cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Mostrar más
Advertising posts
34 383Suscriptores
-824 hours
+1407 days
+1 86730 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የኤርትራ ጦር ከዛላንበሳና አጎራባች ወረዳዎች ሰዎችን አግቶ እየወሰደ ነው ተባለ የዛላአንበሳ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ በርሄ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከምስራቃዊ ዞን  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ታግተዉ ተወስደዋል ብለዋል፡፡ ከዛላ አንበሳ 26 ሰዎች ፣ ከጉለም ወረዳ  50  እንዲሁም ከኢሮብ 28 ሰው በኤርትራ ሰራዊት እንደተወሰደ  ገልፀው በዚህ ሳምንት ደግሞ ቁጥሩ መጨመሩን መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከኢትዮ ኤፍኤም ዘገባ ተመልክቷል። አሁን ላይ ዛላንበሳ ከተማን ጨምሮ  ምስራቃዊው ዞን ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ማህብረሰቡም ብዙ በደል እና ጥቃት እየደረሰበት ነዉ ብለዋል፡፡ የኤርትራ ጦር የአካባቢዉን ነዋሪዎቹ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት  ኤርትራዊ እንደሆኑ በመግለጽ  በኃይል  እንደተቆጣጠረም ተነግሯል፡፡ የፌድራል መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠንም የሚሉት አቶ ብርሀነ ዳግም ጦርነት አንፈልግም ግን ደግሞ ማንነታችንን እና ህልውናችንን ሊያስከብርልን ይገባል ብወዋል። በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በጦሩ  ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ተነስቶ  በከተማው እንዲሁም በአካባቢው ያለው ነዋሪ ለከፋ ችግር እንደተጋለጠም ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ 30ሺ በላይ ነዋሪ ተፈናቅሎ በመቀሌ፤ በአዲግራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኝ  አቶ ብርሀነ ገልፀዋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
👍 10🤬 2
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ሲተዳደሩ የቆዩት የራያ አካባቢዎች ያለ አስተዳዳሪ ወደ ሁለተኛ ሳምንታቸው እየተሻገሩ ነው ከየካቲት ጀምሮ አልፎ አልፎ ሲከሰት የነበረው “በህወሓት ታጣቂዎች” እና “በአካባቢው ሚሊሺያዎች” መካከል ሲደረግ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከፍ ባለ ሁኔታ ተካሂዶ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወዲህ የነበረውን መዋቅር ቀይሮታል። ላለፉት ሦስት ዓመት ገደማ አካባቢዎቹን ሲመሩ የነበሩት ከአማራ ክልል በኩል የተሾሙ አስተዳዳሪዎች፤ ከሚመሯቸው የራያ ወረዳ እና ከተሞች ሸሽተው ቆቦ ከተማ እና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ውስጥ ተጠልለዋል። በቆቦ ከተማ የሚገኙት ከራያ አካባቢዎች የሸሹት የመንግሥት ሹመኞች ብቻ አይደሉም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በወጣው ሪፖርት 50 ሺህ ሰዎች ከራያ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች እንደተፈናቀሉ አስታውቋል። ከተፈናቃዎቹ ውስጥ 42 ሺህ ያህሉ የሚገኙት በሰሜን ወሎ ዞን ስር በምትገኘው ቆቦ ከተማ እንደሆነ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። ሌሎች የራያ አካባቢዎች ነዋሪዎች ግን አሁንም ባሉበት ኑሯቸውን ቀጥለዋል። የአማራ እና ትግራይ ክልሎች የየራሳቸው አስተዳዳሪዎች የተሾሙላቸው የአላማጣ እና የኮረም ከተሞች ያለምንም አስተዳዳሪ ከቀሩ ሁለት ሳምንታት ተቃርበዋል። ከሁለቱም ክልሎች የተሾሙ አመራሮች የሚገኙት በየክልላቸው ውስጥ በሚገኙ አጎራቦች አካባቢዎች ውስጥ ነው። በአላማጣ እና ኮረም ከተማዎች ውስጥ የፌደራል እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንደሚገኙ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሁለቱ ከተማዎች አምስት ነዋሪዎች ተናግረዋል። በከተሞቹ ውስጥ የሚገኙት የፌደራል መንግሥት እንዲሁም የአካባቢ አስተዳደሮችን ተቋማት እና ቢሮዎች እየጠበቁ ያሉት በሁለቱ የፀጥታ አካላት መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት ከተማዋ ውስጥ አንጻራዊ ሰላም እንዳለ ጠቅሰዋል። ባንኮች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ቢሮዎች እንዲሁም የተወሰኑ መደብሮች መከፈታቸውን ሦስት ነዋሪዎች ተናግረዋል። በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች ያልተከፈቱት አካባቢዎቹን ላይ አስተዳዳሪ አለመኖሩ በፈጠረባቸው ስጋት ምክንያት መሆኑን የሚናገሩ አንድ የአላማጣ ነዋሪ፤ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙት የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት እየተንቀሳቀሱ ያሉት በዋና የአስፓልት መንገዶች ላይ እንደሆነ አስረድተዋል። ከትግራይ ክልል በኩል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ዝናቡ ደስታም በተመሳሳይ በከተማዋ ሁለቱ የፌደራል መንግሥት ኃይሎች ቢኖሩም የፀጥታ ሁኔታው በበቂ ሁኔታ እየተሸፈነ አለመሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአማራ ክልል በኩል የተሾሙት የአላማጣ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋ ውስጥ መኖራቸውን አንስተው በአሁኑ ሰዓት ስላለው ሁኔታ ግን “ዝርዝር መረጃ” እንደሌላቸው ጠቅሰዋል። ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ የመንግሥት ኃላፊዎች ከአላማጣ መውጣታቸውን ተከትሎ በመንግሥት ተቋማት ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶች እስካሁን ድረስ እንደቆሙ መሆኑን ሦስት ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማዋ አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነም ጠቅሰዋል። አንድ የከተማዋ ነዋሪ*፤ “[የጤና አገልግሎት] የለም ማለት ይቻላል። አሁን በቅርብ አንዲት ወላድ ነበረች፤ ደም [ያስፈልጋል] ተብላ ወደ ወልዲያ ሄዳለች። ምንም ዓይነት አገልግሎት የለም። በጣም ተቸግራ እዚህ ያሉ ዶክተሮች በግል ተባበሯት፤ …ወደ ቆቦ በትራንስፖርት ሄዳ፣ ከቆቦ ወደ ወልዲያ ወሰዷት” ሲል በከተማዋ ላለው ሁኔታ ማሳያ ጠቅሷል። በኮረም ከተማም በተመሳሳይ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ መሥሪያ ቤቶች ዝግ መሆናቸውን ሦስት የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቀድሞ አስተዳዳሪዎች ለቀው በወጡባት ኮረም ከተማም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ተቋማት እየተጠበቁ ያሉት በፌደራል ፖሊስ እና በመከላከያ ሠራዊት አባላት መሆኑን ተናግረዋል። ይሁንና ከአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ሦስት ነዋሪዎች ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ታጣቂዎቹ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ “ዝርፊያ ፈጽመዋል” ሲሉ ከሰዋል። ታጣቂዎቹ የሰፈሩት በከማው ውስጥ በሚገኙት ስድስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ መሆናቸውን የሚናገሩ አንድ ነዋሪ፤ “የትምህር ቤት መጽሐፍት ‘የአማራ ክልል ናቸው’ በሚል ተቀድደዋል” ሲሉ በትግራይ ታጣቂዎች ተፈጽሟል ያሉትን ድርጊት ጠቅሰዋል። ሌላ ነዋሪ በበኩላቸው፤ በከተማዋ ውስጥ በታጣቃዎቹ በሚፈጸሙት ድርጊቶች ሳቢያ ነዋሪዎች አሁንም ወደ ቆቦ ከተማ እየሸሹ መሆኑን ተናግረዋል። በቆቦ ከተማ የሚገኙት በአማራ ክልል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉም የኮረም ከተማ ነዋሪዎች አሁንም ወደ ቆቦ ከተማ እየገቡ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በትግራይ ክልል በኩል የራያ አካባቢ ወረዳ እና ከተማዎችን በስሩ የያዘው የደቡባዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀፍቱ ኪሮስ፤ በኮረም ከተማ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ገብተዋል ስለመባሉ እና ታጣቂዎቹ ፈጽመዋቸዋል ስለተባሉ ድርጊቶች ከቢቢሲ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በኮረም “በጣም የተረጋጋ ሰላም እና ደኅንነት” መፈጠሩን የሚናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፤ “ኮረም እና አላማጣም ላይ በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ኃይሎች የፀጥታ እና ሰላሙን የመጠበቅ ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ እየፈጸሙ ነው” ብለዋል። አቶ ሀፍቱ፤ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ስለመግባታቸው እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለ መስረፈራቸው ማረጋገጫ ከመስጠትም ሆነ ከማስተባበል ተቆጥበዋል። እንደ ራያ ባሉ አካባቢዎች ላይ ከዚህ ቀደም በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳደር መካከል የነበረው “ከመከላከያ ሠራዊት ውጪ ሌላ ታጣቂ ኃይል አይኑር” የሚለው “ንግግር” በአሁኑ ሰዓት “መቀየሩን” ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል። የፕሪቶሪያ ስምምነትን የተፈራረሙት የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት ከስምምነቱ በታች ያሉ ጉዳዮችን በፖለቲካዊ ንግግር እየፈቱ እና “እያሻሻሉ” እየሄዱ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሀፍቱ፤ “ለምሳሌ አሁን ማሻሻያዎች አሉ። በዚያ አካባቢ ከመከላከያ ሠራዊት እና ከፌደራል ፖሊስ ውጪ ማንኛውም ታጣቂ መኖር የለበትም የሚል የውይይት ሀሳብ እንደነበር ይታወቃል። አሁን እሱ ተቀይሯል። ሌላ እድገት አለው” ብለዋል። ዋና አስተዳዳሪው “ተቀይሯል” ያሉት የታጣቂዎች ጉዳይ የሚወያዩት አካላት ይፋ እንደሚያደርጉት በመጥቀስ ዝርዝሩን ከመናገር ተቆጥባዋል። ሁለቱ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ባለፉት ሳምንታት የተፈጠረውን ሁኔታ የአፍሪካ ኅብረት እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ አገራት ተወካዮች እንዳሰሰባቸው እና ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። የአማራ እና የትግራይ ክልሎች በይገባኛል በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ላይ የህወሓት ታጣቂዎች ወረራ ፈጽመዋል ብሎ ባለፈው ሳምንት የአማራ ክልል መንግሥት መክሰሱ ይታወሳል። ለወሰን እና ለማንነት ጉዳዮች መፍትሄ ለመስጠት እየሠራ መሆኑን የገለጸው የፌደራል መንግሥቱ የህወሓት ኃይሎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ሲል ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። Via ቢቢሲ #ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
👍 13🕊 4😢 1
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተነገረ ከሶስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩንቨርሲቲው አስተዳድር አመራር አባል ለአል ዐይን አማርኛ እንዳሉት "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በስራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ብለዋል። "ፕሬዝዳንቱ ንጉስ ታደሰ ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ የት እንደሄዱ እና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ሲሉም እኝህ አመራር ነግረውኛል ሲል አል አይን መዘገቡን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ሀይሎች መታገታቸውን ሰምተናል ሲሉም አክለዋል። የሰማን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚንስቴር እና የደብረብረሀን ከተማ ፖሊስ ስለ ደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። እንዲሁም የፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም። #ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
😁 11🤔 9👍 3 2😢 2🙏 1
በካፋ ዞን አንድት ሴት ህፃን ጫካ ውሰጥ ተጥላ ተገኘች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ  ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት በ01 ቀበሌ ልዩ ስፍራው እግዚአብሔር አብ ተብሎ በሚጠራበት ጫካ ዉስጥ ተጥላ መገኘቷን ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስም ህፃኗን በማንሳት ወደህክምና ተቋም በመውሰድ አስፈላጊውን የህክምና እርዳታ እንድታገኝ የተደረገ ሲሆን ህፃኗ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ የደብቡ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ከአከባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን የህፃኗን ቤተሰብ በአከባቢው ባህል መሰረት ኦቶ ወይም በአፈርሳታ እያፈላለገ ሲሆን ህፃኗን ከሺሾ እንዴ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በጊዜያዊነት ለአንድ ግለሰብ እንድታሳድጋት መሰጠቷን ተገልጿል። #ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
የካሊፎርኒያ ኮሌጅ በጋዛ ያለውን ጦርነት በመቃወም የተነሳውን ውጥረት ተከትሎ ተጠባቂውን የተማሪዎች የምረቃ ስነስርአት ሰረዘ በሎስ አንጀለስ የሚገኘው የደቡባዊ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ያለውን የደህንነት ስጋት በመጥቀስ ዋናውን እና በግንቦት 10 እንዲካሄድ ቀጠሮ የተያዘለትን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ሰርዟል። ይህ እርምጃ የተወሰደው በእስራኤል እና በጋዛ ጦርነት ምክንያት በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ካምፓሶች ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት ወቅት ነው። በአትላንታ ኤሞሪ ዩኒቨርሲቲ 28 ተቃዋሚዎች ግቢውን ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሐሙስ ዕለት ተይዘዋል ። በኒውዮርክ ከተማ፣ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በግቢው ውስጥ ያለውን ተቃውሞ ለማስቆም ቀነ ገደብ ተጥሏል።ተማሪዎች ግን ድንኳን ሰርተው ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል። በመግለጫው የደቡባዊ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ እንዳስታወቀው 65,000 ተማሪዎች፣ ቤተሰብ እና ጓደኞቻቸው የሚታደሙበት የምረቃ ሥነ ሥርዓት ግቢው ማስተናገድ እንደማይችል ይፋ አድርጓል። እሮብ እለት፣ ፖሊስ ግቢውን ጥሶ በመግባት ከ93 ያላነሱ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ እንደነበር ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ተቃውሞ የፍልስጤም ኬፊህ ወይም ሻርፕ እና በፍልስጤም ባንዲራ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የጆርጅ ዋሽንግተን ሀውልት ለብሶ ታይቷል። በሌላ በኩል በጋዛ በቀጠለው ውጊያ ዙሪያ አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን ወታደሮቹ በታቀደው የምድር ጦር ዘመችም መሰረት “ወደ ፊት እየገሰገሱ ነው” ነው ብለዋል። የራፋህ ምስራቃዊ ክፍል በየጊዜው በመድፍ እየተደበደበ ይገኛል። ከደቡብ ሊባኖስ በተነሳው የሂዝቦላ የሚሳኤል ጥቃት አንድ እስራኤላዊ የጭነት መኪና ሹፌር መገደሉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። የእስራኤል ሚዲያዎች አካባቢው በተመታበት ጊዜ ሰውዬው ወደ እስራኤል ሰሜናዊ ድንበር አቅራቢያ ለወታደሮች የመሠረተ ልማት ስታዎችን ሲያከናውን ነበር ብለዋል ። በሊባኖስ እና በእስራኤል ድንበር ላይ በሄዝቦላህ እና በእስራኤል ጦር መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በኢራን የሚደገፈው ቡድን ከጋዛውያን ጎን መቆሙን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
👍 40 11👏 4👎 1
"እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው።" መዝሙር 68፤35 ገዳመ ወንያት መንታዎቹ ደብር አቡነ ሐራ ድንግል ገዳም ወር በገባ በ11ኛው ቀን ጻድቁ አቡነ ሐራ መታሰቢያ በዓላቸው ነው።ገዳሙ የተአምራት የበረከት የፈውስ ቦታ ነው።ከጻድቁ መቃብር ተዝቆ በማያልቅ ሞልቶ በማይፈስ አፈር እጹብ ድንቅ ተአምራት ይደረጋል። በጻድቁ መካነ መቃብር ላይ የሚገኘውን ቤተክርስቲያን ያሰሩት አፄ ዮሐንስ፬ኛ በጽኑ ነቀርሳ በሳይንሳዊ አጠራር ካንሰር በሽታ ተይዘው የእግዚአብሔር ቸርነት የጻድቁን አማላጅነት ተስፋ አድርገው ከመቀሌ ድረስ ገስግሰው መጥተው በጻድቁ ጸበል ድንቅ ስለተደረገላቸው ፈውስን ስላገኙ የክብር አልጋና ዘውዳቸውን ሰጥተዋል ቤተክርስቲያኑንም አሰርተዋል። ጻድቁ ዛሬም ውሉደ ጥምቀትን ሁሉ ከክፉ ደዌ በጸበላቸው ይፈውሳሉ።ከባሕር ዳር ወደ ጎንደር መንገድ ስንወጣ ዘንዘልማ የምትባል አነስተኛ ከተማ አለች ከዘንዘልማ በስተቀኝ ታጥፎ በ12ኪሎሜትር ላይ ይገኛል።ብዙዎች በጻድቁ አማላጅነት ከደዌ ስጋ ድነዋል መካኖች ወልደዋል እውሮች በርተዋል ለምጻሞችም ነጽተዋል። የጻድቁ በረከት ይደርብን በቃልኪዳናቸው ይጠብቁን ከእለት እኪት ከቀሳፊ ነገር ይሰውሩን ከፍቅር ረሐብ ከዘረኝነት ደዌ ከዝሙት እሳት ከምንፍቅና አሽክላ ይታደጉን።የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም በዓላውያን መንግስታት ዘመን በደረሰበት መከራና ፈተና የተነሣ ተዳክሞ በመቆየቱ የገዳሙ የይዞታ ቦታ በመሉ በአካባቢው አርሶ አደር እና በሌሎች ጥቃቅን ነጋዴዎች እጅ ከገባ አያሌ ዘመናትን ያስቆጠረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድነት ገዳሙ ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን ተከትሎ በርካታ አባቶች መነኮሳትና እናቶች መነኮሳይያት ወደ ገዳሙ በመግባት በመልሶ ማቋቋም ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ቢሆንም የገዳሙ ይዞታ ለረጅም ዘመናት በሌሎች ግለሰቦች እጅ ተይዞ በመቆየቱ ምክንያት እንኳንስ ለገዳሙ ልማት ይቅርና ለመነኮሳቱ መጠለያ ቤት መሥሪያ ቦታ በመጥፋቱ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል፡፡ ይህን መሬት ለማስመለስ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ተጠይቋል።ለዚህም ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ታላቅ የገቢ ማሰባሰብያ መርሀ ግብር በካፒታል ሆቴል ለማካሄድ ቀን ተቆርጧል በሐገር ቤትም በውጭም ያላችሁ የፃድቁ ወዳጆችና ህዝበ ክርስቲያን እንድትረባረቡ ገዳሙ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጠይቋችኃል #ዳጉ _ጆርናል
Mostrar todo...
👍 35 12👎 7🔥 1
👍 1🔥 1