cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Tikvah-University

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
213 499
مشترکین
+6324 ساعت
+6307 روز
+3 27630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#MoE የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ 25 የክልል ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና በተጨማሪ የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እያደሩ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ተናግረዋል። የፈተና አሰጣጡን ስኬታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ሚኒስትር ድኤታዋ ጠቁመዋል። የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተገልጿል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ / ኦንላይን ለመስጠት እየተከናወኑ በሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል። በውውይይቱ ፦ - የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን - የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተሳትፈዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ ለመስጠት ከወዲሁ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ ብለዋል። ፈተናው ኦን ላይን እንደመሰጠቱ ኮምፒውተሮች ፣ ላፕቶፖች እና ታብሌቶችን ጨምሮ ሎሎች አስፈላጊ ግብአቶችን የማሟላት ስራ መጀመሩን አስታውቀዋል። የግል ትምህርት ቤቶች ለፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የማዘጋጀት ተግባራቸውን ከወዲሁ በመጀመር ፈተናው በታቀደለት መርሀ ግብር እንዲሰጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገበል ብለዋል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሀምሌ 3 እስከ 5 የማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሀምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በትላንትናው እለት መግለጹ ይታወቃል። ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ @tikvahethiopia
نمایش همه...
#DambiDolloUniversity ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ዕጩ የቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች #ሞዴል የመውጫ ፈተና መስጠት ጀምሯል፡፡ የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14-21/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይወቃል፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለዕጩ የቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎቻቸው #ሞዴል የመውጫ ፈተና እንዲሰጡ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ያስገድዳል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስታርት አፕ ማዕከል በቅርቡ ሥራ እንደሚያስጀምር ገልጿል፡፡ መንግሥት የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማስፋፋት የስታርት አፕ ልማትን የሚያጎለብቱ የተለያዩ ፖሊሲዎች እያተዘጋጁ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ በቅርቡም የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ወጣቶች ሐሳባቸውን ወደ ተግባር ለማዋል በሚፈልጉበት ወቅት ያለምንም የንግድ ቤት ኪራይ ውል ሥራ መጀመር የሚችሉበትን አዲስ አሠራር መዘርጋቱን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም የውጭ አገር ፈንድ ያገኘ ስታርት አፕ ሙሉ በሙሉ የውጭ ምንዛሪውን ለሚፈልገው ሥራ ማዋል የሚችልበት አሠራር ተግባራዊ መደረጉ ተገልጾ ነበር። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚከፍተው የስታርት አፕ ማዕከል በዘርፉ የተጀመሩ ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር አጋዥ እንደሚሆን ይታመናል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
#ምስላዊ_መረጃ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም ይሰጣል። በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁ ይታወሳል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
👍 34 5👏 2
#የቻናል_ጥቆማ 🔔 ለኢንጂነሪንግ ተማሪዎች እና Construction ዘርፍ ላይ ለተሰማራችሁ በሙሉ‼️ የኮንስትራክሽን፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ የአርክቴክቸር ተማሪ ነዎት? በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት? 📚 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መጻሕፍት፣ ቪዲዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን ዕውቀት ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን! 👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ 👉 አዲስ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣ 👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣ 👉 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሌክቸር የምታገኙበት፡፡ Join Us :- ✅on Telegram 👇 https://t.me/ethioengineers1 https://t.me/ethioengineers1 ✅on TikTok tiktok.com/@ethiocons tiktok.com/@ethiocons
نمایش همه...
👍 23👎 5 3😢 3
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው። @tikvahethiopia
نمایش همه...
"ትምህርት ለትውልድ" በተባለውና የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት መሰብሰቡን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ ባለፈው ዓመት መጨረሻ በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አሰተዳደሮች ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መሰብሰቡን በሚኒስቴሩ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል። በ2016 ዓ.ም ብቻ በትምህርት ለትውልድ መርሐግብር ከ4 ሺህ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡ የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ሥራ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
👍 41👎 17😢 2 1
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙና ዘንድሮ የመልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በበጎ ፍቃደኛ መምህራን በመታገዝ በተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሐግብር አከናውኗል፡፡ በጉዲኦ ዞን ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አምስት ትምህርት ቤቶች ላለፉት ሦስት ዓመታት አንድም ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ አለማሳለፋቸውን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ተቋም ያደረገው ጥናት ያሳያል፡፡ በመሆኑም የማጠናከሪያ ትምህርቱ በጌዴኦ ዞን የሚታየውን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ማነስን ለማሻሻል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለአንድ ወር ከአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን፤ በተመረጡት ትምህርት ቤቶች አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
#ጥቆማ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሐግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል። እነማን ይመዘገባሉ? የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም ስልጠናው መቼ ይጀምራል? ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም (ለሁለት ወራት) (በሳምንት ለአራት ቀናት) ስልጠናው ትኩረት የሚያደርግባቸው፦ ➭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣ ➭ ሮቦቲክስ፣ ➭ ፕሮግራሚንግ፣ ➭ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም። ምዝገባ የማድረጊያ አማራጮች፦ 👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8 👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/ @tikvahuniversity
نمایش همه...
👍 70 13👏 1