cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ko'proq ko'rsatish
Advertising posts
34 379Obunachilar
+1024 soatlar
+2967 kunlar
+1 90730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Обуначиларнинг ўсиш даражаси

Ma'lumot yuklanmoqda...

ኬቨን ደ ብረይነ በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያውን የግምባር ኳስ በመግጨት አስቆጥሯል 😲 ሁሉንም ማሳካት ተችሎታል... ብራይተን 0-3 ማን ሲቲ ጎሎቹን ለመመልከት 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 7🔥 6😁 1
👍 2🥰 1
የቡርኪናፋሶ ጦር በ223 ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰዱን የሰብዓዊ መብት ድርጅት አስታወቀ በተያዘው አመት ከ220 በላይ ንፁሀን ዜጎች፣ ቢያንስ 56 ህፃናት በቡርኪናፋሶ ጦር በአንድ ቀን ተጨፍጭፈዋል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። በሰራዊቱ ላይ የተፈፀመው ጥቃት ለመበቀል ጦረ በሶሮ መንደር 179 ሰዎች ሲገድል 44 ሌሎች  ሰዎች ደግሞ በአቅራቢያው በሚገኘው ኖንዲን መንደር ውስጥ መገደላቸውን የመብት ተሟጋች ቡድሙ ያደረገው ምርመራ አረጋግጧል።የጅምላ ግድያው "በሀገሪቱ ከአስር አመታት ወዲህ ከተከሰቱት እጅግ የከፋ የጦር ሰራዊት ጥቃት" ሲል ገልጿል። የቡርኪናፋሶ ባለስልጣናት በሪፖርቱ ላይ አስተያየት እስካሁን አልሰጡም። ባለፈው ወር የህዝብ አቃቤ ህግ አሊ ቤንጃሚን ኩሊባሊ ከጅምላ ግድያው ጀርባ ያለውን ቡድን ለመለየት ምስክሮች እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በወቅቱ የሟቾችን ቁጥር 170 አድርሶታል። ከጥቃቱ የተረፉ መንደርተኞች ለሂውማን ራይትስ ዎች እንደተናገሩት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንዳለፉ  ከ30 ደቂቃ በኋላ ወታደራዊ ኃይሉ ወደ ኖንዲን መንደር መውረዱን ተናግረዋል። ወታደሮቹ ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ነዋሪዎችን ከቤታቸው እያባረሩ ወንጀሉን ፈፅመዋል ሲሉ ተደምጠዋል። በመቀጠል 5 ኪሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሶሮ መንደር ደርሰው ከአንድ ሰአት በኋላ በመንደሩ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ከጥቃቱ  የተረፉት እማኞች ገልጸዋል። በሁለቱም መንደሮች ወታደሮቹ ለመደበቅ ወይም ለማምለጥ በሞከሩ ሰዎች ላይ መተኮሳቸውን እማኞቹ አክለዋል። የጅምላ ግድያው በወታደሮች የተወሰደው በታጣቂ ቡድን ለተፈፀመባቸው ጥቃት የበቀል እርምጃ ነው ተብሎ ታምኖበታል። የመንደሩ ነዋሪዎች የታጠቁ ተዋጊዎችን ይረዱ ነበር በሚል ተከሰዋል። በሰሜናዊ ያትንጋ ግዛት አቅራቢያ በሚገኝ የጦር ካምፕ ላይ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃት ሰንዝረዋል።የሂዩማን ራይትስ ዎች ዋና ዳይሬክተር ቲራና ሃሰን እንዳሉት በኖንዲን እና በሶሮ መንደር የተፈፀመው እልቂት የቡርኪናፋሶ ወታደሮች በፀረ-ሽምቅ ዘመቻቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈፀሙት የቅርብ ጊዜ የጅምላ ግድያ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👎 12👍 10 2😢 2🤩 1
አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግስት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን በሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ታዬ ደንደአ ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቧል። በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ እና አንቀጽ 257/ሰ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና የጦር መሳሪያ አዋጅን መተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል። በክሱ ላይ እንደተመላከተው÷ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን  ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ነው፡፡ እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ አዋጁን በመተላለፍ በታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም  ከረፋዱ 5 ሰዓት  ላይ በልደታ ክ/ከ ወረዳ 6  በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽን ኮቭ  መሳሪያ ከ2 ክላሽ ካዝና  እና ከ60 ጥይት ጋር ይዘው መገኘታቸው ተጠቅሶ ክስ ቀርቦባቸዋል። ተከሳሽ አቶ ታዬ ደንደአ በአራት ጠበቆቻቸው ተወክለው ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ ተነቦላቸዋል። ክሱ ከተነበበ በኋላ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ ቀርቧል። ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የዋስትና ጥያቄያቸውን ሊያስከለክሉ የሚችሉ ነጥቦችን ጠቅሶ ተከራክሯል። ሰበር ሰሚ ችሎት ዋስትናን በልዩ ሁኔታ ሊከለክል የሚችልባቸው ነጥቦች ማለትም በተደራራቢ ክስ መከሰሳቸውን እና የተከሰሱት ድንጋጌ ከፍ ያለ ቅጣት የሚያስጥል ከሆነ ዋስትና ሊያስከለክል ይችላል በማለት ተከራክሯል። የተከሳሽ ጠበቆችም ሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀመጣቸው ዋስትናን ሊያስከለክሉ የሚችሉ ድንጋጌዎች ተከሳሹ ላይ በቀረበው ክስ የሚመለከቱ አለመሆናቸው ጠቅሰው መልስ ሰጥተዋል። በተጨማሪም  ህጻን ልጃቸውን ጥለው የታሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ በሕገ-መንግስቱ የተቀመጠው የሕጻናት መብት ታሳቢ ተደርጎ በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል። አቶ ታዬ ደንደአ በበኩላቸው÷በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል። ዐቃቤ ሕግ ሌሎች ምርመራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጾ መልስ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱም  በአያያዝ ላይ ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በሚመለከት በጽሑፍ በዝርዝር ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል። ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። Via FBC #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👎 37👍 13
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተዘገበ ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል። ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል። በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።  እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም። Via Addis Maleda #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 30👎 10🤔 7🤬 6😢 2😁 1
ጀርመን በፍቅር ስም ሲያጭበረብር የነበረ የናይጄሪያ የማፍያ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች የጀርመን ፖሊስ በማፍያ ቡድን ውስጥ ከፍተኛ  በፍቅር ስም የማጭበርበር ድርጊቶችን ያቀነባበሩ 11 ናይጄሪያውያንን በቁጥጥር ስር አውሏል። ይህው የብላክ አክስ የተሰኘው ቡድን በአለም አቀፍ ደረጃ "በርካታ የወንጀል ድርጊቶች" ውስጥ ይሳተፋል ሲል የባቫርያ ፖሊስ ባወጠው መግለጫ ገልጿል። በጀርመን ውስጥ ድርጅቱ የሚያተኩረው በፍቅር ቀጠሮ ማጭበርበር እና በገንዘብ ማጭበርበር ላይ ነው ሲል ሃይሉ አክሏል። መግለጫው “የውሸት መታወቂያዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎቹ ለምሳሌረ ለማግባት ፍላጎት እንዳላቸው በማሳየት ለተጨማሪ ግንኙነት በተደጋጋሚ በተለያዩ ሰበቦች ገንዘብ ይጠይቃሉ” ብሏል።በአለም አቀፍ ደረጃ የወሮበሎች ቡድን ዋና ዋና የስራ ቦታዎች "የሰዎች ህገወጥ ዝውውር፣ ማጭበርበር፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ የወሲብ ንግድ እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር" ናቸው። በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ሁሉም የናይጄሪያ ዜግነት ያላቸው እና ከ29 እስከ 53 ዓመት እድሜ ያላቸው እንደሆኑ ተመላክቷል። ከሁለት አመት በላይ የፈጀውን የፖሊስ ምርመራ ተከትሎ በተያዘው ሳምንት ማክሰኞ በባቫሪያ ክልል በተደረገው የፖሊስ ዘመቻ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል ። እ.ኤ.አ. በ 2021 በብላክ አክስ ላይ በተደረገው ምርመራ ቡድኑ ናይጄሪያ ውስጥ ፖለቲካ ውስጥ ዘልቆ በመግባት የግድያ ዘመሻ እንደፈጸመ የሚያሳይ ማስረጃ መገኘቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበው የነበረ ቢሆን የተወሰደበት እርምጃ ግን የለም። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 16 1👏 1😁 1
ከወላይታ ሶዶ - አዲስ አበባ የኤሌትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ታወር ብረትን የሰረቀዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን  በሁልባራግ ወረዳ በዋጮ ሆቢሶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰላም መሊቅ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከወላይታ ሶዶ - አዲስአበባ የኤሌትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ታወር ብረትን የሰረቀዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታዉቋል። ነሰሩ ወርቀ - ነጋ የተባለው ግለሰብ  ዋሚያዚያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ሆን ብሎ በህገወጥ መንገድ በአቋራጭ  ለመበልፀግ በማሰብ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሆነ  ከወላይታ ሶዶ -ገለን ወደ አዲሰ አበባ የተዘረጋውን ዋና የኤሌክትሪክ ኃይል 400 ኪሎ ዋት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታወር ሰርቆ እጅ ከፍንጅ መያዙን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኙነትና ሚድያ ጉዳዮች ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ከድር  ኤርጎሻ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።                  ግለሰቡ ግምቱ እስከ 100 ሺህ ብር ሊያወጣ የሚችል የኤሌክትሪክ ሽቦ መሸከሚያ  ታወር ብረት ሰርቆ ለመውሰድ እያዘጋጀ እያለ  በአካባቢው ህብረተሰብ እጅ ከፍንጅ ተይዞ  ለሁልባራግ ወረዳ ፖሊስ ተላልፎ የተሰጠ ሲሆን ፖሊስም ተከሳሹንና የተሰረቀውን ንብረት በኢግዝቢትነት በመያዝ ቃል ከመቀበል ጀምሮ  አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን  ማስረጃዎች በማሰባሰብና ምርመራ  በማጣራት  መዝገብ  አደራጅቶ ለሁልባራግ ወረዳ  ዐቃቤ ህግ  አቅርቧል። ዐ/ህግም ተከሳሹ  በ1996  ዓ/ም  የወጣውን የኢፌዲሪ  የወንጀል  ህግ አንቀጽ  669(1)(ለ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ በፈጸመው  የስርቆት ወንጀል ክስ መስርቶ ለሁልባራግ ወረዳ ፍ/ቤት አቅርቧል። ፍ/ቤቱም ከዐ/ህግ የቀረበለትን  ይህንን የስርቆት ወንጀል  ክስ ከተገቢ ማስረጃዎች ጋር አገናዝቦ ከመዘነ በኋላ  በተከሳሹ ላይ  የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል። በዚህም መሠረት የሁልባራግ  ወረዳ  ፍ/ቤት  ሚያዚያ 16 ቀን 2016  ዓ/ም  ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹን ነስሩ ወርቀነጋ ላይ የ5 አምስት ዓመት ከ6 ወር ጽኑ  ወስኖበታል ሲሉ የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኙነትና ሚድያ ጉዳዮች ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ከድር  ኤርጎሻ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
👍 17😁 6👎 1👏 1