cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 https://t.me/AiqemAdsMasterBot 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

نمایش بیشتر
Advertising posts
32 580مشترکین
+3524 ساعت
+1967 روز
+61630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በእነ ክስርስቲያን ታደለ ፣ ዘመነ ካሴ፣ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች 52 ግለሰቦች ላይ የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመሰረተ ዓቃቤ ሕግ ያለመከሰስ መብታቸው በተነሳባቸው የሕዝብ ተመራጮች ክርስቲያን ታደለ፣ ዮሐንስ ቧያለው እና ካሳ ተሻገር ላይ የሽብር ወንጀል ክስ መመስረቱን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። በክስ መዝገቡ ከተካተቱት 52 ተከሳሾች መካከል፣ እስክንድር ነጋ፣ ጫኔ ከበደና ዘመነ ካሴ ይገኙበታል። ዓቃቤ ሕግ በክሱ፣ ተከሳሾቹ የፖለቲካ ርዕዮታቸውን በኃይል ለማስፈጸም በማሰብ፣ በኅቡዕ የተቋቋመውን የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን ዓላማዎች ለማስፈጸምና የአማራ ሕዝብ ርሥቶች ናቸው የሚሏቸውን አካባቢዎች በወታደራዊ ኃይል ለማስመለስ የተደራጁ ነበሩ ብሏል። ዓቃቤ ሕግ፣ ተከሳሾቹ ከ1 ሺህ 100 በላይ ለሚኾኑ የጸጥታ አባላትና ሲቪሎች ሞትና 5 ሺህ 689 በላይ ታራሚዎችን በማስመለጥ ወንጀልም ተጠያቂ አድርጓቸዋል። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👎 10👍 6😁 4🤬 1🕊 1
የማሊያው ቁጥር በክብር ተቀመጠ! በድንገት ህይወቱ ያለፈው ወጣቱ አማካይ የእግር ኳስ ተጨዋች አለልኝ አዘነ የሚለብሰው የማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ መወሰኑን ክለቡ ይፋ አድርጓል። የጣና ሞገዶቹ ተጫዋቾች በኮከብ ተጫዋቻቸው ህልፈተ ህይወት የተሰማቸዉን ሀዘን በትዉልድ ስፍራው በመገኘት እንደተሰናበቱ ለማወቅ ተችሏል። አለልኝ አዘነ በባህር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ይለብሰዉ የነበረው የማልያ ቁጥር 23 ከዚህ በኋላ ማንም የክለቡ ተጫዋች የማይለብው ሆኖ በክብር እንዲቀመጥ የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ወስኗል። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
31😢 8👍 5😁 2
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው በማለት ትናንት ከቻይናው ሲጂቲኤን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ያለፈው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት አልነበረም ያሉት ጌታቸው ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና የትግራይ ሕዝብ ድጋሚ ጦርነት እንዳያገረሽ የተቻላቸውን ጥረት ኹሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ጌታቸው ይህን ያሉት ፣ በአላማጣ አቅራቢያ በትግራይ ኃይሎች እና ባካባቢው ሚሊሻዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በተደረገ ማግስት ነው መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል። አቶ ጌታቸዉ ይህንን ይበሉ እንጂ አብን፣ ሕወሃት ለአዲስ ዙር ጦርነት ቅስቀሳ እያደረገ ነው ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት የሕወሃት ተዋጊዎች ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ሳይፈቱና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጸጥታ ለማስከበር ሳይሠማራ ሕወሃት ለሌላ ዙር ጦርነት ፕሮፓጋንዳ በመለፈፍ ተጠምዷል ብሏል። የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥታት የሕወሃትን የጠባጫሪነት ቅስቀሳ በትኩረት እንዲከታተሉና በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት "በንግግር" እና "ድርድር" እንዲፈታም አብን ጠይቋል። የአማራ ሕዝብ ሕወሃት ሊያደርስበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል በአንድነት እንዲቆም የጠየቀው ፓርቲው፣ የትግራይ ሕዝብም ራሱን ከሕወሃት ቀንበር እንዲያላቅቅ ጥሪ አድርጓል። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
🕊 18👍 16 2🙏 1💯 1
‹‹ አብን ትናንት ምሽት ያወጣዉ መግለጫ የግለሰቦች እንጂ የፓርቲዉ አቋም አይደለም ›› - ከፍተኛ አመራር እና የምክር ቤት አባል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ረቡዕ ምሽት ያወጣው መግለጫ እንደማይወክላቸዉ  የምክርቤት  አባላቱና ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ ከፍተኛ የቀድሞ አመራር ለአሻም ነግረዋታል፡፡ የቀድሞው ከፍተኛ አመራር ይህን ያሉበትን ሲያሥረዱ ‹‹ ከ9 ስራ አስፈጻሚ አባላት 6ቱ በሌሉበትና የምክርቤት አባላት የሆኑ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን ጭምር ሰብስቦ ባላወያየበት በጣት በሚቆጠሩ ግለሰቦች ፍላጎትና ሀሳብ ተጠናቅሮ በፓርቲዉ ስም የተሰጠ መግለጫ  ነዉ ›› ሲሉ ነቅፈውታል፡፡ እኚሁ አመራር አስከትለዉም ‹‹ ፓርቲዉ ለእውነት የቆመ ቢሆን  የስራ አስፈጻሚ፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን ጠርቶ በማወያየት ማህበራዊ መሠረቴ ነው፤ እቆምልታለሁ ለሚለዉ ህዝብ፣ ለታሰሩና ለጠፉ አባላቶቹ መግለጫ ያወጣ ነበር ሲሉ ፓርቲያቸዉን ›› ተችተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በእነዚህ ግለሰቦች በፓርቲዉ ስም የወጣዉ ዳግም ግጭት ቀስቃሽ  መግለጫ ጨምሮ  በትግራይና አማራ ክልልና የፌደራሉ መንግስት  በኩል ጉዳዩን  በእርጋታ በመመልከት  ህዝቡን  ከሰብዓዊና ቁሳዊ ዉድመቶች መታደግ ተገቢ ነዉ ሲሉ  የግል አቋማቸዉን አንጸባርቀዋል፡፡ በተመሳሳይ  ፓርቲዉን ወክለዉ የ2013 ምርጫ በተወዳደሩበት ስፍራ አሸንፈው የፌደራል የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል የሆኑት አበባዉ ደሳለዉ በበኩላቸው መግለጫዉ የስራ አስፈጻሚ አባላት ከግማሽ በላይ ያልተሟሉበትና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተሰብስበዉ ያልተወያዩበት በመሆኑ መግለጫዉ የፓርቲዉ ነዉ ለማለት እንቸገራለን ሲሉ ለአሻም ነግረዋታል፡፡ አሻም በጉዳዩ ላይ የፓርቲዉን ሊቀመበር በለጠ ሞላን(ዶ/ር) ጨምሮ ቀሪ የስራ አስፈጻሚ አባላቱን ለማነጋገር ብትሞክርም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው በዘገባው ሊካተቱ አልቻሉም፡፡ Via አሻም #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 15😁 13 5👎 2🤔 2🔥 1
መብራት በመላው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ ዛሬ ከቀኑ 9 ሠዓት 46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ ሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል የተቋረጠ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል። የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ  መሆኑም ተመላክቷል፡፡ እስከዛ ድረስም ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ  ተቋሙ ጠይቋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 28😁 18🤔 4👎 1🤯 1
በአምቦ ወረዳ የ90 ዓመት አዛውንት አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ ኢላሙ ጎሮሙጢ የተባለ አካባቢ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት መቀጣጡት የምዕራብ  ሸዋ ዞን  ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል ፡፡  የምዕራብ ሸዋ ዞን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን የላከእ መረጃ እንደሚያመላክተው ተከሳሽ ለቴራ ቀና የተባለው ግለሰብ  መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የ90 ዓመት ኣዛውንት  በመኖሪያ ቤታቸው  ተኝተው  ባሉበት  ቤታቸውን ሰብሮ በመግባት አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እንደፈጸመ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ ተከሳሽ  በእድሜ  የደከሙ ራሳቸውን መከላከል  የማይችሉ  አዛውንትን  በጉልበት  አስገድዶ  መድፈሩ ፖሊስ በህክምና ማስረጃ ያረጋገጠ እና የምርመራ መዝገቡን አጠናክሮ ለ ዓቃቢህግ መላኩን ብስራት ተመልክቷል ፡፡ በዚኅም  ዓቃቢ ህግ  ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልከቶ  በወንጀለኛ  መቅጫ ህግ መሰረት ክስ መስርቷል፡፡  ክሱን ሲመለከት የነበረው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም  በዋለው ችሎት ተከሳሽ ለቴራ  ቀና በስምንት  ዓመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ  የተላለፈበት መሆኑን  የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን የላከው መረጃ  ያመላክታል ፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
😱 38🤬 22👍 8🤔 7😁 6 5😢 2💔 2🤯 1
ህጋዊ የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች ስራቸው በመቋረጡ የተነሳ ለሰራተኞቻቸው ደሞዝ መክፈል ሊያቆሙ መሆኑን አስታወቀ የቫሞስ እና የሀበሻ የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እንዳስታወቁት ከታህሳስ ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ግብረ ሐይል በማቋቋም እንዲዘጋ መደረጉን ተናግረዋል፡፡የቫሞስ ኢንተርቴይመንት ስራ አስኪያጅ አቶ የኔብልህ ባንታየው እና የሀበሻ ስፖርት ውርርድ ስራ አስኪያጅ አቶ መርሻ ቡዛየሁ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከ5 ዓመት በፊት በብሄራዊ ሎተሪ ፍቃድ የተሰጠው ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሁለቱ ተቋማት በሀገር ውስጥ 156 እና 166 ቅርንጫፎች እንዳሏቸው እና ከ1ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎችም የስራ እድል የፈጠረ ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡የሀበሻ ስፖርት ውርርድ ስራ አስኪያጅ አቶ መርሻ ቡዛየው ከታህሳስ ወር ጀምሮ ድርጅቶቹ መዘጋታቸውን እና ያለምንም ስራ ለሰራተኞቻቸው እንዲሁም ለቤት ኪራይ እየከፈሉ እንደቆዩም ገልፀዋል፡፡ የስፖርት ውርርድ ተቋማቱ በብሄራዊ ሎተሪ መመሪያ መሰረት ከ21 ዓመት በታች እና ተማሪዎች እንዳይገቡ የሚለውን መመሪያ መፈፀማቸውን እና ለዚህም ብለው ከ340 በላይ የጥበቃ ሰራተኞች ቀጥረው እንዳይገቡ ይከለክሉ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ የቫሞስ ኢንተርቴይመንት ስራ አስኪያጅ አቶ የኔብልህ ባንታየሁ አክለውም በስፖርት ውድድር ዘርፍ ውስጥ 8 መቶ ድርጅቶች ህጋዊ መሆናቸው ተነግሮናል፤ ሌሎቹ 3ሺ የሚሆኑት ግን በህገወጥ ስራ የተሰማሩ መሆናቸው ከተለየ የህጋዊነት አግባብ ያለን ድርጅቶች ወደ ስራችን እንድንመለስ መልስ ይሰጠን ሲሉ ጠይቀዋል፡ መልስ በመጠበቅ አራት ወራት እንደቆዩ ለሰራተኞቻቸው ሲከፍሉት የነበረውን ወርሀዊ ደሞዝ ከዚህ በላይ መክፈል የማይችሉበት ከባድ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አቶ የኔብልህ ባንታየሁ እና አቶ መርሻ ብዙአየሁ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።በቅሬታ አቅራቢዎቹ ዘንድ ህጋዊ የስፖርት ቤቶች ይከፈትልን የሚሉ አቤታታዎች ቢኖሩም ዘርፉ መዝጋቱ የሚደግፉና ቁጥጥሩ የላላ በመሆኑ ታዳጊዎች ላልተገባ ሱሱ ተዳርገዋል ሲሉ የሚደመጡም አሉ። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 37👏 6👎 2😁 2🔥 1💔 1
ከእህቱ ሞት ጋር በተያያዘ በመንፈስ ተወግታ ነው በሚል ወሬ ተነሳስቶ የግድያ ወንጀል የፈፀመዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ በኢሊባቡር ዞን በያዮ ወረዳ አጨቦ ቀበሌ ልዩ ቦታው ብርቂቱ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከእህቱ ሞት ጋር በተያያዘ በመንፈስ ተወግታ ነው በሚል ወሬ ተነሳስቶ አንድ ግለሰብን የገደለ ተከሳሽ በእስራት ተቀጥቷል ። የ29 ዓመት እድሜ ያለው ምትኩ በቀለ የተባለ ግለሰብ ኑሮው ከቤተሰቦቹ ጋር አድርጎ ነበር ። ታላቅ እህቱ በተደጋጋሚ በመታመሟ የተነሳ የአዕምሮ መታወክ ይገጥማታል ። ሆኖም ከገጠማት የአዕምሮ መታወክ በህክምና ስትረዳ ከቆየች በኋላ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ትለያለች ። ሞቷ በቤተሰቦቿ ላይ ከፍተኛ ሀዘን ያስከተለ ከመኖኑ ባሻገር ከአማሟቷ ጋር በተያያዘ የሚወራው ወሬ መላ ቤተሰቡን ያስከፋ ሲሆን በተለይም ደግሞ ምትኩን አስደንግጧል ። ወሬውም ሟች ህይወቷ ያለፈው በአካባቢው በምትገኝ ጫልቱ ተረፈ በተባለች ግለሰብ መንፈስ ተወግታ ነው ይባላል ። ይህ ወሬ በመጨረሻም የምትኩን ልብ ለበቀል ያነሳሳል ። ጫልቱ በበኩሏ የሚወራው ችላ በማለት የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዋን ትቀጥላለች ። በዚህም ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም  ዓመታዊውን የመድኃኒዓለም ክብረ በዓል አክብራ ስትመለስ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ምትኩ በቀለ በመንገድ ጠብቆ በገጀራ ጭንቅላቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የኢሉባቡር ዞን ፖሊስ ኮሚኒኬሽን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ገልጿል ። በወቅቱ ተጎጅዋን በመረባረብ ወደ መቱ ካርል ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዳ እርዳታ ቢደረግላትም ህይወቷ መትረፍ ሳይችል ይቀራል ። ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ የምርመራ መዝገቡን አጣርቶ ለዓቃቤ ህግ ይልካል ። ዓቃቤ ህግ በደረሰው ማስረጃ ተመስርቶ በኢሊባቡር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል ። ፍርድ  ቤቱ ዓቃቤ ህግ የመሠረተውን ክስ ሲመለከት ቆይቶ ተከሳሽ ምትኩ በቀለን ጥፋተኛ በማለት በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል ። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 15 3🤬 3
👍 2
وارد شوید و به اطلاعات مفصل دسترسی پیدا کنید

ما این گنجینه ها را پس از تأیید هویت به شما نشان خواهیم داد. ما وعده می‌دهیم که سریع است!