cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወግ ብቻ

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch@zefenbicha Creator @leul_mekonnen1

Show more
Advertising posts
19 529Subscribers
-724 hours
-257 days
-2730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"በቃኝ" ሳይሆን "በቃችሁ" ይበላችሁ! (አሌክስ አብርሃም) የቤተክርስቲያኗ መሪ ብስጭት ብለው ቢሯቸው ክስ ይዘው የተሰበሰቡትን ሴቶች እያናገሩ ነው! "ተው ብየ ነበር...ዘፋኙ ዘፈን በቃኝ ብሎ ሲመጣ ገና በሩን ሲያልፍ ማይክ እየሰጣችሁ ዘምር ስትሉ .... አርቲስቱ ሲመጣ ገና ከበር ተቀብላችሁ መንፈሳዊ ድራማ ስራ ስትሉ ተው አላልኩም? አካውንታቱ ገና ሲገባ ገንዘብ ያዝ ስትሉ ኧረ ይረጋጋ ትንሽ መንፈሳዊ ነገሩ ይጠንክር ቆይ አላልኩም ? አላልኩም ወይ እህቶቸ ? እናተ ምናላችሁኝ? ቤቱን በእልልታ እያቃጠላችሁ ምናለበት አላችሁኝ! ሰው በቃኝ ብሎ ቢወስንም በውሳኔ ብቻ ፈተና አይገታም! ይማሩ ይደጉ አልኩ! እና አሁን አገልጋይ ባሎቻችንን በዝሙት ጣለቻቸው የምትሏት እህታችን "ሴተኛ አዳሪነት በቃኝ" ስላለች ብቻ የወንድሞች አዳር ፆሎት ላይ ሻይ ታፍላ ብላችሁ መደባችኋት፤ ይሄንንም ተው ብየ ነበር! አሁን ምን አድርግ ነው የምትሉኝ? "ይሄ በቀላሉ የሚታይ አይደለም እንከሳለን" አለች አንዷ በቅርብ የዓለም ነገር በቃኝ ብላ የተቀላቀለች ሴት! መሪው ጠየቁ " እህቴ ወደዚህ ቤ/ክ ከመምጣትሽ በፊት ስራሽ ምን ነበር ?" "በሴቶች ጉዳይ ቢሮ ጠበቃ" አያችሁ ... በቃችሁ ካላለን በስተቀር በቃኝ ስላልን ከዓለም ጋር ያስተሳሰረን እትብት አይቆረጥም! ሰው ይወስናል ውሳኔ የሚጠናው እለት እለት በሚገነባው መንፈሳዊ ማንነት ላይ ነው! አሁን ጨርሻለሁ " ሁሉም በቁጣና በእልህ በየአፉቸው ተንጫጩ! በር ላይ የቆመው ቆፍጣና ጠባቂ ድንገት በሩን በርግዶ ገባና "የምን ብጥብጥና ሽብር ነው? እርምጃ ሳልወስድ በፊት ሁላችሁም ውጡ" አለ በቁጣ! በቅርቡ ወደምእመኑ የተቀላቀለ ፌዴራል ፖሊስ ነበር! ገና ከመግባቱ ጥበቃ አድርገውት! @wegoch @wegoch @paappii
Show all...
😁 50👍 36👏 5 4🤔 2
የማባልጋት ባለትዳር ነበረች ። ዋና ተግባራችን ወሲብ ነው ። የምንቀጣጠረው ለወሲብ ብቻ ነው ። የምናወራው ስለ ወሲብ ነው ። አንዳችን አንዳችንን የምንፈልገው ወሲብ ሲያምረን ነው ። አጠገቤ ሆና ባሏ ደውሎ ያውቃል: "ሰውዬሽ ደወለ" ብዬ ስልኳን አቀብያት አቃለሁ ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስታወራው እርቃኗን አትመስልም ነበር። ይገርመኛል ድድብናችን ። ነውራችን ስለተደጋገመ ተግባራችን ብልግና መሆኑ ተሰወረብን ። ቢሮዋ እሄዳለሁ፣ ቢሮዬ ትመጣለች ። ጓደኛዬ ቤት፣ እኔ ቤት፣ የሆነ ኮስመን ያለ ሰዋራ ቦታ ፣የሆነ ድብቅ ፅድት ያለ ስፍራ ፣ መኪና ውስጥ ... ብዙ ብዙ ቦታ ትመጣለች እንዋሰባለን ። የታሪካችን መነሻ እና መድረሻው ወሲብ ነው ። አንድ ቀን በደነገጠ: ተስፋ በቆረጠ ድምፅ "ባሌ አወቀብን" አለችኝ .....ደነገጥኩ ። ጠፋሁኝ ...ጠፋች ከአስራ ሰባት ቀን በኋላ ጓደኞቼ "ገኒ ሃዘን ላይ ነች፣ ሙሉ ከላይ እሰከታች ጥቁር ለብሳለች፣ ከስታለች" አሉኝ "ምን ሆነች?" አልኩ "ባሏ ሞቶባት ነው፤ ራሱን አጥፍቶ ነው የሞተው" አሉ። ስደነግጥ፣ ፊቴ ሲቀያየር ፣ እምባዬ ሲያመልጠኝ አዝኜለት ነው የመሰላቸው ። እኔ እንደገደልኩት አልጠረጠሩም ። የጥፋተኝነት ስሜት ሊገለኝ ሲል ማምለጫ መፅሃፍ ቅዱስ ገለጥኩ። "ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል " የሚለው ከሁሉም ጎልቶ ተነበበኝ ። .. ሰው ይዞ መውደቅ ፤ ማስተካከል የማይቻል አወዳደቅ ፣ ሲያስታውሱት የሚያስነክስ አይነት አወዳደቅ፣ እነሳለሁ የማይሉት አወዳደቅ ፣ ወድቄ ነበር የማይሉት አወዳደቅ። በግዜ ምክንያት የማይደበዘዝ አወዳደቅ ... እንደዚህ አይነት መውደቅ ሲ..ያ...ስ..ጠ..ላ !! ! By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
Show all...
😢 43👍 20👎 6 6😱 1
ኒላ ዘ መንፈስ 4 (አሌክስ አብርሃም) በክፍል ሶስት ትረካችን ኢትዮጵያዊቷ ፊደል እና በሂውማን ሄር ሰበብ በውስጧ የገባችው ኒላ የተባለች የሙት መንፈስ (የፀጉሩ ባለቤት ነኝ የምትል) ከብዙ ስድድብና አለመግባባት በኋላ ቀስ በቀስ እርስ በእርስ ማውራት እንደጀመሩ፤ ፊደል ነገሩ በቁጣና በሐይል የማይሆን ስለመሰላት በውስጧ ተቀምጣ እንደ አለቃ የምታዛትን ነጭናጫዋን ኒላን በፀባይ ለመያዝ እንደወሰነች አይተናል። ይባስ ብሎ ኒላ ገና በቀናት እድሜ ስለፊደልና መሰሎቿ ኢትዮጵያዊያን ባህሪ እየጠቀሰች ፊደልን መምከርና መውቀስ ጀምራለች! ቆሻሻ እንደማትወድ በመግለፅ የፊደልን ቤት አስፀድታታለች! ኒላ መንፈስ ናት፤ ከሁለት ዓመት በፊት ህንድ ውስጥ በ24 ዓመቷ በባቡር አደጋ የሞተች ሴት መንፈስ! ከሞቷ በፊት እጅግ የምትወደውና የምትሳሳለት ፀጉሯ «ሂውማን ሄር» ተብሎ ወደኢትዯጵያ ተላከ ! ፊደል የተባለች ታዋቂ ተዋናይት ገዝታ ተጠቀመችበት፤ በዛው ቅፅበት የኒላ መንፈስ በፀጉሩ በኩል የፊደልን ሰውነት ተጋርቶ መኖር ጀመረ! አሁን ፊደል ማለት አንዲት ሴት ግን በውስጧ ሁለተኛ መንፈስ የሚኖርባት ግራ የተጋባች ሴት ሆናለች! ቀጣዩን እነሆ! * * ** * «አንች ህንዳዊ ነሽ ፣ እንደነገርሽኝ ኢትዮጵያን ካወቅሻት ገና የተወሰኑ ቀናት ቢሆንሽ ነው! ግን ስለእኔም ይሁን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ልክ እዚህ ተወልዶ እንዳደገ ሰው ትናገሪያለሽ ! የምትይውን ነገር ሁሉ እንዴት አወቅሽው? » አለች ፊደል የኒላን ቁጣና ዘለፋ የተቀላቀለበት ምክር በዝምታ ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ! «ስለመንፈስ ምንም አታውቂም? ይሄ የሚበዛው ክፍሉ በማይረባ ዝባዝንኬ የተሞላ አዕምሮሽ ለእኔ እንደኮምፒውተር ወይም እንደስልክ ነው አሰራሩ! መንፈስ ሁኘ ውስጥሽ ስገባ ከህፃንነትሽ ጀምሮ እስከአሁን የተጠራቀመ ትዝታሽ ችሎታሽ ፣ባህሪሽ፣ ስሜትሽ ሁሉም ነገር አንች የምታውቂውና የምታስታውሸው ሁሉ እኔ «ሜሞሪ» ላይ ተጭኗል። ግን የምጠቀመው የምፈልገውን ሲሆን የምጠቀመውም በእኔ በራሴ መንገድ ብቻ ነው! የራሴ ህልውና አለኝ ፣የራሴ አስተሳሰብና ስሜት አለኝ፣ የራሴ ችሎታና አረዳድ አለኝ፣ የሌለኝ አካል ብቻ ነው! አካሌ እዛ ህንድ ተቃጥሎ አመዱ ወንዝ ላይ ተበትኗል! ከእንግዲህ እነዛ ውብ የሰውነት ክፍሎቸ ዳግም አይመለሱም! ያ ውብ ፈገግታየ የለም ፣ ስለዚህ ፈገግታሽን እጋራለሁ፣ እነዛ ውብ እግሮቸ እና እጆቸ የሉም ስለዚህ የአንችን እግርና እጅ እጋራለሁ ፣ ከንፈሮቸ የሉም የአንችን ከንፈሮች እጋራለሁ. . . ለዛ ነው እንደአሳማ የሚያገሳና እንደውሻ የሚናከስ ትንፋሹ ጋን ጋን የሚሸት ወንድ እንዲስምሽ የማልፈልው! ሁለታችንም ያልተስማማንበት ወንድ አጠገብሽ አይደርስም! ምክንያቱም ሰውነትሽ ሰውነቴ ነው! ሂሂሂሂሂ ስንት ነገር አለ! የተረፈኝ ብቸኛ መታሰቢያ ይሄ አንች አናት ላይ የተቀመጠው ፀጉሬ ብቻ ነው! ይሄ ፀጉር ሁሉ ነገሬ ምድር ላይ የቀረኝ ብቸኛ መታሰቢያ ነው። ጓደኞቸ የምወዳቸው ቤተሰቦቸና ነፍሴን የምሰጥለት ፍቅረኛየ ሁሉም ተረት ናቸው አሁን!ለዘላለም አብረውኝ አይኖሩም! ህይዎት እንዴት አጭር ናት? " አለች ባዘነ ድምፅ! «ፀጉርሽ እንዴት ተረፈ ግን?» በቤተሰቦቸ እምነት ሴት ልጅ በህይዎት ዘመኗ ሁለት ጊዜ ፀጉሯን ለምናመልክበት ቤተ መቅደስ ትሰጣለች፣ ልክ እንደስዕለት ነው! አንድ ከማግባቷ በፊት፣ ትዳሯ እንዲባረክ (ይሄ በፍላጎት የሚደረግ ነው) ሁለተኛው በወጣትነቷ ከሞተች! እንደገና ስትፈጠር በመልካም ሰው ወይም እንስሳ እንድትፈጠር! እኔ ግን አንች ውስጥ ተፈጠርኩ ሂሂሂ! ምናልባት ያኔ ፀጉሬን ስቆረጥ ቅር ስላለኝ አምላካችን አዝኖብኝ ይሆናል። ልክ እናተ አስራት መባ ስጦታ እንደምትሉት ነው! በበሃላችን ፀጉር የመጨረሻው የሴት ልጅ ክብር አንዲት ሴት ለምታመልከው ጣኦት ፀጉሯን መስጠቷ ክብሯን ኩራትና ፀጋዋን ሁሉ ለአምላኳ የመስጠት ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጉም አለው! ወይም ከቸገራት ፀጉሯን ሸጣ ኑሮዋን ልትደጉም ትችላለች! ማንም ሴት ቸግሯት ፀጉሯን ስትሸጥ ደስ ብሏት አትሄድም ከእንባ ጋር ነው! «ቤተመቅደሱ ፀጉሩ ምን ያደርግለታል?» አለች ፊደል ቤተመቅደሱ ፀጉሩን ሰብስቦ ሂውማን ሄር ለሚያዘጋጁ ካምፓኒዎች ይሸጠዋል ! ካምፓኒዎቹ አዘጋጅተው ወደመላው ዓለም ይሸጡታል! የእኔም ፀጉር በዚሁ መንገድ ነው የሚመጣው! እኔ የመጀመሪያውን ፀጉሬን በሰጠሁበት ቀን ስድስት ሺ ሴቶች ሰጥተዋል። ወደሁለት ቶን ፀጉር ማለት ነው! ሁለት መቶ ኩንታል ማለት ነው! ይሄ አንዲት ትንሽ ከተማ ላይ ብቻ ነው፤ በመላው ህንድደግሞ ብዙ ሚሊየን ኩንታል ይሆናል! አሁን የገረመኝ ከዛ ሁሉ ጉድ ፀጉር ስንት አገር እያለ እንዲህ አይነት ከአመት አመት ፀሐይና አቧራ የማይለየው፣ ዜጎቹም ግራ የተጋቡበት አገር መንቃቴ ! ይባስ ብሎ እንደአንች አይነት በዚህ ዕድሜዋ እንደ 11 ዓመት ልጅ የምታስብ ሴት ውስጥ መኖሬ . . .» አለች። ፊደል ፈገግ አለችና «ግንኮ በዕድሜ እበልጥሻለሁ ለምን አታከብሪኝም ኒላ?» «እሱማ አገራችሁም በዕድሜ ስንቱን አገር ትቀድማለች ? ግን አሁንም ገና ትላንት እንደተመሰረተ አገር እንደተወዛገበች እንደተደናበረች ነው! ጉራ ብቻ! ገና ጡጦ ላይ እኮናችሁ! የሶስት ሽ ዓመት ሚሚ ! » ፊደል ዝም አለች! አገር ጅኒ ጃንካ ይደክማታል። ፊደል ቀኑን ሙሉ ከተማ ወጥታ ልብስና አስቤዛ ስትገዛ ውላ ተመለሰች! ኒላ ልብስ ታመራርጣት ነበር። በአንዳንድ ምርጫቸው ስለማይጋቡ መጨቃጨቃቸው አልቀረም! ፊደልን ከሩቅ የሚያይዋት ሰዎች «ለየላት» ይላሉ! በተቻላት መጠን ዝም ለማለት ብትሞክርም የኒላ ጭቅጭቅ ዝም የሚኣስብል አልነበረም። እንደውም በአንድ ቀሚስ ከለር ምርጫ ስላልተግባቡ ወደቤት ሲመለሱ ተኮራርፈው ነበር። ፊደል ሻዎር ወስዳ ራት በልታ ወደምኝታዋ ስትሄድ ኒላ ድንገት ወሬ ጀመረች «እኔ የምልሽ ፊደል . . .ለምን የፌስ ቡክ አካውንት አትከፍችም ?» "አለኝ ምን ያደርግልኛል! " ለአንች ማን አለሽ ? እና ለማን ነው ? ለእኔ ! እንዴ ጭራሽ ? ምን ችግር አለው? በስሜ ክፈችልኝ ጓደኞቸን አገሬን ቤተሰቦቸን ማየት እፈልጋለሁ! የድሮ አካውንቴን ባስብ ባስብ ማስታወስ አልቻልኩም! ይመስለኛል የእኔን ሜሞሪ ፕሮሰስ የሚያደርገው የአንች አዕምሮ ማስታወስ ላይ ትንሽ ደከም ያለ ነው መሰል ሂሂሂ ! እና ፌስቡክ አካውንት ያለው መንፈስ ልትሆኝ? አለች ፊደል ነቆራዋን እንዳልሰማ አልፋ! በነገሩ ግርምት ተፈጥሮባት ነበር። አዎ! ክፈችልኝ! በዛውም የፍቅረኛየን የእኔን የድሮ የጓደኞቸን ፎቶ አሳይሻለሁ! ፊደል ጉጉትና ፍርሃት ተቀላቀለባት ! ግን ጉጉቷ አሸነፋት! ይች ከሁለት አመት በፊት ሞትኩ የምትል ሴት ምን ትመስል ይሆን? እውነት ናት አንደሰው ምድር ላይ ኑራ ነበር? ጓጓች ! «ከፈለግሽ ምን ቸገረኝ» አለችና ወደማንበቢያ ጠረጴዛዋ ሄደች! ውስጧ ግን የሆነ የጅል ስራ እንደምትሰራ እየነገራት ነበር። ላፕቶፗን ከፈተችና «እሽ በምን ስም ልክፈትልሽ? » ኒላ N I L A ፊደል ስሙን አስገባች ! ድንገት ግን ኒላ በሳቅ ፍርስ አለች ! ሂሂሂሂሂ ሂሂሂሂሂሂ ካካካካካኣ ምን ያስቅሻል?
Show all...
👍 23 9🔥 1🤔 1
«ታይፕ አደራረግሽ ነዋ! ፊደሎቹን እያፈላለግሽ ነው የምትጫኝያቸው… አያቴ ነበር እንደዚህ የሚፅፈው . . . ይገርማልኮ አሁን አንች የተማርሽ ዘመናዊ ታዋቂ የፊልም ተዋናይ ነሽ! ታይፕ ማድረግ እንኳን በወጉ አትችይም! ይመስለኛል ታይፕ አደራረግ ወደፊት ማስተማር ሳይኖርብኝ አይቀርም! ፊደል በስጨት አለች « አሁን የጀመርነውን እንጨርስ ወይስ ልተኛ ?» አለቻት በቁጣ ! «አትቆጭ ፊደል! ኢትዯጵያዊያን አለመቻላችሁ ሳይሆን አትችሉም መባላችሁ ያበሳጫችኋል! ቀኑን ሙሉ ስልክና ኮምፒውተር ላይ አቀርቅረሽ እየዋልሽ ታይፕ ማድረግ እንኳን በስርዓት አለመቻልሽ ሊያስቆጭሽ ነበርኮ የሚገባው! ትልቅ እውቀት መሆኑ ነው? አለች ፊደል ነውና! እኔ በአስራሁለት ዓመቴ ነው ጥንቅቅ አድርጌ ኪቦርድ አጠቃቀም የቻልኩት «የራስሽ ጉዳይ ወሬ አለብሽ. . . በነገራችን ላይ እየረዳሁሽ መሆኑን አትርሽ » «ሂሂሂሂሂ ሂጅ ካሜራ ማኖችሽን ጥሪና "ኒላን እየረዳኋት" ብለሽ ነገ ለአድናቂዎችሽ እዩልኝ በይ! . . . እሽ እያሳደድሽ የአባቴን ስም ፃፊ! እንዲህ እያሉ ለኒላ አዲስ አካውንት ከፈቱ! በመጨረሻም ኒላ በምትነግራት መሰረት የኒላን ቤተሰቦች አካውንት ከፈቱ ! ኒላ መጀመሪያ ያየችው የወንድሟን አካውንት ነበር . . . እንደነፍሷ የምትወደውን ወንድሟን ! ፕሮፋይሉ ላይ «ውቧ እህቴን ካጣኋት ሁለት ዓመት ሆነ እንወድሻለን» ከሚል የእንግሊዝኛ ፅሁፍ ስር እጅግ ውብ የሆነች ሴት ፎቶ ይታያል! ፊደል ልቧ ስንጥቅ አለ! ካሰበቻት በላይ ቆንጆ ሴት ነበረች ! ፀጉሯ በቀኝ ትከሸዋ በኩል አልፎ ፊት ለፊት እየተዘናፈለ ይወርድና ተፋዋ አካባቢ ድረስ ቁልቁል ወርዷል! ፈገግታዋ ሲበዛ ውብ ፊቷን የበለጠ አስውቦታል! የለበሰችው ደማቅ ቀይ የህንድ ባህላዊ ልብስ ድምቀቷን አጉልቶት ፎቶ ሳይሆን ህያው ስጋና ደም ያላት ፍጥረት አስመስሏታል! «አንች ነሽ ? » አለች ፊደል ! ኒላ ግን ማልቀስ ጀምራ ነበር! ፊደል በዝምታ ቆየች! ኒላ ለቅሶዋን አቁማ ሌላ ስም ነገረቻት! ፊደል ስሙን አስገብታ ስትከፍተው አንድ መልከመልካም ወጣት ከአንዲት ሴት ጋር በባህላዊ የሰርግ ልብስ አምሮ የሚታይበት የሰርግ ፎቶ ስክሪኑን ሞላው! ከጎኑ ቆንጆ ሚስቱ በፈገግታ ቁማለች! ኒላ « ይሄ ቀልድ ወይም ህልም መሆን አለበት » አለች በቀስታ ! ከዚያም ድንገት «ውሻ የውሻ ልጅ » ብላ ጮኸች በጩኸቱ የፊደል ሰውነት ተናወጠ! «ምንድነው ኒላ ?» አለች በፍርሃት ! «ፍቅረኛየ፣ ባቡር ላይ አብረን ሞትን ያልኩሽ ፍቅረኛየ ! ገና ከሞትኩ በሁለት ዓመቴ ጓደኛየን አግብቶ ነዋ! ይሄው አይታይሽም ይች ውሻ ጓደኛየ ናት . . . ጓደኛየ ! የራሴ ጓደኛ » ፊደል ግራ ገባት « ቆይ ባቡሩ ላይ ሞተ አላልሽኝመረ . . .? » «እኔጃ እኔ ስለሞትኩ የሞተ ነው የመሰለኝ ! አላውቅም . . . ምናልባትም ውሻ ቶሎ አይሞትም » ኒላ ዝም አለች ! ረዥም ዝምታ ! ኒላ አለች ፊደል የምታደረገው ግራ ገብቷት መልስ የለም . . . ኒላ ትሰሚኛለሽ ? ዝምታ ! በቀስታ ላፕቶፑን ዘግታ ወደምኝተዋ ሄደች! ዝምታው ያስፈራ ነበር። ይቀጥላል! @wegoch @wegoch @paappii
Show all...
36👍 24👏 6🤬 1
ትዳር ይሁን ስልጣን ሐይማኖት ይሁን ማህበር ከነሸክማችሁ ስለምትገቡ እጣ ፋንታችሁ የሌሎችን ሸክም ማቅለል ሳይሆን ራሳችሁም ሸክም መሆን ነው። ራሳችሁ እንኳን ወደራሳችሁ የምትቀርቡበት አንድ ቀጭን መንገድ አድናቆት ብቻ ነው! ሰው በዚህ ልክ እንዴት ከራሱ ጋር ይጣላል በቡድሃ?! ይቀጥላል! @wegoch @wegoch @paappii
Show all...
41👍 15😁 6
ኒላ ዘ መንፈስ 3 (አሌክስ አብርሃም) የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት አስፈሪ እና ግራ አጋቢ ነበሩ ለፊደል፤ ከባድ ሆነውባት አለፉ! እንቅልፍ ማጣት ግራ መጋባት ...በየቀኑ ፍርሃቷ ቀስ በቀስ እየለቀቃት ቢሄድም መልመድ ያልቻለችው አንድ ነገር መታዘዝን ነበር። ውስጧ ተደላድላ የተቀመጠችው የተረገመች ኒላ ደግሞ ማዘዝ ነፍሷ ነው። መታዘዝ ነፍስ ስጋና መንፈስን ለአዛዢ ማስገዛት ነው! ፊደል ከልጅነቷ በነፃነት ያደገች ልጅ ናት።ከፍ ስትል ከተማሪ እስከአስተማሪ፣ ከመንደር ጎረምሳ እስከሚጠጓት ወንዶች ለውበቷ ተንበርክከው ስትጠራቸው አቤት ስትልካቸው ወዴት ባይ አሽከሮቿ ነበሩ! አሞጋሿ ብዙ ነበር! ዞር ስትል የሚያሟት ፊት ለፊት ይሽቆጠቆጡላታል። ሌሎችን በአይን እይታ ብቻ ቁጭ ብድግ የምታደርጋቸው ፊደል ዛሬ ምንነቷ ለማይታወቅ መንፈስ በእሷ አባባል«ገረድ» ሁናለች። ለምሳሌ ፊደል በተፈጥሮ ውበቷም ይሁን በሽቅርቅር ፋሽን ተከታይነቷ ሊነኳት እንኳን የምታስፈራ ንፁህና ቆንጆ ትሁን እንጅ ቤት ውስጥ ዝርክርክ ነበረች። የበላችበት ዕቃ ለቀናት ሊከመር ልብሷ እዚህና እዛ ተዝረክርኮ ለሳምንታት ሊቆይ ይችላል። ኒላ ደግሞ ፈፅሞ ከዚህ ተቃራኒ ናት። አይደለምና መዝረክረክ ፊደል በራሷ ቤት ከነጫማዋ ምንጣፍ ላይ ከወጣች ታብዳለች! «አንች የማትረቢ ቆሻሻ . . .» ብላ ነው የምትጀምረው! አንድ ቀን ጧት (ሌሊት ማለት ይቀላል ከጧቱ አስር ሰዓት ) ፊደል በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ እንዳለች በሚያስበረግግ ጩኸት «ተነሽ» አለቻት ኒላ !ጩኸቱ ፊደልን አስበርግጎ ቀኑን ሙሉ ለእራስ ምታት ዳረጋት ! ቢሆንም ፊቷን እንዳጨፈገገች ተነስታ አልጋዋ ጫፍ ላይ ተቀመጠች! «ዛሬ ይሄን ቤት እናፀዳለን» «እንዴ . . .» «አፍሽን ዝጊ ! እንደዚህ የተግማማ ቤት ውስጥ ልኖር አልችም! ገና ለገና መንፈስ ነኝ ታይፎይድና ታይፈስ አይዘኝም ብየ ዝም ልል አልችልም! ድብርት ራሱ ከታይፎይድ እኩል ነው! ቆሻሻ አልወድም ነገርኩሽ! ቆይ ለመሆኑ የምትኖሪው ለእነዚህ ተጎልተው የአንችን የማይረባ ፎቶና አርቲ ቡርቲ ፊልም ለሚያዩ ድንዙዞች ነው ወይስ ለራስሽ? ውጭ አፈር አይንካኝ ትያለሽ ቤትሽ ግን በክቷል ለራስሽ ክብር የለሽም ? በዚህ ቤት ነው እንግዳ የምንጋብዘው? » «የምን እንግዳ ነው ! እኔ ማንንም እቤቴ አልጋብዝም. .» «እኔ እጋብዛለኋ» «ምን. . .?» «እ ን ግ ዳ እጋብዛለሁ!! «የምን እንግዳ ነው በቤቴ የምትጋብዥው ? አልበዛም?» « ቤ ታ ች ን በይ!» «አልልም ቤቴ ነው! » «ቤታችን ነው» ፊደል ደከማት ! መንፈስ ግን አይደክመውም ይሆን ስትል አሰበች! የዛን ቀን ለዓመታት ያልተፀዳ ቤቷን ለማፅዳት ስትፈጋ ዋለች!ከኪችን እስከሸንት ቤት ከበረንዳ እስከግቢው ወገቧ እስኪንቀጠቀጥ አፀዳች! ኒላ ዘና ብላ ታዛታለች! ትሰድባታለች ልክ የባሪያ አሳዳሪ ነበር የምትመስለው! » ራሷን እስክትስት ቢደክማትም ውጤቱ ለራሷ ገረማት። በዚህ ሁኔታ አንዴ ሲጣሉ ሌላ ጊዜ ሲኮራረፉ ቀናት ነጎዱ! ይች ግራ የገባት መንፈስ እንደባሪያ ያዘዝኩሽን አድርጊ ስትላት ያለመደችው መታዘዝ ከእልህ ጋር እየተቀላቀለ ግራ የገባት ልጅ አደረጋት! ቢሆንም ይች ወፈፌ ከታዘዘቻት የማትቆጣ እንደውም ትሁትና የጓደኝነት መንፈስ ያላት ፍጥረት መሆኗን ተረድታለች። አንዳንዴ ለቀናት ድምፅዋን ስለምታጠፋ ትታት የሄደች ይመስላት ነበር። ይሁንና ስሟን ጠርታ አለሽ ወይ ማለት ትፈራለች!አብረው በቆዩበት ጊዜ አንዳንድ ባህሪዎቿን ማወቅ ችላለች። እና በፀባይ ልትይዛትና እስከወዲያኛው የምትሸኝባትን መንገድ ለመፈለግ ወሰነች! አንድ ቀን እንዲሁ ሲነታረኩ ውለው እንደተኮራረፉ ፊደል ለመጀመሪያ ጊዜ መንፈሷን በስሟ ጠራቻት «ኒላ » «ምን ፈለግሽ?» «ይቅርታ ስላስቀየምኩሽ . . . ግራ ገብቶኝ ነው » ኒላ ዝም አለች! «እንደምታይው አድናቂ እንጅ ጓደኛም ዘመድም የለኝም! ብቸኛ ነኝ! የሚመጡት ሁሉ ወይ እውቅናየን አልያም ሴትቴን ፈልገው የሚመጡ ናቸው ጥልቅ ብቸኝነት ውስጥ የምኖር ብቸኛ ሴት ነኝ! እባክሽ ተረጅኝ» « የነገርሽኝ ነገር አያሳዝንም. . .እዛ ሂጅና አብራሽ የምታለቃቅስ ሴት ፈልጊ! ልፍስፍስ ሴት አልወድም!ኢትዯጵያዊያን ተያይዘን እንውጣ ከሚላችሁ ይልቅ ሙሾ የሚያወርድላችሁን አስለቃሽ ነው የምትወዱት! አንች ራስሽ ራስሽን የምታደንቂው መስተዋት ፊትኮ ነው! የራስሽ እንኳን ጓደኛ አይደለሽም! ማንም የሚገዛሽ ለገበያ ያቀረብሽውን ነው! መቀመጫሽን ያቀረብሽለት አለም አዕምሮሽን ሊመርጥ አይችልም! ምኔን አይተው ተጠጉኝ ከማለትሽ በፊት ምንሽን አሳየሻቸው? ታዋቂ ነሽ እንጅ አያውቁሽም! ራስን ሸፍኖ እወቁኝ እያሉ ማልቀስ አለ እንዴ? ኪንኪ ፀጉርሽን እንኳን በእኔ ፀጉር ነው የሸፈንሸው! አየሽ የቤት ኪራይ ባልከፍልም በፀጉሬ የመጣልሽን በረከት ተካፋይ ነኝ! ሸበላ ወንድም ከመጣ ተካፋይ ነኝ ሂሂሂሂሂሂሂ! በነፃ አይደለም አንች ውስጥ የምኖረው ሰው ለእናት አገሩ እጁን እግሩን አይንና ሌላ አካሉን እንደሚሰጥ ፀጉሬን ሰጥቸሻለሁ፤ ፀጉር አካል ነው! አፍንጫሽ ላይ ያለው ዲኤን ኤ ፀጉርሽም ውስጥ አለ! ስለዚህ ጡረታ የምወጣው አንች ውስጥ ነው» ፊደል በዝምታ ስትሰማት ቆየች! ኒላ ቀጠለች «ለመሆኑ ሶሻል ሚዲያው ላይ ስንት ተከታይ አለሽ?» «ወደአንድ ሚሊየን. . .»አለች ፊደል! «ለዚህ ሁሉ ተከታይሽ ምን ሰጠሽው? ፎቶ ፎቶ አሁንም ፎቶ . . . ፎቶሽ ምንሽን ያሳያል ? ቂ . . .ሽን ፣ ጡትሽን ፣ እግርሽን ፣ ጥፍርሽን . . . ጥፍራም! ባለፈው ፊልምሽን ልታስመርቂ ስትዘጋጅ ፀጉር ቤት ስንት ሰዓት ቆየሽ . . . አምስት ሰዓት ፣ ማሳጅ ቤት ሶስት ሰዓት ልብስ ስትለኪ ስታወልቂ አራት ሰዓታት ! ቢያንስ በየሳምንቱ «ራስን መጠበቅ» በሚል ሰበብ እድሜሽን መስተዋት ፊት እንደሽንኩርት በመላጥ የምታጠፊውን ጊዜ አስቢ! በዚህ መሃበረሰብ ውስጥ የአንች ቂ . . . ጤና ጣቢያ ነው ትምህርት ቤት? ቁንጅና ጥሩ ነው ! ግን ትንሽ ክፍተት ትንሽ መስኮት ነገር ከቁንጅናሽ አልፈው ወደአንች ሊገቡ ለሚፈልጉ ተይላቸው! ድፍን ቆንጆ ብቻ አትሁኝ!በርና መስኮት የሌለው ደረጃ የሌለው ውብ ህንፃ ጥቅሙ ከውጭ መታየትና ለዙሪያው አዳማቂ መሆን ብቻ ነው!ሰዎች እንዲያርፉብሽ ውስጥሽ ትንሽ ወንበሮች ይኑሩ! እንደዛ ስልሽ እንደመሰል ጓደኞችሽ ነጠላሽን አደግድገሽ ለበዓል ካሜራ ፊት ድሆችን አሰልፈሽ ብሉልኝ ጠጡልኝ የምትይውን የሚያቅለሸልሽ «በጎ ስራ» አይደም! እሱ በጎ ስራ ሳይሆን «በጎ አድናቆት» ነው ! ምግብ መፀወትሽ እውቅናና አድናቆት ተመፀወትሽ! የለማኝ ሰልፍ ውስጥ ነሽ! ተደነቅሽበት ተወደሽበት ግን ባዶ ነሽ! ለራስሽ ስምና ዝና የምትቃርሚበት በጎ ስራ የስም ሜካፕ ነው! ራስሽን ብቻ ነው የሚያሳምረው! አንድ ቀን ሲዘንብ ታጥቦ አስቀያሚነትሽ ያገጣል! «እስኪ ስለራስሽ ንገሪኝ » አለች ፊደል ትንሽ ጨዋታውን ለማስቀየር! ትችት አትወድም! «ወሬኛ አትሁኝ ! እድሜ ልክሽን ስለሌሎች ሰምተሻል ፤አሁን ቢመርም ስለራስሽ መስሚያሽ ነው!. . .ለምንድነው ግን ኢትዯጵያዊያን አብዝታችሁ ስለሌሎች መስማት የምትወዱት? ራሳችሁን ትፀየፋላችሁ ወይስ በራሳችሁ ታፍራላችሁ?» ፊደል ዝም አለች! «ከድህነታችሁ በላይ አስከፊው ባህሪያችሁ ከእራሳችሁ መራቃችሁ ነው! ዙሪያችሁ ገደል እና ሚስጥር ነው . . .
Show all...
👍 38 21
ፊደል ድንገት «ግን አማርኛ እንዴት ቻልሽ ?» አለቻት! ከጠየቀቻት በኋላ በመጠየቋ ተሳቀቀች!እንደሰው እውቅና መስጠትና ማናገር አልፈለገችም ነበር። «አማርኛ ምንድነው?» «እንዴ ይሄ የምታወሪበት ቋንቋ ነዋ» «እኔ የማወራው ሂንዲ ነው፤ አንችም የምታወሪው የሚሰማኝ ጥርት ባለ ሂኒዲ ቋንቋ ነው! ሲጀመር ደግሞ እኔ አላወራም! ለማውራት ከንፈር ምላስ ያስፈልጋል. . . መንፈስ ነኝ ከንፈርም ምላስም የለኝም ! እኔ የማስበውን የአንች ከንፈርና ምላስ ነው የሚያወራው ! አእምሮሽ አድርገሽ እይኝ! አእምሮ አያወራም ያስባል ወደከንፈር ትዕዛዝ ይልካል! በሌላ አባባል መስተዋት ፊት ቁመሽ ስናወራ ብትመለከች የእኔንም የአንችንም ወሬ የሚናገረው የአንችው አፍ ነው! » «እ?» አለች ፊደል የበለጠ ጭንቀት ውስጥ ገብታ! ነገሩ ሁሉ ተገለባበጠባት! የሻወሩን የብረት ድጋፍ ይዛ እንደመቆም አለች። «በይ አሁን እንውጣ . . . ተዘፍዝፈሽ ልታድሪ ነው እንዴ?» «ግን ለምንድነው ስድብ የምትወጅው? » « ስድብ ? ትንሽ ቁጡ ነኝ ! በተለይ ድድብናን አልታገስም. . . ለመሆኑ የስሜ ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ይገባሻል? አናላ ነው ስሜ . . .አናላ ማለት እሳት ማለት ነው! እሳት! እኔ ላይ እንደእንጨት አትድረቂ ትቃጠያለሽ !! ገለባ አትሁኝ ትቃጠያለሽ! ከገለባ ሰዎች ጋር አትጠጊ ውስጥሽ ያለሁት እሳት ነኝ እበላቸዋለሁ! በተለይ ፀጉሬን ማንም ካለእኔ ፈቃድ ከነካ እንደላስቲክ ነው የማቀልጠው! እኔ አናላ ነኝ ፤ አናላ ዘ መንፈስ! ከዚህ በኋላ ይሄ ሰው የሚያጨበጭብለት ከንቱ ሰውነትሽ እንደክብሪት ቀፎ ነው ! ውስጥሽ እሳት የሆንኩ እኔ አለሁ! አብረን አመድ መሆን አልያም የምለውን እያደረግሽ መኖር ነው ምርጫሽ! ይቀጥላል! @wegoch @wegoch @paappii
Show all...
26👍 20🤔 2
ኒላ ዘ መንፈስ 2 (አሌክስ አብርሃም) በክፍል አንድ ትረካችን አናላ ወይም በቁልምጫ ስሟ ኒላ የምትባል ህንዳዊት ሴት ከፍቅረኛዋ ጋር ይጓዙበት የነበረ የመንገደኞች ባቡር ሐዲዱን በመሳቱ ትሞታለች። ይች ሴት በዘመድና ወዳጆቿ ዘንድ የምትታወቀው በውብ ጥቁር ፀጉሯ ሲሆን እርሷም ለፀጉሯ ያላት ፍቅር እና እንክብካቤ የማምለክ ያህል ነበር። ምን ያደርጋል ያ አደጋ ነፍሷን ነጠቃት። ሰው ሟች ነው! ቆንጆም ሴት ትሁን ጀግና ወንድ ማንም ከዚህ ህግ አያልፍም። ይሁንና ኒላ ለራሷም ባልገባት ሁኔታ ከሁለት ዓመት በኋላ እዚች ምድር ላይ ያውም ኢትዮጵያ ፣ ያውም ፊደል የተባለች ታዋቂ ኢትዯጵያዊ የፊልም ተዋናይት ውስጥ መንፈስ ሁና ተከሰተች። ኒላ ራሷ እንደምትለው ለሁለት አመት የት እንደነበረች ምን እንደነበረች አታውቅም! የምታውቀው ነገር ተዋናይቷ የገዛችው «ሂውማን ሄር» የኒላ እንደነበርና ተዋናይቷ ፀጉር ጋር ሲነካካ ለሁለት ዓመት ሙት የነበረ ፀጉሯ ህይዎት እንደዘራ፣ ወዲያው በፀጉሩ በኩል ሙሉ መንፈስ ሁና ሰውነቷ ውስጥ እንደገባች ነው። ቀጣዩን እነሆ . . . ** * **** የዛን ቀን ምሽት ፊደል መተኛት አልቻለችም! በፍርሃት አልጋዋ ላይ ተቀምጣ ሳታቋርጥ ውስጧ ተቀምጣ የምታወራውን ኒላ ግራ በመጋባት ታዳምጣለች። «ተነሽ ገላችንን እንታጠብ፤ በላብ ጠረን ገደልሽኝኮ » አለች ኒላ! ፊደል አሁንም እያላባት ቢሆንም ምን ትሁን ምን ትፈልግ የማታውቃት እንግዳ ፊት ልብሷን ማውለቅ ፈራች! በቀስታ «የእኔ እህት ለምን ወደምትሄጅበት አትሄጅልኝም ? ፀጉርሽንም ውሰጅው አልፈልግም በጣም እያስጨነቅሽኝ ነው!» አለቻት! « አንች የማይገባሽ ደደብ ሴት ነሽ ልበል? ነፍስሽን ከስጋሽ «ተለይተሽ ሂጅ» ማለት ትችያለሽ? ራሴን እንዳጠፋ እየጠየቅሽኝ ነው? በቃ ይሄ የአንች ሰውነት የእኔም ነው! ፈልጌሽ አልመጣሁም! ደህና ያረፈ ነፍሴን አምጥተሽ የቀሰቀሽው አንች ነሽ! እንዴት እንደገባሁም እንዴት እንደምሄድም አላውቅም ! ያለን አማራጭ ተከባብረን አብረን መኖር አለበለዚያ ተያይዘን ወደመቃብር መውረድ ነው! ይብላኝ እንጅ ላንች፣ መሞት እንደሆነ ለእኔ ብርቄ አይደለም. . . ይልቅ ተነሽ እንታጠብ እንዴት ነው ላብ በላብ የሆነው በቡድሃ! ለሞላ ሰውነት እዚች ውስጥ ታስቀምጠኝ! » አለች በቁጣ! ፊደል እየተንቀጠቀጠች ወደሻወር ሄደች! ልብሷን በፍርሃት . . . በቀስታ አወላለቀች! የሻወሩን ውሃ በቀስታ ከፍታ ሙቀቱን በእጇ «ቸክ » ካደረገች ኋላ በደንብ የሞቀ ውሃ እስኪወርድ ሰውነቷን በእጇ ከልላ ዳር ላይ ቆመች! ጠባቡ ሻዎር በእንፋሎት መታፈን ሲጀምር በቀስታ ወደሚወርደው ውሃ ራመድ አለች! «እንዴ ፀጉርሽን ሳትሸፍኝው ልትገቢ ባልሆነ?» አለች ኒላ ! በጩኸት! «እረስቸው ነበር » ብላ ሮዝ ቀለም ያለውን የፀጉር መሸፈኛ የፕላስቲክ ቆብ አጠለቀች ! እና የቀኝ ትከሻዋን አስቀድማ ወደውሃው ገባች! ውሃው የፀጉር መሸፈኛው ላይ ሲያርፍ ዝናብ የቆርቆሮ ጣራ ላይ የሚፈጥረው አይነት ድምፅ ይፈጥራል! ወይም እንደዛ ይመስላታል ፊደል። «ኡኡኡኡ አንች የማትረቢ ሴት አብደሻል? ወደዛ ውጭ ! » ብላ ጮኸች ኒላ! ጩኸቷ ጎረቤት ሁሉ ይሰማ ነበር! «እንዴ ምን ሁነሻል? ታጠቢ አላልሽኝም እንዴ?» ብላ ዘላ ወጣች! «እና ታጠቢ ማለት ተቀቀይ ነው?እንደዚህ በተፍለከለከ ውሃ የምትቀቀይው ድንች ነሽ? ለነገሩ ከአንች ድንች ይሻላል ከንቱ! በዚህ አይነትማ ፀጉሬን ከጥቅም ውጭ ነው የምታደርጊው. . . ቆይ ቆይ ለመሆኑ ተምረሻል? ወይስ ይሄን መቀመጫሽን እያገማደልሸ ብር የሚያሳይሽ ማንም እከካም ቦርጫም ባለትዳር ጋር መተኛት ብቻ ነው እውቀትሽ?» « ለምን ስትናገሪ ስርዓት አይኖርሽም ? እኔ ሴት አዳሪ አይደለሁም፣ የተከበርኩ የፊልም ባለሙያ ነኝ! ለከት ይኑርሽ ! መንፈስ ሁኝ ፀጉር የራስሽ ጉዳይ ነው! . . . » ብላ ቱግ አለች ፊደል! እንባ እየተናነቃት! «ሂሂሂሂሂሂ ! የተከበርኩ? ማነው የሚያከብርሽ? ሂሂሂሂ ያች ጓዝ ሚስቱ ስትደብረው ነው አንች ጋር እየመጣ የሚዝናናው ትራክተር የሆነ ሰውየ ?! ወይስ ያ ካሜራ ፊት እንደበቀቀን የሚጮህ ዳይሬክተር ተብየ? ስሙንማ ይዞታል!የታባቱ ተምሮ ነው ዳይሬክተር የሆነው? የዩ ቲዮብ ምሩቅ ወይስ "ዳይሬክተር" የዳቦ ስም መሰለው እናቱ የምታወጣለት? አንችም "ዳይሬክተር አወጣኝ" እያልሽ ቀሚስሽን ትነሰንሻለሽ! ልብሽ እብጥ ብሏል! "እንዴዴዴ" "የምን እንዴ ነው! ያም ቦርጫም እከካም በገንዘቡ ነው የገዛሽ ፤እንደትራክተር! ትራክተር እንኳን ያርሳል፣ አንች በጀርባሽ ተነጥፈሽ የሰው ባል አምሮት መወጫ ከመሆን ውጭ ምን ጥቅም አለሽ? ፊልም ትላለች እንዴ ? ቦሊውድን ያላየ! ሁለተኛ እንደዚህ ትጮኺብኝና አሳብጀ ልብስሽን አስጥየ ነው መሳቂያ የማደርግሽ! ከንቱ! ሸር . . ጣ! አሁን ውሃውን አቀዝቅዥው ! ዘንቧጣ! ደግሞ ራቁትሽን ሲያዩሽ ምንድነው የምትመስይው? ልብስ ነው ሰው ያስመሰለሽ! ከአምስት ዓመት በኋላ ማንም ዙሮ የማያይሽ ቆዳ ፊት ነው የምትሆኝው! ያ ሰሊጣምና ትራክተራም ራሱ እንዳላየ ነው የሚያልፍሽ » ፊደል ተሳቀቀች! ማንም በሰውነቷ እንዲህ ዝቅ አድርጓት አያውቅም! አይቷት የማይንሰፈሰፍ ወንድ የለም! ቢሆንም መመላለስ አልፈለገችም! ሲጀመር ምን ጋር ነው የምትመላለሰው? ይችን ጉድ ፈራቻት፤ ይችን አስቀያሚ ሴት ክፉኛ ፈራቻት! እናም በትህትና « እኔኮ ቀዝቃዛ ውሃ ስለማልወድ ነው» አለች! ፍርሃት በተቀላቀለበት ሳግ የሚተናነቀው ድምፅ ! ይችን ፍጥረት ትሁን ቅዠት ምኗም መጋጨቱ ...! እንደውም ወደፖሊስ ጣቢያ ሂዳ ኡኡ ልትል አማራት!እዛው አሳድሩኝ ልትል ፈለገች፤ ፈራች በጣም ፈራች! «ወደድሽ አልወደድሽ ግድ አይሰጠኝም! ሰውነቱ የጋራችን መስሎኝ! በሙቅ ውሃ የተቀቀለ አስቀያሚ ሰውነት ውስጥ ተቀምጨ መኖር የሚያስደስተኝ ይመስልሻል? ወጣት ነኝ ሳልሞት በፊት ገና ሃያ አራት ዓመቴ ነበር ! ግን ደደብ አልነበርኩም! ስለሙቅ ውሃ በኃላ አስረዳሻለሁ! አሁን ሙቀቱን ቀንሽው በይ ! ምናይነቷ ውስጥ ነው ያስቀመጠኝ ? ቆንጆ ብቻ ! » ተነጫነጨች! ፊደል ቀዝቃዛ ውሃውን ጨመረችው እና «አሁንስ?» አለቻት የማትታይ የማትታወቅ ሴት በራሷ ፍላጎት ላይ ፈቃድ መጠየቋ ደግሞ አበሳጫት! «በእጅሽ ሞክሪዋ እኔ መንፈስ ነኝ! እጅ የለኝ እግር ፤በአንች እጅ ነው የማውቀው !» ፊደል እጇን ዘርግታ የሚወርደውን ውሃ ሞከረችው «አሁንም ትኩስ ነው በደንብ ቀንሽው » ቀነሰችው «አሁን ይሻላል! » ፊደል በጣም ከመፍራቷ ብዛት ውሃ ውስጥ ሁና ሁሉ ያልባት ነበር። «ይልቅ የገላ ሳሙናሽ ሸታው ደስ ሲል» ፊደል አልመለሰችም! ኒላ ወሬዋን አላቆመችም! « ኡፍፍ ሻዎር ስወስድ. . . ፍቅረኛየ ሮሃንን ነው የማስታውሰው ! በጣም የሚያምር አስተማሪ ነበር . . .እንደዛ ሰሊጣም ሽማግሌሽ እንዳታስቢው! እዛ እከካም ዳይሬክተር ተብየ ጋርም እንዳታወዳድሪው ! ወንዳወንድ ነበር. . . ጅኒየስ! ብዙ ሐሳብ ነበረን!ብዙ! " ጮክ ብላ ማንጎራጎር ጀመረች የህንድ ተራሮች ግዝፈት ሞገስህን አይሸፍኑም ሙቀት ያለህ ስሜት ያለህ ተራራ ነህ ውብ ተራራ በአለት ማንነትህ ውስጥ ፍቅር የሚንተገተግ እንደ እሳተ ገሞራ ...
Show all...
👍 29 14👏 2😁 2
በጣም ዘግናኝ ነገር ማለት አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ሲሞት ሐዘኑ ሳያንስ "አባቴ አባቴ" እያለ መቸና የት እንደተወለደ የማይታወቅ ግድንግድ ልጅ ከች ማለቱ! (ያኔ ሚስቶችን አለማየት ነው! አስከሬኑንን ሁሉ በጀበና ቢፈነክቱት ደስታቸው) ብዙ ወንዶች ድብቅ ናቸው! በኋላ ነው ጣጣቸው እየተጎተተ የሚመጣው! እና ሰውየው ጨዋ ነበሩኮ(ሰባት አመት ተጠናንተው ሁሉ የታጋቡ) በሰፈሩ "ትዳርማ እንደሳቸው" የተባለላቸው...የሁለት ልጆች አባት! ከስራ ቤት ከቤት ስራ "ምነው ልጅ ጨመር ብታደርጉ ሀብት አላነሳችሁ" ሲባሉ "ምንድነው ልጅ ማብዛት ያሉትን በወጉ ማሳደግ ነው ዋናው " የሚሉ! እና ድንገት ሞቱ ... ልክ የቀብሩ ቀን ሶስት እግዜር ዲኤንኤ ውጤታቸውን በመልካቸው የፃፈባቸው ፣ ቁርጥ ሟቹን የመሰሉ ጠረንገሎ ጎረምሶች አባቴ አባቴ እያሉ ተግተልትለው አልመጡም!? ሚስትም ልጆችም ሐዘኑን እረስተው በድንጋጤ ታዛቢ ሆኑ" ይሄ ሁሉ ልጅ" እያሉ... ወዲያው አስከሬን ሊወጣ ሲል አዲሶቹ ልጆች" አሁን አይቀበርም አህህህህ" ብለው እያለቀሱ እየተናፈጡ ምናምን ከለከሉ ! ለምን ይባላሉ... "አራት እህቶቻችን ከኋላ እየመጡ ነው እንጠብቃቸው"😄 @wegoch @wegoch @paappii By alex abrham
Show all...
😁 78👍 9 5😱 4
ፊደል እቤቷ ደርሳ ከገስጥ መኪና ስትወርድ ሁለቱም ከፍርሃታቸው ብዛት ደህና እደር ደህና እደሪ እንኳን አልተባባሉም! እቤቷ እንደገባች በሯን በፍጥነት ዘጋችና በፍርሃት እየተንቀጠቀጠች ዙሪያዋን ማየት ጀመረች! ድንገት ሳታስበው እንባዋ ተዘረገፈ! «ምን ያነፋርቅሻል? ደግሞ እንዳለ ላብ ላብ ሸተሻል ተነሸና ሻዎር ውሰጅ?» አላት ያ የሴት ድምፅ ! «እንዴ ቆይ ማነሽ ?» አለች በድንጋጤ ግድጋዳውን በጀርባዋ ተደግፋ እየተንቀጠቀጠች! «አትፈሪ ! አናላ እባላለሁ ! ነፍሴን ይማረውና ጓደኞቸ ኒላ ነበር የሚሉኝ . . . ኒላ ልትይኝ ትችያለሽ አንችም! » «እሽ ኒላ ምንድነሽ? የት ነሽ? ምንድነው የምትፈልጊው ?. . .» «ኦ እኔ ሰው ነበርኩ እንዳንች . . . በእርግጥ አሁን መንፈስ ነኝ . . . ከሁለት ዓመት በፊት ህንድ ውስጥ ነው የሞትኩት . . .ሁለቱን ዓመት የት እንደነበርኩ እኔም አላውቅም! ይሄ አናትሽ ላይ ያደረግሽው ፀጉር የእኔ ነው! ልክ ፀጉሩን ሰውነትሽ ጋር ሲነካካ አንች ውስጥ ሁኘ ነቃሁ! «እ?» አለች ፊደል በበለጠ ፍርሃት ፀጉሯን እየነካካች! «አዎ ! ፍቅረኛየ ጋር በባቡር ስንጓዝ ነበር ባቡሩ ሃዲዱን ስቶ ያለቅነው! ለመጨረሻ ጊዜ ከአደጋው በፊት ፍቅረኛየ ይሄን ፀጉሬን በእጁ እያበጠረ በጣም እንደሚወደው እየነገረኝ ነበር። እንድንከባከበውም አደራ ብሎኛል! ፀጉሬን አመልከው ነበር። በጓደኞቸ በዘመድ አዝማዱ ሁሉ የተደነቀልኝ ፀጉር! ምን ዋጋ አለው... አንች እንዲህ በማይረባ ቅባትና በዚህ አቧራ አገርሽ አጎሳቆልሽው እንጅ ውብ ነበር። የሆነ ሁኖ ከዚህ በኋላ መንፈሴ በፀጉሬ በኩል አንች ውስጥ ገብቷል። ሰውነትሽ የጋራችን ስለሆነ ለብቻሽ አትወስኝም ። «ነገውኑ ፀጉርሽን እፈተዋለሁ» አለች እየፈራች! ለውጥ የለውም! መንፈሴ ውስጥሽ ነው ያለው ! ፀጉሬን እንደመጓጓዣ ውሰጅው ! መንፈሴ ተጭኖበት የመጣ መጓጓዣ! አገልግሎቱን ጨርሷል። እና ከዚህ በኋላ የማንም ፎከታም ጋር አትሄጅም ፍቅረኛችንን አብረን እንመርጣለን ፣ ምግባችንን ፣ ልብሳችንን ፣ አብረን እንበላለን አብረን እንዘንጣለን ፣ እና ደስ የሚለን ፍቅረኛ ካገኘን አብረን እን. . . ሂሂሂሂ! ይቀጥላል! @wegoch @wegoch @paappii
Show all...
😱 21😁 20👍 16 3🔥 2👏 2