cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ውብ ወግ

እንኳን ወደ ስነ ጹሑፍ ዓለም በሰላም መጡ።በዚህ ቻናል አዝናኝ ፣ አስቂኝ ፣ አስተማሪና አስደናቂ የሆኑ ጹሑፏች ይቀርባሉ።ምርጫዎ ስላደረጉን እናመሰግናለን!

Show more
Advertising posts
396
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሂሳብና ግጭት አፈታት አንድ የሂሳብ ፕሮፌሰር ከስራ ይባረርና ከሂሳብ ውጭ የሆነ ስራ ለመቀጠር ይወስናል:: አካባቢው ያለ የእሳት መከላከያ ብርጌድ እሳት አጥፊ ለመቅጠር ያወጣውን ማስታወቂያ አይቶ ያመለክትና ለቃለመጠይቅ ተጠራ::የመጀመሪያ ጥያቄ "በአንድ ሰፈር እያለፍክ በእሳት የተያያዘ ቤት ቢያጋጥምህ ምን ታደርጋለህ?" መልስ "ለእሳት አደጋ እደውልና እስኪደርሱ ድረስ በራሴ የምችለውን አደርጋለሁ እሳቱን ለመቆጣጠር::" በጣም ጥሩ ነው ይሉትና ሁለተኛ ጥያቄ ይሰጠዋል:: "በሆነ ሰፈር ስታልፍ ምንም ችግር የለም ምን ታደርጋለህ?" አሰበ አሰበና "መጀመሪያ አንዱ ቤት ላይ እሳት ለኩሳለሁ:: ከዚያም እሳት አደጋ ደውልና..." ብሎ ስራውን ሳያገኝ ቀረ:: ቀልድ ለማብራራት ያህል ሂሳብ ላይ የማናውቀው ነገር ከገጠመን ከዚህ በፊት ወደምናውቀው ነገር መቀየር ዋና ስትራቴጂ ነው:: ከዚያ መልስ በበፊቱ አሰራር እንዘጋዋለን:: በግጭት አፈታት የሚመረቁ እንደ ጠ/ሚ ያሉ ሰዎችም እንደዛ ያረጋቸዋል እንዴ? በሆነ ሰፈር ሲያልፉ ...
Show all...
👍 3
ከ ዶ/ር ቦሎዲያ ቀልዶች መሃል😃 ------------------------------ ዶ/ር ጌታቸው ቦሎድያ በAAU የባዮኬሚስትሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ነበር።አሁን ተረት ሆኑዋል። የሳይንስ ፋካልቲ ተማሪ ዶር ጌታቸውን በአባቱ ስም 'ቦሎድያ 'ማለት ይቀናዋል።እኛ ቦሎዲያ ላይ አልደረስንበትም። ቀልዶቹ ላይ ነበር የደረስነው።እናም ስራ ከምንፈታ ውስጥ አዋቂዎች የነገሩንን እና የሰማነውን እንገርብላችሁ እስቲ። •አንድ፦ ሁሌም ኮርሱን ማስተማር ሊጀምር ሲል እንዲህ ይላል "Come and drink from the fountain of knowledge. Here it is... in front of you...one of the best Biochemist in the world and also the only one in the horn of Africa..." •ሁለት፦ በደርግ ጊዜ ነው።አንዴ ወደ አውሮፓ ሊያቀና ሲል ዳጎስ ያለ ብር አስይዝ ይባላል። ይሄኔ "ለምን ሲባል?"ይላል ቦሎዲያ፤ "በዚያው እንዳትጠፋ ነው" ሲሉት፤ "እኔ ጌታቸው ቦሎዲያ ነኝ... አገሬን ለማንም መቶ አለቃና ሻለቃ ጥዬ የምጠፋ! ወይ አለመተዋወቅ።" •ሶስት፦ አንድ ተማሪውን ኦተሩ ብራዲ የሆነውን " ጄኔራል ኬሚስትሪ "የሚባል መፃፍ ይዞ ቦሎድያ ያገኘዋል። ይቀበለውና አገላብጦ፤ "እንዴ ብራዲ መፃፍ አሳተመች!?...አብረን ስንማር እኮ ጥያቄ ፈርታ ከኋላ ነበር የምትቀመጠው።" •አራት፦ አራት ኪሎ ሳይንስ ፋካልቲ ውስጥ አንድ ኤሊ አለች።ዩኒቨርስቲው ሲመሰረት ጀምሮ እዚያው ግቢው ውስጥ ነው የነበረችው።ያው ኤሊዎች የእድሜ ባለፀጋ ስለሆኑ ጌታቸው ቦሎዲያ ኤሊዋን ሲያያት እየሳቀ "ጉድ ሞርኒንግ ፕሮፌሰር ኤሊ!... "ጉድ አፍተርኑን ፕሮፌሰር ኤሊ!" እያለ ነበር አሉ የሚጠራት፤ "ለምንድን ነው?" ሲሉት፤ "እንኳን እሱዋ እነ እከሌ ፣እነ እከሊትም አስር አመት ዩኒቨርስቲ ስለቆዩ ብቻ ረዳት ፕሮፌሰር ተብለው የል እንዴ!"ይላል። . •አምስት፦ እንግዲህ በደርግ ወቅት ማታ ላይ በሬዲዮ በሰማው ዜና ጠዋት ክፍል ገብቶ ያላግጣል። የሰማውን እየደገመ፤ "ፐ! ትናንት የአርበጉጉ ገበሬዎች ...የሬገን አስተዳደርን ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ!!......Dear students...Do you think that the Arbagugu peasants know whether the Ragen administration is a human being or a computer machine?" •ስድስት፦ እንደራሱ በጣም የሚመካባት ሴት ልጁ ማትሪክ ወስዳ አንድ "ቢ "ተቀላቀለባት። "ጁኒየስ ናት ስትል አልነበር ወይ?"አሉት ፍሬንድስ፤ "ምን ላድርግ...የእናቱዋ ጂን ጉድ ሰራኝ።" . •ሰባት፦ ቦሎዲያ ከአንድ ተማሪ ጋር ተደባደበ፤አሉ። ይህን የሰማው የዩኒቨርስቲው አመራር፤ ለማባረር ፈጣን ነውና የተማሪውን መባረር ኖቲስ ቦርድ ላይ ለጠፈ።ቦሎዲያ ሲሰማ ወረቀቱን ገንጥሎ ፕረዘዳንቱ ዶር አብይ ክፍሌ ዘንድ ሄደለት፤ "አብይ ምን አግብቶህ ነው ይህን ምስኪን የምታባረው?...እኔን እንጂ ዩኒቨርስቲውን አልደበደበም!...እኔን ለመታኝ ደጅ ሳገኘው በቡጢ አቀምሰውና ብድሬን እመልሳለሁ። ልጁን አሁን በፍጥነት ወደ ትምህርቱ መልሰው።" •ስምንት፦ አንዴ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በመኪናው ሲመጣ ተማሪውን ያገኘዋል። "አንቺ! ነይ ግቢ" ይለዋል።አብሮት የነበረ ሌላ ተማሪም ይገባል... "አንቺን አላቅሽም...የምን ተማሪ ነሽ?" "የፖለቲካል ሳይንስ " ይላል ልጁ።...አራት ኪሎ ደርሰው ሲወርዱ እንዲህ አለው ልጁን፤ "...Keep the politics to yourself ...but leave the science to me "...ፖለቲክሱን ራስሽ እዛው ያዢው፤ሳይንሱን ግን ለኛ ተይልን እሺ!"
Show all...
👍 4
ውበት —.•: በመሥፈሪያ ከጤፍ ማዳበሪያ ሀሴት — .•: በላይ በላይ ከእንጀራ ምጣድ ላይ ስታስስ ይመሻል — .•: የሚያሳዝን ቀኗ ጨረቃ ሙዚቃ ሥነ-ጥበብ — .•ኮከብ — .•: አይማትርም ዓይኗ ••• ተአምሯ — .•: ማጀቷ ትንግርቷ — .•: ሽንኩርቷ ሲምፎኒዋ — .•: ሳንቲም ግጥሟ — .•: ቲማቲም የልቧ ሥራ — .•: ኩርማን እንጀራ የቀኗ ትጋት —.•: ጉሮሮዋን መዝጋት ••• ለመሰንበት መኖር — • እንደ ሁሉ ወጣት ፍልስፍና የቅኔ ጥፍጥና የመጽሐፍ ምዕራፍ አሪፍ ፎቶግራፍ — • ብዙም ግድ አይሰጣት ••• የመልስህን ዓለም በ’ሷ ጥያቄ ውስጥ — .•: ከምትፈልገው የቄሳርን ዲናር —.•: ለቄሳር አድርገው ••• ዳኛት በራሷ ሕግ ሆዷን —.• ጌታዋን — .• መቅደሷን አትናቀው ኩሽናዋን ስትረግጥ ጫማህን አውልቀው:: ✍ሔኖክ በቀለ
Show all...
3😁 1
ዳያሎግ °°°°°°°° " Students!" ... ቂቅ ብለው በከረባት ...የተሰናዳ የፈረንጅ ሬሳ መስለው " ፕስ..ፕስ..ፕስ..ፕስ....." " You should lower your voice " " ፕስ..ፕስ..ፕስ.." " I am warning you " " ፕስ..ፕስ.." ከፊት አቤልን በጥፊ ሲዘነጥሉት...ገባን! " Today, we will practice a dialogue " ሆዴን ቆረጠኝ እኔ ኢዝ.. ወዝ.. ዚስ.. ዛት ካላሉኝ ያሳክከኛል ክፍሉ በሶስት ረድፍ የተከፈለ ነው። የመጀመሪያው ጎበዝ ተማሪዎች ያሉበት፣ ሁለተኛው መካከለኞች ያሉበት ነው....ሶስተኛው የኛው ነው.. ቲቸር እምሩ " ነጉላ አምባ! " ይሉታል። ኮራጁ ፎራፊው ደጋሚው የሰፈረው በዚህ አምባ ነው። .....ጋላክቲኮሰ ድውያን! " Ok Fikre! " አሉ " Yes teacher "....የምወዳት መልስ " Be ready for your dialogue! " ረዘመ እንግሊዝኛው ለማንኛውም የስ ማለቱ ክፋት የለውምና፡ " Yes teacher! " አልኩ " Your partner will be Samuel " " Yes teacher "... ኪዳነ ቃሏ ትራዳኝ'ንጂ በኔ የስ ማብዛትስ እንጃ! ነገርየው ሰላምታ እንድንለዋወጥ ነው ለሚቀጥለው ተለማምደን እንድንመጣ ብለው፡ የምንነጋገረውን ጽፈው ሰጡን! ወይ ጣጣ! እኔና ሳሚ ልናጠና?...ሳሚ ሁለት ጊዜ የደገመ ነው በነገራችሁ ላይ ሰፈር እንግሊዝኛ ይዘፍናል የቦብ ማርሌይ፡ could you be loved and beloved ን " ኩኒ ጁንዳ ዶንዲዳውን..." እያለ ተርጉሞ..ይሄ ሙሉ ቅል! " ፍቅርሻ አትጨነቅ " አለኝ " ማለት? " " ዝምብለህ አይ አም ፋይን ቴንክ ዩ " በለኝ ይሁና! ቀኑ ደረሰና ሁለታችንም ተማሪዎች ፊት ቆምን። " How are you Fikre? " " አይ አም ፋይን ቴንኪዩ " " Where are you going? " " አይ አም ፋይን ቴንኪ ዩ " ቲቸር ግር አላቸው " Start over please! " ሙሉ ቅሌ ግራ ገባት " I said start over ሙጀሌው! "... ዴባለቁ! " start over " አለ ሳሚ " አይ አም ፋይን ቴንኪዩ "...ትህትናዬን ብታዩ! @wegochi #ፍቅሬ
Show all...
😁 9👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
"አይዞሽ ገለቴ" የዋህነት፣ ፍቅር እና ርህራሄ "አይዞሽ ገለቴ፤ አይዞሽ፤ አይዞሽ በቃ፤ ምን እናድርግ በቃ ምንም ማድረግ አይቻልም።" ስንቶቻችን እንሆን አሸንፈን ወይም ተሳክቶልን የክብር ቦታ ላይ ስንሆን ያዘኑ ያልተሳካላቸው እህት ወንድሞቻችንን "አይዞሽ" የምንል። ከራሳችን ደስታና Celebration ይልቅ ያዘኑ ወንድሞቻችንን ለማፅናናት የምናስብ። ቀነኒሳ በሩጫ ያስመዘገባቸው ድሎች ያኮሩኛል። ሁለት ቅፅበቶች ደግሞ የዋህነቱን፣ ፍቅሩን እና ለሌላ ሰው ያለውን ርህራሄ ያሳዩኛል። አንደኛው እየሮጠ ሀይሌን በአይኑ የፈለገበት ቅፅበት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "አይዞሽ ገለቴ" ያለበት ነው። በበርሊን የአትሌቲክስ ውድድር ቀነኒ በ5ሺህም በ10ሺህም ሁለት ወርቅ አግኝቶ በእንግሊዘኛ ቃለመጠይቅ እየሰጠ ነው። ገለቴ ቡርቃ ደግሞ በ1500 የፍፃሜ ውድድር ስትመራ ቆይታ ውድድሩ ሊያልቅ ሲል ተጠልፋ ወደቀች። አንደኛ መውጣት የምትችልበትን ውድድር በተሰራባት ፋውል ምክኒያት መጨረሻኛ ወጣች። እጅግ አዝና እያለቀሰች ነበር። በውድድሮቹ ላይ ማርሽ የሚቀይረው ቀነኒ ገለቴን ሲያያት ቋንቋውን ቀየረና ጋዜጠኛውን ችላ ብሎ እህቱን በአማርኛ አፅናናት "አይዞሽ ገለቴ፤ አይዞሽ፤ አይዞሽ በቃ፤ ምን እናድርግ በቃ ምንም ማድረግ አይቻልም።" አላት። የራሱ ክብር እንዲሁም የፈረንጅ ጋዜጠኛ ከእህቱ ሀዘን አይበልጥም።ከአስራ አራት አመት በኋላም "አይዞሽ ገለቴ" የሚለው አባባል ንግግራችን ውስጥ አለ። ውብ ቅፅበት፣ ውብ ነፍስ።
Show all...
9👍 1🥰 1
የኢራቅ ኩርዶች እንዲህ ይተርካሉ፤ አንዲት የልዑል ልጅ ነበረች፡፡ አንድ የምታፈቅረው ልጅም ነበረ፡፡ ታድያ ከአንድ የቤተ መንግሥቱ ጠባቂ ጋር ትመካከርና ይህንን ፍቅረኛዋን ክፍሏ ድረስ ታስገባው ነበር፡፡ የቤተ መንግሥቱ ጥበቃ የተወሰነ ገንዘብና ልብስ ትሰጠው ስለነበር በደስታ ምሥጢሩን ይደብቅ ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን ያልታሰበ ነገር ተከሰተ፡፡ ልዕልቲቱና ፍቅረኛዋ አፕል ቆርጠው እየተጫወቱ ይበሉ ነበር፡፡ ሁለቱም አፋቸውን ከፍተው የአፕሉን ቁራጭ አንዳቸው ወደሌላቸው አፍ ወርውሮ የማስገባት ጨዋታ ነበር የሚጫወቱት፡፡  እየተሳሳቁ የአፕል ቁራጭ ወደየአፎቻቸው ሲወረውሩ ልዕልቲቱ የወረወረችው የአፕል ቁራጭ ድንገት የፍቅረኛዋ ጉሮሮ ውስጥ ተቀረቀረ፡፡ ውኃ ብትሰጠው፣ ማጅራቱን ብትመታው ሊወርድለት አልቻለም፡፡ ኡኡ ብላ እንዳትጮህ ልጁ ማነው? እንዴትስ መጣ ? ለሚለው ጥያቄ የምትመልሰው የላትም፡፡ በዚህ መካከል ልጁ ትንፋሽ አጥሮት ሞተ፡፡ የልጁ የመውጫ ሰዓት ሲደርስ የጥበቃ ሠራተኛው መጣ፡፡ እንደቀድሞው ግን ልጁን ደብቆ ሊያስወጣው አይችልም፡፡ አሁን ያለው ሬሳው ነው፡፡ ‹እባክህን የምትችለውን ሁሉ አድርገህ ይህንን ሬሳ አውጣልኝ፤ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ አደርግልሃለው› አለቺው፡፡ የጥበቃ ሠራተኛውም ‹ምንም ችግር የለውም፤ የምፈልገው ግን ገንዘብ ወይም ልብስ አይደለም› አላት፡፡ እርሷም ‹ምንም ችግር የለም፡፡ ብቻ በቶሎ አውጣልኝ› ብላ ለመነችው፡፡ የጥበቃ ሠራተኛው ሬሳውን ቆሻሻ አስመስሎ ደብቆ  አወጣው፡፡ እርሷም እፎይ አለች፡፡ የጥበቃ ሠራተኛው ተመልሶ መጣና ቃል በገባችው መሠረት የሚፈልገውን ነገር እንድታደርግለት ጠየቃት፡፡ ‹ምን?› አለች ልዕልቲቱ፡፡ ‹ካንቺ ጋር መተኛት ነው የምፈልገው› አላት፡፡ ፀሐይ እንደበዛባት ቅል ክው አለች፡፡ ተናደደች፡፡ ‹ምን ደፋር ነህ ከልዕልት ጋር ለመተኛት የምታስብ፤ አሁን ከዚህ ጥፋ› አለቺው፡፡ እሺ ብሎ ወጣና የፍቅረኛዋን አስከሬን ይዞላት መጣ፡፡ ይኼኔ የምታደርገው ግራ ገባት፡፡ ያላት አማራጭ የሰውዬውን ፈቃድ ማሟላት ብቻ ሆነ፡፡ ተሸነፈች፡፡ በአንድ ቀንም ሦስት ነገሮችን አጣች፡፡ ፍቅረኛዋን፣ ክብሯንና የወደፊት ተስፋዋን፡፡ ፍቅረኛዋን በሞት፤ ክብሯንም በአገልጋይዋ እግር ሥር በመውደቅ፤ የወደፊቱንም ተስፋዋን ድንግልናዋን በማጣት፡፡  በዚህ ብቻ አላበቃችም፡፡ ያ የጥበቃ ሠራተኛ እየመጣ ‹አጋልጥሻለሁ› ይላታል፡፡ ያን ቀን ሬሳውን ይዞ የመጣበትን ጆንያም ያሳያታል፡፡ እርሷም ትፈራለች፡፡ በፍርሃትም የማትፈልገው ሰው እግር ሥር ትወድቃለች፡፡ ከእርሱም ጋር ትተኛለች፡፡ ይህ ግን ሊያዛልቃት አልቻለም፡፡ ባርነት ሰለቻት፡፡ ችግሮችን ለመጋፈጥ ካልፈለግህ ችግሮችን እያነገሥካቸው ትሄዳለህ› ይላሉ ኩርዶች፡፡ ችግርን ካታለልከው መልሶ ይይዝሃል፤ ከተጋፈጥከው ግን ጥሎህ ይሸሻል የሚል አባባልም አላቸው፡፡  ልዕልቲቱ አሁንም ችግሩን መፍታት ሳይሆን ማምለጥ ፈለገች፡፡ አንድ ሌሊት የጥበቃ ሠራተኛው ተደብቆ ወደእርሷ ሲመጣ ለአባቷ የምታዘጋጀውን የልዑሉን ወይን አሰናድታ ጠበቀቺው፡፡ በደስታ እየደጋገመ ጠጣ፡፡ ከእርሷም ጋር ከተኛ በኋላ እንደ ተሸነፈ ቦክሰኛ በድካም ተዘረረ፡፡ አርሷም እየጎተተች ወስዳ በልዑሉ መኝታ በር ላይ አጋደመችው፡፡ ሊነጋጋ ሲል ጠባቂዎቹ አዩት፡፡ ጠጋ ብለው ሲያሸቱት አፉ የወይን ጠጅ ይሸታል፡፡ የወይን ጠጁ ሽታ የልዑሉ ወይን መሆኑን ይመሰክራል፡፡ የልዑሉን ወይን ሰርቆ ጠጥቷል ብለው በአደባባይ ሰቅለው ገደሉት፡፡ ነገሩም በዚህ የተቋጨ መሰለ፡፡ ነገር ግን የዕብድ ቀን አይመሽም፡፡ ኩርዶች እንዲህ ይላሉ፡፡ የምትሠራው በር ምንጊዜም ልትሄድበት የምትችል መሆኑን አረጋግጥ፡፡ ለአንድ ጊዜ መውጫ ብለህ በሩን ከሠራኸው ከበሩ በኋላ ወዴት እንደምትሄድ ግራ ይገባሃል፡፡ በሩን ከነ መንገዱ አስበው፡፡ መንገዱን ከነ መዳረሻው፤ መዳረሻውንም ከነመቆያው፤ መቆያውን ከነ መክረሚያው፡፡  የጥበቃው ሠራተኛ በአደባባይ ሲሰቀል፤ የወይኑ ጣዕም አፉ ላይ ቀርቶ ስለነበር እየደጋገመ ከንፈሩን ይልስ ነበር፡፡ የዚህ ምክንያቱ የጠጣው የወይን ጠጅ ጣዕም ነው ተብሎ ተወራ፡፡ ይህንን ወሬ የሰማ የሌላ ልዑል ልጅም ይህንን ወይን ያዘጋጀቺውን የልዑሉን ልጅ ለማግባት ፈለገ፡፡ እናም ወደ ልዕልቲቱ አባት ሽማግሌዎች ላከ፡፡ ይህ ዜና ለአባቷ የምሥራች ለልዕልቲቱ ግን መርዶ ነበር፡፡ ድንግልናዋን አጥታለች፡፡ በኩርድ ደግሞ ድንግል ያልሆነቺውን ልጅ እንኳን ልዑላን ተራዎቹ ሰዎች አያገቡም፡፡ እስካሁን ችግሩን ከመጋፈጥ እየሸሸች፣ ነገር ግን አንዱን ችግር በሌላ ችግር እያለፈች መጥታለች፡፡ አሁን የመጋፈጫው ሰዓት ደረሰ፡፡ ችግርን በመፍትሔ መፍታትና ችግርን በሌላ ችግር ማለፍ ይለያያሉ፡፡ ችግርን በችግር ካለፍከፈው ጊዜ እየገዛህ ነው፡፡ ችግርን በመፍትሔ ካለፍከው ደግሞ ልብ እየገዛህ ነው፡፡ ይላሉ ኩርዶች፡፡  የልዕልቲቱ አባት ጋብቻውን መቀበሉን ስትሰማ እንደተለመደው ልዕልቲቱ አንድ ዘዴ ቀየሰች፡፡ አንዱን ታማኝ አገልጋይዋን ጠራችውና አንድ እፍኝ ወርቅ ሰጥታ እንዲህ ስትል አዘዘችው ‹በመላዋ ኢራቅ ዙር፡፡ በመልክም፣ በቁመትም፣ በጠባይም እኔን የምትመስል ልጅ ፈልገህ ለደንገጡርነት አምጣልኝ›፡፡ ሰውዬውም ለወራት ያህል ከቦታ ወደ ቦታ ዞረ፡፡ በመጨረሻም አንዲት ልጅ አገኘ፡፡ ልዕልቲቱ ስታያት ቁርጥ እርሷን ትመስላለች፡፡ እንዲህ አለቻት ልጅቱን፡፡ አሁን አንቺ ልዕልት ሆነሻል አሉ፡፡ የልዑሉንም ልጅ ታገቢያለሽ፡፡ የጫጉላውንም ጊዜ አብረሽው ታሳልፊያለሽ፡፡ እኔም ያንቺ ደንገጡር ሆኜ አንቺንና ልዑሉን ለጊዜው እታዘዛለሁ፡፡ ልክ የጫጉላው ጊዜ እንዳለፈ ግን ትቀይሪኛለሽ፡፤ እንቺ ወደ ደንገጡርነትሽ እኔም ወደ እመቤትነቴ እመለሳለሁ፡፡ ለዚህ ውለታሽም ለጥሎሽ የሚመጣውን ሀብት ሁሉ ትወስጃለሽ› አለቻት፡፡ ልጂቱም በደስታ ተፍነከነከች፡፡  የሠርጉ ቀን ደረሰ፡፡ ደንገጡሯዋ የሙሽራ ልብስ ለበሰች፡፡ እመቤቲቱ ደግሞ የአገልጋይ ልብስ ለበሰች፡፡ ማንም ሊለያቸው የቻለ የለም፡፡ ልዑሉ መጣ፡፡ ሙሽራዋን ይዞ ሄደ፡፡ አገልጋይዋም ተከትላ ሄደች፡፡ በልዑሉ ቤት የነበረው ድግስ ሲያልቅ ልዑሉና ሙሽራዋ ወደ ጫጉላ ቤት ገቡ፡፡ አገልጋይዋም ከውጭ ቀረች፡፡ ታስበዋለች፡፡ ይህ ዕድል የእርሷ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን አይደለም፡፡ አሁን እርሷ ነበረች እዚያ ውስጥ መሆን የነበረባት፤ ግን ችግርን ለማለፍ ብላ በፈጠረችው ችግር ምክንያት ውጭ ቆማለች፡፡ እዚህ ደረጃ ሳትደርስ ነገሮችን አስተካክላ በክብር ልትወጣ ትችል የነበረባቸውን ዕድሎች ታስታውሳለች፡፡ ዕድሎች ሁሉ አምልጠዋታል፡፡ ችግሮችን በሌላ ችግር በመተካት ዕድሎችን አምክናቸዋለች፡፡ ስለዚህም ክብሯን ለሌላዋ አሳልፋ ሰጠቻት፡፡ ሕዝቡ ጫጉላ ቤት ያለቺው እርሷ መስላቸዋለች፡፡ ግን አይደለችም፡፡ የተመረጠችው እርሷ፣ ወደ ሠገነት የወጣችው ሌላዋ፡፡ የተዳረችው እርሷ፣ ያገባችው ሌላዋ፡፡ የጫጉላዎቹ ቀናት አለፉ፡፡ ልጂቱ ግን ወደ አገልጋይነቷ ልትመለስ አልቻለችም፡፡ አንድ ቀን መታጠቢያ ቤት ውስጥ እመቤትና ደንገጡር ተገናኙ፡፡ ደንገጡሯም ‹አሁን በቃሽ ወደቦታሽ ተመለሽ፡፡ ለውለታሽ ያዘጋጀሁትን ስጦታሽን ውሰጅ; አለቻት፡፡ እመቤቲቱም ‹የዋሕ ነሽ፡፡ ላየው የማልችለውን አሳየሺኝ፤ ላገኘው የማልችለውን ሰጠሽኝ፤ ልደርስበት የማልችለው ቦታ አደረሽኝ፡፡ ያኔ እሺ ስልሽ ይህንን ሁሉ አላውቅም ነበር፡፡ አልጋው እንዲህ የሚመች መሆኑን አልቀመስኩም ነበር፡፡ ክብሩ እንዲህ የሚያጓጓ መሆኑን አላውቅም ነበር፡፡
Show all...
ምቾቱ እንዲህ ልብ የሚለሰልብ መሆኑን አላውቅም ነበር፡፡ ላንቺ ከደንገጡርነት ወደ እመቤትነት መምጣት ቀላል ይሆናል፡፡ ለእኔ ግን ከእመቤትነት ወደ ደንገጡርነት መውረድ ከባድ ነው፡፡ ይህንን የመሰለ ነገር ከቀመስኩ በኋላ ትተውልኛለች ብለሽ ማሰብሽ ሞኝነትሽ ነው፡፡ አልጋ አንዲህ በቀላሉ የሚተው አይደለም፡፡ ሀብቱ ሁሉ የእኔ መሆኑን እያየሁ ያንቺ ስጦታ የሚያጓጓኝ ይመስልሻል› አለቻት፡፡  ›እነሆ› ይላሉ ኩርዶች፡፡ እነሆ በዚህ የተነሣ አገልጋይቱ እመቤት፣ እመቤቲቱም አገልጋይ ሆነው ኖሩ፡፡ ተቀምጣ የሰቀለቺውን ቆማ ማውረድ አቅቷት፡፡  ✍ዳንኤል ክብረት
Show all...
👍 1 1
በአንድ ወቅት አንድ የዋህ የባላገር ሰዉ በገጠራማ አካባቢ መንገድ እየተጓዘ ሳለ የሚረብሽ ድምፅ ሰምቶ ወደ ድምፁ አቅጣጫ በማምራት አዞን በወጥመድ ዉስጥ ተይዞ እንዳየዉ ልቡ ራደ፡፡ ፈጥኖ ምን ሆነህ ነዉ ምን ላድርግልህ? ብሎ አዞዉን በሀዘኔታ ጠየቀዉ፡፡ አዞዉም ክፉ ሰዉ በወጥመድ አስይዞኝ ነዉ፤ አባክህ ከወጥዱ አስጥለኝ ሲል ተማጸነዉ፡፡ የዋሁ ሰዉም ጊዜ ሳያጠፋ አዞዉን ከወጥመዱ አላቆት መንገዱን ሊቀጥል ፊቱን ወደ መጣበት አቅጣጫ አዙሮ አንድ እግሩን አንስቶ መጓዝ ሲጀምር ከመሬት ያልተነሳ እግሩን አዞዉ በጥርሱ ይዞ ይጎትተዉ ጀመር፡፡ ይሄኔ የዋሁ ሰዉ ምነዉ ወዳጄ? በረዳሁህ ትነክሰኛለህ ሲለዉ ፡፡ አዞዉ መልሶ እንግዲህ አለም መንገዷ ይሄዉ ነዉ አለ ፡፡ በዚህ መሃል የሚበላ ፍለጋ የምተባዝብ ጥንቸል ክርክሩን ሰምታ ኖሮ ጠጋ ብላ የክርክሩ ምክንያት ምን እንደሆነ ጠየቀች፡፡ የዋሁ ሰዉም ሂደቱን ተረከላት፡፡ ጥንቸልም ጉዳዩን በጥሞና ካደመጠች በኋላ እኔ ምን ልርዳችሁ? የእኔን ዳኝነት የምትቀበሉ ከሆነ ፍርድ ልስጥ ማለቷን ተከትሎ ሁለቱም በዳኝነቷ ተስማሙ፡፡ ይሄኔ ጥንቸል የዋሁን ሰዉ ሂደቱን በተግባር አሳዬኝ አለችዉ፡፡ ግለሰቡም ብሶቱን መለፍለፍ ጀመረ ፡፡ ጥንቸል በብስጭት አስቁማዉ መጀመሪያ አዞን ያየሄዉ የት ቆመህ ነዉ? አለችዉ፤ ሰዉዬዉ አሳያት፤ አዞስ? ስትለዉ በወጥመድ ዉስጥ የነበረበት ቦታ ሄዶ ቆመ፡፡ ጥንቸልም ወጥመዱ እንዴት ነበር የነበረዉ? ብላ ጠየቀች የዋሁ ግለሰብም ወጥመዱን በአዞዉ ላይ አኑሮ ሲያበቃ ይሄዉ ነዉ አላት ፡፡ ይሄኔ ጥንቸል ታዲያ ምን ትጠብቃለህ? ከመንደርህ ሰዎች ጥራና የምታረገዉን አድርግ ስትለዉ ወደ መንደር ሄዶ በርካታ ሰዎች ጦር፤ ገጀራ፤ ዱላና ድንጋይ ይዘዉ እየመራቸዉ አዞዉ ካለበት ቦታ በመድረስ ያስተባበር ገባ፡፡ ጥንቸልም የሁኔታዉን መጨረሻ ለማየት ጉብታ ላይ ሆና ትከታተል በነበረችበት የየዋሁ ሰዉ ዉሻ አብሮ መጥቶ ኖሮ በጥንቸልዋ ላይ ሲጮህ አይቶ ----ምን ቢል ይሻለዋል?? ጃስ….ጃስ እያለ ወደ ጥንቸልዋ አመለከተ…… ይሄኔ ጥንቸል ለመሮጥ እየተዘጋጀት ምነዉ ወዳጄ? አንተን በማትረፌ ይህ ይገባኛል? ብትለዉ…. …እንግዲህ አለም መንገዷ ይሄዉ ነዉ አለ (This is the way how the world is going on) @wegochi
Show all...
👍 4👎 2
‹‹ሚያው›› አብረን ያየን ሰው ሁሉ ‹‹አፈስሽ አፈስሽ›› እያለ ያወራል። ቆንጆ፣ ሎጋ፣ ረጋ ያለ እና ዝምተኛ ነው። የወንድ ልጅ አማላይነት የተሰራው ከእነዚህ ተንኮለኛ ንጥረ ነገሮች አይደል? በፍቅር መውደቅ ከገደል እንደመውደቅ ያማል? በፍቅር መያዝ እንደ ተስቦ ያማቅቃል? አዎ። ቢሆንም እያመመኝ እወደዋለሁ። እየማቀቅኩ አፈቅረዋለሁ። እኔ እወደዋለሁ። እሱ ግን እንደሁሉም ሰው ሳይሆን ከመላእክት ተዳቅሎ እንደተፈጠረ ይለጠጥብኛል። ይንበላጠጥብኛል። ቢሆንም ስሜቴ ለእርሱ ባሪያ ነው። ሲያወድሰኝ ብቻ የማብብ- ሲኮንነኝ የምጠወልግ ፣ ሲመለከተኝ የማምር- ፊቱን ሲያዞርብኝ የማስቀይም እስከሚመስለኝ ድረስ እወደዋለሁ። ይሄን አውቃለሁ። ፍቅሬ አቅብጦታል። መውደዴ አቀማጥሎታል። ብዙ ጊዜ ደህና ስንጫወት እንውልና በድንገት ያኮርፈኛል። ይኮፈሳል። አይኔን ማየት ይጠላል። ያን ጊዜ ሁሉ ነገር ይዞርብኛል። ሳቄ ይከስማል። የልቤ ቡረቃ በሃዘን አታሞ ይተካል። ይገርመኛል። በስሜቴ ላይ እንዲህ እንዲሰለጥን ከመፍቀዴ በፊት…እሱን ከማግኘቴ በፊት በምን ነበር የምስቀው? በምንስ ነበር የምደሰተው? ‹‹ምን ሆንክብኝ›› እለዋለሁ ልክ እንደዚያ ሲሰራው። ‹‹ምንም አልሆንኩም…ተይኝ ላንብብበት›› ለዚህች ለዚህች ጊዜ ተዘጋጅታ የምትቀመጥ፣ መዥረጥ አድርጎ የሚያወጣት መደበኛ እና የዘወትር መልሱ ናት። – ኤሊ.. – እ… (ከልቡ ሳይሆን) – ሻይ በጦስኝ ላፍላልህ? (ሻይ በጦስኝ ስለሚወድ) – አልፈልግም – ፍሬንድስን ልክፈትልህ? (ፍሬንድስን አይቶ ስለማይጠግብ) – አላሰኘኝም – ቶሎ ሃያ ሁለት ሄጄ የፀሃይን ሽሮ ይዤልህ ልምጣ? (ከትግሬ ሽሮ ሌላ በአለም ላይ ደህና ምግብ ያለ ስለማይመስለው) – አልራበኝም… – እሺ ምንድነው ምትፈልገው? – ተይኝ ላንብብበት… ይሄኔ ነው የአዳም ረታን አንዱን መፅሃፍ አውጥቶ ጥሎኝ የሚሄደው። ይሄኔ ነው የራሱን ክብ አለም ፈጥሮ አፈናጥሮ የሚያስወጣኝ። ያን ጊዜ ማውራት መቀጠሌ ለሬሳ መድሃኒት ከመስጠት እንደማይለይ ስለማውቅ ጥዬው ለመሄድ እሰናዳለሁ። መፅሃፉ ላይ ተተክሎ አንዴ የለዘዘ ፈገግታ ሲያሳይ፣ አንዴ ጮህ ብሎ ሲስቅ፣ ከዚያ እንደማልቀስ ሲሰራው በእሱ ስሜት ላይ በሰለጠነው ብቸኛው ሰው አዳም ረታ እቀናለሁ። አንዳንዴም የምወደውን ልጅ ስለነጠቀኝ እያልጎመጎምኩ በልቤ እረግመዋለሁ። ‹‹ብእርህ ይንጠፍ..እጅህን ቁርጥማት ይዘዝበት›› አይነት ነገር። ‹‹ልሄድ ነው ቻው›› እለዋለሁ ጫማዬን አጥልቄ ስጨርስ። – እሺ..ቻው… ይለኛል ቦግ ቦግ ያሉ አይኖቹን ከመፅሀፉ ሳይለይ። ስሜቱን ከአዳም ረታ ገፀ ባህሪያት ሳያላቅቅ። ያን ጊዜ ከእንባዬ እየታገልኩ ወደ ቤቴ! ስምንት ወር አብረን ስንወጣ- ስንገባ – ስንተኛ ስንነሳ- ብረት አሎሎ ልቡን አልፈታልኝም። ስለአለፈ ሕይወቱ አይነግረኝም። ስለወደፊቱ አያወራኝም። ከቤተሰብ- ጓደኛ አያስተዋውቀኝም። እየቆየ የትርፍ ሰአት ስራው መሆኔ ሲገለፅልኝ ጨምቷ ልጅ ላብድ ደረስኩ። ተዉኩት ስል እያገረሸ በሚያስቸግረኝ አስቀያሚ ፍቅሩ ብሸነፍም ቁርጤን ማወቅ እንዳብኝ አመንኩ። አንዱን ቅዳሜ ስገሰግስ ቤቱ ደረስኩ። ከሰአት 9 ሰአት ቢሆንም አብዝቶ የሚለብሰውን እህቱ ከካናዳ የላከችለትን ፒጃማ አድርጎ ሶፋው ላይ ተጋድሞ ያነባል። ማንን? ያንን በየአመቱ መፅሃፍ የሚያመርተውን አዳም ረታ። – ስማ ኤልያስ …እኔ እንደዚህ መቀጠል አልችልም…ማውራት አለብን… አልኩ ቦርሳዬን አንዱ ሶፋ ላይ ወርውሬ አጠገቡ እየተቀመጥኩ። – እ…. ? አለኝ መፅሀፉን ሳይዘጋ ቀና ብሎ እያየኝ.. – አመልህ ሊገባኝ አልቻለም…እኔ እወድሃለሁ…ግን ማትወደኝ ከሆነ…ማለቴ ልብህን ማትሰጠኝ ከሆነ… ሳልጨርስ አቋረጠኝ። – ምንድነው ምትፈልጊው? ተናዶም በማይለወጠው እርጋታና ግዴለሽነቱ ጠየቀኝ (መፅሃፉን ዘጋ። ጉዳዩ ሲሪየስ ነው!) – እኔ? – አዎ አንቺ…ምንድነው ምትፈለጊው? ምንድነው የምፈልገው? እንዴትስ ብዬ ነው የምጠይቀው…? ከአንጀቱ- እንዲህ በትኩረት እያየኝ ይጠይቀኛል ብዬ አስቤ ስለማላውቅ እያሰብኩ ያንን ውብ ፊቱን አየሁት። ጢሙ እንደምወደው አድጓል። ጠጉሩ ጨብረር ብሏል። መከረኛ ፒጃማው እጅጌ እና አንገቱ ጋር መንችኳል። ዝም ብሎ ያየኛል። ብዙ ጊዜ ይሄን ያህል ጊዜ ሰጥቶ አያየኝም። ሳያስበው አይኖቹን በአይኖቼ ስይዘው አይኖቹ ላይ ትኩረትና ፍቅር አላይም። አንዳንዴ እንደውም ውስጤ መቆየት የሰለቸው… ዘልአለም የከረመ ያህል የታከተው የሚመስል ነገር አይኖቹ ላይ አነባለሁ። እንዲህ አይቶኝ አያውቅም። በማውራት ይሄን ያልተለመደ ክስተት ላቋርጥና ላበላሽ ስላልፈለግኩ ካለሁበት ሶፋ እየተሳብኩ ተጠጋሁት። ማየቱን ቀጥሏል። ደርሼ አንገቴን አንገቱ ውስጥ ቀብሬ በጥልቀት አሸተትኩት። ጦስኝ ጦስኝ ይላል። ልቤ እንደሰም ሲቀልጥ፣ መንፈሴ በስሜት ማእበል ሲታመስ እንኳን የማወራው የማስበው ነገር ከአንጎሌ ሲተን… – እህስ….ምንድነው የምትፈልጊው? አለኝ ከአንገቱ ውስጥ በእጁ ጎትቶ እያወጣኝ… – ምንም… – ምንም አትፈልጊም? – ኤሊ…እንድትወደኝ…እንድትወደኝ ነው የምፈልገው…ያ ይከብዳል? ወደ አንገቱ ስር ተመልሼ ልወሸቅ ስል አሁንም መልሶ አወጣኝና በእነዚያ አሸባሪ አይኖቹ እያየየኝ – መች ጠላሁሽ… ?አለኝ። – እንደማትጠላኝ አውቃለሁ..ግን አንድ ቀን እወድሻለሁ ብለኸኝ አታውቅም…እ…ከመሬት ተነስተህ ታኮርፈኛለህ…ታበሻቅጠኛለህ… – ምንድነው የምትፈልጊው? በስርአት ቁጭ ብለን ይሄን ነገር እንቋጨው…አለኝ ለስብሰባ እንደተቀመጠ ሰው መፅሃፉን እንደተከፈተ ሶፋው ላይ አስቀምጦ፣ እጆቹን አጣምሮ። ቀና ብዬ ተቀመጥኩ። – ልብህን…ልብህን ነው የምፈልገው… እጆቹን አመሳቀለና ሳቀ። ተበሳጨሁ። – ያስቃል? – ሃሃ…አዎ..እዚህ መፅሃፍ ላይ ያለው…አንዱ የአዳም ካራክተር ምን አለ መሰለሽ… ልቤን ለሴት ከምሰጥ ለጎረቤት ድመት ብሰጥ ይሻለኛል… ዝም ብዬ አየሁት። – ምን ታይኛለሽ..ካንጀቴ እኮ ነው…እውነቱን ነው… አሁንም ዝም ብዬ አየሁት – ጨረስን? ወደ መፅሃፌ ልመለስ? – እየቀለድክ አይመስለኝም…አልኩ በተቀመጥኩበት እየተቁነጠነጥኩ – አይደለም አልኩሽ እኮ… – የአንድ ደራሲ ተረት ተረት እያነበብክ የእኛን ሕይወት ማበላሸት አለብህ? – አዳም ስለማይገባሽ አልፈርድብሽም…. – እሱን ተወው..ዝባዝንኬ አይገባኝም…ድመት ምናምን…ሰውየው የሚያወራውን አያውቀውም…ግን አንተ ምነው ለልብህ እንደዚህ ሳሳህ? ልብህን ሰጥተኸው የጎዳህ ሰው ነበር እንዴ…እየተቁለጨለጭኩ ተጠየቅኩት ዝም ብሎ ሲያየኝ ቆየና… – ለምን ጦስኝ ሻይ አታፈይልኝም? ጠዋት የጠጣሁ ነኝ አለኝ መፅሃፉን እያነሳ… – ለምን አትመልስልኝም…ለምንድነው እንደዚህ ፍቅርን የምትፈራው? – በናትሽ ሻዩን…እያዛጋኝ ነው…. የምናብ ደጁ ሊዘጋብኝ ነው። ለዛሬ ከዚህ በላይ ሊያናግረኝ አልፈቀደም። ለሻዩ ወደ ኩሽና መንገድ ጀመርኩና መለስ ብዬ አየሁት -ኤሊ… – እ….? (ከልቡ ሳይሆን) – ልቤን ለሴት ከምሰጥ ለድመት ብሰጥ ይሻለኛል ነው ያልከኝ አይደል..? – እ…አዎ… የኩሽና መንገዴን ቀጠልኩ። ሻይ ጀበናውን በውሃ ሞልቼ ምድጃው ላይ ጣድኩ። ጦስኙን አዘጋጀሁ። የእሱን ልብ እንዳገኝ ሰውነቱ ቀርቶብኝ ምነው ለአንዲት ቀን ድመት ባደረገኝ። የማፈቅረው ልጅ መልሶ እንዲያፈቅረኝ ምነው ለአንድ ሌት ሚያው ባስባለኝ። ሚያው…. ✍ሕይወት እምሻው @wegochi
Show all...
6👍 3
ህንዳዊው ቢሊየነር ራታን ታታ በስልክ ቃለ ምልልስ በሬዲዮ አዘጋጁ ሲጠየቅ የሰጠው አስገራሚ ንግግር ነው።በህይወትህ ውስጥ በጣም ደስተኛ ስትሆን ምን ታስታውሳለህ? ራታንጂ ታታ እንዲህ ብሏል፦ በህይወቴ ውስጥ አራት የደስታ ደረጃዎችን አልፌያለሁ፣እና በመጨረሻም የእውነተኛ ደስታን ትርጉም ተረዳሁ።የመጀመርያው ደረጃ ሀብት ማሰባሰብ ነበር።በዚህ ደረጃ ግን የምፈልገውን ደስታ አላገኘሁም።ከዚያም ውድ ዕቃዎችንና ጌጣጌጥ መሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃ ነበር።ነገር ግን የዚህ ነገር ውጤት ጊዜያዊ እና የከበሩ ነገሮች ብሩህነት ብዙም እንደማይቆይ ተገነዘብኩ። ከዚያም አንድ ትልቅ ፕሮጀክት የመስራት ሦስተኛው ምዕራፍ መጣ፣በህንድ እና በአፍሪካ 95 በመቶው የናፍታ አቅርቦት የነበረኝ ያኔ ነበር።በህንድ እና እስያ ትልቁ የብረት ፋብሪካ ባለቤትም ነበርኩ።ግን እዚህም ቢሆን ያሰብኩትን ደስታ አላገኘሁም። አራተኛው እርምጃ አንድ ጓደኛዬ ለአካል ጉዳተኛ ልጆች ዊልቼር እንድገዛ ሲጠይቀኝ ነበር።ወደ 200 ለሚጠጉ ልጆች በጓደኛዬ ትዕዛዝ ወዲያውኑ ዊልቼር ገዛሁ።ጓደኛዬ ግን አብሬው ሄጄ ዊልቸሮችን ለልጆቹ እንዳስረክብ ነገረኝ። ተዘጋጅቼ አብሬው ሄድኩ።እዚያም ለእነዚህ ልጆች የተሽከርካሪ ወንበሮችን በገዛ እጄ ሰጠኋቸው።በእነዚህ ልጆች ፊት ላይ እንግዳ የሆነ የደስታ ብርሃን አየሁ። ሁሉም በዊልቸር ተቀምጠው ሲዘዋወሩ እና ሲዝናኑ አየሁ። በውስጤ እውነተኛ ደስታ ተሰማኝ።ስጦታዎችን ሰጦቼ ተሰናብቼ ልወጣ ስል ከልጆች አንዱ እግሬን ያዘኝ።እግሮቼን ቀስ በቀስ ለማስለቀቅ ሞከርኩ፣ ነገር ግን ዊልቸር ተቀምጦ እግሬን የያዘው ልጅ ፊቴን ተመለከተ እና እግሬን አጥብቆ ያዘ ጎንበስ ብዬ ልጁን ጠየቅኩት "ሌላ ነገር ያስፈልገሃል?" ይህ ልጅ የሰጠኝ መልስ አስደንጋጭ ብቻ ሳይሆን ለህይወት ያለኝን አመለካከት ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል።ልጁም እንዲህ አለኝ ፦ "በገነት ካንተ ጋር ስገናኝ እንድለይህና በድጋሚ ገነት ላይ እንዳመሰግንህ ፊትህን በደንብ ለማየት እፈልጋለሁ.....!!" ብሎ አንገቴን አቅፎ ፊቴን በደንብ አይቶ ዐይኑ እንባ እያቀረረ ተሰነባብተን ተለያየን።😍😍😍
Show all...
5👏 4