👳🏽ባለዕዳው
Open in Telegram
ሁሉም ስለእኛ ነው ። መሆን ስለምፈልገው ፣ እንድትሆኑ ስለምፈልገው እና መሆን ስላለብን!
Show more3 752
Subscribers
-624 hours
-87 days
-3930 days
Data loading in progress...
Similar Channels
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
September '26
September '26
+6
in 0 channels
August '26
+106
in 1 channels
Get PRO
July '26
+111
in 0 channels
Get PRO
June '26
+98
in 2 channels
Get PRO
May '26
+66
in 1 channels
Get PRO
April '26
+67
in 5 channels
Get PRO
March '26
+46
in 1 channels
Get PRO
February '26
+47
in 5 channels
Get PRO
January '26
+70
in 6 channels
Get PRO
December '25
+31
in 0 channels
Get PRO
November '25
+28
in 3 channels
Get PRO
October '25
+55
in 2 channels
Get PRO
September '25
+44
in 2 channels
Get PRO
August '25
+47
in 2 channels
Get PRO
July '25
+63
in 3 channels
Get PRO
June '25
+51
in 1 channels
Get PRO
May '25
+72
in 1 channels
Get PRO
April '25
+109
in 4 channels
Get PRO
March '25
+186
in 3 channels
Get PRO
February '25
+60
in 1 channels
Get PRO
January '25
+108
in 2 channels
Get PRO
December '24
+114
in 1 channels
Get PRO
November '24
+116
in 0 channels
Get PRO
October '24
+140
in 5 channels
Get PRO
September '24
+110
in 3 channels
Get PRO
August '24
+105
in 0 channels
Get PRO
July '24
+35
in 1 channels
Get PRO
June '24
+1 760
in 0 channels
Get PRO
May '24
+1 159
in 2 channels
Get PRO
April '24
+1 187
in 0 channels
Get PRO
March '24
+2 641
in 2 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 04 September | +3 | |||
| 03 September | +1 | |||
| 02 September | +2 | |||
| 01 September | 0 |
Channel Posts
ለስልጣኔ ያዘነበልኩ አይደለሁም ... የሰው ነፍስ ከተፈጥሮ በመራቅ ውስጥ ድካም እንጂ እርካታ ታገኛለች ብለው ከማያምኑት ነኝ ። ስልጣኔ ስላችሁ ማሽኖችን ተገን ያደረገ ህይወት ... በመስታወጥ የታጠረ ከተማ ... ዛፍና ግንዱ በቋሚ ብረቶች የተተኩበት መንገድ ...ወዘተ ።
የሰው ልጅ ትላልቅ ፎቆችን በመመልከት ... በመስታወት የተለበጡ ከተሞችን በመጎብኘት ለመደሰት መሞከር መች እንደጀመረ አላውቅም ...እናንተ ያስደስታችኋል ? አትደክሙም አትዝሉም ?
ከተፈጥሮ ጋር ስውር ቋጠሮ ያለን ፍጡሮች ነን ... ማናችንም ተራሮችን ወንዝና ሸለቆዎችን ስንመለከት የሚሰማንን ስሜት በሌላ አናገኝም ።
የዛሬ ሀያ አመት ምን አይነት ህይወት እንደሚኖር አስቡት 😶🌫 ሮቦት ውር ውር የሚልባት ነፍስ አልባ አለም 🙌
ደግ አደራችሁን 🤍
| 2 | ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ታውቃላችሁ ?
"ጌታችን ፈጠርኳችሁ ለዚህች ምድርም ኸሊፋ አደረኳችሁ" አለን ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ ? እቺ ምድር የኔ ናት በናንተ ጥረትና በኔ ህግ የምታብብ .... እቺ ምድር ከኔ ለናንተ የተሰጠ አደራ ነው አደራችሁን ጠብቃችሁ ሀላፊነታችሁን ከተወጥታችሁ ሽልማታችሁን የምትቀበሉበት ቀን ይመጣል ... እቺ ምድር አይደለም ለሰው አይደለም ለእንስሳ ንፋስ እዚና እዛ ለሚጥላቸው ሰብሎች የተመቸች ልታደርጓት ይገባል እያለን ነው ።
እኛስ ምን አደረግን ? እኛ ግን ሀላፊነታችንን ሽምጥጥ አድርገን ምድር በክህደት ጨለማ ስትሰጥም በሰላም የምንተኛ ከሀጂ ሆነናል .... አደራዬ ናት ጠብቋት አስውቧት በተባልንባት ምድር ተሳዳጅና ተሸናፊ መሆንን ተቀብለን በነሱው ጨለማ አለም ለመመቻቸት የምንጥር "ከንቱ"ዎች ሆነናል ።
ህፃናቶች ለመኖር የሚፈሯት የባለጌዎች መጫወጫ ስትሆን ምንም እንዳልተፈጠረ በሰላም እየኖርን ያለን ሆነናል .... ምን ነካን ? ምንድነው የሆንነው ? እንዲው ነው የምንቀጥለው ?
ደሞም ቃላቸውን ለጌታቸው ለመሙላት የሚጥሩትን የምንጎትት ሌላ የተሸናፊነት ጭቃ ጠፍጥፎ የሰራን ድኩሞች ሆነናል... አባወራ ቤቱ በሰፈር ዱርዬ ሲመራበት ጥጉን ይዞ አጥንት ይመጠምጣል ? ምን ተክቶን ነው ግን ? | 175 |
| 3 | ከዚ ቪዲዮ በኋላ ኖርማል መሆን አቅቶኛል ... ምንም ልረሳው አልቻልኩም በየጊዜው ነው የማየው ።
እናንተም እዩት ... የትኛውን መይት አካላችንን እንደሚያነቃ ባላቅም እዩት | 79 |
| 4 | ሰው ራሱን ይፈራል ... የነገ እጣውን እያወቀ ከራሱ ሽሽት በሰዎች ህይወት ላይ ራሱን ይጠምዳል ።
ማናችንም ራሳችንን አናውቅም ... ራሳችንን መጋፈጥ አንደፍርም ራሳችንን ለማወቅ አልሞከርንም ።
ከዛ ትንሽ ትንሽ መኖር እንጀምራለን ....ይመስለኛል ። | 89 |
| 5 | ሰው ይወዳል ...ይጠላል ፤ ይ'ጎዳል ይካሳል ፤ ያዝናል ያለቅሳል ..... ይጨነቃል ይፍታታል ።
እኔ ብቻ ነኝ በቃ ዝም ብዬ ምኖረው 😭 ግራ እየገባኝ ነው😄 | 207 |
| 6 | ይህን ትውልድ ለመረዳት አንድ እርምጃ ሳይራመዱ ሁል ጊዜ በምክር ተመለስ ማለት ወፏን ብረሪ እንደማለት ነው ።
ብዙ ተተብትቧል ... ተማሪው ትምህርት ቤት ውስጥ ስቅጥጥ በሚል ሀል ላይ ነው ። ውጪ ላይ ዳዕዋው ልብስና መለያየት ላይ ነው ትውልዱ ትምህርት ቤት ውስጥ የምድርን ጀሀነም እያቀጣጠለ ነው ።
ለመስማት በሚከብዱ ነገሮች ትውልዱ ሰጥሟል.... ደስታ ብሎ በሚያስባቸው ነገሮች ስር በገሀድ ቢያልፍም ከኢስላም ጋር በሚጋጩ ነገሮች ውስጥ ተዘፍቋል ። ዳዒዎቻችንም ቤተቸውን ዘግተው በመስኮታቸው ቀዳዳ "ተው" ከማለት አልፈው ያሉበት ሄደው እጃቸውን በመያዝ ለማውጣት አልደፈሩም "ከመጡ ይምጡ ካልመጡ አይምጡ እሳቱ ለነሱ ነው " በሚል እሳቤ የሚደረግ ዳዕዋ ፍሬ አለው ? ከልጅነት እስከ ጎልምስና ጠላቶቻቸው ተብትበው አስረዋቸው የምን ቸል ማለት ነው ?
እስቲ ትውልዱ የት ነው ብላችሁ ለማጣራት ሞክሩማ 🙌 | 256 |
| 7 | ያው ዱንያ አይደል ? ሁሉም ይመኛል ሁሉም ያቅዳል ... ሁሉም ምኞትና እቅዱ ሁሌ ተደስቶ መኖር ነው።
ግን ምድር ይህን ትፈቅዳለች ? በወጣቶች የነገ ተስፋ በየዘመኑ እየተገረመች " ካለፉት የማይማሩ ብኩን ነፍሶች " የምትል ይመስለኛል ።
በቃ ከፊሉ ያለመውን ይኖራል ... ከፊሉ ካለመው ትንሽ ዝቅ ብሎ ይኖራል አብዛኛው እኖራለው ብሎ የማያስበውን ህይወት ኖሮ ያልፋል ይህ የዚች ምድር ህግ ነው ።
ይህን ስላችሁ ተስፋ ቁረጡ አይደለም ግን ብቻ እንጃ እንዴት እንደማስረዳም ብቻ የትውልዱ ማለቂያ የለሽ ምኞት የህይወትን ትክክለኛ ገፅ ከመጋፈጥ ብዙ ያሰንፋል.... ህይወት ታጋያችሁ ብቻ ነች ። | 297 |
| 8 | ህይወት ከአዛን እስከ ሰላት ያለ የቆይታ ጊዜ ነው ይሉ የለ ..... የምን ትካዜ ነው ? ቀድማችሁ ምኞታችሁን ግደሉ ... ከዛም በመሞት ህያው ትሆናላችሁ ። | 323 |
| 9 | ብዙ ጊዜ ነገራቶች እስኪረጋገጡ ድረስ እይታ ይነፈጋቸዋል ። ጥቅም አልባነታቸውን ለማጉላት ...አለመጥቀማቸውን ለማረጋገጥ ይለፋባቸዋል ። ከዚያም ጥቅማቸው ሲረጋገጥ በነሱ ላይ ጥቅመኝነት ባመነጨው ጉልበት ይለፋል ። ከመቶ አመታት በፊት አሁን በስልጣኔ ማማ ላይ ያሉት ምዕራባዊያን የጨለማው ዘመን ውስጥ ነበሩ...ያኔ ሙስሊሞች በሁሉም ዘርፍ በረቀቁበት እና በጥልቅ ነገሮች ውስጥ ሰጥመው ጥናት ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ምዕራባዊያን በሴት ልጅ ሰው መሆን ላይ ሙሉ እምነት አልነበራቸውም ...ምናልባት ሴት ልጅ በአፈጣጠር ሂደት ውስጥ ያላለቀች ወንድ ትሆን ? ምናልባት ፈጣሪ ተሳስቶ የፈጠራት ፍጡር ናት...አይ ወንድ ለመፍጠር በሚደረግ ሂደት ውስጥ ከሽፎ የተፈጠረች ፍጡር ነች ! አይ ሴትማ የስሜት ሙሌት ነች ! እያሉ በድንቁርና ሲንቀዋለሉ ኢስላም ግን ከሺ አራትመቶ አመታት በፊት ጉዳዩን ዘግቶ ነበር ። በሴትና ወንድ መሀል መበላለጥ ያለው በእምነት ጥንካሬና በፈጣሪ ፍራቻቸው ልክ ብቻ መሆኑን አስረግጦ ፅፎ ብዕሩ ደርቆ ነበር።
እና ከሺ አመት በኋላ ደርሶ መቆርቆር ምንድነው ? ደግሞም በነሱ ሞቅታ ግላ ነፃ-ነቷን ያወጀች ሴት መውደቂያዋ የነሱው ጥቁር እስር ቤት ውስጥ ነው ።
እንደ ሙስሉም ማህበረሰብ ለሴት የሚሰጠው ቦታ ልክ አለመሆኑን አምናለሁኝ ... በሚገባችሁ መልኩ እንዳልያዝናችሁ ረሱል አደራ ባሉት መልኩ አደራችንን እንዳልተወጣን እቀበላለሁኝ እንደውም የዛን ሀሳብ አቀንቃኞቼ ወንዶች ሲቃወሙ ደስ አይለኝም አልኖርነውምና ግን ግን ዲኑ ከማንም ከምንም በላይ አልቋችኋል እሱን አውቃለው ። አማኙ ልክ ባይሆኑም እምነቱ ቦታችሁን አውቆ አስጠብቋል .... የኛው ወንዶቹ ጉዳይ የኛው የቤት ስራ ሆኖ የውጪውን ግን እናንተው ሞግቱት ቦታችሁን ክብራችሁን ታውቃላችሁና ።
ያው ለኛ ወንዶቹም አደራችንን የማንበላ እንድንሆንና ወደአቅላችን እንዲመልሰን ዱዓ አድርጉልን ። | 336 |
| 10 | በዚም አለ በዛ ሰው ደስ የሚል ነገር ነው ።
ለጥቂት ጊዜያት ለተመሣሣይ ነገ ልንታገል ከመጣን አይቀር ተጋግዘንና ተዛዝነን ብናልፍ ... ሞት መምጫው አይታወቅም አይደል ? እስኪመጣ ሌላ ሞት ሆኑን ሰው ባናስጨንቅ መኖርን ባናጣብብ ።
ሰው ሲደሰት ደስ አይልም ?
ሰው ሲስቅ አያምርም ?
ሰው ሲዋደድ አይስብም ?
ለየትኛው ህይወት ነው ምንባላው ? ተውዋ ከእውነታው አንሽሽ ይህ ህይወት በጋራ እንጂ በግል አያምርም ።
እስቲ እንዋደድ ..እንተሳሰብ ልንበሰብስ አይደል ? ቢያንስ ስንኖር እንኑር ። | 394 |
| 11 | ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ
የቂያም ቀን የእሳት ሰዎች ወደ ጀነት ይቀርባሉ፣ ያማረ መዓዛዋን ያሸታሉ ፣ ወደ ፎቆቿም ይመለከታሉ ፣አላህ ለነዋሪዎቿ ያዘጋጀውን ይመለከታሉ ። ከዛም ተጣሪ እንዲህ በማለት ይጣራል " ከጀነት አርቋቸው ከሷ ድርሻ የላቸውም"
እነሱም ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ማንም ተቆጭቶ በማያውቀው መልኩ እየተቆጩ ይመለሳሉ። ጌታችን ሆይ ምናለ ይህንን ምንዳ ፣ ያዘጋጀኸውን ሳታሳየን እሳት ብታስገባን ይቀለን ነበር ይላሉ።
አላህም ይላቸዋል"እሱን ፈልጌ ነው ያሳየኋቹ።
ብቻችሁን ስትሆኑ በትላልቅ ወንጀል ከኔ ጋር ትዋጋላቹ፤ከሰዎች ጋር ስቶኑ በተቃራኒው ትሆናላቹ፣ ሰዎችን ፈራቹ እኔን ግን አልፈራቹኝም፣እነሱን አላቃቹ እኔን ግን አላላቃቹኝም፣ሰዎችን አፈራቹ እኔን ግን አላፈራቹኝም፣ ለሰዎች ብላቹ ወንጀል ተዋቹ ለኔ ብላቹ ግን አልተዋቹም። ዛሬ ይህንን ፀጋ ከመከልከሌ ጋር አሳማሚ ቅጣት አቀምሳቹሀለው።
©️ | 388 |
| 12 | ሲሰዋ እንደትላንት ትዝ ይለኛል .... ግን አንድ አመት አለፈው አላህ ቀብሩን ኑር ያርግለት ። | 413 |
| 13 | አንዳንዴ ኡማው የወከላቸው ሰዎች ያላቸው እሳቤ ሲታይ ተስፋ ያስቆርጣል ።
የሆነ ቀን "ለምሳሌ 1 ሚሊየን ህዝብ ቢሞትብንም 119 ሚሊየን ያልሞተ ህዝብ አለንና እንደሰት " የሚል ሀሳብ ይዞ የሚያብራራ ሰው ( ሀላፍትና የተሰጠው ) ሰው አይቼ ብርግግ እንዳልኩ አለሁኝ ። ትላልቅ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች በግል እሳቤያቸው ብዙሀኑን ሲያስጠቁም አይተናል.... ለወረዱ መጠቃቀሚያዎች ሲበላሉም አይተናል ።
ብቻ ሲወራ የሚቀፍ ርዕስ ነውና እንተወዉ እኛው ነን የነገ ተረካቢዎቹ .. እኛው ነን ብዙ ሀላፍትና ያለብንና በዲኑም በዱንያ እንበርታ በተለይ በተለይ በዲን ... አኽላቅና ትምህርት ላይ አደራ ። | 434 |
| 14 | !!! | 536 |
| 15 | ሰው ሲደሰት ማየት የሚያመነጨው እርካታ እንዴት ያለ ውብ ነው በአላህ ።
ሀቢቢ ﷺ ከሰው ሁሉ ምርጡ ማነው ተብለው ተጠየቁና በመጨረሻም " ሰዎችን ከክፋቱ የጠበቀ " አሉ ። ለሰዎች ደስታ ሰበብ የሆነስ ምን ይሆን ደረጃው ?
-አለምን ከሞላው የኔነት ጭጋግ እንራቅ
-ካልጠቀመኝ ምናገባኝ ከሚል አስጠሊ እሳቤ እንሽሽ
- ለሰዎች በጎ መዋል ..ሰዎችን ማስደሰት የትርፍ ጊዜ ተግባር እስኪመስል ህይወት ተጨማላልቃለችና እሳቤያችንን እናፅዳ ።
ህይወትን የአመታት ትግል አናድርገው በአላህ ... በቃ ሰው ሄዶ ሄዶ ሰው ነው ! አስደስቱ ተደሰቱ ኑሩ ተኗኗሩ ።
ደስታችሁን በሌሎች ውብ ሰዎች ደስታ ስር ፈልጉ🤍 | 521 |
| 16 | አንዳንዱ በሚሰራት ትንሽ ስራ ለቤተሰቡ የሚችለውን እያረገ የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት ይመራል .... ከፊሉ በየቀኑ ብዙ ሺዎችን እያዘዋወረ የቤተሰብነትን ጣዕም ትቶ የተቻኮለ ሀያት ይኖራል ።
ልክ እንዲሁ አንዳንዱ ከእጦቱም በተጨማሪ የሰዎችን ጓዳ እያየ መብቃቃትም ደስታም አጥቶ ይኖራል ... ከፊሉ አላህ ሀብት ሰጥቶት በአግባቡ እየተጠቀመ ተረጋግቶ በደስታ ይኖራል ።
ደስታና መረጋጋት በገንዘብ መጠን የሚወሰኑ ሳይሆኑ ሁሉም ለህይወት ባለው ፍልስፍና የሚገሩ ናቸው ።
ዱንያ ለናንተ ምንድናት ? እሱ ነው ዋናው ነገር ። | 663 |
| 17 | ዜናው
" -የዋጋ ግሽበቱ በዚ በዚ ፐርሰንት ጨምሯል
- በዚ በዚ አካባቢ ድርቅ ተከስቶ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ህዝቦች ረሀብ ተደቅኖባቸዋል
- ይህን ያክል ሰዎች ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለው እንዲህ የሚሆኑት ታግተዋል
-እዚ እዚህ አካባቢ ለአመታት የቀጠለው ጦርነት ተባብሷል "
ህዝቡ
"- በእግሬ ሄጄ የታክሲውን ለቤተሰቤ ዳቦ ልግዛበት ?
- በየት በኩል ሄጄ ቤተሰቤን ከርሀብ ልታደግ
- ልጆቼን እንዴት ላስተምር
መንግስት
" -ግብር ጨምሩ
- ጦቢያ ለአለም አርዓያ የሚሆን እድገት አስመዝግባለች
- ጦቢያ ለነዋሪዎቿ ምቹና ለቱሪስቶች ተመራጭ ሆናለች
- ቢሊየን መድበን የሆነ ጫካ እናለማለን "
ኧረ መንግስትና ኑሮ - መንግስትና ህዝቡ አልስማማ አሉኮ .... ዱባይ እየኖሩ ነው እንዴ የሚመሩን😭 | 67 |
| 18 | የምትጓጉለት ነገ " ድካም ፣ አለመቻል እና መገደብ'ን " የያዘ ነው ። አሁንን ለመኖር እንጣር ... ሲደክመን እንረፍ ስንሰበር ስብራታችንን እየሰነጠቅን መታመማችንን አቁመን ወደመፍትሄ እንሩጥ ።
በሉ ዛሬን እንኑር🤍 | 741 |
| 19 | በጣም ዛልና ?
ሰዎች ተስፋ እየቆረጡ አንገታቸውን ለገመድ እየሰጡ ነው .... ወጣቶች ብዙ አልመው እርምጃ ለመጀመር ሲያስቡ ተተብትበው እየወደቁ ነው ። ውስጡም ውጪውም ለውድቀት የሚጣራ አልፎም የሚጠልፍ ጩኸት ሆኖባቸው ደክሟቸዋል ። አቃጆች አቅደው አቅደው ማህበረሰቡን በማያልቅ አስከፊ አዙሪት ነክረውት ተስፋውን በየዙሩ በየከፍታና ዝቅታው እያሳሱት ነው ..... ግን ይሁን ግድ የለም ።
ከአቃጆችም በላይ አቃጁ አላህ አለ አብሽሩ .... ሴራዎቻቸው ሁሉ ፈርሰው የተሻለ ነገር ይመጣል። ብቻ ታገሉ አትድከሙ....ነፍሳችሁን አበርቷት አላህ አለ.... ነገ አለ በሏት ። አብሽሩማ የልፋታችሁ ውጤት ህመም እንኳ ቢሆን አላህ ጋር ሚዛን አለው .... ጊዜው እስኪመጣ ግን ታገሱ በምትችሉት ሁሉ ታገሉ .... ጊዜው ቀርቧል ኢንሻአላህ ። | 655 |
| 20 | ለመኖር ስል እየነካካው ያለኋቸው ርዕሶች ሁላ ከመኖር ሲያርቁኝ ነው የማስተውለው ። አማኝ ለመሆን ስጥር ከጌታዬ መራቅ ለምን ይሰማኛል ? ለማወቅ ስጥር የውሸት ትርክት የማጎር አይነት ስሜት....ለመጠንከር ስሞክር ድካም... ለምን ?
ጊዜያቶች ባለፉ ቁጥር እቺ አለም የውሸት ሹራብ እየደረበች ...የእውነትን ብርሀን እያደበዘዘች ...የመኖርን ጣዕም እያጎመዘዘች ነው ።
እቺ አለም እንደነበረችው አይደለችም...መሆን እንዳለባትም አይደለችም ። ከዘመናት በፊት የተቀየሰ አዲስ መንገድ ሳይኖር አይቀርም ። ይህ መንገድ ሁሉን ነገር አሳጥቶናል ...እምነታችንን ፣ ህይወታችንን ፣ እኛነታችንን ሁሉ ነጥቆናል ። አማኝነትን በራስ ወዳድነትና በተጨቃጫቂነት ለውጦብናል...ህይወታችንን ለሌሎች በማቀበል ስለሌሎች የሚገበር ተራ የጊዜያት ጥርቅም አድርጎብናል...እኛነታችንን ለማናውቀው እና ፍፁም ደስታችንን ለሚመጠው ሌላ ነገር አሳልፎ ሰጥቶብናል ።
ይህ ሌላ ነገር ግን ምንድነው ? እየኖርን ያለነው ምንድነው ? ምን እየተፈጠረ ነው ግን?
ብቻ መኖር ያለብን ህይወት አለ ....ያን ህይወት ፈልገን ማግኘት አለብን ። | 778 |
