ru
Feedback
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Открыть в Telegram

# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Канал FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት (@fdredefenseforc) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 42 729 подписчиков, занимая 6 090 место в категории Новости и СМИ и 815 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 42 729 подписчиков.

Согласно последним данным от 26 сентября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 68, а за последние 24 часа — 57, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 9.07%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 7.97% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 874 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 3 402 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 31.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 27 сентября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Новости и СМИ.

42 729
Подписчики
+5724 часа
+3367 дней
+6830 дней

Загрузка данных...

Облако тегов
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Входящие и исходящие упоминания
---
---
---
---
---
---
Привлечение подписчиков
сент. '26
сентябрь '26
+496
в 3 каналах
август '26
+492
в 3 каналах
Get PRO
июль '26
+529
в 3 каналах
Get PRO
июнь '26
+410
в 4 каналах
Get PRO
май '26
+1 413
в 8 каналах
Get PRO
апрель '26
+249
в 5 каналах
Get PRO
март '26
+295
в 4 каналах
Get PRO
февраль '26
+674
в 3 каналах
Get PRO
январь '26
+483
в 6 каналах
Get PRO
декабрь '25
+367
в 5 каналах
Get PRO
ноябрь '25
+809
в 6 каналах
Get PRO
октябрь '25
+832
в 2 каналах
Get PRO
сентябрь '25
+997
в 7 каналах
Get PRO
август '25
+511
в 3 каналах
Get PRO
июль '25
+532
в 3 каналах
Get PRO
июнь '25
+436
в 3 каналах
Get PRO
май '25
+848
в 5 каналах
Get PRO
апрель '25
+978
в 5 каналах
Get PRO
март '25
+1 262
в 5 каналах
Get PRO
февраль '25
+574
в 3 каналах
Get PRO
январь '25
+668
в 7 каналах
Get PRO
декабрь '24
+1 304
в 6 каналах
Get PRO
ноябрь '24
+1 358
в 8 каналах
Get PRO
октябрь '24
+1 531
в 7 каналах
Get PRO
сентябрь '24
+1 055
в 7 каналах
Get PRO
август '24
+1 415
в 5 каналах
Get PRO
июль '24
+725
в 6 каналах
Get PRO
июнь '24
+499
в 3 каналах
Get PRO
май '24
+4 830
в 4 каналах
Get PRO
апрель '24
+1 305
в 6 каналах
Get PRO
март '24
+2 140
в 6 каналах
Get PRO
февраль '24
+1 541
в 3 каналах
Get PRO
январь '24
+1 286
в 5 каналах
Get PRO
декабрь '23
+875
в 1 каналах
Get PRO
ноябрь '23
+816
в 1 каналах
Get PRO
октябрь '23
+934
в 2 каналах
Get PRO
сентябрь '23
+747
в 0 каналах
Get PRO
август '23
+1 156
в 0 каналах
Get PRO
июль '23
+443
в 0 каналах
Get PRO
июнь '23
+384
в 0 каналах
Get PRO
май '23
+798
в 0 каналах
Get PRO
апрель '23
+1 106
в 0 каналах
Get PRO
март '23
+246
в 0 каналах
Get PRO
февраль '23
+367
в 0 каналах
Get PRO
январь '23
+827
в 0 каналах
Get PRO
декабрь '22
+415
в 0 каналах
Get PRO
ноябрь '22
+266
в 0 каналах
Get PRO
октябрь '22
+843
в 0 каналах
Get PRO
сентябрь '22
+3 084
в 0 каналах
Get PRO
август '22
+2 993
в 0 каналах
Get PRO
июль '22
+1 996
в 0 каналах
Get PRO
июнь '22
+1 252
в 0 каналах
Get PRO
май '22
+4 577
в 0 каналах
Дата
Привлечение подписчиков
Упоминания
Каналы
27 сентября+10
26 сентября+57
25 сентября+137
24 сентября+152
23 сентября+14
22 сентября+15
21 сентября+2
20 сентября+7
19 сентября+8
18 сентября+14
17 сентября+2
16 сентября+8
15 сентября+8
14 сентября+12
13 сентября+2
12 сентября+2
11 сентября+9
10 сентября+4
09 сентября+4
08 сентября+2
07 сентября0
06 сентября+1
05 сентября+1
04 сентября+4
03 сентября0
02 сентября+11
01 сентября+10
Посты канала
2
ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ የጭንቀት ህመም ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም ጭንቀት የተለመደ እና ሁልጊዜ የሚከሰት የሰው ልጆች የህይወት ክፍል ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታ በገጠማቸው ጊዜ ከሥጋት የተነሳ የሚሰማቸዉ ውጥረት፣ ጫና፣ ግፊትና የሐሳብ ወይም የስሜት አለመረጋጋት ሲሆን ሰዎች ለገጠማቸው እንግዳ ነገር/አስቸጋሪ ሁኔታ የተፈጠሮ ስሜታቸው የሚሰጠው ግብረ-መልስ /reaction/ ነዉ። ምንም እንኳን አብዛኛውን ጊዜ የጭንቀት ስሜት አወንታዊ የሕይወት ገፅታ ባይሆንም ለሰው ልጆች እንደ መረጃ አቀባይ ሆኖ ያገለግላል። ሰው በዕለታዊ ህይወቱ ውስጥ ውጥረት፣ ብስጭት፣ ንዴት፣ተስፋ መቁረጥ ወይም ቁጣ ሊፈጥሩ የሚችሉ አነስተኛ ጭንቀቶች በሕይወታችን ሊያጋጥሙን የሚችሉ  ቢሆንም  ጉዳት ላይ የሚጥሉን አይደሉም። ሆኖም ግን ጭንቀቱ ከልክ ካለፈና የዕለት-ተዕለት ተግባረትን ማስተጓጐል፣ የስሜት ወይም የባሕሪ ለውጥና ሌሎች ምልክቶች መታየት ሲጃምሩ የጭንቀት ህመም ይሆናል። አንድሰው ለጭንቀት ህመም የመጋለጥ ሁኔታው የሚወስነው ግለሰቡ በህይወቱ የሚያገጥሙትን ችግሮች በአካላዊና በሥነ ልቦናዊ የመቋቋም ጥንካሬ ወይም ድክመትይወሰናል። የጭንቀት ህመም ምልክቶች፡- የድካም ስሜት፣ መጫጫን፣ ማዞር፣ ማቅለሽለሽ፣ የደምግፊት ከፍ ማለት፣ ለተወሰነ ጊዜ ቀዝቃዛ ላብ ፤ ያለምክንያት መቆጣት፣ የመሸበር ስሜት፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ያለምክንያት መከፋትና ድብርት፣ በሀሳብ መሸነፍ፤ ቸልተኝነት፣ ግልፍተኝነት (ስሜትን አለማቆጣጠር)፣ የስሜት መዘበራረቅ፣ ጥፋተኝነትን ወደ ሌላ ለማሳበብ መፈለግ፤ በስራ ላይ ትኩረት ማጣት፣ ቀጠሮ መርሳት፤ ዉሳኔ መወሰን አለመቻል፤ የማሰብችሎታ መቀነስ፤ የአመጋገብ ልምዶችን መቀየር፣ ስለግል ንፅሕናው ግድየለሽ መሆን፣ ከሰዎች ጋር ብዙ መነጋገር አለመፈለግ፤ ዝምታን መምረጥ ወይም ከማህበራዊ ግንኙነቱ እራስን ማግለል ወዘተ….ናቸዉ ጭንቀትን የምንከላከልባቸዉ መንገዶች፡- • የጭንቀት መነሻ ምክንያቶችንና ችግሮችን መለየትና ማወቅ • በተፈጠረዉ ችግር ምክንያት ደጋግሞ ራስን አለመዉቀስ • ሌሎች ስለ እኔ መጥፎ ነገር ያስባሉ ብሎ አለመገመት • እረፍት ማድረግና፣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት • አልኮል፣ ትምባሆ፣ ጫትና የመሳሰሉትን አለመጠቀም • እራስን ማዝናናትና የአካል እንቅስቃሴ መስራት • ከታማኝ ጓደኛ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር • ተጫዋችና ቀልደኛ ለመሆን መሞከር ሁልጊዜ መሣቅ ያስፈልጋል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
3 447
3
Нет текста...
3 147
4
የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በቀጠናው ለሚገኘው ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም በደሴና አካባቢው በግዳጅ ላይ ለሚገኘው ሠራዊት ማህበረሰቡ የተለያዩ ዓይነት የለስላሳ መጠጦችንና አልባሳትን ድጋፍ አድርገዋል። የደሴ ከተማ ማህበረሰብ ያደረገው ድጋፍ በግዳጅ ላይ ለሚገኙ የሠራዊቱ አባላት ያለውን አጋርነትና የማይነጠፍ ድጋፍ ለመግለፅ ሲሆን ድጋፉም ህብረተሰቡና ሠራዊቱ በጋራ የሚያደርጉትን የአጋርነት ተግባር ያጠናክራል ሲሉ የክፍሉ አመራር ተናግረዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
5 385
5
+3
Нет текста...
5 121
6
ለዕዙ ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም የማሠልጠኛው ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የምስራቅ ዕዝ በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎች የሠራዊቱን ዝግጁነትና የግዳጅ አፈፃፀም አቅም በማጠናከር ውጤታማ ተልዕኮ ለመፈፀም ማሰልጠኛ ማዕከሉ ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል። የምስራቅ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥና የስልጠና ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ደሳለው ብርሃኔ፣ ማሰልጠኛው የግዳጅ ቀጠናዎችን ሁኔታና የክፍሎችን የተግባር ፍላጎት መሠረት በማድረግ በተግባር የተደገፈ ጠንካራ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል። ማሰልጠኛ ማዕከሉ ስልጠናውን በማዕከሉ ብቻ ሳይገድብ ክፍሎች በግዳጅ ወደተሰማሩባቸው ቀጠናዎች በመድረስ በቀንና በሌሊት ተግባራዊ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል። በዚህም የዕዙ ክፍሎች የግዳጅ ሁኔታዎችን በተሻለ ዝግጁነት እንዲወጡ ከማድረጉም በላይ፣ የሠራዊቱ ዲሲፕሊን፣ የቡድን ትስስርና ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬ እንዲጎለብት አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል። ዕዙ በተጨማሪም በሐረሪ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የጸጥታ አባላትን በማሰልጠን የአካባቢውን የሰላምና የጸጥታ ሥራ ለማጠናከር ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል። ዘገባው የማሰልጠኛ ማዕከሉ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
5 079
7
+1
Нет текста...
4 595
8
Нет текста...
1
9
ለዕዙ ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም የማሠልጠኛው ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የምስራቅ ዕዝ በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎች የሠራዊቱን ዝግጁነትና የግዳጅ አፈፃፀም አቅም በማጠናከር ውጤታማ ተልዕኮ ለመፈፀም ማሰልጠኛ ማዕከሉ ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል። የምስራቅ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥና የስልጠና ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ደሳለው ብርሃኔ፣ ማሰልጠኛው የግዳጅ ቀጠናዎችን ሁኔታና የክፍሎችን የተግባር ፍላጎት መሠረት በማድረግ በተግባር የተደገፈ ጠንካራ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል። ማሰልጠኛ ማዕከሉ ስልጠናውን በማዕከሉ ብቻ ሳይገድብ ክፍሎች በግዳጅ ወደተሰማሩባቸው ቀጠናዎች በመድረስ በቀንና በሌሊት ተግባራዊ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል። በዚህም የዕዙ ክፍሎች የግዳጅ ሁኔታዎችን በተሻለ ዝግጁነት እንዲወጡ ከማድረጉም በላይ፣ የሠራዊቱ ዲሲፕሊን፣ የቡድን ትስስርና ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬ እንዲጎለብት አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል። ዕዙ በተጨማሪም በሐረሪ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የጸጥታ አባላትን በማሰልጠን የአካባቢውን የሰላምና የጸጥታ ሥራ ለማጠናከር ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል። ዘገባው የማሰልጠኛ ማዕከሉ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
1
10
ክፍለጦሩ 85 ሺህ ብር የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የ6ኛ ዕዝ ፈንቅል ክፍለጦር 85 ሺህ ብር በማዋጣት በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ እና ሞጣ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ የመግዛት አቅም ለሌላቸው 100 ተማሪዎች 50 ደርዘን ደብተር እና 20 ፓኬት እስክሪብቶ እንዲሁም 200 እርሳስ ድጋፍ ማድረጋቸውን የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ሞገስ አሳልፍ ገልፀዋል። ባለፉት አመታት ፅንፈኛ ቡድኑ በፈጠረው ግጭት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ርቀው መቆየታቸውን ያወሱት ኮሎኔል ሞገስ አሳልፍ የተደረገው ድጋፍ  በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህት ውጪ እንዳይሆኑ በማሰብ ነው ብለዋል። ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው በክፍለጦሩ ለተደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። ዘጋቢ ደሱ ኦጌ ፎቶግራፍ ሱራፌል እንድሪያስ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
4 838
11
+2
Нет текста...
4 217
12
የአካባቢው ህዝብና መስተዳደር በግዳጅ ቀጠና በመገኘት ሠራዊቱን አበረታቱ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የራያ ቆቦ ፣ የሃራ ከተማ መስተዳድር እና ነዋሪዎች በግንባር የሚገኘውን የሠራዊት አባላት ግዳጅ ቀጣና ድረስ በመገኘት አበረታተው ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድርገዋል። ሰላም ጠሉ ህወሀት ወቅት እየጠበቀ የአካባቢያቸውን ሰላም መንሳትና ልማት ማደናቀፍ የተለመደ ተግባሩ መሆኑን የጠቀሱት የከተማው ነዋሪዎች እና  የመስተዳድር አካላት ተወካዮች የህወሀትን ትንኮሳ ለመመከት በሚደረገው ዘመቻ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሠራዊቱ ጎን የሚቆሙ መሆኑን ገልፀዋል። ለሠራዊቱ የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት ኬሎኔል  ደሳለኝ ደጉ የከተሞቹ ህብረተሰብና የመስተዳድር አካላቱ የቀንድ ከብቶችን ፣ ጁስ እና እሽግ ውሃዎችን ይዘው ግዳጅ ቀጣና ድረስ በመምጣትና ለተዋጊው ኃይላችን በመደገፍ የሠራዊቱ ደጀን መሆናቸውን አረጋግጠዋል ብለዋል። በተልዕኮዎቻችን ሁሉ የጥንካሬና የድል ባለቤትነታችን ምንጭ ህዝባችን ነው ያሉት ኃላፊው የህዝቡ ድጋፍና ማበረታቻ ሠራዊቱን ለሌላ የላቀ ድል የሚያነሳሳ መሆኑንም ነው ያስረዱት። ዘግባው የሁንያለው ፈጠነ ነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
4 487
13
+4
Нет текста...
4 121
14
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ማህበራዊ ተሳትፎንና ሰራተኞችን የሚያበረታታ ተግባራትን አከናወነ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም የኢፌዴሪ አየር ኃይል በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኘው “እኛው ለእኛው” አረጋውያንና ህፃናት መርጃ ማዕከል የአልባሳት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ ለማዕከሉ ነዋሪዎችም  ማዕድ አጋርቷል። በአየር ኃይል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮለሸኔል ቸኮለች ወንዳቸው አየር ኃይሉ ህዝብን ከመደገፍና ከማገልገል አኳያ አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ገልፀው፣ ለማዕከሉ የተደረገው ድጋፍ ተቋሙ ከህዝብ ጎን መሆኑን የሚያሳይ ተግባር ነው ብለዋል። የማዕከሉ መስራችና ሊቀመንበር አቶ አሳምነው ደበላ በበኩላቸው፣ የአየር ኃይል አባላት በየዓመቱ ለማዕከሉ የሚያደርጉት ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ለተደረገው ድጋፍና የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ምስጋና አቅርበዋል። በተቋሙ ውስጥም የአየር ኃይል ወታደራዊ መደብሮችና መዝናኛ ክበቦች መምሪያ ለረጅም ዓመታት በትጋትና በቅንነት ላገለገሉ ሲቪል ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል። በመምሪያው ደረጃ በተዘጋጀው የሽልማት መርሃ ግብር ላይ የመምሪያው ኃላፊ ኮሎኔል ንጉሴ ለማ ለሰራዊቱ አባላት፣ ለሲቪል ሰራተኞችና ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያደርገው ድጋፍ እንዲሁም ሰራተኞችን የማበረታታት ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። የአየር ኃይል ወታደራዊ መደብር ዋና ክፍል ኃላፊ ሻለቃ አማረ ዘገየ በበኩላቸው፣ ሽልማቱ በመደብሩ ለረጅም ዓመታት በትጋት ያገለገሉ ሰራተኞችን ለማበረታታትና ለመደገፍ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል። በመርሃ ግብሩ ለረጅም ዓመታት በተቋሙ ላገለገሉ የመደብር ዋና ክፍል ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፣ ለመስቀል በዓል መዋያ የዶሮና የእንቁላል ስጦታም ተበርክቷል። ዘጋቢ ፍቃዱ እሸቱ ፎቶ ግራፍ ሰውነት ነጋሽ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
4 488
15
+4
Нет текста...
4 411
16
ከመከላከያ ሠራዊት እና ከፀጥታ ኃይሎች ለተውጣጡ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ለአራት ቀናት ለሽብርተኝነት የሲቭል- ወታደራዊ ምላሾች በሚል ርዕስ በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል። በዚሁ የስልጠና መዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ማቲው ኮፕ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ወክለው በመካከላችን ስላለው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል። እኛ የምንሰራው ለሀገሮቻችን ነው ያሉት ኮሎኔል ማቲው  እኛ ለህግ የበላይነት እና ለሰብዓዊ መብቶች ዋጋ የምንሰጥ ሀገሮች ነን ሽብርተኞች ግን ለህግ የበላይነትና ለሰብዓዊ መብቶች አልፎም ለሰው ልጆች ህይወት ዋጋ አይሰጡም ብለዋል። የወል ጠላታችን የሆነው ሽብርተኝነት እኛን ያጠናናል፤ በየቀኑ እናንተንም ያጠናችኋል ሲሉ የገለፁት ኮሎኔል ማቲው ጉዳት የማድረስ አቅሙን ማጥበብ የምንችለው አብረን ስንሰራ ነው ብለዋል ። በመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት የሁለትዮሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ሽዋቀና አማን በበኩላቸው በተለይም የጋራ የደህንነት ስጋቶችን ለመቋቋም የሚያስችል ተቋማዊ አቅምንና ትብብርን ለማጠናከር ላሳዩት ቀጣይነት ያለው አጋርነት፣ ሙያዊ ልምድ፣ ቴክኒካዊ ድጋፍና ቁርጠኝነት ለአሜሪካ ኤምባሲ ፣ለአሜሪካ ወታደራዊ ቡድንና ለሁሉም ተሳታፊ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የዚህ ሥልጠና እውነተኛ ስኬት የሚለካው ያገኘናቸውን ትምህርቶች በየተቋሞቻችን ውስጥ ወደ ተግባራዊ መሻሻል እንዴት እንደምንለውጣቸው በሚለው ላይ  ነው ያሉት ኮሎኔል ሽዋቀና ሁሉም ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ለባለደረቦቻቸው እንዲያካፍሉና ወደ ተግባርም በመተርጎም ሊሰሩበት እንደሚገባ ገልፀዋል ። ከመከላከያ እና ከፀጥታ አካላት የተወጣጡት አባላት በሰጡት አስተያየት ከስልጠናው አገራችንን ከሽብር ጥቃት እንዴት መከላከል እና ሽብርተኞችን በቀላሉ  መምታት የሚቻልበትን ሳይንሳዊ እዉቀት ቀስመናል ብለዋል። ዘጋቢ በላቸው ክንዴ ፎቶ ግራፍ ገነት አወቀ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
5 947
17
+4
Нет текста...
5 444
18
ሠራዊቱ የአርሶ አደሮችን ሰብል የማረም ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም   በደቡብ ዕዝ ተወርዋሪው ኮከብ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና የሚገኙ አርሶ አደሮችን ሰብል በማረም ድጋፍ አድርጓል። የክፍለ ጦሩ ዘመቻ ኃላፊ ሻለቃ ግርማ አሰፋ እንደገለጹት፣ ክፍለ ጦሩ ከግዳጅ ተልዕኮው ጎን ለጎን በሚሰማራባቸው አካባቢዎች ለህዝቡ የተለያዩ የድጋፍና የልማት ሥራዎችን ያከናውናል። አቅመ ደካማ የሆኑ ወገኖችን በገንዘብና በጉልበት መደገፍ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል መሆኑን የገለጹት ሻለቃ ግርማ፣ ይህም "ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር" የሚለውን የተቋሙን እሴት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል። በሰብል ስብሰባው የተሳተፉት ሃምሳ አለቃ የሂኔስ አብራሌ እና ሃምሳ አለቃ ሳሙኤል አሰፋ በበኩላቸው፣ ከግዳጃቸው ጎን ለጎን ህዝቡን ማገዝ የደስታ ምንጫቸው መሆኑን ገልጸዋል። ዘጋቢ በቃሉ ክንዴ ነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
5 609
19
+2
Нет текста...
5 740
20
በቀጠናው የሚገኘው ኮር ከሰሜን ወሎ ዞን አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ኮሩ ከሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ ከሚገኙ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር በወቅታዊ የሠላም ሁኔታ ውይይት አካሂዷል። ውይይቱን የመሩት የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ደጀኔ ደበሌ በቀጠናው ተሰማርቶ የሚገኘው የኮሩ የሰራዊት አባላት ከፀጥታ ሀይሉና ከመስተዳደር አካላት ጋር በመቀናጀት በፅንፈኞች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የህዝቡን ሰላም በዘላቂነት የማረጋገጥ ተግባር የመፈፀም ስራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል። የፀረ ሰላም ሀይሎችን ፍላጎት ቀድሞ በመረዳትና የገቢ ምንጩን በማድረቅ ማንኛውንም ድጋፍ እንዳያገኝ በጋራ መስራት ይኖርብናል ያሉት ምክትል አዛዡ በህዝቡ ውስጥ ተደብቀው የፅንፈኞችን ፕሮፖጋንዳ የሚነዙና ዘረፍን የሚፈፅሙ ቡድኖችን ተከታትሎ በመያዝ እርምጃ በመውሰድ አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባም አንስተዋል። የወልድያ ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ደርበው አዳነ መከላከያ ሰራዊታችን ቀን ከሌሊት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ በቀጠናው ሲንቀሳቀስ በነበረው የፅንፈኛ ቡድን ላይ እርምጃ በመውሰዱ አሁን ላይ በዞኑ ሰላም መስፈን ችሏል ለዚህም የዞኑ የፀጥታ አካላት ከሰራዊቱ ጋር በመሆን የሰሩት የሰላምና ፀጥታ ስራ ውጤት ነው ብለዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የፀጥታ አካላትም ከአካባቢው መስተዳደር ጋር በመቀናጀት ፀረ ሰላም ሀይሎችን በመታገል የቀጠናውን ሰላም ለማረጋገጥ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል። ዘጋቢ ጌትነት አስናቀው ፎቶ ግራፍ ዮናስ ካንቻማ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
5 749