fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ

رفتن به کانال در Telegram

Every one comment us about the informations that we are uploading. you are also very wellcommed to give us nominations which helps us to improve our capability with regard to the concerns of the organization.

نمایش بیشتر
1 588
مشترکین
+224 ساعت
+127 روز
+1530 روز

در حال بارگذاری داده‌ها

ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
نوامبر '26
نوامبر '26
+15
در 0 کانال‌ها
اکتبر '26
+40
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '26
+52
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '26
+70
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '26
+47
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '26
+51
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '26
+38
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '26
+33
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '26
+37
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '26
+30
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '26
+37
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '25
+42
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '25
+64
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '25
+52
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '25
+44
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '25
+47
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '25
+47
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '25
+37
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '25
+31
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '25
+50
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '25
+52
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '25
+51
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '25
+79
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '24
+134
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '24
+98
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '24
+95
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '24
+74
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '24
+111
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '24
+32
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '24
+32
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '24
+51
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '24
+177
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '24
+555
در 0 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
07 نوامبر0
06 نوامبر+2
05 نوامبر+4
04 نوامبر+4
03 نوامبر+1
02 نوامبر+4
01 نوامبر0
پست‌های کانال
#የከተማችን ሌላኛው ድምቀት አደይ አበባ የመሰለችው ሀያ ሁለት
+4
#የከተማችን ሌላኛው ድምቀት አደይ አበባ የመሰለችው ሀያ ሁለት

2
بدون متن...
222
3
ከችግር ተናጋሪነት ወደ መፍትሔ አመንጪነት፤ አፍሪካ በኮፕ 32 አፍሪካ ባለፉት ዓመታት በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርድር መድረኮች ላይ ስትታወቅበት የቆየው ትልቁ ገጽታ "የችግር ተናጋሪነት" አድርጎ የማቅረብ ትርክት ነበር። ይህ በሌሎች መንግሥታት ርህራሄ ላይ የተንጠለጠለ አካሄድ፤ አፍሪካ የራሷን ዕጣ ፈንታ በባለቤትነት እንዳትመራ የጫነባት ሥነ-ልቦናዊና ፖለቲካዊ ጫና ቀላል አልነበረም። ይህንን የተሳሳተና አፍሪካን እንደጠባቂ አድርጎ የሚያቀርበውን አመለካከት በመቀየር አፍሪካ ችግሮችን በራሷ መፍትሔ አቅራቢና የአረንጓዴ ዕድገት አቅጣጫ ጠቋሚ መሆኗን ለማሳየት መጪው የኮፕ 32 ጉባኤ ሚናው ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይጠበቃል። በመድረኩ አፍሪካ ለዓለም የምታበስረው ትልቁ መልዕክት በችግር ውስጥ ሆነው ፈጠራን እና ተጨባጭ ተግባርን ማስቀደም እንደሚቻል በተጨባጭ የሚያሳይ ነው። ለዚህ አህጉራዊ መፍትሔ ደግሞ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ለተከሰተው የአየር ንብረት ቀውስ በተግባር የፈነጠቀችው ተስፋና ያሳየችው አርዓያነት ትልቁ ምሰሶ ነው። ሀገራችን ባለፉት ዓመታት ያከናወነችው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል፣ የተራቆቱ መሬቶችን በመሸፈን እና ብዝሃ-ሕይወትን በማነቃቃት ረገድ ዓለም አቀፍ አድናቆትን ያተረፈ ከመሆኑም በላይ በቁጥርና በጥራትም አህጉራዊ ስኬትን አጎናጽፏታል። ይህ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ተግባር አፍሪካ ለአካባቢ ጥበቃ የሰጠችውን ትኩረት የሚያንፀባርቅ ነው። ከዚህ በላይ ኢትዮጵያ የምትከተለው የኃይል አጠቃቀም ፖሊሲ ለአረንጓዴ ሽግግር ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው። በተለይም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለቀጣናዊ እና ለዓለም አቀፍ የንጹህ ኃይል አቅርቦት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል የላቀ ፋይዳ ያለው መፍትሔ ነው። አፍሪካ ከችግር ተናጋሪነት ተላቃ ወደ መፍትሔ አምጪነት የምትሸጋገረው በእነዚህ የዕድገት ማሳያዎች ልክ ድምጿን ከፍ አድርጋ ስታሰማ ነው። ለዚህ ታላቅ የትርክት ለውጥ እና አህጉራዊ ድምጽ ማጠናከሪያ ደግሞ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የኮፕ32 ጉባኤ ወሳኝ ምዕራፍ ይሆናል። አፍሪካ የራሷን የዕድገት ጎዳና በባለቤትነት በመምራት የነገዋ ዓለም የተስፋ ብርሃን መሆኗን በዚሁ ታላቅ መድረክ ታረጋግጣለች።
242
4
بدون متن...
292
5
የአረንጓዴ ልማቱ ያስመዘገበው ስኬት ከተማችን ለአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የባለብዙ ወገን ስብሰባዎችና ጉባኤዎች ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን ትልቅ ምክንያት ሆኗል። የሰው ልጅ በተፈጥሮው መልካም እና ለምለም ነገሮችን የመውደድ መስተጋብር አለው። አረንጓዴ ልምላሜ ውስጣዊ እርካታን ከመስጠት ባለፈ ተስፋን ያለመልማል፤ የደከመ አእምሮንም ያድሳል። በዕለት ተዕለት የኑሮ ውጥረትና ስራ የዛለ አእምሯችን፣ በጥበብ ወደ ለሙ የአረንጓዴ ስፍራዎች አምርቶ ሲዝናና ሙሉ እፎይታን ያገኛል፤ አዲስ ጉልበትና ተነሳሽነት ሰንቆም ለቀጣይ ተግባር ዝግጁ ይሆናል። ለዚህም ነው የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ግንባታ ለአንድ ከተማ ነዋሪዎች የአእምሮና የአካል ጤና ወሳኝ ሚና የሚጫወተው። ይህ በጥበብ የታገዘ የአረንጓዴ መሰረተ ልማት እና የተፈጥሮ መልከዓ-ምድር ውበት የመዲናችንን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የቱሪዝም እና የዲፕሎማሲ ስበት ማዕከል እየሆነ መጥቷል። ከውጭ ሀገራትም ሆነ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ መዲናችን የሚመጡ እንግዶች እነዚህን የለሙ ስፍራዎች ሲጎበኙ ልዩ የደስታ ስሜት እንደሚሰማቸው በተለያዩ ጊዜያት ከሚሰጡት ምስክርነቶች መገንዘብ ይቻላል። ከተማችንን የሚያስውቡት እነዚህ ፓርኮችና አረንጓዴ ስፍራዎች አሁን ላይ የአዲስ አበባ ዋነኛ የክብር አምባሳደር ሆነዋል። የአረንጓዴ ልማቱ ያስመዘገበው ስኬት ከተማችን የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የባለብዙ ወገን ስብሰባዎችና ጉባኤዎች ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን ትልቅ ምክንያት ሆኗል። መሰል ትልልቅ ጉባኤዎች በመዲናችን በተደጋጋሚ መካሄዳቸው ደግሞ የሀገራችንን የቱሪዝም እና የሆቴል ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ ያነቃቃል። ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን መልካም ገጽታ በመገንባት ረገድ እና ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ይበልጥ እንዲያድግ እያደረገ ይገኛል። ስለሆነም ለሀገራችን ሁለንተናዊ ለውጥና ሽግግር እንደ ዜጋ እና እንደ መዲናዋ ነዋሪ የእኛ ድርሻ የማይናቅ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል። የተጀመሩ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና ይበልጥ እንዲስፋፉ በንቃት በመረባረብ መንግስት የያዘውን "አረንጓዴና ስማርት ከተማን" የመፍጠር ታላቅ ግብ ሁላችንም ደጀን ሆነን በጋራ ልናሳካው ይገባል።
270
6
بدون متن...
247
7
+1
بدون متن...
374
8
በመዲናችን የተገነቡ ዘመናዊ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች ለከተማችን ውበት፣ ለጤናችንና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያላቸዉ ሚና የጎላ ነው። በአንድ አገር ወይም ከተማ ውስጥ የሚታይ የስልጣኔ ደረጃ የሚለካው በህንፃዎች መርዘም ወይም በመንገዶች መዘርጋት ብቻ ሳይሆን፣ የማኅበረሰቡን የግልና የአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ባህል በማሳደግ ጭምር ነው። መዲናችን አዲስ አበባን ሳቢ፣ ንፁህ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹና በጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ ለማድረግ ሰፊ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡት ዘመናዊ የንፅህና መጠበቂያ (የሕዝብ መጸዳጃ) ቤቶች ለአካባቢ ጤና፣ ለከተማ ውበትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያላቸው ሚና የጎላ ነው። እነዚህ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች የተገነቡበት ዋና ዓላማ ማኅበረሰቡ በሰለጠነ መንገድ ንፅህናውን እንዲጠብቅ ለማስቻል፣ ያለ ቦታ መፀዳዳት የሚያስከትላቸውን ተላላፊ በሽታዎች ለመከላከልና የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ነው። ከተማችንን ዘመናዊና ንፁህ ማድረግ ንፅህናን የዕለት ተዕለት ባህላችን ከማድረጉም ባሻገር፣ እነዚህን የንጽህና ቤቶች የሚያስተዳድሩ በርካታ ወጣቶችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ በማድረግ የኢኮኖሚ ምንጭ እየሆነ ይገኛል። በዚህም ነዋሪው ንፁህ አገልግሎት እያገኘ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለዜጎች የገቢ ማግኛ መሆን ተችሏል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን በተወሰኑ አካባቢዎች ያለ ቦታ የመፀዳዳትና የአካባቢን ንፅህና የማጓደል ሁኔታዎች አልፎ አልፎ ይታያሉ። ይህንን ጎጂ ልማድ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል የመጸዳጃ ቤቶቹን በአግባቡ በመጠቀምና በመንከባከብ የአካባቢ ጥበቃ ድርሻውን መወጣት ይኖርበታል። ለከተማችን ንፅህናና ውበት ከእኛ በላይ ባለቤትና ተቆርቋሪ የለምና፣ የተሰሩ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን በባለቤትነት ስሜት በመጠቀም አዲስ አበባን የሥልጣኔና የንፅህና ተምሳሌት እናድርጋት።
375
9
+1
بدون متن...
359
10
ዓለም አቀፍ ዕውቅናን የተጎናጸፈው የአዲስ አበባ አረንጓዴ ትንሳኤ የዛሬይቱ አዲስ አበባ ከጥቂት ዓመታት በፊት ወንዞቿ የከተማዋን የትላንት ድብቅ ገመናዋን መሸፈኛ ነበሩ፣ የከተማዋ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣ ፍሳሽ እና መጸዳጃ ማስወገጃ፣ ለበርካታ ተላላፊ በሽታዎች እና ለህዝብ ጤና መጓደል መንስኤ ሆነው ኖረዋል። ዛሬ ላይ ግን ያ ታሪክ ላይመለስ ተቀይሮ ሕይወት ዘርተዋል፣ የታመሙ ወንዞቿ ታክመው ከበሽታ ምንጭነት ወደ ጤና ማዕከልነት፣ ከቆሻሻ ማከማቻነት ወደ ውበት ሰገነትነት፣ ለመጠጋት ከሚፈራበት ወደ ማረፊያ፣ ጊዜ ማሳለፍያ እና መዝናኛነት ተቀይረዋል፡፡ በቅርቡ የተመረቁት ከቀጨኔ፣ በአምባሳደር፣ ጊዮን፣ ኢሬቻ እስከ ባምቢስ የሚዘልቀው እንዲሁም፤ ከእንጦጦ፣ አንድነት እና ወዳጅነት አደባባይ ፓርኮች አንስቶ እስከ ፒኮክ፣ ቀበና እና አፍንጮ በር የወንዝ ዳርቻዎች ድረስ የተከናወኑት ግዙፍ ልማቶች የከተማዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይረዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች ከከተማዋ ሰፋ ያለ የኮሪደር ልማት ጋር ተቀናጅተው የእግርና የብስክሌት መንገዶችን እንዲሁም አዳዲስ ዘመናዊ ፓርኮችን ለነዋሪዎች አበርክተዋል። ይህም የከተማዋ ነዋሪዎች ከስራ ውጥረት በኋላ እፎይታ የሚያገኙባቸው፣ አየር የሚቀበሉባቸው እና ማህበራዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩባቸው ምቹ ቦታዎችን ፈጥሯል። ይህ የልማት እንቅስቃሴ የከተማዋን ሥነ-ምህዳር ከመታደግና የጎርፍ አደጋን ከመከላከል ባለፈ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አስገኝቷል። ይህም በከተማዋ ውስጥ ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል፤ የቱሪዝም ዘርፉን አነቃቅቷል፤ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲቀጥፍ አድርጓል። በሌላ በኩል ለልማቱ ሲባል የተነሱ ነዋሪዎችን በተለዋጭ ቤቶች እና በመልሶ ማቋቋም ማካተት መቻሉ፣ እንዲሁም የወንዝ ዳርቻ የጥበቃ የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ሕጎችን ማጥበቅ የፕጀክቱን ዘላቂነት አረጋግጧል። ይህ የከተማ ውበት እና የሥነ-ምህዳር ማገገም ብቻ ሳይሆን፣ ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ከተተከሉበት እና የሀገራችን የደን ሽፋን ከ17.2 ወደ 23.6 በመቶ ካሳደገው ታላቁ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ጋር ተዳምሯል፡፡ ይህ ሁሉ ጥረት ኢትዮጵያን በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም እና በዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት የአግሪኮላ ሜዳሊያ ተሸላሚ በማድረግ የዓለም አቀፍ እውቅና እና አድናቆት ባለቤት አድርጓታል። በተጨማሪም የአየር ንብረት የመቋቋም አቅም ዕውቅና በጂኦስፓሻል ኩባንያ ጥናት መሠረት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ዓለም አቀፍ ከተሞች ከአፍሪካ አንደኛ፣ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን አግኝታለች። የቆሻሻ አስተዳደርና የአረንጓዴ ሽፋንን በማሳደግ ከተማዋን ውብና ፅዱ ማድረግ በመቻሏ የተሰጠ ዕውቅናን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ዕውቅና አግኝታለች። ዛሬም ለአፍሪካ እና ለዓለም አርአያ የሆነ የአረንጓዴ ልማት ማዕከል በመሆን በግንባር ቀደምትነት እየተጠቀሰች ትገኛለች።
327
11
بدون متن...
315
12
+2
بدون متن...
441
13
በአረንጓዴ መሠረተ ልማት በእንክብካቤ ዘርፍ ለተሰማሩ ማህበራት በሙያዊ ስነ ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አዲስ የሥራ ዕድል ለተፈጠረላቸውና በአረንጓዴ መሰረተ ልማት እንክብካቤ ላይ ለተሰማሩ ማህበራት በሙያዊ ስነ ምግባር ዙሪያ ያዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና  ሰጥቷል። የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው የእንክብካቤ ማህበራት ስራቸውን ከማንኛውም ዓይነት ሙስናና ሌብነት በፀዳ መልኩ እንዲከውኑ ለማስቻል ነው። ማህበራቱ ከቢሮው ጋር በገቡት ውል መሰረት ስራቸውን በታማኝነትና በታታሪነት እንዲፈጽሙ፤ መብትና ግዴታቸውን በተገቢው መንገድ ተረድተው ህግንና አሰራርን ብቻ መሰረት አድርገው እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑም ተመላክቷል። በቢሮው የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘሩ ከበደ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን፣ ማህበራቱ የተጣለባቸውን ኃላፊነትና ግዴታ በሚገባ ተረድተው የተሰጣቸውን የህዝብና የመንግስት አደራ በታማኝነት መወጣት ስለሚችሉበት ሁኔታ በቂ ግንዛቤ አስጨብጠዋል። አሰልጣኙ አክለውም ማህበራቱ በገቡት ውል መሰረት ህግና አሰራርን ጠብቀው አለመስራት የሚያስከትለውን የህግ ተጠያቂነት በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል የአረንጓዴ አካባቢዎች አያያዝና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ አጥናፉ ከአረንጓዴ መሰረተ ልማት እንክብካቤ ጋር ተያይዘው ባሉ ተጨባጭ የሥራ ሂደቶች ዙሪያ ለማህበራቱ ግልጽና ሰፊ ግንዛቤ ፈጥረውላቸዋል። በዚህ እጅግ አስፈላጊ በሆነው የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የከተማው ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ግዛው እንዲሁም የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት  ኃላፊ ተገኝተዋል።
332
14
بدون متن...
331
15
#አፍንጮ በር ሌላኛው የከተማው ድምቀት
#አፍንጮ በር ሌላኛው የከተማው ድምቀት
381
16
+5
بدون متن...
498
17
ህፃናት በአካል፣ በአዕምሮና በማህበራዊ ክህሎት ዳብረው የነገ ሀገር ተረካቢ እንዲሆኑ ከልጅነት ጀምሮ የተሻለ የእድገት መሠረት መጣል እንደሚገባ ተገለፀ። ለነገዋ ሀገር ተረካቢ ህፃናት የተሻለ የእድገት መሠረት ለመጣል የቀዳማዊ ልጅነት ዲዛይንና የመጫወቻ ቦታዎች ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የቀዳማዊ ልጅነት ዲዛይን ዝግጅት፣ ትግበራና ክትትል ዳይሬክቶሬት በቀዳማዊ ልጅነት ዲዛይን ዝግጅትና በህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ግንባታ ዙሪያ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። ስልጠናው ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ለተወከሉ 22 ፎካልና ረዳት ሰልጣኞች፣ ለአራት አማካሪ ማህበራት እንዲሁም ለቢሮው የዘርፉ ባለሙያዎች እየተሰጠ ሲሆን፣ ዓላማውም በዘርፉ የሚሰሩ አካላት የተሻለ እውቀትና ግንዛቤ እንዲያገኙ ማስቻል ነው። የስልጠናው ዋና ትኩረት በቀዳማዊ ልጅነት ዲዛይን ዝግጅትና በህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ግንባታ ላይ የተሳተፉ አካላት በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው፣ በሳይንሳዊ ጥናትና በሙያዊ እውቀት ላይ ተመስርተው ዘመኑን የሚመጥኑ፣ ለህፃናት ዕድገት የሚያግዙና ደህንነታቸውን የሚጠብቁ የመጫወቻ ቦታዎችን እንዲያዘጋጁና እንዲያለሙ ማገዝ ነው። በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ አለሙ፣ የቀዳማዊ ልጅነት ዘርፍ ለነገዋ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት በአካል የሚዳብሩበት፣ በአዕምሮ የሚቀረፁበትና ማህበራዊ ክህሎታቸው የሚጎለብትበት ወሳኝ የእድገት ምዕራፍ መሆኑን ገልፀዋል። ኃላፊው አክለውም ሰልጣኞች በዘርፉ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃትና በተጠያቂነት እንዲወጡ፣ ስልጠናውን በትኩረት ተከታትለው ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር እንዲለውጡ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል። በዘርፉ ልምድና ሙያዊ እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ተሳታፊዎች በቀዳማዊ ልጅነት ዲዛይን ዝግጅትና በመጫወቻ ቦታዎች ልማት ዙሪያ ያላቸውን አቅም እንዲያሳድጉና በተግባር ላይ ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ እንደሚያግዝ ይጠበቃል። ስልጠናው በቀጣዩ ቀንም በጥብቅ ዲሲፕሊን እንደሚቀጥል ተገልጿል። ለህፃናት የተሻለ የመጫወቻና የእድገት አካባቢ መፍጠር፣ ለተሻለች ከተማና ለጠንካራ ትውልድ መሠረት መጣል ነው!
327
18
بدون متن...
272
19
+9
بدون متن...
341
20
بدون متن...
270