fa
Feedback
ወግ ብቻ

ወግ ብቻ

رفتن به کانال در Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch@zefenbicha Creator @leul_mekonnen1

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ወግ ብቻ

کانال ወግ ብቻ (@wegoch) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 17 130 مشترک است و جایگاه 4 942 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 1 958 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 17 130 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 10 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -117 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 0 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 19.71% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 7.27% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 376 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 246 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 67 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch ✔ @zefenbicha Creator @leul_mekonnen1

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 11 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

17 130
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+147 روز
-11730 روز

در حال بارگیری داده...

ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
ژوئن '26
ژوئن '26
+37
در 0 کانال‌ها
مه '26
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '26
+27
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مارس '26
+19
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '26
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '26
+37
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '25
+61
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '25
+24
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '25
+29
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '25
+28
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اوت '25
+11
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '25
+36
در 3 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '25
+19
در 2 کانال‌ها
Get PRO
مه '25
+38
در 1 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '25
+21
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مارس '25
+39
در 1 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '25
+49
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '25
+120
در 1 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '24
+150
در 1 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '24
+63
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '24
+80
در 1 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '24
+25
در 2 کانال‌ها
Get PRO
اوت '24
+25
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '24
+40
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '24
+12
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '24
+177
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '24
+118
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '24
+123
در 2 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '24
+69
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '24
+140
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '23
+98
در 3 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '23
+85
در 2 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '23
+53
در 2 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '23
+45
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '23
+62
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '23
+69
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '23
+64
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '23
+87
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '23
+56
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '23
+46
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '23
+42
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '23
+86
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '22
+169
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '22
+216
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '22
+112
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '22
+56
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '22
+88
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '22
+70
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '22
+152
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '22
+155
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '22
+113
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '22
+68
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '22
+49
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '22
+132
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '21
+194
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '21
+47
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '21
+35
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '21
+67
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '21
+83
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '21
+142
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '21
+62
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '21
+80
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '21
+87
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '21
+189
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '21
+202
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '21
+119
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '20
+28 778
در 0 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
11 ژوئن0
10 ژوئن+2
09 ژوئن+3
08 ژوئن+3
07 ژوئن0
06 ژوئن0
05 ژوئن+4
04 ژوئن+13
03 ژوئن+6
02 ژوئن0
01 ژوئن+6
پست‌های کانال
እየመጡ ነው! (አሌክስ አብርሃም) ቦሌና መገናኛ ጫማ ልትገዙ ስትሄዱ ድንገት አግኝታችሁት እንዳትደነግጡ ከወዲሁ ልንገራችሁ። የቻይናው ብሔራዊ የሕክምና ምርቶች አስተዳደር NEO (Neural Electronic Opportunity) ጭንቅላት ውስጥ የሚቀበር ቺፕ ለገበያ እንዲውል በይፋ ፈቅዷል። በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የጭንቅላት ውስጥ ቺፕ የንግድ ፈቃድ ተሰጠ ማለት ነው። (እንደፈራነው) ጦቢያዊያን ለአመታት ችብስ 666 ...ስንለው የነበረው ጉዳይ ያው እየመጣ ነው። ነገ እንደጥርስ ማስታወቂያ በተወሳሰቡ የህክምና ቃላት ታጅቦ "አስመጥተናል" የሚል ማስታወቂያ መነገሩ አይቀሬ ነው። ለጊዜው ለአካል ጉዳተኞች ረዳትነት ብቻ ይውላል ብለዋል። ያው አንድ ነገር ከተመረተ በኋላ የቴክኖሎጅውን ፍጥነት በስልክ ማየት ነው። ዝርዝሩ ይቅርብን ግን ኤሎን ማስክ 'Neuralink' ብሎ የጀመረውን ፕሮጀክት ቻይናወቹ ቀድመው ለገበያ አውለውታል።የሆነ ቀን ቱርክ ፀጉር ከቱርክ አንጎል ከቻይና አሰገጥመን ሸገር ላይ እንግሊዝኛውን ልናዶለዱለው እንችላለን። ችግሩ ሀክ ሊደረግም ይችላል የሚል ስጋት መኖሩ ነው። አስበሽዋል እናት የሰርግሽ ቀን የባልሽ አንጎል ሃክ ቢደረግ? ወጩ ጋር ተዳምሮ... @wegoch @wegoch @paappii

2
የጠቋር ሚስት ጓደኛዬ አዲስ ሙሽራ ነው። ገና ስድስት ወሩ ነው ካገባ። የሆነ እሁድ ጠዋት ልጠይቃቸው ቤታቸው ስሄድ ይሄን ገንገበት ጓደኛዬን ባለቤቱ “ዳዲ” እያለች ስትጠራው ሰማሁ። ተወልዳ እስክታድግ በአንድ የአምበሳ ቆዳ ጫማ እየዳከረ ያሳደጋትን የአባቷን ስም እንደቀልድ ለስድስት ወር ባሏ መስጠቷ ግርም አለኝ። አጎቴ "ሴትና የቀበሌ ቤት የኔ ነው አይባልም" የሚለው እውነት ሳይሆን አይቀርም። ቤታቸው የሄድኩት እሁድ ጠኋት ስለነበር “ቸርች ልንሄድ ስንል መጣህ” ብለው አብረን ካልሄድን አሉኝ። ላለመሄድ ብሞክርም ባለቤቱ ቆጣ ብላ “ኖህ! ወደድራፍት ቤት እንሂድ ቢሉህ መች እምቢ ትላለህ? በል ተነስ” አለችኝ። ይሄ ግምብ ራስ ባሏ ድራፍት እንደምወድ ነግሯታል ማለት ነው። ሰነድ መሻሻጥ ተጀመረ? ብዬ እያመነታሁ አብሬያቸው ሄድኩ። የወሰዱኝ ቸርች አንድ ነብይ የሚያገለግልበት አዲስ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ነው። ጓደኛዬ ባለቤቱ በቅርቡ ጌታን እንደተቀበለች ነግሮኛል። ገና ውስጥ ገብተን አረፍ እንዳልን በከፍተኛ ድምፅ እየጮኸች ትፀልይ ጀመር። “ጌታ ሆይ ለዚህ አብሮን ለመጣው፣ ነፍሱ በሃጢአት ለታሰረችው ጎስቋላ ወንድሜ ዛሬ ድረስለት” ስትል ደነገጥኩ። ጭራሽ ስለኔ ነው ፀሎቱ? “ጌታ ሆይ” አለች ጭራሽ ተንጠራርታ እጇን ትከሻዬ ላይ ጭና። ድምጿ እየጨመረ ነው “ጌታ ሆይ፥ ዛሬ ስለዚች ነፍስ እፀልያለሁ ...” አለች። {እቺ ነፍስ የተባልኩት እኔው ነኝ} “ዛሬ እቺ ነፍስ ከስካርና ከሃጢአት ቀምበር እንድትላቀቅ እፀልያለሁ፥ እቺ ነፍስ ዛሬ ከዝሙትና ጌታ ከማይከብርበት የሃጢአት ልምምድ እንድትፈታ እፀልያለሁ” ስትል ቀና ብዬ ምእመኑን አየሁ። እኛ አጠገብ ያሉ ምእመናን ሁሉም ወደኔ እጃቸውን ዘርግተው ይፀልዩልኛል። የት ልግባ? ጭራሽ በሰው ሁሉ ፊት ሰካራም ነው። ያመነዝራል። ትበለኝ? ለምን አንደኛዋን የቲክቶክ ቪዲዮ አትሰራብኝም? ዞር ብዬ ጓደኛዬን ሳየው ሳቁን አፍኖ በቆረጣ ያየኛል። በስጋ ብገለጥበት ደስ ባለኝ። እሱ ነው አብረን በነበርን ግዜ ምንሰራውን ነገር ሁሉ ዘክዝኮ ነግሯት የሰው መሳቂያ ያረገኝ። የተወሰነ ቆይቶ ነብዩ ወደመድረክ ወጥቶ ፀሎት ማድረግ ጀመረ። ቤቱ ፀጥ አለ። አንዳንድ ሰዎች ብቻ በየመሃሉ አሜን ይላሉ። እሱም ትንሽ ከፀለየ በኋላ ... “የጌታ መንፈስ ጅብ ጋላቢ መንፈስ ያሳየኛል” አለ። የዚህ ግዜ የጓደኛዬ ሚስት ዞር ብላ አታየኝም መሰላችሁ? ምናባሽ ላርግሽ? ብላት ደስ ባለኝ። አንተ ነህ ለማለት ፈልጋ ነው? ይሄ የተረገመ ልጅ ጅብም ይጋልባል ብሏት ይሆን እንዴ? ነብዩ ቀጠለ። “በጉባኤ ውስጥ አንድ ሰው ይታየኛል። ቤተሰቦቹ ቃልቻ ነው ሚያመልኩት። እሱንም በልጅነቱ በአጋዘን ደም ያጥቡት ነበር። ዋናው የአጋንንቶች አለቃ ይጠቀምበታል” ሲል በሃዘኔታ እንደገና ዞራ አየችኝ። አረ እቺ ሴትዮ ለምን አትፋታኝም? እያልኩ ፀሎቱን መከታተል ጀመርኩ። ነብዩ ወደኔ አካባቢ ፍጥጥ ብሎ ካየ በኋላ ከመድረክ ወርዶ ቀጥ ብሎ መጣ ..... አሁንስ እኔም ፈራሁ። ስለኔ ነው እንዴ ሚያወራው? የሚል ሃሳብ ውልብ አለብኝ። ምናልባት ነፍስ ሳላውቅ ቤተሰቦቼ እንዳለው በአጋዘን ደም አጥበውኝ ይሆን እንዴ? መቸስ ሰው ማመን ከባድ ነው በዚህ ዘመን ምናምን እያልኩ ሳስብ ነብዩ አይኑን አፍጥጦ ቀጥ ብሎ እኛ ወዳለንበት መጣና እጁን አንስቶ....... የጓደኛዬ ሚስት ላይ ሲጭን ከተቀመጠችበት ወምበር ሁለት ሜትር ወደላይ ነጥራ መሬት ላይ ተነጠፈች። እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ። ምን ጉድ ነው? በኔ ሲስቅ የነበረው ጓደኛዬ ሚስቱ እንደዚያ ስትሆን ሲያያት ክፉኛ ደነገጠ። እኔም ምን መጣ ብዬ አንዴ ነብዩን አንዴ እሷን ማየት ጀመርኩ ነብዩ “ዋናው መንፈስ ተያዘ!” ሲል ጉባኤው በጩኸትና በጭብጨባ ተሞላ። ከዚያማ ያቺ ድምፀ ለስላሳዋ የጓደኛዬ ሚስት በሙላቱ አስታጥቄ ድምፅ ትለፈልፍ ጀመር “ተቃጠልኩ! አረርኩ!” “ማነህ?” አለ ነብዩ “ጠቋር ነኝ” “ተናገር የት ነው የያዝካት?” “ባሏ ነኝ። ከልጅነቷ አሳድጌ ነው ያገባኋት” አለ ሴጣኑ። ጓደኛዬን አየሁት ሚገባበት ጠፍቶታል። “ጭራሽ የሌላ አካልን ሚስት ነው ያገባሁት?” የሚል ይመስላል። አጋንንቱ ጭራሽ ወደሱ አፍጥጦ “አጠፋሃለሁ አንተ እርጉም ሚስቴን ነጠቅከኝ” እያለ መጮህ ጀመረ። ቺት አድርጋበት መሆኑ ነው። ጓደኛዬ እንዲሁም ፈሪ ነው ጭራሽ አሁን ከሰይጣን ጋር የግል ፀብ ውስጥ በመግባቱ ያልበው ጀመር። ያቺ መላአክ የመሰለች ሚስቱ ጭራሽ አይኗን አፍጣ በወፍራም ድምፅ ዛቻዋን ቀጠለች። “ወንድወሰን ደበበ ጊሚራው” አለችው ሌባ ጣቷን ወደሱ ጠቁማ። {ዳዲ ቀረ በቃ} ነብዩ ዝም ብሎ ያያል። “አንተን ካላጠፋሁ እኔ ጠቋር አይደለሁም” አለ መንፈሱ። ጓደኛዬ እንባ ተናነቀው። በሆዱ "Who TF did i marry?" እያለ ነው “ብዙ ግዜ በተኛህበት በገጀራ እንድትሰነጥቅህ አቅጄ ነበር። ዛሬ ይሄ ነብይ ቀደመኝ” እያለ ማጓራት ጀመረ። ጓደኛዬ እንባውን በአራት መንታ አወረደው። ምን ውስጥ ነው የገባሁት? የሚል ይመስላል። ብቻ አጋንንቱ ከነብዩ ጋር ውጣ አትውጣ እያለ ሲታገል እኔ እንደምንም ሾልኬ ወጥቼ ወደቀበሌ ጃምቦ ቤት ሮጥኩ። ከአዳራሹ ወጥቼ ጥቂት እንደሮጥኩ ሩጫዬን አቀዘቀዝኩና ወደኋላዬ ስዞር ጓደኛዬ ኮቱን ጥሎ በሩጫ ወደኔ ይመጣል። አጠገቤ ሲደርስ እያለከለከ ቆመና “ወዴት ነው ጥለኸኝ ምትሮጠው” አለኝ “እንዴ አንተስ ሚስትህን ጥለህ ወዴት ነው?” ስለው “አፍህን ዝጋ” ብሎኝ አብሮኝ ወደግሮሰሪ አመራ። አሁን ሰባተኛ ጃምቧችን ላይ ደርሰናል። “እኔ ግደሉኝ እንጂ ያቺን ሴት አምኜ እዛች ቤት አላድርም” ስላለ ተሰብስበን ወደቤቱ እንዲሄድ እየለመንነው እንገኛለን። By Noah Daniel @wegoch @wegoch @paappii
2 395
3
የቆሰለ ነገር ፣የከሳ ፣የኮሰመነ እንሰሳ እሚያድን አውሬ ያስጠላኛል ምቹ ግዜ እየጠበቀ ድምፁን እና ሁኔታውን የሚቀያይር ሰው ግን ያስፈራኛል። ስዩም ፦ ጓደኛው ነኝ ጓደኛዬ ግን አይደለም። ብዙኅ አሳልፈናል ። ቢሰማብኝ የማፍረውን ነገር ወይ ቢሰማብኝ ጉድ የሚያደርግብኝን ነገር አልነግረውም ። እፈራዋለሁ። ቋሚ ወዳጅ ስለሌለው እና ዋሉልኝ ያለቸውን ሰዎች ሁሉ በየምክንያቱ ስለሚተዋቸው እፈራዋለሁ ። ከጓደኞቹ X ስር ስለማይጠፋ ስሜቱን ሁሉ የተሰማው ሰዓት ስለማያንፀባርቅ አብሬው ሆኜ አይጥ ለመያዝ ትክ ብላ እንደምታደባ ድመት ነው የማየው። እሱ እንደድመቷ ትኩረት ሲያደርግ ሁኔታው እንደድመቷ አይነት አይደለም አያስታውቅበትም ። ዘና እያለ እየሳቀ ሚስጥር እየነገረ ነው ሚስጥር የሚያስወጣው ። ስዩምን እፈራው ነበረ .....! ችግር ገጠመኝ ከሁሉም በላይ አብሮኝ ሆነ ያለውን ሁሉ ሰጠኝ አሰጣጡ ስሙልኝ እዩልኝ ያለው አልነበረም በችግሬ አብረውኝ ያልነበሩትን ስወቅሳቸው እያገዘ አላባባሰብኝም... "ተዋቸው አልሞላ ብሎቸው ነው" አለኝ ....ከነሱ ጋ ሆኜ ያጣጣልኩት ስዩም አብሮኝ ቆመ .... ተፀፀትኩ ...! ከብዙ ግዜያት በኋላ ስዩምን በየወሬው እንደዚ አትመስለኝም ነበር እያልኩ እሱ ላይ ያለኝን አቋም ተናዘዝኩ አልተናደደም ሳቀ ስልከው እና ሲላከኝ እንደኩያ አይደለም እንደታናሽ ነው ሲተማመንብኝ እንደታላቅ ነው ...! እሚያግዘን እና የሚኮራብን ወዳጅ የኛ ሲሆን የሚሰማውን ምቾት አሰማኝ ከጥቂት ግዜ በኃላ ... ስራ በዛብኝ ብዬ የሰጠሁንት ላግዝ ብሎ የወሰደውን ሙሉ ውክልና ተጠቅሞ መኪናዬን ሸጦ አውሮፓ መግባቱን ከሳምንት በሆላ ሰማሁኝ ... ስስቅ ላየኝ ሰው ተታልዬ አልመስልም ነበር ... ማመን ከመጠራጠር በላይ ዋጋ ያስከፍላል ማለት ነው ?? መፍራት ከመድፈር በላይ አቅም አለው ማለት ነው ?? ኮቴ በሰማን ቁጥር እየባነንን የት ድረስ እንሄዳለን ?? የሄድንበትን መንገድ እየጠየቅን መሄድ የሰውነት እጣ ፈንታ ነው ??.... በርግጥ የግዜ ጉዳይ እንጂ ከተካደ ሰው የከዳ ሰው ያሳዝናል!! By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
3 376
4
🌄 We’re Back And We’re Hiking Again Hey Sunset community 🌄 Life happened. The city got louder. And for a while, the sunsets
🌄 We’re Back And We’re Hiking Again Hey Sunset community 🌄 Life happened. The city got louder. And for a while, the sunsets were quieter without us. Sunset Hiking is officially back with a stronger team, clearer plan, and a growing 4,000+ hiking community ready to move again. Over the next weeks, we’ll be sharing: 🥾 Upcoming sunset hikes 🌅 Community moments 🧭 Safe, well-organized experiences If you’re still here, it means you love nature as much as we do. Let’s start again one sunset at a time. 🌄👣
4 375
5
የ ሥዓሊ እና መምህር ኃይሉ ክፍሌ "ተገማች፡ ዋዜማ" የሥዕል አውደርዕይ እዚህ ትርዒት ላይ ተገኝቼ፣ በከተማ ዝመና ውስጥ የማንነትንና የትዝታን ትርጉም የሚፈትሹ ስራዎችን ተመልክቻለሁ። የጥበብ ስራዎ+9
የ ሥዓሊ እና መምህር ኃይሉ ክፍሌ "ተገማች፡ ዋዜማ" የሥዕል አውደርዕይ እዚህ ትርዒት ላይ ተገኝቼ፣ በከተማ ዝመና ውስጥ የማንነትንና የትዝታን ትርጉም የሚፈትሹ ስራዎችን ተመልክቻለሁ። የጥበብ ስራዎቹ የሚጠቀሟቸው ቁሶችና የሚያነሷቸው ሰብአዊ ጥያቄዎች ቆም ብሎ ለማሰብ ትልቅ እድል ይሰጣሉ። የለውጥ ሂደቱ ወዴት እየወሰደን ነው? የጋራ ትዝታችንን እያካተትን ነው ወይስ እየረሳን? እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን የሚመልስ ድንቅ ትርዒት ነው። እድሉ ያላችሁ እንዳያመልጣችሁ! 📍 እስከ ግንቦት 24 ድረስ ክፍት ነው @Seiloch #Hailukifle #artExhibition.
5 035
6
ሰው ብቻ አይደለሽም! Sirak Wondemu እናትነት ዓለምን አምጦ መውለድ ነው። በምጥ ጣር ተይዞ ለሚቃትት ነፍስ የውልደት እልልታን በከንፈሩ ሰማይ ይዞ እንደሚዞር ደመና ነው። ሰው እውነትን መፃፊያ ጠመኔ ሲሆን እናት የጠመኔው መዳረሻ ሰፊ ሰሌዳ ናት። ትሁንልህ መወደሻ ተብላ በባርኮት የተሰጠች ስጦታ! በግምባሯ መስመር ላይ ዘመን ፅፋለች። በመዳፏ ስር ሕይወት ወልዳለች። ሽብሽብ ቆዳዋ እድሜን ዘምሯል። ዳሳሽ ጣቶቿ ቀንን ፈክሯል። ሰው ብቻ አይደለችም! በወዟ ጠፈፍ ከራሰ የሻሿ ጨርቅ የበለጠ የዓለም ታሪክ የለም። ጊዜና የሕይወት ዑደት አዳውረው በጥቁር ጸጉሯ መሀል እንደበተኑት የሽበት ተክል ያህል መቆዘሚያ ሀሳብ አልነበረም። እማማ ንፁህ ፈገግታሽ የንግስ ቀን ነው። የእሺታ ደጅሽ የዓለም ብርሃን ነው። ሁሉን ቻይ ልብሽ ዕፁብ ተምሳሌት ... በጊዜ ጣይ ፊት የማይሞት አይነት ፤ ነው። ኩርፊያሽ ውስጥ እንደነገሩ የወለድሽው ልጅ ፈገግታሽ ያጫውተኛል። የውሸት ተኮሳትረሽ ከሸበሸብሽው የግምባርሽ መስመር ላይ መጥምቁ ዮሐንስ እየሱስን ባጠመቀበት ቅፅበት ትከሻው ላይ ያረፈችውን ፀዓዳ እርግብ እመለከታለሁ። አለሀሳብ መከደን ካማረው መንታ ዓይኖችሽ ውስጥ ፍቅር ጠምቃለሁ። ሰው ይርበኛል። ተስፋ ጠምጄ... እምነት አርሳለሁ! እማማ ልጄ ሰው ሆነልኝ ዩኒቨርስቲ ገባልኝ ብለሽ ግማሽ ደስታ ግማሽ ሀዘን ሆነሽ የሸኘሽኝ ቀን ትምህርትን ለዘላለም ረገምኩ። ከእነዚያ ብርሃናማ ዓይኖች ብርቅ ... ከህመም ፈዋሽ ጠረኖችሽ ብሸሽ ... ከሞት መላሽ ዳሳሽ ጣቶችሽ ብሰደድ ፤ ማወቅ የገሀነም ፀሎት ሆነብኝ። ክረምቱ መጥቶ ጉያሽ ውስጥ ሽሽግ እንድል አርጩሜ ቆርጠሽ በጋውን አባሪልኝ። ኮስተር ብለሽ ሀምሌን ጥሪው። ነሀሴም ይምጣ! አንቺ ከተቆጣሽ ሁሉም ቀና ይሆናል! እማማ እምባ አርግዞ በስስት የሚያየኝ ክርትት አይኖችሽ እንዴት ናቸው? ዛሬም ለመንገደኛ እንዳዘኑ ነው? ለነፍሰጡር ላም እንደተንሰፈሰፉ ነው? በቅርሻቴ ያረጠብኩት ጀርባሽ ... ዓለሜን የተሸከመው ጫንቃሽ ዛሬም ከመቻሉ አልተፈታም? እኔማ እነሱን ለማየት ለመንካት በስንት ቀናትና ወራቶች ደረት ላይ ተሳብኩ! ሺህ ናፍቆት ከፊቴ ሺህ ጉጉት ከኋላዬ አጅቦኝ በርሽ ለመቆም ተሳልኩ! ለስንት ንጋቶች ለፈፍኩ! ሰው ብቻ አይደለሽም። ብትይኝም አላምንሽም! ሞገስሽ ልክ እንደታቦት ነው። ቁጣሽ ሀገር ያርማል። የወደቀ ቀዬን አንስቶ በውል ያቆማል። ዝምታሽ እንደፍርድ ቀን ይጨንቃል። ይጠባል። ሳቅሽ እንደእሸት ባቄላ ታኝኮ አይጠገብም። መርቀሽ የሳምሽኝ ግንባሬ ዛሬም በብርሃን እንደታጀበ ነው። ኑርልኝ ብለሽ የመረቅሽኝ ምርቃት እኔ ካልሰለቸኝ ከሞት እንደሚታደገኝ ቃል ገብቶልኛል። እማዬ ከእንግዲህ ይራባል ብለሽ አትስጊ! ይልቅ የስጋት በርሽን ዝጊ! ያኔ በጨቅላነቴ ዘመኔ እንደወፍ ልጅ ከአፍሽ ነጥቄ የጎረስኩት እስከ እለተ ሞቴ ከአንጀቴ ይኖራል። አምሳያ የሌለው ውዴታሽ ሞትን ማምለጫዬ ነው። የአንቺ ትካዜ የሀገር መፍረስ ነው። ያ ልዝብ ቃልሽ የንጋት ቀን ነው። ሰው ብቻ አይደለሽም! በነጠላሽ ጫፍ የሰው ልጅ ቋንቋ የማይገልፀው የእረፍት ዋኔ - በመቀነትሽ ስር ያልታየ ያልተሰማ ስውር ቅኔ ተቋጥሯል። ከአንቺ ጋር አይደለም አስር ሀያዬን ሰባ ሰማኒያዬን መሰንበት እፈልጋለሁ። እማ አንቺ ወዳጅ የለሽም ወዳጅሽ እኔ ነኝ። እኔም የአንቺን ያህል ግምት ሰጥቶ የሚቀበለኝ ወዳጅ የለኝም። ወዳጄ አንቺ ነሽ! ቀሚስሽን በለጋ ጣቶቼ ጨብጬ የቆምኩባቸው የጎረቤት ቡና ቅፅበቶች አይረሱኝም። ገበያ ሄደሽ እስክትመለሺ መንገድ መንገዱን እያየሁ ጉበን ታቅፌ የተኮራመትኩባቸው ወቅቶች አይኔ ላይ ናቸው። አባቴ ነጥቆሽ ዓመት ከዓይንና ድምፅሽ ርቄ የተመለስኩ ቀን ዘማች በህይወት ተርፎ እንደመጣልሽ ሁሉ በስስት ያነባሽው ዕምባ አንቺ ብትፈቅጂ ወንዝ ሆኖ ይወስደኝ ነበር። ሰውነትን የለካሁብሽ ፤ የፍቅርን ትርጉም የሰፈርኩብሽ ፤ ትናንትን ፣ ዛሬንና ነገን የመዘንኩብሽ ሚዛኔ ነሽ። ሳቅሽ ውሎ ሳይገባ እንዳይመሽ እፀልያለሁ። ስጋትሽ ስጋት በልቶት ሳይጠፋ ዘመን እንዳያልፍ እፈልጋለሁ። በትከሻሽ ላይ ቆሜ ጎበዝ ተብያለሁ። አንድ የናፍቆትሽ ዘለላ አንገቴ ላይ ቢታሰር ይዞኝ ጥልቅ እንደሚወርድ ግን የተረዳኝ የለም። አድጌ አንቺን ረሳለሁ? ቤት ይኖረኛል? እሸሽሻለሁ? አመመኝ ብትይ እረጋጋለሁ? ልቤ ይሰክናል? እኔ'ንጃ ! ልጅ ሆኜ አጎቴ ሞቶ በሀዘን ቅስምሽ ስብር ሲል ፤ ማቅ ስትለብሺ እግዜር ከትምህርት ቤታችን ዳገት በላይ ያለ እየመሰለኝ ሄጄ «አንተ አትችልም እናቴ ትሁን! » ብዬ መኮሳተር ያምረኛል። ሰፈር ሰው ሞቶ ለቅሶ ስትሄጂ መንደርተኛው እርር ሲል ... ምርር ብሎ እምባውን በጉንጩ በራፍ ሲደፋ ያ አባባሌ እውነት ሆኖ እታዘባለሁ። « በቃ እሱ አይችልም እናቴ ትሁን! » እላለሁ በልቤ። እዝነት እንደሌለው ሁሉ ፤ ምህረትን እንደማያውቅ ዝንጉ አባት ፍፁምነቱን እንድጠራጠር ያደረገኝ ፍቅርሽ ነው። ለሁሉም ነገር ሆደ ባሻ የሚሆነው አዛኝ አንጀትሽ ነው። አንቺ እኮ እግዜርን ብትሆኚ የሰፈራችን ሰዎች በሙሉ ማሪያም ቤተክርስቲያን እንዳሉ ዛፎች ሰማይ ጠቀስ እንደሆኑ ይሸብቱ ነበር። እማማ እርጅና በአንቺ ላይ ስልጣን እንዳይኖረው የአንቺን ቁጣ ኮርጄ እቆጣዋለሁ። ሞት በሰፈርሽ እንዳያልፍ በርሽ ላይ አያ-ጅቦ እንዳለ ነግሬ አስፈራራዋለሁ። እማማዬ ቃል የእምነት እዳ ነው ይላል ፀጋዬ። ቃል የእምነት ዕዳ መሆኑን የተረዳሁት ግን በአንቺ ነው። ዛሬም በሰው ሀገር ሆኜ የተቆላ ቡና ሲሸተኝ ትዝ ትይኛለሽ። ትኩስ ሽሮ ሲሸተኝ ፤ ጠይም ፈገግታም እናት ስመለከት ዓይኔ በእምባ ይሞላል። ማን ያውቃል ዛሬም ህፃን ልጅ ሲጮህ ትደነግጫለሽ አይደል? በሌለሁበት ቀዬ ተጋደሉ ሲሉሽ እግርሽን ብርክ ብርክ ይልሻል አይደል? እማዬ ጌሾ ያልወቀጠልሽ እጄን እጠላዋለሁ። ስታዢኝ በእምቢታ የሰበቅኳቸውን ትከሻዎቼን እጠየፋቸዋለሁ። ለእነዚያ ጊዜ ... ለእነዚያ ወቅቶች መዳፍሽ ስር ፊቴን ቀብሬ ማልቀስ እፈልጋለሁ። ስትገርፊኝ ያኮረፍኩባቸውን ቀኖች ባገኛቸው እንደልጅነቴ ድንጋይ ወርውሬባቸው ሮጣለሁ። ማጀትሽ በጥጋብ ይሙላ! ... ሰላምሽ እንደአሸን ይፍላ! የጦር ቃል ጆሮው ይደፈን ... በደጅሽ ፍቅር ይሸመን! ማሳሽ ላይ አዝዕርት ይብቀል! ... ይመር ሰማዩ እንደምንጭ ይጥለል። አዛኝ ነሽና መርቂኝ አለሁ... ክፉሽን ከቶ አልስማ ሳለሁ! ገብያሽን ጥጋብ ይውረሰው አይጉደል ዘመኑን ሙሉ... የተኳረፈም ይታረቅ ሁሉ! አካል ነሽና ለምድሩ ለሰው... ስሁት ደስታሽን ቀን ይደግሰው! ብቻ እማማ አንቺ ሰው ብቻ አይደለሽም ፤ እግዜር ነሽ ለልጅሽ ... ሚዛን ነሽ ለምድሩ.. ባርኮት ነሽ ለሰማይ አድባር ነሽ አውጋር ነሽ የኔ አድባር። መላዕክ ነሽ ልዩ ሰው! የአጥቢያ ዳኛ የአንቺን ያህል ፍትሕ አያውቅም! ውብ አዝማሪ ከእሽሩሩሽ የተሻለ ዜማ አይደርስም። በዓይኖችሽ ስር የፀነስሽው የተስፋ እምባ ለመኖሬ ለመዳኼ ሆኗል መባ! አለው ዋጋ! አለው ፀጋ። አስራቴ ነሽ ጃኖ ጥለት... ወደር የለሽ የሰው ቁመት። ብቻ ብቻ . . . አንቺ ሰው ብቻ አይደለሽም... ብትይኝም አላምንሽም። . . . መልካም የእናቶች ቀን ❤
4 594
7
ሶምሶማ የአጫጭር ልቦለዶች መጽሐፍ -በጃፋር መጽሐፍት መደብር(ለገሀር) -አብዱ book delivery (ፒያሳ) - +251994886247 ሰለሞን አራት ኪሎ ያገኙታል።@sirakoo @wegoch @wegoch @wegoch
4 205
8
ADDIS ABABA — FOR SUDAN Voices From Sudan On April 21, join us for a powerful evening where film, music, and community come t
ADDIS ABABA — FOR SUDAN Voices From Sudan On April 21, join us for a powerful evening where film, music, and community come together to mark the 3rd anniversary of the Sudan war. The night opens with a special live performance by The Tana Quintet by Hazim Alshafei, bringing the rhythm, soul, and resilience of Sudan to life—followed by a screening of the acclaimed film Khartoum. ✨ Free Entrance This is more than a screening. It’s a gathering. It’s a shared moment. It’s solidarity in action. Expect a full house, a powerful atmosphere, and a night that will stay with you. 📅 Tuseday, April 21, 2026 📍 Bata Complex 22, around Golagul 🕠 5:30 PM Bring your friends. Be present. Stand with Sudan. #Khartoum #Sudan #AddisAbaba #InDeepCultures #FilmScreening #LiveMusic #1960Films #AddisCinemaClub
0
9
📌 በሀዋሳ ከተማ አዲስ የስነ-ጥበብ ትምህርት ቤት የምዝገባ ጥሪ! ጥበብን ለሚወዱ እና ተሰጥኦአቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ ሁሉ ታላቅ እድል! በሀዋሳ ከተማ ከዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አዲስ የስነ-ጥበብ (ስዕል) ትምህርት ቤት ስራ ሊጀምር ዝግጅቱን አጠናቋል። 🎨 ለምን ይመዘገባሉ? • በዘርፉ ብቁ በሆኑ ባለሙያዎች የታገዘ ስልጠና ለማግኘት። • ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በተቀናጀ መልኩ እውቀትን ለማዳበር። • የፈጠራ ስራዎትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር። 🌟 የእርስዎ ድርሻ፦ ጥበብ የሀገር መገለጫ ናት! ይህ መልዕክት እንዲደርሳቸው የሚገባቸው ወጣቶች እና ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰቦች እንዲያውቁት በማጋራት (Share በማድረግ) ማህበራዊ ሀላፊነትዎን ይወጡ። ምዝገባው ተጀምሯል!👇👇 link ይጫኑ https://tally.so/r/D4Jjrl.
0
10
ፖስታዬንና ክርታሴን አንጠልጥዬ እንትና በሰጠኝ አድራሻ ታክሲ ይዤ አዲስአባ አስራምስት ቀን ያህል ቆይተን ለመመለስ ሁለት ቀኖች ሲቀረን ሄድኩ። ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር አካባቢ ነበር። በር ሳንኳኳ የከፈቱልኝ ጥምጥም ያደረጉ፤ ፂማቸውን የተላጩ፣ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ገፅ ያላቸው መልከ መልካም ጠይም ሽማግሌ ነበሩ፡፡ መምጣቴን ቀደም ብዬ ስልክ ደውዬ ነግሬአቸው ስለነበር፣ በስሜ ጠርተው በትህትና እንድገባ ጋበዙኝ፡፡ ቤት ውስጥ እሳቸውና ፊታቸው ብቻ እስኪቀር የተከናነበ ሌላ ሴት ነበሩ፡፡ ገና እንደተቀመጥኩ ራት በልቼ (ማታ ላይ ነበር የደረስኩት) እንድሄድ ሲጠይቁኝ፣ በሥነስርዓት ተከላክዬ ፖስታውንና እቃቸውን በእጃቸው ሰጠኋቸው። ስለ ልጃቸው ጤንነት ከጠየቁኝ በኋላ፤ የሚያበረታታቸውን መልስ ሰጥቼ ከተቀመጥኩበት ስነሳ፣ አንድ የሚያጫውቱኝ ነገር ስላለ በጥሞና እንድሰማቸው አግባቡኝና ተመልሼ በመመቻቸት ተቀመጥሁ። «እግዚአብሄር አንድ ነው፣ አየህ፤ ስሙን ሰዎች ይለያዩታል እንጂ አላህ ብትል፣ እግዚአብሄር ብትል አንድ ነው። ቅድመ አያቴ እስላም ነበሩ። ልጃቸው ክርስቲያን አገባና ከዚያ በኋላ ክርስትናው ቤታችን ገባ። የድሮ ሰዎች ናቸው። ለምን? በለኝ አላህ በለው እግዜር በለው ያው ነው። ልጄ ሆላንድ የቤተክርስቲያን አመራር ይሠራል ሲባል ሰምቼአለሁ፣ እሱም አንዴ ሰላም ሊል ደውሎ አጫውቶኛል። ልክ ነው? (‘ኧረ የማይገባበት ቦታ የለም’) አንድ ነገር ልንገርህ፤ እኔ ወደ ቅድመ አያቶቼ ሐይማኖት ተመልሼአለሁ» ግድግዳ ላይ በመስታወት ውስጥ ሆኖ የተሰቀለ ዳንቴል የመሰለ የዐረብኛ ነገር የተፃፈበት ነገር አሳዩኝ፡፡ «ዐረብኛውን ባላውቀውም አላህ ከሰዎች ጋር በሚገባቸው ቋንቋ ይናገራል፡፡ ነቢዩም እንዲህ ነው የሚያስተምሩት፤ ስማቸው ይባረክና፡፡ ግን ልጄ እንዲከፋው አልፈልግም፡፡ ‛አባቱም እናቱም ሰለሙ' ተብሎ ቢሰማ ያዝናል፣ ይበሳጫል፡፡ (ኧረ ካሽ ካገኘ ግድ የለውም)፡፡ ግን እዚያም ስገዱ ነው፣ እዚህም ስገዱ ነው። 'አለማየሁ' የተባለ ስሜን ‛አብዱላሂ' አሰኝቼአለሁ፡፡ የሰፈር ሰው ገና አለማየሁ' ነው የሚለኝ፡፡ ክፋት የለውም፡፡ እንዲህ ያደረግነው ለጥቅም አይደለም፡፡ ለእሱ ነው። ለእምነቱ ነው። ታዲያ ከልጄ ጋር ተገናኝታችሁ ድንገት ወሬ ቢነሳ መነሳቱ መቼም አይቀር፣ እንደ ሰለምኩ አትንገረው፡፡ ይኼን ቃል ግባልኝ፡፡ ያለዛሬ አይቼህ አላውቅም፡፡ መቼም ታምነህ የተላክህ ሰው ስለሆንክ፣ ብትግባቡ ነው መቼም (‛ከቴም ተግባባን') ቢሰማ ችግርይኖረዋል? እንጃ እንግዲህ ባትነግረው ባታወራው ግን ይመረጣል፡፡ እንዳይሳትህ ብዬ ነው» ሴትዮዋ/ባለቤታቸው ከእኛ ራቅ ብለው በጋቢያቸው ተሸፋፍነው ታስረው የተቀመጡ መስለዋል፡፡ ቃል አውጥተው አይንገሩኝ እንጂ ከአስተያየታቸው፣ ከአንገት አደፋፋቸው እየተለማመጡኝ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ለሰውዬው ከአፌ ቃል እንደማይወጣኝ፣ በተፈጥሮዬ (ምናልባት ስወለድ ጀምሮ ወይም ከእናቴ ሆድ ጀምሮ ለሐይማኖት ግድ እንደሌለኝ፤ እንደውም እሳቸው ያሉት የእግዜር መመሳሰል ትልቁ እውነት እንደ ሆነ አንስቼ) ሳይሆን አይቀርም ሚስጢር ቀርቃሪ በመሆኔ ትንፍሽ እንደማልል፣ አንዲት ቃል ከአፌ ጠብ እንደማትል ቃሌን ሰጠኋቸው፡፡ ክርስቶስን ጠርተው መረቁኝ፡፡ ከተቀመጡበትም ተነስተው ትከሻዬ ላይ ሳሙኝ፡፡ ሲሰናበቱኝና ሲሸኙኝ ሽማግሌው ዐይኖች ውስጥ ሊሸፍኑት ያልቻሉት ወፍራም እፍረት ነበር፡፡ ለመቅደስ ይሄን ሁሉ አልነገርኳትም፡፡ *** By | አዳም ረታ/ 📖 ይመያመ @wegoch @wegoch @paappii
0
11
የሳሪሱ ወጣት እና የቱርኳ Player ------------------------------------- ምነው ባላወቅኳት ያልኩበት ጊዜ ነበር...! at that time She gave me a Trauma. የደግነት ማስኳን አጥልቃ ነገር ግን የክ-ፋት ሀሳቧንም በውስጧ ሰቅዛ ተለሳልሳ ስትቀርበኝ ምን ነበር አይኔን የጋረደው..? 😁 . . እንዴት ልታሳየኝ የፈቀደችውን ብቻ ተመለከትኩላት..? ልትደብቅ የሞከረችውን ማንነት እንዴት ማየት አቃተኝ..? ወቅቱ 2014 ዓ.ም ነው። ወርሀ መጋቢት። ክስተቱ ዛሬ ድፍን አራት አመት ሞላው። በአንዲት የቢሾፍቱ ቆንጆ የተታለልኩበት ሁኔታ እና አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር። አጃጃለችኝ። አሞኘችኝ። አጭበ-ረበረችኝ። አወጫበረችኝ። የምትኖረው ቱርክ ነው። በወቅቱ Turkey መኖር ከጀመረች 3 አመታትን ያህል አስቆጥራለች። የተዋወቅነው በ Facebook ነው። Long Distance Relationship መሆኑ ነው እንግዲህ። ከ Messanger ወደ Telegram ባደገው የስልክ ልውውጣችን - በየቀኑ ለሰአታት በ Video call እናወራ ነበር። አስታውሳለሁ የሆነ ሰአት ላይ እንዲሁ በ Telegram - Video call አውርተን ስንጨርስና መጨረሻ ላይ ቻው ስንባባል - ስልኩን "አንተ ዝጋው..አንቺ ዝጊው..አንተ ዝጋው.." ተባብለን እናውቃለን። ከአንዴም ብዙ ጊዜ። Straight 5 ሰአት ያህል በስልክ የምናወራበትም ጊዜም ነበር። . እንደ እኔ እንደ እኔ ይህ ፍቅር የሚባለው ነገር መጃጃል ነው የሚመስለኝ።It is all Imagination. Glazing a person without any valid reason. There is no reason to glaze someone like that. ይህ ጉዳይ በሳይንሳዊው ዓለም Limerence ወይም ደግሞ Halo Effect ተብሎ ይጠራል። አንድ ሰው ሲያፈቅር አንጎሉ ውስጥ የሚረጩት Dopamine እና Oxytocin ልክ እንደ እ-ፅ ናቸው። እነዚህ ኬሚካሎች ሲበዙ ደግሞ... የወደድነውን ሰው ድክመት እንዳናይ ያደርገናል፣ የማይረቡ ነገሮችን እንደ ትልቅ ቁምነገር እንድንቆጥር ያደርገናል፣ በዚህ ሰዓት የምንወስነው ውሳኔ Logic የለውም። . ለማንኛውም.. የባለታሪካችንን ስም R እንበለው። R እሳት ነች ፤ ዛሬ ላይ ሁሉም ነገር አልፎ ሳስበው አድናቂዋ ነኝ። እንዴት እንዳወጫበረችኝ ሳጤነው በራሴ ሽምቅቅ እላለሁ። ቢሾፍቱ ተወልዳና አድጋ የመሀል ከተማ ልጅ [ የአዲስአበባ ልጅ ] ለዛውም የሳሪስ ልጅ ላይ ድራማ የሰራች እሳት ናት። መጀመርያ ከእኔ ጋር የፍቅር ግንኙነት ስትጀምር ሌላ ያላለቀ ግንኙነት ላይ እያለች ነው። እኔ ይህንን አላውቅም ነበር። መጨረሻ ላይ ነው የደረስኩበት። መጀመርያውኑ ፍቅረኛ እያላት ለምን ከእኔ ጋር መሆን ፈለገች..? . ከእኔ ጋር እንደተዋወቅን እንዲሁም ለረጅም ጊዜ [ ለ 4 ወር ያህል ] in Contact እያለን የበፊት ፍቅረኛዋን ሙሉ ለሙሉ አልተወችውም። በሳምንት 1ዴ ወይም 2ቴ እየደወለች ታወራዋለች። ከእኔ በፊት የነበረውን ልጅ ከመተዋወቋ በፊት ደግሞ ሌላ ፍቅረኛ ነበራት - unfortunately ያንንም አልተወችውም። ከዛ በፊትም ሌላ ፍቅረኛ ነበራት - ያንንም አልተወችውም። ሁላችንንም አልተወችንም። እንደ የቤት አውቶሞቢል [ የቤት መኪና ] በአንድ ጊዜ 4 ሰው አሳፍራ ነበር ስትጓዝ የነበረው። ልጅቷ Multi-tasking ትችላለች። በአንድ እጇ ለኔ ቴክስት እየፃፈች፣ በሌላኛው እጇ ደግሞ ከሌላው ጋር ቪዲዮ ኮል ታደርጋለች። 4 መኪና በአንድ ጊዜ የምትነዳ Formula 1 ድራይቨር ናት። ይሄን ሁሉ መጨረሻ ላይ ነው የማውቀው። ከአንድ ወንድ ጋር ሆና - ወደ ሌላ ወንድ። እኔን አስምጣ ወደ ሌላ - ያኛውንም አስምጣ ወደ ሌላ - ይሄኛውንም አስምጣ ወደ ሌላ። She is a player type of sh-it. . በአንድ ጊዜ አራት ወንዶችን እንደ ቼዝ ጠጠር እያገላበጠች ስታጫውት አንዱ ለሌላው እንቅፋት እንዳይሆን ያደረገችው Scheduling የሚገርም ነበር። እኔ ስልኩን "አንቺ ዝጊው.. አንተ ዝጋው" እየተባባልኩ በቪዲዮ ኮል ስሟገት፣ እሷ ግን ለካ በሌላ ስልኳ ሌላኛውን "አንተ ዝጋው.." እያለችው ነበር። ፍቅር ሳይሆን ለካ የኔትወርክ መጨናነቅ ውስጥ ነበርኩ..😁 በነገራችን ላይ.. እኔ በጣም ጠንቃቃ ነኝ። እንደ እኔ ተጠራጣሪ ሰው አልነበረም / አሁንም የለም። ማንንም አላምንም። መጨረሻ ላይ ይሄ ባህሪዬ ወይም ጥርጣሬዬ [ my Gut felling ] ነው እውነታው ላይ እንድደርስ ያደረገኝ። እኔ ጥላዬንም አላምንም። እሷን ግን እንዴት ላምናት እንደቻልኩና - ሙሉ ሀሳቤን እንደሰጠኋት ሳስብ ይገርመኛል። እንኳን ክፉ ድርጊት ሊያደርግ ያሰበን ሰው ይቅርና ያላሰበን ሰው ራሱ የምጠራጠር አይነት ሰው ነኝ። . ልባችሁ የሆነ ነገር ሲነግራችሁ አትናቁት። ልባችሁ የሚነግራችሁን አትናቁ። እኔ ተጠራጣሪው የሳሪስ ልጅ፣ በውበቷ ምክንያት እውነታው ተጋርዶብኝ Gut Fellingኤን አላዳመጥኩም ነበር። ቆንጆ ፊትና የተረጋጋ አንደበት ሁልጊዜም ቅንነትን አይወክሉም። አንዳንዴ እጅግ Calculated የሆነ አቀራረብ ከጀርባው የተቆፈረ ጥልቅ ጉድጓድ እንዳለው ማወቅ ነበረብኝ። እኔ ተጠራጣሪ ነኝ እያልኩ ግን የእኔ Gut feeling የሚሰጠኝን ምልክት ውበቷ ሸፍኖብኝ ነበር። ጥርጣሬ መጥፎ አይደለም። መጠርጠር ማለት ነፍስህ ራስህን እንድታድን የምትሰጥህ Alarm ማለት ነው። Infact በመጀመርያዎቹ ሳምንታት ያሳየችኝ እጅግ Calculated የሆነ - እንዲሁም የተጠና አቀራረብ አውሮኝ ነበር። . በውበቷ አሻፍዳኝ፣ በምላሷ አታላኝ የገባሁበት የ 6 ወር የፍቅር ህይወት በመጠኑም ቢሆን Scar ጥሎብኝ አልፏል። ፍቅር እውር ነው ይላሉ። እኔ ግን ሽፍድናዬ ነው ያሳወረኝ እላለሁ። ልጅቷ ቆንጆ ናት። በተለምዶ ቀይ የምንለው ወይም Light skinned የሆነው የቆዳ ቀለሟ - እንዲሁም ሰላም ተስፋዬን የሚመስለው መልኳ - ጨዋ ጨዋ የምትጫወተው ነገር - ምሁር ምሁር አንባቢ አንባቢ የሚያደርጋት ነገር - ይሄ ሁሉ ተደማምሮ አስምጣኝ ነበር። በኋላ ላይ ግን ሁሉንም ነገር ስደርስበት እኔ ብቻ አይደለሁም የተጣላኋት። እያንዳንዱ ስታወራቸው የነበሩ ወንዶችን ሰብስቤ እስካሁን እየተጫወተችብን እንደሆነ ነግሬያቸው አስረድቻቸው እነሱም አይንሽን ለአፈር ብለው ተለይተዋታል። . ታዲያ በመጨረሻ ሁሉንም መኪናዎች በአንድ ጊዜ ለማሽከርከር የሞከረችው Formula 1 ድራይቨራችን፣ በራሷ ስህተት Crash አደረገች። እያንዳንዱን ተሳፋሪ / ተበዳይ ሰብስቤ እውነታውን ሳስረዳቸው፣ ለካ ሁላችንም በአንድ ቃል ተገዝተን፣ በአንድ መስመር ስንታለል የነበርን ምስኪኖች ነን። ፍቅር እውር አይደለም ፤ ፍቅር አስተዋይ ነው ፤ እውር የሚያደርገን ግን የምናየው ውበት ሳያንስ የምንመኘው ህልም ነው። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ግን ይሄ ራሱ አንድ ትልቅ ትምህርት ነው። አሁን የገዛ ጥላዬንም ቢሆን ፋይዳ መታወቂያ / National ID ካላሳየኝ አላምነውም..! 😁 By Fraol Habesha @wegoch @wegoch @paappii
0
12
የተወደዳችሁ የወግ ብቻ ቻናል አባላት ነገ በወመዘክር ጊቢ ተገኝታችሁ መጽሐፌን ትመርቁልኝ ዘንድ ልባዊ ግብዣዬ ነው!!
የተወደዳችሁ የወግ ብቻ ቻናል አባላት ነገ በወመዘክር ጊቢ ተገኝታችሁ መጽሐፌን ትመርቁልኝ ዘንድ ልባዊ ግብዣዬ ነው!!
0