es
Feedback
👳🏽ባለዕዳው

👳🏽ባለዕዳው

Ir al canal en Telegram

ሁሉም ስለእኛ ነው ። መሆን ስለምፈልገው ፣ እንድትሆኑ ስለምፈልገው እና መሆን ስላለብን!

Mostrar más
3 755
Suscriptores
-424 horas
-87 días
-3830 días

Carga de datos en curso...

Nube de Etiquetas
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Menciones Entrantes y Salientes
---
---
---
---
---
---
Atraer Suscriptores
septiembre '26
septiembre '26
+3
en 0 canales
agosto '26
+106
en 1 canales
Get PRO
julio '26
+111
en 0 canales
Get PRO
junio '26
+98
en 2 canales
Get PRO
mayo '26
+66
en 1 canales
Get PRO
abril '26
+67
en 5 canales
Get PRO
marzo '26
+46
en 1 canales
Get PRO
febrero '26
+47
en 5 canales
Get PRO
enero '26
+70
en 6 canales
Get PRO
diciembre '25
+31
en 0 canales
Get PRO
noviembre '25
+28
en 3 canales
Get PRO
octubre '25
+55
en 2 canales
Get PRO
septiembre '25
+44
en 2 canales
Get PRO
agosto '25
+47
en 2 canales
Get PRO
julio '25
+63
en 3 canales
Get PRO
junio '25
+51
en 1 canales
Get PRO
mayo '25
+72
en 1 canales
Get PRO
abril '25
+109
en 4 canales
Get PRO
marzo '25
+186
en 3 canales
Get PRO
febrero '25
+60
en 1 canales
Get PRO
enero '25
+108
en 2 canales
Get PRO
diciembre '24
+114
en 1 canales
Get PRO
noviembre '24
+116
en 0 canales
Get PRO
octubre '24
+140
en 5 canales
Get PRO
septiembre '24
+110
en 3 canales
Get PRO
agosto '24
+105
en 0 canales
Get PRO
julio '24
+35
en 1 canales
Get PRO
junio '24
+1 760
en 0 canales
Get PRO
mayo '24
+1 159
en 2 canales
Get PRO
abril '24
+1 187
en 0 canales
Get PRO
marzo '24
+2 641
en 2 canales
Fecha
Crecimiento de Suscriptores
Menciones
Canales
03 septiembre+1
02 septiembre+2
01 septiembre0
Publicaciones del Canal
ይህን ትውልድ ለመረዳት አንድ እርምጃ ሳይራመዱ ሁል ጊዜ በምክር ተመለስ ማለት ወፏን ብረሪ እንደማለት ነው ። ብዙ ተተብትቧል ... ተማሪው ትምህርት ቤት ውስጥ ስቅጥጥ በሚል ሀል ላይ ነው ። ውጪ
ይህን ትውልድ ለመረዳት አንድ እርምጃ ሳይራመዱ ሁል ጊዜ በምክር ተመለስ ማለት ወፏን ብረሪ እንደማለት ነው ። ብዙ ተተብትቧል ... ተማሪው ትምህርት ቤት ውስጥ ስቅጥጥ በሚል ሀል ላይ ነው ። ውጪ ላይ ዳዕዋው ልብስና መለያየት ላይ ነው ትውልዱ ትምህርት ቤት ውስጥ የምድርን ጀሀነም እያቀጣጠለ ነው ። ለመስማት በሚከብዱ ነገሮች ትውልዱ ሰጥሟል.... ደስታ ብሎ በሚያስባቸው ነገሮች ስር በገሀድ ቢያልፍም ከኢስላም ጋር በሚጋጩ ነገሮች ውስጥ ተዘፍቋል ። ዳዒዎቻችንም ቤተቸውን ዘግተው በመስኮታቸው ቀዳዳ "ተው" ከማለት አልፈው ያሉበት ሄደው እጃቸውን በመያዝ ለማውጣት አልደፈሩም "ከመጡ ይምጡ ካልመጡ አይምጡ እሳቱ ለነሱ ነው " በሚል እሳቤ የሚደረግ ዳዕዋ ፍሬ አለው ? ከልጅነት እስከ ጎልምስና ጠላቶቻቸው ተብትበው አስረዋቸው የምን ቸል ማለት ነው ? እስቲ ትውልዱ የት ነው ብላችሁ ለማጣራት ሞክሩማ 🙌

2
ያው ዱንያ አይደል ? ሁሉም ይመኛል ሁሉም ያቅዳል ... ሁሉም ምኞትና እቅዱ ሁሌ ተደስቶ መኖር ነው። ግን ምድር ይህን ትፈቅዳለች ? በወጣቶች የነገ ተስፋ በየዘመኑ እየተገረመች " ካለፉት የማይማሩ ብኩን ነፍሶች " የምትል ይመስለኛል ። በቃ ከፊሉ ያለመውን ይኖራል ... ከፊሉ ካለመው ትንሽ ዝቅ ብሎ ይኖራል አብዛኛው እኖራለው ብሎ የማያስበውን ህይወት ኖሮ ያልፋል ይህ የዚች ምድር ህግ ነው ። ይህን ስላችሁ ተስፋ ቁረጡ አይደለም ግን ብቻ እንጃ እንዴት እንደማስረዳም ብቻ የትውልዱ ማለቂያ የለሽ ምኞት የህይወትን ትክክለኛ ገፅ ከመጋፈጥ ብዙ ያሰንፋል.... ህይወት ታጋያችሁ ብቻ ነች ።
230
3
ህይወት ከአዛን እስከ ሰላት ያለ የቆይታ ጊዜ ነው ይሉ የለ ..... የምን ትካዜ ነው ? ቀድማችሁ ምኞታችሁን ግደሉ ... ከዛም በመሞት ህያው ትሆናላችሁ ።
ህይወት ከአዛን እስከ ሰላት ያለ የቆይታ ጊዜ ነው ይሉ የለ ..... የምን ትካዜ ነው ? ቀድማችሁ ምኞታችሁን ግደሉ ... ከዛም በመሞት ህያው ትሆናላችሁ ።
272
4
ብዙ ጊዜ ነገራቶች እስኪረጋገጡ ድረስ እይታ ይነፈጋቸዋል ። ጥቅም አልባነታቸውን ለማጉላት ...አለመጥቀማቸውን ለማረጋገጥ ይለፋባቸዋል ። ከዚያም ጥቅማቸው ሲረጋገጥ በነሱ ላይ ጥቅመኝነት ባመነጨው ጉልበት ይለፋል ። ከመቶ አመታት በፊት አሁን በስልጣኔ ማማ ላይ ያሉት ምዕራባዊያን የጨለማው ዘመን ውስጥ ነበሩ...ያኔ ሙስሊሞች በሁሉም ዘርፍ በረቀቁበት እና በጥልቅ ነገሮች ውስጥ ሰጥመው ጥናት ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ምዕራባዊያን በሴት ልጅ ሰው መሆን ላይ ሙሉ እምነት አልነበራቸውም ...ምናልባት ሴት ልጅ በአፈጣጠር ሂደት ውስጥ ያላለቀች ወንድ ትሆን ? ምናልባት ፈጣሪ ተሳስቶ የፈጠራት ፍጡር ናት...አይ ወንድ ለመፍጠር በሚደረግ ሂደት ውስጥ ከሽፎ የተፈጠረች ፍጡር ነች ! አይ ሴትማ የስሜት ሙሌት ነች ! እያሉ በድንቁርና ሲንቀዋለሉ ኢስላም ግን ከሺ አራትመቶ አመታት በፊት ጉዳዩን ዘግቶ ነበር ። በሴትና ወንድ መሀል መበላለጥ ያለው በእምነት ጥንካሬና በፈጣሪ ፍራቻቸው ልክ ብቻ መሆኑን አስረግጦ ፅፎ ብዕሩ ደርቆ ነበር። እና ከሺ አመት በኋላ ደርሶ መቆርቆር ምንድነው ? ደግሞም በነሱ ሞቅታ ግላ ነፃ-ነቷን ያወጀች ሴት መውደቂያዋ የነሱው ጥቁር እስር ቤት ውስጥ ነው ። እንደ ሙስሉም ማህበረሰብ ለሴት የሚሰጠው ቦታ ልክ አለመሆኑን አምናለሁኝ ... በሚገባችሁ መልኩ እንዳልያዝናችሁ ረሱል አደራ ባሉት መልኩ አደራችንን እንዳልተወጣን እቀበላለሁኝ እንደውም የዛን ሀሳብ አቀንቃኞቼ ወንዶች ሲቃወሙ ደስ አይለኝም አልኖርነውምና ግን ግን ዲኑ ከማንም ከምንም በላይ አልቋችኋል እሱን አውቃለው ። አማኙ ልክ ባይሆኑም እምነቱ ቦታችሁን አውቆ አስጠብቋል .... የኛው ወንዶቹ ጉዳይ የኛው የቤት ስራ ሆኖ የውጪውን ግን እናንተው ሞግቱት ቦታችሁን ክብራችሁን ታውቃላችሁና ። ያው ለኛ ወንዶቹም አደራችንን የማንበላ እንድንሆንና ወደአቅላችን እንዲመልሰን ዱዓ አድርጉልን ።
295
5
በዚም አለ በዛ ሰው ደስ የሚል ነገር ነው ። ለጥቂት ጊዜያት ለተመሣሣይ ነገ ልንታገል ከመጣን አይቀር ተጋግዘንና ተዛዝነን ብናልፍ ... ሞት መምጫው አይታወቅም አይደል ? እስኪመጣ ሌላ ሞት ሆኑን ሰው ባናስጨንቅ መኖርን ባናጣብብ ። ሰው ሲደሰት ደስ አይልም ? ሰው ሲስቅ አያምርም ? ሰው ሲዋደድ አይስብም ? ለየትኛው ህይወት ነው ምንባላው ? ተውዋ ከእውነታው አንሽሽ ይህ ህይወት በጋራ እንጂ በግል አያምርም ። እስቲ እንዋደድ ..እንተሳሰብ ልንበሰብስ አይደል ? ቢያንስ ስንኖር እንኑር ።
370
6
ረሱል صلى الله عليه وسلم  እንዲህ አሉ የቂያም ቀን የእሳት ሰዎች ወደ ጀነት ይቀርባሉ፣ ያማረ መዓዛዋን ያሸታሉ ፣ ወደ ፎቆቿም ይመለከታሉ ፣አላህ ለነዋሪዎቿ ያዘጋጀውን ይመለከታሉ ። ከዛም ተጣሪ እንዲህ በማለት ይጣራል " ከጀነት አርቋቸው ከሷ ድርሻ የላቸውም" እነሱም ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ማንም ተቆጭቶ በማያውቀው መልኩ እየተቆጩ ይመለሳሉ። ጌታችን ሆይ ምናለ ይህንን ምንዳ ፣ ያዘጋጀኸውን ሳታሳየን እሳት ብታስገባን ይቀለን ነበር ይላሉ። አላህም ይላቸዋል"እሱን ፈልጌ ነው ያሳየኋቹ። ብቻችሁን ስትሆኑ በትላልቅ ወንጀል ከኔ ጋር ትዋጋላቹ፤ከሰዎች ጋር ስቶኑ በተቃራኒው ትሆናላቹ፣ ሰዎችን ፈራቹ እኔን ግን አልፈራቹኝም፣እነሱን አላቃቹ እኔን ግን አላላቃቹኝም፣ሰዎችን አፈራቹ እኔን ግን አላፈራቹኝም፣ ለሰዎች ብላቹ ወንጀል ተዋቹ ለኔ ብላቹ ግን አልተዋቹም። ዛሬ ይህንን ፀጋ ከመከልከሌ ጋር አሳማሚ ቅጣት አቀምሳቹሀለው። ©️
364
7
ሲሰዋ እንደትላንት ትዝ ይለኛል .... ግን አንድ አመት አለፈው አላህ ቀብሩን ኑር ያርግለት ።
ሲሰዋ እንደትላንት ትዝ ይለኛል .... ግን አንድ አመት አለፈው አላህ ቀብሩን ኑር ያርግለት ።
384
8
አንዳንዴ ኡማው የወከላቸው ሰዎች ያላቸው እሳቤ ሲታይ ተስፋ ያስቆርጣል ። የሆነ ቀን "ለምሳሌ 1 ሚሊየን ህዝብ ቢሞትብንም 119 ሚሊየን ያልሞተ ህዝብ አለንና እንደሰት " የሚል ሀሳብ ይዞ የሚያብራራ ሰው ( ሀላፍትና የተሰጠው ) ሰው አይቼ ብርግግ እንዳልኩ አለሁኝ ። ትላልቅ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች በግል እሳቤያቸው ብዙሀኑን ሲያስጠቁም አይተናል.... ለወረዱ መጠቃቀሚያዎች ሲበላሉም አይተናል ። ብቻ ሲወራ የሚቀፍ ርዕስ ነውና እንተወዉ እኛው ነን የነገ ተረካቢዎቹ .. እኛው ነን ብዙ ሀላፍትና ያለብንና በዲኑም በዱንያ እንበርታ በተለይ በተለይ በዲን ... አኽላቅና ትምህርት ላይ አደራ ።
411
9
!!!
!!!
451
10
ሰው ሲደሰት ማየት የሚያመነጨው እርካታ እንዴት ያለ ውብ ነው በአላህ ። ሀቢቢ ﷺ ከሰው ሁሉ ምርጡ ማነው ተብለው ተጠየቁና በመጨረሻም " ሰዎችን ከክፋቱ የጠበቀ " አሉ ። ለሰዎች ደስታ ሰበብ የሆነስ ምን ይሆን ደረጃው ? -አለምን ከሞላው የኔነት ጭጋግ እንራቅ -ካልጠቀመኝ ምናገባኝ ከሚል አስጠሊ እሳቤ እንሽሽ - ለሰዎች በጎ መዋል ..ሰዎችን ማስደሰት የትርፍ ጊዜ ተግባር እስኪመስል ህይወት ተጨማላልቃለችና እሳቤያችንን እናፅዳ ። ህይወትን የአመታት ትግል አናድርገው በአላህ ... በቃ ሰው ሄዶ ሄዶ ሰው ነው ! አስደስቱ ተደሰቱ ኑሩ ተኗኗሩ ። ደስታችሁን በሌሎች ውብ ሰዎች ደስታ ስር ፈልጉ🤍
494
11
አንዳንዱ በሚሰራት ትንሽ ስራ ለቤተሰቡ የሚችለውን እያረገ የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት ይመራል .... ከፊሉ በየቀኑ ብዙ ሺዎችን እያዘዋወረ የቤተሰብነትን ጣዕም ትቶ የተቻኮለ ሀያት ይኖራል ። ልክ እንዲሁ አንዳንዱ ከእጦቱም በተጨማሪ የሰዎችን ጓዳ እያየ መብቃቃትም ደስታም አጥቶ ይኖራል ... ከፊሉ አላህ ሀብት ሰጥቶት በአግባቡ እየተጠቀመ ተረጋግቶ በደስታ ይኖራል ። ደስታና መረጋጋት በገንዘብ መጠን የሚወሰኑ ሳይሆኑ ሁሉም ለህይወት ባለው ፍልስፍና የሚገሩ ናቸው ። ዱንያ ለናንተ ምንድናት ? እሱ ነው ዋናው ነገር ።
634
12
ዜናው " -የዋጋ ግሽበቱ በዚ በዚ ፐርሰንት ጨምሯል - በዚ በዚ አካባቢ ድርቅ ተከስቶ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ህዝቦች ረሀብ ተደቅኖባቸዋል - ይህን ያክል ሰዎች ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለው እንዲህ የሚሆኑት ታግተዋል -እዚ እዚህ አካባቢ ለአመታት የቀጠለው ጦርነት ተባብሷል " ህዝቡ "- በእግሬ ሄጄ የታክሲውን ለቤተሰቤ ዳቦ ልግዛበት ? - በየት በኩል ሄጄ ቤተሰቤን ከርሀብ ልታደግ - ልጆቼን እንዴት ላስተምር መንግስት " -ግብር ጨምሩ - ጦቢያ ለአለም አርዓያ የሚሆን እድገት አስመዝግባለች - ጦቢያ ለነዋሪዎቿ ምቹና ለቱሪስቶች ተመራጭ ሆናለች - ቢሊየን መድበን የሆነ ጫካ እናለማለን " ኧረ መንግስትና ኑሮ - መንግስትና ህዝቡ አልስማማ አሉኮ .... ዱባይ እየኖሩ ነው እንዴ የሚመሩን😭
67
13
የምትጓጉለት ነገ " ድካም ፣ አለመቻል እና መገደብ'ን " የያዘ ነው ። አሁንን ለመኖር እንጣር ... ሲደክመን እንረፍ ስንሰበር ስብራታችንን እየሰነጠቅን መታመማችንን አቁመን ወደመፍትሄ እንሩጥ ።
የምትጓጉለት ነገ " ድካም ፣ አለመቻል እና መገደብ'ን " የያዘ ነው ። አሁንን ለመኖር እንጣር ... ሲደክመን እንረፍ ስንሰበር ስብራታችንን እየሰነጠቅን መታመማችንን አቁመን ወደመፍትሄ እንሩጥ ። በሉ ዛሬን እንኑር🤍
710
14
በጣም ዛልና ? ሰዎች ተስፋ እየቆረጡ አንገታቸውን ለገመድ እየሰጡ ነው .... ወጣቶች ብዙ አልመው እርምጃ ለመጀመር ሲያስቡ ተተብትበው እየወደቁ ነው ። ውስጡም ውጪውም ለውድቀት የሚጣራ አልፎም የሚጠልፍ ጩኸት ሆኖባቸው ደክሟቸዋል ። አቃጆች አቅደው አቅደው ማህበረሰቡን በማያልቅ አስከፊ አዙሪት ነክረውት ተስፋውን በየዙሩ በየከፍታና ዝቅታው እያሳሱት ነው ..... ግን ይሁን ግድ የለም ። ከአቃጆችም በላይ አቃጁ አላህ አለ አብሽሩ .... ሴራዎቻቸው ሁሉ ፈርሰው የተሻለ ነገር ይመጣል። ብቻ ታገሉ አትድከሙ....ነፍሳችሁን አበርቷት አላህ አለ.... ነገ አለ በሏት ። አብሽሩማ የልፋታችሁ ውጤት ህመም እንኳ ቢሆን አላህ ጋር ሚዛን አለው .... ጊዜው እስኪመጣ ግን ታገሱ በምትችሉት ሁሉ ታገሉ .... ጊዜው ቀርቧል ኢንሻአላህ ።
631
15
ለመኖር ስል እየነካካው ያለኋቸው ርዕሶች ሁላ ከመኖር ሲያርቁኝ ነው የማስተውለው ። አማኝ ለመሆን ስጥር ከጌታዬ መራቅ ለምን ይሰማኛል ? ለማወቅ ስጥር የውሸት ትርክት የማጎር አይነት ስሜት....ለመጠንከር ስሞክር ድካም... ለምን ? ጊዜያቶች ባለፉ ቁጥር እቺ አለም የውሸት ሹራብ እየደረበች ...የእውነትን ብርሀን እያደበዘዘች ...የመኖርን ጣዕም እያጎመዘዘች ነው ። እቺ አለም እንደነበረችው አይደለችም...መሆን እንዳለባትም አይደለችም ። ከዘመናት በፊት የተቀየሰ አዲስ መንገድ ሳይኖር አይቀርም ። ይህ መንገድ ሁሉን ነገር አሳጥቶናል ...እምነታችንን ፣ ህይወታችንን ፣ እኛነታችንን ሁሉ ነጥቆናል ። አማኝነትን በራስ ወዳድነትና በተጨቃጫቂነት ለውጦብናል...ህይወታችንን ለሌሎች በማቀበል ስለሌሎች የሚገበር ተራ የጊዜያት ጥርቅም አድርጎብናል...እኛነታችንን ለማናውቀው እና ፍፁም ደስታችንን ለሚመጠው ሌላ ነገር አሳልፎ ሰጥቶብናል ። ይህ ሌላ ነገር ግን ምንድነው ? እየኖርን ያለነው ምንድነው ? ምን እየተፈጠረ ነው ግን? ብቻ መኖር ያለብን ህይወት አለ ....ያን ህይወት ፈልገን ማግኘት አለብን ።
733
16
ሁለት ወፎች በአንድ ሽቦ አጥር ውስጥ ታስረዋል ... ወፎቹ በተጣሉ ቁጥር አሳሪው ላባቸውን ይነቅላል ። በዛ ቅፅበት መጣላታቸውን ትተው ያጉረመርማሉ ...ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደጥላቸው ይመለሳሉ አሳርያቸውም ላባቸውን መንቀል ይቀጥላል ። ከረጅም ጊዜ በኋላ የማሰሪያውን በር ከፈተላቸው ግን ... ግን አልበረሩም አላመለጡም ... አዎ ክንፍ አልነበራቸውም ። እኚህ ወፎች እኛው ነን ... እኛው ሙስሊሞች ! ሀቢቢﷺ እንዲህ ቅጡ የጠፋውን ኡማቸውን ቢያዩ እንዴት ያማቸው ይሆን ... የማንም መጫወቻ ሆኖ እርስ በርሱ ለመቶ አመታት ሲታገል የከረመውን ኡማ ቢያዩ ምን ያህል ያማቸው ይሆን ? ጠላቶቻቸው ለመቶ አመታት የሚዘልቅ ሴራ አሲረው ኢስላምን ያፈራርሳሉ የነሱ ኡመት እርስ በርስ ይፋተጋል ... ያለአላማ የርስ በርስ ትግል ራሱንና ዲኑን ያደክማል ።
691
17
ውጤት ጠባቂዎች ...... አላህ ኸይሩን ያሰማችሁ🤍
668
18
መጨረስ አልቻልኩም ማለት የፈለኩትን አላልኩም ...ቢሆንም ይሁን በቃ
744
19
በቁሙ የጊዜ ክምር ማንነቱን በከንቱነት ወዳለመኖር እንዲሄድ የፈቀደው ትውልድ ከምን ጊዜውም በላይ ለእምነቱ ተቆርቋሪ ሆኗል ¡ ሁላችንም አንድ ቁስል ተሸክመናል ..... አለመኖር። ይህን ቁስል የምናስተናግድበት ሂክማውም ...የመኖር አቅሙም የለንም ምክንያቱም አለመኖራችንን ለመርሳት ሄደን የተጠለልንበት ጥላ "ዲን" ነው ። የእምነታችንን መሠረቶች ሁሉ ከማመን በዘለለ ወደነፍሳችን አላስገባንም .... አምልኮ የምንለው ሁሉ አድካሚ ድርጊት ሆኖብን የጊዜ ክምራችንን ሁሉ በባዶነት ውስጥ እየፈረካከስን እየሞላን ነን ። ነፍሳችንን አለማችንን የምንዋጋበት አንድ ተራ መሣሪያ የሌለን ጦረኛ ነን .... ሀሳባችንን አስገዝተን ያለ አንድ መሣሪያ ከተመሣሣዬ "የሀሳብ ባርነት" ውስጥ ካለ አካል ጋር እየተዋጋን አለመኖራችንን ...ባርነታችንን የዘነጋን ። እያልኖርን ያለነውን ዲን ሽሽት ዲን ስር የተጠለልን ... መገዛት ጠንቶን ተገዢ በሚያስመስል ርዕስ ውስጥ የምንርመሰመስ አመፀኞች ። ሌት ተቀን ሰዎችን አተልቀን አላህን አሳንሰን በ አመፅ ባህር ውስጥ የምንዋኝ ግና በእምነታችን ፍፁማዊ ለመምሰል ሌላ የማስመሰል ትግል የምንታገል ወዳቂዎች ። በጌታችን ትዕዛዝ ውስጥ መኖር ጠንቶን የአለመኖርን መራራ ፅዋ እየቀመስን አለመታዘዛችንን ሽሽት ወደዲኑ ተሸጉጠን ለመርሳት የምንጥር እፍረት የለሾች ። ማነን ? ቆይ ማነን ? ቁርጭራጭ የህክምና ፅሁፎችን አንብበን ሀኪም የሆንን ? የሆነ ቦታ ስለግንባታ አንብበን ኢንጂነር የሆንን ? እስቲ ማነው በቁርጥራጭ ንባብ ዶክተር የሚጋፈጠው ? ማነው በሶስት ቀን ፖድካስት እራሱን አዋቂ አርጎ ኢንጂነር የሚከራከረው ? እስልምናና አስተምህሮቱ ከህክምና ያነሰ ቦታ ነው ያላቸው ? የእስልምና አስተምህሮት ከኢንጂነሪንግ ያነሰ ቦታ ነው ያለው ? ምነው ዲናችን ላይ ሲሆን ደረታችን አበጠ ? የኪታብ ስም የማያነበው ሁሉ ምንው አዋቂ ነኝ ብሎ ቁጭ አለ ! " ያወከውን አስተላልፍ " የሚል ሀዲስ ስላለ ነው ? እሺ ልክ ነው ግን መች አወቅን ?ለእያንዳንዱ መረጃ ወደ ሰርች ባር የሚሮጥ ሁሉ ዲን ላይ ቃዲ ይመስል ሲያከፍር ሲያሰልም ... ለዲኑ ሲታገል ሲሳደ* ይውላል ። ኧረ ምን አይነት እፍረት የለሽ ትውልድ ነን በአላህ ።
805
20
አሁን ረጅጅም ፅሁፍ ልለቅ ነው ወይ ደግሞ አጭር ። ወይ ወቀሳ ነው ወይ ሌላ ነገር ነው .... ለማን እንደምፅፍ አላቅም ለራሴ ...ለናንተ ? እንጃ ብቻ
484