cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Thoughts

ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው? እናንተስ ጎራ አትሉም? Since: Dec-10-2022 discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk

Show more
Advertising posts
2 618
Subscribers
+424 hours
+257 days
+32630 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
እንባ እንባ ይለኛል      ይተናነቀኛል እንባ የት አባቱ ደርቋል       ከረጢቱ ሳቅ ሳቅም ይለኛል   ስቆ ላይስቅ ጥርሴ     ስቃ እየነደደች መከረኛ ነብሴ             ፨ ፨ ፨ ❇️በአሉ ግርማ
4508Loading...
02
"ሆጵላስ!" ይሄን ያውቃሉ ? ይህ ቃል የተፈጠረበት አጋጣሚ  አንድ ፈረንጅ በሀገራችን የድንጋይ ናዳ መንገድ ይዘጋበታል። ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ድንጋዩን ከዘጋው መንገድ ለማስወጣት አብሮ መግፋት ይጀምራል። እየገፋም "hopeless!" (ተስፋ የለሽ!) ይላል። ይህንን በሰሙት የአበሻይቱ ልጆች አማካኝነት "ሆጵላስ!" ማበረታቻ ሆና በቋንቋችን ውስጥ ተፈጠረች። ሆጵላስ ደና ደሩ 😂
85013Loading...
03
https://www.instagram.com/reel/C3npBpfrfDw/?igsh=MWNuN2h6d21haGF2Mw==
8710Loading...
04
Denzel 🙏🙏
1 0173Loading...
05
" ያ ደግ ሰው በመንገዱ እየኼደ ሳለ ሽፍታ አገኘ፡፡ ያ ደግ ሰው፤ “ሰላም ለአንተ ይኹን! በዚህ ስፍራ ለምን ብቻህን ትዘዋወራለህ?” አለው። ያ ሽፍታም፡ “እኔ ሽፍታ ነኝ! ለዚህም ነው በዚህ ሰዋራ ስፍራ የምዘዋወረው:: ይልቅ ምን ይዘሃል? ወዲህ በል የያዝኸውን ኹላ! አምጣው!” አለው። ያ ደግ ሰው፡ “ለምን ግን ሠርተህ አትበላም? ሰው የደከመበት ገንዘብ ላንተ ምን ያደርግልሃል?" አለው፡፡ ያ ሽፍታ እየሣቀ፡ “ስማ! ማር በልተህ ታውቃለህ?" አለው:: ያ ደግ ሰው፡ “እንዴታ! በደንብ አድርጌ ነዋ የምበላው!" አለው:: ያ ሽፍታ፡ “ሠርተህ ነው ወይስ ከንብ ቀምተህ ነው? በጭስ እያስፈራራህ፣ እንዳትታይ በጭንብል እየተከለልህ ነው ንብ ለፍታ የሠራችውን የምትቀማት” አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፤ ኹሉም ስው “ለፋኹበት” በሚለው ጕዳይ ወስጥ መዝረፍ እንዳለበት ዐወቀ። ከዚያም፣ ለሽፍታው “ብዙ ገንዘብ የለኝም:: ምናልባት ይህቺ ኹለት ፈረንካ ከበቃችህ እንካ” አለው፡፡ ያ ሽፍታ፡ “ለዛሬው ምሬሃለኹ፣ ከዚህ በኋላ ግን በማያገባህ ጕዳይ አትግባ" አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፡ “እንኳን ማርኸኝ እንጂ በል ደኅና ሰንብት" ብሎት ፈጠን ፈጠን እያለ ተራመደ፡፡ በመንገዱም ላይ ሳለ እንዲህ እያለ እያሰበ ነበር፡፡ “አኹን ግን የእውነት እንቁላልን ዶሮ የምትሸጠው ቢኾን ዋጋው ስንት ይኾን ነበር? ሰው ከዕቅፏ ፈልቅቆ ይወስድባታል እንጂ መቼ ይጠይቃታል። እና፣ ከደምና ከዐጥንቴ ያልሠራኹትን ገንዘብ ሽፍታ ወስዶብኝ እንዲህ ከተንገበገብኹ ልጅ ይኾነኛል ያልኹትን፣ ከብቤ ያኖርኹትን ቢያነሡብኝ ቀድሜ አበድኹኝ” እያለ ኑሮውን እየታዘበ ኼደ፡፡ " " ግርባብ ያ ደግ ሰው " በፍቃዱ አየልኝ መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል :: @jafbok
99312Loading...
06
⭐#ዋጋህን_እወቀው! መነበብ ያለበት አስተማሪ ታሪክ "ትናንት ማታ አንድ ቪዲዮ እያየሁ ነበር። ሰባኪው የመቶ ብር ኖት ይዟል። እንዲህ ሲል ሰማሁት 'ይህ የብር ኖት እንደታተመ ምንም ዓይነት መጨማደድ አልነበረበትም። ከዚያ በኋላ ግን ሰዎች፦ ➡️እጽ ለመግዛት ተጠቅመውታል። ➡️ ለዝሙት ከፍለውታል። ➡️ጭቃ ውስጥ ነበር። ➡️ተቀዷል፣ ➡️ጠርዞቹ ተቆርጠዋል። ✅️ከዚህ ሁሉ ቀኋላ ይህ የመቶ ብር ኖት አሁን ዋጋው ስንት ነው? አሁንም ዋጋው ያኔ አዲስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ዋጋ ነው። አምላካችንም እኛንም የሚያየን እንደዚህ ነው። ያለፈው ታሪካችን ምንም ሆነ ምንም፣ የቱንም ያህል የተጎዳን እንሁን፤ ለእሱ ዋጋችን ያኔ ሲፈጥረን እንደነበረው ነው።' " ✅️👉#የተሰቀለው_ንጉሥ መጽሐፍ (አዲስ መጽሐፍ) 👉 #The_Crucifixion_of_the_King_of_Glory ✅️@Enmare1988 ✅️✅️@Enmare1988
4731Loading...
07
ሁለቱም እኩል ደወሉ እነማናቸው? ሳባ እና ዳዊት ለማንኛቸው እንደማነሳ ግራ ስጋባ ተዘጋ ሳባ መልሳ ደወለች እሱ text ላከ "ሚኪዬ ተቆጣኝ" አለቺኝ ይሄንን ሀረግ አውቀዋለው  የእሱም መልዕክት "ዛሬ ቀኑ ፈካ አላለብህም?" ይላል የሁለቱም ሀሳብ ትርጓሜው አዲስ ሰው ተዋውቀው ተመችተዋቸዋል ማለት ነው። "ኧ? ተቆጣኛ" አለቺኝ ምን ልበላት? ሁለቱም ጓደኞቼ ናቸው እሷ የመጨረሻ ኮስታራ ወንድ አጠገቧ የማታደርስ አይነት ሴት ናት የመጀመሪያዬ ጥሎኝ ሲሄድ ነው እንደዚህ የሆንኩት ትላለች እሱ ደግሞ የለየለት ሱሰኛ ነው እሱም  "ተከድቼ ነው" ነው ሰበቡ   በአንድ የተቀደሰ ልበለው የተረገመ ቀን አስተዋወቅኳቸው አጠገባቸው እኔ የሌለው ያህል በነፃነት ተሸኮረሟመሙ ከዛማ በቃ እፍ አሉ ሌላ ሰው የሌለ ያህል በየጎዳናው በየጥጋጥጉ በየቦታው አብረው ታዩ ከዛ ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳያብራሩልኝ በቃ ተደባበርን ብለው ተለያዩ ከዛ ዳዊት የሆነ ቅዳሜ ቀን መጥቶ "በቃ ንሰሀ ገብቼ መጣሁ ለእስከዛሬው ከዚ በኋላ ሱስ ደጅ ብደርስ" ብሎ እየተንጎራደደ ነገረኝ "ወገኛ! ሲሉ ሰምተሀል" ብዬ ችላ አልኩት እውነቱን ነው ብዬ አላሰብኩማ!! እሱ ግን አምርሮ ኖሯል እንዳለውም እርግፍ አድርጎ ተወው ሳባ እንዲተው እንዴት ትፈልግ እንደነበረ አስታውሼ "በእሷ ምክንያት ነዋ?" ብዬ ስጠይቀው ፊቱ ልወውውጥ ብሎ "ምንም ከሷ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም" አለኝ መልሴን ከፊቱ ላይ ስላገኘሁ "እሺ" አልኩት በሳምንቱ ከሳባ ጋር ተገናኝተን እያወራን እያለ በመሀል "እና በቃ ረሳሽው?" አልኳት ፊቷ ድምን ሲል እያየሁት "ማንን" አለቺኝ "ሳባ አትቀልጂ የእውነቴን..." ስላት ስልኳ ጠራ "ዳጊ" ይላል "ወዪዬ ዳጊዬ"  ብላ አነሳችው ዳግም ሲቆላመጥ ዳጊ ቆይ ዳጊዬን ምን አመጣው?! ደግሞ እኔ የማላውቀው ዳግም ማነው? እያልኩ ሳሰላስል "እኔም ናፍቀኸኛል እንገናኛለን" ብላ የውሸት ጥርስ በጥርስ ሆና ዘግታው "ዳግም ማነው" ስላት "አለ ባክህ የሚያዝገኝ" አለች "ፈገግታሽ እያዛገሽ አይመስልም" አልኳት "እ" አለች ከስልኳ ላይ ቀና ሳትል ከእጇ ላይ ነጥቄ ሳየው "እዩ" ይላል "መቼ ነው የማገኝሽ" ብሏት ሳትመልስለት ነው የተቀበልኳት "ተው ይደብረዋል ልመልስለት" ብላ መልሳ ወሰደችው "ምንድነው" አልኳት ዝም አለቺኝ የመጀመሪያው ፍቅረኛዋ ዝምተኛ አደረጋት የኔው ጉድ ጋር ስትለያይ ደግሞ የማንም ሆነች እሱ ደግሞ የመጀመሪያዋ ሱስ ውስጥ ዘፈቀችው ሳባ ስትተወው ደግሞ ሱስ ለምኔ አለ። ዛሬ ሁለቱም አዲስ ሰው እንደተዋወቁ እና ያ የተረገመ "ልዩ ስሜት" ስለተሰማቸው ነው የደወሉልኝ። እሺ አሁንስ ደግሞ እንዴት ያደርጋቸው ይሆን ምን አይነት ተፅዕኖ አሳድሮ ምን አይነት አሻራ ጥሎባቸው ያልፍ ይሆን? "ሄሎ ሚኪ አይሰማም እንዴ ተቆጣኝ እያልኩህ እኮ ነው" አለቺኝ ለካ እያናገርኳት ነው "ለምን እቆጣሻለው ጥፋት እኮ አይደለም" አልኳት "በምን አወቅክ" አለች በጥርጣሬ "አዲስ ነገር አይደለም ይሄ ለሶሰተኛ ጊዜ ስናስተናግደው ነው ብቻ አንድ የምልሽ ምንም ነገር እንደዚ እንዲያናውጥሽ እንዳትፈቅጂ እሺ" አልኳት "እሺ" ብላ ስልኩ ተዘጋ ወዲያው ለዳዊት መለስኩለት "ገና ለገና ሌላ ሴት መጣች ብለህ ወደዛ ሱስህ እመለሳለሁ ብትል እፈነክትሀለሁ" ብዬ መለስኩለት ✍nani
1 1262Loading...
08
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ይህን👆 የገብረ ክርስቶስ ደስታን ገጠመኝ እና ስዕሉን ባየ ጊዜ ልቡ ተነካና ብዕሩን አንስቶ እንዲህ ሲል ተቀኘለት እዩት ይህን ጠቢብ ሸራው እስኪደማ በቀይ እየወጋ በደም እየሳለው እንጨት አመሳቅሎ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ላይ ሰቀለው። ቀራኒዮ ሆነ የወጠረው ሸራ ጎለጎታ ሆነ የወጠረው ሸራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ። ደም ከደም አረገው አበዛበት ጣር ብሩሹን አሹሎት እንደጎኑ ጦር። እየወጋ ሳለው በጣም ጨከነበት ገብረ ክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ የቆዳው አይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ። እየወጋ ሳለው እየሳለ ወጋው ደሙ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ ደሙ እስከሚናገር የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው አገር። እንዳንለው ፈረንጅ እንዳንለው ጥቁር እንዳንለው ቀይ በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ስቃይ። በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው። ከቀናት ባንዱ ለት ሰዎች ሲሟገቱ በቀለሙ ጉዳይ ሲከራከሩበት በተመፃዳቂ የምሁር አንደበት። በአንዱ አፍ ሲጠቁር በአንዱ አፍ ሲነጣ መታገስ አቃተው ሰዓሊው ተቆጣ ስሜቱ ገንፍሎ በብሩሽ ጫፍ ወጣ ሀሳቡን የሚገልፅ ቀለም እስከሚያጣ። ሸራ ላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ አልወጣልህ አለው ፍቅርን ስሎ ስሎ ስሎ ስሎ ስሎ ፍቅርን ስሎ ስሎ በሳለው እየወጋ በደማው እየቀባ። ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀለም እንጨቱ ላይ ያለው እውነት ይሄ አይደለም። እያለ እስኪናገር የስዕሉ አንደበት ገብረ ክርስቶስም ለክርስቶስ ’ሚሆን ቀለም እስኪያልቅበት በነጩ ሸራ ላይ እስካሁን የሚወርድ ደም አፈሰሰበት። ቀለም ቀይ ቀለም የደም ቀለም የጥላ ቀለም የሁሉም ነው እንጂ የማንም አይደለም ፍቅር ዘር አይደለም። @wegochi
1 4506Loading...
09
You realize you wouldn't have learned how to ride a bike if someone you trusted hadn't let you go. God works differently
2234Loading...
10
ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ስእል በሚያስተምርበት ወቅት ተማሪዎቹ የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ስለዉ እንዲያመጡ በቤት ስራ መልክ አዘዛቸው ። ሁሉም በመሠለዉ መልክ ኢየሱስ ክርስቶስን ስሎ ሲያመጣ አንድ ተማሪ ግን የክርስቶስን ስዕል በጥቁር ወይም አፍሪካዊ መልክ ስሎ ያስረክባል ። ገብረ ክርስቶስ በስእሉ ተገርሞ ለምን ክርስቶስን ጥቁር አድርጎ እንደሳለው ሲጠይቀው ተማሪው «ክርስቶስ ፈረንጅ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ፈረንጆች በጣም ጨካኞች ናቸው። ኢየሱስ ነጭ ሳይሆን ጥቁር ነው» ብሎ ይመልሳል። ይህን ግዜ ነው ገብርዬ ወደቤቱ ሲበር ሄዶ ኢየሱስ ክርስቶስን ቀለም እንዳይኖረው ፣ ዘር እንዳይኖረው ፣ ነገድ እንዳይኖረው አርጎ ከፀጉሩ እስከእግር ጥፍሩ ድረስ በደም ለውሶ ሳለው። ገብርዬ በስዕሉ "ፍቅር ዘር የለውም። ፍቅር ቀለም የለውም። ፍቅር የነገድና የቀለም አጥርን ይሻገራል። ክርስቶስ ሲያድነን ዘር ቀለም ፆታ አልመረጠም። ክርስቶስ ያዳነን በደሙ እንጂ በቆዳው ቀለም ወይም በዘሩ አይደለም። በመስቀል ላይ የፈሰሰው የክርስቶስ ደም ለሁሉ ይበቃል።እኔነት ባለበት ፍቅር በዚያ የለም!!!" ሲል ይህን ዘመን ተሻጋሪ ስዕል ሊስለው ችሏል። ገጣሚና ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ኢትዮጵያዊ ባይሆን ኑሮ በዚህ ስዕሉ ከዳቪንች እኩል በመላው ዓለም እውቅና በተጎናጸፈ ነበር። . እንኳን አደረሳችሁ!!! @wegochi
1 29310Loading...
11
" ሰዎች ፍቅር እውር ነው ይላሉ፣ እንዲህም የሚሉት የፍቅርን ትርጓሜ ስላላወቁ ነው፣ እኔ ግን እላቹሀለው ፍቅር ብቻ ነው አይን ያለው። ከፍቅር ውጪ ሌላው በሙሉ እውር ነው።" ✍🏼 ተሰብሰቡ
1 3360Loading...
12
ስብሐት ስለ ደራስያን ምን ይላል? ማስተርፒስ ወደ አማርኛ ስነፅሁፍ እየመጣች ነው ―ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የዘነበ ወላን "ልጅነት" ካነበበ በኋላ ዶስቶቭስኪ ሲፅፍ ዝርክርክ ነበር። በቴክኒክ ረገድ ያልተዝረከረከው ‘ወንጀልና ቅጣት’ ብቻ ነበር። ታድያ ማንበቡ ሲጥምህ እንኳንም ተዝረከረከ ነው የምትለው። ―ስብሐት ስለ ዶስቶቭስኪ በአማርኛ ስነፅሁፍ ውስጥ እንደ አዳም ረታ የተዋጣለት የአጭር ልብወለድ ደራሲ የለም። ―ስብሐት ስለ አዳም ረታ(ልብ ማለት ያለብን ስብሐት አብዛኛዎቹን የአዳም ረዣዥም ልብወለዶች ለማንበብ አልታደለም ካፒታልን ያነበብኩት በደርግ ዘመን መፅሀፉን ወደ አማርኛ እንዲመልስ በተዋቀረው ኮሚቴ አባል ሆኜ ነው። ሰዎች ማርክስ ቤተሰቡን አስርቦ ነው የፃፈው ይላሉ። ፍልስፍናው ሲገባህ አውራጃም በተራበ ነው የምትለው። ―ስብሐት ስለ ካርል ማርክስ አደፍርስን ሳነበው "ሌቱም አይነጋልኝን" በእንግሊዝኛ የተተየበ 65 ገፅ ላይ ደርሼ ነበር። ከዛ በፊት አማርኛ ለስነፅሁፍ ብቁ አይደለም የሚል እምነት ነበረኝ። ዳኛቸው በአማርኛ መፃፍ እንደሚቻል ከሰተልኝ። ―ስብሐት ስለ ዳኛቸው ወርቁ ፍሩይድ ተአምረኛ ነበር። ወደ ራሱ ውስጥ ገብቶ የመረመረ ጂኒየስ ነው። እራሱ በርቶለት የኔንም ውስጤን አበራልኝ። ―ስብሐት ስለ ፍሩይድ በአሉ ጎበዝ አለቃ ነው። ከዛ ቀጥሎ ነው ደራሲነቱን የማደንቀው። በአሉ ባህሪውም መልኩም የስነጽሑፍ ችሎታውም ያማረ ሰው ነበር። ‘አይገኝም እንጂ እንዳማሩ መሞት’ የሚለውን የአንዳንድ ግዜ ህግ ጥሶታል። ―ስብሐት ስለ በአሉ ግርማ በዛኛው አለም አራት የአጭር ልብወለድ ጠበብቶች አሉ። አንደኛው ጊ ደ ሞፓሳ ነው። ሞፓሳ በ43 አመቱ ከ400 በላይ አጭር ልብወለድ ያመረተ ጎበዝ ደራሲ ነበር። ምን ያደርጋል ቂጥኝ በአጭር አስቀረው(ስብሐት ከአይኑ እንባ ዱብ አለ) ―ስብሐት ስለ ጊ ደ ሞፓሳ ፀጋዬ የኛ ዎሌ ሾይንካ ነው። ኦክስፎርድ ድረስ ሄዶ ስነፅሁፋችንን አለማቀፋዊ ያደረገ ደራሲ ነው። ―ስብሐት ስለ ፀጋዬ ዲክንስ የታችኛውን ማህበረሰብ ህይወት ነው የፃፈው። እንደ ሩስያ ስነፅሁፍ እንባ በእንባ ነው የሚያደርግህ። የእንግሊዝ ነገሥታትና ልኡላን ዲክንሰን አነበቡት። ከዛ በኋላ ነው ድሆችን የሚረዳ ድርጅት በእንግሊዝ መቋቋም የጀመረው። ዲክንስ በስነፅሁፉ ጉልበት በሃገር ደረጃ ማህበራዊ ተፅእኖ መፍጠር የቻለ ታላቅ ደራሲ ነው። ―ስብሐት ስለ ቻርልስ ዲክንስ ኃይለመለኮት መዋእል ‘ጉንጉን’ ውስጥ አማርኛን ከነለዛዋ ከነማእረጓ ፅፎ አስደነቀኝ። ደግሞም ኃይለመለኮት ብእሩ ብቻ ሳይሆን አንደበቱም ርቱእ ነው። ―ስብሐት ስለ ኃይለመለኮት ፕሩስት አይሁድ ነው። የፈረንሳይ አይሁድ። ጂንየስ ነው። አይሁድ መሆን ጂኒየስ ያደርጋል መሰለኝ። ሰባት ልብወለድ ጽፏል። ስለ ራሱ ነው የፃፈው። በልብወለዱ ውስጥ ያሉት ሁለት መቶውም ገፀባህሪያት ፈረንሳይ ውስጥ በሕይወት ያሉ ሰዎች ናቸው። በፈረንሳይኛ ነው ያነበብኩት። ፈረንሳይኛን እንደሱ የሚያውቅበት ደራሲ የለም። ―ስብሐት ስለ ማርሴል ፕሩስት ጋሽ ሐዲስ አለማየሁ ቆንጆ ስታይል ነው ያላቸው። ተረታዊ አቀራረባቸውን እወደዋለሁ። በአማርኛ የሚፅፉ ቶልስቶይ ልትላቸው ትችላለህ። ―ስብሐት ስለ ሐዲስ አለማየሁ ኒቼ ከዘመናዊ ታላላቅ ፈላስፎች አንዱ ነው። ግማሽ ጎኑ ፖላንድ ነው። በጣም ብሪሊያንት ነበር። ከኤግዚስቴንሽያሊዝም አያቶች አንዱ ነው። ፍልስፍናው በጣም ተፅእኖ ፈጣሪ ነው አሁን ድረስ። ኒቼ የቂጥኝ በሽታ ነበረበት። በዚሁ ጦስ አብዶ ነው የሞተው። ―ስብሐት ስለ ፍሬድሪክ ኒቼ ከበደ ሚካኤል በዘመናቸው ለነበረ ትውልድ ትክክለኛ ደራሲ ናቸው። ለአሁኑ ትውልድ ግን እንጃ። ምክንያቱም ስራቸው ግብረገብ ይበዛበታል። ቢሆንም መደነቅ ይገባቸዋል። ―ስብሐት ስለ ከበደ ሚካኤል አልቤር ካሙ ጋዜጠኛም ፈላስፋም ደራሲም ነበር። ደግሞም ሰው ነው። ላመነበት ነው የሚኖረው። በእኛ ዘመን ካሙን እና ሳርትርን ያላነበበ ኢንተሌክችዋል ወጣት አልነበረም። ስራቸው ፍልስፍናም ምርምርም ነበር። ―ስብሐት ስለ አልቤር ካሙ ከተርጓሚዎቻችን መሐል ያነበብኳቸው እና የወደድኳቸው ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም፣ ባሴ ሃብቴና መስፍን አለማየሁ ናቸው። በተለይ ባሴ በሲራኖ ትርጉሙ አስደንቆኛል። ―ስብሐት ስለ ተርጓሚዎች ገተ የጀርመን የስነጥበብና የባህል አባት ነው። በአውሮፓ የመጀመሪያውን ሮማንቲክ የሆነ አብይ ልብወለድ የፃፈው ገተ ነበር። ፎስት ይባላል። ፎስት የታወቀ የጀርመን ሌጀንድ ሲሆን ገተ በስነፅሁፍ ህያውና ዘለአለማዊ አድርጎታል። ―ስብሐት ስለ ዎልፍጋንግ ገተ ብርሃኑ ዘርይሁንን ሳገኘው ከኔ የባሰ አይናፋር ነው። ማእበልን ጀምሬ መጨረስ አልቻልኩም። አፃፃፉ ጥሩ ነበር። ግን የረሃብ ሰቆቃውን ተቋቁሜ ማንበብ አልቻልኩም። እንዴት ችሎት ጻፈው! ―ስብሐት ስለ ብርሃኑ ዘርይሁን © Tewodros Shewangizaw
1 5397Loading...
13
ሮፍናን ZETEGN | HARAMBEE አልበም ታምሪያለሽ 👇👇👇 @old_musica ሼር🙏
1 2966Loading...
14
⭐አንዳንድ ግንኙነቶች አሉ. . በዝምታ የሚያልቁ ንግግሮች፤ ያልተጨበጡ ደቂቃዊ ደቃቅ ቆይታዎች፤ ያልታቀፉ ገላዎች፤ ድፍረት ያልጎበኛቸው አሳቦች፤ የሽቶ ጠረን፤ በዓይን በአንገት የሚናገሩት፤ መነካካት፣ መሳሳም፣ መተቃቀፍ፣ መላፋት የናፈቁ፤ አንዳንድ ግንኙነቶች አሉ ላለመገኘት የተገናኙ.. ⭐@Enmare1988 ✅️@Enmare1988
1 1065Loading...
15
"ተናጋሪው" ቅዳሜ ጠዋት ከቤተክርስቲያን ተመልሰን አረፍ ከማለታችን ሚጣዬ ሄዳ ቲቪ ከፈተች አሻንጉሊቷን ልታይ መሆኑ እኮ ነው ተቆጥቼ አስቀየርኳት "ቅዳሜ እንኳን የእኛ ተራ ይሁን ብዬ" ከዛ channel ቀይራ እጇን አጣምራ ተቀመጠች ማኩረፏ እኮ ነው ሆ ሆ የዘንድሮ ልጅ እያልኩ በሆዴ... ቁርስ ቀራርቦ መብላት ጀመርን። እንደዛ ተቆጥቼ ያስቀየርኩትን ቲቪ ሳየው አንድ ተናጋሪ ነኝ ባይ መድረክ ሙሉ ህዝብ ሰብስቦ ያወራል። "እኔ ልዩ ነኝ ማለት አለብን ምክንያቱም ሁላችንም የተለያየን ነና..."ሲል "እማ እማ" አለቺኝ "ወዬ ሚጣዬ" ስላት "እኔ ልዩ ነኝ ማለት ምን ማለት ነው?" አለቺኝ እውነት ግን ልዩ ነን ምን ማለት ነው? ከመሰረታዊ ፍላጎቶቻችን አንፃር ሁላችንስ ከእንስሳት በምን እንሻላለን? ፍቅር የማያሸንፈው አለ? አንዳንድ ማህበራዊ ተፅዕኖዎች ከፈጠሩብን የባህሪ እና የቀለም ልዩነት ውጪ አብዛኛው ነገራችን እኮ አንድ ነው። "እ መልሺልኛ?" አለቺኝ ለአራት አመት ህፃን ምን ተብሎ ይሄ ይብራራል "ይሄ የትልቅ ሰው ወሬ ነው አልኳት" እሺ ብላ ዝም አለች። በሚገባት ባብራራላት ይሻል ነበረ ወይስ ስታድግ ራሷ ትጋፈጠው እያልኩ ከራሴ ጋር ስሟገት ተናጋሪ ነኝ ባዩ ሰውዬ "በቃ ስኬታማ ለመሆንም በሉት የውስጥ ሰላም ለማግኘት ልባችሁን አዳምጡት ልባችሁን ተከተሉት" አለ። የፈራሁት አልቀረልኝም "እማ ልብ መከተል ምን ማለት ነው" አለቺኝ። ዛሬስ እኔም ግራ ገባኝ ልብ መከተል? ልብን ለመከተል እኮ በራስ መተማመን ያስፈልጋል፥ ራስን ማዳመጥ፥ ከራስ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል ታዲያ አሁን ያለው አለም ይሄንን የሚፈቅድ ነው? ሁሉም የራሱን ሀሳብ የሚጭንብህ እንጂ እንድታስብ የሚፈልግ የለም። እኔ ራሴ እንኳን ቅድም ያደረግኩትን ሳስብ ራሴን ታዘብኩት "የትልቅ ሰው ነው ምንም አያደርግልሽም" ስላት የማሰብ አድማሷን እያጠበብኩት እኮ ነው። "እንዴ እማ የጠየኩሽን ረሳሽው እንዴ?" ስትለኝ አሁንም ቢሆን እንዴት እንደማስረዳት ማወቅ አልቻልኩም ቀና ብዬ ሳየው አሁንም እያወራ ነው ሰውየው ሌላ እኔም ያልተረዳሁት ጥያቄ ከመጠየቋ በፊት ብዬ "በቃ ቀይሪው ወደ ምትፈልጊው አታድርቂኝ" አልኳት ወዲያው ቀይራ አሻንጉሊቷን ማየት ጀመረች። ✍nani
1 5283Loading...
16
Media files
8 1851Loading...
17
👍'' በምሽት ብልጭ የምትል አንዲት ሐሳብ ለታላቅ ክብር አሊያም ለስደት ትዳርጋለች ...የአንዲት ሴት ዓይኖች ቅፅበታዊ ዕይታ የዓለማችን ደስተኛ ሰው ሊያደርግህ ይችላል... ከሰው ልጅ ከናፍር የሚወጣ አንድ ቃል ሀብታም ወይም ደሃ ሊያደርግህ ይችላል ።❤️❤️
1 2914Loading...
18
Media files
3310Loading...
19
franz kafka
3250Loading...
20
At 40, Franz Kafka (1883-1924),who never married and had no children, walked through the park in Berlin when he met a girl who was crying because she had lost her favourite doll. She and Kafka searched for the doll unsuccessfully. Kafka told her to meet him there the next day and they would come back to look for her. The next day, when they had not yet found the doll, Kafka gave the girl a letter "written" by the doll saying "please don't cry. I took a trip to see the world. I will write to you about my adventures." Thus began a story which continued until the end of Kafka's life. During their meetings, Kafka read the letters of the doll carefully written with adventures and conversations that the girl found adorable. Finally, Kafka brought back the doll (she bought one) that had returned to Berlin. "It doesn't look like my doll at all," said the girl. Kafka handed her another letter in which the doll wrote: "my travels have changed me." the little girl hugged the new doll and brought her happy home. A year later Kafka died. Many years later, the now-adult girl found a letter inside the doll. In the tiny letter signed by Kafka it was written: "Everything you love will probably be lost,but in the end,love will return in another way."
4063Loading...
21
Media files
3700Loading...
22
𝙳𝚊𝚖𝚗, 𝚝𝚑𝚎 𝚠𝚘𝚛𝚕𝚍 𝚋𝚎𝚌𝚘𝚖𝚎 𝚠𝚊𝚛𝚖𝚎𝚛 𝚎𝚟𝚎𝚛𝚢𝚍𝚊𝚢, 𝚋𝚞𝚝 𝚠𝚎 𝚊𝚛𝚎 𝚌𝚘𝚕𝚍𝚎𝚛 𝚒𝚗𝚜𝚝𝚎𝚊𝚍.
1 5802Loading...
23
ፈጣሪ ያጎደለብኝ ምን አለ? ሰፈራችንን የሚጠብቁ አንድ ሰውዬ አሉ፣ አንድ እይታ ይበቃል እሳቸውን ለማስተዋል ብዙም ያልተቸገረ የሚመስለው ፈገግታቸው ከሩቅ ይጣራል፣ ሁሌም እናቴ ስላሉበት ሁኔታ ስጠይቃቸው ፈጣሪ ያጎደለብኝ ምን አለ ሲሉ ነው የምሰማቸው፣ እግር ጣለኝና ትናንት በወሬያቸው መሀል ገባሁ፡ በምን እንደተነሳ ባላውቀውም፡ የሶስት ልጆች አባት እንደሆኑ እናም ብዙ ብዙ ውስጠ ሚስጥራቸውን ለእናቴ አጫወቷት፣ በንግግራቸው መሀል መሀል ላይ ጣል የሚያደርጓት ፈገግታቸው ግን ሀሴት ይሰጣል፣ በመኖር ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ልጆቼን እና ባለቤቴን ብቻ ነው፡ ቀሪ ሀብት ንብረት የለኝም ለመኖር ስል ማብቂያ የሌለው ገንዘብ ሳባርር፣ በህይወት ላይ ማቆሚያ የሌለው ሰልፍ ስጠብቅ ማብቂያው ምን እንደሆነ ሳላውቅም ስሮጥ ኖሪያለሁ፣ ብቻ ሳላውቀው እየሮጥኩኝ የሆነ ነገር ብቻ ለመያዝ እያሳደድኩ እንዳልሞት እፈራለሁ፣ ለዚ ነው ፈጣሪ ያጎደለብኝ አንዳች ነገር እንደሌለ እያወራሁ በፈገግታ እና በምስጋና ህይወቴን ምገፋው አሏት፥ የህይወት ትግል የማያልቅ እና ማብቂያ የሌለው ነው…ያለትርጉም ያለፋይዳ ማብቂያ የሌለው ሩጫ...ድንገት ተራ ሲደርስ ደግሞ ባኖደውም ማረፍ…አለቀ!! ግን ደግሞ በዚህ ስክንሳር በሞላበት አለም ላይ ፈገግታ ካለን ጠላት አይኖረንም፡ ፈገግታ የሀሴት መርጫ ሲሪንጅ ነው፡ ዛሬን በሀዘን አትግደሉ አለም ላይ የሌለን ነገር ሁሉ ቢደመር እና ቀመር ቢሰራ ያለንን ግማሽ አያክልምና!!
1 1742Loading...
24
@Jaymasangula_bot | info
1112Loading...
25
Found this in lofi studies...
950Loading...
26
⭐አዲስ ቀን ሲጀምር ፥ በአመስጋኝነት ፈገግ ለማለት አትፍራ። ኢ-ፍትሃዊነት ሲኖር ፥ መጀመሪያ ለመኮነን አትፍራ። ✅️ሕይወት ያሸነፈችህ ስትመስልህ ፥ መልሰህ ለመዋጋት አትፍራ። ጊዜው አስቸጋሪ ሲመስል ፥ የበለጠ ጠንካራ ለመሆን አትፍራ። አንድ ሰው በሚጎዳበት ጊዜ ፥ የአቅምህን ለመርዳት አትፍራ። መንገዱ ለጠፋው ሰው ፥ እንዲፈልግ ለመርዳት አትፍራ። ጓደኛህ ሲወድቅ ፥ እጅህን ለመዘርጋት የመጀመሪያው ለመሆን አትፍራ። ጥሩ ስሜት ሲሰማህ ፥ ሌላ ሰውም ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ለመርዳት አትፍራ። ጨለማ ሲሆን ፥ ብርሃን ለማብራት የመጀመሪያው ለመሆን አትፍራ። የምትችለውን ያህል ጥሩ ለመሆን ደፋር ሁን። ⭐አትፍራ...መልካም ምሽት❤
9525Loading...
27
😞
1 2753Loading...
28
🔪🔪🔪ግድያው🔪🔪🔪 ክፍል 9 ብዙም የደም ምርመራው ውጤት ከቤተሰቡ ውስጥ የአንዳቸው ደም ውስጥ ቅድም ያልኳችሁን አደንዛዥ እፅ አገኘን ስለዚህ ግምታችን ከሞላ ጎደል ተረጋገጠ ማለት ነው። እንደነገርኳችሁ የተወጋባቸው ቦታዎች ሲታዩ ጥልቅ ስለነበሩ በሴቶች እጅ ይሆናል ብለን አልገመትንም ነበረ እንደገመትነውም አደንዛዥ እፁ የተገኘው ከወንዶቹ አንዳቸው ደም ውስጥ ነው።" ጉሮሮው የደረቀበት ስለመሰለው ውሀ ሊጠጣ ንግግሩን ገታ ሲያደርግ ሁሉም ልብ አንጠልጣይ ድራማ እንደሚያዩ ተመስጠው እየሰሙት ነበረ። "ከዛ ደሙ ውስጥ ያገኘንበትን ሰው ወስደን መረመርነው። ያው እንዳልኳችሁ የተጠቀምነው መንገድ ህጋዊ አይደለም ግን እውነታው ላይ እንድንደርስ ጠቅሞናል። ያው የተጠቀምነውን ተጠቅመን..." ሲል አያሌውና ብስራት ተያዩ "የተጠቀምነውን ተጠቅመን አናዘነዋል... ያው የግድያው ምክንያት ብዙም አዲስ ነገር የለውም እኛ እንደ ቀልድ ልጆቻችንን ከሌሎች ልጆች ጋር ስናወዳድር የሚፈጥርባቸውን ጉዳት አለማወቅ ብቻ ነው። እዚህም የሆነው ይህ ነው ግን የሚገርመው ይሄ ልጅ ያደገው ከሟች ጋር ሲፎካከር በመሆኑ ሳያውቀው በውስጡ ትልቅ ቅናት ተፈጥሯል ሌላውን ተዉት ከማክዳ ጋር ባለው ነገር ሳይቀር ነበረ በቅናት የሚቃጠለው እናም ለራሱ ራሱ ሳያውቀው sub-consciously ባደረበት ቅናት የተነሳ ሊገድለው ችሏል" አለ እና ጨረሰ። "እና... አቤል ነበረ ማለት ነው?!" አለ ብስራት አፉን በእጁ ሸፍኖ ሁሉም አጉረመረሙ። "አይ፤ ብሩክ ነው" የገደለው። አለ ሚኪ ተፈፀመ ✍nani
1 6403Loading...
29
Media files
8 5753Loading...
30
Media files
1 6124Loading...
31
🔪🔪🔪ግድያው 🔪🔪🔪 ሊያልቅ አንድ ክፍል ቀረው... ክፍል  8 "ግድያው ከተፈፀመ በኋላ የተረሳ ነገር መኖሩን ለማረጋገጥ በተደጋጋሚ የፖሊስ ቡድን እየላክን ስናጣራ ነበረ እኛ ምንም የተለየ ያገኘነው ነገር አልነበረም። ከዛ ግን በሶስተኛው ቀን አደገኛ አደንዛዥ እፅ በችኮላ ተጥሎ ተገኘ። የእፁ መገኘት ከግድያው ጋር ሊያያዝ ይችላል የሚል ጥርጣሬ ስለነበረን... ከሌሎች ማስረጃዎች ያገኘነው ደግሞ ከዛ ቤተሰብ ውጭ እንዳልሆነ የሚያመላክት ስለነበረ ማድረግ የምችለው ሁሉንም መመርመር ነበረ ምክንያቱም የተገኘው እፅ LSD ይባላል በጣም ከባድ እፅ ነው እናም ይሄንን እፅ ለየት ሚያደርገው ተጠቃሚው flash back effect ያጋጥመዋል ይህም ማለት ትላንትና የወሰደው ሰው በማግስቱ የእፁ ተፅዕኖ ይኖርበትና የተለያዩ ድርጊቶችን ሊፈፅም ይችላል። የሚገርማችሁ ነገር ይሄንን ሁሉ የሚያደርገው ሰው ምንም አለማስታወሱ ነው። ስለዚህ ወንጀለኛው ወንጀሉን ስለመፈፀሙ አያውቅም ማለት ነው። ስለዚህ የማምለጥ ወይም ራሱን የመሸሸግ ሙከራ አለማድረጉ ወንጀለኛውን ለመያዝ ቀላል አድርጎልናል።" "ታድያ ገዳዩ ማን ነው??" አለ የሆነ ድምፅ ከተሰበሰበው መሀል ✍nani
1 3293Loading...
32
Media files
8 2431Loading...
33
ppl lets vote🙏🙏
5220Loading...
34
Media files
3290Loading...
35
ገጣሚ እና አንባቢ: nani 👤ተወዳዳሪ፡ናርዶስ(nani) 🎩Code፡ ⓶⓼ 🔍መወዳደሪያ ዘርፍ፡📜ስነጽሑፍ መልካም እድል🌟"ከባዶ እጆች..." @gbw_dan
3510Loading...
36
🔪🔪🔪ግድያው 🔪🔪🔪 ክፍል 7 እስካሁን አፉን ዘግቶ የቆየው ብስራት ሚኪ 'ሁሉም ደም እንዲሰጡ እፈልጋለሁ' ሲል "ደሞ እሱ ምን ማለት ነው?! እኛ እኮ ገዳዩን አግኝ እንጂ ደም አስለግስ ማን አለህ??" ብሎ ወደ አያሌው ተመለከተ "ተፈቅዶልሀል" አለ አያሌው ጠረጴዛው ላይ ያለውን የተስተካከለውን ወረቀት ድጋሜ እያስተካከለ። ሚኪም ያንን የተረገመ ፈገግታውን ለብስራት ፈግጎለት ወጣ። *** ሚኪ እንዳሰበው ሄዶ 'ደም አምጡ ማለት ቀላል አልሆነለትም' "ለምን ሲባል አሉ?" በዛ ላይ የዛን እለት ቤት ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ውጭ አይደለም ገዳዩ መባሉ የጎረቤት መጠቋቆሚያ አድርጓቸው ተሸማቀዋል እንኳን ደም ሊሰጡ?! *** ፤ከአምስት ቀን በኋላ፤ አያሌው በሩ ሲቆረቆር "ይግቡ" አለ ቀና ሳይል ሚኪን ሲያየው ገረመው ሳምንት ሰጥቶት በአምስተኛው ቀን እንዴት? "መቼም ቀን ጨምርልኝ ልትለኝ መሆን አለበት" አለ ወንበሩ ላይ ለጠጥ ብሎ እየተቀመጠ ሚኪ እስኪጨርስ ብሎ ዝም አለው "ያው ስራውን ካልቻልክ ለሌላ ሰው መስጠት ይቻላል እንጂ ተጨማሪ.... " "ገዳዩን አግኝቼዋለሁ" አለ በሙሉ መተማመን "እና ማነው?" አለ አያሌው ሰፍ ብሎ "እንዴ ሙሉ crew ይሰብሰብ እና ነው እንጂ በቀላሉማ የደከምኩበትን ቢሮ ውስጥ አልናገርም" ብሎ ወድያው የወንጀል ምርመራ ቡድኑ ተሰብስቦ ሚኪ ረጅም ገለፃውን ጀመረ። "እንዴት ሬሳውን እንዳገኘነው ሁላችሁም የምታውቁት ጉዳይ ስለሆነ የምጀምረው ከምርመራው ነው። እንግዲህ ይህ የምርመራ ሂደት ከብዙዎቻችሁ ጋር የሚያስማማኝ ስላልነበረ በምስጢር አብዛኛውን ነገር ያደረግኩት። ማክዳን ለመመርመር አንዳንድ ህጎቻችን የማይፈቅዱትን ነገር አድርጊያለሁ። የሆነው ሆነና ማክዳ ገዳይ አለመሆኗን  በተለያየ ማስረጃ ተረጋገጠ። ከዛ በኋላ የሆነው ነገር የገዳዩ ጓደኞች ከእኛ ጋር ተባበሩ ብል ይቀለኛል።"የብዙዎቹ ፊት ላይ ግራ መጋባት ይታያል።ሚኪ አጠገቡ በነበረው ውሀ ጉሮሮውን አራጥቦ ቀጠለ። ✍nani
1 5806Loading...
37
Media files
7 5692Loading...
38
👤ተወዳዳሪ፡ኤልያስ ገላሼ 🎩Code፡ ⓶⓻ 🔍መወዳደሪያ ዘርፍ፡📜ስነጽሑፍ መልካም እድል🌟"ከባዶ እጆች..." @gbw_dan እንዲሁ... በጨፍጋጋው አየር ብስክስክ ድሪቶዬን ለብሼ ከመኖ ፍለጋዬ ስመለስ ከተማውን እንደማላውቀው ሁሉ እንደ አዲስ እቃኛለሁ ..... በረንዳዎች ሁሉ ግዛቴ ይመስሉኛል፣ 'ዶሮ ብታልም ጥሬዋን' ነውና ላስቲክ አልብሶ ለመኖር አመቺ የሆኑ ቦታዎችን ልብ ሳልላቸው አላለፍኩም።በጉዞዬ መካከል..... እንዲሁ መንገድ እዳር አየኋት ፤ በብጭቅጫቂ ካርቶን እሳት ስታያይዝ። እንዲሁ ያለ አፍረት ቀረብኳት፤ብጭቅጫቂ ካርቶን እያዋጣው። ለአፍታ ሳትገላምጠኝ ካርቶኑን ከእጄ ወሰደች፤ እንዲሁ ተኮራምታ እንደተቀመጠች። ልቅም ያለች ቆንጆ...... መሽኮርመም ሳያስፈልጋት የተሽኮረመመች ፤መሳቅ ሳያስፈልጋት የሳቀች....ግን እሷ አትሽኮረመምም ፤አትስቅም እንዲሁ በዝምታ የተማረከች ልጅ...... እንዲሁ ጥያቄ ወረወርኩባት "ምን አመጣሽ ከኔ ቦታ?" "እንዲሁ ነው ለዝምታ" "ሌላ ቦታ ዝም ጠፍቶ ?" "ስሜት ገዳይ ተንሰራፍቶ" ዋይታዋን ስሰማት ፤መንፈሴ ተረበሸላት ፤መንገዱ ዳር እንደሚነፍሰው ነፋስ ስሜቴ ሁሉ ነፈሰላት፤ እንዲሁ ዥውው...... ቀረብኳት አልተንቀሳቀሰችም ፤ አቀፍኳት አልተቆጣቺኝም ፤እንዲሁ ብጫቂ ካርቶን አንስታ ወደ እሳቱ ወረወረች። በዝምታ አቅፊያታለው ፤ ዝም ብላለች ።እንዲሁ ፀጥ ብላለች...... ብዙ አቀፍኳት፤ ብዙ ዝም አለች ግን ሰውነቷ መንዘፈዘፍ ጀምሯል ፤እንዲሁ ተብሰከሰከቺብኝ። አንገቷን ከስሬ አውጥቼ ፊቷን በስስት ተመለከትኩት፤ እንዲሁ ፍዝዝ ብዬ አየኋት። ፊቷ በዕንባ እርሷል ፤እቅፌ ስር ገብቶ ማን ተቆጣብኝ?የኔ ውድ ስታለቅስም ያምርባታል፤እንዲሁ ቁንጅት ትላለች። የዕንባዋን ተጠያቂ ማወቅ አሰኘኝ ፤ሁለተኛ ጥያቄ ወረወርኩባት፤እንዲሁ ውበቷ ለአንዴ ብሸሸው የሚፈስ ይመስል እንዳፈጠጥኩባት። "ምነዋ ቆንጆ ፊትሽ ወረዛ ስንቡኩ ጉንጭሽ በዕንባሽ ወዛ?" "እንባዬ ያውጣው ታፍኜ ኖሬ የልብን ሰሚ ካገኘው ዛሬ" ወየው ለኔ!! ክፋቴ ለበዛው.....ለምን ግን ብሶቷን ቀሰቅስባታለው፤እንድትተኛ ለምን አልፈቅድም? እራስ ወዳድነት ነው?እንዲሁ ስግብግብ መሆን..... መልሼ አቀፍኳት እንደ ህፃን አባበልኳት ደረቴ ላይ አንቀላፈች፤እኔም ፀጉሯን ተንተርሼ አሸለብኩ። ✍️ኤልያስ ገላሼ
1 2782Loading...
39
ትዝታ ክፉ እንግዳ ነው የማይመጣ ይመስልሀል፥ ከዛ ሳትዘጋጅ ሳያሳውቅህ ጓዙን ጠቅልሎ ይሰፍርብሀል.... ቶሎም አይሄድልህም ትንሽ ካደቀቀህ በኋላ በመከራ ትሸኘዋለህ። አዬ አንተ ምስኪን አርቀህ የሸኘኸው እንዳይመለስ መሆኑ ነው አይደል?! ትዝታ እኮ ርቆ አይርቅም መዘናጋትህን አይቶ መመለሱ አይቀርም...
8 47434Loading...
40
🔪🔪🔪ግድያው🔪🔪🔪 ክፍል 6 በማግስቱ ልክ ቢሮ ሲገባ ስንታየሁ "ብስራት እና አያሌው አያሌው ቢሮ ውስጥ እየጠበቁህ ነው" አለችው 'ኦ ኦ ከባድ ጥምረት ነው' አለና ለራሱ 'መቼም ስለዛች ልጅ ነው የሚሆነው' እያለ አንኳኩቶ ቢሮውን ሲገባ አያሌው ኮስተር ብሎ ተሰይሟል የብስራት ፈገግታ ግን ነገር ያዘለ ይመስላል "እንዴት አደራችሁ" አለ ድባቡ ግራ አጋብቶት አያሌው ፊቱን የባሰ አጨማደደ "አሁን የጠራንህ ስለዚህ ብልቃጥ ማብራሪያ እንድትሰጠን ነው" አለ ብስራት ተቻኩሎ "የት አገኛችሁት?!" አለ ድንጋጤውን ለመደበቅ እየሞከረ " የተገኘበት ቦታ አይደለም ቁምነገሩ ለምን መጠቀም አሰፈለገህ የሚለው ነው" አለ አያሌው እመር ብሎ ተነስቶ "ቢያንስ ወንጀለኛን ከመደብደብ አይሻልም" አላቸው እጁን ደረቱ ላይ አጣምሮ አያሌው መልስ ለመስጠት ጊዜ ፈጀበት መልሱ ከፊል እውነትነት ስላለው... "ጠቃሚ ቢሆን ለምን በአለምአቀፍ ደረጃ ተከለከለ??" አለ ብስራት መሀል ገብቶ "ምነው ብስሬ  አንተ ነህ መሰለኝ ያገኘኸው ትንሽ research ሰርተሻል እንዴ?" አለው ሚኪ ፈገግ ብሎ ብስራት የሚመልሰው አጥቶ ፊቱ በቁጣ ሲቀያየር... አያሌው ጉሮሮውን ጠራርጎ ሚኪም ትኩረቱን ወደሱ አደረገ "ይሄንን ተጠቅመህ ነዋ ስትንዘባነን የነበረው ግን ድሮ ገና በቀረ መድሀኒት ምን ያህል ብትተማመን ነው አፍህን ሞልተህ ማውራት የቻልከው" አለው አሁን በስሜት ሳይሆን እንደባለሞያ ሰከን ብሎ ነው የጠየቀው " የተወጋበትን ቦታዎች ምርመራ ተደርጎባቸው በጣም ጥልቅ መሆናቸውን ሰምቻለሁ ይሄ ደግሞ ሴት ሆና ያውም ማክዳ ልታደርገው የምትችለው አይደለም ምናልባት ይሄ ጥሩ ነጥብ ከሆነ..." ብሎ አንጠልጥሎ  ተወው "እምም... ኦኬ የአሁኑ ምንም አይልም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ግን የፈለግከውን ተጠቅመህ ገዳዩን እንድታገኘው እፈልጋለሁ ደግሞ በመላ ምት አይደለም በማስረጃ የተደገፈ ነገር ነው የምፈልገው ይሄንን ኬዝ ጨርስና ስለ ብልቃጧ እንነጋገራለን " አለው " በራሴ መንገድ??... የምፈልገውን ተጠቅሜ??..." ሚኪ ፊቱ በራ 'አዎ' አሉት በጭንቅላት ንቅናቄ ከዛ አያሌውም ብስራትም  ያልጠበቁትን ነገር ተናገረ "እንግዲያውስ ሁሉም የቤተሰብ አባል ደም እንዲሰጡ እፈልጋለሁ" ✍nani
1 3164Loading...
Repost from ካሲና🫳🏿
እንባ እንባ ይለኛል      ይተናነቀኛል እንባ የት አባቱ ደርቋል       ከረጢቱ ሳቅ ሳቅም ይለኛል   ስቆ ላይስቅ ጥርሴ     ስቃ እየነደደች መከረኛ ነብሴ             ፨ ፨ ፨ ❇️በአሉ ግርማ
Show all...
👍 15🔥 6
Photo unavailableShow in Telegram
"ሆጵላስ!" ይሄን ያውቃሉ ? ይህ ቃል የተፈጠረበት አጋጣሚ  አንድ ፈረንጅ በሀገራችን የድንጋይ ናዳ መንገድ ይዘጋበታል። ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ድንጋዩን ከዘጋው መንገድ ለማስወጣት አብሮ መግፋት ይጀምራል። እየገፋም "hopeless!" (ተስፋ የለሽ!) ይላል። ይህንን በሰሙት የአበሻይቱ ልጆች አማካኝነት "ሆጵላስ!" ማበረታቻ ሆና በቋንቋችን ውስጥ ተፈጠረች። ሆጵላስ ደና ደሩ 😂
Show all...
😁 49👍 6 1
Repost from ካሊድ አቅሉ
Photo unavailableShow in Telegram
Denzel 🙏🙏
Show all...
13🔥 5
Repost from ኑ እናንብብ
Photo unavailableShow in Telegram
" ያ ደግ ሰው በመንገዱ እየኼደ ሳለ ሽፍታ አገኘ፡፡ ያ ደግ ሰው፤ “ሰላም ለአንተ ይኹን! በዚህ ስፍራ ለምን ብቻህን ትዘዋወራለህ?” አለው። ያ ሽፍታም፡ “እኔ ሽፍታ ነኝ! ለዚህም ነው በዚህ ሰዋራ ስፍራ የምዘዋወረው:: ይልቅ ምን ይዘሃል? ወዲህ በል የያዝኸውን ኹላ! አምጣው!” አለው። ያ ደግ ሰው፡ “ለምን ግን ሠርተህ አትበላም? ሰው የደከመበት ገንዘብ ላንተ ምን ያደርግልሃል?" አለው፡፡ ያ ሽፍታ እየሣቀ፡ “ስማ! ማር በልተህ ታውቃለህ?" አለው:: ያ ደግ ሰው፡ “እንዴታ! በደንብ አድርጌ ነዋ የምበላው!" አለው:: ያ ሽፍታ፡ “ሠርተህ ነው ወይስ ከንብ ቀምተህ ነው? በጭስ እያስፈራራህ፣ እንዳትታይ በጭንብል እየተከለልህ ነው ንብ ለፍታ የሠራችውን የምትቀማት” አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፤ ኹሉም ስው “ለፋኹበት” በሚለው ጕዳይ ወስጥ መዝረፍ እንዳለበት ዐወቀ። ከዚያም፣ ለሽፍታው “ብዙ ገንዘብ የለኝም:: ምናልባት ይህቺ ኹለት ፈረንካ ከበቃችህ እንካ” አለው፡፡ ያ ሽፍታ፡ “ለዛሬው ምሬሃለኹ፣ ከዚህ በኋላ ግን በማያገባህ ጕዳይ አትግባ" አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፡ “እንኳን ማርኸኝ እንጂ በል ደኅና ሰንብት" ብሎት ፈጠን ፈጠን እያለ ተራመደ፡፡ በመንገዱም ላይ ሳለ እንዲህ እያለ እያሰበ ነበር፡፡ “አኹን ግን የእውነት እንቁላልን ዶሮ የምትሸጠው ቢኾን ዋጋው ስንት ይኾን ነበር? ሰው ከዕቅፏ ፈልቅቆ ይወስድባታል እንጂ መቼ ይጠይቃታል። እና፣ ከደምና ከዐጥንቴ ያልሠራኹትን ገንዘብ ሽፍታ ወስዶብኝ እንዲህ ከተንገበገብኹ ልጅ ይኾነኛል ያልኹትን፣ ከብቤ ያኖርኹትን ቢያነሡብኝ ቀድሜ አበድኹኝ” እያለ ኑሮውን እየታዘበ ኼደ፡፡ " " ግርባብ ያ ደግ ሰው " በፍቃዱ አየልኝ መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል :: @jafbok
Show all...
16👍 5
Repost from እንማር
Photo unavailableShow in Telegram
#ዋጋህን_እወቀው! መነበብ ያለበት አስተማሪ ታሪክ "ትናንት ማታ አንድ ቪዲዮ እያየሁ ነበር። ሰባኪው የመቶ ብር ኖት ይዟል። እንዲህ ሲል ሰማሁት 'ይህ የብር ኖት እንደታተመ ምንም ዓይነት መጨማደድ አልነበረበትም። ከዚያ በኋላ ግን ሰዎች፦ ➡️እጽ ለመግዛት ተጠቅመውታል። ➡️ ለዝሙት ከፍለውታል። ➡️ጭቃ ውስጥ ነበር። ➡️ተቀዷል፣ ➡️ጠርዞቹ ተቆርጠዋል። ✅️ከዚህ ሁሉ ቀኋላ ይህ የመቶ ብር ኖት አሁን ዋጋው ስንት ነው? አሁንም ዋጋው ያኔ አዲስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ዋጋ ነው። አምላካችንም እኛንም የሚያየን እንደዚህ ነው። ያለፈው ታሪካችን ምንም ሆነ ምንም፣ የቱንም ያህል የተጎዳን እንሁን፤ ለእሱ ዋጋችን ያኔ ሲፈጥረን እንደነበረው ነው።' " ✅️👉#የተሰቀለው_ንጉሥ መጽሐፍ (አዲስ መጽሐፍ) 👉 #The_Crucifixion_of_the_King_of_Glory ✅️@Enmare1988 ✅️✅️@Enmare1988
Show all...
7
ሁለቱም እኩል ደወሉ እነማናቸው? ሳባ እና ዳዊት ለማንኛቸው እንደማነሳ ግራ ስጋባ ተዘጋ ሳባ መልሳ ደወለች እሱ text ላከ "ሚኪዬ ተቆጣኝ" አለቺኝ ይሄንን ሀረግ አውቀዋለው  የእሱም መልዕክት "ዛሬ ቀኑ ፈካ አላለብህም?" ይላል የሁለቱም ሀሳብ ትርጓሜው አዲስ ሰው ተዋውቀው ተመችተዋቸዋል ማለት ነው። "ኧ? ተቆጣኛ" አለቺኝ ምን ልበላት? ሁለቱም ጓደኞቼ ናቸው እሷ የመጨረሻ ኮስታራ ወንድ አጠገቧ የማታደርስ አይነት ሴት ናት የመጀመሪያዬ ጥሎኝ ሲሄድ ነው እንደዚህ የሆንኩት ትላለች እሱ ደግሞ የለየለት ሱሰኛ ነው እሱም  "ተከድቼ ነው" ነው ሰበቡ   በአንድ የተቀደሰ ልበለው የተረገመ ቀን አስተዋወቅኳቸው አጠገባቸው እኔ የሌለው ያህል በነፃነት ተሸኮረሟመሙ ከዛማ በቃ እፍ አሉ ሌላ ሰው የሌለ ያህል በየጎዳናው በየጥጋጥጉ በየቦታው አብረው ታዩ ከዛ ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳያብራሩልኝ በቃ ተደባበርን ብለው ተለያዩ ከዛ ዳዊት የሆነ ቅዳሜ ቀን መጥቶ "በቃ ንሰሀ ገብቼ መጣሁ ለእስከዛሬው ከዚ በኋላ ሱስ ደጅ ብደርስ" ብሎ እየተንጎራደደ ነገረኝ "ወገኛ! ሲሉ ሰምተሀል" ብዬ ችላ አልኩት እውነቱን ነው ብዬ አላሰብኩማ!! እሱ ግን አምርሮ ኖሯል እንዳለውም እርግፍ አድርጎ ተወው ሳባ እንዲተው እንዴት ትፈልግ እንደነበረ አስታውሼ "በእሷ ምክንያት ነዋ?" ብዬ ስጠይቀው ፊቱ ልወውውጥ ብሎ "ምንም ከሷ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም" አለኝ መልሴን ከፊቱ ላይ ስላገኘሁ "እሺ" አልኩት በሳምንቱ ከሳባ ጋር ተገናኝተን እያወራን እያለ በመሀል "እና በቃ ረሳሽው?" አልኳት ፊቷ ድምን ሲል እያየሁት "ማንን" አለቺኝ "ሳባ አትቀልጂ የእውነቴን..." ስላት ስልኳ ጠራ "ዳጊ" ይላል "ወዪዬ ዳጊዬ"  ብላ አነሳችው ዳግም ሲቆላመጥ ዳጊ ቆይ ዳጊዬን ምን አመጣው?! ደግሞ እኔ የማላውቀው ዳግም ማነው? እያልኩ ሳሰላስል "እኔም ናፍቀኸኛል እንገናኛለን" ብላ የውሸት ጥርስ በጥርስ ሆና ዘግታው "ዳግም ማነው" ስላት "አለ ባክህ የሚያዝገኝ" አለች "ፈገግታሽ እያዛገሽ አይመስልም" አልኳት "እ" አለች ከስልኳ ላይ ቀና ሳትል ከእጇ ላይ ነጥቄ ሳየው "እዩ" ይላል "መቼ ነው የማገኝሽ" ብሏት ሳትመልስለት ነው የተቀበልኳት "ተው ይደብረዋል ልመልስለት" ብላ መልሳ ወሰደችው "ምንድነው" አልኳት ዝም አለቺኝ የመጀመሪያው ፍቅረኛዋ ዝምተኛ አደረጋት የኔው ጉድ ጋር ስትለያይ ደግሞ የማንም ሆነች እሱ ደግሞ የመጀመሪያዋ ሱስ ውስጥ ዘፈቀችው ሳባ ስትተወው ደግሞ ሱስ ለምኔ አለ። ዛሬ ሁለቱም አዲስ ሰው እንደተዋወቁ እና ያ የተረገመ "ልዩ ስሜት" ስለተሰማቸው ነው የደወሉልኝ። እሺ አሁንስ ደግሞ እንዴት ያደርጋቸው ይሆን ምን አይነት ተፅዕኖ አሳድሮ ምን አይነት አሻራ ጥሎባቸው ያልፍ ይሆን? "ሄሎ ሚኪ አይሰማም እንዴ ተቆጣኝ እያልኩህ እኮ ነው" አለቺኝ ለካ እያናገርኳት ነው "ለምን እቆጣሻለው ጥፋት እኮ አይደለም" አልኳት "በምን አወቅክ" አለች በጥርጣሬ "አዲስ ነገር አይደለም ይሄ ለሶሰተኛ ጊዜ ስናስተናግደው ነው ብቻ አንድ የምልሽ ምንም ነገር እንደዚ እንዲያናውጥሽ እንዳትፈቅጂ እሺ" አልኳት "እሺ" ብላ ስልኩ ተዘጋ ወዲያው ለዳዊት መለስኩለት "ገና ለገና ሌላ ሴት መጣች ብለህ ወደዛ ሱስህ እመለሳለሁ ብትል እፈነክትሀለሁ" ብዬ መለስኩለት ✍nani
Show all...
17👍 12
Repost from ውብ ወግ
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ይህን👆 የገብረ ክርስቶስ ደስታን ገጠመኝ እና ስዕሉን ባየ ጊዜ ልቡ ተነካና ብዕሩን አንስቶ እንዲህ ሲል ተቀኘለት እዩት ይህን ጠቢብ ሸራው እስኪደማ በቀይ እየወጋ በደም እየሳለው እንጨት አመሳቅሎ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ላይ ሰቀለው። ቀራኒዮ ሆነ የወጠረው ሸራ ጎለጎታ ሆነ የወጠረው ሸራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ። ደም ከደም አረገው አበዛበት ጣር ብሩሹን አሹሎት እንደጎኑ ጦር። እየወጋ ሳለው በጣም ጨከነበት ገብረ ክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ የቆዳው አይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ። እየወጋ ሳለው እየሳለ ወጋው ደሙ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ ደሙ እስከሚናገር የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው አገር። እንዳንለው ፈረንጅ እንዳንለው ጥቁር እንዳንለው ቀይ በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ስቃይ። በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው። ከቀናት ባንዱ ለት ሰዎች ሲሟገቱ በቀለሙ ጉዳይ ሲከራከሩበት በተመፃዳቂ የምሁር አንደበት። በአንዱ አፍ ሲጠቁር በአንዱ አፍ ሲነጣ መታገስ አቃተው ሰዓሊው ተቆጣ ስሜቱ ገንፍሎ በብሩሽ ጫፍ ወጣ ሀሳቡን የሚገልፅ ቀለም እስከሚያጣ። ሸራ ላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ አልወጣልህ አለው ፍቅርን ስሎ ስሎ ስሎ ስሎ ስሎ ፍቅርን ስሎ ስሎ በሳለው እየወጋ በደማው እየቀባ። ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀለም እንጨቱ ላይ ያለው እውነት ይሄ አይደለም። እያለ እስኪናገር የስዕሉ አንደበት ገብረ ክርስቶስም ለክርስቶስ ’ሚሆን ቀለም እስኪያልቅበት በነጩ ሸራ ላይ እስካሁን የሚወርድ ደም አፈሰሰበት። ቀለም ቀይ ቀለም የደም ቀለም የጥላ ቀለም የሁሉም ነው እንጂ የማንም አይደለም ፍቅር ዘር አይደለም። @wegochi
Show all...
❤‍🔥 14👍 1
You realize you wouldn't have learned how to ride a bike if someone you trusted hadn't let you go. God works differently
Show all...
👍 2

26👍 11