cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Show more
Advertising posts
34 149Subscribers
+624 hours
+9837 days
+1 76030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በአዲስ አበባ ከተማ ከአየር ብክለት ጋር ተያይዞ በየዓመቱ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት እንደሚያልፍ ተነገረ በአዲስ አበባ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአየር ብክለት መጠን እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በየአመቱ 2 ሺህ አራት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ለህልፈት ይዳረጋሉ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ  የአየር ንብረት ለውጥና አማራጭ ኢነርጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰይድ አብደላ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከማገዶ በሚወጣ ጭስ፣ ቆሻሻን በአግባቡ ባለማስወገድ እንዲሁም ከአምራች ኢንዱስትሪዎች በሚወጡ ፍሳሾች እና በሌሎች ምክንያቶች  ሳቢያ የአየር ብክለት ይከሰታል ብለዋል። ከተሽከርካሪዎች የሚወጣ ጭስ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚስተዋለው የአየር ብክለት ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ  አቶ ሰይድ ተናግረዋል።ይህ ሁኔታ ከአካባቢ ብክለት ባለፈ በሰዎች ጤና ላይ ሞትን የማስከተል እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ ለጉዳዮ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል።አዲስ አበባንም ከብክለት የፀዳች ፣ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ እንድትሆን ለማድረግ ከተሽከርካሪ የሚወጣ ጭስን ለመከላከል የሚያስችለው መመሪያ እንዲፀድቅ እየተደረገ ይገኛል። በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፓርት ብክለትን ለመቆጣጠር  የወጣው መመሪያ እንዲፀድቅ ለፍትህ ቢሮ ተልኳል ሲሉ የተናገሩት አቶ ሰይድ  መመሪያው ተሽከርካሪዎች  በተቀመጠው የልቀት መጠን ስታንዳርድ  መሰረት እንዲያሽከረክሩ ያስገድዳል ብለዋል።አያይዘውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ  ከትራንስፓርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር እንዲሁም ከደረጃዎች ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን ስታንዳርዱ  እንዲዘጋጅ  አድርጓ። የመመሪያውን ተፈፃሚነት በሚመለከትአንድ አሽከርካሪ ስታንዳርዱን ጠብቆ ስለማሽከርከሩ  ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተጠቅሷል።በዚህም ትናንሽ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ መለስተኛና ሌሎች መኪኖች   እንደክብደታቸው  እና አይነታቸው የሚለቁት የጭስ መጠን በአግባቡ የሚለካ ይሆናል ሲሉ አቶ ሰይድ አብደላ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡ በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 4👎 4😁 1🤔 1
ዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ የማላዊ ባለስልጣናትን በሙስና ክስ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ አገደች አራት የቀድሞ የማላዊ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሙስና ወንጀል ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ ተጥሎባቸዋል።እነሱም የቀድሞ የፖሊስ አዛዥ ጆርጅ ካይንጃ፣ የቀድሞ የህግ አማካሪ እና የፍትህ ፀሀፊ ሬይኔክ ማትምባ፣ የቀድሞ የህዝብ ግዥ እና የንብረት ማስወገድ ዳይሬክተር ጆን ሱዚ-ባንዳ እና የቀድሞ የፖሊስ አገልግሎት ጠበቃ ሚዋቢ ካሉባ ናቸዉ። አራቱ በዩናይትድ ስቴትስ ዲፓርትመንት ስማቸዉ የተጠቀሱት ግለሰቦች "በአጠቃላይ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመግባት ብቁ አይደሉም፣ ምክንያቱም በከፍተኛ ሙስና ውስጥ በመሳተፋቸው"ነዉ ተብሏል።እገዳው በቀድሞ ባለስልጣናት የትዳር አጋሮች ላይም የጸና ነዉ ተብሏል፡፡ የታገዱት ባለስልጣናት “ለማላዊ ፖሊስ አገልግሎት የመንግስት ግዥ ውል ለመስጠት ከአንድ የግል ነጋዴ ጉቦ እና ሌሎች ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች በመቀበል ህዝባዊ ሀብትን አላግባብ ተጠቅመዋል” ብሏል።የቀድሞ ባለሥልጣናቱም ከብሪታኒያው ነጋዴ ዙኔት ሳትታር ጋር በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፀረ-ዘረፋ አካል የተከሰሱ ከ80 በላይ ታዋቂ የማላዊ ዜጎች ስም ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱ በኋላ በማላዊ ክስ ቀርቦባቸዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 2 1
ከአላማጣ እና ከሌሎች የራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፤ በቆቦ ኢንዱስትሪ መንደር እንዲጠለሉ መደረጋቸው ተነገረ በአማራ እና የትግራይ ክልሎች “የወሰን ይገባኛል” ጥያቄዎች ከሚነሱባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው የራያ አካባቢ ባለፉት ቀናት ውጊያ መካሄዱን ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ቆቦ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ወቅት ከቆቦ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ የኢንዱስትሪ መንደር በጊዜያዊነት እንዲጠለሉ መደረጋቸውንም አስታውቀዋል። በአወዛጋቢዎቹ የራያ አካባቢዎች ውጊያ የተቀሰቀሰው፤ ከአካባቢው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ በማይጨው እና መኾኒ ከተማዎች ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ መሆኑን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከሰላማዊ ሰልፎቹ  በኋላ በሪ ተኽላይ እና ገርጃለ በተባሉ አካባቢዎች፤ በትግራይ ኃይሎች እና በአማራ ክልል ታጣቂዎች መካከል “ከባድ የተኩስ ልውውጥ” ሲደረግ እንደነበር እማኞቹ አስረድተዋል። የአላማጣ ከተማ ከሰኞ አመሻሽ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥጥር ስር ከገባ በኋላ በከተማይቱ መረጋጋት መታየቱን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የአላማጣ ነዋሪዎች አመልክተዋል። በትላንትናው እና በዛሬው ዕለት መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ቢቀጥልም፤ የህዝብ አገልግሎት ሰጪዎች እና ተቋማት ግን አሁንም ዝግ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።  የመንግስት ሰራተኞች በጸጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ስራ ገበታ ለመመለስ መቸገራቸውን እና የተወሰኑትም ከተማይቱን ለቅቀው መሄዳቸውን ነዋሪዎቹ አክለዋል። በአላማጣ ከተማ የነበሩ የስራ ኃላፊዎች፤ ከትላንት በስቲያ ከሰዓት በአጎራባች ወደምትገኘው ቆቦ ከተማ መግባታቸውን የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃይሉ አበራ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።  Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 3🕊 2😁 1
የ42 ዓመቷ ብራዚላዊት ሴት ህይወቱ ያለፈ ሰውን ወደ ባንክ አምጥታ በስሙ ከባንክ ብድር ለማዉጣት ስትሞክር በቅርቡ በቁጥጥር ስር ውላለች። ማክሰኞ ሚያዚያ 9 ቀን ኤሪካ ዴ ሱዛ ቪየራ ኑነስ የተባለችዉ ግለሰብ ህይወቱ ካለፈዉ የ68 ዓመቱ ፓውሎ ሮቤርቶ ብራጋ ስም 3,200 ዶላር የባንክ ብድር ለማዉጣት ወደ ባንጉ፣ ሪዮ ዴጄኔሮ ወደሚገኘው የኢታው ዩኒ ባንኮ ቅርንጫፍ መጥታለች። የአዛውንቱን በዊልቸር ላይ የነበሩ ሲሆን አጎቷ እንደሆኑ እና የመጀመሪያ ተንከባካቢ መሆኗን ተናግራለች። የባንኩ ሰራተኞች ብዙም ሳይቆይ በብራጋ ላይ ከባድ ችግር እንዳለ አስተውለዋል፡፡ምክንያቱም ይህችዉ ሴት የሟችን ጭንቅላት በእጇ ስትደግፍ ጥርጣሬ ፈጥሮባቸዋል። እናም ምንም አይነት በህይወት እንዳለ የሚያሳይ ምልክት አልታየበትም፣ ነገር ግን ቪየራ ኑነስ በተፈጥሮው ዝምተኛ እንደሆነ ለባንኩ ሰራተኞቹ እየነገራቻቸዉ ነበር ተብሏል። ምንም እንኳን ለምትጠይቀዉ ጥያቄ መልስ የመስጠት አቅም እንደሌለው ግልጽ ቢሆንም አስክሬኑን ልታናግረው ስትሞክር ትታያለች፡፡“አጎቴ እየሰማህ ነው? መፈረም አለብህ። ካልፈረምክ ምንም መንገድ የለም ” እያለች ስትናገር እንደነበር ምስክሮች ኤሪካ ዴ ሱዛ ቪዬራ ኑነስ በዊልቸር ላይ ለተቀመጠዉ አስከሬን ስትናገር ሰምተዋል፡ "ላንተ መፈረም አልችልም፤ማድረግ የምችለውን አደርጋለሁ፤ ተጨማሪ ራስ ምታት እንዳትሰጠኝ ስምህን መዝግብ ስትል ትደመጣለች፡፡ ከባንኩ ሰራተኞች አንዱ "ደህና ነው ብዬ አላምንም" ሲል ይደመጣል፤ቪዬራ ኑኔስ ግን "አጎቷ" ደህና እንደሆነ ትናገራለች ፣ ትንሽ ዝምታ ስለሚያበዛ ነዉ በማለት ለማስተባበል ሞክራለች፡፡ ግን በዚህ ደረጃ መቀጠል ስላልተቻለ የባንክ ሰራተኞች የድንገተኛ ጊዜ አገልግሎት እና ፖሊስን ለመጥራት ተገደዋል፡፡ፖሊሶች እስኪመጡ ባለዉ ጊዜ የ 42 ዓመቷ ሴት “አጎቴ የሆነ ነገር እየተሰማህ ነው? ደህና ካልሆንክ ወደ ሆስፒታል ልወስድህ ነው። እንደገና ወደ ድንገተኛ ክፍል መሄድ ትፈልጋለህ? ” በማለት ለማስመሰል ስትሞክር ተስተዉላለች፡፡ ፓውሎ ሮቤርቶ ብራጋ ቢያንስ ባንክ ከመምጣቱ ከጥቂት ሰዓታት በፊት መሞቱን የህክምና ባለሙያዎች ያረጋገጠየ ሲሆን ቪዬራ ኑነስ አስክሬንን በማንቋሸሽ እና በማጭበርበር ወንጀል ተይዛ ተከሳለች።የኤሪካ ደ ሱዛ ቪዬራ ኑኔስ ጠበቃ ለብራዚል ጋዜጠኞች እንደተናገሩት እውነታው በፖሊስ ምንጮች ተሳስቷል። ኤሪካ ወደ ባንክ ስታመጣዉ ፓውሎ ሮቤርቶ ብራጋ በህይወት እንደነበረ እና በብድር ማፅደቁ ሂደት ላይ ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ በበኩሉ የ42 ዓመቷ ሴት ወደ ባንክ ስታመጣዉ አጎቷ መሞቱን እንደምታውቅ እና ተቋሙን ማጭበርበር ብቻ እንደምትፈልግ ተናግሯል። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው የእናቷ ወንድም እንዳልሆነና የሩቅ ዘመድ ስለመሆኗ ቢረጋገጥም የሟች ጠባቂ እንደነበረች በራሱ ግልጽ አይደለም ሲል የብራዚል ፖሉስ አክሏል፡፡ በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😁 29👍 10😱 3👏 2🤔 2 1🥰 1
በጅማ ከተማ 18 የቤት ክዳን ቆርቆሮ ከተቀጠረበት መደብር ውስጥ የሰረቀው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በጅማ ከተማ አስተዳደር ፌርማታ መርካቶ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ 18 የቤት ቆርቆሮ ክዳን የሰረቀው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የጅማ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል። የጅማ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት የምርመራ ክፍል ሀላፊ ም/ኢንስፔክተር አስፋው ምስጋና ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን እንደተናገሩት ተከሳሽ መሀመድ ሙስጠፋ በህንፃ መሸጫ መደብር ውስጥ በእቃ ጫኝ እና አውራጅነት ይሰራ ነበር ብለዋል። የተቀጠረበትን የመጋዘገን ቁልፍ ከድርጅቱ ባለቤት አታሎ በመውሰድ ከድርጅቱ መጋዘን ውስጥ ገብቶ 18 የቤት ክዳን ቆርቆሮዎችን ሰርቆ ሊወስድ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል።ተከሳሹ ከመደብሩ ገብቶ የወሰደውን ቆርቆሮ 10ሺ800 ብር የሚያወጣ መሆኑን ተናግረዋል።ፖሊስም ተከሳሹን ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር አውሎ በአፋጣኝ የምርመራ መዝገቡ ለአቃቤህግ ተልኳል። አቃቤህግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ለጅማ ከተማ ወረዳ አንድ ፍርድ ቤት ክስ መስርቷል።ፍርድቤቱም ተከሳሽ መሀመድ ሙስጠፋ በፈፀመው ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ2 ዓመት እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት ም/ኢንስፔክተር አስፋው ምስጋና ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል። በምህረት ታደሰ #
Show all...
👍 6👎 2
የቡርኪናፋሶ መንግስት ሶስት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን ከሀገሪቱ አባረረ የቡርኪናፋሶ መንግስት ሶስት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶች የሀገሪቱን ህግ ጥሰዋል በሚል ከሀገሪቱ አባሯል። የቡርኪናፋሶ መንግስት ማክሰኞ ለት ለፈረንሳይ ኤንባሲ በላከዉ ደብዳቤ ሶስቱ ፈረንሳዊያን በ 48 ሰዓታት ሀገሪቱን ለቅቀዉ እንዲወጡ ያሳሰበ ነበር። ሶስቱ ዲፕሎማቶች የተከሰሱበት ጉዳይ በዝርዝር አልተገለጸም የተባለ ሲሆን የፈረንሳይ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴርም በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ አልሰጠም ተብሏል። ቡርኪናፋሶ ለዚህ ዉሳኔ የደረሰችዉ ሶስቱ ዲፕሎማቶች ከሲቪል ማህበረሰብ አባላት ጋር ካደረጉት ዉይይት በኋላ መሆኑ ተነግሯል። ቡርኪናፋሶ እ.ኤ.አ በ 2022 በመፈንቅለ መንግስት አዲስ ወታደራዊ አመራር ካገኘች ወዲህ በተለይም ከፈረንሳይ ጋር ያላት ግንኙነት ለየቅል ሆኗል። የኦጋዱጉዉ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላም ፈረንሳይ አምባሳደሯን እንድትጠራ ያስገደዱ ዉሳኔዎችን አስተላልፏል። የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቅቀዉ እንዲወጡም ያደረገ ሲሆን አንዳንድ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃኖችንም አግዷል። የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግስት የአልቃይዳ እና ኢስላሚክ ስቴት ታጣቂዎች በሀገሪቱ የፈጠሩትን የጸጥታ ችግር ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገም ቢገኝም በመብት ተሟጋች ድርጅቶች ነጻነትን በመንፈጉ እና የመናገር መብትን በመገደቡ ትችት እየቀረበበት ይገኛል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 19 4👏 2👎 1
#Update ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ መፍቀዱ ተሰምቷል፡፡ የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ሴኪዩሪቲዎች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ ማቅረቡን ዳጉ ጆርናል ከፋና ዘገባ ተመልክቷል። በዚህ መነሻ መሰረትም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው፤ ይሁን እንጂ ወንጀል አለመፈጸማቸውን አስረድተዋል። ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ፈቅዷል። #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 13👏 10😁 5💯 1