cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

በዚህ የንጽጽር አደባባይ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክታት የተገለጸው እውነት ሲፈጸምና ይፈጸም ዘንድ በመላው ዓለም ሲንቀሳቀስ የሚከሰቱ ጉዳዮችን እናቀርባለን ! ስለእምነታችን እንማማራለን ! ስለመልዕክታቱ እንነጋገራለን ! ➝ ይህ የአልፋና ዖሜጋ ( @christian930 ) ገጽ ቅርንጫፍ የንጽጽርና የመማሪያ ገጽ ነው።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
4 378
المشتركون
+524 ساعات
+327 أيام
+10130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿  ✤ 🌿 ✤ ✤ ••┈┈•• በመስቀሉ ሰላምን አደረገ ••┈┈•• ✤ #ቀዳሚት_ሥዑር (#ሥዑር_ቅዳሜ) እግዚአብሔር ሥነ ፈጥረትን ከመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት ዅሉ፣ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው አምላካችን ክርስቶስ በከርሰ መቃብር አርፎባታል፡፡ (ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (በሰንበት አይጾምም ግን የጾም ቀን በመኾኗ) "የተሻረች - ሥዑር" ለማለት ነው። የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያትና ሌሌችም የጌታ ወዳጆች ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ፥ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡ #_ለምን_ቄጠማ_እናስራለን? ቅዳሜ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ ‹‹ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፤ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ፥ መሠረተ›› እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡ ምእመናን የምሥራች ቄጠማ ያድላሉ፡፡ ቄጠማው በኖኅ ዘመን በንፍር ውኃ ምድር በተጠለቀለቀች ጊዜ፤ አባታችን ኖኅ የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን ልኮ እርሷም ቄጠማን እንደ የምሥራች ምልክት በአፏ ይዛ በመመለስ፥ የውኃውን መድረቅ እንደተነገረችውና እንደተደሰተ ሁሉ (ዘፍ. ፱፥፩-፳፱) ‹‹በክርስቶስ ሞት፤ ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ፤›› ስንል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜ ጠዋት ቄጠማ ታድላለች፡፡ የምሥራች ተምሳሌት የኾነውን ቄጠማም፤ ከሲኦል ቃጠሎ ወደ ጥንተ ማኅደራችን ገነት መመለሳችንን  ለመመስከር በግንባራችን እናስረዋለን፡፡ ▸ አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ | t.me/Ewnet1Nat ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤
إظهار الكل...
«የራስ ቅል የሚሉት ስፍራ !!» 📌የአለቃ አያሌው ታምሩ ድንቅ ትምህርት፡፡ t.me/christian930
إظهار الكل...
إظهار الكل...
የእመቤታችን ማርያም ኃዘን

ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት የሚነበብ

20
      ✥ ••┈•┈•• ✞ ••┈•┈•• ✥ #ዘበእንቲአሃ_ለቤተክርስቲያን_ተጸፋእከ በውስተ ዐውድ ከመ ትቀድሳ በደምከ ክቡር ዘበእንቲአሃ ዝግሐታተ መዋቅሕት ፆረ ወተዐገሰ ምራቀ ርኩሰ እንዘ አልቦ ዘአበሰ #አምላክ_ዲበ_ዕፀ_መስቀል_ተሰቅለ። ❮ትርጉም❯ #ለቤተክርስቲያን_ብለህ ልትቀድሳት በደምህ በአደባባይ በጥፊ ተመታህ። ንጹሕ ክርስቶስ በአዳም ጥፋት ልትወቀስ በከንቱ ልትከሰስ አመላለሱህ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ ሁሉን ቻይ ሳለህ ምንም ማድረግ ሳይሳንህ በአይሁድ እጅ ተገረፍህ! ወዮ! ወሰን ለሌላት ትዕግስት ስለኛ ብለህ መከራ ተቀበልህ ምንም በደል ሳይኖርብህ አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉህ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ
إظهار الكل...
25👍 5
#በግብረ_ሕማማት ውስጥ የሚገኙ #እንግዳ_ቃላት_እና_ትርጉማቸው፦ በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ #ኪርያላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነው፡፡ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ" ማለት ነው፡፡ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ "አቤቱ ማረን" ማለት ነው፡፡ "ኪርያላይሶን" የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው "ዬ" ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ" ን ፈጥረው ነው፡፡ #ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፣ ማረን" ማለት ነው፡፡ #እብኖዲ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው፡፡ "እብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው። #ታኦስ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣ አምላክ" ማለት ነው፡፡ "ታኦስ ናይናን" ማለትም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነው፡፡ #ማስያስ፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ "መሲሕ" ማለት ነው፡፡ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነው #ትስቡጣ፦ "ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው። #አምነስቲቲ_ሙኪርያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ" ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡ ▰ ▰ ▰
إظهار الكل...
19👍 5
የእመቤታችን ማርያም ኃዘን በቅዱስ አባ ሕርያቆስ የተደረሰ
إظهار الكل...
የእመቤታችን ማርያም ሐዘን

ዓርብ በሦስት ሰዓት የሚነበብ

19👍 2😭 2
#የሕማማት_አርብ ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ #_ዕለተ_ስቅለት ❨የድኅነት ቀን❩ #_አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ! {ኦ እግዚኦ በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበን} #_ስገዱ_ጸልዩ_አልቅሱ ስለ ነፍሳት ኹሉ! ••┈•┈••
የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው፧ ምን ከንፈር ነው፧ ምን አንደበት ነው፧ የፍቍር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ፥ ልብ ይለያል፤ ኅሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል። #_የማይሞተው_ሞተ! ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ! ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ! [ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ]
••┈•┈•• ▸ አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ | t.me/Ewnet1Nat
إظهار الكل...
👍 5 1