cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

ሶፊ 👉 @umsofi27 enjoy ✌ "I don't write words; i write sentiments." -®Sofi Do what it worth to live..." . . . በካፊያ አልደነግጥም የተዘጋጀውት ለዶፍ ነው። . . #💚💛❤ @sofimemo

نمایش بیشتر
أثيوبيا4 700امهری3 557دسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
3 704
مشترکین
+124 ساؚت
-47 عوز
-230 عوز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ሆይ ሆይ... ቅድም አዲስ የተከፈተው "ዳኦ ቡና" ቁጭ ብዬ (የሚገኘው ጎፋ ገብርኤል አደባባዩ ጋር ፤ ባላንስ ህንፃ በፓርኪንጉ ሥፍራ ነው። ማስታወቂያ አይደለም።) እና የንዋይን ዘፈን እየሰማኹ ነበር።አንዱ የግጥም ስንኝ ቀልቤን ሳበውና ደጋግሜ አሰብኹት... "ንብ ሆኜ መጥቼ እንዳይሽ ፈገግ ብሎ ይቆየኝ ጥርስሽ ።" ምን አሰብክ አትሉኝም? ቆይ ነገሩን ከስር ዠምሬ ልንገራችኹ። Teenage እያለኹ ዝም ብሎ ነበር "ፍቅር" የሚይዘኝ i mean sight love. ትክክለኛው ፍቅር ነው ወይ? የሚለው ሌላ ጥናት ይፈልጋል።(እኔ ጉንፋን ይመስል ቶሎ ቶሎ ነበር የሚይዘኝ...) እኛ ሰፈር ያሉትን አብዛኛዎቹን ቆንጆ ሴቶች ተራ በተራ አፍቅሬያቸዋለኹ። እንዴት ? እሱ ለእኔም ጥያቄ ነው ። ማለት እኔ ሲደብረኝ "አሁን ደግሞ ማንን ላፍቅር ?" እያልኹ ነበር የማስበው።ከዛም በዛ ሰሞን ነጋዴ የገበያ ጥናት እንደሚያደርገው ፤ አካባቢዬን አጠናና በወቅቱ የፍቅር ገበያ ልቤ ያተርፍበታል ብዬ የማስባት ላይ ላፈቅር እወስናለኹ። "ፍቅር" ነው የሚለው በትምህርተ ጥቅስ እንደ ተቀመጠ ሆኖ ማለት ነው። እናላችኹ አፍቅሬ አፍቅሬ አስራ ሰባተኛዋ ላይ ደረስኹ።( አያችሁልኝ ? እንዴት ያለኹ ስራ ፈት ብሆን ነው ጎ'በዝ?) የሚገርመው ነገር አንዳቸውንም አናግሬ አለማወቄ ነው።በቃ ሰፈር ውስጥ ፈፅሞ ከሴት ጋር የማልቀራረበው ልጅ ነኝ። አስራ ሰባተኛዋ የቤት ልጅ ናት።ጠዋት አባቷ ነው በመኪና ትምህርት ቤት የሚወስዳት ስትመለስም እርሱ የሚያመጣት ይመስለኛል።(ስትመለስ አጋጥሞኝ አያውቅም።) እና የት አይተህ ነው የወደድካት አትሉኝም? የሆነ ፀዴ ድግስ ነበር ቤታቸው አስታውሳለኹ የቅዱስ ሚካኤል ዝክር ልበላ ድንኳን ሰብሬ ገብቼ ተበላኹ ነው የምላችኹ።ሳያት አልቻልኹም እዛው ላፈቅራት ወሰንኹ። ውብ ናት ! ውብ ናት ! ብዬ እንደታምራት ደስታ በልቤ ጮኹ። ከዛም በኋላ አንድ ሁለት ቀን ሱቅ ከሰራተኛቸው ጋር ስትመጣ አየኋት...እኔ ሱቁ ጋር ካሉ ጎረምሶች ጋር ነበር ድድ የማሰጣው ።(ስራ ፈትነቴን እኮ ተንከባክቤ ነው ያሳደግኹት...ሌላ አለም ላይ በእዛ እድሜ ስንት ስራ ይሰራሉ እኔ እቴ...) እናም አስራ ሰባተኛዋ ሌላ በምንም አጋጣሚ ላያት አልችልም።"ፍቅሯ" ፀናብኝ ።ፍቅር ህመም ነው ይላሉ እኔም እንደዛ ይመስለኛል። ናፍቆ አለማያት ህመም ነው ፤ ፈልጎ አለማግኘት ስቃይ ነው ። እስከመፈጠሬ የማታውቀኝን ልጅ ማየት ለእኔ ልዩ የህይወት ትርጉም ይሰጠኝ ነበር። እና ነዋይ ደበበ በዘፈኑ "ንብ ሆኜ መጥቼ እንዳይሽ..." ሲል... እኔም የሆነ ተሳቢ እንስሳም ቢሆን ሆኜ...ወይም የምበር ትንሽ ፍጥረት ሆኜ...ልጅቷን አይቼ የአይኔን ርሀብ ባስታገስኹ እያልኹ እመኝ እንደነበር አስታወሰኝ። ሆይ ሆይ ሌላ ሳላወራ ሰላም እደሩ። ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
نمایش همه...
👏 6🤣 5🥰 4
«አይዞሽ ገለቴ አይዞሽ። አይዞሽ በቃ። ምን እናርግ በቃ ምንም ማድረግ አይቻልም» 2009 የበርሊኑ የአለም ሻምፒዮና ላይ በ1500 ሜትር ገለቴ ቡርቃ እየመራች ነው። ወርቅ የማግኘት እድሉ በእጇ ነው። ነገር ግን ወደማብቂያው አካባቢ ስፔናዊቷ ናታሊያ ሮድሪጌዝ ገፈተረቻት። ገለቴ ወደቀች። ለገለቴ አሳዛኝ ቀን ነው። እጅግ በጣም አሳዛኝ ቀን። ያን ቀን ቀነኒሳ በቀለ ከ10ሺህ ሜትር የወርቅ አሸናፊነቱ መልስ በ5ሺህ ሜትር በድጋሚ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል። ቀነኒሳ interview እየተደረገ ነው። Interviewer: So the 10k and now the 5k it was a battle at the end there. Kenenisa: emmm… you know… not… not bad but you know… it was a beautiful race. This 5000 meter. so i am so happy to win this race again… emm you know… i am so happy. interviewer: You have to. You had a confidence in your kick because it was a slow pace? kenenisa: Yes uhhm… i dont know… i dont… i dont know that time it was fast or so slow… but during the race… አይዞሽ ገለቴ አይዞሽ። አይዞሽ በቃ። ምን እናርግ በቃ ምንም ማድረግ አይቻልም። but you know its… she is fifteen hundred meter she fell down. You know somebody… emmm you know kicked her. when 200 meters left. ቀነኒሳ በኢንተርቪው መሃል ዞር ሲል ያያትት የሀገሩን ልጅ ለማፅናናት ንግግሩን አቋረጠ። ቋንቋውን ከኢንጊሊዘኛ ወደ አማርኛ ቀይሮ ገለቴን አናገራት። ተመልሶ ደግሞ ለጋዜጠኛው ገለቴ ቡርቃ ላይ የተፈጠረውን ነገር ማብራራቱን ቀጠለ። ቀነኒሳ ይህንን ከማድረግ ምንም ነገር አላገደውም። አለም የሚከታተለውን ቃለ መጠይቅ ችላ ብሎ የገለቴን ሀዘን በአደባባይ ተጋራት። በንግግሩ መሃል ቀልቡን ተከትሎ የማፅናኛ ቃሎችን ወረወረ። አልተጠነቀቀም። ሰው ምን ይለኛል አላለም። አይዞሽ ገለቴ አለ። ይህንን ቃል ብዙዎች መቀለጃ አድርገውት ኖረዋል። አሁንም ድረስ ሁላችንም አፍ ውስጥ አለ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይሄንን iconic ንግግር እንደ ርህራሄ እና የዋህነት መገለጫ አድርገን ወስደነዋል። ቀነኒሳ ግን ሁላችንንም ቀድሞናል። ስንቶቻችን ሰው ለማፅናናት እና ከሰው ጎን ለመቆም ቦታ እንደምንመርጥ የታወቀ ነው። ያውም እኛ አሸናፊዎች ሆነን? ቀነኒ ከልቡ ቅን ሰው ነው። እንደዚህ አይነት ውብ ነገሮችን ሳያስብ የሚያደርግ ሰው ይማርከኛል። ከተደጋጋሚ ድሎቹ በተጨማሪ ቀነኒሳን ድንገት ባደረጋቸው፤ የዋህነቱን እና ቅንነቱን ያየንበትን ሁለት ነገሮች አስታውሰዋለሁ። አንደኛው ሀይሌ ገብረስላሴን ወደ ኋላ ዞሮ በአይኑ ሲፈልግ የነበረበት እና ሁለተኛው "አይዞሽ ገለቴ" ያለበት። በነገራችን ላይ ቀነኒሳ አሁንም እየሮጠ ነው። መልካም ልደት Greatest of all time. ድርሻዬ 🤙
نمایش همه...
❤ 40👍 10
Photo unavailableShow in Telegram
“I was sitting in a bar on Western Ave. It was around midnight and I was in my usual confused state. I mean, you know, nothing works right: the women, the jobs, the no jobs, the weather, the dogs. Finally you just sit in a kind of stricken state and wait like you're on the bus stop bench waiting for death.” ~ Charles Bukowski, from the story “No Way to Paradise”
نمایش همه...
❤ 11👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
በመጨነቅ ምንም ነገር አትጨምሩም ነገር ግን ብዙ ነገር ታጎላላችኹ... __
نمایش همه...
👍 7❤ 6
Photo unavailableShow in Telegram
ለ Ex ሳችሁ መልእክት አስቀምጡ ብትባሉ ምን ትላላችሁ? (አንተ መልካም ሰው ነበርክ ምናምን የሚል ሳክስ እንዳታወሩ...) እኔ እንኳንም ተለያየን ! የሚቆጨኝ አንድ ነገር እንደማይሆን እያወቅሁት ፤ ማብቃት ባለበት ጊዜ ስላበቃን ይቆጨኛል። ጎድተሺኝ ከብቸኝነት ሽሽት ጭቅጭቅሽን መናፈቄ ትዝ ሲለኝ ይበሰጨኛል። ብቻ ባስታወስኹሽ ቁጥር አይ ልጅነት ብዬ ፈገግ እላለሁ።እንኳን ቀረሽብሽ እንኳን ቀረኹብሽ !
نمایش همه...
❤ 11🔥 4👍 2🤣 1
Photo unavailableShow in Telegram
አንተ ሰው ! እስኪ ንገረኝ ... ተራራ ምን ይመስልሃል !? < እንጃ ...እስኪ አንቺ ንገሪኝ ... ተራራ ምንድን ነው !? > ተራራ አኩራፊ ሰው ነው ። ኩፍ ያለ ወዳጅ ፣ ለንቦጩን የጣለ ወንድም ፣ ግንጭሉን የነፋ አባወራ ነው ። ~ቴዎድሮስ ካሳ ✌️
نمایش همه...
❤ 18😁 5
ሰላም ተወዳጆች እንደምን አመሻችሁ...ለሆነ ነገር ፈልጌው ነው (ለምን እንደሆነ ጊዜው ሲደርስ እነግራችኋለሁ።) ፤ ከታች የዘረዘርኋቸው ሰፈር አካባቢ የምትገኙ ብቻ ቲክ አድርጉልኝ። አመሰግናለሁ ።Anonymous voting
  • ጎፋ ገብርኤል
  • ቄራ
  • ጎፋ ካምፕ
  • መብራት ሃይል
0 votes
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
ደመናዎቹ ጉበዝ ሸማኔ ያደወራቸው ጋቢ እንደሚመስሉ እኔ መቼ አውቄ ፤ አንተ ስታወራ አስተዋልኋቸው። ከዋክብቶቹን እኔ ቁብ ሰጥቼ መቼ አይቻቸው ፤ አንተ ስለአንድሮሜዳ ተመስጠህ ስታወራ ልብ አልዋቸው። ስለኮረብታ ፣ ስለተራራ ፣ስለፀሐይ ፣ ስለጨረቃ ስትደነቅ ተመልክቼ ወደድኋቸው እንጂ የት አይቻቸው? እነዚህን ባደነቅህበት አይንህ የእኔን ውበት አይተህ ስታደንቅበት ጊዜ ደግሞ ይበልጥ አስገረምከኝ ። አረ እንዴት ቻልክበት ?! ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
نمایش همه...
😁 20🥰 4🔥 3👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የሆነ ጊዜ እንደምትተወኝ አይነ ውሃ ነግሮኝ ነበር...እዚህ ጋር ትተወኛለህ ብዬ ግን አልገመትኩም ፤ በጣም በምታስፈልገኝ ሰዓት...! የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
نمایش همه...
💔 25👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ስላንቺ መልካምነት ስነግረው እንዲህ ብሎ መከረኝ... ህይወት ወዴት እንደሚወስድህ አታውቅም።በልብ-ወለድ የምታነባቸው መከዳቶች፣በፊልም የምታውቃቸው ጭካኔዎች ሩቅ አይደሉም።በአንተም ህይወት ተከስተው ያስደነግጡሃል...የፈራኽው ይደርሳል። አውቀዋለኹ የምትለው ሰው ታጣለህ፣ያላሰብከው ሰው ይከዳሀል፣የራሱን ጥቅም አስጠብቆ ያንተንም ሲነጥቅ አይፀፀትም።የእኔ የምትለው ሰው አይኖርም ፤ አንተ ራሱ በራስህ እምነት እንዳይኖርህ አድርገው ያጠራጥሩሃል። ከዛ ዝም ብሎ ይደክምሃል ፣ ሁሉም ይሰለችሃል።ባህር ላይ እንደተንሳፈፈ ሸንበቆ መሄጃህን አንተ አትወስንም ከፍሰቱ ጋር ትሄዳለህ። ...ህይወት ወዴት እንደምትወስድህ አታውቅም ሶፊ ፤ እንኳን ስለ ነገ ስለ ዛሬም ርግጠኛ አትሁን።ዛሬን ግን ኑረው ፤ በጎ አድርግ...የነገ ስንቅ እርሱ ነው። ...እና ሶፊዬ እሷን የተዋወቅኋት እንደዚህ ባለ የህይወት መዛል ውስጥ ሆኜ ነው።ስንቴ መርጬ ስንቴ ተሳሳትኹ ፤ ደክሞኝ ነበር። አጋጣሚ ወደ ህይወቴ ሲያመጣት ፤ አብራኝ እንድትሆን ፈቀድኹላት። ምክንያቱም "አታገባም?" የሚለው ጥያቄ አሰልችቶኝ ነበር።ነይ አላልኋትም፤መጣች።አልመዘንኋትም የሆነችውን ትሁን ብዬ ተቀበልኋት።"እንጋባ?" ስትል "እሺ" አልኋት።ከቤተሰቤ ቤት ወጥቼ ብቻዬን ተከራየኹ፤የሚጠበቅብኝን፥የምችለውን አደረግኹ።እሷ ግን ምን አደረገች ሶፊ አብረን እንድንኖር የተከራየሁት ቤት አልመጣችም።እንደውም ቀረች። "ቀረሁ..." የሚል መልእክት እንኳን የደረሰኝ ከወራት በኋላ ነበር ።ቴሌግራም ላይ አሜሪካ እንደገባች ፃፈችልኝ። ሶፊ ህይወት ወዴት እንደምትወስድህ አታውቅም።ፊልም ላይ የምታውቃቸው ጭካኔዎች እና መከዳቶች ሩቅ አይደሉም። የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
نمایش همه...
💔 14🔥 8🤔 3❤ 2👍 1😍 1