ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Hasen Injamo

Hasen Injamo

Открыть в Telegram

Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው:: https://telega.io/c/Haseniye

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Hasen Injamo

Канал Hasen Injamo (@haseniye) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 024 подписчиков, занимая 7 916 место в категории Экономика и финансы и 2 353 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 024 подписчиков.

Согласно последним данным от 18 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 73, а за последние 24 часа — 4, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 29.78%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 13.60% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 475 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 044 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 32.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው:: https://telega.io/c/Haseniye”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 19 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Экономика и финансы.

15 024
Подписчики
+424 часа
+187 дней
+7330 дней
Архив постов
ለፋይናንስ ሲስተሙ ግማሽ መንገድ (50%) ለመጓዝ ቤት መግዛት ነው ተባብለናል:: ታዲያ ቤት ስትገዙ ሁለት ነገሮች መሟላታቸውን ከግምት አስገቡ:: አንደኛው ዲጂታል ካርታ መያዙን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ካርታው የያዘው ማነው? የሚለው ነው:: ባለይዞታው አሁናዊ የትዳር ሁኔታው ወሳኝ ነው:: ተፋተው ወዲያው ያላገባ ሊያወጡ ይችላሉ:: የንብረት ክፍፍል ውሳኔ ከነአፈጻጸሙ ካልያዙ ዱዲ መክፈል አያስፈልግም:: እዚሁ ጋር የእዳ, ዋስትናና እግድ ጉዳዮች ይታያሉ:: ከእነዚህ ሁሉ ጽድት ያለ ካላገኘህ መክፈልህ ቤት አለኝ አያስብልህም:: ለሪል ኢስቴት ቀብድ ከከፈልክ ቤት ሳይሆን ኢንቨስትመንት ነው:: በአንዴ ከምከፍል እየሠራሁ ቤት ይኑረኝ ዐይነት ነገር ነው:: ታማኝ አልሚ ካገኘህ እድለኛ ነህ:: በሒደት ቤት ይኖርሃል:: ካላገኘህ ግን በርቶብሃል:: ሿሿ ላይ ነህ:: ውሱን ጥሩ አልሚዎች አሉ:: እነርሱም በሚወጡ ሕጎችና መመሪያዎች ሊወላከፉ ይችላሉ:: ገንብተው ካርታ ለመበተን ቢያንስ የውስጥ ፓርቲሽን መጨረስ አለባቸው:: ለየቤቱ ስም ለማዞር በርና መስኮት ገጥመው የመጠቀሚያ ፈቃድ አውጥተው ከገቢዎች ክሊራንስ መጨረስ አለባቸው:: ምሳሌ:- አንድ ሕንጻ 60 ቤቶች ቢኖሩት 60 ሽንሽን ካርታ እና 60 የገቢዎች ክሊራንስ ይኖሩታል:: ክሊራንሱ የሚያገለግለው ለሦስት ወራት ብቻ ነው:: ባንኮች የሚሰሙህ ዲጂታል ካርታ ስትይዝ ብቻ ነው:: ቤቱ የሌላ ሰው ከሆነ የብድር ዋስ ሊሆንህ ይችላል:: እናልህ ካርታ የሌለው ስቴዲዮም አለኝ ከምትል ሰነዱ ጽድት ያለ ስቱዲዮ ይሻልሃል:: የሀብታምነት ጉዞ ላይ 50% ደርሰሃል:: ቀሪው ንግድ ፈቃድ አውጥቶ ቢዝነስ መሥራት ነው:: (መ-ገንዘብ 2 እና 3 ይህንን ያስረዳሉ)::

coffe_order_en_new.jpg0.48 KB

አሁን በቅርብ ያለው ስልጠና ይህ ብቻ ነው:: ኢምፖርት ግን እናሳውቃለን::
አሁን በቅርብ ያለው ስልጠና ይህ ብቻ ነው:: ኢምፖርት ግን እናሳውቃለን::

''Finance for Non-Finance Managers'' ለ 3 ቀናት ጥቅምት 10, 11 እና 12 ጠዋት ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር ACC. No. 1000762139646 HAB Management and Technologies መመዝገቢያ ሊንክ: 1. በድርጅቱ ድረ-ገጽ www.hab.et/register ወይም 2. በቴሌግራም t.me/hab_management 3. 🤳 +251990555599

''Finance for Non-Finance Managers'' ለ 3 ቀናት ጥቅምት 10, 11 እና 12 ጠዋት ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር ACC. No. 1000762139646 HAB Management and Technologies መመዝገቢያ ሊንክ: በድርጅቱ ድረ-ገጽ www.hab.et/register ወይም 2. በቴሌግራም t.me/hab_management 🤳 +251990555599

ከስልጠና ወደ ስልጠና ያለረፍት እየተጓዝን ነው:: ከሁሉም የሚገርመው 5 የተለያዩ ዓይነት ስልጠናዎችን አዘጋጅተን ቢያንስ ሦስቱን የተሳተፉ ብዙ ናቸው:: አምስቱንም የወሰዱ አሉ:: ሳናውቀው ለካ ብዙ
+2
ከስልጠና ወደ ስልጠና ያለረፍት እየተጓዝን ነው:: ከሁሉም የሚገርመው 5 የተለያዩ ዓይነት ስልጠናዎችን አዘጋጅተን ቢያንስ ሦስቱን የተሳተፉ ብዙ ናቸው:: አምስቱንም የወሰዱ አሉ:: ሳናውቀው ለካ ብዙ ቤተሰብ አለን:: ደስ ይላል:: ይህኛው ፎቶ ከትናንትና ወዲያ ሐሙስ የተጠናቀቀው የኢምፖርት ስልጠና ነው:: የኢምፖርት ይቀጥላል:: የትራንዚቱን በትራንዚተር ብቻ ሳይሆን ጉምሩክ በሠሩና በቂ ስልጠና ባላቸው አሰልጣኞች ... የውጭ ምንዛሪ ላይ ምርጥ በሚባሉ ባንኮች የ International Banking Divisions ባለሙያዎችን ... የ Single windowsም እንደዚያው በባለሙያ ... የቻይናውም ከቻይና Live እንገባለን:: ሌላውም በሚመለከተው ክፍል ነው የሚሰጠው:: ዳሸን ባንኮች ገራሚ ስልጠና ነው የሰጡልን:: አንድ እርምጃ የቀደመ ስልጠና:: _ Finance for non-financial managers የሚል ስልጠና የፊታችን ማክሰኞ, ረቡዕና ሐሙስ የሦስት ግማሽ ግማሽ ቀናት ስልጠና አለ:: ምዝገባ መጨረሻው ቀን ላይ ነን:: ቦታ አዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት አካባቢ በአካል ብቻ

መ-ገንዘብ መጽሓፍ ከፍሎ በወቅቱ አድራሻ በትክክል ጽፎ ያልተላከለት ያለ አይመስለኝም:: እስካሁን ያልደረሰው ምእመን - ወይ ፖስታ ቤቶች ሲደውሉ ስልኩ ዝግ የሆነ - ወይ ወትሮም አድራሻ ያልሞላና ዘግይቶ ሰጥቶን ፕሮሰስ ላይ ያለ - ወይ ከነጥራሹኑ ያልሰጠን - ወይ Bot ላይ ሲሞላ የሆነ ለተወሰነ ሰዓታት ክራሽ ያደረገ ወቅት ነበር:: ያኔ ሞልቶ ሳይደርሰን የቀረ:: ቢሆንም ቢሆንም 99% ፐርሰንት በላይ ለከፈለ አድርሻለሁ:: የቀረ ምእመን በክብር የማድረስ ውዴታ አለብኝ:: መጨረሻ ላይ አድራሻ ሰጥታችሁኝ ያልተላከ እጅግ few የሚባል ሰው አለ:: አጣራና በቅርቡ እልካለሁ:: ማጣሪያው ነው የሚያደክመው:: እንዳያመናጭቁዋችሁ እኔው እራሴው ነኝ የማስተናግደው:: ያልገዛ ግን ጃእፈር ጋር

መኖሪያ ቤት ከምትገዛ በብሩ ነግድበትና በትርፉ ቤት ትገዛለህ ይባል ነበር:: በወቅቱ ስህተት ላይሆን ይችላል:: ምክንያቱም ግሽበት ብዙም ስላልተስፋፋ የእቃ ይሁን የቤት ዋጋ ጭማሪ ብዙም አይራመድም ነበር:: አሁን ግን ተቃራኒው ነው ያለው:: ስለዚህ አሁን ደግሞ እጅህ ላይ ባለው ብር ቤት ትገዛና ቤቱን አስይዘህ በሞኝ የቁጠባ ብር ትነግዳለህ:: ይህ ሲባል ከሰው ሰው ይለያያል:: ሥራህ ፈጣን ትርፍ የሚያመጣበት ወቅት ላይ ከሆንክ ንግድህን አጧጡፍ:: ግን ቤት ለመግዛት አትዘግይ:: ምክንያቱም ከባንክ የመጀመሪያውን ብድር ለማግኘት ያለው ውጣ ውረድ ቀላል አይደለም:: ከዚያ ግን የሞባይል ካርድ መሙላት በለው:: ቤት ግዛ ስልህ ደግሞ አደራ:: ዲጂታል ካርታ የያዘና የባለቤትነት ችግር የሌለበት ማለትም ባለትዳሮች የተስማሙበት እና የውርስ ችግር የሌለበት ይሁን:: ይሄ ሪል ኢስቴት ላይ ቀብድ ከፍሎ ቁጭ ማለት ክሪፕቶከረንሲ ላይ የሆነ ብር ቀርቅረህ የሚሆነውን እንደመጠባበቅ ነው:: እርሱን ታማኝ ገንቢ ካገኘህ እና እንደ ኢንቨስትመንት ከቆጠርከው ጥሩ ሊሆን ይችላል:: ቀስ እያልክ ቤት ይኖርሃል:: ይህኛው ባንዴ መግዛት ለማይችል እና ባወጣው ያውጣው ለሚል ነው:: እርሱን አላልኩም:: እኔ እያወራሁ ያለሁት ስለፋይናንስ እና ታክስ አድቫንቴጅ ነው:: አስማት የሚመስለውን የእድገት ምሥጢርን ነው:: ጅብ ግልቢያ ሁሁይ የለውም:: Pure ማትስ ነው:: በራስህ ንጹሕ ብር ግንባታውም ሰነዱም የተጠናቀቀ ቤት ትገዛና ብሩን በንግድ ፈቃድህ በኩል ትስበዋለህ:: ይህንን multiply ✖️ ማድረግ ነው:: መኪና አስቀድሞ መሯሯጥ የሚመርጥ ይኖራል:: ይህም ስህተት ላይሆን ይችላል:: የፋይናንስ ሥርዓቱ መቆሚያ ሁለቱ እግሮች ኢንተረስና ታክስ ናቸው:: እነርሱን ነው የምታጫውተው::

የግብርና ባንክ በቅርቡ እንደሚቋቋም ሰምተናል:: በጣኣኣኣኣም ደስ ይላል:: እኔ ላቋቁመው ሳይሆን ላስቋቁመው ብዙ ወትውቻለሁ:: ምክንያቱም በግለሰብ ደረጃ የሚቋቋም ተራ ባንክ አይደለም:: እጅግ በጣ
የግብርና ባንክ በቅርቡ እንደሚቋቋም ሰምተናል:: በጣኣኣኣኣም ደስ ይላል:: እኔ ላቋቁመው ሳይሆን ላስቋቁመው ብዙ ወትውቻለሁ:: ምክንያቱም በግለሰብ ደረጃ የሚቋቋም ተራ ባንክ አይደለም:: እጅግ በጣም ግዙፍ እና ሀብታም ባንክ ስለሆነ ብዙ ዝግጅት የሚፈልግ ነው:: መንግሥት ቀድሞም አስቦበት ይሆናል አላውቅም:: እንደዚያ ነው ብለን እናስብ:: የእኔ አካሄድ የሚመለከታቸው የመንግሥት ቢሮዎች በአንክሮ እንዲመለከቱት ማድረግ በመሆኑ ቀዳማይ ታርጌቴ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የመንግሥት ሚዲያ አደረግሁ:: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያስፈለገው ካሪኩለም እንዲያሻሽል ሲሆን የመንግሥት ሚዲያ ደግሞ ስለባንኩ ምንነት እንዲያስረዳ ነበር:: ለዚህም ETVን በተለይ ጋዜጠኛ አብርሃምና የዝግጅት ክፍሎችን አመሰግናለሁ:: ቀጣይ የነበረው የግብርና ሚኒስቴር እና ብሔራዊ ባንክ ነበሩ:: ለዚህም Concept note አዘጋጅቼ ሞቅ ያለ ፕሮግራም ልናዘጋጅ ሰነዶቹን ልኬ ነበር:: ችግሩ ስሜን አልጽፍበትም:: ማንም ይጀምረው ማን ዋናው መጀመሩ ነው:: እኔ በሠራሁት ጥናት ግብርና ባንክ በጣም ሀብታም ባንክ ነው:: ምክንያቱም የሀብቱ ምንጭ ፊያት ሳይሆን ምርት ነው:: ማእድናትም ጭምር ስከሚያካልል ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የሚለምኑት ከግብርና ባንክ ነው:: ፔፐሩን ከፈለጋችሁ በኮሜንት አለላችሁ:: ሙሉ ፔፐር 👇🏼👇🏼👇🏼 https://etd.aau.edu.et/server/api/core/bitstreams/d2a9e377-3330-48ac-9ea5-b4b0593b8820/content 👇🏼👇🏼👇🏼ከጆርናል www.ijmdrr.com/admin/downloads/070820234.pdf

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ CBDC እጀምራለሁ ብሏል:: CBDC ምንድነው? ከንግድ ባንክ ዲጂታል መገበያያ በምን ይለያል? ይህንን ነጥብ ለታዳጊዎች በሚገባ ቋንቋ ሳይቀር ጽፌዋለሁ:: ለልጆች በሚገባ መ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ CBDC እጀምራለሁ ብሏል:: CBDC ምንድነው? ከንግድ ባንክ ዲጂታል መገበያያ በምን ይለያል? ይህንን ነጥብ ለታዳጊዎች በሚገባ ቋንቋ ሳይቀር ጽፌዋለሁ:: ለልጆች በሚገባ መልኩ መጻፍ ይከብድ ነበር:: ያው ግን ተወጥቼዋለሁ:: በአዋቂዎችም በታዳጊዎችም መጽሓፍ ውስጥ አለላችሁ:: የገዛችሁ ሰዎች መልሳችሁ ገርቡት:: BRICS ደግሞ እንደ መገበያያ ያስቀመጠው ወርቅ የደገፈው CBDC ነው:: ብሪክስ ግብይቱ ከንግድ ባንክ ይልቅ ብሔራዊ ባንክ ጋር ይሆናል:: ብሔራዊ ባንክ ከወርቅ ጋር ትስስር አለ:: ብሪክስም ከእኛ ጋር የምትዋዋሉት በባዶ ፊያት ሳይሆን ወርቅ ጋር የተደገፈ ሲቢዲሲ ይሁን ብለዋል:: እኛም ወርቅን ማንጠር ጀምረናል:: ብቻ ደስ የሚል ነገር ይታየኛል:: ያድርገው:: ስለግብርና ባንክ ስሰማ ደግሞ በደስታ እንባዬ ነው የመጣው:: በትክክል የሚተገበር ያድርገው::

የግብርና ባንክ በሦስት ወራት ውስጥ ይጀመራል የሚል ዜና Capital መጽሔት ላይ አነበብኩ:: Congratulations 🎈🎉🍾 ========= የቻይና ግብርና ባንክ ባየሁ እና በተጠቀምሁ ቁጥር
የግብርና ባንክ በሦስት ወራት ውስጥ ይጀመራል የሚል ዜና Capital መጽሔት ላይ አነበብኩ:: Congratulations 🎈🎉🍾 ========= የቻይና ግብርና ባንክ ባየሁ እና በተጠቀምሁ ቁጥር ሀገሬ ላይ እንደሚኖረን እመኝ ነበር:: ይልቅስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፔፐሬም በዚሁ ላይ ነው:: ፔፐሩም ከጋዜጠኛ አብርሃም ታደሰ ጋር በተከታታይነት አቅርበነዋል:: የባንኩ ሠራተኞች ዝግጅት በተመለከት ተጨማሪ ባለሙያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋብዤ በETV አቅርበነዋል:: በመጽሓፎቼም ርዕስ ሰጥቼ የዕድገታችን የመፍትኄ አካል አድርጌ ሠርቼዋለሁ:: ልዩ ትኩረት ከሰጠሗቸው ጉዳዮች ግብርና ባንክ ከበፊተኞቹ ነው:: መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ለመጀመር መድረሱ የተሰማኝ ደስታ ወደር የለውም:: ፎቶ:- ቻይና ከ Agricultural Bank of China (ABC) ፊትለፊት

ሆድህ ሲበዛ ጾታህ ይቀያየራል:: (ዋናው ፖስቱ ግን ይህ አይደለም)::
ሆድህ ሲበዛ ጾታህ ይቀያየራል:: (ዋናው ፖስቱ ግን ይህ አይደለም)::

ብዙ ቢዝነስማኖች እና ውማኖች የተዝረከረከ ድርጅታቸውን ሲስተም እንዳሲዝላቸው ይጠይቁኛል:: -> መጀመሪያ ረጅምምም የተዝረከረከ ሳቅ እስቃለሁ:: ፖለቲካውና የሕግ ሥርዓቱ ሥርዓት ባልያዘበት ሀገር እንደውም እብ^ድ የዘገነው በሶ ማስመሰል ነው እንጂ የምን ሲስተም መዘርጋት አመጣህ? ጨበጥ አድርገው:: ወንድሜ ከቻልክ አሮጌና አዲስ ሁለት ዓይነት መኪና ግዛ:: ትራፊኮችን ከፈራህ ገመቺሱን ይዘህ ውጣ:: መብራት ብትጥስ እንኳ አያስቆሙህም:: አሮጌ ከያዝክ እኮ ይቀምሉታል አይገልጸውም:: ዝንጀሮ እንኳ ልጇን እንዲህ አትቀምልም:: የሱሪ ቀበቶ አላሰርክም ብለው ሊከሱህ ይችላሉ:: Well, አጋቾችን ከፈራህ ደግሞ አሮጌውን ይዘህ ውጣ:: ኑሮ በዘዴ (ኢኮኖሚክስ) እንዲህ ነው:: ሐቀኛ ግብር ከፋይ ሁን:: ግን የሽልማት ቀን ተወካይ ወይም ጥበቃህን ላክ:: የከፈልከውን ታክስ ለዴሲማል 0.3 ሲያካፍሉት ሽያጭህ ጋር ይደርሳሉ:: ይህ እኮ ደረሰኝ የቆረጠለት ነው:: ያልቆረጠለት አምስት እጥፍ እንቅስቃሴ አለው ብለው አዋክበው በቀጣይ ዓመት አጭ^በርባሪ ተብለህ ልትቆለመም ትችላለህ:: ቢሆንም ቢሆንም ሥርዓት የያዘ ድርጅት ከፈለጋችሁ ሁለት ይኑራችሁ:: አንደኛው ዘመኑን እየዋጀ በመዋቅር ይሂድ:: ነባሩ እንደ ካራቺና ሌጎስ ባለበት ትቶ አቡጃና ኢስላማባድ መመሥረት ነው:: ____ እንዲህ እንዲህ ያሉ የኑሮ በዘዴ ትምህርቶችን ከፈለጋችሁ AK ዓርባ ሰባት ላይ የዱዓ ይዛችሁ ብቅ በሉ::

አሚርነት መጣሁልሽ
አሚርነት መጣሁልሽ

መሪ ስትሆን ሕዝቡን አንድ የሚያደርግ ባለሥልጣን ስታገኝ አባርረው:: በጥሩ ቀርቶ በመጥፎ ካስተባበረ ጠላ-ትህ ነው:: የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ምእመኑን በአንድ የተቃውሞ አጀንዳ ሲያሰልፍ ነው የቆየው:: ምሳሌ:- ታርጋ ሁሉንም ሾፌር ይመለከታል:: ስለዚህ የማይተባበር የለም:: So divide and mis-rule (ቸርችረህ ሽጠው) ነው የሚተገበረው:: ቅድሚያ የቤት መኪና ብቻ ቢል ... ምእመኑ በብሔ^ር ማለቴ በታርጋ ተከፋፍሎ አይተባበርም ነበር:: ከዚያ ዓመት ጠብቆ ታክሲ ብቻ ይቀይር ይላል:: ጫጫታ ሲነሳ ነዳጅ ተደጎመ ብሎ 80 ሳንቲም ይቀንሳል:: ወር ጠብቆ 60 ሳንቲም ይቀንስና ከሁለት ወር በሗላ 4 ብር ጨምሮ ያካክሳል::

ደስ የሚል ዜና ነው:: ኢትዮጵያ ግዙፍ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ገንብታለች:: ትኩረቴም መጽሓፎቼም ወርቁ ላይ ናቸው:: 1944 ላይ አሜሪካ ዓለምን ያቸነፈችው በወርቅ ክምች ነበር:: 1971 ላይ ካ^
ደስ የሚል ዜና ነው:: ኢትዮጵያ ግዙፍ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ገንብታለች:: ትኩረቴም መጽሓፎቼም ወርቁ ላይ ናቸው:: 1944 ላይ አሜሪካ ዓለምን ያቸነፈችው በወርቅ ክምች ነበር:: 1971 ላይ ካ^ደች:: ብዙ ሀገራት ከአሜሪካን ዶላር ተጽእኖ ለማገገም የቻሉት በወርቅ ነው:: ዓለም ሁሉ ወርቅ ወርቅ እያለ ነው:: ለ BRICS መገበያያ ወርቅን እንደ ደጋፊ ሀብት ቀርቧል:: ለዚህም ብሔራዊ ባንክ ወደ CBDC እየሄደ ነው:: ስለ CBDC በመ-ገንዘብ ላይ በስፋት ቢብራራም በድምጽ ማብራራት ይፈልጋልና ወይ ቴሌግራም ወይ ቲክቶክ ላይ እንገናኛለን::

አንዳንዴም ቲክ እና ቶክ ላይ መከሰት ያስፈልጋል በሚለው 👇🏼👇🏼 https://vt.tiktok.com/ZSbppgv4m/

ከላይኩ ኮሜንቱ በለጠ::
ከላይኩ ኮሜንቱ በለጠ::

እንደ ሀገር የድህነታችን ዋነኛ ምንጭ የተፈጥሮ ሀብት ማነስም መብዛትም ... መጥፎ መንግሥት መኖር አለመኖር ... ሥራ መጥላታችን አለመጥላታችን ብቻ አይደለም:: ከዚህ የሚከፋና ለመቀየር ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍል የፋይናንስ ፒራሚድ አለ:: ብዙ ቡና እና ወርቅ አመረትን እንበል:: ከዚያ የተሻለ ማሽን ብንፈልግ በምን እንገዛዋለን? -> በአሜሪካን ዶላር:: እኛ ልናትመውም ልንቆጣጠረውም አንችልም:: ስለዚህ ሳንወድ በግድ አሜሪካንን እንለማመጣለን:: መንግሥታችንን ያለ እነርሱ ውክልና መምረጥ አይታሰብም:: የተመረጠውም ውልፍት ካለ .. አያድርም:: ካደረም አይውልም:: ልክ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዐብይ ላይ ቢተብት ማለት ነው:: የትግ^ራዩ የደፂ ትእቢት በዓብይ ላይ እና የዓብይ ትእቢት በአሜሪካ ላይ ይለያያሉ:: ደፂና ዐብይ ሊሸናነፉ ይችላሉ:: ያው አለቃ-አሜሪካ ነች የምታጫውታቸው:: አሜሪካንን ግን ማን ያጫውታል ቢሉ ያው ፈጣሪ ብቻ ነው:: እኛ እንደ ሀገርም እንደ ግለሰብም ይህንን ሲስተም እና አቅማችንን ከግምት ያስገባ እንቅስቃሴ ነው ማድረግ ያለብን:: (ለዚህም መ-ገንዘብ ፎርሙላዎችን propose አድርጓል)::

Hasen Injamo - Статистика и аналитика Telegram-канала @haseniye