قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Відкрити в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
910
Підписники
-324 години
-157 днів
+4830 днів
Архів дописів
♦️♦️♦️በፈገግታ ተገናኝተን በጥላቻ ለምን እንለያያለን?
📌ግን ለምንድነው የሰው ልጅ ሲገናኝ በፈገግታ፣ በደስታና በፍቅር የሚቀራርበው፤ ሲለያይ ግን ለመጠላላት ምክንያት፣ ለመከፋፈል ሰበብ፣ የተቃውሞ ቃል እና የቁርሾ ምክንያት ፈልጎ የሚሄደው?
📍ሲገናኝ እያንዳንዱ ሰው የሌላውን መልካምነት ይመለከታል፤ ፈገግታውን ያያል፣ መልካም ቃሉን ይሰማል፣ ውብ ጎኖቹን ያደንቃል። ጊዜ ሲያልፍ ግን የሰውን ጉድለት ማየት ይጀምራል፤ ከዚያም አንድ ትንሽ ስህተት ትልቅ ሆኖ ይታየዋል። የብዙ ዓመታት መልካምነት በአንድ ቅጽበት ይረሳል።
አሳዛኙ ነገር ግን መለያየቱ አይደለም፤ እንደ ጠላት መለያየቱ ነው።
📌አንድ ቀን በፍቅር የተገናኛችሁ ሰዎች ለምን በጥላቻ መለያየት አለባችሁን? አንድ ቀን የተዋደዳችሁትን ሰው ዛሬ ስለተለያያችሁት ለምን መጥፎ ሰው ማድረግ ያስፈልጋል?
📍አንዳንድ ሰዎች ከሕይወታችን ሊወጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ከሕይወታችን መውጣታቸው በልባችን ውስጥ ጠላት ሆነው እንዲቀሩ አያስገድደንም። መንገዳችሁ ቢለያይ፣ ልባችሁ አይለያይ። መገናኘታችሁ ቢያበቃ፣ ክብራችሁን አትጨርሱ።
👌ሰውን በመልካምነት ማግኘት ብቻ ትልቅ ነገር አይደለም፤ በመልካምነት መሰናበትም የሰውነት ትልቅነት ነው።
📍እናም ከአንድ ሰው ስትለያዩ፣ ምክንያት ፈልጋችሁ እንዳትጠሉት፤ ያሳለፋችሁትን መልካም ጊዜ አስቡ። ያደረገላችሁን መልካም ነገር አስቡ። ካልቻላችሁም ቢያንስ ዝም ብላችሁ በሰላም ተለያዩ።
🗳ምክንያቱም መለያየት የግድ ጥላቻን አይፈልግም፤ አንዳንድ ጊዜ መለያየት ብቻ በቂ ነው።
ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Repost from ፍቅር እስከ ጀነት | ራማስ አል ሀናኒ
1⃣ኡሙ ረያን
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13519
2⃣ኡሙ ሀፋሳ
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13583
3⃣ሰአዳ ኢብራሂም
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13591
4⃣ኡሙ አቲካ ሱመያ
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13637
5⃣ኡሙ ሀቲም መኪያ
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13523
6⃣ኡሙ ፈውዛን ሶፊያ ቢንት አብደሏህ
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13513
7⃣ኡሙ አፊፍ
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13605
8⃣ቢንት ዩሱፍ
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13681
9⃣ረምላ ኡሙ ፈውዛን
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13527
1⃣0⃣ቢንት ጀማል አል አሰሪ
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13687
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ሱረቱል-ካህፍ
🎙ቃሪዕ ሚስባህ ሳኒ
https://t.me/Misbah_sain
https://t.me/Misbah_sain
Repost from ስለ ዲናችን
يارب مع فجر يوم الجمعة ارزقنا من فضلك وسخّر لنا كل ما نتمناه ، يسّر لنا امورنا واشرح لنا صدورنا وافتح لنا ابواب رزقك ، وأكرمنا بفيض نعمك ورحمتك يا كريم🍃.
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎችን እንተግብር
➖➖➖➖➖➖➖
↩️💎 سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿
➊ 💎الغسل
➋💎 الطيب
➌ 💎السواك
➍💎 لبس الجميل
➎💎 قراءة سورة الكهف
➏💎 التبكير لصلاة الجمعة
➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
➊ 🌺መታጠብ
➋ 🌺ሽቶ መቀባት
➌🌺 ሲዋክ መጠቀም
➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ
➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን
➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት በግዜ መጣድ
➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
🌺በሰለዋት በዚክር ያውለን ያረብ
ﷺ 🌹 .................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹
ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹
በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
🌿 የሙስሊሞችን ጉዳይ ችግር ማቃለል ማስወገድ የመልካምነት ታላቅ በር ነው።
አላህ ሱበሀነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሎናል፦
﴿وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴾
«መልካምን ሥሩ፤ ምናልባትም ልትድኑና ነጃ ልትወጡ ትችላላችሁ።»
🤍 የሰውን ጉዳይ ማስተናገድ ትንሽ ሥራ አይደለም…
አንድ ሰው በችግር ውስጥ ሆኖ ሲመጣብህ፣ ምናልባት በእጅህ ያለው ነገር ትንሽ ይመስልህ ይሆናል፤ አንተ ግን ለእሱ ያደረግከው ነገር በሕይወቱ ትልቅ ቦታ ሊኖረው ይችላል።
አንድ ሰው በጭንቀት ላይ እያለ በአንድ ቃል ማጽናናት፣
●አንድ ሰው ጉዳዩን ማስፈጸም፣
●የሚያስፈልገውን ሰው ማገዝ፣
●በችግሩ ጊዜ ከጎኑ መቆም፣
●የሚያውቀውን መረጃ መንገር፣
●አንድ የተዘጋ በር እንዲከፈትለት ምክንያት መሆን…
●እነዚህ ሁሉ የሙስሊም ወንድማማችነት ምልክቶች ናቸው።
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«المُسْلِمُ أَخُو المُسْلِمِ، لَا يَظْلِمُهُ وَلَا يُسْلِمُهُ، وَمَنْ كَانَ فِي حَاجَةِ أَخِيهِ كَانَ اللهُ فِي حَاجَتِهِ، وَمَنْ فَرَّجَ عَنْ مُسْلِمٍ كُرْبَةً فَرَّجَ اللهُ عَنْهُ بِهَا كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ القِيَامَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ اللهُ يَوْمَ القِيَامَةِ.»
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
🌿 “የወንድሙን ፍላጎት ለማሟላት የሚጥር ሰው አላህ ፍላጎቱን ያሟላለታል”
ይህ ቃል ልብን የሚነካ ታላቅ ተስፋ ነው።
እኛ የሰውን ጉዳይ ስናስተናግድ እንዲህ እንበል፦
“ይህን ሰው ለማገዝ አላህ ምክንያት አድርጎኛል።”ከዚያ የምናገኘው ክብር ወይም ምስጋና ሳይሆን፣ የአላህ ውዴታ ይሁን የምንፈልገው። ሰዎች አመስግነውን ይሆናል፤ አላመሰገኑንም ይሆናል። ሰዎች አስታውሰውን ይሆናል፤ ረስተውንም ይሆናል። አላህ ግን የሠራነውን መልካም ሥራ አይረሳም።
● አንድ ሰው የእኛን እርዳታ ሲፈልግ አንተ የምታየው ችግሩን ብቻ ነው፤ አላህ ግን የሚያየው የአንተን አቋም ነው።
ለዚህ ነው አንዳንድ ጊዜ ትንሽ የምናደርገው ነገር በአላህ ዘንድ ታላቅ የሚሆነው።
●አንድ ሰው እንባውን እንዲያብስ ምክንያት ሆነህ ሊሆን ይችላል።
●አንድ ቤተሰብ ችግሩን እንዲያልፍ ምክንያት ሆነህ ሊሆን ይችላል።
●አንድ ወንድም ተስፋ እንዳይቆርጥ አንተ ምክንያት ሆነህ ሊሆን ይችላል።
እነዚህን መልካም ስራዎች አታቃልል።
ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እንዳስተማሩን፣ የሰውን ጭንቀት ማስወገድ እንኳን በቂያማ ቀን ከጭንቀቶች አንዱን እንዲያስወግድልን ምክንያት ይሆናል።
● ወንድማማችነት የሚታየው በደስታ ጊዜ ብቻ አይደለም…
ሰው ሲደሰት ከእሱ ጋር መደሰት ቀላል ነው። ነገር ግን ሲወድቅ እጁን መያዝ፣ ሲጨነቅ ማጽናናት፣ ሲደክም መደገፍ ነው እውነተኛ ወንድማማችነት።
ሰዎች በሚያስፈልጉን ጊዜ ብቻ አንቅረባቸው፤ እኛም ሌሎችን በሚያስፈልጋቸው ጊዜ እንቅረብ።
የሙስሊም ወንድምህ ጉዳይ ካለው፣ “እኔ ምን አገባኝ?” ከማለት በፊት “ምን ላግዘው እችላለሁ?” ብለህ አስብ።
🌿 ምናልባት ያ ትንሽ እገዛህ በአላህ ዘንድ የተቀበለች ትሆናለች።
🌿 ምናልባት ያ የሰጠኸው ጊዜ ነገ አንተ በችግር ላይ ስትሆን የምትፈልገው ምሕረት ይሆናል።
🌿 ምናልባት የሰውን ጭንቀት ያስወገድክበት ቀን አንተም ከቂያማ ቀን ጭንቀት እንድትወጣ ምክንያት ይሆናል።
● እንግዲህ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በቻልነው አቅም እንርዳ…
● ጉዳያቸውን እናስፈጽል፣
● ችግራቸውን እናቅልል፣
● እንባቸውን እናብስ፣
● ምስጢራቸውን እንጠብቅ፣
● ነውራቸውን እንሸፍን፣
● በችግራቸውም ጊዜ ከጎናቸው እንቁም።
ምናልባት ነገ እኛ የምንፈልገው እርዳታ ዛሬ ለሌላ ሰው የሰጠነው እርዳታ ትሆናለች።
⚠️ አላህ ሆይ! የሙስሊሞችን ጭንቀት አስወግድ፣ ጉዳያቸውን አስተካክል፣ እኛንም የተጨነቁትን ከሚያጽናኑ፣ የተቸገሩትን ከሚረዱ፣ የወደቁትን ከሚያነሱ ባሮችህ አድርገን። እኛ የሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት ስንሮጥ፣ አላህ የእኛን ፍላጎት የሚያሟላልን ጌታ ነው።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy«تُكفى همك، ويُغفر ذنبك»
يقول ابن باز رحمه الله:
إذا جعل الإنسان وقتًا يصلي فيه على النَّبي ﷺ كثيرًا، فالله -جلَّ وعلا- يأجره على ذلك، والحسنة بعشر أمثالها، إلى ما لا يحصى من الفضل، وإذا صرف ذلك الوقت كله في الصلاة على النبي ﷺ؛ حصل له هذا الفضل: «تُكفى همّك» يعني: يكفيك الله همك «ويُغفر ذنبك».
اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد، وعلى آله وصحبه أجمعين.
Repost from مركز الإمام أحمد الإسلامي
ዛሬም - በአሏህ ጥበቃ - ኢኽዋኖችን የምንጠላ ከነሱም መንገድ እጅጉን የራቅን የሰለፎቻችን ተከታዮች ነን !
አሏህ ከሸራቸው ይጠብቀን !
https://t.me/MerkezulimamiAhmed
«አንዳንድ ልቦች እንደ ዝናብ ጠብታ ናቸው፤በፅጥታ መጥተው በነፍስ ውስጥ የማይጠፋ ሕይወትን ትተው ያልፋሉ።»
=
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ባንዲራሽ ከፍ ይበል!!
ክብርና ዝናሽ ለአለም ይነገር፡
የነብዩ ኢስማኢል የሙሀመድ ሀገር፡
ግርማና ሞገስሽ የዑሁድ ተራራ፡
የነብዩ ወዳጅ ያ የጀነት ጎራ፡
የወህዩ መፍለቂያም ከአንች ጋር ነው ሒራ፡
ያለሽ ተአምራት አያልቅም ቢጠራ፡
በዝርዝር በወሳ ቢተረክ ቢወራ።
----------------------------------
ሶፋና መርዋ ደግሞም ሙዝደሊፋ፡
ሐጅ መተግበሪያው እንደት ነው አረፋ፡
በርቀት እያየሁ እያፈሰስኩ እንባ፡
ሀጀረል-አስወዱ ሆድን እያባባ፡
ቅዱሱ ቦታችን እንደምነው ከዕባ፡
-------------------------------------
ባንዲራሽ ከፍ ይበል!!
ለወደደሽ መልካም ለጠላሽ ሴራ አፍራሽ፡
የተዐምር ሀገር አምረሽ የተሰራሽ፡
ሁሌ ትርፋማ ሁኝ አይታይ ኪሳራሽ፡
በሔደሰሽበት ሁሉ ከፍ ይበል ባንድራሽ፡
የጠላሽ ይጠላ ሽንፈትን ይቀበል፡
ሁሌም በሔድሽበት ባንድራሽ ከፍ ይበል፡
በኑረዲን አል አረቢ
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
قال الإمام بن القيم رحمه الله
أغبى الناس من ضل في أخر سفره وفد قارب المنزل
ከሰዎች ይበልጥ ሞኝ ማለት (ጉዞ ወቶ) በጉዞዉ መጨረሻ ላይ ወደ መዳረሻዉ ከቀረበ በኋላ መንገድ የሳተ ግለሰብ ነዉ ::
አል ኢማም ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸዉ
الفوائد ١٠٧
አሏህ የመንገዳችንን መጨረሻ ያሳምረዉ
.
ልክ ማለት ምን እንደሆነ ሲገባህ ልክ ማለፍ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትረዳለህ‼️
🎤 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
Repost from N/a
ማንኛውም አይነት ከሸሪዓ ጋር የማይጋጩ የስራ
ማስታወቂያዎችን በአንድ ቻናል ላይ በነጻ
ማስተዋወቅ እንዲሁም ስራ ለማግኘት ከፈለጉ
Halal Jobsን ይቀላቀሉ!👇
🟢ከአረብኛ ቋንቋ ውጭ በሌላ ቋንቋ ኹጥበህ ማድረግ እንዴት ነው?
⏸ፈታዋውን ከሰጡት ዑለማዎች ውስጥ፡
አሸይኽ ሙቅቢል አልዋዲዒይ ረሂመሁላህ
አሸይኽ ናሲሩዲን አልአልባኒይ ረሂመሁላህ
አሸይኽ ሳሊህ አልዑሰይሚን ረሂመሁላህ
አሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን ሐፊዘሁላህ
⏸ፈታዋዎቹ ውስጥ ከሚገኙ ቁም ነገሮች ውስጥ፦
✏️የኹጥበህ መሰረቱ በአረብኛ ነው። የኢስላም መሰረታዊ ቋንቋም ነው።ሙስሊሞች ሁሉ ኢስላማዊ ቋንቋ ሊያውቁ ይገባል።
✏️አረብኛ ለማይችሉ አዳማጮች በቋንቋቸው መደረግ አለበት።
✏️አዳማጩ አረብኛ የሚችልና የማይችል ቅልቅል ከሆነ በአረብኛ ተደርጎ ይተረጎማል።
✏️ዋናው የኹጥበህ አላማ መልእክቱን ማብራራት ነው።
አላህ እንደተናገረው።
{وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا بِلِسَانِ قَوْمِهِۦ لِيُبَيِّنَ لَهُمْ ۖ فَيُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهْدِى مَن يَشَآءُ ۚ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ}
{በህዝቦቹ ቋንቋ እንጂ ከመልክተኛ ማንኛውንም በሌላ አልላክንም፡፡ለእነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ። አላህም የሚፈልገውን ያጠማል፡፡ የሚፈልገውንም ያቀናል፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡}
✏️ሰላት መስገድና ቁርዓን ቲላዋ ግን ከአረብኛ ውጭ አይቻልም። አይሆንም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
ስለ ተውሂድ የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ ➍🥉አከባቢ ሙሓደራወች❶ ተውሂድ ➋ ተውሂድ እና አህባሽ ❸ ተውሂድ እና ሽርክ እና ተቅዋ ➍ ተውሂድ እና ኢትዮጵያ ➎ ቅድሚያ ለተውሂድ ➏ ተውሂድ እና ላኢላሀኢለሏህ ➐ ተውሂድ እና ሽርክ ➑ ተውሂድ እና አሳሳቢነናቱ ❾ ተውሂድ አፍራሾች ❿ ስለ ተውሂድ ❶❶ ተውሂድ እናትሩፋት ❶➋ ለምን ተፈጠርን ❶❸ ስለ ተውሂድ አስፈላጊነት ❶➍ ተውሂድ እና ነብዩ ኢብራሂም ❶➎ ተውሂድ የመጀመሪያ ግደታ ነው ❶➏ ቅድሚያ ለተውሂድ ❶ ➐ ስለ ተውሂድ አንገብጋቢነት ❶➑ ተውሂድን አደራ አደራ አደራ ❶❾ ተውሂድ እና ሽርክ ➋0 ተውሂድ ሩብብያ ➋❶ ተውሂድ ወሳኝ ርዕሰ ነወ ➋➋ ተውሂድ እና ሽርክ ➋❸ ታላቁ አደራ ተውሂድ ➋➍ ተውሂድ የጀነት ቁልፍ ነወ ➋➎ ተውሂድ አሳሳቢነት እና ሽርክ አስከፊነት ➋➏ ተውሂድ ስትጣራ ቅጥል ይሰጥሃል ➋➐ ተውሂድ በአጭሩ ➋➑ የአማናወች አማና ተውሂድ ➋❾ ተውሂድ አሳሳቢነት ❸0 ቅድሚያ ለተውሂድ ❸❶ ተውሂድ የነብያቶች ሁሉ ጥሪ ነው ❸➋ ተውሂድ ሁሌም አድስ ሲያወሩት የሚጣፍጥ ❸❸ ተውሂድ ምንነት ❸➍ አሁንም ቅድሚያ ለተውሂድ ❸➎ ተውሂድ ከሁሉም እደሚቀደም ❸➏ ተውሂድ ቢያወሩት የማይጠገብ ❸➐ ተውሂድ እና የሀገራችን ❸➑ ዛሬም ነገም ቅድሚያ ለተውሂድ ❸❾ ለምን ቅድሚያ ለተውሂድ ➍0 ቅድሚያ ለአቂዳ ➍❶ ቅድሚያ ለተውሂድ ➍➋ ቅድሚያለተውሂድ ከሁሉም ነገር በፊት ➍🥉ለምን ቅድሚያ ለተውሂድ እንላለን ❓
🔶 የህዝብ ግርግር እንዳያታልለን!
👉የህዝብ ብዛትና ግርግር በፍፁም የ የሐቅ መለኪያ አይደለም። ሀቅ የሚለካው በማስረጃ እንጂ በጩኸትና በስብስብ አይደለም። ስለዚህ በሰው ብዛት እንዳንሸወድ ታሪክን ስንመለከት ብዙ ግርግሮችን አይተናል፦
1. የአብራርና የጀማል ግርግር
2.ስቴዲየም የሞላው የኢኽዋን ግርግር
3.የሚሊኒየም አዳራሽ ግርግር
4. #የዱናው የለተሞ ግርግር
5.የቡታጅራ የተብሊግ ግርግር
6.የአብሬትና የቃጥባሬ የሱፊያ ግርግሮች ታይተዋል። እነዚህ ሁሉም ግርግሮች መጥተው አልፈዋል።ዋናው ነገር በሀቅ ላይ መፅናት እንጂ የመንጋን ጩኸት መከተል አይደለም። መልዕክት በተፎካካሪዎችና በብዛት ለሚመኩ ሁሉ፦ በስብስባችሁ ብዛትና በደጋፊያችሁ ጩኸት የምትመኩ ወገኖች ሆይ! የሰው ብዛት የሀቅ ሚዛን ሆኖ አያውቅም። በሶሃቦች ዘመን እንኳን 12,000 ኸዋሪጆች በታላላቅ ሶሃቦች ላይ ተነስተው ነበር። ብዛታቸው ከሀቅ አላደረሳቸውም። በየዘመኑ ስንትና ስንት የጥመት አንጃዎች ብዙ ተከታይ ይዘው ብቅ ብለዋል፤ ሁሉም ከንቱ ሆነው ቀርተዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "ከዑመቴ ውስጥ ወደ 73 አንጃዎች ይሆናሉ፤ አንዷ ስትቀር ሁሉም የእሳት ናቸው።" ሶሃቦችም "እርሷ ማን ናት?" ብለው ሲጠይቋቸው፣ "እኔና ሶሃቦቼ በላዩ ላይ ያለንበት መንገድ ላይ የፀና ነው" በማለት መልሰዋል። ስለዚህ እውነተኛው የሀቅ መለኪያ ሊሆን የሚገባው፦
1.የነብዩንና ﷺ የሶሃቦቻቸውን መንገድ መከተል ነው።
2. ለእያንዳንዱ አቋም ከቁርዓንና ከሀዲስ የማያዳግም ማስረጃ ማቅረብ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው የሰው ብዛት፣ ጩኸትና ግርግር ሁሉ እንደ ጉም በኖ የሚጠፋ ጊዜያዊ ስሜት ብቻ ነው።
አላህ ሀቅን ሀቅ አድርጎ ያሳየን የምንከተለውም ያድርገን፤ባጢልንም ባጢል አድርጎ ያሳየን የምንርቀውም ያደርገን። አሚን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
⚠️ታላቅ የደእዋ እና የኒያ ፕሮግራም
የቤተሰቦቿን ህይወት ለመቀየር ብላ ስደት የወጣችው እህታችን ሀናን አህመድ በደረሰባት ከባድ የሆነ ህመም ከዚህ በፊት በመካ ሆስፒታል ሶስት ጊዜ ቀዶ ጥገና ያደረገች ሲሆን ከ25,000 ሪያል በላይ አውጥታለች አሁን ላይ ያለችበት ሁኔታ እየባሰባት ስለሄዴ ምንም መነካካት እንዴለለበት ዶክተሮቹ ስለነገሯት ህገወጥ ስለሆነች ወደ ሀገሯ ለመግባት የአየር ትኬት መቁረጫና 9,000 ሪያል የሰው እዳ ስላለባት የእኛን የእህትና ወንድሞቿን እርዳታ ትፈልጋለች ሁላችንም ከእህታችን ጎን በመቆም ለቤተሰቧቿ እናብቃት።
ተጋባዥ እንግዶቻችን
🎙ኡስታዝ ኸድር አህመድ ኸሚሴ
🎙ኡስታዝ አቡ ፈውዛን ዐብዱሽኩር
🎙ኡስታዝ አቡ ሂበቱላህ አልአሰሪ
🎙ኡስታዝ አቡ ሀሳን አሊይ ዩሱፍ
📖 ቲላዋ የሚጋብዘን :-
🎙ወንድም አቡ ሐይደር ዓልይ
ፕርግራሙን በድምቀት የሚመሩልን ወንድሞች
📣አቡ ሚሂ
📣አቡ ሁዘይፋ ሰኢድ
📣አቡ ሹራ አህመድ ካሳዬ
ቀን እና ሰአት ጁሙዐ ከምሽቱ ----
በኢትፕያ .🇪🇹ከ3.00 ጀምሮ
በሳውዲ. 🇸🇦.ከ9.00ጀምሮ
በዱባይ. 🇦🇪ከ.4.00ጀምሮ
ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት ቻናል:-👇👇
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
"የአመቱ ምርጥ ንግግር 15 cm በማይሞላው ፊቱ ላይ የሸሪዓ ህግ ሲይተገበር ሙስሊሙን #ለአብዮት ይቀሰቅሳል።"
ተወዳጁና ተናፋቂው ኡስታዛችን ኡስታዝ ሙሐመድ አህመድ ሙነወር (ኢብኑ ሙነወር) ሐፈዘሁላህ.
ቢያንስ ከራሳችን እንማር
~
መቼም እንደ ሰለፊያ ደዕዋ የጎንዮሽ ፍትጊያ እና የርስ በርስ መናቆር የበዛበት የለም። ይሄ አሳዛኝ እውነታ በየ ሃገሩ በሰፊው የሚታይ ነው። ጉዳዩ መተራረም ላይ ቢቆም ጥሩ ነበር። መናቆሩ ግን ከዚያ በብዙ ርቀት ያልፋል።
* አንዱ በሌላው ጉዳት፣ በሌላው ህመም፣ በሌላው ሞት እስከሚደሰት ይደርሳል።
* ከሱና ማስወጣት፣ ተብዲዕ መደራረግማ በሰፊው የተንሰራፋ ነው። ከእስልምና ለማስወጣት ዳር ዳር የሚልም አይጠፋም።
* ጉዳዩ በደንብ ስሜት እንደገባበት ከሚያጋልጡ ነጥቦች ውስጥ አንዱ መኮራረፉ ሶላት እስካለመከተል መድረሱ ነው። የባሱ ሰዎችን እየተከተሉ ትናንት አብረዋቸው የነበሩትን ግን በተለያዩ ማግስት ለሶላት እስከመሸሽ የሚደርሱ አሉ። በሱና ስም ስሜት መጋለብ!
* በሰላም ጊዜ ያልተወራ ነውር በተጋጩ ማግስት ይዘከዘካል። (ያው ውንጀላው ውሸትም ሊሆን ይችላል።)
* በሰላም ጊዜ ሲወዳደሱ እንዳልነበር ከግጭት በኋላ "እከሌ ጃሂል ነው" ማለት የተለመደ ነው።
* ንግግርን እየቆለመሙ መወንጀል፣ ያልተባለ መለጠፍ፣ ሰቅጣጭ ስድቦችን መሰዳደብ የተለመደ ነውር ነው።
* በአንድምታ (በላዚም) መክሰስ በስፋት አለ። "ላዚሙል መዝሀብ ለይሰ ቢመዝሀብ" የሚለው ነባር ቃዒዳ ተዘንግቷል።
* ረድ አድርጎ ማለፍ የሚባል አይታወቅም። ነጋ ጠባ መጨቃጨቅ፣ ሰዎችን በዚህ መጥመድ በስፋት የሚታይ ነው። አንዳንዶች የሚጠሉት አካል ጥፋት ላይ ሲወድቅ ለቀደመ የውሃ ቀጠነ ክሳቸው ማሳመኛ አገኘን ብለው ሰርግና ምላሻቸው ይሆናል። በማዘን ፋንታ ይቦርቃሉ። "ተመልሻለሁ" ቢባሉ እንኳ የማይዋጣቸው፣ ደጋግመው በዚያው ክሳቸው የሚቀጥሉ በተጨባጭ አሉ።
* ያለ ገደብ "እነ እከሌ ከኢኽዋን የከፉ ናቸው" እያሉ መወረፍ ጎልቶ ይታያል።
* የራስን ጅህልና ሸፍኖ ወይም የራስን ጃሂል አቅፎ ሌሎችን በጅህልና ማጣጣል ይጎላል።
* ውሸት በጣም በዝቷል። ያውም በሰው ክብር ላይ ለመረማመድ!! በውሸት እከሌ በጥቅም ተገዝቷል፣ እከሌ አክስዮን ገብቷል፣ እከሌ እንዲህ ሆኖ ነው፣ ... ማለት በብዛት አለ።
* የርስ በርስ ጥላቻው እስከ መደባደብ፣ አንዱ ሌላውን ለማጥፋት እስከ መሞከር ይደርሳል። እዚሁ በሃገራችን ውስጥ በስለት የተወጋጉ፣ በዱላ የተደባደቡ፣ በዚህ የተነሳ ወህኒ የገቡ፣ የውሸት ክስ እየለጠፉ ለፖሊስ አሳልፈው የሚሰጡ፣ ፈቃድ ከመንጠቅም በላይ ለባሰ አካል አሳልፈው የሰጡ፣ ... ብዙ አሳፋሪ ተግባሮች አሉ። ትዳር የፈረሰበት፣ ቤተሰብ የተለያየበት ብዙ አሳዛኝ ነገሮች አሉ።
የሚታዩትና የሚደርሱት ብዙ ናቸው። እነዚህን ነገሮች ባላነሳቸው እመርጥ ነበር። የሌሎች መሳቂያ፣ መሳለቂያ መሆን በጣም ያማል። ነገር ግን የአደባባይ ሐቅ ከሆነ በኋላ መመካከሩ እንጂ መሸፋፈኑ ፋይዳ አይኖረውም።
አይናቸው ላይ ባጠለቁት የልዩነት መነፅር በመመልከት የምፅፈውን ሃሳብ በቅንነት የማያዩት፣ አልፎም በሚፈልጉት መልኩ የሚመነዝሩት እንደሚኖሩ ይገባኛል። የችግሩ አንዱ መገለጫም ይሄው ነው። ቢሆንም ዝምታ መፍትሄ አይሆንም። ቢሆንም "ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርምና" የሌሎችን ውንጀላ በመስጋት ከመመካከር መራቅ አይገባም። "ብልጥ ከሌሎች ይማራል፤ ሞኝ ከራሱ ይማራል" ይባላል። የመጀመሪያውን ብስለት ባለማስተዋል፣ ራስን ባለመቆጣጠር አልፈነዋል። ቢያንስ ከራሳችን ድክመት ብንማር ጥሩ ነው። ከደረሱትና ከሚደርሱት እንማር። በምን መልኩ?
1. ወደራሳችን በጥልቀት እንመልከት። #ራስን_ጥሎ ሁሌ ሌሎችን ማሳደድ ኣኺራን ይጎዳል፣ ቡድንተኝነትን ያወርሳል። የልብ ድርቀትን ያስከትላል።
2. የዑለማኦችን አካሄድ የምንፈልገውን እየመረጥን ሳይሆን ወይም በሌሎች የተመረጠልንን ሳይሆን ከነፍሲያ ወጥተን ከሁሉም አቅጣጫ እንመልከት። ነጠላ ንግግሮቻቸውን ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ አፈፃፀማቸውንም እናጥና። የእውነት እኛ በምናደርገው መጠን ሰው ላይ በማክ * ፈርም ይሁን ተብዲዕ በማድረግ ላይ የተናጠል ፍርድ ለመስጠት ይቸኩላሉ ወይ? በጭራሽ!
3. በምናራምዳቸው እርምጃዎች ላይ የደዕዋችንን መስለሐ በሚገባ እናጢን። ደዕዋችንን የሚያሳጣን፣ መስጂዶቻችንን የሚያስነጥቀን ከሆነ ጩኸታችን ምን ፋይዳ አለው? አካሄዳችን የሰለፊያን ደዕዋ የሚያጠለሽ ከሆነ ወደድንም ጠላንም የጠላትን አጀንዳ እየፈፀምን ነው።
4. ከሱና ዑለማኦች ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ላይ አንገደብ። ይሄ አካሄድ አንዳንዶችን ተ0ሱብና ጉሉው ላይ ሲጥላቸው እያየን ነው። እውነታውን የማያምኑት ችግሩ ስለሸፈናቸው ነው።
5. ተዝኪየተ ነፍስ ላይ እናተኩር። ለችግሩ መስፋት አንዱ ትልቅ ሰበብ የተቅዋ፣ የወረዕ መሳሳት ነው። ሌሎች ላይ ዋሽቶ መክሰስ፣ ሳያረጋግጡ በግምት መወንጀል፣ በጥላቻ ድንበር ማለፍ፣ የራስን ነውር እየደበቁ ሌሎችን መናከስ፣ ... አላህን መፍራት እንደሌለ ወይም እንደሳሳ የሚያጋልጥ ነው። እና እራሳችንን አንርሳ።
6. አቅማችንን እንወቅ። ከቁመታችን በላይ የሆኑ ርእሶችን አናቡካ።
7. ወደ ኢስላም ጠቅልለን እንግባ። አኽላቅም፣ ዙህድም፣ ወረዕም፣ ሲራም፣ ተርጊብና ተርሂብም የኢስላም አካል መሆናቸውን ከምላስ ባለፈ በተግባር እናረጋግጥ። ሰለፎች ከነዚህ ነጥቦች አንፃር የነበሩበትን የላቀ ደረጃ እናጥና።
8. ሰው ተከትለን ገደል እንዳንገባ እንጠንቀቅ። በየመንደሩ የወደድኩትን ውደዱ፣ የጠላሁትን ጥሉ የሚሉ የሹም ዶሮዎች ይኖራሉ። እናስተውል! እነዚህ አካላት አብረውን ቀብር አይገቡም። እጃችንን ይዘው ሲራጥ አያሻግሩንም። እርቃናችንን ብቻችንን ለሒሳብ እንደምንቆም እናስብ። ነገ ከመመርመራችን በፊት ዛሬ ራሳችንን፣ አካሄዳችንን እንመርምር። እናስተውል! ከአንዳንዶች መናከሶች ጀርባ በሱና ስም የሚቀርብ የተዳፈነ የግል ቅሬታ አለ። የአንዳንዶቹ ጉልበት ጭፍን ጭፍራቸው ስለሆነ ገለል በማለት ራሳችንንም እናድን፣ እነሱንም እናስተንፍስ። ይጠቅማቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም።
9. የታየ ሁሉ ባደባባይ አይወራም። ጥፋት የመሰለን ነገር ጊዜ ስንወስድ እንዳሰብነው ላይሆን ይችላል። ክፍተትም ቢሆን መናገሩ ችግር የሚያባብስ ከሆነ አያያዛችንን ማጤን ያስፈልጋል።
10. ለሰፊው ህዝብ እንዘን። በመጯጯህ ከሱና፣ ከዒልም፣ ከመስጂድ የምናርቃቸው እንዳይኖሩ ጥንቃቄ እናድርግ።
11. የመንሀጅ ጥንካሬ ብዙ በመጮህ፣ ብዙ በመዝለፍ፣ ሳያጣሩ በግምት በመወንጀል፣ ንግግር እየቆለመሙ በመፈረጅ አይደለም የሚለካው። ስንወድም፣ ስንጠላም፣ ስናወድስም ስንተችም በልክ በሚዛን ሊሆን ይገባል። ይሄ ቁርኣናዊ መርህ ነው።
ማሳሰቢያ፦
የፅሁፉ አላማ ራሳችንን ከችግሩ ነፃ አድርገን ሌሎችን መንካት አይደለም። ይልቁንም ሰከን ብሎ በማጤን ለራሳችንም፣ ለወገናችንም፣ ለደዕዋችንም እንዘን፣ ሁላችንም እናስተውል የሚል ነው። አላህ ያለለት ሰው፣ ጎድቶም ተጎድቶም የኋላ ኋላ ሊነቃ ይችላል። በጊዜ ብንነቃ ግን ጉዳት እንቀንሳለን። ደግሞም ሳይመለሱ መሄድም አለ። በሰው ሐቅ ላይ ድንበር መተላለፍ ደግሞ ለመመለስም እንቅፋት ሊሆን ይችላል። አላህ ማስተዋሉን ያድለን።
✍️ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
