Alex Abreham - በነገራችን ላይ
رفتن به کانال در Telegram
በገበያ ላይ የሚገኙ የአሌክስ አብረሃም መፅሐፍት ዝርዝር 1- አልተዘዋወረችም 2- ከዕለታት ግማሽ ቀን 3- ዙቤይዳ 4 - ዶክተር አሸብር 5 - እናት ሀገር ፍቅር 6 - አንፈርስም አንታደስም 💚💛❤️ Official Fan Channel ! አሌክስ ማለት በቃ አሌክስ ነው:: Contact me @akexeth
نمایش بیشتر6 998
مشترکین
+124 ساعت
+117 روز
+430 روز
در حال بارگیری داده...
کانالهای مشابه
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
ژوئن '26
ژوئن '26
+43
در 0 کانالها
مه '26
+100
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '26
+87
در 2 کانالها
Get PRO
مارس '26
+97
در 1 کانالها
Get PRO
فوریه '26
+102
در 1 کانالها
Get PRO
ژانویه '26
+61
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '25
+65
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '25
+64
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '25
+76
در 2 کانالها
Get PRO
سپتامبر '25
+123
در 2 کانالها
Get PRO
اوت '25
+106
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '25
+112
در 1 کانالها
Get PRO
ژوئن '25
+96
در 1 کانالها
Get PRO
مه '25
+124
در 2 کانالها
Get PRO
آوریل '25
+172
در 1 کانالها
Get PRO
مارس '25
+109
در 1 کانالها
Get PRO
فوریه '25
+112
در 2 کانالها
Get PRO
ژانویه '25
+190
در 2 کانالها
Get PRO
دسامبر '24
+178
در 3 کانالها
Get PRO
نوامبر '24
+85
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '24
+124
در 1 کانالها
Get PRO
سپتامبر '24
+96
در 1 کانالها
Get PRO
اوت '24
+118
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '24
+97
در 1 کانالها
Get PRO
ژوئن '24
+77
در 0 کانالها
Get PRO
مه '24
+129
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '24
+144
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '24
+86
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '24
+124
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '24
+165
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '23
+51
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '23
+40
در 1 کانالها
Get PRO
اکتبر '23
+44
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '23
+33
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '23
+36
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '23
+58
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '23
+57
در 0 کانالها
Get PRO
مه '23
+72
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '23
+62
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '23
+77
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '23
+73
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '23
+142
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '22
+148
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '22
+207
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '22
+152
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '22
+141
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '22
+150
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '22
+191
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '22
+278
در 0 کانالها
Get PRO
مه '22
+94
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '22
+83
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '22
+97
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '22
+50
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '22
+67
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '21
+65
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '21
+55
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '21
+42
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '21
+114
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '21
+152
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '21
+232
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '21
+191
در 0 کانالها
Get PRO
مه '21
+267
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '21
+266
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '21
+132
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '21
+129
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '21
+140
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '20
+5 006
در 0 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 11 ژوئن | +1 | |||
| 10 ژوئن | +6 | |||
| 09 ژوئن | +4 | |||
| 08 ژوئن | +10 | |||
| 07 ژوئن | +6 | |||
| 06 ژوئن | +2 | |||
| 05 ژوئن | +3 | |||
| 04 ژوئن | +1 | |||
| 03 ژوئن | +3 | |||
| 02 ژوئن | +2 | |||
| 01 ژوئن | +5 |
پستهای کانال
እየመጡ ነው!
(አሌክስ አብርሃም)
ቦሌና መገናኛ ጫማ ልትገዙ ስትሄዱ ድንገት አግኝታችሁት እንዳትደነግጡ ከወዲሁ ልንገራችሁ።
የቻይናው ብሔራዊ የሕክምና ምርቶች አስተዳደር NEO (Neural Electronic Opportunity) ጭንቅላት ውስጥ የሚቀበር ቺፕ ለገበያ እንዲውል በይፋ ፈቅዷል። በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የጭንቅላት ውስጥ ቺፕ የንግድ ፈቃድ ተሰጠ ማለት ነው። (እንደፈራነው) ጦቢያዊያን ለአመታት ችብስ 666 ...ስንለው የነበረው ጉዳይ ያው እየመጣ ነው። ነገ እንደጥርስ ማስታወቂያ በተወሳሰቡ የህክምና ቃላት ታጅቦ "አስመጥተናል" የሚል ማስታወቂያ መነገሩ አይቀሬ ነው።
ለጊዜው ለአካል ጉዳተኞች ረዳትነት ብቻ ይውላል ብለዋል። ያው አንድ ነገር ከተመረተ በኋላ የቴክኖሎጅውን ፍጥነት በስልክ ማየት ነው። ዝርዝሩ ይቅርብን ግን ኤሎን ማስክ 'Neuralink' ብሎ የጀመረውን ፕሮጀክት ቻይናወቹ ቀድመው ለገበያ አውለውታል።የሆነ ቀን ቱርክ ፀጉር ከቱርክ አንጎል ከቻይና አሰገጥመን ሸገር ላይ እንግሊዝኛውን ልናዶለዱለው እንችላለን።
ችግሩ ሀክ ሊደረግም ይችላል የሚል ስጋት መኖሩ ነው። አስበሽዋል እናት የሰርግሽ ቀን የባልሽ አንጎል ሃክ ቢደረግ? ወጩ ጋር ተዳምሮ...😁
| 2 | ባሰብኩት ቁጥር ፈገግ የሚያደርገኝ የምርጫ ክርክር..ምርጫ ዘጠና ሰባት ላይ ኢህአዴግን ወክለው የተወዳደሩ ሁለት የመብራት ሐይል ሰራተኞች ነበሩ። አጋጣሚ ይሁን ታስቦበት እኔጃ !
እና የጦፈ ክርክር ላይ"እኛ ብንመረጥ በብርሃን ነው መንገዱን ሁሉ የምናጥለቀልቀው.... ምናምን ሲሉ የቅንጅት ተፎካካሪያቸው ጣልቃ ገብቶ ምን ቢል ጥሩ ነው " እነዚህን ሰወች ብትመርጧቸው አንዱ መብራት ያጠፋል ሌላው ያበራል፣ ከዚያ ሽፍት ይቀያየራሉ አብሪው ያጠፋል አጥፊው ያበራል" 😁 | 827 |
| 3 | ዛሬ አዳሬን አንድ ሁለት መርከብ በሚሳኤል አኖጋሁ ትላለች ኢራን፤ አዳሬን አንድ ስድስት የሚሳኤል ጣቢያ አደባየሁ ትላለች አሜሪካ፤ የነዳጅ ጉድጓድ ሲኦል አደረኩ ትላለች ኢስራኤል፣ የሀይል ማመንጫ አደባየሁ ትላለች ሩሲያ በዮክሬን። የሱዳኖቹ ጎረምሶች ድሮን ጣልኩ ከተማ አነደድኩ ይባባላሉ፤ የኛም አገር አከርካሪ ሰበርኩ ቅልጥም ሰበርኩ ይባባላሉ(አጥንት ነክ ነው ጦርነታችን) እና በአንድ ሌሊት በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር እየነደደ ዓለምን ሲያሞቅ ለምንድነው እኔ ቀዳዳ ጫማ የማደርገው፣ ለምንድነው የቤት ኪራይ የምጨነቀው? ለምንድነው ልጆቸ ልኳንዳ የተሰቀለ ስጋ እያዮ ምራቃቸውን የሚውጡት? ለምንድነው መታከሚያ አጥቸ እያቃሰትኩ የምኖረው? ለምንድነው ሰላሳ ቀን ለፍቸ እንደይሁዳ ሰላሳ ዲናር ደመወዜ ከንቱ የሚሆነው? ማለት አያምራችሁም? ለምን? ወይስ በዚህ ሁሉ ጦርነት ህዝብ ሲረግፍ እኔ መትረፌ ለምን እንበል? | 841 |
| 4 | ብዢታ
(አሌክስ አብርሃም)
የሆነ ቀን ሶፋ ላይ ጋደም እንዳለች እንቅልፍ ወሰዳት። ስትነቃ ብዢ ብሎባታል። የግድግዳውን ሰዓት ተመለከተች፤ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ይላል። ተበሳጨች፣ ባሏ አልገባም። "ይሄ ደደብ ዛሬም ሰክሮ ሊመጣ ነው!" አለች። ትንሽ ቆይታ አእምሮዋ ከእንቅልፍ ሙሉ ለሙሉ ሲነቃና በደንብ ማሰብ ሲጀምር ግን ብቻዋን በሳቅ ፈረሰች... ባሏ ከሁለት ወር በፊት መሞቱን ረስታው ነበር። | 1 003 |
| 5 | "እኔን ዋትስ አፕ ወላንሳ?
(አሌክስ አብርሃም)
የሆነ ጊዜ ከልተው ከልተው እያልኩ ከስራ ስመለስ የተከራየሁበት ቤት ድግስ ተደግሶ፣ ሙዚቃ ተከፍቶ ደረስኩ። የሆነ አሰልቺ «ልዩ ልዩ ቀን ነው...» የሚል ዘፈን ያላዝናል፣ ከዚያ ደግሞ የብሔር ብሔረሰቦች ዘፈን ይጮኻል። እናትየዋ ጥርስ ብቻ ሆነው «ካልገባህ» ሲሉኝ ገባሁ። ጎረቤቱ ቢራ ይራጫል፤ ክትፎው ወጡ በዓይነት ቀርቧል። ጎረቤቱ ሁሉ «እንኳን ደስ ያላችሁ!» ይላል። በኋላ ስሰማ፣ የሐኪሞች ይሁን የሕክምና ቦርድ የሚባል የባለቤቶቹን ልጅ ወላንሳን «ውጭ አገር ትታከም» የሚል ውሳኔ በማሳለፉ ኖሯል። ጭራሽ እዛ ሁሉ ሰው ፊት " በቸሩ መድሃኒያለምና በአንተ እርዳታ ለዚህ በቃች" ብለው የጎረቤት ቆነጃጅቶች ሁሉ ከዚያ በኋላ "አሜሪካ የሚልከው ልጅ" እያሉ በፍቅር ያዮኝ ጀመር።
በእርግጥ ለቦርዱ «ይህን ጻፍልኝ»፣ ለሆነ ድርጅት «ኢሜይል ላክልኝ» እያሉ ወደ አንድ ዓመት ፍዳዬን አብልተውኛል። በተለይ ቁጥር ስፍር የሌለውን የመድኃኒት ማዘዣ (የሐኪም ጽሕፈት አስባችሁታል?) «አንብብልን» እያሉ ያበሉኝ መከራ አልረሳውም። ኧረ ስንት ቀን ሰው ጠፍቶ እኔና እናቷ እየደገፍን ዋናው መንገድ ድረስ ወስደናታል። የሆነ ሆኖ ልጅቱ «ለሕክምና» ሄደችና በዚያው ቀረች ቀረች። እኔም በሰላምና በጤና አራት ዓመት ኖርኩ።
በኋላ ግን፣ ያውም በክረምት፣ «ልጄ ከአሜሪካ ልትመጣ ስለሆነ ቤት ልቀቅ» ተባልኩ። ነገረኛ መሆን ፈለግኩና «ኧረ እለቃለሁ! እንኳን ሕክምናዋን ጨረሰች እንጂ» ስላቸው ፊታቸው እንዴት እንደተቀያየረ! 😁 ሁላችንም «ሾርት ሜሞሪ» ያለን ነው እንዴ የሚመስላቸው? አጋጣሚ ሆኖ እዚያው ሦስት ግቢ አልፎ ቤት አገኘሁ። ተከራዮ የነበረው ልጅ በትንሽ ፀብ (ስድስት ጥርስ አውልቆ፣) ሦስት ዓመት ተፈርዶበት ታስሮ እስኪፈታ ድረስ «ኑርበት» ተብዬ።
እናም ልጅቱ ከአሜሪካ መጣች። ከሳምንት በኋላ በሁለት ጎረምሶች በግራና በቀኝ ተደግፋ እየተንቀጠቀጠች ስትሄድ አየኋት። እንደገና ያመማት መስሎኝ (መቼም ቂም የሚባል ነገር አላውቅም) «እኔን እህቴን!» ብዬ በቅንነት ብጠጋ፣ ለካስ ያደረገችው ባለ ረዢም ሂል ጫማ መራመድ አስቸግሯት ኖሯል! (ምንስ ውድ ብራንድ ቢሆን እንዲህ መሰቃየት ምን ይባላል?) ደግሞ ደጋፊወቹስ ቢሆኑ ያኔ የት ነበሩ?! ጭራሽ ስታየኝ አራት ጣቶቿን በቄንጥ አውለብልባ «ዋስ አፕ!» አለችኝ።
ፋሲል ደመወዝ «እኔን ዋትስ አፕ ፍቅር አዲስ?!» ያለው ወዶ ነው! እኔን ዋትስ አፕ ወላንሳ?! | 2 124 |
| 6 | የእሹሩሩ ሆርሞን!
(አሌክስ አብርሃም)
ለተመልካች በጣም አስገራሚ እና የብዙ ሰዎችን ቀልብ የሚስብ ነገር ነው። ስጋ በል የሆኑ አዳኝ እንስሳት (ነብር፣ አንበሳ ወይም አቦሸማኔ ወዘተ) የትንሽ ሚዳቆዎችን ወይም የሌሎች እንስሳት ግልገሎችን ድንገት ይይዛሉ። እና ሳይገድሏቸው ሲያጫውቷቸው ወይም ጥበቃ ሲያደርጉላቸው ይታያል። የእንስሳት ዶክሜንተሪወች ላይ አይታችሁ አታውቁም?
ይህ ባህሪ በባለሙያወቹ አጠራር "Maternal Instinct" ይባላል። "የወላድ ደመነፍስ" ልትሉት ትችላላችሁ። በተለይ ያደነችው እንስሳ በቅርብ የወለደች እናት ነብር ፣ አንበሳ ... ከሆነች፣ኦክሲቶሲን እና ፕሮላክቲን የሚባሉትን ሆርሞኖች በውስጧ ከፍ ይላሉ። እነዚህ ሆርሞኖች የአዳኝነት ስሜታቸውን ለጊዜው በመጫን የማቀፍ፣ የመጠበቅና የመንከባከብ የእናትነት ባህሪ እንድታሳይ ያደርጋታል። በደሟ ውስጥ ያለው የሆርሞን መጠን የትኛውንም ህጻን ግልገል የመንከባከብ ስሜት ሊያድርባት ይችላል። እንደው ከሌሎች አዳኝ እንስሳ ሁሉ እየተፋለመች ትከላከልላቸዋለች። ለግልገሎች አንጀቷ ይንሰፈሰፋል።
መጨረሻቸው ምን ይሆናል ነው ጥያቄው....አሳድገው ለወግ ማረግ ያበቋቸዋል?(በሰውኛ)
በአጭሩ የእነዚህ ህጻናት ሚዳቆዎች የመጨረሻ እጣ ፈንታ አያምርም!! የአዳኟ እንስሳ የእናትነት ሆርሞን ሲቀንስ ፣ መራብ ስትጀምር ወይም የዱር እንስሳነቱ የአዳኝነት ተፈጥሮ ድንገት ሲቀሰቀስ፣ ያ ሲንከባከቡት የነበረውን ግልገል ክትፎ መስሎ ይታያቸው ይጀምራል፣ ቁርጥ መስሎ ይታያቸዋል.... ባልታሰበ ቀን ገነጣጥለው ይሰለቅጡታል።
ምንም እንኳን ነብሮችና አንበሳወች ለተወሰነ ጊዜ የዋህነትና የእናትነት ስሜት ቢያሳዩም፣ ተፈጥሮ ጨካኝ በመሆኗ የእነዚህ ህጻናት ሚዳቆዎች ታሪክ መጨረሻው አያምርም። በህይወት የመትረፍ ዕድላቸው ወደ ዜሮ የተጠጋ ነው። ምን ለማለት ነው? (((ከእሹሩሩ ሆርሞን ራሳችሁን ጠብቁ! እንክብካቤ ሁሉ ፍቅር አይደለም! ))) | 2 121 |
| 7 | بدون متن... | 1 540 |
| 8 | ስማ አብርሽ አሁን የወፎች ጫጫታ ምኑ ነው ዝማሬ እየተባለ የሚሞካሸው?
እኔጃ አስቸ!
ጭጭጭጭ ሲያስጠሉ። መርካቶ ይሻላል። የሰው ልጅ አሽቃባጭ ስለሆነ እንጅ የወፍ ጩኸት ከውሻ ከጅብ ከድመት ጩኸት በምን ይለያል? ዛሬኮነው ድንገት በጧቱ ነቅቸ በደንብ የሰማኋቸው።
እና ደበረህ?
ቀላል ደበረኝ! ጆሮየን ሁሉ ነው የያዝኩት። የጅብ ጩኸት ከእነሱ የተሻለ ዜማ አለው። እኔ የምልህ ዶሮ የወፍ ዘር ነው?
መሠለኝ
የዶሮ ጩኸት ይሻላል...አይንህን ከድነህ ስትሰማው ዶሮ ወጥ ያስታውስሃል የሆነ የሚፍለቀለቅ አጥንቱ ብቅ ጥልቅ የሚል ቀይ ወጥ። የዶሮ ጩኸት ነው መዝሙር። መዝሙር ያለተስፋ ምን መዝሙር ነው?!😁
ሁልጊዜ መቃሚያ ሊጠይቀኝ ከፈለገ ይፈላሰፋል😁 | 1 801 |
| 9 | አሜሪካ ሄጀ ወያላ ልሁን የሚል ኮሜንት እንዳትሰጡ!
(አሌክስ አብርሃም)
ባለፈው አንድ መኪና ከፊቴ ቆመና የ "STOP" ምልክቱን ዘረጋ። ሁላችንም ከኋላ ተደርድረን ቆምን። ልክ እንደስኩል ባስ አይነት ግን ትንሽ ቫን ነገር ነው። እና በሩ ተከፍቶ አንድ ውሻ ሮጦ ወጣና ቁማ ወደምትጠብቀው ሴት ጋር ሄዶ በደስታ ይቦርቅ ጀመር። አቅፋ ሳመችው። ውሾች ልክ እንደትምህርት ቤት ውለው ሲመለሱ የሚመላለሱበት የውሻ ሰርቪስ ነው። Doggy Daycare Bus” ወይም “Puppy School Bus” እየተባለ ይጠራል።
ውሾቹ የት ነው የሚውሉት? ብየ ጎግል ሳደርግ
እነዚህ ውሾች የሚሄዱት ባለቤቶቻቸው ስራ ሲሄዱ "Doggy Daycare" ወደሚባሉ ቦታዎች ነው። እዚያ ቀኑን ሙሉ ብቻቸውን ቤት ውስጥ ከመቀመጥ ይልቅ እንደልጆች ጧት ከየቤታቸው በሰርቪስ ሄደው ከሌሎች ውሾች ጋር ይጫወታሉ፣ ዋና ይዋኛሉ፣ እንቅልፍ ይተኛሉ፣ እንዲሁም አንዳንድ የስነ ምግባር ስልጠናዎችን ያገኛሉ።
ባለቤቶች ጠዋት ወደ ስራ ከመሄዳቸው በፊት ውሻቸውን ማቆያ ቦታ ድረስ መውሰድ ስለሚደክማቸው፣ ይህ የባስ አገልግሎት ትልቅ እፎይታ ሆኖላቸዋል። አስባችሁታል "ውሻሽ የት ነው የሚማረው?" ምናምን ሲባባሉ!
ወደቲክቶክ ስመለስ አንዲት መንግስት ቤት 20 ዓመት የሰራች ሴትዮ ከኮየ ፈጨ በሰልፊ ቪዲዮ ቅሬታዋን እያቀረበች ነው። "ለሚመለከተው አድርሱልኝ... 56 ቁጥር ባስ ቀረችብኝ ይሄው ሕዝቡ ተሰልፎ እየጠበቀ ... ከስራ አረፈድን " እያለች። | 1 611 |
| 10 | ቻይናዊው ሻወር እየወሰደ እያለ፣ ድንገት ቤቱ በእሳት ይያያዛል... ራቁቱን በመስኮት ዘሎ ይወጣል። ትንሽ እንደተረጋጋ ሚስቱ የሚቃጠለው ቤት ውስጥ መቅረቷን ያስታውሳል፤ ነገር ግን "እንግዲህ ቀኗ ካልደረሰ መውጣቷ አይቀርም" ብሎ ችላ ይላታል።
ወዲያው ግን አንድ በጣም አስደንጋጭ ነገር ትዝ ይለውና፣ በአስደናቂ ጀግንነት ድጋሚ ዘሎ ወደሚቃጠለው ቤት ይገባል። ሚስቱንም አንከብክቦ ይዟት ይወጣል።
በኋላ ላይ ጋዜጠኞች ተሰብስበው፦ "እንዴት በዚህ ድፍረት ወደሚቃጠለው ቤት ገብተህ ሚስትህን ልታተርፋት ቻልክ? ስታገኛትስ በምን ሁኔታ ላይ ነበረች?" ብለው ጠየቁት።
ስሜቱን በራሱ ቋንቋ እንስማው...
我不能把手机和妻子单独留在家里。我一直担心她会拿起我的手机偷看信息。当我急匆匆地冲进家门时,果然不出所料,她正一边被浓烟包围着剧烈咳嗽,一边在翻看我的手机。最终,我把她和手机一起救了出来。
አቻ ትርጉም ከትንሽ ቅመም ጋር
"ስልኬንና ሚስቴን ብቻቸውን እቤት ውስጥ መተው ፈጽሞ አልችልም! 'የተላላኩትን መልዕክት እያነበበች ይሆን?' የሚለው ስጋት እረፍት ነሳኝ። ዘልዬ እቤት ውስጥ ስገባ ልክ እንደፈራሁት፤ በጭስ ተከባ የቀሚሷ ጫፍ በእሳት እየተቀጣጠለና እያሳለች ስልኬን ስትፈትሽ አገኘኋት! በጨዋነት ስልኬን ተቀብየ ልወጣ ስሞክር 'ዢዋን ማናት? ለምንስ የልብ ኢሞጂ ላክህላት?' እያለች በዚያ ጭስ ውስጥ መጨቃጨቅ ጀመረች። ሌላ አማራጭ ስላልነበረኝ፣ ከነስልኩ አንጠልጥዬ ይዣት ወጣሁ።"
ክፉ ጊዜ ላይ ነን እ? 😁 | 2 081 |
| 11 | ግንቦት ሃያ ማይደል ሁለት አስገራሚ ነገሮች!
(አሌክስ አብርሃም)
1
እዚህ ከመጣሁ ያወቅኋቸው በጣም የተረጋጉ ባልና ሚስቶች አሉ። እርሷ ከትግራይ፣ እርሱ ደግሞ ከደቡብ ክልል ነው። ርግት ያሉ ጴንጤዎች ናቸው። አቤት መከባበር! አቤት ፍቅር!
እና የሆነ ቀን በምን እንደተነሳ እንጃ፤ "እንዴት ተገናኛችሁ?" አልኳቸው። ተሳሳቁና "ንገረው እንጂ፤ ራስህ ንገረው" ሲባባሉ ቆይተው እርሱ መናገር ጀመረ፦
"ማርካ ነው ያገባችኝ" አለና እየሳቀ በፍቅር እጇን በእጁ ያዘ።
"በፍቅር ነው?" ለመቀለድ ሞከርኩ።
"የምን ፍቅር... እኔ ወታደር ነበርኩ፤ እርሷ የወያኔ ታጋይ... 'ክምር ድንጋይ' በሚባል ቦታ በ1983 ዓ.ም. ስንዋጋ ማረከችኝ። ሁሉም አልቆ እኔና አንድ ሻለቃ ብቻ ነን የተማረክነው። ትውውቃችን እዚያ ነው። በኋላ በ1986 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ እንደገና ተገናኘን። ቆይቶ ጌታ ሁለታችንንም ማረከን" በማለት በሳቅ አጀበው። 😁
2.
አሁን በቅርቡ የሰሜኑ ጦርነት ወቅት "ከዕለታት ግማሽ ቀን" የሚል መጽሐፍ አሳትሜ ነበር። አንባቢዎቼ ከተለያየ ቦታ መጽሐፉን ይዘው ፎቶ እየተነሱ ይልኩልኛል። አንድ ወታደር ከወራት በኋላ መጽሐፉን ይዞ የተነሳውን ፎቶ ላከልኝና እንዲህ የሚል መልዕክት ጨመረበት፦
"አሌክስ፣ አድናቂህ ነኝ፤ የእግዚአብሔር ነገር ይገርማል። አዲስ መጽሐፍ ማውጣትህን አላወቅሁም ነበር። እንደምታየው ችግር ላይ ነን (ጦርነቱን ማለቱ ነው)፤ አንድ ቦታ በነበረ ውጊያ የተገደሉ የጠላት ወታደሮችን ስንፈትሽ፣ አንዱ የሞተ ወታደር ቦርሳ ውስጥ አዲሱን መጽሐፍህን አገኘሁት።" | 2 082 |
| 12 | "ምን ጎዳና ጎዳና ትላላችሁ? አሜሪካም ጎዳና ተዳዳሪ አለ"
እንዲ የሚሉ ቅን አሳቢ ሰዎች አያለሁ። ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጭምር እንዲህ ሲናገሩ ማየቴ ይገርመኛል። ልክ ናቸውኮ፤ አሜሪካ ያለ ጎዳና ተዳዳሪ ቁጥር ስፍር የለውም። ግን የአሜሪካ ጎዳና ተዳዳሪ ከኢትዮጵያ ጎዳና ተዳዳሪ ጋር ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ ሀብታም ጋር ነው መነጻጸር ያለበት የሚል ሐሳብ አለኝ። መረጃ ላቅርብ፦
1. አንድ የአሜሪካ የጎዳና ተዳዳሪ ነጻ የህክምና አገልግሎት ያገኛል። የሚያገኘው ህክምና ኢትዮጵያዊ ሀብታም ወይም ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ወደአሜሪካ ሄዶ የሚያገኘውን፣ ወይም አንድ ደሃ በሐኪሞች ኮሚቴ ተወስኖለትና በህዝብ ተዋጥቶለት የሚያገኘውን በአለም አቀፍ ደረጃ የተመሰከረለትን ህክምና ነው። እንዲህም ሆኖ አሜሪካ ለጎዳና ተዳዳሪወች የምትሰጠው ህክምና በቂ አይደለም፣ የአእምሮና ከሱስ የማገገም ህክምና በደንብ በነፃ ሊሰጥ ይገባል እያሉ ዜጎች ፖለቲከኞች ይሞግታሉ።
አንዲት ሆምለስ ብታረግዝ ከእርግዝና ክትትል እስከማዋለድ የምታገኘው ነፃ ህክምና ኢትዮጵያዊያን ሴት አርቲስቶችና የሐብታም ሚስቶች አሜሪካ ሄደው ከሚያገኙት ህክምና ጋር እኩል ነው።
2. ከሁለት ዓመት በፊት የተሰራ ጥናት አንብቤያለሁ፤ USDA ወይም WHO ይመስለኛል ያስጠናው። የአሜሪካ ጎዳና ተዳዳሪወች ከብዙዎቹ የአፍሪካና ኤዢያ እንዲሁም ደቡብ አሜሪካ አገራት ነዋሪዎች የተሻለ ብዛትና ጥራት ያለው በካሎሪ ይዘቱም የተሻለ ምግብ ያገኛሉ።
3. ስለ ልብስ የሚጨነቅ የጎዳና ተዳዳሪ አለ ማለት ይከብዳል። ልብስና ጫማ እንደ አሜሪካ ዶኔት የሚደረግበት ሕዝብ በምድር ላይ የለም። አንድ አሜሪካዊ ከአውሮፓዊ ጋር ሲነፃፀር በአመት ከ6-8 ዕጥፍ ልብስ ይሸምታል። ያንኑ ያህል በየአመቱ እያወጣ ዶኔት ያደርጋል። በቁማቸው ቆሽሸው፣ አሳዛኝ ጠረናቸው አካባቢውን የሚረብሽ፣ በድራግ ራሳቸውን የረሱ የጎዳና ተዳዳሪዎች በብዛት አሉ። ከፈለጉ ግን ልብስ ያን ያህል አሳሳቢ አይደለም። በርካታ ድርጅቶች ልብስ ይሰጧቸዋል።
4. ትራንስፖርትን በተመለከተ፤ ከአመት እስከ አመት የነጻ አውቶቡስና የባቡር ኮፖን የሚሰጡ በርካታ ድርጅቶች አሉ። እየጫሩ ወደፈለጉበት ይሄዳሉ። መኪና ያላቸው ሆምለሶችም በጣም ብዙ ናቸው።
5. ኢንተርኔት የ24 ሰዓት የማይቆራረጥ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የሌለው የጎዳና ተዳዳሪ ካጋጠማችሁ። ብሶበት ነገር አለሙን የተወ መሆን አለበት።
6.ንፅህና የገላ መታጠቢያና የልብስ ማጠቢያ በርካታ የበጎ አድራጎት ተቋማት አሉ።
7. ትምህርት፦ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ልማር ካለ እልል ብለው የትምህርት ወጭውን የሚሸፍኑ፣ የግልም የመንግስትም በጎ አድራጎት ድርጅቶች አሉ። እንደውም የከተማ አስተዳደሮች በጀት መድበው የጎዳና ተዳዳሪወችን ለማስተማር በየጊዜው እንደለመኑና ማበረታቻ ቃል እንደገቡ ነው።
8. ሰብዓዊ ክብር፦ አንድን የጎዳና ተዳዳሪ ማነው ዝንምቡን እሽ የሚለው? እንኳን ሌላ አንዴ የቀመስክለትን ምግብ በቅንነት ብትሰጥ ነውርም ወንጀልም ተደርጎ ይታያል። ንፁህ ምግብ የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነው። ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ውስጥ በአለባበሱ በማንነቱ እንዳይጠቀም መከልከል ነውርም ወንጀልም ነው። ።
9. ፍትህ፦ ተበደልኩ ብሎ ለፖሊስ ቢደውል ለምን ቢሊየነር አትሆንም ፖሊስ በእኩል አይን ያስተናግድሃል። ካርቶን አንጥፈህ የምተኛበት በረንዳ ድረስ እየተንቀለቀ ከች የሚለና "ማናባቱ ነው ያስቀየመህ" የሚል የፍትህ ስርዓት አላቸው። አንድ አይምሮውን ነካ የሚያደርገው የጎዳና ተዳዳሪ ወደአርባ ጊዜ እየደወለ "ሰወች ሊገድሉኝ ነው" በማለቱ አርባውንም ጊዜ ፖሊሶች ሄደው ቸክ እንዳደረጉት አንዴ ሰምቻለሁ። ከአርባው አንዱ እውነት ቢሆንስ?
10. ህዝብም መንግስትም የእውነት ይራራላቸዋል።
እንዲህ ስልህ አሜሪካን ገነት አድርገህ ካየህ የዋህ ነህ። እነዚህ ሰወች ይሄ ሁሉ ቢሳካላቸውም ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው በሚዘገንን የአካልና የመንፈስ ስብራት የሚኖሩ ሰወች ናቸው። ህይወት ከቁስ ያለፈ ነገር እንዳላት የሚታይበት አገር ነው። በተለይ አደንዛዢ እፅ ሰውን እንደበቆሎ ፈልፍሎ ቆረቆንዳውን ሲያስቀር የሚታይበት ዘግናኝ ህይወት። ከላይ የዘረዘርኩት አንድ አገር ለዜጎቹ የሚያሳየውን እውነተኛ ክብር ማሳየትና አንዳንዴ ከማይሆን ንፅፅር ወጥተን እንደአቅማችን ለህዝባችን እንድንሰራ ለመጠቆም ያህል እንጅ የአሜሪካን ሐብት መስበክ አይደለም።
አሜሪካ ግራ ታጋባሀለች። ለምሳሌ ግሮ ጥሮ የሚያድረውን ሕዝብ ተመልከት። በቀን ሁለት ሰዓት እንኳ የማይተያዮ ባልና ሚስት ። ለሁለት ሰርተው በቢል አናታቸው የዞረ ሚስኪኖች ታያለህ። ባጭሩ ስትሰራ ታስከፍልሃለች ካልሰራህ ትረድሃለች። ደሃው በቀላሉ የሚያገኘውን መካከለኛ ገቢ ያለው ፍዳውን በልቶ ያገኘዋል። ወዘተ። | 2 659 |
| 13 | ነበርንም አለንም!
(አሌክስ አብርሃም)
እኔ ያደግኩበት ልጅነት በስልክ አልተረበሸም፤ በሰላሳ ለዛ ቢስ የቴሌቪዥን ቻናሎች አልተወረረም፤ በኢንተርኔት ሶሻል ሚዲያ አልተበከለም። ንፁህ ነበር እንደ ተፈጥሮ፤ ፍንትው ያለ፣ ብሩህና ጣፋጭ ነበር እንደ ጧት ፀሐይ።
ትምህርት ቤት እንሄዳለን፤ ስንመለስ ተሰብስበን ኳስ እንጫወታለን። እነ ኃይሌ ሲሮጡ፣ ወርቅና ብሩን ሲጠራርጉት እናያለን። የሆነ ቀን የአባባ ተስፋዬን ተረት አለ፤ ነፍሳችን ደስ ይላታል። ቤተሰብ የጀርመንንና የአሜሪካን ሬዲዮ እያንኮሻኮሹ ሲሰሙ ተደብረን ይሆናል፤ ቢሆንም የነጃርሶን ትረካ በዛው ሬዲዮ አጣጥመናል።
እነ ብርቱካን ሐረገወይን፣ ዓለምነህ ዋሴ፣ እነ ነጋሽ መሐመድ የዓለምን ምስቅልቅል እንደ ወተት በዜና አጠቡን። እነ ጋሽ ደጀኔ ጥላሁን ፣ አነጌትነት እንየው በሬዲዮ መጻሕፍትን ተረኩ፤ ጓጉተን ሰማናቸው። ከፍ ስንል መጻሕፍት ጠበቁን። እንደነ ሐዲስ አለማየሁ፣ ፀጋየ ገብረ መድህን በዓሉ ግርማ፣ ስብሃት ለዓብ፣ ሀይለመለኮት መዋዕል፣ እነጃርሶ፣ እነሲሳይ ንጉሱ፣ ፍቅረማርቆስ ደስታ፣ ሰርቅ ዳ ስራወች ጠበቁን።
የምስራቅና የምዕራብ ፍልስፍና ቀመስ መጻሕፍት ከተማችንን ወረሩ፤ "አርፋችሁ ትምህርታችሁን አታጠኑም?" እየተባልን በትርጉም አነበብን። የነኦሾን ቅማንጅር ፣ የእነ አጋታ ክርስቲ የወንጀልና የምርመራ ልብ-ወለዶች፣ የእነ ሲድኒ ሸልደን የሴራና ልብ ሰቃይ ልብ-ወለዶች፣ የእነ ማክሲም ጎርኪ የመረሩ ውብ የሩሲያ ተረኮች፣ የነ ኒኮላይ ጎጎል አስደማሚ አጭር ልብ-ወለዶች፣ የነ ኧርነስት ሄሚንግዌይ የሕይወት ትግል... አነበብን። ጋዜጣና መፅሄቶች መጡ " ከረቫት የሚለብስ ወንድ ደስ ይለኛል የሚሉ ቆነጃጅት የሽፋን ፎቶ ሆኑ ወጣት ልባችን በሙቀት አያቸው።
ይህ ሁሉ ሲሆን ዕድሜያችን ከአስራዎቹ አልዘለለም። ዛሬ የአርባና የአምሳ ዓመት ሰዎች መጥተው፣ እንደ ተአምር በልጅነት ያለፍናቸውን ተረቶች እንደ አስደማሚ ነገር ጢማቸውን እየላጉ፣ ከረቫታቸውን እያስተካከሉ፣ ሂውማን ሄራቸውን እየነሰነሱ "ካልነገርናችሁ" ሲሉን ትዕግሥት ብናጣ ይፈረድብናል? ቢሰለቸን፣ ቢያንገሸግሸን ትታዘቡናላችሁ? ከሰለቻችሁ አትሄዱም ይሉናል የት? በእድሜና በሀብት በስልጣንና ስም የቀደሙን ከፊታችን ይጃጃላሉ። መንገድ ዘግተው። ኋላችን ሮንቃ ነው የአሳማ ግልገሎች የሚቦርቁበት።
"እናቅልለው" ብለን ቀለን፣ "እናክብደው" ያሉት በቀለለባቸው ፍዳችንን እንብላ? ቅንጡ መኪና ሰልችቶት "ለጤናዬ" ብሎ በእግሩ የሚሄድን ሰው በባጃጅ ሊያስደምሙ የሚጋጋጡ ዜጎች ዓይነት ባሕርይ ሞላው ዘመኑን! ጭራችንን እያወዛወዝን "አይ ጊዜ!" አንል ነገር ገና ሰላሳ ውስጥ ነን። አርጅተናል ወይስ ዘመኑ እንጩጭ ሆኖብናል? እንጃ... እንጃ! ብቻ ነበርንም አለንም! | 3 070 |
| 14 | "ዱርየነት" የሚባለውን ባህሪ ፣ ሱሰኝነት፣ ወሲብ፣ ባህልና ወግ መጣስ ከከተማ ልጆች ጋር አያይዞ ማሰብና የገጠር ልጆችን ባህላቸውን ጠባቂ፣ ቁጥብ፣ ሐይማኖተኛ፣ በትምህርታቸው ጎበዝ፣ ቤተሰብና ማህበረሰባቸውን አክባሪ ወዘተ አድርጎ መሳል በጣም የተለመደ ነው። የኔ ጌታ (አጠቃላይ ገጠርን አይወክልም ይሄ ንግግሬ) ግን ቲክቶክ ላይ ያሉ የገጠር ልጆችን ተመልከት። በቃ ስልክና ኔትወርክ እጃቸው ላይ ከገባ ሴቶቹ አንድ የባለጌ ፋብሪካ የተመረቱ እስኪመስል የመጨረሻ ዘግናኝ ከሆነ የወሲብ ወሬ ውጭ ምንም አያወሩም። መሰልጠን ማለት ይሄ ልቅነት ይመስላቸዋል። በዚህ ጉልድፍነት ላይ ትንሽ ገንዘብ ከተጨመረማ በቃ!
ደግሞ አወራራቸው ሲቀፍ፣ ሲያስጠላ። ቲክቶክ ላይ ከየትኛውም ብሔር ይምጡ ብቻ የገጠር ሴቶችን ከሶስት ርዕሰ ጉዳዮች ውጭ ካገኘሃቸው እኔ ልቀጣ...
* ልቅና የቆሸሸ የወሲብ ወሬ... ባል ውሽማ ምናምን፣ አካላዊ ነገር ጋር የተያያዘ አቅለሽላሽ ቀልድ፣
*በለው ውቃው፣ ፍለጥ ቁረጥ ዘፈን ከፍቶ መደለቅ፣ እና
* ሐይማኖተኛ መምሰል፤ ግን ሐይማኖት ስለሚባለው ጉዳይ ርጋፊ ንባብም ዕውቀትም አለመኖር፤ የሐይማኖት ፀብ ንትርክ ካለ ዳይቭ ገብተው በዛ ጉልድፍ ዕውቀት ማንቦጫረቅ። የወንዶቹን ተወው! ፖለቲካ ይጨምሩበታል። እንዴ የከተማ ልጅኮ "ሸም" የሚባል ነገር ያውቃል። የእውነት ከጤፍና ከበቆሎ ጋር ባለጌም ከገጠር ወደከተማ ይጫናል? (እደግመዋለሁ የገጠር ሰው ሁሉ እያልኩ አይደለም) | 2 448 |
| 15 | ምክንያቱም ስራ አለኝ።
(አሌክስ አብርሃም)
ልክ ስራ እንደጀመርኩ ቅዳሜ ከቤቴ ወደ ሜክሲኮ በታክሲ እሄዳለሁ፤ 1.50 ብቻ ከፍዬ። ሜክሲኮ እንደደረስኩ የተቀጣጠርኩት ሰው ካለ ከሰው ጋር፣ ከሌለም ብቻዬን የምወደውን እንቁላል ፍርፍር አዛለሁ፤ በላዩ ላይ ቆንጆ ቡና እጠጣለሁ። የእለቱን ጋዜጦችና መፅሔቶች በስሙኒ ኪራይ አነባለሁ፤ የወደድኩትን ጋዜጣ ወይም መፅሔት እገዛለሁ። ጠቀም ያለ ቲፕ ለአስተናጋጆች እተዋለሁ፤ ምክንያቱም... ስራ አለኝ!
በታክሲ ወደ ፒያሳ አቀናለሁ። አራዳ ህንፃ ላይ አረፍ ብዬ ውሃ አዛለሁ፤ ለስራ የማገኛቸው ወዳጆቼ ጋር እናወራለን። «ቁርስ ካልበላችሁ ብሉ፣ ጠጡ» እላለሁ። እናም ለመክፈል ግብግብ እንገጥማለን፤ «እኔ ነኝ የምከፍለው... ስርዓት ያዝ!» እየተባባልን፤ ምክንያቱም ...ስራ አለን!
ከዳላስ ሙዚቃ ቤት አለፍ ብሎ የሚገኝ ካፌና ሬስቶራንት ነበር፤ እዛ እንሄዳለን። ማኪያቶ ቡና እንጠጣለን፣ እናወራለን፤ ፒዛቸውም አሪፍ ነበር፣ ፒያሳ በወርቅ ቤቶቹ መደዳ አልፎ ያሉት ካፌወች ውስጥ .... እንዝናናለን፤ ምክንያቱም... ስራ አለን!
ምሳ ሰዓት ይደርሳል፤ ብዙ ምርጫ ነው ያለው። ወደ አራት ኪሎ አመራለሁ፤ ሮሚና ቋንጣ ፍርፍር ወይም እዛው ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል። (ምሳ ሰዓት ፒያኖ የምትጫወት ጠይም ሴት ነበረች)፤ አጤ ሚኒሊክ ራሳቸው እዛ ሆቴል እንደ እኛ አልተዝናኑም፤ ምክንያቱም... ስራ አለን! ስራ ለራስ የሚሰጠው ንግስና አለ።
ከሰዓት ሌላ ጀመዓ ይመጣል፤ በልቶ ጠጥቶ የሚያዛጋ። «እናንተ ልጆች ይሄን ጫት ተው ብል በቃ አልሰማ አላችሁ?» እልና፣ «እግዜር ለጫት አዋጣህ እንዳይለኝ፤ እስቲ አሪፍ ራት ማታ ብሉ» ብዬ የሆነ ብር ሸጎጥ አደርጋለሁ፤ ምክንያቱም... ስራ አለኝ!
ስንለያይ ወደ አሮጌ ተራ ወይም ኤልያስ ጨበሬው ጋር ጎራ እልና ወይም እግር ከጣለው አዟሪ አዲስ የታተመ መፅሐፍ ካለ መፅሐፎች እሸምታለሁ። አለፍ ስል አንዱ ሱቅ ቆንጆ ቲሸርት ወይም ጫማ ካየሁ እሸምታለሁ፤ምክንያቱም.. ስራ አለኝ።
ማሳረጊያዬ ቲያትር ነው፤... ቲያትር አያለሁ። ወደ ቤት ስመለስ «ሺህ ዓመት አይኖር!» እልና 40 ወይም 50 ብር ሆጭ አድርጌ በኮንትራት ላዳ ታክሲ ነው። መግቢያዬ ላይ ካለች ፍራፍሬ መሸጫ የተወሰነ ማንሳቴም አይቀርም፤ ምክንያቱም... ስራ አለኝ!
ሩቅ አይመስልም? ከአስር ዓመት ብዙ አይርቅም! እኔ የምለው... ስራ አላችሁ? እስቲ «ስራ አለኝ» ብላችሁ ጀምሩና ስራችሁ እንዴት እንደሚያኖራችሁ አካፍሉን... | 2 614 |
| 16 | አጭር መልስ
ማሳጅ ቤት የፈለገ ፕሮፌሽናል ቢሆን፤(ከህክምና ጉዳይ ውጭ) ሚስትህ በወንድ ባለሙያ ማሳጅ ብትደረግ ወይም ባልሽ በሴት ምቾት ይነሰሃል/ይነሳሻል? በተለይ ባለሙያወቹ ከእናንተ የተሻለ አካላዊ ቁንጅና ቢኖራቸው?😁 | 3 191 |
| 17 | ሰው የፈለገ ቢሳሳት የመቃብር ሐውልት ላይ ፊደል ይሳሳታል?
(አሌክስ አብርሃም)
አሜሪካ ውስጥ በአገሩ ዘግናኝ ወንጀል የፈፀመ፣ ወይም ቢሊየን ብሮች የዘረፈ ወንጀለኛ ተሰዶ ይኖራል። አሁን እንደምነግራችሁ አይነት ሚስኪን ሰው ደግሞ አለ፣ በአንዲት ፊደል ምክንያት ለስደት የተዳረገ። በአንዲት ፊደል ብቻ!
ባለፈው ወደሆነ ቦታ በኡበር ታክሲ እየሄድኩ ነበር። ሹፌሩ ከማሌዢያ የመጣ ትልቅ ሰው ነው። እያወራኝ "ሀገሬ ላይ በጣም አሪፍ ቢዝነስ ነበረኝ። የመቃብር ላይ ጽሑፍ እጽፍ ነበር፤ ተንደላቅቄ ነበር የምኖረው" አለኝ። ባዘነ ድምፅ።
"እና ታዲያ ለምን ወደዚህ መጣህ?"
"የተሰደድኩት የአንድ የተረገመ ባለስልጣን ሚስት የመቃብር እምነበረድ ላይ አንዲት ፊደል ተሳስቼ በመጻፌ፣ ሊገድለኝ ስለፈለገ ነበር" አለኝ።
"እውነትህን ነው? ለአንዲት ፊደል?!"
"አዎ ጌታዬ! አየህ፣ የምንጠቀመው ማላይኛ (ባሃሳ ማሌዢያ ይሉታል) በላቲን ፊደላት ነው የሚጻፈው። አንዲት ፊደል የምትፈጥረው ስህተት ቀላል እንዳይመስልህ። በእኛ ቋንቋ 'Kota' ማለት 'ከተማ' ማለት ነው። እኔም ሐውልቱ ላይ (('ባልሽ ብቻ ሳይሆን ቸርነትሽን የቀመሰው ሙሉ ከተማው አንቺን ይናፍቃል)) ብዬ አሳምሬ ጻፍኩ። ነገር ግን የሐውልቱ ምርቃት ቀን፣ ድፍን የከተማው ባለስልጣናትና ሀብታሞች በተሰበሰቡበት የተሸፈነበት ጨርቅ ሲነሳ... 'Kota' የሚለው ቃል ላይ ተሳስቼ 'a'ን በ 'e' ተክቻት ነበር። የተረገመች 'e'!" አለና መሪውን በቡጢ ነረተው።
"እና 'e' ስትጨምርበት ምን ሆነ?" አልኩት።
"Kote ሆነ!"
"እኮ 'Kote' ምንድን ነው?"
"የወንድ ብልት!" | 3 621 |
| 18 | ሶስት ሽማግሌወች ቀንዶ አረቄ ወይም አብጤ እንደሚሉት ደግ ልጅ ሶስት ጁስ ይዘው በባጃጅ ወይም በራይድ ሄደው "ልጃችሁን ለልጃችን" ካሉ በቂ ነው። ሽምግልና ከዚህ ማለፍ የለበትም! "ኧረ በዚህ የኑሮ ውድነት ቀንዶ አረቄ ከየት ይመጣል... ምናምን" የሚል ከሆነ እንዳታገቢው፤ እከካም! ፊት ሲሰጡት በጣም ያካል እንዴ! | 3 308 |
| 19 | የኛ ሴቶች የደፈሯችሁ በከንፈራቸው ነው...
(አሌክስ አብርሃም)
በጣሊያን ሰሜናዊ ክፍል የሚገነባ የከፍተኛ ፍጥነት ባቡር ሀዲድ አለ። የጣሊያኑን ቱሪን ከፈረንሳዩ ሊዮን ከተሞች የሚያገናኝ። ሕዝቡ ግንባታውን ተቃወመ። ምክንያቱ ደግሞ የባቡር ሀዲዱ እንዲያልፍባቸው የታቀዱት የአልፕስ ተራራዎች ሲቆፈሩ እንደ አስቤስቶስ እና ዩራኒየም ያሉ አደገኛ ንጥረ ነገሮች ሊወጡና የአካባቢውን ውሃና አየር ሊበክሉ ይችላሉ ፣ በግንባታው ምክንያት የሚፈናቀሉ ሰወችም አልተስማሙም፣ ለግንባታው የሚፈሰው በቢሊየን የሚቆጠር ዮሮ ለትምህርት፣ ለጤናና ለአገር ውስጥ መሠረተ ልማት ማሻሻያ ይዋል የሚል ነው። ይሄው መንግስትና ሕዝብ እንደተነታረከ 35 ዓመት አለፈው። No TAV (No Treno Alta Velocità) የሚባል የተቃውሞ መሀበር ሁሉ አላቸው።
ታዲያ የሆነ ጊዜ ለተቃውሞ ሕዝቡ ወጣ፣ ለመከላከልም ፖሊስ ቆመጡን ይዞ ተሰለፈ። ኒና ዴ ቺፍሬ የተባለች ወጣት ድንገት ያደረገችው ነገር ዓለምን ያጥለቀለቀ ዜና ሆነ። አንዱን ፖሊስ በሄልሜቱ ላይ አማላይ በሆነ ሁኔታ ስትስመው ካሜራ ያዛት። ዓለም 35 ዓመት ከተጮኸለት ተቃውሞ ይልቅ ይች መሳሳም መሰጠችው። (ሴሰኛ ዓለም)
የጣሊያን ፖሊስ ግን ጉዳዩን በቀላሉ አልተመለከተውም ። ይች ዱርየ ፖሊሴን ስማብኛለች አማላብኛለች ብሎ ፍርድ ቤት ገተራት! የጣሊያን የፖሊስ ማህበር (COISP) ሁለት ዋና ዋና ክሶችን ነበር ያቀረበው።
1. ፖሊሱ ሳይፈልግና ሳይፈቅድ በግዳጅ ስመዋለች የፆታ ትንኮሳ ነው ትቀፍደድልኝ አለ።
2. የመንግስት ባለስልጣንን መስደብ ወይም ማዋረድ ወይም ማቂያቃል ነው፤ ድርጊቱ ፖሊሱን ለማዋረድና ትንኮሳ ለማድረግ የታለመ ነው በሚል።
(ልማቱን ለማሰናከል የሚል ክሰሰ ጣሊያን የለም?)
ምንም እንኳን በወቅቱ አቃቤ ህግ ምርመራ ቢጀምርም ድርጊቱ ከፖለቲካዊ ተቃውሞ እና ከወቅቱ ግልፍተኝነት የመነጨ እንጂ "ወሲባዊ ጥቃት" የመፈጸም ፍላጎት የለውም በሚል ውሳኔ ተቋጭቷል። የፖሊስ መሃበሩ መሪ "እስካሁን አንድ ፖሊስ አንዲትን ሴት ቢስም ዓለም ይገለባበጥ ነበር" ሲሉ አማረሩ።
እዚህ ላይ "ልጅቱ የሳመቻችሁ በከንፈሯ ነው፤ የእናንተ ፖሊሶች ሴቶቻችንን በቆመጥ ሲስሟቸው ነው የኖሩት" የሚል ሀሳብ ፀሀፊው ውልብ አለበት።
(አንባቢ ሆይ በባቡር ሀዲዱ ግንባታ ከተፈናቀሉትና መርዛማ ኬሚካል መንደራቸውን ከበከለባቸው ሰወች ይልቅ ምናለ ፖሊሱ ሄልሜት ባይለብስ ኑሮ እያልክ እንደምታስብ ገብቶኛል። ምን ያለኸው ነህ?😁) | 4 091 |
| 20 | بدون متن... | 2 508 |
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
