cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

በዚህ የንጽጽር አደባባይ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክታት የተገለጸው እውነት ሲፈጸምና ይፈጸም ዘንድ በመላው ዓለም ሲንቀሳቀስ የሚከሰቱ ጉዳዮችን እናቀርባለን ! ስለእምነታችን እንማማራለን ! ስለመልዕክታቱ እንነጋገራለን ! ➝ ይህ የአልፋና ዖሜጋ ( @christian930 ) ገጽ ቅርንጫፍ የንጽጽርና የመማሪያ ገጽ ነው።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
4 681
Obunachilar
-324 soatlar
+107 kunlar
+13330 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🟢🟡🔴 ሐምሌ 6 | የእኚኝ የከበሩ አባቶቻችን የዕረፍት በዓል ነው፨ 🌿 ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ ከጴጥሮስ ጋር አልዋሕ ወደምትባል ቦታ ሄዶ በአትክልተኝነት ተሸጦ ወንጌልን ሰበከ። የውሻ ፊት ያላቸው (ገጸ ከለባት) እየታዘዙለት በብዙ ሀገራት ወንጌልን ሰበከ። በኋላም የከሃዲው ንጉሥ የአግሪጳን ሚስትም ትምህርቱን ሰምታ በጌታችን አመነች፡፡ ንጉሡ አግሪጳም በዚህ እጅግ ተቆጥቶ ቅ/በርተሎሜዎስን ብዙ ካሠቃየው በኋላ አሸዋ በተሞላ ትልቅ ከረጢት ውስጥ ከቶ ከነሕይወቱ ባሕር ውስጥ እንዲጥሉት አደረገ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን አውጥተው በክብር ቀብረውታል፡፡ 🌿 ጳውሎስ የተባለ #ቅዱስ_መርቄሎስ ይህም ከ72 አርድእት ውስጥ ነው። እርሱም ሐዋርያትን ያገለገለ፣ ወንጌልንም ለመስበክ ከእነርሱ ጋር የሔደ፣ የቅ/ጴጥሮስን መልእክቶች ያደረሰ ነው። ከእርሱም በመከራው ኹሉ አልተለየም። ቅ/ጴጥሮስም በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ይህ ረድእ መርቄሎስ መጥቶ ከመስቀል ላይ አወረደው። በከበሩ ልብሶችም ከሽቱ ጋር ገነዘው። በሣጥንም አድርጎ ከምእመናን በአንዱ ቤት አኖረው። የጴጥሮስ ደቀ መዝሙርም እንደሆነ በኔሮን ዘንድ ወነጀሉት። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውነተኛ አምላክ እንደሆነ ታመነ። ስለዚህም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ገረፈውም ዘቅዝቀው ሰቅለውም ከበታቹ ጢስን አጤሱበት። ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኔሮን እንዲገርፉትና እንደ መምህሩ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ። የሰማዕታትንና የሐዋርያትን አክሊል ተቀበለ። 🍀 ጌታችን ተገልጦላቸው በፍቅር የተወጋ ጎኑን በእጃቸው እንዲዳስሱ የፈቀደላቸው፣ ምጽዋትን ከሰጡ በኋላ ሌላ የሚመጸውቱት ቢያጡ እርቃናቸውን እስኪቀሩ ድረስ የለበሱትን ልብሳቸውን እያወለቁ ለነዳያን የሚሰጡ መፍቀሬ ነዳያን #አባ_ዘግሩም ዕረፍታቸው ነው፡፡ T.me/Ewnet1Nat
Hammasini ko'rsatish...
8👍 4
ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት ? በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት እና መግለጫ ክፍል - 4 ( ሀ )
Hammasini ko'rsatish...
ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_ተዋሕዶ_ኦርቶዶክስ_ማን_ናት_ትምህርት_ክፍል_4_1.mp326.16 MB
ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_ተዋሕዶ_ኦርቶዶክስ_ማን_ናት_ትምህርት_ክፍል_4_2.mp327.63 MB
8
ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት ? በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት እና መግለጫ ክፍል - 4 ( ለ )
Hammasini ko'rsatish...
ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_ተዋሕዶ_ኦርቶዶክስ_ማን_ናት_ትምህርት_ክፍል_4_2.mp327.63 MB
Photo unavailableShow in Telegram
🟢🟡🔴 | ሐምሌ 5 የከበረ መልአክ #ቅዱስ_ሳቁኤል የተሾመበት መታሰቢያ በዓሉ ነው። ይኽም መልአክ በሞት መልአክ ላይ የሰለጠነ፣ መልአከ ሞትን የሚያዝዝ ኃያል ነው። እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት የሰው ነፍስ ስትወጣ መልአከ ሞት የሚያሸሽ፣ የሚያዝዝ ነው። እንዲሁም፦ ፩. ጻድቃን ነፍሳቸው ልትወጣ ስትል በጎን ኾኖ የሚያጸና፣ ፪. ቅዱሳን ነፍሳቸውን ከሥጋቸው የገነትን ተክል መዓዛ በማሸተት የሚያስወጣ፣ ፫. በመላእክት ሠራዊት ዝማሬ ነፍሳቸውን የሚያሳርግ ብርሃናዊ መልአክ ነው። ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት ሲያርፍ ቅዱስ ሚካኤል እና ቅዱስ ገብርኤል መቃብሩን ሲያዘጋጁ ይኽ ቅዱስ መልአክ ሳቁኤል በድኑን ይዞ የሔደው ነው። ወር በገባ በ5 ቀን አስቡት፤ ዘክሩት። በረከቱ ትድረሰን። ▬ ▬ ▬ #ሰላም_ለራጉኤል_ወለሳቁኤል፤ ለአፍኒን ወለራሙኤል እለ የዐውዱ መንበሮ ለልዑል። ❮ ትርጉም ❯ የልዑል ዙፋኑን ለሚዞሩ ለራጉኤልና #ለሳቁኤል፤ ለአፍኒንና ለራሙኤል ሰላምታ ይገባል፡፡ #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ (ተአምኆ_ቅዱሳን) t.me/Ewnet1Nat ✨🍀✨🍀✨
Hammasini ko'rsatish...
45👍 6😭 2
Photo unavailableShow in Telegram
🟢 🟡 🔴 | ሐምሌ 5 #_ቅዱስ_ጴጥሮስ_ሊቀ_ሐዋርያት የዮና ልጅ ስምዖን ጴጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው። ይሔውም ዓለት (መሠረት) እንደ ማለት ነው። በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ አድጎ ሚስት አግብቶ ዕድሜው 56 ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው። በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ፣ በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል። ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል። (ማቴ. 16፥17፣ ዮሐ. 21፥15) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው ስሕተት ንስሐ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል። ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በኋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል። ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል። በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል። አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል። እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል። የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ። ቅዱስ ጴጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ66 ዓ/ም የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው። "እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም" አላቸው። እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል። በበጎ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል። በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ 88 አካባቢ ደርሶ ነበር። የቅዱስ ጴጥሮስ መጠሪያዎች፦ 1. ሊቀ ሐዋርያት 2. ሊቀ ኖሎት (የእረኞች / ሐዋርያት አለቃ) 3. መሠረተ ቤተ ክርስቲያን 4. ኰኵሐ ሃይማኖት (የሃይማኖት ዐለት) 5. አርሳይሮስ (የዓለም ሁሉ ፓትርያርክ) ◦🌿◦🌿◦🌿◦
Hammasini ko'rsatish...
26👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
🟢 🟡 🔴 | ሐምሌ 5 #ቅዱስ_ጳውሎስ_ሐዋርያ የቤተ ክርስቲያን ብርሃኗ #ቅዱስ_ጳውሎስ ከነገደ ብንያም ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት፣ ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር። ጌታ በደማስቆ ጎዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት ምርጥ ዕቃ አደረገው። ይህ የሆነው በ42 ዓ/ም ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር። ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ። ጨው ሆኖ አጣፈጠ። ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም፣ እስከ እልዋሪቆን (የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ። ስለ ወንጌል ተደበደበ፤ ታሠረ፤ በእሳት ተቃጠለ። በድንጋይ ተወገረ፣ በጦር ተወጋ። በአፍም በመጽሐፍም ብዙ አገለገለ። በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ። ለ25 ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ። እርሱን የመሰሉ እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ፣ በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል። ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል። ልክ ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ማርቆስን እንዳገዘው። የቅዱስ ጳውሎስ መጠሪያዎች፦ 1. ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ) 2. #ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ) 3. #ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ) 4. #ብርሃነ_ዓለም 5. #ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ) 6. #የአሕዛብ_መምሕር 7. #መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ) 8. #አእኩዋቲ (በምስጋና የተሞላ) 9. #ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ) 10. #መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን) 11. #መርስ (ወደብ) 12. #ዛኅን (ጸጥታ) 13. #ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምህርትን ከአንደበቱ ያፈለቀ) 14. #ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ / ባሕር) 15. #ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ) . . . እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን። ከበረከታቸውም ያድለን። ◦🌿◦🌿◦🌿◦
Hammasini ko'rsatish...
24👍 1
ስለ (ፋይዳ) ብሔራዊ መታወቂያ {National ID} (ከዚህ በፊት የተከሰተ የኮቪድ ክትባትና አንዳንድ ከጽዋ ማኅበራት መታገድ እንደነበሩ ይታወሳል) ለሁሉ ነገር ለማትፈልጓቸው ነገሮች አስገዳጅ ነገር እስካልመጣ ድረስ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እንደ እንደዚህ አይነት ነገሮች ውስጥ ባትገቡ መልካም ነው እንላለን። ግን አስገዳጅ ኾኖ ካቅም በላይ የሚኾኑ ነገሮች ሲመጡ  የዛን ሰዓት ፥ እንግዲህ የምንጠብቀው የቸሩ መድኃኔዓለምን የተስፋ ቃል ይዘን ነውና የምንጠብቀው እግዚአብሔር ኹሉን ነገር በሰዓቱና በጊዜው እንደሚያከናውነው ስለምናምን፥ አስገዳጅ ከኾነ ምንም ማድረግ አትችሉም። እነሱ "አድርጉ፣ አውጡ፣ ግዴታ ነው" ብለው በሚያስገድዱበት ጊዜ እናንተ ተግባራዊ ብታደርጉት እናንተ ላይ የሚያመጣው አንዳች ጉዳት የለም። እናንተ እስከ መጨረሻው ድረስ አናደርግም ብላችሁ እስከ መጨረሻው ጥግ ድረስ መሔድ መልካም ነው። ከአቅማችሁ በላይ ከኾነ ግን በምትወስዱት ማንኛውም የራሳችሁ የኾነ አካሔድ እግዚአብሔር እናንተን አይጠይቅም። ...  ግዴታ ከኾነ ይኼ፥ በዛ ሂደት ውስጥ መግባታችሁ ፍጹም እናንተን ሊያስወቅሳችሁ አይችልም ይኼ። ኃላፊነቱ ስለ'ናንተ ነፍስ ስለ የትኛውም ስለ አኗኗራችሁ ስለ ኹሉ ነገር ሳትፈቅዱ ያደረጋችሁት ነውና ሰጪው ነው ኃላፊነቱን የሚወስደው። እና ያው ይኽ ሂደት እንደሚታወቀው የማን አሠራር እንደኾነ ግልጽ ነው። ...  በዘመናዊነት ስም የሚመጣ ዲያቢሎሳዊ አሠራር እንደኾነ ግልጽ ነው። ይኼ ምንም አይዋሽም። (ራዕ 13፥16) በግልጽ እግዚአብሔር አስቀምጦታል። ጊዜውና ዘመኑ መፈጸሙን ማለቁን፣ ያልተፈጸመ ማንኛውም ትንቢት እንደሌለ  የምትገነዘቡበት ሂደት ይኼ ነው። ስለዚህ አስገዳጅ ኾኖ ይሄ ሂደት ውስጥ የገባችሁ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች 'ከጽዋ ማኅበራት ትታገዳላችሁ' የሚል መመሪያ የለንም፤ ወደፊትም አይኖረንም። እንድታውቁ እንፈልጋለን። በፍጹም ይኼ አይደረግም! እና አስገዳጅ ኾኖብናል ስትሉ ይኼንን አካሔድ ይኼንን እርምጃ መሔድ ትችላላችሁ። የራዕይ ዮሐንስ 20 ማሳሰቢያ ሐምሌ 1፥ 2016 ዓ.ም ከ42ኛው ደቂቃ ጀምሮ የተቀነጨበ
Hammasini ko'rsatish...
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

🟩 🟨 🟥 ማሳሰቢያ ከራዕይ ዮሐንስ 20 | ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ብቻ!  ሐምሌ - 1 - 2016 ዓ.ም

29👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
በቀኑ 90 አዳዲስ የአዕምሮ ጤና እክል ያለባቸው ታካሚዎች ወደ አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ይመጣሉ ተባለ የአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተጠናቀቀዉ የ2016 በጀት ዓመት ለ135 ሺ ለሚደርሱ ታካሚዎች በተመላላሽ ህክምና ለመስጠት እቅድ ይዞ እንደነበር ለብስራት የተናገሩት የሆስፒታሉ የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አብዩ የኔአለም ከእቅዱ ውስጥ 114 ሺ614 ታካሚዎችን በተመላላሽ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማድረጉን አስታዉቀዋል፡፡ የአዕምሮ ጤና ህክምና  ፈላጊዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን ያስታወቀው ሆስፒታሉ ከአንድ አመት በፊት በቀን 30 አዳዲስ የአእምሮ ጤና ፈላጊዎች ወደ ሆስፒታሉ ይመጡ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ይሄ ቁጥሩ ከእጥፍ በላይ ጨምሮ በቀን 90 አዳዲስ የአዕምሮ ጤና ችግር ያጋጠማቸው ታካሚዎች ሆስፒታሉን ይጎበኛሉ ተብላል።ሆስፒታሉ በቀን 600 ለሚሆኑ ታካሚዎች ህከምና እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል። በሌላ በኩል ሆስፒታሉ ሊያሳካቸው ከያዛቸው አገልግሎቶች አንዱ የአስተኝቶ ህክምና አገልግሎት ጥራት ማሻሻል ሲሆን በ12 ወራት 1ሺ 135 ለሚሆኑ ታካሚዎች አገልግሎቱን በአስተኝቶ የአእምሮ ህክምና መስጠት ችሏል፡፡በድንገተኛ ህክምና አገልግሎቱን ሆስፒታሉ  በ12 ወራት መጨረሻ ላይ ለ 3931 ታካሚዎች አገልግሎቱን መስጠት መቻሉን አቶ አብዩ ጨምረው ለብስራት ሬዲና ቴሌቪዥን  ተናግረዋል፡፡ ሆስፒታሉ አሁን ላይ 239 አልጋዎች ያሉት ሲሆን በተኝቶ፤ በተመላላሽ፤ በድንገተኛ ህክምና፤ በጭንቅላት ምርመራ (EEG)፤ በኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምና (ECT)፤ በህፃናት የአዕምሮ ህክምና ፤ ከህግ ጋር የተያያዘ የአዕምሮ ህክምናና ምርመራ (ፎረንሲክ)፤ እንዲሁም የነርቭ ህክምናዎችን ጨምሮ እየሰጠ የሚገኝ አንጋፋ ሆስፒታል ነው። ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😭 9👍 4👏 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.