cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የተፈታው በርባን YETEFETAW BERBAN

አንድያ ልጁን እስከመስጠት ወዶናል💙 የተፈታው በርባን👇👇 🔵ንፁህ የሆነው ኢየሱስ የሞት ፍርድን ሲቀበል 🔴አመፀኛውና ሞቱን ሲጠባበቅ የነበረው በርባን ነፃ ወጣ 🤎ይቀላቀሉ ለሌዎችም ያጋሩ🧡 👤 @teme_arega bot: @berbantefeta_bot Group🙋 @tsegahybeqagnal https://youtube.com/channel/UCylvsUSCX9tGgikroJ65fig

Show more
Advertising posts
9 661Subscribers
-124 hours
-407 days
-14930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

1ኛ ሳሙኤል 24 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ የዳዊትም ሰዎች፦ እነሆ፥ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ በዓይንህም ደስ የሚያሰኝህን ታደርግበታለህ ብሎ እግዚአብሔር የነገረህ ቀን፥ እነሆ፥ ዛሬ ነው አሉት። ዳዊትም ተነሥቶ የሳኦልን መጎናጸፊያ ዘርፍ በቀስታ ቈረጠ። ⁵ ከዚያም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የሳኦልን የልብሱን ዘርፍ ስለቈረጠ የዳዊት ልብ በኀዘን ተመታ።      ሳኦል እግዚአብሔርን ከመከተል የተመለሰ፣ የዳዊት ዋና ጠላት እና አሳዳጅ፤ ዳዊትንም ደግሞ እጅግ ይጠላው ነበር። ክፉ መንፈስ ሳኦልን ሲያስጨንቀው፣ በእጁ በገና እየመታ፣ ክፉውን በቅዱስ መንፈስ እያባረረ እረፍት ይሰጠው ነበር። ሳኦል ግን ጦር ይወረውር እና ሊገድለው፣ ከተቀመጠበት ግድግዳ ጋር ያጣብቀው ዘንድ ይመኝ ነበር። ነፍሱን ሊወስድ ለሚወደው ክፉ ስለ ልብስ ዘርፉ መቆረጥ አዘነ! መፅሀፍ እንዳለ “በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛልና፥” በከንቱ እና ያለ ምክኒያት እንዲሁም በመልካም ፈንታ ክፉ ሊመልስለት ይፈልገው ነበር። መሲሁ (ጌታችን) እንዳለ “ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።” ቀኑን ሁሉ ክፉ ከአፉ እንዲወጣ ይፈላልጉት ነበር፤ ሊያጠፉት በቀን እና በለሊት የሚኖርበትን ይፈልጉ እና ይማከሩበት ነበር። የሚከሱበትን ነገር ዘወትር ያለ መታከት ይፈልጉበት እና ይፈትኑት ነበር።      አርሱ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ሲቀርብ አያት እና አለቀሰላት፣ እርሱ ለረሃባቸው ጥጋብ፤ ለጥማታቸው እርካታ ነበር፤ ለእርሱ ጥማት ግን ሆምጣጤ አቀረቡለት። በመልካም ፈንታ ክፉ፣ በበጎ ፈንታ ሞት መለሱለት። ትላንት ከአንድ ወንድም ጋር እየተጫወትን፣ ድንገት የዳዊትን ህይወት እያወጋን እንገረም ነበር፤ በእርግጥ እርሱ የመሲሁ (የጌታ) ጥላ ነው። ንጉስ ሳኦል ለሞት ይፈልገዋል፤ የንጉሱን የልብስ ዘርፍ ስለቆረጠ ዳዊት ልቡ በሀዘን ተመታ። ለጠላቱ እጅግ አዘነ፤ እግዚአብሔር ቀብቶት ለነበረ እና አሁን ግን ለተጣለ እጅጉን አዘነ። ለወደቀ ወንድምህ ታዝናለህን? ለጠላቱ እና ምሬትን ላሳየው ልቡ እጅግ በሀዘን ተመታ! አንድ ጌታ አለና፤ ለአንድ መንግስት እንሰራለንና፤ አንድ መንግስት እንወርሳለንና፤ አንዳችሁ ለሌላችሁ አስቡ እና ፀልዩ፣ ማንም በመውደቁ ደስ አይበላችሁ። ሁለት ጌቶች ቢኖረን፥ ምን ግድ ብሎን ሁሉም ለጌታው ሲል ሌላውን ይንቃል፣ ይገፋል። ለእኛ ግን እንደዚህ አይደለም፤ አንድ ጌታ አለንና እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!      እንግዲህ እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፤ ደግሞም ፍቅርን፣ እምነትን፣ ፅድቅን፣ ሰላምን ተከተሉ! በፍቅር ተመላለሱ! በአለም እንደሚታይ አርሾ በእናንተ አይገኝ! ነገር ግን ክፋትን ሁሉ አስወግዳችሁ፤ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ህንፃ ለመሆን ተሰሩ፤ እርስ በእርሳችን ብልቶች ስለሆንን፤ ሁሉን በሰፊ ልብ ተቀበሉ፣ የተናቀና ትንሽ የአካል ክፍል እንኳ እጅግ የሚበልጥ አገልግሎት እና ስራ በመሀከላችን አለውና!!!      እግዚአብሔር አምላክ በነገር ሁሉ ፊተኛ እና ቀዳሚ ያድርጋችሁ! የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
Show all...
🔥 5👍 3🥰 3😁 1
ከመሞትህ በፊት ይሄን ስማ❗️❗️😳 🛑መደመጥ ያለበት ድንቅ መልዕክት👇👇👇 ለሁሉም ሰው እንዲደርስ share share share https://youtu.be/aoGr6HVSMMM
Show all...
4👍 2
🎥Watch Now🎥
⏯ክፈት
“በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? — መኃልየ. 8፥5 Share share share share Tiktok    telegram    YouTube የተፈታው በርባን
Show all...
😭 10 6🥰 5👍 3🔥 3
የቆላስይስ መፅሐፍ ትምህርት ክፍል ዘጠኝ በነብይ ጥላሁን ፀጋዬ Colossians by prophet Tilahun Tsegaye Share share share share Tiktok    telegram    YouTube የተፈታው በርባን
Show all...
6👍 2🙏 1
አሁን መሆን ያለበትን የምናደርጉበትን አቅም አሁን መሆን የሌለበትን ነገር የምንጠብቅበትን ትዕግስት ያብዛልን። ነገር ውብ የሚሆነው ሳይፈጥንና ሳይረፍድ በጊዜው ሲሆን ነው
Show all...
10🥰 4🙏 4👍 1
ይሄን ቦት ሞክሩት ለኔ ሰርቶልኛል👇 https://t.me/hulepay_official_bot?start=r0331810065 https://t.me/hulepay_official_bot?start=r0331810065 1 ሰው ስትጋብዙ 3 ብር ይሰጣችኋል
Show all...
🙏 2
ሮሜ 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ¹⁵ ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ። ¹⁶ እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። ¹⁷ ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ¹⁸ ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ። ¹⁹ ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ²⁰ ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። ²¹ ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
Show all...
👍 19 4
ዎኒ አዋንዲ | Qinea worship team Woni Awandi Wolaita Ethiopian Gospel song ወላይትኛ መዝሙር Share share share share Tiktok    telegram    YouTube የተፈታው በርባ ን
Show all...
7🔥 3👍 1
“አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ።” — ሉቃስ 6፥36
Show all...
33👍 1