👳🏽ባለዕዳው
الذهاب إلى القناة على Telegram
ሁሉም ስለእኛ ነው ። መሆን ስለምፈልገው ፣ እንድትሆኑ ስለምፈልገው እና መሆን ስላለብን!
إظهار المزيد3 759
المشتركون
-424 ساعات
-57 أيام
-3330 أيام
جاري تحميل البيانات...
القنوات المماثلة
سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
سبتمبر '26
سبتمبر '26
+2
في 0 قنوات
أغسطس '26
+106
في 1 قنوات
Get PRO
يوليو '26
+111
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '26
+98
في 2 قنوات
Get PRO
مايو '26
+66
في 1 قنوات
Get PRO
أبريل '26
+67
في 5 قنوات
Get PRO
مارس '26
+46
في 1 قنوات
Get PRO
فبراير '26
+47
في 5 قنوات
Get PRO
يناير '26
+70
في 6 قنوات
Get PRO
ديسمبر '25
+31
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '25
+28
في 3 قنوات
Get PRO
أكتوبر '25
+55
في 2 قنوات
Get PRO
سبتمبر '25
+44
في 2 قنوات
Get PRO
أغسطس '25
+47
في 2 قنوات
Get PRO
يوليو '25
+63
في 3 قنوات
Get PRO
يونيو '25
+51
في 1 قنوات
Get PRO
مايو '25
+72
في 1 قنوات
Get PRO
أبريل '25
+109
في 4 قنوات
Get PRO
مارس '25
+186
في 3 قنوات
Get PRO
فبراير '25
+60
في 1 قنوات
Get PRO
يناير '25
+108
في 2 قنوات
Get PRO
ديسمبر '24
+114
في 1 قنوات
Get PRO
نوفمبر '24
+116
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '24
+140
في 5 قنوات
Get PRO
سبتمبر '24
+110
في 3 قنوات
Get PRO
أغسطس '24
+105
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '24
+35
في 1 قنوات
Get PRO
يونيو '24
+1 760
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '24
+1 159
في 2 قنوات
Get PRO
أبريل '24
+1 187
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '24
+2 641
في 2 قنوات
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 02 سبتمبر | +2 | |||
| 01 سبتمبر | 0 |
منشورات القناة
ያው ዱንያ አይደል ? ሁሉም ይመኛል ሁሉም ያቅዳል ... ሁሉም ምኞትና እቅዱ ሁሌ ተደስቶ መኖር ነው።
ግን ምድር ይህን ትፈቅዳለች ? በወጣቶች የነገ ተስፋ በየዘመኑ እየተገረመች " ካለፉት የማይማሩ ብኩን ነፍሶች " የምትል ይመስለኛል ።
በቃ ከፊሉ ያለመውን ይኖራል ... ከፊሉ ካለመው ትንሽ ዝቅ ብሎ ይኖራል አብዛኛው እኖራለው ብሎ የማያስበውን ህይወት ኖሮ ያልፋል ይህ የዚች ምድር ህግ ነው ።
ይህን ስላችሁ ተስፋ ቁረጡ አይደለም ግን ብቻ እንጃ እንዴት እንደማስረዳም ብቻ የትውልዱ ማለቂያ የለሽ ምኞት የህይወትን ትክክለኛ ገፅ ከመጋፈጥ ብዙ ያሰንፋል.... ህይወት ታጋያችሁ ብቻ ነች ።
| 2 | ህይወት ከአዛን እስከ ሰላት ያለ የቆይታ ጊዜ ነው ይሉ የለ ..... የምን ትካዜ ነው ? ቀድማችሁ ምኞታችሁን ግደሉ ... ከዛም በመሞት ህያው ትሆናላችሁ ። | 196 |
| 3 | ብዙ ጊዜ ነገራቶች እስኪረጋገጡ ድረስ እይታ ይነፈጋቸዋል ። ጥቅም አልባነታቸውን ለማጉላት ...አለመጥቀማቸውን ለማረጋገጥ ይለፋባቸዋል ። ከዚያም ጥቅማቸው ሲረጋገጥ በነሱ ላይ ጥቅመኝነት ባመነጨው ጉልበት ይለፋል ። ከመቶ አመታት በፊት አሁን በስልጣኔ ማማ ላይ ያሉት ምዕራባዊያን የጨለማው ዘመን ውስጥ ነበሩ...ያኔ ሙስሊሞች በሁሉም ዘርፍ በረቀቁበት እና በጥልቅ ነገሮች ውስጥ ሰጥመው ጥናት ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ምዕራባዊያን በሴት ልጅ ሰው መሆን ላይ ሙሉ እምነት አልነበራቸውም ...ምናልባት ሴት ልጅ በአፈጣጠር ሂደት ውስጥ ያላለቀች ወንድ ትሆን ? ምናልባት ፈጣሪ ተሳስቶ የፈጠራት ፍጡር ናት...አይ ወንድ ለመፍጠር በሚደረግ ሂደት ውስጥ ከሽፎ የተፈጠረች ፍጡር ነች ! አይ ሴትማ የስሜት ሙሌት ነች ! እያሉ በድንቁርና ሲንቀዋለሉ ኢስላም ግን ከሺ አራትመቶ አመታት በፊት ጉዳዩን ዘግቶ ነበር ። በሴትና ወንድ መሀል መበላለጥ ያለው በእምነት ጥንካሬና በፈጣሪ ፍራቻቸው ልክ ብቻ መሆኑን አስረግጦ ፅፎ ብዕሩ ደርቆ ነበር።
እና ከሺ አመት በኋላ ደርሶ መቆርቆር ምንድነው ? ደግሞም በነሱ ሞቅታ ግላ ነፃ-ነቷን ያወጀች ሴት መውደቂያዋ የነሱው ጥቁር እስር ቤት ውስጥ ነው ።
እንደ ሙስሉም ማህበረሰብ ለሴት የሚሰጠው ቦታ ልክ አለመሆኑን አምናለሁኝ ... በሚገባችሁ መልኩ እንዳልያዝናችሁ ረሱል አደራ ባሉት መልኩ አደራችንን እንዳልተወጣን እቀበላለሁኝ እንደውም የዛን ሀሳብ አቀንቃኞቼ ወንዶች ሲቃወሙ ደስ አይለኝም አልኖርነውምና ግን ግን ዲኑ ከማንም ከምንም በላይ አልቋችኋል እሱን አውቃለው ። አማኙ ልክ ባይሆኑም እምነቱ ቦታችሁን አውቆ አስጠብቋል .... የኛው ወንዶቹ ጉዳይ የኛው የቤት ስራ ሆኖ የውጪውን ግን እናንተው ሞግቱት ቦታችሁን ክብራችሁን ታውቃላችሁና ።
ያው ለኛ ወንዶቹም አደራችንን የማንበላ እንድንሆንና ወደአቅላችን እንዲመልሰን ዱዓ አድርጉልን ። | 240 |
| 4 | በዚም አለ በዛ ሰው ደስ የሚል ነገር ነው ።
ለጥቂት ጊዜያት ለተመሣሣይ ነገ ልንታገል ከመጣን አይቀር ተጋግዘንና ተዛዝነን ብናልፍ ... ሞት መምጫው አይታወቅም አይደል ? እስኪመጣ ሌላ ሞት ሆኑን ሰው ባናስጨንቅ መኖርን ባናጣብብ ።
ሰው ሲደሰት ደስ አይልም ?
ሰው ሲስቅ አያምርም ?
ሰው ሲዋደድ አይስብም ?
ለየትኛው ህይወት ነው ምንባላው ? ተውዋ ከእውነታው አንሽሽ ይህ ህይወት በጋራ እንጂ በግል አያምርም ።
እስቲ እንዋደድ ..እንተሳሰብ ልንበሰብስ አይደል ? ቢያንስ ስንኖር እንኑር ። | 339 |
| 5 | ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ
የቂያም ቀን የእሳት ሰዎች ወደ ጀነት ይቀርባሉ፣ ያማረ መዓዛዋን ያሸታሉ ፣ ወደ ፎቆቿም ይመለከታሉ ፣አላህ ለነዋሪዎቿ ያዘጋጀውን ይመለከታሉ ። ከዛም ተጣሪ እንዲህ በማለት ይጣራል " ከጀነት አርቋቸው ከሷ ድርሻ የላቸውም"
እነሱም ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ማንም ተቆጭቶ በማያውቀው መልኩ እየተቆጩ ይመለሳሉ። ጌታችን ሆይ ምናለ ይህንን ምንዳ ፣ ያዘጋጀኸውን ሳታሳየን እሳት ብታስገባን ይቀለን ነበር ይላሉ።
አላህም ይላቸዋል"እሱን ፈልጌ ነው ያሳየኋቹ።
ብቻችሁን ስትሆኑ በትላልቅ ወንጀል ከኔ ጋር ትዋጋላቹ፤ከሰዎች ጋር ስቶኑ በተቃራኒው ትሆናላቹ፣ ሰዎችን ፈራቹ እኔን ግን አልፈራቹኝም፣እነሱን አላቃቹ እኔን ግን አላላቃቹኝም፣ሰዎችን አፈራቹ እኔን ግን አላፈራቹኝም፣ ለሰዎች ብላቹ ወንጀል ተዋቹ ለኔ ብላቹ ግን አልተዋቹም። ዛሬ ይህንን ፀጋ ከመከልከሌ ጋር አሳማሚ ቅጣት አቀምሳቹሀለው።
©️ | 334 |
| 6 | ሲሰዋ እንደትላንት ትዝ ይለኛል .... ግን አንድ አመት አለፈው አላህ ቀብሩን ኑር ያርግለት ። | 365 |
| 7 | አንዳንዴ ኡማው የወከላቸው ሰዎች ያላቸው እሳቤ ሲታይ ተስፋ ያስቆርጣል ።
የሆነ ቀን "ለምሳሌ 1 ሚሊየን ህዝብ ቢሞትብንም 119 ሚሊየን ያልሞተ ህዝብ አለንና እንደሰት " የሚል ሀሳብ ይዞ የሚያብራራ ሰው ( ሀላፍትና የተሰጠው ) ሰው አይቼ ብርግግ እንዳልኩ አለሁኝ ። ትላልቅ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች በግል እሳቤያቸው ብዙሀኑን ሲያስጠቁም አይተናል.... ለወረዱ መጠቃቀሚያዎች ሲበላሉም አይተናል ።
ብቻ ሲወራ የሚቀፍ ርዕስ ነውና እንተወዉ እኛው ነን የነገ ተረካቢዎቹ .. እኛው ነን ብዙ ሀላፍትና ያለብንና በዲኑም በዱንያ እንበርታ በተለይ በተለይ በዲን ... አኽላቅና ትምህርት ላይ አደራ ። | 398 |
| 8 | !!! | 428 |
| 9 | ሰው ሲደሰት ማየት የሚያመነጨው እርካታ እንዴት ያለ ውብ ነው በአላህ ።
ሀቢቢ ﷺ ከሰው ሁሉ ምርጡ ማነው ተብለው ተጠየቁና በመጨረሻም " ሰዎችን ከክፋቱ የጠበቀ " አሉ ። ለሰዎች ደስታ ሰበብ የሆነስ ምን ይሆን ደረጃው ?
-አለምን ከሞላው የኔነት ጭጋግ እንራቅ
-ካልጠቀመኝ ምናገባኝ ከሚል አስጠሊ እሳቤ እንሽሽ
- ለሰዎች በጎ መዋል ..ሰዎችን ማስደሰት የትርፍ ጊዜ ተግባር እስኪመስል ህይወት ተጨማላልቃለችና እሳቤያችንን እናፅዳ ።
ህይወትን የአመታት ትግል አናድርገው በአላህ ... በቃ ሰው ሄዶ ሄዶ ሰው ነው ! አስደስቱ ተደሰቱ ኑሩ ተኗኗሩ ።
ደስታችሁን በሌሎች ውብ ሰዎች ደስታ ስር ፈልጉ🤍 | 475 |
| 10 | አንዳንዱ በሚሰራት ትንሽ ስራ ለቤተሰቡ የሚችለውን እያረገ የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት ይመራል .... ከፊሉ በየቀኑ ብዙ ሺዎችን እያዘዋወረ የቤተሰብነትን ጣዕም ትቶ የተቻኮለ ሀያት ይኖራል ።
ልክ እንዲሁ አንዳንዱ ከእጦቱም በተጨማሪ የሰዎችን ጓዳ እያየ መብቃቃትም ደስታም አጥቶ ይኖራል ... ከፊሉ አላህ ሀብት ሰጥቶት በአግባቡ እየተጠቀመ ተረጋግቶ በደስታ ይኖራል ።
ደስታና መረጋጋት በገንዘብ መጠን የሚወሰኑ ሳይሆኑ ሁሉም ለህይወት ባለው ፍልስፍና የሚገሩ ናቸው ።
ዱንያ ለናንተ ምንድናት ? እሱ ነው ዋናው ነገር ። | 533 |
| 11 | ዜናው
" -የዋጋ ግሽበቱ በዚ በዚ ፐርሰንት ጨምሯል
- በዚ በዚ አካባቢ ድርቅ ተከስቶ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ህዝቦች ረሀብ ተደቅኖባቸዋል
- ይህን ያክል ሰዎች ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለው እንዲህ የሚሆኑት ታግተዋል
-እዚ እዚህ አካባቢ ለአመታት የቀጠለው ጦርነት ተባብሷል "
ህዝቡ
"- በእግሬ ሄጄ የታክሲውን ለቤተሰቤ ዳቦ ልግዛበት ?
- በየት በኩል ሄጄ ቤተሰቤን ከርሀብ ልታደግ
- ልጆቼን እንዴት ላስተምር
መንግስት
" -ግብር ጨምሩ
- ጦቢያ ለአለም አርዓያ የሚሆን እድገት አስመዝግባለች
- ጦቢያ ለነዋሪዎቿ ምቹና ለቱሪስቶች ተመራጭ ሆናለች
- ቢሊየን መድበን የሆነ ጫካ እናለማለን "
ኧረ መንግስትና ኑሮ - መንግስትና ህዝቡ አልስማማ አሉኮ .... ዱባይ እየኖሩ ነው እንዴ የሚመሩን😭 | 67 |
| 12 | የምትጓጉለት ነገ " ድካም ፣ አለመቻል እና መገደብ'ን " የያዘ ነው ። አሁንን ለመኖር እንጣር ... ሲደክመን እንረፍ ስንሰበር ስብራታችንን እየሰነጠቅን መታመማችንን አቁመን ወደመፍትሄ እንሩጥ ።
በሉ ዛሬን እንኑር🤍 | 683 |
| 13 | በጣም ዛልና ?
ሰዎች ተስፋ እየቆረጡ አንገታቸውን ለገመድ እየሰጡ ነው .... ወጣቶች ብዙ አልመው እርምጃ ለመጀመር ሲያስቡ ተተብትበው እየወደቁ ነው ። ውስጡም ውጪውም ለውድቀት የሚጣራ አልፎም የሚጠልፍ ጩኸት ሆኖባቸው ደክሟቸዋል ። አቃጆች አቅደው አቅደው ማህበረሰቡን በማያልቅ አስከፊ አዙሪት ነክረውት ተስፋውን በየዙሩ በየከፍታና ዝቅታው እያሳሱት ነው ..... ግን ይሁን ግድ የለም ።
ከአቃጆችም በላይ አቃጁ አላህ አለ አብሽሩ .... ሴራዎቻቸው ሁሉ ፈርሰው የተሻለ ነገር ይመጣል። ብቻ ታገሉ አትድከሙ....ነፍሳችሁን አበርቷት አላህ አለ.... ነገ አለ በሏት ። አብሽሩማ የልፋታችሁ ውጤት ህመም እንኳ ቢሆን አላህ ጋር ሚዛን አለው .... ጊዜው እስኪመጣ ግን ታገሱ በምትችሉት ሁሉ ታገሉ .... ጊዜው ቀርቧል ኢንሻአላህ ። | 610 |
| 14 | ለመኖር ስል እየነካካው ያለኋቸው ርዕሶች ሁላ ከመኖር ሲያርቁኝ ነው የማስተውለው ። አማኝ ለመሆን ስጥር ከጌታዬ መራቅ ለምን ይሰማኛል ? ለማወቅ ስጥር የውሸት ትርክት የማጎር አይነት ስሜት....ለመጠንከር ስሞክር ድካም... ለምን ?
ጊዜያቶች ባለፉ ቁጥር እቺ አለም የውሸት ሹራብ እየደረበች ...የእውነትን ብርሀን እያደበዘዘች ...የመኖርን ጣዕም እያጎመዘዘች ነው ።
እቺ አለም እንደነበረችው አይደለችም...መሆን እንዳለባትም አይደለችም ። ከዘመናት በፊት የተቀየሰ አዲስ መንገድ ሳይኖር አይቀርም ። ይህ መንገድ ሁሉን ነገር አሳጥቶናል ...እምነታችንን ፣ ህይወታችንን ፣ እኛነታችንን ሁሉ ነጥቆናል ። አማኝነትን በራስ ወዳድነትና በተጨቃጫቂነት ለውጦብናል...ህይወታችንን ለሌሎች በማቀበል ስለሌሎች የሚገበር ተራ የጊዜያት ጥርቅም አድርጎብናል...እኛነታችንን ለማናውቀው እና ፍፁም ደስታችንን ለሚመጠው ሌላ ነገር አሳልፎ ሰጥቶብናል ።
ይህ ሌላ ነገር ግን ምንድነው ? እየኖርን ያለነው ምንድነው ? ምን እየተፈጠረ ነው ግን?
ብቻ መኖር ያለብን ህይወት አለ ....ያን ህይወት ፈልገን ማግኘት አለብን ። | 686 |
| 15 | ሁለት ወፎች በአንድ ሽቦ አጥር ውስጥ ታስረዋል ... ወፎቹ በተጣሉ ቁጥር አሳሪው ላባቸውን ይነቅላል ። በዛ ቅፅበት መጣላታቸውን ትተው ያጉረመርማሉ ...ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደጥላቸው ይመለሳሉ አሳርያቸውም ላባቸውን መንቀል ይቀጥላል ።
ከረጅም ጊዜ በኋላ የማሰሪያውን በር ከፈተላቸው ግን ... ግን አልበረሩም አላመለጡም ... አዎ ክንፍ አልነበራቸውም ።
እኚህ ወፎች እኛው ነን ... እኛው ሙስሊሞች !
ሀቢቢﷺ እንዲህ ቅጡ የጠፋውን ኡማቸውን ቢያዩ እንዴት ያማቸው ይሆን ... የማንም መጫወቻ ሆኖ እርስ በርሱ ለመቶ አመታት ሲታገል የከረመውን ኡማ ቢያዩ ምን ያህል ያማቸው ይሆን ? ጠላቶቻቸው ለመቶ አመታት የሚዘልቅ ሴራ አሲረው ኢስላምን ያፈራርሳሉ የነሱ ኡመት እርስ በርስ ይፋተጋል ... ያለአላማ የርስ በርስ ትግል ራሱንና ዲኑን ያደክማል ። | 653 |
| 16 | ውጤት ጠባቂዎች ...... አላህ ኸይሩን ያሰማችሁ🤍 | 631 |
| 17 | መጨረስ አልቻልኩም ማለት የፈለኩትን አላልኩም ...ቢሆንም ይሁን በቃ | 699 |
| 18 | በቁሙ የጊዜ ክምር ማንነቱን በከንቱነት ወዳለመኖር እንዲሄድ የፈቀደው ትውልድ ከምን ጊዜውም በላይ ለእምነቱ ተቆርቋሪ ሆኗል ¡
ሁላችንም አንድ ቁስል ተሸክመናል ..... አለመኖር። ይህን ቁስል የምናስተናግድበት ሂክማውም ...የመኖር አቅሙም የለንም ምክንያቱም አለመኖራችንን ለመርሳት ሄደን የተጠለልንበት ጥላ "ዲን" ነው ።
የእምነታችንን መሠረቶች ሁሉ ከማመን በዘለለ ወደነፍሳችን አላስገባንም .... አምልኮ የምንለው ሁሉ አድካሚ ድርጊት ሆኖብን የጊዜ ክምራችንን ሁሉ በባዶነት ውስጥ እየፈረካከስን እየሞላን ነን ።
ነፍሳችንን አለማችንን የምንዋጋበት አንድ ተራ መሣሪያ የሌለን ጦረኛ ነን .... ሀሳባችንን አስገዝተን ያለ አንድ መሣሪያ ከተመሣሣዬ "የሀሳብ ባርነት" ውስጥ ካለ አካል ጋር እየተዋጋን አለመኖራችንን ...ባርነታችንን የዘነጋን ።
እያልኖርን ያለነውን ዲን ሽሽት ዲን ስር የተጠለልን ... መገዛት ጠንቶን ተገዢ በሚያስመስል ርዕስ ውስጥ የምንርመሰመስ አመፀኞች ። ሌት ተቀን ሰዎችን አተልቀን አላህን አሳንሰን በ አመፅ ባህር ውስጥ የምንዋኝ ግና በእምነታችን ፍፁማዊ ለመምሰል ሌላ የማስመሰል ትግል የምንታገል ወዳቂዎች ።
በጌታችን ትዕዛዝ ውስጥ መኖር ጠንቶን የአለመኖርን መራራ ፅዋ እየቀመስን አለመታዘዛችንን ሽሽት ወደዲኑ ተሸጉጠን ለመርሳት የምንጥር እፍረት የለሾች ።
ማነን ? ቆይ ማነን ?
ቁርጭራጭ የህክምና ፅሁፎችን አንብበን ሀኪም የሆንን ? የሆነ ቦታ ስለግንባታ አንብበን ኢንጂነር የሆንን ? እስቲ ማነው በቁርጥራጭ ንባብ ዶክተር የሚጋፈጠው ? ማነው በሶስት ቀን ፖድካስት እራሱን አዋቂ አርጎ ኢንጂነር የሚከራከረው ?
እስልምናና አስተምህሮቱ ከህክምና ያነሰ ቦታ ነው ያላቸው ? የእስልምና አስተምህሮት ከኢንጂነሪንግ ያነሰ ቦታ ነው ያለው ? ምነው ዲናችን ላይ ሲሆን ደረታችን አበጠ ? የኪታብ ስም የማያነበው ሁሉ ምንው አዋቂ ነኝ ብሎ ቁጭ አለ !
" ያወከውን አስተላልፍ " የሚል ሀዲስ ስላለ ነው ? እሺ ልክ ነው ግን መች አወቅን ?ለእያንዳንዱ መረጃ ወደ ሰርች ባር የሚሮጥ ሁሉ ዲን ላይ ቃዲ ይመስል ሲያከፍር ሲያሰልም ... ለዲኑ ሲታገል ሲሳደ* ይውላል ።
ኧረ ምን አይነት እፍረት የለሽ ትውልድ ነን በአላህ ። | 740 |
| 19 | አሁን ረጅጅም ፅሁፍ ልለቅ ነው ወይ ደግሞ አጭር ። ወይ ወቀሳ ነው ወይ ሌላ ነገር ነው .... ለማን እንደምፅፍ አላቅም ለራሴ ...ለናንተ ? እንጃ ብቻ | 454 |
| 20 | ©️©️©️
ቁድወቱና ፊል ኢብቲሳመህ
ስለ ዉዱ ነብያችንﷺ ሌሊት አብዛኞቻችን እንሰማለን እንዲህ ሲባል...
"ረሱል ﷺ ለሊት እግራቸው እስኪሰነጠቅ ድርስ ይቆሙ ነበር... ኡመቴም እያሉ ያለቅሱ ነበር።"
በዚህ መንገድ ግን አስበነው እናውቃለን? እንደዚያ ሌሊቱን በእንባ ሚያሳልፉት ነብይﷺ ፤ ቀኑን በፈገግታ እንጂ አይታዩም ነበር።
ጀሪር ኢብኑ ዓብዲላህ እንዲህ ይላል...
"በሕይወቴ አንድም ቀን አላለፈም የኔው ነብዬ ﷺ ሲያዩኝ ፈገግ ያሉ ቢሆን እንጂ"
በፈገግታቸው ነው ከሰው ሁሉ ልብ የገቡት።
በፈገግታቸው ነው ያነባን አይን ያበሱት
በፈገግታቸው ነው የሰሃባን ተስፋ ያለመለሙት
ፈገግታቸው አንድ የጥሪ መንገድም ነበር።
ፈገግታቸው የመሃባ መንገድም ነበር።
ፈገግታቸው ብዙ ብዙ ነገር ሆኖ አልፏል።
ለዚያም ነው በኛ ዉስጥም ሱና ሊሆን የቻለው
ፈገግ እንበል ፣ የሰዎችን ሕይወት በፈገግታችን እናድሰው የቁድዋችን የተፈቃሪያችን ነብይ ﷺ መንገድ ነዉና
ሰሉ ዓለል ሀቢብ | 583 |
