National ID Program - Ethiopia
Identity is the new collateral! መታወቅ ለመተማመን። የፋይዳ ቁጥር ለማግኘት ወደ *9779# ይደውሉ። ሁሉን አገልግሎቶች በአንድ የሚያገኙበትን የፋይዳ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ከአፕ ስቶር (https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp) ወይም https://apps.apple.com/app/fayda-i) ያውርዱ።
نمایش بیشتر📈 تحلیل کانال تلگرام National ID Program - Ethiopia
کانال National ID Program - Ethiopia (@idethiopia) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 102 791 مشترک است و جایگاه 1 187 را در دسته فناوری و برنامهها و رتبه 302 را در منطقه أثيوبيا دارد.
📊 شاخصهای مخاطب و پویایی
از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 102 791 مشترک جذب کرده است.
بر اساس آخرین دادهها در تاریخ 05 نوامبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 276 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 23 بوده و همچنان دسترسی گستردهای حفظ شده است.
- وضعیت تأیید: تأیید شده (به صورت رسمی توسط تلگرام)
- نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 23.95% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 6.57% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب میکند.
- دسترسی پستها: هر پست به طور میانگین 24 613 بازدید دریافت میکند. در اولین روز معمولاً 6 749 بازدید جمعآوری میشود.
- واکنشها و تعامل: مخاطبان بهطور فعال حمایت میکنند؛ میانگین واکنش به هر پست 48 است.
📝 توضیح و سیاست محتوایی
نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاههای شخصی توصیف میکند:
“Identity is the new collateral!
መታወቅ ለመተማመን።
የፋይዳ ቁጥር ለማግኘት ወደ *9779# ይደውሉ።
ሁሉን አገልግሎቶች በአንድ የሚያገኙበትን የፋይዳ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ከአፕ ስቶር (https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp) ወይም https://apps.apple.com/app/fayda-i) ያ...”
به لطف بهروزرسانیهای پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 06 نوامبر, 2026)، کانال همواره بهروز و دارای دسترسی بالاست. تحلیلها نشان میدهد مخاطبان بهطور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته فناوری و برنامهها تبدیل کردهاند.
در حال بارگذاری دادهها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 06 نوامبر | +5 | |||
| 05 نوامبر | +37 | |||
| 04 نوامبر | +30 | |||
| 03 نوامبر | +12 | |||
| 02 نوامبر | +37 | |||
| 01 نوامبر | +2 |
| 2 | በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት፦ የመረጃ «እርማት» እና «ማሻሻያ» ልዩነታቸውን ያውቃሉ?
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሲመዘገቡ ሙሉ ስምዎ (የእርስዎ፣ የአባትዎ እና የአያትዎ ስም) እና የትውልድ ዘመንዎ ተቀባይነት ካላቸው ሰነዶች (እንደ ነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ) ጋር ተመሳሳይነቱ ተረጋግጦ ይመዘገባል።
ሆኖም ከተመዘገቡ በኋላ መረጃዎን ማረም ወይም ማሻሻል ሊያስፈልግዎ ይችላል። ታዲያ ልዩነታቸው ምንድነው?
1. የመረጃ እርማት (Correction)
በምዝገባ ወቅት የተፈጠረ የፊደል ግድፈት፣ የፊደላት መለዋወጥ ወይም የመዝጋቢ ባለሙያ ስህተትን በማስተካከል መረጃዎን ካቀረቡት ሰነድ ጋር ማጣጣም ነው።
ምሳሌ፦ በስህተት የተጻፈን ስም በትክክለኛ ፊደላት ማስተካከል (የስም ለውጥ የማይኖረው ከሆነ ብቻ)
2. የመረጃ ማሻሻያ (Update)
ቀድሞ የተመዘገበን መረጃ በአዲስ ማስተካከል ወይም መተካት ማለት ነው። ይህ ሂደት ለምሳሌ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ የስም ለውጥ ማድረግን፣ እንዲሁም ከቀረበው የልደት፣ የፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ሰነድ ላይ የተለየ የትውልድ ዘመን ወይንም አድራሻን ቀይሮ ማስመዝገብን ያጠቃልላል።
ምሳሌ፦ በምዝገባ ወቅት የነበረው ስልክ ቁጥር የሌላ ሰው ከነበረ ወይም በአዲስ ስልክ ቁጥር መለወጥ ስያስፈልግ
📌 ጠቃሚ ማስታወሻዎች፦
• የመረጃ እርማት እንዲሁም ማሻሻያ በድረገጽ id.et/update ላይ ወይም በምዝገባ ጣቢያዎች በቀላሉ መጠየቅ ይችላሉ።
• አንዳንድ መረጃ ማሻሻል ሲፈልጉ እንደ ስም እና የልደት ቀን ለውጥ ሲኖር የፍርድ ቤት ውሳኔ እና አስፈላጊ ማስረጃዎችን ይዘው መቅረብ ያስፈልጋል። የበለጠ መረጃ id.et/resources ላይ ያገኛሉ።
#ፋይዳለኢትዮጵያ | 9 027 |
| 3 | በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት፦ የመረጃ «እርማት» እና «ማሻሻያ» ልዩነታቸውን ያውቃሉ?
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሲመዘገቡ ሙሉ ስምዎ (የእርስዎ፣ የአባትዎ እና የአያትዎ ስም) እና የትውልድ ዘመንዎ ተቀባይነት ካላቸው ሰነዶች (እንደ ነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ) ጋር ተመሳሳይነቱ ተረጋግጦ ይመዘገባል።
ሆኖም ከተመዘገቡ በኋላ መረጃዎን ማረም ወይም ማሻሻል ሊያስፈልግዎ ይችላል። ታዲያ ልዩነታቸው ምንድነው?
1. የመረጃ እርማት (Correction)
በምዝገባ ወቅት የተፈጠረ የፊደል ግድፈት፣ የፊደላት መለዋወጥ ወይም የመዝጋቢ ባለሙያ ስህተትን በማስተካከል መረጃዎን ካቀረቡት ሰነድ ጋር ማጣጣም ነው።
ምሳሌ፦ በስህተት የተጻፈን ስም በትክክለኛ ፊደላት ማስተካከል (የስም ለውጥ የማይኖረው ከሆነ ብቻ)
2. የመረጃ ማሻሻያ (Update)
ቀድሞ የተመዘገበን መረጃ በአዲስ ማስተካከል ወይም መተካት ማለት ነው። ይህ ሂደት ለምሳሌ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ የስም ለውጥ ማድረግን፣ እንዲሁም ከቀረበው የልደት፣ የፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ሰነድ ላይ የተለየ የትውልድ ዘመን ወይንም አድራሻን ቀይሮ ማስመዝገብን ያጠቃልላል።
ምሳሌ፦ በምዝገባ ወቅት የነበረው ስልክ ቁጥር የሌላ ሰው ከነበረ ወይም በአዲስ ስልክ ቁጥር መለወጥ ስያስፈልግ
📌 ጠቃሚ ማስታወሻዎች፦
• የመረጃ እርማት እንዲሁም ማሻሻያ በድረገጽ id.et/update ላይ ወይም በምዝገባ ጣቢያዎች በቀላሉ መጠየቅ ይችላሉ።
• አንዳንድ መረጃ ማሻሻል ሲፈልጉ እንደ ስም እና የልደት ቀን ለውጥ ሲኖር የፍርድ ቤት ውሳኔ እና አስፈላጊ ማስረጃዎችን ይዘው መቅረብ ያስፈልጋል። የበለጠ መረጃ id.et/resources ላይ ያገኛሉ።
#ፋይዳለኢትዮጵያ | 1 |
| 4 | ጥቅምት 30 ደረሰ!
የባንክ ሒሳብዎን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር የማስተሳሰር ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ 5 ቀናት ብቻ ቀሩት።
እርስዎ ወይም ወዳጅዎ የባንክ ሂሳብ ከፋይዳ ጋር እስካሁን ካላስተሳሰሩ በቀላሉ በዲጂታል አማራጭ id.et/connect ላይ ይግቡ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ያስተሳስሩ ፤ አዳዲስ አገልግሎቶች እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ። ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት በማስተሳሰር የባንክ ሂሳብዎ ከወጪ እንቅስቃሴ እንዳይታደግ ማድረግ ይችላሉ።
ያስተውሉ፡ ቀነ-ገደቡ በመጠናቀቁ የባንክ ሂሳብዎ ወጪ ማድረግ ከተከለከለ፣ ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር እንዳስተሳሰሩ ወዲያውኑ የሚስተካከል ይሆናል።
#ፋይዳለኢትዮጵያ | 9 083 |
| 5 | ደረጃዎን በፋይዳ ያሳድጉ!
የቴሌብር አካውንትዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር በቴሌብር ሱፐርአፕ በማስተሳሰር ደረጃዎን ያሳድጉ።
ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ደረጃችን ከፍ ሲል እንዲህ ነን!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን | 8 757 |
| 6 | ነገ ከቀኑ 10፡00 በቲክቶክ ላይቭ እንገኛኝ!
በተደጋጋሚ በአስተያየት መስጫ እና በውስጥ መስመር ለምትጠይቁን ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 24፣ 2019 ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በቲክቶክ ላይቭ እንገናኝ፡
✅ ይፋዊ የቲክቶክ ቻናላችንን tiktok.com/@idethiopia ይከተሉ።
ጥያቄዎን ይዘው ነገ ይጠብቁን!
#ፋይዳለኢትዮጵያ | 15 424 |
| 7 | የፋይዳ የሳምንቱ ፎቶ፡ በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ መንዝ ማማ ወረዳ ተማሪዎች ለፋይዳ መታወቂያ ሲመዘገቡ
#ፋይዳለኢትዮጵያ | 17 319 |
| 8 | በፋይዳ ምዝገባ ወቅት ስምዎ ተሳስቷል ወይስ ከምዝገባ በኋላ ስም መቀየር ፈልገዋል? የፍርድ ቤት ውሳኔ የሚጠይቁት የትኞቹ ጉዳዮች ናቸው?
1️⃣ ማስተካከያ (በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም)
ሰነድዎና የፈቃደኝነት ቅጽዎ ትክክል ሆነው በሂደት ላይ ስህተት ሲፈጠር፦
• የምዝገባ ባለሙያ ስህተት፦ id.et/update ላይ ወይም በምዝገባ ጣቢያ በመሄድ ያመልክቱ።
• ትርጉም የማይቀይር የአጻጻፍ ስህተት፦ ትክክለኛውን አጻጻፍ የሚያረጋግጥ ሰነድ (የልደት ምስክር ወረቀት፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ሌላ ተቀባይነት ያለው) በማቅረብ ይስተካከላል።
2️⃣ ለውጥ (በፍርድ ቤት ውሳኔ)
• ከቀደመው የተለየ ስም ማስመዝገብ ሲፈልጉ
• ከምዝገባ በኋላ ስምዎን፣ የአባት ወይም የአያት ስምዎን ሲቀይሩ
የሚያስፈልግ ማስረጃ፦ የፍርድ ቤት የስም ለውጥ ውሳኔና ትዕዛዝ
📌 ያስተውሉ
• አቤቱታዎ “በፋይዳ ላይ ስሜ በስህተት ተመዝግቧል” ሳይሆን “የስም ለውጥ ጥያቄ አቀርባለሁ” የሚል መሆን አለበት።
• የአባትነት ማረጋገጫ ውሳኔ ብቻውን የአባት ወይም የአያት ስም ለመቀየር በቂ አይደለም።
• የጉዲፈቻ ውሳኔ ስም የሚያስቀይረው ውሉ አዲሱን ስም ገልጾ በፍርድ ቤት ከጸደቀ ብቻ ነው።
❌ ሆን ብሎ ሀሰተኛ ስም ማስመዝገብ በወንጀል ያስጠይቃል።
ለበለጠ መረጃ፦ id.et/resources | 20 309 |
| 9 | Ethiopia’s digital finance ecosystem is experiencing rapid growth, driven largely by the Fayda digital ID.
By streamlining eKYC and secure banking access, Fayda has facilitated over $148 billion in digital transactions in just nine months.
Read this Biometric Update article to learn how foundational digital identity is expanding financial inclusion and advancing the 2030 Digital Ethiopia strategy: https://www.biometricupdate.com/202610/fayda-national-id-helps-drive-ethiopias-digital-finance-ecosystem | 17 079 |
| 10 | የልደት ቀን በምዝገባ ወቅት ከተሳሳተ ለማስተካከል ምን ማድረግ ይኖርብዎታል?
በድረገጽ id.et/update ወይም በአካል በምዝገባ ጣቢያዎች መረጃዎን ማስተካከል ሲፈልጉ እነዚህን ዋና ዋና ነጥቦች ያስተውሉ።
❓ማሻሻያ ወይስ እርማት❓
📌 ማሻሻያ (በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚከናወን)፦ በልደት ምስክር ወረቀት፣ ፓስፖርት ወይም ቀበሌ መታወቂያ ካለው የተለየ አዲስ ሕጋዊ ዕድሜ (የትውልድ ቀን) ማስመዝገብ ሲፈልጉ።
📌 እርማት (በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት የሚከናወን)፦ የፋይዳ መረጃዎ ከማንነት ማረጋገጫ ሰነድዎ ወይም ከፈቃደኝነት ቅጽ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ወይም የተሳሳተ/የተለየ የትውልድ ዘመን ሲይዝ የሚደረግ ማስተካከያ ነው።
📌 ልብ ይበሉ፦ የፍርድ ቤት አቤቱታ ሲያቀርቡ እንደ “የፋይዳ ስህተት” ያሉ አገላለጾችን አለመጠቀም እና ፋይዳን በማስረጃ ዝርዝር ውስጥ አለማካተት
📌 ያስተውሉ፡ ትክክለኛ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያላቀረበ ማመልከቻ ተቀባይነት ስለማይኖረው ማመልከቻው ውድቅ የሚደረግ ይሆናል።
📌 ለልደት ቀን ማሻሻያ ወይም እርማት በሚጠይቁበት ጊዜ ማቅረብ ስለሚገባዎ እና ማድረግ ስለሚጠበቅብዎት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረገጻችንን፡ id.et/resources ይመልከቱ።
#ፋይዳለኢትዮጵያ | 19 319 |
| 11 | 140,000 Credentials in 2 Months!
With FaydaPass, managing your digital ID credentials and other service credentials has never been easier.
Get access to your Fayda ID, scan and verify #Fayda card, order card print, update demographic data, and take full control of other verified service credentials all from one convenient app.
Download FaydaPass NOW:
FaydaPass Android፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp
FaydaPass iOS ፦
https://apps.apple.com/app/id6740314990 | 21 199 |
| 12 | መታወቂያ ኮፒ ማድረግ ቀረ!
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደንበኞቻችሁ ለማንነት ማረጋገጫ የሚያቀርቡትን የፋይዳ ካርድ ትክክለኛነት እንዴት እያረጋገጣችሁ ነው?
የፋይዳ መታወቂያ ካርድ ትክክለኛ የግለሰቡ መሆኑን "FaydaPass" ሞባይል መተግበሪያን በማውረድ ኢንተርኔት ሳያስፈልግዎ "Offline" ስልክዎን ብቻ በመጠቀም ማረጋገጥ ይችላሉ።
ፋይዳፓስ ለአንድሮይድ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp
ፋይዳፓስ ለአይፎን (iOS)፦
https://apps.apple.com/app/id6740314990
#ፋይዳለኢትዮጵያ | 29 066 |
| 13 | Partner Spotlight: Addis Bike
Making urban mobility smarter, simpler, and more accessible! Addis Bike is transforming urban mobility through convenient, technology-driven bike sharing. By integrating with Fayda, Addis Bike leverages digital identity to enable more efficient user verification and seamless service access, bringing greater trust and convenience to everyday mobility.
Driving Real Impact Together:
31,581+ registered users
100 eco-friendly bikes
14 strategic stations, starting in Bole Sub-City and Meskel Square, with plans to expand across Addis Ababa.
This partnership demonstrates how Fayda integration connects digital identity with everyday services, helping enterprises enhance user experiences and build a more connected digital ecosystem.
Integrate your system with Fayda and unlock smarter, more trusted digital services! ID.ET/API
#digitaltransformation | 27 526 |
| 14 | የቀሩት 20 ቀናት ብቻ ናቸው!
ወደ ባንክ ቤት በአካል መሄድ ሳይጠበቅብዎ ባሉበት ሆነው ፣ ወደ ድረ-ገጻችን https://id.et/connect በመግባት ብቻ የሁሉም ባንኮች ማስተሳሰሪያ ሊንኮች ያገኛሉ።
📅 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የባንክ ሂሳብዎን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዎ ጋር ያስተሳስሩ። | 22 490 |
| 15 | Request for Expression of Interest: Finance Officer (Accountant)
The National ID Program invites qualified professionals to apply for the Finance Officer (Accountant) position in its Program Management Unit (PMU).
The role supports financial planning, reporting, payroll, reconciliations, and audit processes for Ethiopia’s Digital ID program.
Details to apply: https://projects.worldbank.org/en/projects-operations/procurement-detail/OP00475679 | 25 143 |
| 16 | የፋይዳ የሳምንቱ ፎቶ፡ መታወቅ ከልጅነት
በኦሮሚያ ክልል ሐረማያ ወረዳ በተካሄደ የመታወቂያ ምዝገባ ሱፐርቪዥን ወቅት የተወሰደ
@ICS_Ethiopia #ፋይዳለኢትዮጵያ | 25 177 |
| 17 | ስለ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሊያውቋቸው የሚገቡ ዋና ነጥቦች
✨ ካርድ እንዴት ላሳትም?
በደረገጽ id.gov.et/card ላይ የህትመት ሰጪ ተቋም በመምረጥ ካርድ ህትመት ማዘዝ ይችላሉ
✨በኦንላይን ባሉበት ሆነው የግል መረጃ ስህተት ለማስተካከል ወይም ለማደስ፦ id.gov.et/update
📍 በአካል ሄደው ለማስተካከል፡ id.gov.et/updatecenters
✨የተለያዩ የተቋማት ሰነዶችዎን በዲጂታል መልኩ በፋይዳፓስ መተግበሪያ ያገኛሉ።
ፋይዳፓስ ለአንድሮይድ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp
✨ በቴሌግራም ቦት የፋይዳ ቁጥር ያግኙ፣ መረጃ ያስተካክሉ፣ ካርድ ይዘዙና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ።
https://t.me/FaydaHelpBot
✨ የፋይዳ ቁጥርዎ ካልደረሰኝ ወይም ከጠፋብኝስ?
ወደ *9779# በመደወል ያስላኩ።
ሌላ ምን ማወቅ ይፈልጋሉ? በኮመንት ይጻፉልን! | 28 172 |
| 18 | የፋይዳ መታወቂያ ካርድ ትክክለኛነት በምን ማረጋገጥ ይቻላል?
✅ "FaydaPass" ሞባይል መተግበሪያን : ከፕሌይ ስቶር https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp
እንዲሁም ከአፕ ስቶር
https://apps.apple.com/app/id6740314990
በመጠቀም ካርድዎ ጀርባ ላይ የሚገኘውን QR ኮድ ስካን በማድረግ ትክክለኛነቱን ያረጋግጡ።
✅ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ካርድ ማለት QR ኮድ ስካን ሲደረግ ትክክለኛውን የግለሰቡን መረጃ የሚያሳይ ማለት ነው።
✅ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ካርድ ለማሳትም ህጋዊ የህተመት አጋሮች ከሆኑት በድረገጽ id.et/card በመግባት ይዘዙ።
#ፋይዳለኢትዮጵያ | 27 263 |
| 19 | መረጃዎን ካስተካከሉ በኋላ የፋይዳ መታወቂያ ካርድዎን በድጋሚ ለማሳተም ምን ማድረግ እንዳለብዎ ያውቃሉ?
1. ወደ id.et/card ላይ በመግባት ከዚህ ቀደም ካዘዙበት ህትመት ሰጪ ተቋም "በድጋሚ ለማሳተም" የሚለውን ይንኩ
2. በመቀጠል የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን/ የፋይዳ ካርድ ቁጥርዎን በማስገባት "OTP" ወይም የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል በማስላክ ማረጋገጥ
3. በመቀጠል በድጋሚ ካርድ ህትመት የሚያዙበትን ምክንያት ከተሰጡት አማራጮች ይምረጡ።
📌 በድጋሚ የሚያሳትሙት መረጃ አዘምነው ስለሆነ መረጃዎ መስተካከሉን የሚያሳይ የማረጋገጫ መልዕክት ከደረስዎ በኃላ የድሮውን ካርድ ለሁለት በመስበር በሚታይ መልኩ ፎቶ በማንሳት ይጫኑ "upload" ያድርጉ።
4. በመቀጠል አስገብ "Submit" የሚለውን በመጫን የማረጋገጫ መልዕክት ይጠብቁ ፤ ያስገቡት ትዕዛዝ ተጣርቶ ካለቀ በኃላ ክፍያ እንዲፈፅሙ በስልክዎ መልዕክት ይደርሶታል። መልዕክቱ እንደደረስዎ ወደ ክፍያ ሂደት በመሔድ ክፍያዎን አጠናቅቀው በመረጡት ቅርንጫፍ በቀጠሮ ቀን በመሄድ ይውሰዱ።
ያስተውሉ፡ ድጋሚ ህትመት ከማዘዝዎ በፊት ለማዘመን የጠየቁት መረጃ መስተካከሉን ያረጋግጡ። | 29 472 |
| 20 | ፋይዳ ለመላው የሀገራችን ህዝቦች እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰላም አደረሳችሁ እያልን ፤ እንደ አንዱ የዲጂታል ኢትዮጵያ የባንዲራ ፕሮጀክት (flagship project) የኢትዮጵያን ዲጂታል ማንነት በማረጋገጥ የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በዲጂታሉ መድረክ ከፍ በማድረጋችን ደስታ ይሰማናል!
#ዲጂታልኢትዮጵያ2030 | 25 367 |
