ-አማልክት አምላኪ) አመለካከት: "ከአንድ በላይ የሆኑ ብዙ አማልክት አሉ" ብሎ ያምናል። መግለጫ: እያንዳንዱ አምላክ የየራሱ የኃይል ወይም የተፈጥሮ ክፍል (የዝናብ፣ የፀሐይ፣ የጦርነት አምላክ...) አለው ብሎ ያምናል። (ለምሳሌ፦ የጥንታዊ ግሪክ እና ሮማውያን እምነት)። 9. ሞኖቴይስት (Monotheist - አንድ-አምላክ አምላኪ) አመለካከት: "በእውነት ያለ እና የሚመለክ አምላክ አንድ ብቻ ነው" ብሎ ያምናል። መግለጫ: ከእሱ ውጭ ያሉ አማልክትን በሙሉ የሉም ወይም ሀሰተኛ ናቸው ብሎ ይኖራል። 10. ፓነንቴይስት (Panentheist - አምላክ በተፈጥሮ ውስጥ እና ከዚያም በላይ) አመለካከት: "ዓለም በአምላክ ተከቦ ይኖራል፤ ነገር ግን አምላክ ከዓለም ይበልጣል" ብሎ ያምናል። መግለጫ: ተፈጥሮ የአምላክ አካል ቢሆንም፤ ግን አምላክ ከፍጡራኑ እና ከአጽናፈ ዓለም ወሰን በላይ የሆነ የራሱ ህልውና አለው ብሎ ያምናል። (ወሃb እዚህ ግድም ይመደባል) 11. ኦቶቴይስት (Autotheist - እራስ-አምላኪ) አመለካከት: "እራሴ ወይም የሰው ልጅ እራሱ አምላክ ነው" ብሎ ያምናል። መግለጫ: ከውጭ የሚጠበቅ መንፈሳዊ ኃይል የለም፤ የሰው ልጅ የራሱ ህይወት፣ እጣ ፈንታ እና መንፈሳዊነት የበላይ ገዢ እራሱ ነው የሚል አስተሳሰብ ነው። 12. ዲስቴይስት (Dystheist - አምላክ ሙሉ በሙሉ መልካም አይደለም) አመለካከት: "አምላክ አለ፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ቸር/መልካም አይደለም" ብሎ ያምናል። መግለጫ: አምላክ ፍጹም መልካም እንዳልሆነ እና አንዳንዴም ክፉ ወይም ግራ የሚያጋባ ባህሪ ሊኖረው እንደሚችል እንደ ፍልስፍናዊ እውነታ ይቀበላል። 13. ኢግኖስቲክ (Ignostic - የትርጉም ጥያቄ አቅራቢ) አመለካከት: "'አምላክ' የሚለው ቃል ግልጽ የሆነ ትርጉም ስለሌለው ስለ እሱ መከራከር ትርጉም የለውም" ይላል። መግለጫ: አምላክ አለ ወይም የለም ብሎ ከመከራከር በፊት "ለመሆኑ አምላክ ማለት ምን ማለት ነው?" የሚለው ትርጉም በግልጽ ካልተበየነ በቀር ውይይቱ ፍሬ አልባ ነው ብሎ ያምናል። 14. አፓቴይስት (Apatheist - ደንታ-ቢስ) አመለካከት: "አምላክ ቢኖርም ባይኖርም ለእኔ ምንም አያግደኝም/አያስጨንቀኝም" ይላል። መግለጫ: የአምላክ መኖር ወይም አለመኖር በሰው ልጅ እለታዊ ህይወት ላይ ምንም የሚያመጣው ለውጥ የለም ብሎ ስለሚያስብ ስለ ጉዳዩ ማሰብም ሆነ መከራከር አይፈልግም።

<<በቤት ኪራይ ተሰቃየን:: መሄጃ አጣን:: እሺ መሬት ስጡን:: አዲሱ ትውልድ የት እንግባ>> እያለች ታለቅሳለች:: ይህ የሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው:: 1968 ላይ መሬት
<<በቤት ኪራይ ተሰቃየን:: መሄጃ አጣን:: እሺ መሬት ስጡን:: አዲሱ ትውልድ የት እንግባ>> እያለች ታለቅሳለች:: ይህ የሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው:: 1968 ላይ መሬት ላራሹ ተብሎ አዋጅ ታውጆ ትውልዱ መሬት አገኘ:: ከዚያ ወዲህ መሬት የሚባል ነገር አልተሰጠም:: መንግሥት መሬትን የሚያህል ሀብት አንቆ ይዞ ሊደባ^ደብ የሚሄደው የግለሰብ አከራዮች ጋር ነው:: መንግሥት ብር, መሬት, ቀረጥ, ሕግ ሁላ ይዞ ያልቻለውን መንግሥታዊ ሪል ኢስቴት ማለትም ኮንዶሚኒየም ሳይሰጥ... የግል አልሚዎች ካላሟላችሁ ይላል:: መንግሥት መሬትን በአግባቡ ማደል ሲገባው በሊዝ ያከራያል:: ትውልዱ ይሰቃያል:: ቢቸግራቸው ተሰደው ለፍተው መጥተው የወጠሩትንም ላስቲክ ያፈርሱባቸዋል:: መንግሥት መሬት ይስጥ, ኮንዶሚኒየም ይገንባ, የግሎችም የተረፈውን ይሸፍኑ:: በዋለ ባደረ ቁጥር ትውልዱ እየጨመረ የቤት ግንባታ ባለበት ቆሞ ወይም ቀንሶ እንዴት ሊጣጣም ይችላል? መጠለያ መሠረታዊ ፍላጎት ስለሆነ ወደድንም ጠላንም አብዮት ያስነሳል:: ምግብ መሠረታዊ ስለሆነ አብዮት ያስነሳል::

በመደበኛ ባንክ እና በወለድ በነጻው ባንክ መሃል ያለው መሠረታዊ ልዩነት ስጋትን (Risk)ን መጋራት ነው:: መደበኛውና ለዘመናት የምናውቀው ባንክ በተወሰነ መልኩ ስጋት (risk) ይጋራል:: ለቆጣቢ መጠነኛ የግሽበት ማካካሻ ይሰጣል:: ከተበዳሪም በኩል ያልሠሩበትን ዘመን ትርፍ አያስከፍልም:: ውሉም ግልጽ ነው:: ወለድ በነጻው ግን በፍጹም ስጋት (Risk) አይጋራም:: ቆጣቢ ብር በነጻ ያመጣል:: ተበዳሪም "የተሸጠ ዕቃ አይመለስም" በሚል አሠራር ያልሠራበትን ዘመን ትርፍ ይከፍላል:: ባንኩ ብር ማከራየቱን ባላየ ለማለፍ ሲሚንቶ ወይም ብረት ልግዛልህ ይላል:: ከደሃ ቆጣቢ ደግሞ ሲሚንቶ ቆጥቡ ... ብረት ቆጥቡ አይልም:: አታሎ በነጻ ይቀበልና በትርፍ ያበድራል:: ውሉ እጅግ የተቀሸበና ግልጽነት የጎደላቸው አናቅጽ አሉበት:: ብዙ ውሎች እጄ ላይ ስላሉ ነው:: የኢስላም ሕግጋትን በጽኑ ይጻረራሉ:: ባንኩ በመደበኛው አሠራር ሲጋራቸው የነበሩ ስጋቶችን (Risks) ከራሱ ላይ ሲያሸሽ ወለድ በነጻ ይሆናል:: በነገራችን ላይ ከቲዎሪው በተቃራኒው ነው:: ሙዷረባን እንዴት 180 ዲግሪ እንደገለበጡት ፊያት መገበያያና ወለድ መጽሓፍ ላይ በዝርዝር አለላችሁ::

ለፋይናንስ ሲስተሙ ግማሽ መንገድ (50%) ለመጓዝ ቤት መግዛት ነው ተባብለናል:: ታዲያ ቤት ስትገዙ ሁለት ነገሮች መሟላታቸውን ከግምት አስገቡ:: አንደኛው ዲጂታል ካርታ መያዙን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ካርታው የያዘው ማነው? የሚለው ነው:: ባለይዞታው አሁናዊ የትዳር ሁኔታው ወሳኝ ነው:: ተፋተው ወዲያው ያላገባ ሊያወጡ ይችላሉ:: የንብረት ክፍፍል ውሳኔ ከነአፈጻጸሙ ካልያዙ ዱዲ መክፈል አያስፈልግም:: እዚሁ ጋር የእዳ, ዋስትናና እግድ ጉዳዮች ይታያሉ:: ከእነዚህ ሁሉ ጽድት ያለ ካላገኘህ መክፈልህ ቤት አለኝ አያስብልህም:: ለሪል ኢስቴት ቀብድ ከከፈልክ ቤት ሳይሆን ኢንቨስትመንት ነው:: በአንዴ ከምከፍል እየሠራሁ ቤት ይኑረኝ ዐይነት ነገር ነው:: ታማኝ አልሚ ካገኘህ እድለኛ ነህ:: በሒደት ቤት ይኖርሃል:: ካላገኘህ ግን በርቶብሃል:: ሿሿ ላይ ነህ:: ውሱን ጥሩ አልሚዎች አሉ:: እነርሱም በሚወጡ ሕጎችና መመሪያዎች ሊወላከፉ ይችላሉ:: ገንብተው ካርታ ለመበተን ቢያንስ የውስጥ ፓርቲሽን መጨረስ አለባቸው:: ለየቤቱ ስም ለማዞር በርና መስኮት ገጥመው የመጠቀሚያ ፈቃድ አውጥተው ከገቢዎች ክሊራንስ መጨረስ አለባቸው:: ምሳሌ:- አንድ ሕንጻ 60 ቤቶች ቢኖሩት 60 ሽንሽን ካርታ እና 60 የገቢዎች ክሊራንስ ይኖሩታል:: ክሊራንሱ የሚያገለግለው ለሦስት ወራት ብቻ ነው:: ባንኮች የሚሰሙህ ዲጂታል ካርታ ስትይዝ ብቻ ነው:: ቤቱ የሌላ ሰው ከሆነ የብድር ዋስ ሊሆንህ ይችላል:: እናልህ ካርታ የሌለው ስቴዲዮም አለኝ ከምትል ሰነዱ ጽድት ያለ ስቱዲዮ ይሻልሃል:: የሀብታምነት ጉዞ ላይ 50% ደርሰሃል:: ቀሪው ንግድ ፈቃድ አውጥቶ ቢዝነስ መሥራት ነው:: (መ-ገንዘብ 2 እና 3 ይህንን ያስረዳሉ)::

coffe_order_en_new.jpg0.48 KB

አሁን በቅርብ ያለው ስልጠና ይህ ብቻ ነው:: ኢምፖርት ግን እናሳውቃለን::
አሁን በቅርብ ያለው ስልጠና ይህ ብቻ ነው:: ኢምፖርት ግን እናሳውቃለን::

''Finance for Non-Finance Managers'' ለ 3 ቀናት ጥቅምት 10, 11 እና 12 ጠዋት ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር ACC. No. 1000762139646 HAB Management and Technologies መመዝገቢያ ሊንክ: 1. በድርጅቱ ድረ-ገጽ www.hab.et/register ወይም 2. በቴሌግራም t.me/hab_management 3. 🤳 +251990555599

''Finance for Non-Finance Managers'' ለ 3 ቀናት ጥቅምት 10, 11 እና 12 ጠዋት ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር ACC. No. 1000762139646 HAB Management and Technologies መመዝገቢያ ሊንክ: በድርጅቱ ድረ-ገጽ www.hab.et/register ወይም 2. በቴሌግራም t.me/hab_management 🤳 +251990555599

ከስልጠና ወደ ስልጠና ያለረፍት እየተጓዝን ነው:: ከሁሉም የሚገርመው 5 የተለያዩ ዓይነት ስልጠናዎችን አዘጋጅተን ቢያንስ ሦስቱን የተሳተፉ ብዙ ናቸው:: አምስቱንም የወሰዱ አሉ:: ሳናውቀው ለካ ብዙ
+2
ከስልጠና ወደ ስልጠና ያለረፍት እየተጓዝን ነው:: ከሁሉም የሚገርመው 5 የተለያዩ ዓይነት ስልጠናዎችን አዘጋጅተን ቢያንስ ሦስቱን የተሳተፉ ብዙ ናቸው:: አምስቱንም የወሰዱ አሉ:: ሳናውቀው ለካ ብዙ ቤተሰብ አለን:: ደስ ይላል:: ይህኛው ፎቶ ከትናንትና ወዲያ ሐሙስ የተጠናቀቀው የኢምፖርት ስልጠና ነው:: የኢምፖርት ይቀጥላል:: የትራንዚቱን በትራንዚተር ብቻ ሳይሆን ጉምሩክ በሠሩና በቂ ስልጠና ባላቸው አሰልጣኞች ... የውጭ ምንዛሪ ላይ ምርጥ በሚባሉ ባንኮች የ International Banking Divisions ባለሙያዎችን ... የ Single windowsም እንደዚያው በባለሙያ ... የቻይናውም ከቻይና Live እንገባለን:: ሌላውም በሚመለከተው ክፍል ነው የሚሰጠው:: ዳሸን ባንኮች ገራሚ ስልጠና ነው የሰጡልን:: አንድ እርምጃ የቀደመ ስልጠና:: _ Finance for non-financial managers የሚል ስልጠና የፊታችን ማክሰኞ, ረቡዕና ሐሙስ የሦስት ግማሽ ግማሽ ቀናት ስልጠና አለ:: ምዝገባ መጨረሻው ቀን ላይ ነን:: ቦታ አዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት አካባቢ በአካል ብቻ