fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

رفتن به کانال در Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
908
مشترکین
-324 ساعت
-157 روز
+4830 روز
آرشیو پست ها
📢 አስደሳች ዜና! ከዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የተርቢያ ማዕከል 💎 ዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የተርቢያ ማዕከል ለ2019 ዓ. ል የትምህርት ዘመን በአዳሪ መርሃግብር ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል። ☑️ የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦ 📍ጾታ፦ ለወንዶች ብቻ (አዳሪ) 📍 እድሜ፦ ከ10 - 20 ዓመት 📍 ጤንነት፦ ከማንኛውም በሽታ ነፃ የሆነ 📍 ስነ-ምግባር፦ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ የሆነ 📍 ፍላጎት፦ ለመቅራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው 📍ክፍያ፦ ወርሃዊ ክፍያን መክፈል የሚችል ☑️ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች፦ 📌 የቁርአን ሒፍዝ (በቃል መያዝ) 📌 የቁርአን ነዘር (ንባብ) እና ሙራጀዓ (ክለሳ) 📌 ቃዒደቱን ኑራኒያ እና የተጅዊድ ትምህርቶች 📌 የተለያዩ የዲን ኪታቦች ☎️ ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ፡ +251911171786 | +251910034682 በቴሌግራም ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈 በዋትስ አፕ  ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈          የቴሌግራም አድራሻ፡ 🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial 🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial 🏢 አድራሻ: አንፎ 105 ከዘቢዳር ሆቴል ጀርባ

የጁሙዐህ ኹጥባ ርዕስ፦ የዒልም ደረጃ (በላጭነት) 🏙በደሴ ጂብሪል ጎራ መስጂድ 🎙አቡ ዑሠይሚን ዒዙዲን የቴሌግራም ቻናል፦ ¤t.me/Ezedin_Ibnu_Shafi

📌محاضرة :-الثبات على الدين                          በዲን ላይ ጽናት 🎙አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

●ምረጪው ጀግናውን ያን ሰለፍይ ወጣት ●ጎስቋላ ቢሆንም ቢጎዳውም ማጣት ●ሰለፍዩን ወጣት ምረጪው ያን ጀግና ●የነብያት ወራሽ የኢስላም ናሙና ●ያንን የሱና ሰው ጀግናውን ምረጪው ●በኒቃብ ተውበሽ ያንቺ ይሁን አምጪው ●በይ ምረጪው ውዴ ምንም አታመንቺ ● በቃ ይሁንልሽ አባወራሽ ላንቺ ። 🫵በቃ ምረጪው ✍️

♦️ለነዚያ ለታሪክ አተላወች ♦️ለነዚያ የራፊዷ ገረዶች ♦️ለመጁሳ ቅጥረኞች አድርሱልኝ⁉️ ሲሰድቡሽ ቢውሉ ከሽዓ ወግነው፡ የተውሒድን መርህ ስለማያውቁ ነው፡ ለአህባሽ፣ለኢኽዋን ደግሞም ለሱፍያ፡ ግልፅ ነው ይጠላል ደዕዋ ሰለፍያ፡ 🎙በኑረዲን አል-ዓረቢ http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ረድ የሸይኽ ሙሀመድ ሀሚድን ስህተቶች وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡ 🇸🇦የቴሌግራም ቻናል https://t.me/KedmiyaLetewhid9

﴿رَبِّ إِنّي لِما أَنزَلتَ إِلَيَّ مِن خَيرٍ فَقيرٌ﴾ القارئ : عبدالعزيز الغامدي 🩶.

ወደ ዩኒቨርሲቲ ለምትገቡ አዲስ ተማሪዎች፦ ከላይ የተቀመጠው መረጃ የየዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎችን መረጃ የያዘ ሲሆን በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ስለ ዩኒቨርስቲዎቹ፤ ጀመዓዎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎ
ወደ  ዩኒቨርሲቲ ለምትገቡ አዲስ ተማሪዎች፦     ከላይ የተቀመጠው መረጃ የየዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎችን መረጃ የያዘ ሲሆን በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ስለ ዩኒቨርስቲዎቹ፤ ጀመዓዎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች መጠየቅ ትችላላችሁ።    አላህ ለስኬት መሠረት የሆነን ቆይታ ያድላችሁ።

♦️♦️♦️በፈገግታ ተገናኝተን በጥላቻ ለምን እንለያያለን? 📌ግን ለምንድነው የሰው ልጅ ሲገናኝ በፈገግታ፣ በደስታና በፍቅር የሚቀራርበው፤ ሲለያይ ግን ለመጠላላት ምክንያት፣ ለመከፋፈል ሰበብ፣ የተቃውሞ ቃል እና የቁርሾ ምክንያት ፈልጎ የሚሄደው? 📍ሲገናኝ እያንዳንዱ ሰው የሌላውን መልካምነት ይመለከታል፤ ፈገግታውን ያያል፣ መልካም ቃሉን ይሰማል፣ ውብ ጎኖቹን ያደንቃል። ጊዜ ሲያልፍ ግን የሰውን ጉድለት ማየት ይጀምራል፤ ከዚያም አንድ ትንሽ ስህተት ትልቅ ሆኖ ይታየዋል። የብዙ ዓመታት መልካምነት በአንድ ቅጽበት ይረሳል። አሳዛኙ ነገር ግን መለያየቱ አይደለም፤ እንደ ጠላት መለያየቱ ነው። 📌አንድ ቀን በፍቅር የተገናኛችሁ ሰዎች ለምን በጥላቻ መለያየት አለባችሁን? አንድ ቀን የተዋደዳችሁትን ሰው ዛሬ ስለተለያያችሁት ለምን መጥፎ ሰው ማድረግ ያስፈልጋል? 📍አንዳንድ ሰዎች ከሕይወታችን ሊወጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ከሕይወታችን መውጣታቸው በልባችን ውስጥ ጠላት ሆነው እንዲቀሩ አያስገድደንም። መንገዳችሁ ቢለያይ፣ ልባችሁ አይለያይ። መገናኘታችሁ ቢያበቃ፣ ክብራችሁን አትጨርሱ። 👌ሰውን በመልካምነት ማግኘት ብቻ ትልቅ ነገር አይደለም፤ በመልካምነት መሰናበትም የሰውነት ትልቅነት ነው። 📍እናም ከአንድ ሰው ስትለያዩ፣ ምክንያት ፈልጋችሁ እንዳትጠሉት፤ ያሳለፋችሁትን መልካም ጊዜ አስቡ። ያደረገላችሁን መልካም ነገር አስቡ። ካልቻላችሁም ቢያንስ ዝም ብላችሁ በሰላም ተለያዩ። 🗳ምክንያቱም መለያየት የግድ ጥላቻን አይፈልግም፤ አንዳንድ ጊዜ መለያየት ብቻ በቂ ነው። ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

1⃣ኡሙ ረያን http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13519 2⃣ኡሙ ሀፋሳ http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13583 3⃣ሰአዳ ኢብራሂም http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13
1⃣ኡሙ ረያን http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13519 2⃣ኡሙ ሀፋሳ http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13583 3⃣ሰአዳ ኢብራሂም http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13591 4⃣ኡሙ አቲካ ሱመያ http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13637 5⃣ኡሙ ሀቲም መኪያ http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13523 6⃣ኡሙ ፈውዛን ሶፊያ ቢንት አብደሏህ http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13513 7⃣ኡሙ አፊፍ http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13605 8⃣ቢንት ዩሱፍ http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13681 9⃣ረምላ ኡሙ ፈውዛን http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13527 1⃣0⃣ቢንት ጀማል አል አሰሪ http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13687

يارب مع فجر يوم الجمعة ارزقنا من فضلك وسخّر لنا كل ما نتمناه ، يسّر لنا امورنا واشرح لنا صدورنا وافتح لنا ابواب رزقك ، وأكرمنا بفيض نعمك ورحمتك يا كريم🍃.

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎችን እንተግብር ➖➖➖➖➖➖➖ ↩️💎 ‏سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿 ➊ 💎الغسل ➋💎 الطيب ➌ 💎السواك ➍💎 لبس الجميل ➎💎 قراءة سورة الكهف ➏💎 التبكير لصلاة الجمعة ➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➊ 🌺መታጠብ ➋ 🌺ሽቶ መቀባት ➌🌺 ሲዋክ መጠቀም ➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ ➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን ➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት በግዜ መጣድ ➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰 «اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ   🌺በሰለዋት በዚክር ያውለን ያረብ ﷺ 🌹 .................🌹 ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹  ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹 በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !! = የቴሌግራም ቻናል፦               https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

🌿 የሙስሊሞችን ጉዳይ ችግር ማቃለል ማስወገድ የመልካምነት ታላቅ በር ነው። አላህ ሱበሀነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሎናል፦ ﴿وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴾ «መልካምን ሥሩ፤ ምናልባትም ልትድኑና ነጃ ልትወጡ ትችላላችሁ።» 🤍 የሰውን ጉዳይ ማስተናገድ ትንሽ ሥራ አይደለም… አንድ ሰው በችግር ውስጥ ሆኖ ሲመጣብህ፣ ምናልባት በእጅህ ያለው ነገር ትንሽ ይመስልህ ይሆናል፤ አንተ ግን ለእሱ ያደረግከው ነገር በሕይወቱ ትልቅ ቦታ ሊኖረው ይችላል። አንድ ሰው በጭንቀት ላይ እያለ በአንድ ቃል ማጽናናት፣ ●አንድ ሰው ጉዳዩን ማስፈጸም፣ ●የሚያስፈልገውን ሰው ማገዝ፣ ●በችግሩ ጊዜ ከጎኑ መቆም፣ ●የሚያውቀውን መረጃ መንገር፣ ●አንድ የተዘጋ በር እንዲከፈትለት ምክንያት መሆን… ●እነዚህ ሁሉ የሙስሊም ወንድማማችነት ምልክቶች ናቸው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «المُسْلِمُ أَخُو المُسْلِمِ، لَا يَظْلِمُهُ وَلَا يُسْلِمُهُ، وَمَنْ كَانَ فِي حَاجَةِ أَخِيهِ كَانَ اللهُ فِي حَاجَتِهِ، وَمَنْ فَرَّجَ عَنْ مُسْلِمٍ كُرْبَةً فَرَّجَ اللهُ عَنْهُ بِهَا كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ القِيَامَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ اللهُ يَوْمَ القِيَامَةِ.» (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) 🌿 “የወንድሙን ፍላጎት ለማሟላት የሚጥር ሰው አላህ ፍላጎቱን ያሟላለታል” ይህ ቃል ልብን የሚነካ ታላቅ ተስፋ ነው። እኛ የሰውን ጉዳይ ስናስተናግድ እንዲህ እንበል፦ “ይህን ሰው ለማገዝ አላህ ምክንያት አድርጎኛል።”ከዚያ የምናገኘው ክብር ወይም ምስጋና ሳይሆን፣ የአላህ ውዴታ ይሁን የምንፈልገው። ሰዎች አመስግነውን ይሆናል፤ አላመሰገኑንም ይሆናል። ሰዎች አስታውሰውን ይሆናል፤ ረስተውንም ይሆናል። አላህ ግን የሠራነውን መልካም ሥራ አይረሳም። ● አንድ ሰው የእኛን እርዳታ ሲፈልግ አንተ የምታየው ችግሩን ብቻ ነው፤ አላህ ግን የሚያየው የአንተን አቋም ነው። ለዚህ ነው አንዳንድ ጊዜ ትንሽ የምናደርገው ነገር በአላህ ዘንድ ታላቅ የሚሆነው። ●አንድ ሰው እንባውን እንዲያብስ ምክንያት ሆነህ ሊሆን ይችላል። ●አንድ ቤተሰብ ችግሩን እንዲያልፍ ምክንያት ሆነህ ሊሆን ይችላል። ●አንድ ወንድም ተስፋ እንዳይቆርጥ አንተ ምክንያት ሆነህ ሊሆን ይችላል። እነዚህን መልካም ስራዎች አታቃልል። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እንዳስተማሩን፣ የሰውን ጭንቀት ማስወገድ እንኳን በቂያማ ቀን ከጭንቀቶች አንዱን እንዲያስወግድልን ምክንያት ይሆናል። ● ወንድማማችነት የሚታየው በደስታ ጊዜ ብቻ አይደለም… ሰው ሲደሰት ከእሱ ጋር መደሰት ቀላል ነው። ነገር ግን ሲወድቅ እጁን መያዝ፣ ሲጨነቅ ማጽናናት፣ ሲደክም መደገፍ ነው እውነተኛ ወንድማማችነት። ሰዎች በሚያስፈልጉን ጊዜ ብቻ አንቅረባቸው፤ እኛም ሌሎችን በሚያስፈልጋቸው ጊዜ እንቅረብ። የሙስሊም ወንድምህ ጉዳይ ካለው፣ “እኔ ምን አገባኝ?” ከማለት በፊት “ምን ላግዘው እችላለሁ?” ብለህ አስብ። 🌿 ምናልባት ያ ትንሽ እገዛህ በአላህ ዘንድ የተቀበለች ትሆናለች። 🌿 ምናልባት ያ የሰጠኸው ጊዜ ነገ አንተ በችግር ላይ ስትሆን የምትፈልገው ምሕረት ይሆናል። 🌿 ምናልባት የሰውን ጭንቀት ያስወገድክበት ቀን አንተም ከቂያማ ቀን ጭንቀት እንድትወጣ ምክንያት ይሆናል። ● እንግዲህ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በቻልነው አቅም እንርዳ… ● ጉዳያቸውን እናስፈጽል፣ ● ችግራቸውን እናቅልል፣ ● እንባቸውን እናብስ፣ ● ምስጢራቸውን እንጠብቅ፣ ● ነውራቸውን እንሸፍን፣ ● በችግራቸውም ጊዜ ከጎናቸው እንቁም። ምናልባት ነገ እኛ የምንፈልገው እርዳታ ዛሬ ለሌላ ሰው የሰጠነው እርዳታ ትሆናለች። ⚠️ አላህ ሆይ! የሙስሊሞችን ጭንቀት አስወግድ፣ ጉዳያቸውን አስተካክል፣ እኛንም የተጨነቁትን ከሚያጽናኑ፣ የተቸገሩትን ከሚረዱ፣ የወደቁትን ከሚያነሱ ባሮችህ አድርገን። እኛ የሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት ስንሮጥ፣ አላህ የእኛን ፍላጎት የሚያሟላልን ጌታ ነው። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

«تُكفى همك، ويُغفر ذنبك» يقول ابن باز رحمه الله: إذا جعل الإنسان وقتًا يصلي فيه على النَّبي ﷺ  كثيرًا، فالله -جلَّ وعلا- يأجره على ذلك، والحسنة بعشر أمثالها، إلى ما لا يحصى من الفضل، وإذا صرف ذلك الوقت كله في الصلاة على النبي ﷺ؛ حصل له هذا الفضل: «تُكفى همّك» يعني: يكفيك الله همك «ويُغفر ذنبك». اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد، وعلى آله وصحبه أجمعين.

ዛሬም - በአሏህ ጥበቃ - ኢኽዋኖችን የምንጠላ ከነሱም መንገድ እጅጉን የራቅን የሰለፎቻችን ተከታዮች ነን ! አሏህ ከሸራቸው ይጠብቀን ! https://t.me/MerkezulimamiAhmed

«አንዳንድ ልቦች እንደ ዝናብ ጠብታ ናቸው፤በፅጥታ መጥተው በነፍስ ውስጥ የማይጠፋ ሕይወትን ትተው ያልፋሉ።» = https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.
«አንዳንድ ልቦች እንደ ዝናብ ጠብታ ናቸው፤በፅጥታ መጥተው በነፍስ ውስጥ የማይጠፋ ሕይወትን ትተው ያልፋሉ።» = https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

ባንዲራሽ ከፍ ይበል!! ክብርና ዝናሽ ለአለም ይነገር፡ የነብዩ ኢስማኢል የሙሀመድ ሀገር፡ ግርማና ሞገስሽ የዑሁድ ተራራ፡ የነብዩ ወዳጅ ያ የጀነት ጎራ፡ የወህዩ መፍለቂያም ከአንች ጋር ነው ሒራ፡ ያለሽ ተአምራት አያልቅም ቢጠራ፡ በዝርዝር በወሳ ቢተረክ ቢወራ። ---------------------------------- ሶፋና መርዋ ደግሞም ሙዝደሊፋ፡ ሐጅ መተግበሪያው እንደት ነው አረፋ፡ በርቀት እያየሁ እያፈሰስኩ እንባ፡ ሀጀረል-አስወዱ ሆድን እያባባ፡ ቅዱሱ ቦታችን እንደምነው ከዕባ፡ ------------------------------------- ባንዲራሽ ከፍ ይበል!! ለወደደሽ መልካም ለጠላሽ ሴራ አፍራሽ፡ የተዐምር ሀገር አምረሽ የተሰራሽ፡ ሁሌ ትርፋማ ሁኝ አይታይ ኪሳራሽ፡ በሔደሰሽበት ሁሉ ከፍ ይበል ባንድራሽ፡ የጠላሽ ይጠላ ሽንፈትን ይቀበል፡ ሁሌም በሔድሽበት ባንድራሽ ከፍ ይበል፡ በኑረዲን አል አረቢ http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi