uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Відкрити в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
910
Підписники
-324 години
-157 днів
+4830 днів
Архів дописів
ቢያንስ ከራሳችን እንማር ~ መቼም እንደ ሰለፊያ ደዕዋ የጎንዮሽ ፍትጊያ እና የርስ በርስ መናቆር የበዛበት የለም። ይሄ አሳዛኝ እውነታ በየ ሃገሩ በሰፊው የሚታይ ነው። ጉዳዩ መተራረም ላይ ቢቆም ጥሩ ነበር። መናቆሩ ግን ከዚያ በብዙ ርቀት ያልፋል። * አንዱ በሌላው ጉዳት፣ በሌላው ህመም፣ በሌላው ሞት እስከሚደሰት ይደርሳል። * ከሱና ማስወጣት፣ ተብዲዕ መደራረግማ በሰፊው የተንሰራፋ ነው። ከእስልምና ለማስወጣት ዳር ዳር የሚልም አይጠፋም። * ጉዳዩ በደንብ ስሜት እንደገባበት ከሚያጋልጡ ነጥቦች ውስጥ አንዱ መኮራረፉ ሶላት እስካለመከተል መድረሱ ነው። የባሱ ሰዎችን እየተከተሉ ትናንት አብረዋቸው የነበሩትን ግን በተለያዩ ማግስት ለሶላት እስከመሸሽ የሚደርሱ አሉ። በሱና ስም ስሜት መጋለብ! * በሰላም ጊዜ ያልተወራ ነውር በተጋጩ ማግስት ይዘከዘካል። (ያው ውንጀላው ውሸትም ሊሆን ይችላል።) * በሰላም ጊዜ ሲወዳደሱ እንዳልነበር ከግጭት በኋላ "እከሌ ጃሂል ነው" ማለት የተለመደ ነው። * ንግግርን እየቆለመሙ መወንጀል፣ ያልተባለ መለጠፍ፣ ሰቅጣጭ ስድቦችን መሰዳደብ የተለመደ ነውር ነው። * በአንድምታ (በላዚም) መክሰስ በስፋት አለ። "ላዚሙል መዝሀብ ለይሰ ቢመዝሀብ" የሚለው ነባር ቃዒዳ ተዘንግቷል። * ረድ አድርጎ ማለፍ የሚባል አይታወቅም። ነጋ ጠባ መጨቃጨቅ፣ ሰዎችን በዚህ መጥመድ በስፋት የሚታይ ነው። አንዳንዶች የሚጠሉት አካል ጥፋት ላይ ሲወድቅ ለቀደመ የውሃ ቀጠነ ክሳቸው ማሳመኛ አገኘን ብለው ሰርግና ምላሻቸው ይሆናል። በማዘን ፋንታ ይቦርቃሉ። "ተመልሻለሁ" ቢባሉ እንኳ የማይዋጣቸው፣ ደጋግመው በዚያው ክሳቸው የሚቀጥሉ በተጨባጭ አሉ። * ያለ ገደብ "እነ እከሌ ከኢኽዋን የከፉ ናቸው" እያሉ መወረፍ ጎልቶ ይታያል። * የራስን ጅህልና ሸፍኖ ወይም የራስን ጃሂል አቅፎ ሌሎችን በጅህልና ማጣጣል ይጎላል። * ውሸት በጣም በዝቷል። ያውም በሰው ክብር ላይ ለመረማመድ!! በውሸት እከሌ በጥቅም ተገዝቷል፣ እከሌ አክስዮን ገብቷል፣ እከሌ እንዲህ ሆኖ ነው፣ ... ማለት በብዛት አለ። * የርስ በርስ ጥላቻው እስከ መደባደብ፣ አንዱ ሌላውን ለማጥፋት እስከ መሞከር ይደርሳል። እዚሁ በሃገራችን ውስጥ በስለት የተወጋጉ፣ በዱላ የተደባደቡ፣ በዚህ የተነሳ ወህኒ የገቡ፣ የውሸት ክስ እየለጠፉ ለፖሊስ አሳልፈው የሚሰጡ፣ ፈቃድ ከመንጠቅም በላይ ለባሰ አካል አሳልፈው የሰጡ፣ ... ብዙ አሳፋሪ ተግባሮች አሉ። ትዳር የፈረሰበት፣ ቤተሰብ የተለያየበት ብዙ አሳዛኝ ነገሮች አሉ። የሚታዩትና የሚደርሱት ብዙ ናቸው። እነዚህን ነገሮች ባላነሳቸው እመርጥ ነበር። የሌሎች መሳቂያ፣ መሳለቂያ መሆን በጣም ያማል። ነገር ግን የአደባባይ ሐቅ ከሆነ በኋላ መመካከሩ እንጂ መሸፋፈኑ ፋይዳ አይኖረውም። አይናቸው ላይ ባጠለቁት የልዩነት መነፅር በመመልከት የምፅፈውን ሃሳብ በቅንነት የማያዩት፣ አልፎም በሚፈልጉት መልኩ የሚመነዝሩት እንደሚኖሩ ይገባኛል። የችግሩ አንዱ መገለጫም ይሄው ነው። ቢሆንም ዝምታ መፍትሄ አይሆንም። ቢሆንም "ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርምና" የሌሎችን ውንጀላ በመስጋት ከመመካከር መራቅ አይገባም። "ብልጥ ከሌሎች ይማራል፤ ሞኝ ከራሱ ይማራል" ይባላል። የመጀመሪያውን ብስለት ባለማስተዋል፣ ራስን ባለመቆጣጠር አልፈነዋል። ቢያንስ ከራሳችን ድክመት ብንማር ጥሩ ነው። ከደረሱትና ከሚደርሱት እንማር። በምን መልኩ? 1. ወደራሳችን በጥልቀት እንመልከት። #ራስን_ጥሎ ሁሌ ሌሎችን ማሳደድ ኣኺራን ይጎዳል፣ ቡድንተኝነትን ያወርሳል። የልብ ድርቀትን ያስከትላል። 2. የዑለማኦችን አካሄድ የምንፈልገውን እየመረጥን ሳይሆን ወይም በሌሎች የተመረጠልንን ሳይሆን ከነፍሲያ ወጥተን ከሁሉም አቅጣጫ እንመልከት። ነጠላ ንግግሮቻቸውን ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ አፈፃፀማቸውንም እናጥና። የእውነት እኛ በምናደርገው መጠን ሰው ላይ በማክ * ፈርም ይሁን ተብዲዕ በማድረግ ላይ የተናጠል ፍርድ ለመስጠት ይቸኩላሉ ወይ? በጭራሽ! 3. በምናራምዳቸው እርምጃዎች ላይ የደዕዋችንን መስለሐ በሚገባ እናጢን። ደዕዋችንን የሚያሳጣን፣ መስጂዶቻችንን የሚያስነጥቀን ከሆነ ጩኸታችን ምን ፋይዳ አለው? አካሄዳችን የሰለፊያን ደዕዋ የሚያጠለሽ ከሆነ ወደድንም ጠላንም የጠላትን አጀንዳ እየፈፀምን ነው። 4. ከሱና ዑለማኦች ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ላይ አንገደብ። ይሄ አካሄድ አንዳንዶችን ተ0ሱብና ጉሉው ላይ ሲጥላቸው እያየን ነው። እውነታውን የማያምኑት ችግሩ ስለሸፈናቸው ነው። 5. ተዝኪየተ ነፍስ ላይ እናተኩር። ለችግሩ መስፋት አንዱ ትልቅ ሰበብ የተቅዋ፣ የወረዕ መሳሳት ነው። ሌሎች ላይ ዋሽቶ መክሰስ፣ ሳያረጋግጡ በግምት መወንጀል፣ በጥላቻ ድንበር ማለፍ፣ የራስን ነውር እየደበቁ ሌሎችን መናከስ፣ ... አላህን መፍራት እንደሌለ ወይም እንደሳሳ የሚያጋልጥ ነው። እና እራሳችንን አንርሳ። 6. አቅማችንን እንወቅ። ከቁመታችን በላይ የሆኑ ርእሶችን አናቡካ። 7. ወደ ኢስላም ጠቅልለን እንግባ። አኽላቅም፣ ዙህድም፣ ወረዕም፣ ሲራም፣ ተርጊብና ተርሂብም የኢስላም አካል መሆናቸውን ከምላስ ባለፈ በተግባር እናረጋግጥ። ሰለፎች ከነዚህ ነጥቦች አንፃር የነበሩበትን የላቀ ደረጃ እናጥና። 8. ሰው ተከትለን ገደል እንዳንገባ እንጠንቀቅ። በየመንደሩ የወደድኩትን ውደዱ፣ የጠላሁትን ጥሉ የሚሉ የሹም ዶሮዎች ይኖራሉ። እናስተውል! እነዚህ አካላት አብረውን ቀብር አይገቡም። እጃችንን ይዘው ሲራጥ አያሻግሩንም። እርቃናችንን ብቻችንን ለሒሳብ እንደምንቆም እናስብ። ነገ ከመመርመራችን በፊት ዛሬ ራሳችንን፣ አካሄዳችንን እንመርምር። እናስተውል! ከአንዳንዶች መናከሶች ጀርባ በሱና ስም የሚቀርብ የተዳፈነ የግል ቅሬታ አለ። የአንዳንዶቹ ጉልበት ጭፍን ጭፍራቸው ስለሆነ ገለል በማለት ራሳችንንም እናድን፣ እነሱንም እናስተንፍስ። ይጠቅማቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም። 9. የታየ ሁሉ ባደባባይ አይወራም። ጥፋት የመሰለን ነገር ጊዜ ስንወስድ እንዳሰብነው ላይሆን ይችላል። ክፍተትም ቢሆን መናገሩ ችግር የሚያባብስ ከሆነ አያያዛችንን ማጤን ያስፈልጋል። 10. ለሰፊው ህዝብ እንዘን። በመጯጯህ ከሱና፣ ከዒልም፣ ከመስጂድ የምናርቃቸው እንዳይኖሩ ጥንቃቄ እናድርግ። 11. የመንሀጅ ጥንካሬ ብዙ በመጮህ፣ ብዙ በመዝለፍ፣ ሳያጣሩ በግምት በመወንጀል፣ ንግግር እየቆለመሙ በመፈረጅ አይደለም የሚለካው። ስንወድም፣ ስንጠላም፣ ስናወድስም ስንተችም በልክ በሚዛን ሊሆን ይገባል። ይሄ ቁርኣናዊ መርህ ነው። ማሳሰቢያ፦ የፅሁፉ አላማ ራሳችንን ከችግሩ ነፃ አድርገን ሌሎችን መንካት አይደለም። ይልቁንም ሰከን ብሎ በማጤን ለራሳችንም፣ ለወገናችንም፣ ለደዕዋችንም እንዘን፣ ሁላችንም እናስተውል የሚል ነው። አላህ ያለለት ሰው፣ ጎድቶም ተጎድቶም የኋላ ኋላ ሊነቃ ይችላል። በጊዜ ብንነቃ ግን ጉዳት እንቀንሳለን። ደግሞም ሳይመለሱ መሄድም አለ። በሰው ሐቅ ላይ ድንበር መተላለፍ ደግሞ ለመመለስም እንቅፋት ሊሆን ይችላል። አላህ ማስተዋሉን ያድለን። ✍️ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

  ኢላሂ.......! ድክመቴን ታውቃለህ....ማንም ያላየውን ሰው ፊት ስቄ ቆሜ....ማታ  የማለቅሰውን።

🛑ታሪካችን እንማር 🛑የእስልምና ጠላትስ እነማናቸዉ …⁉️❓ 🎙ኡስታዝ ዓብዱሶመድ ሙሐመድ ኑር https://t.me/AbdusomedMNur_Channel

قيل " من الحكمة أن تعرف ما تقول وليس من الحكمة أن تقول كل ما تعرف لأن الكلام كالدواء إن أقللت منه نفع وإن أكثرت منه صدع." " የጥበበኛ ብለሀተኛ ብሎ ማለት የምትናገረውን ማወቅጅ የምታዉቀዉን ሁሉ መናገር አይደለም. ምክኒያቱም ንግግር ልክ እንደ መድሀኒት ነዉ በልክ ከተሰጠ ጠቃሚ ይሆናል በጣም ከልክ ክለፈ/ከበዛ ያሳማል." منقول

Repost from ፈዋኢድ
‎ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ‎ ‎🎊 ልዩ የዳዕዋና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 🎉 ‎__ ‎ ‎🔉 እነሆ የፊታችን ጁሙዓ ‎📅 ቀን፦ 8/01/2019 ኢ.አ ‎⏰ ሰዓት፦ ከም
‎  السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ‎ ‎🎊 ልዩ የዳዕዋና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 🎉 ‎__ ‎ ‎🔉 እነሆ የፊታችን ጁሙዓ ‎📅 ቀን፦ 8/01/2019 ኢ.አ ‎⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 3፡00 ጀምሮ (በኢትዮ) ‎ ‎በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ‎       የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌግራም ግሩፕ ‎ ‎⏬ ተጋባዥ እንግዶቻችን ⏬ ‎ ‎🎙 ኡስታዝ ዐብዱናስር መኑር ‎🎙 ኡስታዝ አቡ ሱፊያን አል በናን ‎ ‎🔗 የፕሮግራሙን የሚተላለፍበት ግሩፕ   ሊንክ ‎👉 https://t.me/Ibnu_Abas_Mesjid_wku ‎ ‎ ‎ሁላችንም ሼር በማድረግ ላልሰሙት እናሰማ ! ‎  الدال على الخير كفاعله 👈 ‎

ስለ ሰይዪድ ቁጥብ ተከታታይ ~ ክፍል አንድ፦ የሰይዪድ ቁጥብን ኻሪጂነት እና ህዝበ ሙስሊሙን በጅምላ ከኢስላም ማስወጣቱን የሚመለከት ነው። = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

جزى الله الأستاذ الفاضل ابن منور خير الجزاء على محاضرته القيّمة بعنوان: «مَن هو سيد قطب؟»، وما تضمّنته من بيانٍ للحق، وكشفٍ للشبهات، وردٍّ على ما أُثير حوله، ومنها شبهات الشيخ محمد حامي الدين، نسأل الله أن يبارك في علمه، وينفع بمحاضرته، ويجعلها في ميزان حسناته.

⭕️👉ለውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አላህ አፍያ ያድርገውና አድርሱልኝ።✅             <<አንተን ክፉ አይንካህ>> የነብያት ወራሽ ዳዒ ነህ ታታሪ፤ የኢስላም ወታደር ባጢል አባራሪ። የሱና ሳተና የቢዲዓ ጠላት፤ በሁጃ ተውበህ ሀቅን ያፀናሀት፤ ባጢልን አባረህ አጭደህ የወቃሀት። በእኔ ጭልፍ ሆሄ በአጭር አማረኛ፤ ሊደርስህ ባይችልም ተራ ፈረሰኛ፤ ላንጎራጉር ብየ እንደመንገደኛ፤ ሲሰማኝ ቋጠርኳት ከውስጤ ማደኛ። የኔ ጀግና ብየ ባወሳህ አልጠግብም፤ አንበሰና ነህ ብልህ አንጀቴ አይገግብም። የሀበሻው ኮከብ ስጦታው ይደንቃል፤ በማራኪ አንደበት ዒልምን ያስታጥቃል ። #አህባሽ ግሳንግሱ ብቅ ሲል ሀበሻ፤ በሎጅክ ለማጥመቅ ሲያሳጣ መድረሻ፤ ወገቡን ሰበረው በሁጃ መዶሻ። ተዕዊል እና ተዕጢል አንግቦ በውስጡ፤ ሹብሀ እየነዙ ምድር ሲቀውጡ፤ የሱናን ሰው ጠልተው ከሀገር ሲያስወጡ፤ ሲያስገርፉ አሳስረው ዋሽተው ሲያናውጡ። የነብዩን መንገድ ገርሳሹ ሲበዛ፤ ውሸትን ተዋጋው ቆልቶት እየነዛ፤ ቁርአን ሀድስን ከሰለፎች መቅጃ፤ ኢጅማዕን አስፍሮ አጣቅሶ ማስረጃ፤ አበረከተልን ሹብሀን ማስወገጃ፤ ጀግናው የኔ ዑስታዝ ድንቅ ኢብኑ ሙነወር፤ ኢላማው አይስትም ሁጃው ሲወረወር። ሱፍያን፣አህባሽን ድባቅ ያስገባቸው፤ ከአርሹ በላይነው ብሎ ፃፈባቸው። የአህባሾች መሪ "ሀሰን ታጁ" ሲዋሽ፤ ከኢኽዋኖች መጥቶ  በመውሊድን ሲቀረሽ፤ እርምት አረገበት የታሪኩን ግድፈት፤ በማስረጃ አድርጎ ውሸትን ቀበራት። በሱና ስም ሰርገው ፊልም ለሚሰሩ፤ ተገቢ ያልሆነን ተግባር ላሰመሩ፤ አደብ አስያዛቸው በውብ መነፀሩ። ሀጃዊራ ዘልቃ ያለ አግባብ ስትቀረሽ፤ የሁጃ ጦር ስሎ በደሊሉ ጥንቅሽ። አልበያንን ከትቦ እያሰጣ ቀንጣሽ፤ ከታላላቆቹ ማስረጃን አጣቃሽ፤ አንተኮ ነህ ጀግናእውነትን አስታዋሽ። አካሄዱ በሳል ንግግሩ ቁጥብ፤ ምክሩ አንጀት አርስ ነው ልብን የሚያረጥብ፤ በምን ፊደል ላውሳው በምን ቃላት ነጥብ፤ ብቻ ማር ያዘንባል ጀግና ነው እንደ ንብ። ለፊትና አይቸኩልም ይፈራል አደጋ፤ ሱናን ይጠብቃል ነቅቶ ሳይዘነጋ፤ ወዳሴም አይሻ የማንንም ታርጋ፤ አፉን የለጎመው የለተሞን መንጋ፤ ያላግባብ ሲወራጭ ተሳክሮ ሲንጋጋ፤ ድምፅ ባለው ፅሁፍ ቅጥፈት የተዋጋ፤ የሙነወር ልጅ ነው የባጢል አለንጋ ፤፦ የተክፊርን ቅሪት ወገቡን የቀጨው፤ በአንድ ንግግሩ መንጋውን ያጋጨው፤ አንድ ኳስ ወርውሮ "ሽ" ያነጫነጨው። ለሀቅ ዘብ ቆሞ ለፍትህ የሚኖር፤ ለሱና ኻድም ነው የኢስላም መምህር። ልክ እንደ ፔንዱለም ፊትና ሲያናውጠን፤ ድንገት ተከስቶ አካቦ ሲውጠን፤ ፈጥነህ በመመከት እረፍት የምሰጠን። አላህ ይጠብቅህ ከመከራ ከጭንቅ፤ ከሴረኞች ተንኮል ከአይሁድ ከሙናፊቅ። ሻፊ ነው ጌታችን በቶሎ ያሽርህ፤ ወንጀልክን አብሶ በኸይር ያበሽርህ። የአንተን ሀላፊነት የለም የሚተካህ፤ የሀበሻው ኮኮብ አንተን ክፉ አይንካህ። ✍بقلم أبي شورى أحمد https://t.me/Sobabilalmesjid https://t.me/Sobabilalmesjid

የድምፅ ቅጂውን በቴሌግራም ቻናሌ ላይ በቅርቡ እለቃለሁ፣ ኢንሻአላህ።

~ አልሐምዱሊላህ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወርን የመሰሉ የሱና አናብስቶች እስካሉ ድረስ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከኸይር አይወገድም ኢንሻአላህ። አላህ ይጠብቅህ ውዱ ኡስታዛችን። የሀበሻው ኮከብ የዘመናችን ድምቀት
~ አልሐምዱሊላህ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወርን የመሰሉ የሱና አናብስቶች እስካሉ ድረስ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከኸይር አይወገድም ኢንሻአላህ። አላህ ይጠብቅህ ውዱ ኡስታዛችን። የሀበሻው ኮከብ የዘመናችን ድምቀት። በቅርቡ ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን በሰይድ ቁጥብ ጉዳይ በነዙት ብዥታ ላይ አጥጋቢ ምላሽ እየተሰጠ ነው። አጉል ኩራትህን አሽቀንጥረህ ጣልና ገብተህ አዳምጥ። = https://t.me/IbnuMunewor?livestream=abaae191d35c62b5f9

ያ 'ሰላም ና ማነህ ግባ አዳምጥ ይልቅ ይጠቅምሀል፣ ሚዛናዊ መስሎ ነገር አቀላጥፎ ኢኽዋን ይበላሀል፣ የ'ኢኽዋኖች ተልቢስስ ፣ውሸት መቀጣጠፍ ፣ የነሱን ኹራፋት ወደ ዲን መለጠፍ፤ ቀጠሉ እኮ ደግሞ መ
ያ 'ሰላም ና ማነህ ግባ አዳምጥ ይልቅ ይጠቅምሀል፣ ሚዛናዊ መስሎ ነገር አቀላጥፎ ኢኽዋን ይበላሀል፣ የ'ኢኽዋኖች ተልቢስስ ፣ውሸት መቀጣጠፍ ፣ የነሱን ኹራፋት ወደ ዲን መለጠፍ፤ ቀጠሉ እኮ ደግሞ መቸ በዚህ ቆሙ፣ ለ'ሰይድ ቁጥብ ዲፋዕም በማድረግ ድምፅንም አሰሙ፣ ሚዛናዊነቱ ፍፁም የጎደለ፣ ያልሆነውን ሁኗል ብሎ እያሻሻለ፣ በዲነል ኢስላም ላይ ከቶ እንደ ኢኽዋኖች ማን የቀለደ አለ።

ያሰላም እስኪ ገብታችሁ ስሙት 🌹 አንበሳውን የሙነወርን ልጅ🌹 እየተነተነው ነው። ውሾች ቢንጫጩም ግመሎች ጉዟቸው ላይ ናቸው አይደል ነገሩ።

አሰላሙ ዐለይኩም ~ ባለፈው ሳይመቸኝ በመቅረቱ የተላለፈው ሰይድ ቁጥብን የሚመለከተው ፕሮግራም ዛሬ ምሽት 3፡00 ላይ ይኖራል። በዚህ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፣ ኢንሻአላህ :- የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

📢 መልካም ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ! ​መርከዝ መናሩ-ሱና በኦንላይን (Online) የሚሰጣቸውን የቋሚ ኪታብና የተፍሲር ትምህርቶች ለመከታተል የሚፈልጉ አዳዲስ ተማሪዎችን መመዝገብ ጀምሯል። ​
📢 መልካም ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ! ​መርከዝ መናሩ-ሱና በኦንላይን (Online) የሚሰጣቸውን የቋሚ ኪታብና የተፍሲር ትምህርቶች ለመከታተል የሚፈልጉ አዳዲስ ተማሪዎችን መመዝገብ ጀምሯል። ​ትምህርት ቤታችን በተፍሲር ዘርፍ የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎቹን የትምህርት ማረጋገጫ (ሸሀዳ) በመስጠት ያስመረቀ ሲሆን፣ በአቂዳ ዘርፍ ደግሞ ላለፉት 4 ዓመታት ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎችን በአላህ ፈቃድ ከወር በኋላ የሚያስመርቅ ይሆናል። ​በመሆኑም በዚህ የታላቅ እውቀት ማዕድ ላይ ባሉ የተወሰኑ ክፍት ቦታዎች ቀድመው እንዲመዘገቡ ተጋብዘዋል። {​የመምህራን እና የትምህርት መርሃ-ግብር መረጃ} ➠​የተፍሲር ትምህርት፦ በሸይኽ አቡ አማር አወል ቢን አህመድ የሚሰጥ ➠​የዐቂዳ ትምህርት፦ በአቡ ዑበይዳ የሚሰጥ {​የትምህርት ቀናት፦} ከጁሙዓ ውጭ በየቀኑ (ትምህርቱ ሙሉ በሙሉ እርማት ያካተተ ነው)    { ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች} ◈ ​ቁርኣንን በነዞር (በምልከታ) ቀድሞ ያጠናቀቀ/ች ◈ ​ጥሩ አደብና ኢስላማዊ ሥነ-ሥርዓት የተላበሰ/ች ◈ ​ያለፈቃድ ከትምህርት የመቅረት ልማድ የሌለው/ላት ◈ ​የግሩፑን ደንብና መመሪያ በጥብቅ የሚያከብር/ የምታከብር ◈ ​ትምህርቱን በየቀኑ ሙራጃዐ (ክለሳ) እያደረገ/ች በጥራት የሚከታተል/ የምትከታተል ​📲[ የምዝገባ አድራሻዎች] ●​ለቁርኣን ተፍሲር ትምህርት ለመመዝገብ፦ @Hawie71 ● ​ለዐቂዳ ትምህርት ለመመዝገብ፦ @Ferst6335 ​ማስታወሻ፦ ቦታዎቹ ሳይሞሉ ቀድመው ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ!

رب اجعلني مقيم الصلاة ومن ذريتي ربنا وتقبل دعاء . ربنا تقبل منا إنك أنت السميع العليم وتب علينا إنك أنت التواب الرحيم.

አንድ ከለተሞ መንጋዎች ቻናሉን ልክ ቴሌግራም በአሁን ሰዓት በራሱ ጊዜ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን በቻናሎች ላይ እንደሚለቀው እንዴት እንደሆነ ባላውቅም የልጁም ቻናል በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ቻናል ላይ እየተለቀቀ ነው።ለማንኛውም ሰዎቹ ቻናልህን በሙመይዓ ቻናል ላይ ሼር ተደርጎ አይተናል ብለው አስፈንጥረው ሙመይዕ ብለው እንዳይተኩሱበት ይጠንቀቅ።!

ሙስሊም መሪን በተመለከተ የሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊይ አቋም ቁርኣንና ሐዲሥ ላይ የተመሰረተ ነው። ኢኽዋኖችና የነሱ ፍልፍሎች እንደሚቀጥፉባቸው ሸሪዐ በማይፈቅደው መልኩ መሪዎችን በመታዘዝ ላይ የሚሰብኩ አልነበሩም። ከብዙ ንግግሮቻቸው ውስጥ አንድ ማስረጃ ላቅርብ፦ "እኛ፣ በአላህ እንምላለን፤ ሰይፎች በአንገታችን ላይ ቢደገኑ እንኳን፣ ውሸትን ወይም የተሳሳተ ነገርን መናገር ፈጽሞ የምንፈቅድ አይደለንም። የምንለው፦ “መሪዎችን አላህን መታዘዝ ባለበት ጉዳይ ላይ ታዘዝ፤ አላህን ማመፅ ባለበት ጉዳይ ግን አትታዘዛቸው” ነው። “መሪዎችን አላህን መታዘዝ ባለበት ነገር ታዘዙ፤ አላህን በማመፅ ባለበት ነገር ግን አትታዘዟቸው።” ይህ ኢስላማዊ መርህ ነው ወይስ እስላማዊ መርህ አይደለም? እኔ ይህንን እውነት ነው ለወጣቶች የማቀርበው፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነውን መብትና በላዩ ያለውን ግዴታ እንዲያውቅ ነው። እንዲሁም የነቢዩ ﷺ ትምህርት ያሰመሩበትን መንገድ፣ እንደነገርኳችሁ፣ በትክክል እንዲያውቁ እገልጻለሁ። እኛ የእውነትን ቃል በድፍረት እንናገራለን፤ በአላህ ጉዳይም የሚወቅሰንን ሰው ምንም አንፈራም፤ ይህም በገዢውም ሆነ በተገዢው ላይ ነው። ስለዚህ አላህ በማመፅ በሆነ ነገር ላይ ማንኛውንም ገዢ አትታዘዙ፤ አላህን በመታዘዝ ባሉበት ነገር ግን ታዘዟቸው። ይህ ግዴታ ነው።" = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

♦️♦️♦️እህቴ ሆይ…አቤት ብለሽ ማንበብ እንደጀመርሽ ተስፋ አደርጋለሁ 📌መልካም የሆነን ባል ለረጅም ጊዜ ስትጠብቂ ቆይተሻልን? ብዙ ጊዜ በሌሊት እጆችሽን ወደ ሰማይ አንስተሽ፣ በእንባ ዓይኖችሽን ሞልተሽ፣ “ያ አላህ! የእኔ ተራ መቼ ነው? በሩን አንኳክቶ ወደ ሕይወቴ የሚገባው ሰው መቼ ነው?” ብለሽ ይሆናል። 📍ጓደኞችሽ አንድ በአንድ ሲዳሩ አይተሽ ይሆናል። አንቺ ግን አሁንም ትጠብቂያለሽ። 🔷ሰዎችም ልብሽን በሚያሳምሙ ቃላት፦ “መቼ ነው የምትዳሪው?” “ለምን እስካሁን ዘገየ?” ብለው ይጠይቁሽ ይሆናል። ነገር ግን እህቴ ሆይ፣ ማንም ሰው ሊያውቀው የማይችለውን አንድ እውነት አስታውሺ፦ አላህ አልረሳሽም! እንባሽን ያውቃል። የልብሽን ህመም ያውቃል። የምስጢር ዱዓሽን ይሰማል። ማንም ሰው የማያውቀውን ያንቺን ልብ ያውቃል። አንቺ ገና ያላወቅሽውን ሰው እንኳን አላህ ያውቀዋል። ስለዚህ የትዳርሽ መዘግየት እንዲሰብርሽ አትፍቀጂ። ይልቁንም ወደ አላህ የሚያቀርብሽ ይሁን። 📍ሌሊት ሰዎች በተኙበት ጊዜ ተነሺ። ሁሉም ዝም ባለበት ጊዜ ከአላህ ጋር ተነጋገሪ። እጆችሽን አንስተሽ እንዲህ በይ፦ “ያ አላህ! ማንኛውንም ወንድ አልፈልግም። አንተ ለእኔ የመረጥከውን ሰው እፈልጋለሁ። ያ አላህ! አንተን የሚፈራ፣ ሶላቱን የሚጠብቅ፣ ቁርአንን የሚወድ፣ በእኔ ላይ የሚራራ፣ የሚያከብረኝ እንጂ የማያዋርደኝ፣ ስሳሳት በርኅራኄ የሚመክረኝ፣ ስደክም የሚያግዘኝ፣ በአንተ መታዘዝ ላይ የሚረዳኝን ባል ስጠኝ።” ከዚያም የነበዩ ሙሳን عليه السلام ዱዓ አስታውሺ፦ ﴿رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنْزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ﴾ “ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ወደ እኔ ለምታወርደው ማንኛውም መልካም ነገር በጣም ተፈላጊ ነኝ።”                       እህቴ ሆይ… ምናልባት ዛሬ በመዘግየቱ ታለቅሺ ይሆናል፤ ነገ ግን ወደ ኋላ ተመልሰሽ፦ “ያ አላህ! ያኔ ያንን ሰው ለምን አልሰጠኸኝም ብዬ ነበር፤ አሁን ግን ለምን ከእሱ እንደጠበቅኸኝ ገባኝ። አልሐምዱሊላህ!” ትዪ ይሆናል። ምናልባት የምትፈልጊው ሰው አላህ ላንቺ የማይስማማ መሆኑን ያውቃል። ምናልባት እሱ የልብ ሰባሪሽ ይሆን ነበር። ምናልባት ዲንሽን ያዳክም ነበር። ምናልባት ልጆችሽ የማይገባቸውን ነገር እንዲያዩ ምክንያት ይሆን ነበር። አንቺ ግን አታውቂም፤ አላህ ያውቃል። ስለዚህ አንድ በር ሲዘጋ አታልቅሺ፤ ምናልባት ከኋላው ያለውን ጉዳት አላህ እያራቀልሽ ይሆናል።            አደራ አደራ ...... በትዳር መዘግየት ምክንያት የማይመችሽን ሰው አትቀበዪ። የትዳር ጉዳይ የአንድ ቀን ደስታ ብቻ አይደለም። ትዳር ዕድሜ ነው። ትዳር ቤተሰብ ነው። ትዳር ልጆች ናቸው። ትዳር ዲን ነው። ትዳር የወደፊት ሕይወት ነው። ስለዚህ ከገንዘብ፣ ከውበትና ከማዕረግ በፊት ዲንና መልካም ሥነ-ምግባር ተመልከቺ። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «إذا جاءكم من ترضون دينه وخلقه فزوجوه» “ዲኑንና ሥነ-ምግባሩን የምትወዱት ሰው ወደናንተ ከመጣ አጋቡት።”                እህቴ ሆይ…እያነበብሽ ነዋ አላህ የጻፈልሽ ነገር በፍጹም አያመልጥሽም። ሰዎች ቢያግዱት ይመጣል። ሩቅ ቢሆን አላህ ያቀርበዋል። ጊዜው ቢዘገይ ጊዜው ሲደርስ ይመጣል። አላህ ያልጻፈልሽ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ቢሰበሰቡ ሊያገኙልሽ አይችሉም። ስለዚህ እንዲህ በይ፦ “ያ ረቢ! እኔ በአንተ እተማመናለሁ። ለእኔ ምረጥልኝ፤ እኔ ለራሴ የማላውቀውን አንተ ታውቃለህ። ለእኔ የሚሆነውን አንተ ምረጥ።” ከዚያም ልብሽን አሳርፊ። አትጨነቂ። አትቸኩዪ። ተስፋ አትቁረጪ። የአላህን ምሕረት አትጠራጠሪ። ምክንያቱም… እንባሽን ያየ አላህ አለ። ዱዓሽን የሰማ አላህ አለ። ልብሽን የሚያውቅ አላህ አለ። ዕጣሽንም በእጁ የያዘ አላህ አለ። በመጨረሻም አላህ ሆይ! በሙስሊም ሴቶች ልብ ውስጥ ያለውን፣ አንተ ብቻ የምታውቃቸውን ምኞቶች ፈጽምላቸው። አላህ ሆይ! ለእነርሱም ሳሊህ ባሎችን ስጣቸው፤ በዲናቸው ላይ የሚረዷቸውን፣ የሚያከብሯቸውን፣ የሚወዷቸውንና በእነርሱ ጉዳይ አንተን የሚፈሩትን ስጣቸው። አላህ ሆይ! የተሰበረ ልብ ካለ አጽናው። ብቸኛ ልብ ካለ አጽናናው። የሚጠብቅ ልብ ካለ በመልካም ነገር አስደስተው። አላህ ሆይ! ከእያንዳንዱ መጠበቅ እፎይታን፣ ከእያንዳንዱ ዱዓ መልስን፣ ከእያንዳንዱ ሐዘን ደስታን ስጣቸው። አላህ ሆይ! ባል የሌላት አንዲትም ሴት አትተው፤ ለእሷ የሚሆን ሳሊህ ባል ስጣት። የተሰበረ ልብ አትተው፤ ጽናትና ደስታ ስጠው። አላህ ሆይ! በኢማን፣ በፍቅር፣ በምሕረትና በሰላም የተሞሉ ቤቶችን ስጣቸው።                  አሚን ያ ረብ ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba