በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ
前往频道在 Telegram
Every one comment us about the informations that we are uploading. you are also very wellcommed to give us nominations which helps us to improve our capability with regard to the concerns of the organization.
显示更多1 471
订阅者
+124 小时
+77 天
+730 天
数据加载中...
吸引订阅者
六月 '26
六月 '26
+23
在0个频道中
五月 '26
+38
在0个频道中
Get PRO
四月 '26
+33
在0个频道中
Get PRO
三月 '26
+37
在0个频道中
Get PRO
二月 '26
+30
在0个频道中
Get PRO
一月 '26
+37
在0个频道中
Get PRO
十二月 '25
+42
在0个频道中
Get PRO
十一月 '25
+64
在0个频道中
Get PRO
十月 '25
+52
在0个频道中
Get PRO
九月 '25
+44
在0个频道中
Get PRO
八月 '25
+47
在0个频道中
Get PRO
七月 '25
+47
在0个频道中
Get PRO
六月 '25
+37
在0个频道中
Get PRO
五月 '25
+31
在0个频道中
Get PRO
四月 '25
+50
在0个频道中
Get PRO
三月 '25
+52
在0个频道中
Get PRO
二月 '25
+51
在0个频道中
Get PRO
一月 '25
+79
在0个频道中
Get PRO
十二月 '24
+134
在0个频道中
Get PRO
十一月 '24
+98
在0个频道中
Get PRO
十月 '24
+95
在0个频道中
Get PRO
九月 '24
+74
在0个频道中
Get PRO
八月 '24
+111
在0个频道中
Get PRO
七月 '24
+32
在0个频道中
Get PRO
六月 '24
+32
在0个频道中
Get PRO
五月 '24
+51
在0个频道中
Get PRO
四月 '24
+177
在0个频道中
Get PRO
三月 '24
+555
在0个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 14 六月 | +3 | |||
| 13 六月 | +1 | |||
| 12 六月 | +1 | |||
| 11 六月 | +2 | |||
| 10 六月 | +1 | |||
| 09 六月 | +4 | |||
| 08 六月 | +1 | |||
| 07 六月 | +3 | |||
| 06 六月 | +2 | |||
| 05 六月 | +2 | |||
| 04 六月 | 0 | |||
| 03 六月 | +1 | |||
| 02 六月 | +2 | |||
| 01 六月 | 0 |
频道帖子
ከተፈጥሮ ጥበቃ እስከ ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት
***
ባለፉት ዓመታት የብዝሃ ሕይወት መመናመን፣ የመሬት መራቆት፣ የምርታማነት መቀነስ እንዲሁም የውኃ አካላት በደለል መሞላትና መጥፋት ማኅበረሰባችንን ለድርቅ፣ ለጎርፍ እና ለምግብ ዋስትና ችግሮች ተጋላጭ አድርጎት መቆየቱ ይታወሳል።
ይህን ታሳቢ በማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሀገር በቀል ዕፅዋትንና የተፈጥሮ ሀብትን ከመጠበቅ ባለፈ፣ የአየር ንብረት ለውጥን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከልና የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ግንባር ቀደም የለውጥ መሠረት መሆን ችሏል።
ባለፉት ሰባት ዓመታት በተሰሩ ብርቱ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን፣ በመርሐ ግብሩ እስካሁን 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የሀገራችን አረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል።
ይህ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ባለፈ፣ የአየር ንብረት ተፅዕኖን በመቀነስ ለሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና ዲፕሎማሲያዊ መስኮች ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እያስገኘ ይገኛል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተፈጥሮን የመንከባከብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገርን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ታላቅ ተግባርም ጭምር ነው።
በተለይም ለምግብነት የሚውሉ ዛፎችና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ባላቸው ዕፅዋት ላይ ትኩረት መደረጉ ለምግብ ዋስትና እና ለሥርዓተ ምግብ መሻሻል ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ አቅም ፈጥሯል።
መርሐ ግብሩ የውኃ እጥረትን በከፍተኛ ደረጃ ከመቅረፉና የውኃ አካላት በደለል እንዳይሞሉ ከመከላከሉ ጋር ተያይዞ፣ አርሶ አደሮች ከክረምት ወቅት ጥገኝነት ወጥተው በበጋ ወቅትም በመስኖ በዓመት ሁለቴና ከዚያም በላይ እንዲያመርቱ ሰፊ ዕድል ከፍቷል።
ስለሆነም ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገበት የሚገኘው 7ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የነገዋን ኢትዮጵያ ገጽታ የሚወስን ታላቅ ብሔራዊ ንቅናቄ ነው።
ይህንን መርሐ-ግብር በታቀደለት መንገድ ማሳካት የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ፣ አረንጓዴና የተደላደለች ሀገርን በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ዋነኛው መሣሪያ በመሆኑ "ነገን ዛሬ እንትከል፣ የነገው አረንጓዴ አሻራ የዛሬው እጃችን ሥራ ነው"።
| 2 | 没有文字... | 57 |
| 3 | የነገው ውርስ - ተስፋን የመትከል የሕልውና ዘመቻ
******
(የዕለቱ መልዕክት)
ተፈጥሮ በለመለመ እቅፏ አውርሳን የነበረችውን ድንቅ ምድር፣ ዛሬ በእኛ እጅ ውበቷ እንዳይደበዝዝ ታላቅ አደራ ከፊታችን ተደቅኗል።
ኢትዮጵያ ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የዛሬ ሰባት ዓመት የጀመረችውን የአረንጓዴ ዐሻራ በጎ ተግባር አስቀጥላለች።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሀገራችንን የነገ ዕጣ ፈንታ የሚወስን፣ ጊዜውን የዋጀ እና ትውልድን የሚታደግ ብሩህ ጎዳና ነው።
ይህ ንቅናቄ ተባብረን እና ተጋምደን ሀገራችንን ከቀውስ የምንታደግበት፣ የትናንት የነጻነት ዐርበኝነታችንን በተፈጥሮ ጥበቃ የምንደግምበት የዘመናችን ድንቅ ዓድዋ ነው።
ይህ የዘመናችን ዓድዋ ደግሞ የዛሬውን “የመደመር ትውልድ” የታሪክ ዐሻራ እና ሁለንተናዊ አቅም የሚፈትን ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ ነው። ትናንት አባቶቻችን ልዩነቶቻቸውን አክስመው በዓድዋ ዓውድማ ላይ በአንድነት ለነጻነት እንደቆሙ ሁሉ፣ የዛሬው የመደመር ትውልድም ዕውቀቱን፣ ጉልበቱን እና ፍቅሩን አስተባብሮ ለሀገራችን አረንጓዴ ልብስ ሊያለብሳት ይገባል።
ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ከዳር ለማድረስ ሰፊ ጉልበት እና አቅም ያለው የመላው ኅብረተሰብ ንቁ ተሳትፎ ያስፈልጋል።
የባለቤትነት ስሜት በሁላችንም ልብ ውስጥ ይበልጥ እንዲያብብ እና አረንጓዴው ዐሻራ እንዲያፈራ፣ ሥራው በወል መሬት ላይ ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዱ ዜጋ የግል ይዞታ እና ደጃፍም ጭምር መተግበር አለበት።
እያንዳንዷ በየቤታችን የምንተክላት ችግኝ ነገ ተያይዛ ታላቅ ደን፣ ታላቅ ሀገራዊ ኃይል ትሆናለች። ዛሬ በእኛ በመደመር ትውልድ ትከሻ የምናደርገው ጥረት ሀገራችን የምግብ ዋስትናዋ በዘላቂነት የተረጋገጠ እና የአየር ንብረት መዛባት የማይበግራት ጽኑ እንድትሆን ያደርጋታል።
የደን ልማት አካል የሆነው ይህ በጎ ተግባር ከሀገራዊ ፋይዳው ባሻገር፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ በረከቶችን እና ሰላምን የተሸከመ የሕልውናችን መሠረት ነው።
ለሀገራችን የደን ልማት የቅንጦት ወይም የውበት ጉዳይ ሳይሆን፣ በቀጥታ ከሕልውና ጋር የተያያዘ ቁልፍ ጉዳይ ነው።
በዘንድሮው አረንጓዴ ዐሻራ መሪ ቃላችን እንደተመላከተው “ተስፋን እንትከል”! አዎ፣ ዛሬ የምንተክላት እያንዳንዷ ችግኝ ለነገው ትውልድ የምናበረክታት የሕይወት፣ የሰላም እና የብልጽግና ተስፋ ናት።
ይህ ተግባር የመጪው ትውልድ ድንቅ ቅርስ እና የማያረጅ ውርስ ነው። “እናት ሙታ ልጅ አታሳድግም” እንደሚባለው ሁሉ፣ የተራቆተች እና የደረቀች ምድርም የነገ ልጆቿን ልታቅፍ፣ ልትመግብ እና ልታሳድግ አትችልም።
ስለዚህ ነገ በታሪክ እና በትውልድ ፊት እንዳናፍር፣ የለመለመች እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት ዛሬ ሁላችንም በጋራ ልንነሣ እና ታሪካዊ የዓድዋ ድላችንን በአረንጓዴ ልማት ልንደግመው ይገባል።
እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን አረንጓዴ ዐሻራ በማሳረፍ ተስፋን ይትከል፤ ለተተኪው ትውልድ የሚበቅል፣ የሚለምልም እና የሚጠቅም ሕያው ቅርስ ያውርስ። የተስፋችን ምድር ትለምልም። | 216 |
| 4 | 没有文字... | 187 |
| 5 | አረንጓዴ አሻራ የ7 ዓመታት ጉዞ
***
✅ ጠቅላላ የተተከሉ ችግኞች ➡ ከ48 ቢሊዮን በላይ
✅ የችግኞች የመጽደቅ ምጣኔ ➡ 84% (ከ40 ቢሊዮን በላይ የጸደቁ)
✅ የሀገራችን የደን ሽፋን ➡ ከነበረበት 3% ተነሥቶ ወደ 23.6% ደርሷል
✅ ያገገመ የተራቆተ መሬት ➡ ከ10 ሚሊዮን ሔክታር በላይ
✅ የተፈጠረ ጠቅላላ የሥራ ዕድል ➡ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች | 226 |
| 6 | 没有文字... | 228 |
| 7 | የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ወቅት ላይ እንገኛለን። ከስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ በሆኑበት በዚህ ወቅት፣ አረንጓዴ ለሆነች ነገ፣ ሁላችንም ተስፋን እንትከል!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) | 204 |
| 8 | 没有文字... | 171 |
| 9 | #የመዲናዋ የአረንጓዴ ልማት ከታሪካዊና ባህላዊ ሀዉልቶቿ ጋር ተደምረዉ ለከተማዋ ድምቀት ሰጥቷታል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ ታሪካዊና ባህላዊ ሀውልቶች ለከተማዋ የውበት፣ የታሪክና የቱሪስት መስህብነት እሴት እጅግ ከፍተኛ ፋይዳ አላቸው።
እነዚህ ሀውልቶች የከተማዋን የስነ-ህንጻ ውበት ከማሳደግ ባለፈ የሀገሪቱን ማንነት፣ ጀግንነትና የኪነ-ጥበብ ጥልቅ ምስጢር ለዓለም ህዝብ በጉልህ የሚያሳዩ ህያው ምስክሮች ናቸው። በዚህ ላይ ሀዉልቶቹ የቆሙበት አካባቢዎች በአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች እያሸበረቁ መምጣታቸዉ ከተማዋ ይበልጥ ደምቃ እንድትታይ የራሳቸዉን ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡
የከተማዋን ስነ-ውበት (Aesthetics) ማበልጸግ
ሀውልቶች የአንድን ከተማ አሰልቺና ተመሳሳይነት ያላቸውን ህንጻዎችና መንገዶች እይታ በመስበር ለዓይን ማራኪ የሆነ የከተማ ውበትን ይፈጥራሉ።
በአደባባዮችና በዋና ዋና የትራፊክ መጋጠሚያዎች ላይ የሚቆሙት ቅርሶች ለከተማዋ ልዩ የንድፍ (Design) መዋቅር ይሰጧታል። እነዚህ የጥበብ ስራዎች ከአካባቢያቸው አረንጓዴ ልማትና ዘመናዊ መንገዶች ጋር ተዋህደው ሲታዩ ለአዲስ አበባ ልዩና ውብ እይታን ያጎናጽፏታል።
ታሪክንና ባህልን በኪነ-ጥበብ የመግለጽ ፋይዳ
ሀውልቶች ዝምተኛ ነገር ግን ተናጋሪ የከተማዋ ጌጦች ናቸው። ከተማዋን ውብ ከሚያደርጓት ነገሮች አንዱ ታሪኳን በአደባባይ መግለጧ ሲሆን፣ እንደ ሰማዕታት ሀዉልት (ስድስት ኪሎ) እና ሚያዝያ 27 የድል ሀውልት (አራት ኪሎ) ያሉ የኪነ-ጥበብ ስራዎች የሀገሪቱን ነፃነትና መስዋዕትነት በግልጽ ያሳያሉ።
በቅርቡ ደግሞ ታድሰዉ በመሰራታቸው መዲናዋ የኪነ-ጥበብና የባህል ማዕከል መሆኗን በማሳየት ረገድ የራሳቸውን ውበት ጨምረዋል።
ለቱሪዝም መስህብነትና ለከተማዋ ገፅታ ያላቸው ሚና
አንድን ከተማ ለጎብኚዎች ማራኪ ከሚያደርጉ ዋና ዋና መዳረሻዎች መካከል በዋና ዋና መንገዶችና ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ ሀውልቶች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።
ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ የውጭ ሀገር ቱሪስቶችም ሆኑ የአገር ውስጥ ጎብኚዎች እነዚህን መዋቅሮች በመጎብኘት ፎቶግራፎችን ይነሳሉ፤ ይህም ከተማዋ በቱሪዝም ዘርፍ ያላትን ውበትና ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል። ሀውልቶቹ ከዘመናዊ የከተማ ኮሪደር ልማት ጋር ተዋህደው ሲደራጁ አዲስ አበባን የባህልና የኪነ-ጥበብ መዲናነቷን ይበልጥ ያጎላታል።
በቅርቡ ተሰርተዉ ለህዝብ ክፍት የተደረጉ በኪነ ጥበቡ አንቱ ለተባሉ ሰዎች፤ ሀገራችንን በአለም አደባባይ ያስተዋወቁ ለታዋቂ አትሌቶቻችን፤በጦር ግምባሮች ጭምር ተጉዘዉ መከላከያችንን የሚያጀግን የአርት ስራዎቻቸዉን በማቅረብ ከጠላት ጋር ፍልሚያ አድርገዉ ለሀገራቸዉ ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ለፈፀሙ አርቲስቶቻችን የቆመዉ ሀዉልት ለመዲናችን አስደማሚ ዉበት አጎናፅፏታል፡፡
በመዲናዋ የተሰሩና በመሰራት ላይ ያሉ ሀውልቶች የከተማዋን የቀድሞ ታሪክ ከዘመናዊው ውበት ጋር በማስተሳሰር፣ አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹና ለዓይን ማራኪ፣ ለጎብኚዎቿ ደግሞ የማይረሳ ትዝታ የምትሰጥ ከተማ እንድትሆን ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
#የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ
ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት | 200 |
| 10 | 没有文字... | 181 |
| 11 | ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በምን መልኩ እንዘጋጅ?
አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሀገራችንን ስነ-ምህዳር ለመጠበቅ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የተጀመረ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህንን የክረምት ወቅት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስኬታማ ለማድረግ እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል አስቀድሞ መዘጋጀት እና የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅበታል።
እንደ ህዝብ እና ማህበረሰብ የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች
የአረንጓዴ ልማት ስራ ስኬታማ የሚሆነው መላው ህብረተሰብ በባለቤትነት ስሜት ሲንቀሳቀስ ነው። ማህበረሰቡ አስቀድሞ የሚተከሉበትን ቦታዎች መለየት፣ የመትከያ ጉድጓዶችን ማዘጋጀት እና ለአካባቢው አየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ችግኞችን መምረጥ አለበት።
በችግኝ ተከላ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ የጋራ እቅዶችን ማውጣት እና የተተከሉ ችግኞች እንዳይጠፉ የጥበቃና የእንክብካቤ ስርአት መዘርጋት ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል።
የወጣቶች ዝግጅት እና ተሳትፎ
ወጣቶች የጉልበት እና የፈጠራ አቅም ባለቤቶች በመሆናቸው የንቅናቄው ግንባር ቀደም መሪዎች ናቸው።
ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ መድረኮች ስለ አረንጓዴ አሻራ ጠቀሜታ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መስራት ይኖርባቸዋል።
በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረቱ የችግኝ ተከላ ግብረ-ኃይሎችን በማደራጀት ጉድጓዶችን በመቆፈር፣ ችግኞችን በማጓጓዝ እና በመትከል ረገድ ግንባር ቀደም ሚና መጫወት አለባቸው።
የቡድን እና የተደራጁ አካላት ሚና
የተለያዩ ማህበራዊ፣ እምነት ተኮር እና የበጎ አድራጎት ቡድኖች አባሎቻቸውን በማስተባበር የተጠናከረ ዝግጅት ማድረግ ይችላሉ።
እያንዳንዱ ቡድን የተወሰነ የተከላ ቦታ (ብሎክ) በመረከብ ለችግኞቹ ቀጣይነት ያለው እንክብካቤ ለማድረግ ኃላፊነት መውሰድ አለበት። በቡድን ደረጃ የሚደረግ ዝግጅት ስራዎችን በተደራጀ መንገድ በፍጥነት ለመከወን እና የተከላውን ጥራት ለመጠበቅ በእጅጉ ያግዛል።
የከፍተኛ እና የታችኞቹ ተቋማት ኃላፊነት
የመንግስት፣ የግል እና የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ስኬት የንብረት፣ የገንዘብ እና የሰው ኃይል ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ተቋማት ለሰራተኞቻቸው የተከላ መርሃ ግብር በማዘጋጀት፣ የችግኝ መግዣ በጀት በመመደብ እና ተቋማዊ አሻራቸውን የሚያሳርፉበት ስፍራ በማዘጋጀት መሳተፍ አለባቸው። ከተከላው ባሻገር ችግኞቹ እስኪጸድቁ ድረስ የክትትል ስልቶችን ቀርጾ መተግበር ከተቋማት የሚጠበቅ ታላቅ ኃላፊነት ነው።
የተማሪዎች ተሳትፎ እና ዝግጅት
ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻቸው ውስጥ ባሉ የአካባቢ ጥበቃ ክለቦች አማካኝነት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይችላሉ። የትምህርት ቤት ቅጥር ግቢዎችን እና አካባቢዎችን በመለየት የችግኝ መትከያ ቦታዎችን ማዘጋጀት ከተማሪዎች የሚጠበቅ ተግባር ነው።
በትምህርት እረፍት ወቅትም በየአካባቢያቸው በሚደረጉ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች ላይ በመሳተፍ እና ችግኞችን በመንከባከብ የአረንጓዴ ልማት ባህልን በተግባር ሊላመዱ ይገባል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሁላችንንም የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ካሁኑ በተደራጀ መንገድ በመዘጋጀት የዘንድሮውን የክረምት ወቅት በታላቅ ስኬት ማጠናቀቅ ይኖርብናል። | 329 |
| 12 | 没有文字... | 283 |
| 13 | አረንጓዴ ዐሻራ ለምግብ ሉዓላዊነት
++++++++++
#የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ-ግብር ተፈጥሮን የመንከባከብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ የሀገርን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተግባርም ጭምር ነው።
በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል አቅም ላይ የደረሰው ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ዘመቻ፤ የደን ሽፋናችንን ከማሳደግና ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር፤ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ፣ ለሥርዓተ-ምግብ መሻሻልና ለሀገር ሉዓላዊነት ሰፊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
በተለይም ለምግብነት የሚውሉ ዛፎችና የተለያዩ ጠቀሜታዎች ያላቸው ዕፅዋት ላይ ትኩረት መደረጉ፤ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ አቅም ፈጥሯል፡፡
የውኃ እጥረትን በከፍተኛ ደረጃ ስለሚቀርፍና የውኃ አካላት በደለል እንዳይሞሉ ስለሚከላከል፤ አርሶ አደሮች ከክረምት ወቅት ጥገኝነት ወጥተው በበጋ ወቅትም በመስኖ በዓመት ሁለቴና ከዚያም በላይ እንዲያመርቱ ዕድል ይሰጣቸዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ-ግብር የአየር ንብረቱን በማመጣጠን፣ ዝናብ በወቅቱ እንዲጥልና የአካባቢ ሙቀት እንዲቀንስ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና አለው።
መርኃ-ግብሩ አርሶ አደሩን ካልተጠበቀ የተፈጥሮ አደጋ ተከላክሎ አስተማማኝ ምርት እንዲሰበስብና የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ይረዳዋል። ይህ ደግሞ የአየር ንብረት መለዋወጥ የምርት እጥረት በሚያስከትልበት አስቸጋሪ ወቅት እንኳ የምግብ አቅርቦት እንዳይቋረጥ ዋስትና ይሆናል። | 304 |
| 14 | 没有文字... | 316 |
| 15 | ከሀገር በቀል ጥበብ እስከ መዲናዋ ውበት
አዲስ አበባን ከተፈጥሮ ጋር ያስታረቀው አረንጓዴ ልማት
አዲስ አበባ የተመሰረተችው ከተራራ እና ከውኃ ጋር በተያያዘ የሕይወት ዑደት ውስጥ ነው። እንጦጦ ለአዲስ አበባ የተፈጥሮ ውበቷና ከነፋስ መከላከያ መከታዋ ሲሆን፤ ቀጨኔ፣ ቀበና፣ ግንፍሌ፣ ቡልቡላ እና ሌሎችም ወንዞች ደግሞ የከተማዋ ዋነኛ የሕይወት መስመሮች ነበሩ።
ይህንን የቆየና የልማት አቅጣጫ በአዲስ እሳቤ ለመቀየር፣ አዲስ አበባ አረንጓዴ እና ተፈጥሮን ማዕከል ያደረገ መንገድ መያዝ ግድ ስላላት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት ይፋ የሆነውን ከተማዋን የማስዋብ ፕሮጀክት በመቅረጽ በ2011 ዓ.ም ወደ ተግባራዊ ስራ ተገብቷል።
በዚህ አዲስ መዋቅር ከተሰሩ በርካታ ስኬታማ ተግባራት መካከል የሚጠቀሰው የእንጦጦ-ቀጨኔ መድኃኔዓለም የወንዝ ዳርቻ ልማት፤ የተራራ፣ የሸለቆ፣ የባህል፣ የሥራ ፈጠራ እና የአካባቢ ጥበቃ ታላቅ ድምር ውጤት ሆኗል።
ይህ ልማት ሀገር በቀል ማንነትንና እውቀትን ያከበረ መሆኑን ያሳየበት፣ የኮንሶዎችን የዘመናት ጎርፍ የመከላከል ጥበብ የእርከን ሥራ በተግባር የተገበረበት ነው፡
አረንጓዴ ልማት ውበት ብቻ ሳይሆን የጠንካራ ኢኮኖሚ መሰረትም ጭምር ነው። በእንጦጦ-ቀጨኔ እና በመላው አዲስ አበባ የሚገኙ የወንዝ ዳርቻ የልማት ሥፍራዎች አሁን ላይ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድልን መፍጠር ችለዋል።
ካፌዎች፣ የብስክሌት ሽያጭና ኪራዮች፣ እንዲሁም የቱሪስት አገልግሎቶች ለነዋሪው አዲስ የገቢ ምንጭ የፈጠሩ ሲሆን፤ በሌላ በኩል የሚፈጠሩት የባህል እና የገበያ ትስስሮች ለአካባቢው ልዩ ድባብ መፈጠሪያ እና ለማኅበረሰቡ ማንነትን መግለጫ መንገድ ሆነዋል።
በተለይም ቀጨኔን በሸክላ ሥራዋ፣ ሽሮሜዳን ደግሞ በሸማ ጥበቧ የምናውቃቸውን የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ምርቶቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ፣ ለጎብኚዎች በቀላሉ በሚደርስ እና ንጽህናው በተጠበቀ የሕዝብ ገበያ ለማቅረብ ሰፊ ዕድል አግኝተዋል።
ፅዱ ከተማ ማለት ውብ መንገድ ብቻ ሳይሆን ጤናማ ነዋሪ፣ የተጠበቀ ተፈጥሮ፣ የተነቃቃ ኢኮኖሚ እና ለትውልድ የሚተርፍ ማለት ነው። | 318 |
| 16 | 没有文字... | 279 |
| 17 | አረንጓዴ ዐሻራ - የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ሞተር
*****
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሥነ ምኅዳር ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከያነትን ተሻግሮ፣ የሀገራችን ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት መሪ ሞተር እና አዲሱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እየሆነ መጥቷል።
ከተፈጥሮ ጥበቃው ባሻገር ያለው ተጨባጭ የኢኮኖሚ እምቅ አቅም በሀገራችን ቁልፍ ዘርፎች እና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ላይ ትልቅ መዋቅራዊ ለውጥ እያመጣ ይገኛል።
ይህ ታላቅ ብሔራዊ ንቅናቄ በሁለት ምዕራፎች ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያን አረንጓዴ ማልበሱን ቀጥሏል።
ይህ ተግባር የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ በማቋቋም የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ እና የብዝኃ ሕይወትን በመጠበቅ ረገድ ዓለም አቀፍ አድናቆትን ከማትረፉም በላይ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መድረክ የድርድር አቅሟን እንድታሳድግ አስችሏታል።
በግብርና ምርታማነት እና የምግብ ዋስትና ላይ የደን ሽፋኑ መጨመር የአፈር መሸርሸርን በመግታት የከርሰ-ምድር ውኃ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲበለጽግ አድርጓል።
ይህ የተፈጥሮ ሚዛን መስተካከል የግብርና ምርታማነትን ከማሳደጉም በላይ፣ የሀገራችንን የክረምት ዝናብ ጥገኝነት በመቀነስ ለዘመናዊ የመስኖ ልማት እና ለበጋ ስንዴ ምርት ሰፊ እና አዳዲስ ምቹ ዕድሎችን ከፍቷል።
በተለይም አቮካዶ፣ ፓፓያ እና አፕልን ጨምሮ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት መተከላቸው የሀገር ውስጥ ገበያን ከማረጋጋት አልፎ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች ጠንካራ ግብዓት በመሆን እና በውጭ ንግድ (ኤክስፖርት) ዘርፍ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ላይ ይገኛል።
ይህ ንቅናቄ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን፣ በተለይም ሴቶችን እና ወጣቶችን በችግኝ ማፍላት እና መትከል ሂደቶች ላይ በማሳተፍ ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
ከዚህም ባለፈ የአካባቢ መለምለም እንደ ዘመናዊ የንብ ማነብ፣ የፍራፍሬ ልማት እና የሐር ምርት ያሉ አዳዲስ እና ዘላቂ የገቢ ምንጮችን ለአርሶ አደሩ እና ለአነስተኛ ነጋዴዎች በማስገኘት ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስሩን አጠናክሮታል።
ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የጀመረችውን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ የአረንጓዴ ዐሻራ ሚና የላቀ ነው።
በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ እንዲሁም በሌሎች የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች ተፋሰስ አካባቢዎች የሚደረገው የችግኝ ተከላ የአፈር ደለል ወደ ግድቦቹ እንዳይገባ ይከላከላል።
ይህም የኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን ደኅንነት በመጠበቅ የግድቦቹን ዕድሜ እና የማመንጨት አቅም ያሳድጋል።
የኢትዮጵያ ደኖች እያደጉ ሲሄዱ የሚመጥጡትን የካርቦን መጠን ወደ ገንዘብ በመቀየር ወደ ዓለም አቀፉ የካርቦን ገበያ እና እንደ REDD+ ወዳሉ የካርቦን ንግድ ሥርዓቶች ለመግባት ሰፊ በር ከፍቷል።
ይህም ሀገራችን አዲስ የውጭ ምንዛሬ እና የአረንጓዴ ልማት ፈንድ እንድታገኝ ያደርጋታል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በማጋራት የምታሳየው አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በቀጣናው የትብብር መንፈስን በመፍጠር፣ የበረሃማነት መስፋፋትን በጋራ ለመከላከል እና የጋራ የባሕር ዳርቻ እና የወደብ ደኅንነትን ጭምር ታሳቢ ያደረገ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትሥሥርን ለማጠናከር ትልቅ መሣሪያ ሆኗል።
በአረንጓዴ ዐሻራ አማካኝነት እያገገሙ የመጡ የተፈጥሮ ደኖች እና በመዲናዋም ሆነ በክልሎች የተገነቡት ዘመናዊ አረንጓዴ ፓርኮች ለቱሪዝም ዘርፉ አዲስ ሕይወት ዘርተዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ለመቀነስ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ የምትመኘውን ዘላቂ፣ ሁሉን አቀፍ እና ለአየር ንብረት የማይበገር ዘመናዊ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ሥርዓት ለመገንባት ዋነኛ ስትራቴጂያዊ መሣሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። | 440 |
| 18 | 没有文字... | 353 |
| 19 | የመዲናዋ የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ዝግጅት አፈፃፀም የላቀ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መጪውን ክረምት ተከትሎ ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የችግኝ ዝግጅት በሚፈልገው ደረጃ ልክ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
የከተማ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አመራሮች በመዲናዋ የተለያዩ ክ/ከተሞች የሚገኙትን የችግኝ ጣቢያዎችን ችግኝ ዝግጅት ተዘዋዉረዉ የተመለከቱ ሲሆን ለ2018/19 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስፈላጊ የሆኑ የችግኝ ዓይነቶች በታቀደላቸዉ ጊዜ መሠረት ከወዲሁ ማዘጋጀት መቻሉን በምልከታቸዉ አረጋግጠዋል ፡፡
ችግኝ ጣቢዎች የተለያዩ ዓይነት ስብጥር ያላቸውን የጥላ፤ ለምግብነት የሚዉሉ ፍራፍሬ ችግኞች ፤ለዉበት እና ለመድኃኒትነት አገልግሎት የሚሰጡ ችግኞችን ማዘጋጀት ተችሏል።
በተለይ ለዘንድሮዉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ሀገር በቀል ዛፎችና የፍራፍሬ ችግኝ ዝግጅት ላይ ትኩረት ተደርጎ ተሰርቷል።
በመጨረሻም አመራሮች በቀጣይነት ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ አንኳር ጉዳዮች ዙሪያ ለችግኝ ጣቢያዎቹ ተጨማሪ የስራ መመሪያና አቅጣጫ ሰጥተዋል። | 567 |
| 20 | 没有文字... | 418 |
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
