3 756
Subscribers
+224 hours
+117 days
+4930 days
Posts Archive
Repost from Tikvah-University
"ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት"፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር "የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር አፈጻጸምን" አስመልክቶ በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተፈረመ ሰርኩላር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል፡፡
ሰርኩላሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሠራሮችን አስቀምጧል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች በሚኒስቴሩ ከተላለፈ የምደባ ውጤት ውጭ ተማሪን በራሳቸው ተነሳሽነት መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡
ተቋማቱ ከተቀመጠው የምደባ መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ፣ በልዩ ትዕዛዝ ወይም ለአንድ ተማሪ ብቻ በሚደረግ ልዩ አሠራር የትምህርት መስክ ምደባ መቀየር አይችሉም።
ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ሲሆን፣ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት ተብሏል።
የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስቴር የተማረ እና ከፕሮግራሙ 50 በመቶ በላይ ያላጠናቀቀ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር ሊፈፀም የሚችል ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል፡፡ (ሰርኩላሩ ከላይ ተያይዟል፡፡)
@tikvahuniversity
Repost from Tikvah-University
#ጥቆማ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ2026/2027 የትምህርት ዘመን የድኅረ-ምረቃ አመልካቾች መቀበል ጀምሯል፡፡
አመልካቾች ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትነው ያለፋ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ አመልካቾቹን የሚቀበለው የትምህርት ክፍል የፅሑፍ እና የቃል ፈተናዎች ይሰጣል፡፡
የሕክምና ትምህርት ቤት (በመደበኛ መርሐግብር)
ስፖንሰር፦ በግል ወይም በመንግሥት
ፕሮግራሞች፦ በአራት የMSc ትምህርት መስኮች
የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት (በመደበኛ እና በዕረፍት ቀናት መርሐግብር)
ስፖንሰር፦ በግል ወይም በመንግሥት
ፕሮግራሞች፦ በስድስት የMPH ትምህርት መስኮች
የነርሲንግ ትምህርት ቤት (በመደበኛ መርሐግብር)
ስፖንሰር፦ በግል ወይም በመንግሥት
ፕሮግራሞች፦ በስምንት የMSc ትምህርት መስኮች
የምዝገባ ጊዜ 👇
ከመስከረም 11-27/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ፦
https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement
@tikvahuniversity
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ምደባ ይፋ ሆነ።
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።
በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ።
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement
ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።
በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement
እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
#MoE
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
Repost from Ministry of Education Ethiopia
ማስታወቂያ
ለ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
በ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች፣ በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት ስማችሁንና ሪፈረንስ ቁጥራችሁን በማስገባት እስከ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ ፦ ያሉን ቦታዎች ውስን በመሆናቸው በተጠባባቂነት ከተያዙ መካከል የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑን እየገለጽን ምደባ የሚካሄደው ክፍት ቦታዎች ባሏቸው ት/ቤቶች እንደሚሆን እናሳውቃለን።
የትምህርት ሚኒስቴር
Repost from Tikvah-University
+2
#ጥቆማ
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ2019 የትምህርት ዘመን በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስኮች በሪሚዲያል መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ተዘጋጅቷል፡፡
ከላይ በምስሉ ላይ የተገለፀውን የመቁረጫ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ያሳወቀ በመሆኑ፤ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡
በኢንስቲትዩቱ በሪሚዲያል መርሐግብር የሚታቀፉ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚመጡ ተማሪዎች የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ የሚመጡ ተማሪዎች የምግብ አገልግት ብቻ ያገኛሉ፡፡
የማመልከቻ ጊዜ 👇
እስከ መስከረም 15/2019 ዓ.ም
የማመልከቻ ቦታ 👇
በአዲስ አበባ ዋና ካምፓስ፣ ከላምበረት መናኸሪያ 500 ሜትር አለፍ ብሎ ወደወሰን መስመር
አስፈላጊ ሰነዶች፡-
➻ የ11ኛ እና 12ኛ ከፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
➻ የ12ኛ ከፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬት
➻ የፋይዳ መታወቂያ ዋናውና ኮፒው
(የመቁረጫ ነጥብ እና የትምህርት መስኮች ዝርዝር ከላይ በምስሉ ተያይዟል፡፡)
@tikvahuniversity
Repost from Tikvah-University
+1
#ጥቆማ
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም በአማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም (Alternative Teachers' Training Program) ለዘጠኝ ወራት ሰልጥነው በተለያዩ ክልሎች ውል ፈርመው በመምህርነት ለማገልገል የሚፈልጉ አመልካቾችን ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የስልጠና ዘርፎች
➻ Biology
➻ Chemistry
➻ Mathematics
➻ Physics
➻ History
➻ Geography
➻ Citizenship
➻ Economics
➻ Agriculture
➻Performing and Visual Arts
➻ English Language
➻ Information Communication Technology
የማመልከቻ መስፈርቶች
➻ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመርያ ዲግሪ ያለው/ያላት እና የመውጫ ፈተና ያለፉ
➻ ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ የኦፊሺያል ትራንሰከሪፕት ማስላክ የሚችል/የምትችል
➻ በመምህርነት ለማገልገል ፍላጎት ያላቸው
➻ ከግል ትምህርት ተቋማት የተመረቁ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኝነት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡
የማመልከቻ ጊዜ
ከመስከረም 9-25/2019 ዓ.ም
ያመልክቱ 👇
https://forms.gle/PhDzQiRbRjkrRcRp8 ላይ በመግባት አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላትና የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በማያያዝ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።
ለሴት አመልካቾች እንዲሁም የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት ለማይፈልጉ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
Repost from Ministry of Education Ethiopia
ማስታወቂያ
በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7/ 2019 ዓ.ም. እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ እንድትሞሉ እንገልጻለን።
የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences
Repost from Tikvah-University
#AASTU
በ2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ያመለከቱና የመግቢያ ፈተና የወሰዱ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የቅበላ የመቁረጫ ነጥብ በዩኒቨርሲቲው ይፋ ሆኗል።
ለኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች
➻ አማካይ ውጤት 69.50 እና ከዚያ በላይ
ለአፕላይድ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች
➻ አማካይ ውጤት 48.00 እና ከዚያ በላይ
ይህ የመቁረጫ ነጥብ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን ለመረጡ ብቻ የሚሠራ ነው፡፡
ውጤት ለመመልከት 👇
https://www.aastu.edu.et/result/
የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እና ሌሎች መረጃዎችን በቅርቡ እንደሚገልፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
@tikvahuniversity
አዎ፣ ይህ ዜና እውነት ነው። ዛሬ፣ መስከረም 4 ቀን 2026፣ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ “Correct the Map” የተሰኘውን ውሳኔ በ164 ድምፅ ደግፎ፣ 1 ተቃውሞ (አሜሪካ) እና 6 ድምፀ ተአቅቦ አጽድቋል።
🌍 ምን ማለት ነው?
ዋናው ጉዳይ አፍሪካን በካርታ ላይ በትክክለኛው የመሬት ስፋቷ ማሳየት ነው።
የMercator projection በ16ኛው ክፍለ ዘመን ለባሕር አሰሳ የተሠራ ሲሆን፣ ከኢኳተር ርቀው ያሉ አካባቢዎችን በካርታ ላይ እጅግ ያሰፋል። በዚህም አፍሪካ ከእውነተኛ ስፋቷ በጣም ትንሽ እንደሆነች ትታያለች።
እውነታው:
🌍 አፍሪካ ≈ 30.3 ሚሊዮን km²
🇬🇱 ከግሪንላንድ ወደ 14 ጊዜ ያህል ትበልጣለች
አፍሪካ ውስጥ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ጃፓን፣ ሜክሲኮ እና ተጨማሪ የአውሮፓ ክፍል በአንድ ላይ ሊገቡ ይችላሉ።
🗺️ አዲሱ ካርታ
የTogo እና African Union የሚደግፉት Equal Earth የተባለው የካርታ ፕሮጀክሽን የአህጉራትን የመሬት ስፋት መጠን በተመጣጣኝ ሁኔታ ያሳያል።
⚠️ ግን አስፈላጊ ማስታወሻ: ይህ ውሳኔ ህጋዊ ግዴታ አይደለም። ስለዚህ ነገ ጀምሮ በዓለም ላይ ሁሉም ካርታዎች ይቀየራሉ ማለት አይደለም። ይልቁንም መንግሥታት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሚዲያዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት የበለጠ ትክክለኛ የካርታ ፕሮጀክሽኖችን እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ።
በአጭሩ፦ “አፍሪካ አሁን ትልቅ ሆነች” ማለት አይደለም—አፍሪካ ሁልጊዜም ትልቅ ነበረች፤ አዲሱ ካርታ ግን ያላትን እውነተኛ ስፋት በተሻለ ሁኔታ እንድናይ ያደርጋል። 🌍❤️💚💛
fine Fact ff page
ተመድ የአፍሪካን ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ አጸደቀ
NBC Ethiopia
። ። ። ። ። ። ። ። ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ፤ የአፍሪካን እውነተኛና ትክክለኛ መልክዓ-ምድራዊ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ በይፋ አጽድቋል።
ይህ ታሪካዊ ውሳኔ የተላለፈው በአፍሪካ ህብረት ስም በቶጎ አቅራቢነት የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ መሰረት በማድረግ ሲሆን፣ ዓላማውም ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የተዘጋጀውን የተዛባ የካርታ አሰራር እንዲያከትም ማድረግ ነው።
በውሳኔው መሠረት፣ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለውና ለአፍሪካ አህጉር ትክክለኛ ያልሆነ ስፋት ይሰጥ የነበረው የሜርካቶር ካርታ ከስራ ውጪ እንደሚሆን ቢቢሲ ዘግቧል።
በምትኩ ደግሞ እንደ እ.ኤ.አ. በ2018 ይፋ የሆነውና የምድርን ትክክለኛ መጠንና ድርሻ የሚያንጸባርቀው "ኢኩዋል አርዝ"(Equal Earth) የመሳሰሉ ዘመናዊ እና እኩል አቀራረብ ያላቸው የካርታ ቀመሮች በስራ ላይ ይውላሉ።
ይህ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘ ሲሆን፣ 164 ሀገራት የውሳኔ ሀሳቡ እንዲፀድቅ ድጋፍ ሰጥተዋል።
የተለመደውና የድሮው ካርታ የተሰራው እ.አ.አ በ1569 በደች (ፍሌሚሽ) ካርታ ሰሪ በጄራርዱስ ሜርካቶር ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በወቅቱ ለባህር ዳር መርከበኞች ማሰሻነት እንዲያገለግል ነበር።
ይሁን እንጂ ይህ ካርታ ከምድር ወገብ (Equator) እየራቀ ሲኬድ የመሬትን ስፋት እያጋነነ የሚያሳይ በመሆኑ፣ የምድር ወገብ አቅራቢያ የሚገኙ አካባቢዎችን በዕይታ በእጅጉ እንዲቀንሱ አድርጓል።
በዚህ የተዛባ የካርታ አሰራር ምክንያት አፍሪካ ከግሪንላንድ ደሴት ጋር ተቀራራቢ መጠን እንዳላት ሆና ስትታይ ቆይታለች።
አፍሪካ ከግሪንላንድ በ14 እጥፍ የምትበልጥ ትልቅ አህጉር መሆኗ ይታወቃል።
የዘመቻው ደጋፊዎች እና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኞች ይህንን እርምጃ በዓለም አቀፍ የትምህርት ስርዓት እና የካርታ ስራ ውስጥ ለዘመናት የዘለቀውን የምዕራባውያን አድሎአዊ እይታ ለማስተካከል የተወሰደ ትልቅ ታሪካዊ እርምጃ አድርገው እንደወሰዱት የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 100 አመልካቾችን በአታሼ (Attaché) የሥራ መደብ ለመቅጠር የሥራ ማስታወቂያ አውጥቷል።
- የሥራ መደብ፦ አታሼ (Attaché)
- የሚቀጠሩ ሰዎች ብዛት፦ 100
- ደመወዝ፦ ብር 12,566
- የማመልከቻ ጊዜ፦ 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት
➡️ ተፈላጊ ችሎታ ፦ በማንኛውም ትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪና 0 ዓመት የስራ ልምድ
ምዝገባው በወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲሱ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተቀመጠው የመመዝገቢያ ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ ይቻላል https://forms.gle/R7PmwCNeqEE3EQBN6
📌 Tikvah Economy and Jobs https://t.me/TikvahEconomy/138
@tikvahethiopia
Repost from Addis Ababa Education Bureau
በክፍል ውስጥ ትምህርታቸውን በትኩረት ከሚከታተሉ ተማሪዎች መካከል እንደምትጠቀስ የገለጸችው ተማሪዋ፣ ይህም ለፈተና ዝግጅት ከፍተኛ እገዛ እንዳደረገላት አብራርታለች። እንዲሁም በማንበብ ሂደት ውስጥ ማስታወሻ መያዝ እጅግ ጠቃሚ ነገር መሆኑን እና ይህም በፈተና ወቅት ከፍተኛ በራስ መተማመን እንደሚፈጥርላት ተናግራለች።
እቅዷ ከ580 በላይ ውጤት ማምጣት እንደነበር ለኤ ኤም ኤን የገለጸችው ተማሪ ኤፍራታ፣ በፈተናው ወቅት የነበሩትን ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት በማስገባት “በቃ 570 ካመጣሁ ይበቃኛል” ብላ እንደነበርም አንስታለች።
ለዚህ ድል ስኬት ከፈጣሪዋ በመቀጠል የእቴጌ መነን ትምህርት ቤት ማህበረሰብ፣ መምህራን እና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ሰራተኞች ድጋፍ የላቀ እንደነበር ተማሪዋ አስገንዝባለች።
ተማሪዋ አራት ዓመት ሙሉ ከጎበዝ ተማሪዎች ጋር መማሯን እና የመምህራንም ሁለገብ ድጋፍ ትልቅ መነቃቃትን እንደፈጠረላት ገልጻለች።
አያቷ የፊዚክስ ትምህርት መምህር እንደነበሩ ያነሳችው ተማሪ ኤፍራታ ከልጅነቷ ጀምሮ ላደረጉላት ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ ምስጋና አቅርባለች።
ሀገራችን አሁን ላይ በርካታ የተማረ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል እንደምትፈልግ የጠቆመችው ተማሪ ኤፍራታ፣ በዲጂታሉ ዘመን ለሚከሰቱ ችግሮች ተግባራዊ መፍትሄዎችን በማምጣት የህክምናውን ዘርፍ የመቀላቀል ትልቅ እቅድ እንዳላት መጠቆማን AMN ዘግባል።
Repost from Addis Ababa Education Bureau
በልጃገረዶች 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት ያመጣችው ተማሪ ለሕክምና ትምህርት መዘጋጀቷን ገለጸች።
በ2018 የትምህርት ዘመን ከእቴጌ መነን የልጃገረዶች 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ለሕክምና ትምህርት መዘጋጀቷን ተማሪ ኤፍራታ አለማየሁ ገለጸች።
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ይፋ እየሆነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ከእቴጌ መነን አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተፈጥሮ ሳይንስ ሥርዓተ ትምህርት ስትከታተል የነበረችው ተማሪ ኤፍራታ አለማየሁ አስደናቂ ውጤት ማስመዝገቧን ገልጻለች።
ተማሪ ኤፍራታ አለማየሁ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 574.84 ነጥብ በማምጣት በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቋ ይታወቃል።
ተማሪዋ ለዚህ ስኬቷ በዋነኝነት የፈጣሪዋ እገዛና ጸሎት ዋነኛው ምስጢር መሆኑን የገለጸች ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ በየቀኑ ለሚገጥሟት ፈተናዎች እጅ ባለመስጠት እና ፈተናዎችን በትዕግስት በመሻገር በየቀኑ ያለማቋረጥ በትጋት ከተጠና ውጤታማ የማይሆንበት መንገድ እንደሌለ ጠቁማለች።
በተጨማሪም ለራሳችን መስራት እንደምንችል እና ያለንን አቅም በማመን እና በራስ የመተማመን ስሜት ማጥናቷ ለውጤቱ መመዝገብ መሰረት እንደሆናት ተናግራለች።
በተቻላት አቅም ያልገቧትን ጥያቄዎች በመጠየቅ፣ የክፍል ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ እና አስተማሪዎች ጥያቄዎችን ሲጠይቁ በንቃት እንደምትሳተፍ የምትናገረው ተማሪ ኤፍራታ፣ አብዛኛውን የትምህርቷን ርዕስ በክፍል ውስጥ አጠናቅቃ እንደምትወጣ ገልጻለች።
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ውጤት ይፋ ተደርጓል።
ተማሪዎች https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Remedial Examination ከሚለው ስር View Results የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ " ሙሉ ውጤታችን Disqualified ተደርጓል " ያሉ በርካታ ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅርበዋል።
ተማሪዎቹ " ይፋ በተደረገው የፈተና ውጤት ላይ የገጠመን ከፍተኛ ችግር እንዲሰማልን እንፈልጋለን " ብለዋል።
ቅሬታቸውን ካቀረቡት መካከል በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳንይንስ ተማሪዎች ውጤታቸው " ሙሉ በሙሉ Disqualified " የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ፥ በደብረ ብርሃን፣ ወሎ፣ አርባ ምንጭ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ሰመራ፣ ባህርዳር፣ ወልቂጤ፣ ኦዳ ቡልቱም፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የተለያዩ ተማሪዎች ውጤት ላይ ተመሳሳይ ችግር እንደገጠማቸው አመልክተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ቅሬታቸውን ተመልክቶ ምክንያቱን በመለየትና በማሳወቅ እንዲሁም በመመርመር አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና 53,620 ተፈታኞች መውሰዳቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
Repost from AAU-Official
ከ2019 ዓ.ም ቅድመ ምረቃ ትምህርት ማመልከቻ ጋር በተያያዝ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ
1. ለ አጠቃላይ የቅድመ ምረቃ ማመልከቻ
2. ለቅድመ ምረቃ ለቀን መደበኛ መርሃ ግብር ትምህርት አመልካቾች:
3. ለቅድመ ምረቃ ለማታ ተከታታይ መርሃ ግብር ትምህርት አመልካቾች፡
4. ለ ልዩ ፕሬዝዴንሻል የስኮላርሺፕ የትምህርት እድል፤
5. ለ ልዩ የስኮላርሺፕ እድል ለመምህራን ትምህርት፡
ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ ገጽ እና ቴሌግራም ቻናሎች እንድትጠቀሙ እናሳውቃለን፡፡
· ድረ-ገጽ፡ https://www.aau.edu.et/
· ቴሌግራም ቻናሎች፡ https://t.me/aau_official ወይም https://t.me/aauGAT
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
Repost from AAU-Official
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የምዝገባ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ ምረቃ መደበኛ (በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሃ-ግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል።
በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከዚህ በታች በተጠቀሱት ቀናት እና መስፈርቶች መሠረት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
አስፈላጊ መስፈርቶች እና ቀናት
* የምዝገባ ቀን፡ ከነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ።
* መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡
* በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ
* የመግቢያ ፈተና (UAT) የሚሰጥበት ቀናት ከጳጉሜን 02 እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ም
* ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ:- https://admission.aau.edu.et
