👳🏽ባለዕዳው
Ir al canal en Telegram
ሁሉም ስለእኛ ነው ። መሆን ስለምፈልገው ፣ እንድትሆኑ ስለምፈልገው እና መሆን ስላለብን!
Mostrar más3 811
Suscriptores
-324 horas
+97 días
-2730 días
Archivo de publicaciones
3 809
ሀብት ?
ህይወት የምንታገልላትን አትመስለኝም ። ልንርቀው ላንቀርበው የሚገባንን የመኖር መንገድ በመጎተት ላይ ያለን ሚስኪኖች የሆንን ሳንሆን አንቀርም ። ያ ቃሩናዊ እሳቤ እጅግ ተውቦ ሰልጥኖ ሙስሊሞችን አስምጦ የገነነበት ሰዓት ነው ። ያን አማፂ ቃሩን መሆንን የሱን መሳይ ሀብትን ይመኙ ነበር .... እኛም አሁን የነዛን አማፂ ቃሩኖች ሀብት እየቆጠርን የነሱን እየተመኘን እየጎመዠን አለን ። የኛና የቃሩን ዘመን ገንዘብ አምልኮሽ የሚለየው ቃሩን መስመጡ ነበር ! የኛዎቹ ቢሰምጡ የኛም ምላሽ ተመሣሣይ እንደሚሆን አያጠራጥርም ።
አሁን ላይ cool መሆን ማለት ...ጓደኝነትን ፣ወዳጅነትን ሁሉ በገንዘብ ሚዛን እየመዘኑ ሁሉን ተው ገንዘብህን ብቻ አሳድ ሌላው ተከትሎ ይመጣል የሚለው እሳቤ ሆኗል ! እንዴት የቆሸሸ እሳቤ ነው ። ለእያንዳንዱ ችግር ገንዘብ ብቻ ይኑርህ የሚል እምነት ነው አለምን ያጥለቀለቀው ....እንዴት ያለ አስቀያሚ እምነት ነው ።
ደጋግ የነበሩ በዛውም ልክ ሀብታም የነበሩ ብዙ አልፈዋል .... ሀብት መያዝ ክፉ ሆኖ አይደለም ግን አሁን ያለውን እሳቤ መያዝ እጅግ ሰቅጣኝ ባርነት ወላ ...ሰቅጣጭ ባርነት ።
فَخَرَجَ عَلَىٰ قَوْمِهِ فِي زِينَتِهِ ۖ قَالَ الَّذِينَ
يُرِيدُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا يَا لَيْتَ لَنَا مِثْلَ مَا أُوتِيَ قَارُونُ إِنَّهُ لَذُو حَظٍّ عَظِيمٍ በሕዝቦቹም ላይ በጌጡ ውስጥ ኾኖ ወጣ፡፡ እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት የሚፈልጉት «ወይ ምኞታችን! ቃሩን የተሰጠው ብጤ ምነው ለእኛ በኖረን፤ እርሱ የታላቅ ዕድል ባለቤት ነውና» አሉ፡፡
3 809
አዲስ አመት ገብቷል .... ሙሀረም 1
አዲስ ስሜት
አዲስ አቅም
አዲስ ተስፋ
አዲስ ደስታ
አዲስ ሰላም
አዲስ ሆኖ በጎ ነገር ሁሉ ወደሀያታችሁ ይግባ 🤍
3 809
ብዙ የምለው የለኝም ።
ግን ይህን አለም እንዲህ ሆኖ እንደማየት ህመም የለም ። አንድ ተራ ግለሰብ ዲሞክራሲ በፈጠው ውስብስ አለም ላይ እየተነሳ በሚወስነው ውሳኔ ሚሊዮኖች ሲሞቱ ዝም ብሎ እንደማየት ..... ከሱም ብሶ ተራን እንደመጠበቅ ህመም የለም ።
ለብዙ አስርት አመታት ራሳቸው በፈጠሩት ስርዓት አለም ስትሞት .... ስለሰው ነፍስ ፍፁም ግዴለሽ ሆነው ህይወት ተራ የሰከንድ ጥርቅም ይመስል ሲቀጥፉ ኖረው አሁንም ትልቁ ስጋታቸው ግን ሸሪዓ ነው ። ያ ስለሰዎች ቀልብ ...ስለሰዎች እንባ ግድ ሰጥቶት ህግ ስላዘጋጀው የአለም መመሪያ ! አሁንም ለሺ ጥፋታቸው የሚወቅሱን ፍፁም ልኩን ሸሪዓ ነው ።
እኛም ሰቀቀኑ ደልቶን ...ሀላፊነታችንን ረስተን የመኖር ምክንያታችንን ትተን ትርጉም አልባ ህይወት እየኖርን... ትርጉም የለሽ መኖር እያለምን ነው ።
ዝቅ ስለተደረገው የአላህ ቃል ረስተን ነፍሳችንን በነሱ አለም ለማመቻቸት እየታገልን ነው ..... የተረሳውን የአላህ ህግ ችላ ብለን ለህጋቸው ስለመገዛት እየሰበክን ነው ።
አስተዳዳሪዎቹ ነበርን ... የአላህን ቃል ከፍ አርገው ከሚይዙት ባሮች መሆን ነበረብን ግን ግን እዚህ ነን ! አዎ አሁን የሆነውን ነን ! ምን ያህል ከፋን ።
3 809
አንዳንዴ በህይወታቹ ውስጥ የማይደረግ ነገር እያደረጋችሁ ለመዝናናት ሞክሩ .... ልክ ከጓደኞቻችሁ ጋር በልታችሁ ጠጥታችሁ ሂሳብ ሊመጣ አካባቢ ሸውዳችሁ እንደመውጣት አይነት 😁 ማታ ከአንድ ወንድሜ ጋር አድርገነው ምሽታችን ቦግ ብሎ አለፈ።
የማትገመት ሁን🙂↔️
3 809
Repost
ደስተኞች ነበርን...ከቤታችን ሳንርቅ ደስተኞች ነበርን ከጊዜያት በኋላ ግን ደስታ የሚገዛ መሆኑን አሳመኑን ። ደስታንም እንሸጣለን ብለው ቀመሩና አለምን ወደገበያነት ለወጧት....እኛም ደስታችንንም ገንዘባችንንም ማጣታችንን ቀጠልን
ቲሽ.... አንዳንዴ ምንም መለወጥ አለመቻል የባሰ ያበሽቃል።
3 809
ልክ ሳሎን ስገባ ይሄን አይቼ ሳቄ መጣ😁 .... ከዛ እዛው የፈረደበት ሀሳብም መጣ ።
በቃ ሁሉ እንዲህ ነው ....
ስትወዱ እስከ ጥግ ሂዱ
ስትፈልጉ እስከ ጥግ ታገሉ
ስትታገሉ መንገድ ሁሉ ፈልጉ ።
ቶሎ ተስፋ አትቁረጡ ....ታጣላችሁ🙌
3 809
አላህ ለእያንዳንዱ አምልኮ ማቅለያ አለው .... ከዛ ውስጥ የሰላት ማቅለያው አለመስገድ እስኪመስል ድረስ የተግራራ ነው ።
ግን በየትኛውም ሀል ላይ ሰላት ዋጂብ ነው .... እጅግ አስፈሪ በሆነ ጦርነት ላይ እንኳ ሰላት አይወድቅም ! እየጋለብክም እየተራመድክም እየሮጥክም ቢሆን ትሰግዳታለህ ።
ስለደበረህ የማትሰግደው ... ስለተጫጫነሽ የማትሰግጂውስ🙂
3 809
ተስፋ መቁረጥ ሩጫ አይፈልግም ድካም አያሻውም ። መጠንከር ግን በሁሉም አቅጣጫ ምት አለው እነሱን መቋቋም ትልቁ ፈተና ነው ። የህይወት አቅሟ ፈተና ነውና ጠንክሩ ስለ ተስፋ መቁረጥ ለሰከንድ እንዳታስቡ ።
3 809
አዎ ጊዜው እየፈጠነ ነው ... አመቶች እንደቀልድ እየተደራረቡ ነው ።
ሞታችንም እንዲሁ ! የፈጠነው ሰዓት አይደለም ... የፈጠነው የመኖር ጊዜያቾን ነው ።
3 809
ታሪካዊው መድረክ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል!
ቅስቀሳው ቀጥሏል፤ ዝግጅቱም ደምቋል! በመጪው እሁድ ሰኔ 07/2018 ዓ.ል በጦር ኃይሎች ረያን መስጂድ የሚካሄደው ታላቅ የፓናል ውይይት እንደተጠበቀ ነው። ይህ መድረክ የሙስሊም ተማሪዎች ሕገ-መንግስታዊ መብቶች የሚከበሩበትን፣ እንደ ኒቃብና ሒጃብ ያሉ የእምነትና የማንነት መገለጫዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች በሕጋዊ መንገድ የሚመከቱበትንና ዘላቂ መፍትሔ የሚቀመጥበትን አቅጣጫ የሚያሳይ ነው። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (ትራንስፖርት በተዘጋጀላቸው ካምፓሶች) ጀምሮ በከተማዋ የምትገኙ የከፍተኛ ትምህርት፣ የኮሌጅና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በሙሉ የዚህ ታሪክ አካል እንድትሆኑ ጥሪያችን የፀና ነው። እምነታችን፣ መብታችንና ምርጫችን ይከበር ዘንድ፣ ሰኔ 7 ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ ልባችንና አቅጣጫችን ወደ ረያን መስጂድ ይሁን። ሁላችንም ለአንድ ዓላማ በአንድነት እንሰባሰብ።
ዝግጁ ናችሁ?!👍🫡
@aaumsu
3 809
ልጆቿ የርሀብ ዋይታን... የመኪና ጡሩንባን ሁሉ ችለው አካልን ከሚያደቀው የእግረኞች መንገድ ላይ ተጋድመዋል ። ከአጠገባቸው የተኛውን ባለቤቷን መመልከት ጀመረች .... አጥንቶቹ ቦታቸውን ለመቀየር እየታገሉ ይመስል ስጋውን ገልብጠው ከላይ ፊጥ ብለዋል ... አፍንጫውን በሁለት ግዙፍ ተራራዎች መሀል ያለ አነስተኛ ተራራ ይመስል የጉንጮቹ አጥንቶች ውጠውታል ።
ምግብ በቅጡ መመገብ ከተው አመት አልፏቸዋል ... መንገደኛ ከሚጥልላቸው ሳንቲም ውጪ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የላቸውም ... ኧረ የደስታም የሰላምም የምቾትም ምንጭ የላቸውም ። ለምደውት ከነበር ህይወት ተነስተው እዚ መውደቃቸው በነፃነት እንዳይለምኑ አግዷቸዋል .... ግን ግን እናት መንገድ አግኝታለች ።
በነጋታው ሁሉንም የሚያጠግብ ምግብ ይዛ ተመለሰች ... " ይኸው ብሉ ካሁን በኋላ አይርባችሁም " እያለች ከመንገዱ ጥግ ራሷን ወረወረች ።
የደከማት ይመስላል... ራሷን እየቆረሰች ቤተሰቧን ለማጥገብ የወሰነች እናት መስላለች ።
የምትሸጠው እሷነት እንዳለ አምናለች ... በስህተት እቅፍ ቤቷ ሲሞቅ ተመልክታለች ... አዎ መንገድ አግኝታለች ።
3 809
ሀሳቦቻችሁኮ በጣም ልክ ናቸው .... የምታነሷቸው ነጥቦች ሁሉም ሰው የሚያልፍባቸው ... የምር ከሆነው ህይወት ጋር የገጠሙ ናቸው .... ግን
ግን የኔ ህይወት ከህይወት ጋር አልገጠመም ምን ላርግ ?😭
¡Ya disponible! Investigación de Telegram 2025 — los principales insights del año 
