cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Bemnet Library

ሁሉም ዓይነት መፅሀፍ ለእርስዎ ቀርቧል #ማጋራት መተሳሰብ ነው ! ከ 2014 ጀምሮ! እንደ እርስዎ ላሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቁጥር 1 ምርጫዎች ነበርን Adv @Bemni_Alex

Show more
Advertising posts
49 296
Subscribers
+624 hours
+6147 days
+1 52830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ሕግ 12
የምታጠቃውን ሰው ትጥቅ ለማስፈታት በአሳቻ ሰዓት የማይጠብቀውን ሃቀኝነት እና ለጋስነትን አሳየው!"
ለጠላትህ በማይጠብቀው ሰዓት ከልብህ በሚመስል መልኩ ሃቀኝነት እና ለጋስነትህን አሳየው! በዚህ መልኩ እጅግ ተጠራጣሪ የሚባሉትን ሰዎች ሁሉ ልብ መግዛት ትችላለህ። እንዲህ አድርገህ ልባቸውን ታስከፍትና ቀስ በቀስ ጉድጓዳቸውን ትቆፍርላቸኃለህ! በገዛ ፍቃዳቸው በከፈቱልህ ልባቸው ገብተህ እንደልብህ ልታታልላቸው እና ልታጦዛቸው ትችላለህ። አንዳንዴ ያልጠበቁትን ስጦታ በመስጠት ሳይቀር ልባቸውን ሰርስረህ ግባ! ከሕግ 1 ለመጀመር https://t.me/Bemnet_Library/3982 📓48ቱ የኃይል ህጎች ✍️ ሮበርት ግሪን 📚 @Bemnet_Library
Show all...
👍 5😱 4 1
Photo unavailableShow in Telegram
ፀሀይ ከመውጣቷ አስራ አምስት ደቀቃዎች ቀደም ብሎ፤ሰማዩ ፈገግ ማለት ሲጀምር፤ ልክ አንድ ሰው ፍቅረኛውን እንደሚጠብቀው ጠብቁና ተመልከቱ።በደስታና በተስፋ ተሞልታችሁ፤ በፀጥታ ተጠባበቁ።ፀሀይ ስትወጣም ምልከታችሁን ቀጥሉ።ማፍጠጥ አያስፈልግም፤ የአይኖቻችሁ ቆቦች እንደተለመደው እንዲርገበገቡ ተዋቸው።በተመሳሳይ ጊዜም ልክ እንደ ፀሀይ ውጣት ሁሉ፣አንድ ነገር በውስጣችሁ እየተነሳሳ እንደሆነ ይሰማችሁ ፀሀይ አድማስ ላይ ስትመጣ፤ልክ እምብርታችሁ አጠገብ፤የሆነች ያህል ይሰማችሁ።እዛ ደመቅ ትላለች።እና እዚህም እብርታችሁ ውስጥ መድመቋ ይቀጥላል።እዛ ፀሀይ እየወጣች ነው፤እዚህ ደግሞ ውስጠ ብርሃናችሁ እየተነሳ ነው።አስር ደቂቃዎች ይበቃሉ፤ከዛም አይኖቻችሁን ክደኑ።ፀሀይዋን በመጀመሪያ በአይናችሁ ስትመለከቷት ተንፅባርቃ አቅጣጫዋን ትቀይራለች፤አይኖቻችሁን ስትከድኑ ደግሞ ፀሀይዋ ውስጣችሁ ስታበራ ይሰማችኋል።ይሄ በእጅጉ ይቀይራቹኋል። 📓 ፍቅርና ተመስጦ ✍️ ኦሾ 📚 @Bemnet_Library
Show all...
27👍 16
Photo unavailableShow in Telegram
ጠዋት ጠዋት መሮጥ ጀምሩ፤በግማሽ ማይሎች ጀምሩ።ወደ አንድ ከዚያም ቢያንስ ወደ ሶስት ማይሎች አድርሱት።በምትሮጡበት ጊዜ መላው አካላችሁን ተጠቀሙ።ልክ እጁ እንደታሰረ ሰው አትሩጡ።መላው አካላችሁን፤እግሮችና እጆቻችሁን ተጠቅማችሁ፤ልክ እንደ ትንሽ ልጅ ሩጡ። ከሆድ እቃችሁ በጥልቁ ተንፍሱ።ከዛም ዛፍ ስር ተቀመጡ፤እረፍት ውሰዱ፤ላባችሁ ይውረድ፤ቀዝቃዛው ንፋስ ይንፈስባችሁ፤ሰላም ይሰማችሁ።ይሄ በጥልቁ ይረዳችኋል። አልፎ አልፎ መሬት ላይ በባዶ እግሮቻችሁ ቁሙና ቅዝቃዜው ይሰማችሁ።ልስላሴው፤ሞቅታው ይሰማችሁ።ምድሪቱ በዛ ቅፅበት የምትሰጣችሁን ማንኛውንም ስሜት ይሰማችሁ።ወደ ውስጣችሁ እንዲዘልቅ ፍቀዱ፣የናንተም ሀይል ወደ ምድሪቱ እንዲዘልፍ ፍቀዱ፤ከምድር ጋር ተዋሃዱ። 📓 ፍቅርና ተመስጦ ✍️ ኦሾ 📚 @Bemnet_Library
Show all...
44👍 28🔥 4
Photo unavailableShow in Telegram
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ @Zephilosophy https://t.me/joinchat/RVzIu0-BTYG_XaN8 👆👆👆 በዚህ ቻናል  የአለምን የአስተሳሰብ መንገድ የቀየሩ የታላላቅ ፈላስፋዎች አስተሳሰቦች እና ፍልስፍናዎች ከየመፅሀፉ እየተጨለፉ ለእናንተ ይቀርባሉ።አለም ላይ የማይፋቅ አሻራዎቻቸውን ያሳረፋ ግለሰቦች፤ በዘመናት ውስጥ የተፈጠሩ ሀይማኖቶች ፣ስርዓቶች ርዕዮተ ዓለሞች ሁሉ ይዳሰሳሉ። ለዓለም ያስገኙት ሞራላዊና መንፈሳዊ ትሩፋቶች ይወዳሳሉ። ታሪካዊ ህፀፆቻው ደግሞ ያለምህረት ይተቻሉ!! ማህበረሰቡ የሚሳሳላቸው ባህሎቹ እና እምነቶቹ በነፃነት ይጠየቃሉ ፣ይመረመራሉ ። እንደ ጣት ቁስል የተፈሩ እውነቶች መሀረባቸው ይገለጣል። እንደ ማህበረሰብ በጉያችን የጋረድናቸው እባጮች የግንባር ስጋ ይሆናሉ።ከግለሰብ እስከ ቡድን ፤ከሀይማኖት እስከ ርዕዮተ -ዓለም ፤ ከኋለቀር ባህሎች እስከ ዘመናዊ ስልጣኔዎች ያለምንም ፍርሃት በግላጭ ይሞገታሉ፣ ይመረመራሉ፤ይጠየቃሉ ውስጣቸው የተደበቀው እውነት እስኪገለጥ ድረስ በአውድማው ላይ መንሽ እየተፈለገ ፍሬው ከገለባ ይለያል። መንሻችን የሰላ አምክንዮዊ አእምሮ፣ የሰከነ የሞራል ልዕልና እና ንፁህ ሰዋዊ ህሊና ናቸው። Join 👇👇👇👇 @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
6👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከ24 ሰአት ውስጥ አንዱን ወይም ሁለቱን ሰአት ለመዝናናት  ብታውሉት ራሳችሁን በጥልቀት መመልከት እንደምትጀምሩ ስታስተውሉት ትደነቃላችሁ። ይሄም ውጫዊ ባህሪያችሁን ይለውጠዋል።የተረጋጋችሁና ዝምተኛ ትሆናላችሁ።የስራችሁን ጥራት ይለውጠዋል።ስራችሁ የበለጠ ጥበባዊና ማራኪ ይሆናል።የምትሰሯቸው ስህተቶች ይቀንሳሉ፤ምክንያቱም አሁን የበለጠ ስብስብ ያላችሁና አስተዋይ ሆናችኋል። መዝናናት ተአምራዊ ሀይሎች አሉት።መዝናናት መስነፍ አይደለም።ሰነፍ ሰው ከውጪ ሲታይ ምንም የማይሰራ ቢመስልም አይምሮው በተቻለው ፍጥነት እየሰራ ነው።አንድ ሰው ሲዝናና አካሉ፤አይምሮው ልቡ በሙሉ ይዝናናሉ።ለሁለት ሰአታት ያህል ይጠፋል።በእነዚያ ሁለት ሰአታት ውስጥ አካሉ ያገግማል፤ልቡ ያገግማል።ብልህነቱ ያገግማል፤ከዚያም የስራውን ፍሬ ይመለከታል። 📓አካለ አዕምሮ ✍️ኦሾ 📚 @Bemnet_Library
Show all...
👍 48 8😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዴርቶጋዳ ማለት "አናቆምም አናፈገፍግም" ማለት ነው።"We Never Hesitate" ማለት ነው።"አናፈገፍግም" ማለት ነው።እንዲያውም የመዝሙሩ ሁለት ስንኞት ትርጉሙን የያዙ ናቸው.....ልዘምርላችሁ..." አብረውት ባንድ ላይ እየዘመሩ ወደ ዴር33 አውሮፕላን ተከታትለው ገቡ።......... ዴርቶጋዳ ዴርቶጋዳ.......... ማንም ሰው ላይመጣ እኛን ለመለወጥ አናፈገፍግም አናቅማማም ለለውጥ። ዴርቶጋዳ ዴርቶጋዳ........... ያቀረቀርክበት አንገት ያስደፋህ ቀን ነግቷል ብለህ ተነስ ፍዳና ሰቀቀን።....... 📓 ዴርቶጋዳ ✍️ ይስማዕከ ወርቁ 📚 @Bemnet_Library
Show all...
88👍 36💯 4
ለብቻችሁ በምትሆኑ ጊዜ የበለጠ ግርማሞገስ ይኖራችኋል።ምክንያቱም አትጨነቁም።የሚከለክላችሁ ሰው የለም።ብቻችሁን ስትሆኑ ከሌላው ጊዜ ይልቅ የዋህና ብፁእ ትሆናላችሁ።ልክ እንደ ህፃን ልጅ ትመስላላችሁ። መስታወት ፊት ቆማችሁ ገፃችሁን እንዳሻችሁ እያጨማደዳችሁ፤ዐይናችሁን እያፈጠጣችሁ፤ምላሳችሁን እያወጣችሁ እንደቀውስ ብትሆኑ ደስ ይላችኋል።ብቸኝነት በጣም አስደናቂውና ጣፋጩ የተዝናኖት ማዕከል ነው። 📓 ራስን ማግኘት ✍️ ኦሾ 📚 @Bemnet_Library
Show all...
👍 93 18🔥 5
ከ40 በላይ ተመስጦዎችን ያካተተ መጽሐፍ.. 📓 ፍቅርና ተመስጦ (ወንድና ሴት) ✍️ አሾ ማጋራት መተሳሰብ ነው! 📚 Bemnet_Library
Show all...
ፍቅርና ተመስጦ.pdf15.73 MB
👍 25 4💯 4
የአዕምሮ ሚዛናዊነት የሚገኘው በህይወቱ ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው አንኳር ጉዳዮች የጠራ አስተሳሰብ ያለውና ቅድሚያ ለሚሰጣቸውን ነገሮች ለመቀዳጀት ትኩረት ባደረገ ሰው ላይ ነው። 📚 ርዕሰ፦ 7ቱ የስኬት ሚስጥራት 📝 ፀሃፊ፦ ስቴፈን R.ኮቬይ ✍️ ትርጉም፦ ቢኒያም አለማየሁ ማጋራት መተሳሰብ ነው!! 📚 @Bemnet_Library
Show all...
2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.