قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Відкрити в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
914
Підписники
-324 години
-177 днів
+5330 днів
Архів дописів
Repost from ስለ ዲናችን
ከሞት በኋላ ላለው ሀገር መዘጋጀት
🎙በሸይኽ ከማል
🕌በደገር ከተማ
መስጂድ ኑር ላይ የተደረገ
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/Yedeger_selefioch_jemea
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
●➝ይኑራችሁ°°
ኸይር እንዲገጥማችሁ መራቂ እናት አባት፤
አብሽር ባይ መከታ ታማኝ ወንድም እህት፤
ተጨንቆ ጠያቂ አክስትና አጎት፤
በሀዘን በደስታው ከጎን የሚሆኑ፤
ይኑራችሁ ዘመድ ሞልቶ በግገኑ፤
በችግር አበርቺ ደርሶ ወጋገኑ፤
አትጡ ቤተሰብ የደስታ ሞሰብ፤
እናት ይኑራችሁ በሩቅ የምታስብ፤
ስትደክሙ አበረታች አብሽር ባይ አናብስት፤
የችግር ተካፋይ የጀግንነት አርስት፤
ሚስት ትኑራችሁ ከሩቅ የምትሰስት፤
አብሽር ባይና አፅናኝ ከጎንሽ የሚቆም፤
ይኑርሽ ውድ ባል ሰርቶ የማይደክም፤
ሚስጥርን ተካፋይ አማካሪ ወንድም፤
የምትወዱት ከልብ በሙቀት በበብርድም፤
አቤት የሚል ታማኝ ጓደኛ እሚያምናችሁ፤
አበረታች ወገን ሁሌም ይኑራችሁ፤
✍ወንድማችሁ አቡ ሹራ
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid
“በእውነት ዘረኝነት እየሠራ ነውን? ወይስ የምንወቅሰው የግሩፑ ስም ብቻ ነው?”
ምክንያቱም ስሙን ተመልክተን የሰውን ኒያ መፍረድ አንችልም።
እንዲሁም አንድ ሰው ተሳስቶ ከተገኘ፣ ምክር እንስጠውጅ፤ ሰውን በነገር አንውጋ።
የሰለፊያ መንሐጅ የሚያስተምረን እውነትን በእውነት እንድንመዝን እንጂ ሰዎችን በግምትና በጥርጣሬ እንድንመዝን አይደለም።
🌍 ከአካባቢ ተነስተን ለሁሉም ተውሒድን ሱናን ሰለፊያን እናድርስ!
በእውነት የሚያምረው አካሄድ ይህ ነው፦
የደሴ ልጆች የደሴን ልጆች ይሰብስቡ።
የራያ ልጆች የራያን ልጆች ይሰብስቡ።
የወረባቦ ልጆች የወረባቦን ልጆች ይሰብስቡ።
የመርሳ ልጆች የመርሳን ልጆች ይሰብስቡ።
የሀርቡ ልጆች የሀርቡን ልጆች ይሰብስቡ።
የአዲስ አበባ ልጆች የአዲስ አበባን ልጆች ይሰብስቡ። ሁሉም በያለበት ይሰባሰብ ይዋደድ ይከባበር ይተጋገዝ አንዱን አንዱ አይጥላ አንዱ ከሌላው የተሻልኩ ነኝ ብሎ አያስብ በሰለፊያ ላይ አንድ እንሁን።
ነገር ግን ከዚያ በኋላ፦
ሁላችንም በተውሒድ እንሰብሰብ፣
በሱና እንሰብሰብ፣
በቁርኣን እንሰብሰብ፣
በኸይር እንተባበር፣
በአካባቢ ሳንለያይ በእስልምና በሱና እንደጋገፍ። ይህ ነው የሚያምረው።
አንድ አካባቢ ልጆች ተሰብስበው ቁርኣን ይቀራሉ፤ ሌላው አካባቢ ደግሞ ይህንን አይቶ ይማራል።
“እነሱ እዚያ ተሰብስበው ቁርኣን እየተማሩ ነው፤ እኛም በአካባቢያችን እንጀምር እንጠክር!”ይላል።
ከዚያ ሌላ አካባቢ ይነሳል።
ከዚያ ሌላ።
በመጨረሻም በውጭ ሀገርም በሀገር ውስጥም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች፦
ቁርኣን የሚቀሩ፣
ኪታብ የሚያጠኑ፣
ደዕዋ የሚያደርጉ፣
ወላጅ አልባን የሚረዱ፣
መስጂድን የሚገነቡ፣
መርከዝን የሚደግፉ፣
እርስ በርሳቸው የሚጠናከሩ ትውልድ ይፈጠራል ከዛም ትልቅ የኸይር ንቅናቄ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
⚠️ የመጨረሻ ምክሬ ለሰፊይ ወንድምና እህቶቼ
የሰለፊይ ወንድማማችነት እንዳይሰበር እንጠንቀቅ።
የምንሠራውን ኸይር እንመርምር፤ የምንተቸውንም ሰው በፍትሕ እንመርምር።
የአካባቢ ስም መጠቀም በራሱ ዘረኝነት አይደለም።
የአካባቢን ስም በመጠቀም ሌሎችን መንቀፍና ማጥላላት ግን የሚወገዝ ነው።
የአካባቢን ልጆች ለማጠናከር መሰብሰብ የሚከለከል አይደለም፤ ሌሎችን በማሳነስ ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ግን አይፈቀድም።
የሰለፊይ ወንድማማችነት ከደሴ ይበልጣል፤ ከራያ ይበልጣል፤ ከወረባቦ ይበልጣል፤ ከአዲስ አበባ ይበልጣል ከስልጤ ይበልጣል ከኦሮሞ ከአማራ ከትግራ ከሶማሌ ከአሜሪካ ከቻይና ከቱርክ ከሳዑድ ከሁሉ ይበልጣል የትም ሀገር ቢሆን ሰለፊይ አስከሆነ ድረስ ወንድማችን ነው እህታችን ናት ይሄ ነው ሚዛናችን።
ስለዚህ ከአካባቢያችን እንነሳ፤ ነገር ግን በአካባቢያችን አንወሰን ደዕዋውን እናስፋው።
ከሰፈራችን እንነሳ፤ ነገር ግን ሌላውን አንግፋ።
የእኛን ልጆች እናጠናክር፤ ነገር ግን የሌላውን ልጅ አንጠላ አንርሳ።
በተውሒድ እንሰብሰብ፣ በሱና እንጠናከር፣ በኸይር እንተባበር፤ የአካባቢ ልዩነታችን ደግሞ የምንተዋወቅበት መንገድ እንጂ የምንለያይበት ግድግዳ አይሁን።
🌿 አላህ ልባችንን በተውሒድና በሱና ላይ ያሰባስበን፤ በኸይር ላይ እንድንተባበር ያድርገን፤ ከጃሂሊያ የወገንተኝነት መንፈስም ይጠብቀን። አሚን።
🌿 ከአካባቢ ተነስተን—ለኡማው ተውሒድና ሱናን እናድርስ!
ውድ ሰለፊይ እህትና ወንድሞች በዚህ ፅሁፍ ላይ ስህተት ካገኛችሁ መታረም ያለበት ነገር ካለ ጠቁሙኝ አስተካክሉኝ
ይሄን ፅሁፍ በመልካም ተረዱት መልካም ነገር ታስቦ የተፃፈ ነውና።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Abu Hayder Aliy
🛑 ما نصيحتكم للشبــــــاب ، و خـــــــاصة طلبـة العلـــــم 🍁⁉️
الشيخ صالح الفوزان حفظه اللّه
ጥያቄ (السؤال):
በዚህ ጊዜ ለወጣቶች፣ በተለይም ለሃይማኖት ዕውቀት ፈላጊዎች (ተማሪዎች) የሚሰጡት ምክር ምንድን ነው?
የሼክ ሳሊህ አል-ፈውዛን መልስ ባጭሩ (إجابة الشيخ):
የወጣቶች አስፈላጊነት፡ ወጣቶች ከአላህ በመቀጠል የሕዝቡ (ኡማው) ፍሬና መሠረት ናቸው፤ ምክንያቱም ከአባቶቻቸው በኋላ ይህንን ታላቅ ኃላፊነትና የበላይነት የሚወርሱትና ለሰው ልጅ የሚያደርሱት እነሱ ናቸውና።
ኃላፊነትና ጥንቃቄ፡ ለወጣቶች ትኩረት መስጠት ይገባል፤ ወጣቶችም ግዴታቸውን አውቀው ኃላፊነትን ለመሸከም ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው።
ከተሳሳቱ አስተሳሰቦች መጠበቅ፡ በተለይም በዚህ ዘመን ወጣቶች ከባዕድ አስተሳሰቦች እና ወደ ጥመት ከሚጠሩ አካላት (ለምሳሌ፡ የኸዋሪጅ፣ የሙርጂኣ፣ የሙዕተዚላ እና የሌሎች መንገድ ተከተዮች አደገኛ አስተሳሰቦች) መጠንቀቅና ንቁ መሆን አለባቸው።
ትክክለኛውን መንገድ መከተል፡ የነቢዩ ባልደረቦች (ሶሓባዎች)፣ ተበእዮችን፣ የተመሰገኑት ክፍለ ዘመናት ሰዎች፣ አራቱ አኢማዎችና በጎ ተከታዮቻቸው የጸኑበትን የአህል-ሱና ወል-ጀማዓን መንገድ አጥብቆ መያዝ አስፈላጊ ነው።
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
قال الشيخ حمَّاد الأنصاري رحمه الله:
... لم يؤلِّف وينشر ويطبع ضدَّ الدعوة السلفية أحد في الدُّنيا مثل تركيا ودولة الروافض في إيران، فإنَّ العقيدة السلفية ما قلَّ انتشارها حتَّى حكم الأتراك وهم نقشبندية، والنقشبندية أعداء للعقيدة السلفية ...
[المجموع: 2 - 691 ]
የኡስታዞች መታጣት ወይስ ኡስታዞች ገቢ ማጣት?
በተቻለ ያህል የዲን ሀላፊነት ላይ ያሉ ሰዎችን ማገዝ ሙስሊሙን ህዝብ ከማገዝ እና ለአኺራ ስንቅን ከማዘጋጀት መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።ነገር ግን ባሁኑ ሰዓት ትልቁ ችግር ኡስታዞች ሚኖሩበትን ያህል ገቢ ያለማግኘት አይደለም።በብዛት ቁርኣንም ይሁን ኪታብ አስተማሪዎች ወይ በደሞዝ አልያም በክፍያ ነው ሚያስቀሩት።ትልቅ ችግር እየሆነ ያለው ነገር ዳዒዎችን አራት አምስቴ እንኳ ጠርቶ ያለማግኘት ነው።በክፍያ እንኳ በተገኙ!!ምክንያቶቹ ብዙ ቢሆኑም ሙሉ በሙሉ በአካባቢ ቂርኣት ቢዚ መሆን እና በዱንያ ጉዳይ መይያዝ ተጠቃሽ ናቸው።
ከጥቂት አመታት በፊት ችግሩ በዚህ ደረጃ አልነበረም።በየአካባቢው በጥቂት ሳምንታት ወይም ወራት ውስጥ በቀላሉ የዳዕዋ እድል ይገኝ ነበር።አሁን ላይም ቢሆን-አላህ የኸይር ጀዛቸውን ይመንዳቸውና-ጊዜ እና ሌላ ሐጃቸውን መስዋዕት አድርገው ለዳዕዋ ቅድሚያ ሚሰጡ ዳዒዎች መኖራቸው አይካድም።
ዳዕዋ በማድረግ የሚገኘው ጥቅም ኪታብን እንደማስቀራት ጥልቅ ባይሆንም እንኳ ተነሳሽነትን እና ወኔን ከመፍጠር አንፃር የሚናቅ አይደለም።ብዙ መለማመጥ ሳይኖር ዳዒዎች ተናበው የተቀናጀ ስራ ቢሰሩ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይቻላል።ማይሳካ ከሆነም ሌላ ሚያነቃን አካል ሳንጠብቅ በራሳችን ተነሳስተን መደበኛ የዒልም ማእዶችን መከታተል እና በአላህ ፍቃድ ለወደፊት ችግሩን ለመፍታት የተቻለንን ያህል ማድረግ ነው።والله أعلم
ሁለት ሰዎች ብቻ በጀማዐ ሲሰግዱ ተከታዩ ከኢማሙ ትንሽ ወደ ኋላ መሆን ልክ ነው?
~
ሁለት ሰዎች ብቻ ጀማዐ ሶላት የሚሰግዱ ከሆነ ተከታዩ ከኢማሙ ትንሽ ወደ ኋላ ሆኖ ሲቆም ማየት የተለመደ ነው። በርግጥ ይህንን የመረጡ ዓሊሞች አሉ። ይሁን እንጂ ትክክለኛው አፈፃፀም ተከታዩ ከኢማሙ ጋር እኩል ሆኖ መቆሙ ነው። ኢማሙል ቡኻሪ ረሒመሁላህ በሶሒሕ ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ የሚል ርእስ አስፍረዋል፦
" يَقُومُ عَنْ يَمِينِ الإمَامِ بحذائهِ سواءً، إذا كَاناَ اثْنَيْن".
“ከኢማሙ በቀኙ በኩል እኩል ሆኖ ይቆማል፣ ሁለት ከሆኑ።”
ከዚያም ተከታዩን የኢብኑ ዐባስን ረዲየላሁ ዐንሁማ ሐዲሥ አስፍረዋል፦
"بِتُّ فِي بَيْتِ خَالَتِي مَيْمُونَةَ، فَصَلَّى رَسُولُ اللَّهِ ﷺ العِشَاءَ، ثُمَّ جَاءَ فَصَلَّى أَرْبَعَ رَكَعَاتٍ، ثُمَّ نَامَ، ثُمَّ قَامَ، فَجِئْتُ فَقُمْتُ عَنْ يَسَارِهِ، فَجَعَلَنِي عَنْ يَمِينِهِ،... "
“ከየሹማዬ መይሙና ዘንድ አድሬ ነበር። የአላህ መልእክተኛ ﷺ ዒሻእን ሰገዱ። ከዚያም (እቤት) መጡና አራት ረከዐዎችን ሰገዱ። ከዚያም ተኙ። ከዚያም ለሶላት ቆሙ። በግራቸው በኩል ቆምኩኝ። በቀኛቸው አደረጉኝ።...” [ቡኻሪ፡ 697]
“ይሄ የኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ ሐዲሥ እኩል ሆኖ መቆምን ያስጨብጣል ወይ?” ከተባለ “አዎ” ነው መልሱ። ኢብኑ ሐጀር ረሒመሁላህ “ከቀኝ ጎናቸው አደረጉኝ” የሚለውን የኢብኑ ዐባስን ንግግር ሲያብራሩ “ጉልህ መልእክቱ እኩል ሆኖ መቆም ነው” ብለዋል።
የቡኻሪን ርእስ አስመልክተውም እንዲህ ብለዋል፦
በዚህ ርእስ አሰጣጣቸው የፈለጉት በሶላት ውስጥ ኢማምና ተከታይ ብቻቸውን ከተገኙ ተከታዩ ከኢማሙ በቀኝ ጎን እኩል ሆኖ ማለትም በመቆሚያው ቦታ ላይ መቀደምም ሆነ መዘግየት ሳይኖር እኩል መሆናቸው ነው።” [ፈትሑል ባሪ፡ 6/197]
.
በሌላ ዘገባ ላይም ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦
" أَتَيْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مِنْ آخِرِ اللَّيْلِ، فَصَلَّيْتُ خَلْفَهُ، فَأَخَذَ بِيَدِي، فَجَرَّنِي، فَجَعَلَنِي حِذَاءَهُ، فَلَمَّا أَقْبَلَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَى صَلاتِهِ، خَنَسْتُ، فَصَلَّى رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَلَمَّا انْصَرَفَ قَالَ لِي: مَا شَأْنِي أَجْعَلُكَ حِذَائِي فَتَخْنِسُ؟
فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ! أَوَيَنْبَغِي لِأَحَدٍ أَنْ يُصَلِّيَ حِذَاءَكَ، وَأَنْتَ رَسُولُ اللهِ الَّذِي أَعْطَاكَ اللهُ؟
قَالَ: فَأَعْجَبْتُهُ، فَدَعَا اللهَ لِي أَنْ يَزِيدَنِي عِلْمًا وَفَهْمًا... "
“የአላህ መልእክተኛ ﷺ ዘንድ የሌሊቱ መጨረሻ ላይ መጣሁኝ። ከኋላቸው ልሰግድ ቆምኩኝ። እጄን ይዘው በመጎተት ከሳቸው ጎን ትይዩ አቆሙኝ። የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶላታቸው ላይ ሲያተኩሩ ጊዜ ወደኋላ አልኩኝ። የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሰገዱ። ባጠናቀቁ ጊዜ፦ ‘ምነው? እኔ በጎኔ ሳደርግህ ወደኋላ ትላለህሳ?’ አሉኝ።
‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በአንተ ትይዩ ሆኖ ለማንስ ሊሰግድ ይገባዋልን? አንተ አላህ ያደለህ የአላህ መልእክተኛ ሆነህ ሳለ?’ አልኳቸው። ገረምኳቸው። እውቀትንና ግንዛቤን እንዲጨምረኝ አላህን ለመኑልኝ።” [አሶሒሐህ፡ 6/174 - 175]
ከጃቢርም ተመሳሳይ መልእክት ተላልፏል። [ሙስሊም፡ 3010]
በተጨማሪም ዐብዱላህ ብኑ ዑትባህ ብኒ መስዑድ እንዲህ ብለዋል፦
دخلت على عمر بن الخطاب رضي الله عنه بالهاجرة «فوجدته يسبح، فقمت وراءه. فقربني حتى جعلني حذاءه عن يمينه»
“ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘንድ ቀትር ላይ ስገባ ሱና እየሰገዱ አገኘኋቸው። ከኋላቸው ቆምኩኝ። በቀኛቸው በኩል አድርገው አቀረቡኝ።” [ሙወጦእ ማሊክ፡ ሐዲሥ ቁ. 364]
.
አልሓፊዝ ኢብኑ ረጀብም ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
" الإمام إذا لم يأتم به غير واحد، فإنه يقيمه عن يمينه بحذائه، ولو كان صبيا لم يبلغ الحلم. وهذا كالإجماع من أهل العلم.
وقد حكاه الترمذي فِي "جامعه" عَن أهل العلم من أصحاب النّبيّ - صلّى الله عليه وسلّم - فمن بعدهم، قالوا: إذا كان الرّجل مع الرّجل يقوم عن يمين الإمام. وحكاه ابن المنذر عَن أكثر أهل العلم... "
“አንድ ኢማም ከአንድ ሰው ውጭ የሚከተለው ከሌለ በቀጥታ ከቀኙ በኩል ሊያቆመው ይገባል። ለአቅመ ሃላፊነት ያልደረሰ ህፃን ቢሆን እንኳ። ይሄ የእውቀት ባለቤቶች ዘንድ ልክ እንደ ኢጅማዕ ነው። ቲርሚዚ በጃሚዐቸው ውስጥ ከነብዩ ﷺ ባልደረቦች እና ከነሱ በኋላ ከመጡ አዋቂዎች ጠቅሰውታል። አንድ ሰው ከአንድ ሰው ጋር ብቻ ከሆነ ከኢማሙ ቀኝ ይቆማል ብለዋል። ኢብኑል ሙንዚርም ከብዙ የእውቀት ባለቤቶች ጠቅሰውታል።” [ፈትሑል ባሪ፡ 6/197 – 198]
በተጨማሪም ኢብኑ ጁረይጅ ረሒመሁላህ “ 'አንድ ሰው ከአንድ ሰው ጋር ብቻ ሆኖ የሚሰግድ ከሆነ ከየት በኩል ነው የሚሆነው?' ብየ ዐጧእን ጠይቄ ነበር” ይላሉ።
ዐጧእ፦ “በቀኙ በኩል” አሉ።
ኢብኑ ጁረይጅ፦ “አብሮት እስከሚሰለፍ ድረስ በሱው አቅጣጫ ነው የሚሆነው? አንዱ ሌላውን ሳይቀደም?”
ዐጧእ፦ “አዎ!”
ኢብኑ ጁረይጅ፦ “በመሃላቸው ክፍተት እስከማይኖር ድረስ?
ዐጧእ፦ “አዎ!” [ሙሶነፉ ዐብዲረዛቅ፡ ቁ. 3870]
ስለዚህ ሁለት ሆነው በሚሰግዱ ጊዜ ከኢማም ትንሽ ወደ ኋላ መቅረት ምንም እንኳ የደገፉት ዓሊሞች ቢኖሩም ማስረጃ የሚደግፈው ግን አይደለም። ይህንን ማድረግ የተወደደ ቢሆን ኖሮ ተጨባጭ መረጃ ከነብዩ ﷺ ይተላለፍ ነበር። ነገር ግን የለም። ከሶሐቦችም ይገኝ ነበር። ይህም የለም። መረጃ አለመኖሩ መሰረት እንደሌለው ያሳያል። እንደሚታወቀው ነብዩ ﷺ “ስሰግድ እንዳያችሁኝ ስገዱ” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 631] የሳቸው አሰጋገድ ውስጥ ደግሞ ከአንድ ተከታይ ጋር ብቻ ሆነው በሰገዱበት ላይ ትንሽ የተቀደሙበት አልተገኘም። ይልቁንም የተገኘው ከዚህ በተለየ እኩል ጎን ለጎን መቆም ነው። ይሄኛው አቋም ከዘመናችን ዓሊሞች ውስጥ የኢብኑ ባዝ፣ የአልባኒይ እና የኢብኑ ዑሠይሚን አቋም ነው።
=
@IbnuMunewor
Repost from N/a
🎵 አባታዊ ምክር 🎵
👉 የዚድ (አድ ደያ፞ን) ቢን ቀጠን አል ሃሪሲይ ሴት ልጁን እንዲህ ሲል መከራት :
✔️ ልጄ ሆይ! ድምፅሽ ከባልሽ ድምፅ በላይ ከፍ አይበል,
✔️ ጉዳይሽ ከጉዳዩ በላይ አይሁን,
✔️ ደግሞም እወቂ! የተከበሩ ሴቶች ማለት ተሸናፊዎች እንጂ አሸናፊዎች አይደሉም,
✔️ ባልሽ ትንሽ ነገር ቢሰጥሽ ተጨማሪ ጠይቂ እንጂ ስጦታውን አትናቂ,
✔️ በዛ አድርጎ ከሰጠሽ ደግሞ አመስግኚው እንጂ አትኩሪ,
✔️ የሆነ ስነ ምግባሩ ቢያስጠላሽ/ቢያስከፋሽ/ ለዘብተኛ ሁኚለት,
✔️ እወቂ! ቸር የሆነ ድሃ ስስታም ከሆኑ አስር ሀብታሞች ይሻላል።
🔑 أَوصى الديَّان بن قطن الحارثي ابنته؛ فقَال:
💎 «يا بُنيَّة لا يَعلوَنَّ صوتُكِ على صوتِ زوجك،
💎 ولا يكون أمركِ علَى أمره،
🧿 واعلمي أنَّ كِرام النِّساء المَغلوبات لا الغالِبات،
🧿 فإنْ أعطاكِ يسيرًا؛ فاستَزيدي ولا تُحقِّري، وإنْ أكثَر لكِ فاشْكُري ولا تبطري،
💎 وإنْ ساءتكِ منه خليقة، فكوني به رقيقة،
💎 واعلمي أنَّ جوادًا مُعسرًا خير مِن عَشرة مَياسير بُخلاء».
https://t.me/Abusehla1
ስለ ጀምዕያ የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ አከባቢ ❶❹ ሙሓደራወች❶ጀምዕያ ማለት ምን ማለት ነው ❷ኡለሞች የፈቀዷት ጀምእያ ❸እውን በጀምዕያ ብቻ ሰዎችን ከሱና ማስወጣት ይቻላልን? ❹ጀምዕያ እና ተያያዥ ነጥቦች ❺ጀምእያ በረሱል ጊዜ ከሌለች ለምን ቢድአ አልተባለችም? ❻ጀምእየቱል ኸይርያ ❼ጀምዕያ እና ሹበሀወች ➑በስማቸው የተመሰረት ያቋቋሙት ጀምዕያ ❾ሙስጠፋ ጀምዕያ የፈቀደበት ➓ሙስጠፋ ጀምዕያን በግልፅ ሲፈቅድ ጀምዕያ ላይ ውይይት ሰለፍዮች እና ሀጁሪዩች
ኡስታዝ አቡ ረይስ ሙሐመድ እና ሌሎችም ወንድሞች እና ሀጁሪዮችክፍል ❶ ክፍል ❷ በከለላ ከተማ የተደረገ
በኡስታዝ አቡ ሂዛም አብዱረህማን ሰኢድ &የተለያዩ ሀጁሪዮችክፍል ❶ ክፍል ❷
እውን ሰው ስለሌለ ነው ሙስሊም የማይሽሾመው?
~
በሃገር አቀፍ ደረጃም ይሁን በአንዳንድ ክልሎች ቁልፍ የሹመት ድልድል ላይ ሊስተካከል ያልቻለ፣ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ሙስሊሞችን ማግለል ይታያል። ይሄ ማንም የሚታዘበው ሐቅ ነው።
ታዲያ ሙስሊሞች ይህንን ጉዳይ በማንሳት ቅሬታቸውን ሲገልፁ ተደጋግሞ የሚነሳ በቅጡ ያልተፈተሸ አንድ ግልብ ምላሽ አለ። ይሄውም "ሙስሊሙ ከፖለቲካ ወይም ከትምህርት ስለሚርቅ ነው ይሄ የሚሆነው" የሚል ነው። አዎ ከፖለቲካውም ከትምህርቱም የሚርቀው ሙስሊም ቀላል አይደለም። ለዚህ ብዙ ምክንያቶች አሉ። ይሄ ራሱን ችሎ የብቻው መታየት ያለበት ጉዳይ ነው።
ነገር ግን "ሙስሊሙ ከፖለቲካ ወይም ከትምህርት ስለሚርቅ ነው ይሄ የሚሆነው" ማለት በቅጡ ያልተፈተሸ ሰነፍ ድምዳሜ ነው። ይህንን የዋህ ምላሽ ማን እንደጀመረው እንጃ የሚያስተጋባው ብዙ ነው። ያልተማረው ብቻ ሳይሆን ቀለም የቀመሰውም ጭምር ቁም ነገር ብሎ ሲቀባበለው ይደንቀኛል። አግላዮቹ አካላት የሚሾሙት ሙስሊም ጠፍቶ ተቸግረው እንጂ እነሱ ከፍተው አይደለም የሚል አንድምታ ያለው አፍ ማስያዣ ነው ይሄ ምላሽ። እውነታው ፈፅሞ እንደዚያ አይደለም። በሃገር ደረጃም ይሁን በክልል ወይም ከዚያ በታች ባሉ እርከኖች ላይ ቀላል የማይባል የተማረ ሙስሊም አለ። ሙስሊም የማይሾሙት ፈልገው ስላጡ አይደለም። በጭራሽ!
እውነትነት የሌላቸው ምክንያቶችን መደርደር ለሴረኞች ጥሩ ሰበብ ማቀበል ነው። ችግሩ አጋጣሚ እንዳይመስላችሁ። በአብዛኛው የታቀደበት ነው። ታች ወርዳችሁ ሙስሊም በዝ የሆኑ ወረዳዎችን ጭምር መታዘብ ትችላላችሁ። በቂ የተማረ ሙስሊም ባለበት ሁኔታ የሙስሊም አመራሮች ቁጥር ግን የለም ባይባልም በጣም የሳሳ ነው። እዚች ሃገር ውስጥ ከላይ ከምናየው በላይ በህቡእ የሚንቀሳቀሱ ስውር እጆች አሉ። ለውጥ ለማምጣት ትግል ያስፈልጋል እንደምትሉኝ አስባለሁ። እውነት ነው። ያልሆነ ምክንያት መደርደር ግን ትግል አይደለም። ይሄ ለሴረኞች ዱላ ማቀበል ስለሚሆን ብናስተውል መልካም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
በአካባቢያችሁ ቁርኣን ወይም ኪታብ የሚያስተምሩ፣ የመስጂድ ኢማሞች፣ ሙአዚኖች ኑሯቸው ምን ይመስላል? ምን ያህል ድጋፍስ ይደረግላቸዋል? የቤት ኪራይ፣ የቤተሰብ ወጭ፣ የህክምና፣ የልጆች ትምህርት፣ ብዙ ጣጣዎች አሉ። የአብዛኞቹ ኑሮ በጣም ከባድ ነው። አላህ አቅም የሰጠው ሰው ቢያግዛቸው ለነሱ ብቻ ሳይሆን ለህዝብ ጭምር ትልቅ ውለታ መዋል ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from الــــســــنـــةسفــــينة نــــــــوح🖊
የፍቅር ስቃይ.....!
በኡስታዝ አቡ ሱፍያን አላህ ይጠብቀው!
ስለ ቀልባችን☑️
➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
ሐዘን ልብን ያደክማል፤ የሰውን ልጅ ጽናትና ብርታት ያላላል
ታላቁ ዓሊም የኢማም ኢብኑል ቀይም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "ያለፉ አሳዛኝ ትውስታዎችን ደጋግማችሁ ወደ ራሳችሁ
አትጥሩ!"
ሐዘን ልብን ያደክማል፤ የሰውን ልጅ ጽናትና ብርታት ያላላል፤ እንዲሁም ጠንካራ የመሥራት ፍላጎትንና ውሳኔን (ኢራዳን) ይጎዳል።
ለአማኝ ባሪያ ከሐዘንና ከተስፋ መቁረጥ ይበልጥ በሰይጣን ዘንድ የሚወደድ (የሚያስደስት) ምንም ዓይነት ነገር የለም። ምክንያቱም ሰይጣን አማኝን በሐዘን ሰንሰለት አስሮ ከጌታው መንገድና ከሕይወት ብርሃን ሊያርቀው ይፈልጋልና።
ስለዚህ ወዳጄ ! ያለፈውን አሳዛኝ ታሪክህን እየቆሰቆስክ ዛሬህን አታጨልም። ሐዘን የሰይጣን ትልቁ መሣሪያ መሆኑን
አውቀህ፤ ልብህን በጌታህ እዝነትና በተስፋ ብርሃን አስውበው። ጌታችን አላህ ከሐዘን፣ ከጭንቀትና ከሰይጣን ወስዋስ ይጠብቅን።
https://t.me/Asselefiyah_Channel
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
የጀነት በር ጠባቂ መላዒካ ረድዋን ይባላል፡፡
⚠️አስቸኳይ የነፍስ አድን ጥሪ
👉ያአህባብ እዪልኝ ይሄን በጭፈራ ላይ የተመሠረተ አምልኮ የልዕለ ሀያሉ ጌታችንን አላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ እንደት እንደተዳፈሩት እያያችሁ ነዉ የመኪና ብዛት የህዝብ ስብስብ ዶሪህ ለመለመን ችግራቸዉን ለጅን አቤቱታ የሚያቀርቡ ከሙስሊሙ የወጡ ሰዎች ባሻገር ክሪስቲያኖች ጭምር ለአላህ በመናገር ፋንታ ግን እነሱ ምንም ለማያደርግላቸዉ ዶሪህ ተናግረዉ ይሄዳሉ በአመቱ ተመልሰዉ መተዉ ስለታቸዉን ለጅን ያርዳሉ!!
የቦረናው ሸህዬ
የቦረናው ደግዬ
እርዱን አባብዬ
ይህ የሽርክ ግጥም የሚዘመርባት ከተማ ከ500ሺ ህዝብ በላይ ሽርክን ለማንገስ ከአድስ አበባ እስከ ባሌ ከወለጋ እስከ ሐረር ከወሎ እስከ ጎጃም ከጎንደር እስከ ሸዋ ሳይቀር ሰው ስለቱን ይዞ ኮርማውን እየነዳ ሽቱውን ገዝቶ መጋረጃ ሸምቶ ልክ እንደ ግሸን ማርያም ክብረ_በዓል መንገድ በአይሱዚና በቅጥቅጥ እንድሁም በህዝብ ብዛት ጥቅምት 15 የዶሪኋን ታቦት በማነገስ ከተማዋ ትጨናነቃለች ። በዚያ ሌሊት የሚጎራ ጉሪያ የሚወገር ድቤ የሚጮህ ጩኸት የሚለቀስ ለቅሶ የሚጨስ አድሩስ የሚታረድ በግና ፍየል ምን ልበልህ ባጭሩ ራሷ ከተማዋ ታብዳለች ።
ለወንድም እህቶቼ ፦
ወንድም እህቶቼ፣ በየዓመቱ ብዙ ሰዎች ችግራቸውን ይዘው ወደ እዚህ ቦታዎች ይጓዛሉ። ብዙዎቹ በሕመም፣ በችግርና በጭንቀት የተጎዱ ናቸው።
ስለምንወዳቸው ነው የምናስታውሳቸው፤ ከአላህ ውጭ ሌላ አያድናቸውም።1️⃣ አላህ ቅርብ ነው وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ «ባሮቼ ስለ እኔ ቢጠይቁህ እኔ ቅርብ ነኝ፤ ለማኙ ሲለምነኝ ልመናውን እቀበላለሁ።»
ሱረቱል -በቀራህ ምዕራፍ 2:አንቀፅ 186وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ «ጌታችሁም አለ፦ ለምኑኝ፣ እመልስላችኋለሁ።»
ሱረቱል ጋፊር ምዕራፍ 40:አንቀፅ 60አላህ ከእኛ ጋር አማላጅ ሳያስፈልገው ቅርብ ነው። በሌሊት፣ በሱጁድ፣ በየትኛውም ቦታ ልንለምነው እንችላለን። 2️⃣ ዱዓ ኢባዳ ነው «الدُّعَاءُ هُوَ الْعِبَادَةُ» «ዱዓ (ልመና) ኢባዳ (አምልኮ) ነው።»
📚ቲርሚዚ፣ አቡ ዳውድ ዘግበውበታልኢባዳ ደግሞ ለአላህ ብቻ ይገባል፦ وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا «መስጊዶች የአላህ ናቸው፤ ስለዚህ ከአላህ ጋር ማንንም አትለምኑ።»
ሱረቱል አል-ጂን ምዕራፍ 72:አንቀፅ 18)«إِذَا سَأَلْتَ فَاسْأَلِ اللَّهَ، وَإِذَا اسْتَعَنْتَ فَاسْتَعِنْ بِاللَّهِ» «ከጠየቅህ አላህን ጠይቅ፤ ርዳታ ከፈለግህ በአላህ ተረዳ።»
📚ቲርሚዚ ዘግበውታል3️⃣ ከአላህ ሌላ የሚለመኑት ሊጠቅሙ አይችሉም وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا دُعَاءَكُمْ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም:: ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም:: ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም
ሱረቱል ፋጢር ምዕራፍ 35:አንቀፅ 13-14ምንም ሊያደርጉልን የማይችሉትን መለመን ጊዜና ተስፋ ማባከን ነው። 4️⃣ ማረድ ለአላህ ብቻ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ لَا شَرِيكَ لَهُ «በል፦ ሶላቴ፣ እርዶቼ (ሥርዓተ አምልኮዬ)፣ ሕይወቴና ሞቴ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው። አጋር የለውም።»
ሱረቱል አል-አንዐም ምዕራፍ 6:አንቀፅ 162-163«لَعَنَ اللَّهُ مَنْ ذَبَحَ لِغَيْرِ اللَّهِ» «ለአላህ ላልሆነ ያረደን አላህ ረግሟል።»
📚(ሙስሊም) ዘግበውታል5️⃣ ሽርክ ከሁሉ የከበደ ሐጢአትነው إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ «አላህ በእሱ ላይ ማጋራትን አይምርም፤ ከዚያ ሌላውን ለሚሻው ይምራል።»
ሱረቱል አን-ኒሳእ አን ምዕራፍ 4:አንቀፅ 48ስለዚህ ነው የምናስጠነቅቀው፤ ስለምንጠላችሁ ሳይሆን ስለምንወዳችሁ። ወደ አላህ መመለስ (ተውበት) በር ግን ዛሬም ክፍት ነው። 6️⃣ ምን እናድርግ❓ 🤲 ችግራችሁን በሌሊት ተነስታችሁ በሱጁድ ለአላህ አቅርቡ። 🩺 ሕመም ካለ ወደ ሐኪም ሂዱ፤ ከሕክምና ጋር ሩቅያ ሸርዒያን (በቁርኣንና በነቢያዊ ዱዓዎች መታከምን) ተጠቀሙ። 💝 ሰደቃ ስጡ፤ ለችግረኛ መርዳት ችግርን ያቀልላል። 📖 ተውሒድን ከታመኑ ዑለማ ተማሩ። 🌿 ቤተሰብና ጎረቤትን በፍቅር፣ በትዕግስትና በግል አነጋግሩ። አላህ ሁላችንንም ከሽርክ ይጠብቀን፣ ችግር ውስጥ ያሉትንም አውጣቸው፣ ወደ ቀጥተኛው መንገድም ይምራን። አሚን። የቴሌግራም ቻናል t.me/yedeger_selefioch_jemea የቴሌግራም ግሩፕ t.me/yedeger_muslim_Wetatoch_jemea
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
ከወንጀሎች ቅጣቶች መካከል አንዱ፦ የእድሜን በረካ፣ የርዝቅን በረካ፣ የእውቀትን በረካ፣ የመልካም ተግባርን በረካ እና የዒባዳን በረካ የሚያጠፉ መሆናቸው ነው።ባጠቃላይ፣ የሃይማኖትንም ሆነ የዱንያን በረካ ያጠፋሉ።
ابن القيم | الداء والدواءt.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
↩من أعظم النعم على المؤمن .. أن يهبه بصيرة يميّز بها الحق من الباطل والطيب من الخبيث والخير من الشر.
