cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Addis Ababa Education Bureau

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Show more
Advertising posts
106 055Subscribers
-2424 hours
-1537 days
-32130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ውቧ አዲስ አበባ (ቀን ሚያዚያ 10/ 2016 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/ You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- [email protected] Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Show all...
ማዕከሉ ተማሪዎቻችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ ታስቦ በከፍተኛ በጀት እንደመቋቋሙ ትምህርት ቤቱ አመራር ተገቢውን የክትትል ስራ እንደሚሰራ ርዕሰ መምህሩ አቶ ካሳዬ ጫላ አስረድተዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/ You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- [email protected] Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Show all...
በፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገነባው የኢ-ስኩል ማዕከል ተመረቀ። (ቀን ሚያዚያ 10/ 2016 ዓ.ም) ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቭለፕመንት የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ካደረገው ፔስታሎዚ የህጻናት መርጃ ድርጅት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስገነባውን የኢ-ስኩል ማዕከል አስመረቀ። በማዕከሉ ግምታቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮች፣ ጠረጴዛዎችና ወንበሮችን ጨምሮ ሄድ ፎኖች የሚገኙ ሲሆን ማዕከሉ ትምህርት ቤቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትምህርት አገልግሎት በመስጠት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እንዲችል የሚያግዝ መሆኑን በኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቭለፕመንት የፕሮጀክቱ ማኔጀር አቶ ደመላሽ አድማሱ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቭለፕመንት ስራ አስካሄጅ ወይዘሮ ሀረገወይን አሸናፊ ድርጅታቸው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 12 ትምህርት ቤቶች ትምህርትን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የገንዘብ ድጋፍ ላደረገው ድርጅትና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል። የፔስታሎዚ የህጻናት መርጃ ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አበበ ደምሴ በበኩላቸው ማዕከሉ የሚፈለገውን አገልግልት መስጠት እንዲችል የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ድርጅታቸው በትምህርት ቤቱ በመገኘት ክትትል የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
Show all...
Show all...
👍 7 1
በትምህርት ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ላይ ኦረንቴሽን ተሰጠ:: ( ቀን ሚያዚያ 10/ 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ለማሻሻል በተደረገ ጥናት አላማ ፈፃሚ ባለሞያዎችን በተሻሻለው የአደረጃጀት መሰረት ስራዎች እንዲሰሩ የሚያስችል ሰነድ ላይ ለሚመለከታቸው አካላት ኦረንቴሽን ሰጥቷል :: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ይህ አዲስ አደረጃጀት መፈጠሩ ለትምህርት ጥራትና ውጤታማ ትውልድ ከማፍራት አንፃር ቢሮው እያደረገ ላለው ጥረት ከፍ ያለ ሚና እንደሚኖረው አብራርተው የቀረበው ሰነድ ላይ ግንዛቤ ፈጥረን በመመሪያው መሰረት ጥናቱን በተግባር ላይ በማዋል የትምህርት ሥርዓቱ ብቃት ባለው አላማ ፈፃሚ ባለሙያ እንዲመራና የትምህርት ሥርዓቱን ውጤታማ ማድረግ ያስችላል ብለዋል :: የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ አሰፋ የትምህርት ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ሰነድ ለውይይት አቅርበው ለተነሱ የግልፅነት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል ። በውይይቱ በሁሉም ክፍለከተሞች የሚገኙ ትምህርት ፅ/ቤት አስተባባሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል::
Show all...
👍 12 2
Show all...
Addis Ababa Education Bureau | WhatsApp Channel

የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን ስልጠና ሰጠ :: (ቀን ሚያዚያ 10/ 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የመንግስት ንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጠ :: የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ ሲሳይ አበራ በስልጠናው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር ሠራተኞች ለስራ ማስኬጃ የሚሆኑ የመንግስት ንብረቶችን በአግባቡና ለታለመለት አላማ እንዲውል ለማስቻል ሰራተኛው በንብረት አስተዳደር ላይ በቂ ግንዛቤ ማግኘት አለበት ብለዋል :: አቶ ሲሳይ አያይዘውም ስልጠናው የቋሚ ንብረትን በአብዛኛው ጊዜ የሚያስተዳድሩ የቢሮ ፀሐፊዎች  ቋሚ ንብረትን በምን መልኩ ማስተዳደርና ለተገቢው አላማ ማዋል እንደሚገባቸው እንዲሁም ሾፌሮች የተሽከርካሪ ነዳጅ በኖርሙ መሰረት እንዲጠቀሙና መኪናዎች የጥገና ጊዜያቸውን ሳያሳልፉ ለፍተሻ መቅረብ እንዲችሉ ግንዛቤ ያገኛሉ ብለዋል:: ስልጠናው ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጥናትና መረጃ ትንተና ቡድን መሪ አቶ ኪዳኑ ፈለቀ አማካኝነት የመንግስት ንብረት አስተዳደር ፣ የቋሚ ንብረት አስተዳደር ሥርዓት ፣ የተሽከርካሪ ስምሪትና አጠቃቀም እና የስቶክ አስተዳደር ላይ ያተኮሩ የሕግ ማዕቀፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ተሰጥቷል :: በስልጠናው የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ሠራተኞች ፣ የሚመለከታቸው የግዥ ፣ ፋይናንስና ውስጥ አዲት ሰራተኞች እንዲሁም የቢሮው ፀሐፊዎች እንደሚሳተፉ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::
Show all...
👍 8
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመካሄድ ላይ የሚገኘው የተማሪዎችና መምህራን ስፖርታዊ ውድድር በ5   የስፖርት አይነቶች የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው በየክፍለ ከተማው አሸናፊ የሆኑ ትምህርት ቤቶች በከተማ ደረጃ በሚካሄደው ተመሳሳይ ውድድር ተ ሳታፊ እንደሚሆኑ በመጠቆም ቢሯቸው ውድድሩ በድምቀት እንዲካሄድ ከወዲሁ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በተያያዘ በመጪው ቅዳሜ ሚያዝያ 12//2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት በሚጀመረው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርት ውድድር መክፈቻ መርሀ ግብር ተማሪዎችን ጨምሮ የትምህርት ማህበረሰቡ ተገኝቶ የመክፈቻ ፕሮግራሙ ድምቀት እንዲሆን ከወዲሁ የተለያዩ የንቅናቄ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ገልጸዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et  Email;- [email protected]     Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Show all...
👍 8
ከተማ አቀፉን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎችና መምህራን ስፖርታዊ ውድድር በአግባቡ ለማካሄድ እየተከናወኑ በሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ። (ቀን ሚያዚያ 10/ 2016 ዓ.ም)በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉን ጨምሮ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት፣የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት እና ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ ስፖርታዊ ውድድሩን ለማካሄድ እየተከናወኑ የሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻልም ሆነ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው በክፍለ ከተማ ደረጃ በሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመካሄድ ላይ የሚገኘው ውድድር ሲጠናቀቅ በከተማ ደረጃ ውድድሩ በድምቀት የሚካሄድ መሆኑን በመግለጽ ለመርሀ ግብሩ ስኬታማነት ከወዲሁ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
Show all...
👍 5
Show all...
👍 13 5