en
Feedback
ቶጳዝዮን

ቶጳዝዮን

Open in Telegram

"ቶጳዝዮን"ማለት ቢጫ የከበረ ድንጋይ ፣ዕንቍ ማለት ነው። በተስፋ የተቃኘዉን ሀሳባችንን እና ስሜቶቻችንን በዕንቊ ቃላቶች እያዋዛን በብዕራችን የምንገልፅበት ምርጥ ቻናል ነው። ለማንኛውም አስተያየት👇👇 @Ediwub @Tirrubel

Show more
3 582
Subscribers
+124 hours
+77 days
+5730 days

Data loading in progress...

Attracting Subscribers
September '26
September '26
+24
in 2 channels
August '26
+154
in 9 channels
Get PRO
July '26
+160
in 10 channels
Get PRO
June '26
+170
in 10 channels
Get PRO
May '26
+149
in 10 channels
Get PRO
April '26
+161
in 13 channels
Get PRO
March '26
+169
in 8 channels
Get PRO
February '26
+181
in 8 channels
Get PRO
January '26
+144
in 9 channels
Get PRO
December '25
+155
in 11 channels
Get PRO
November '25
+88
in 8 channels
Get PRO
October '25
+99
in 10 channels
Get PRO
September '25
+86
in 8 channels
Get PRO
August '25
+150
in 18 channels
Get PRO
July '25
+232
in 19 channels
Get PRO
June '25
+154
in 10 channels
Get PRO
May '25
+222
in 11 channels
Get PRO
April '25
+197
in 10 channels
Get PRO
March '25
+166
in 12 channels
Get PRO
February '25
+110
in 13 channels
Get PRO
January '25
+174
in 8 channels
Get PRO
December '24
+175
in 7 channels
Get PRO
November '24
+280
in 14 channels
Get PRO
October '24
+159
in 8 channels
Get PRO
September '24
+322
in 8 channels
Get PRO
August '24
+303
in 9 channels
Get PRO
July '24
+146
in 10 channels
Get PRO
June '24
+156
in 12 channels
Get PRO
May '24
+85
in 7 channels
Get PRO
April '24
+69
in 4 channels
Get PRO
March '24
+92
in 3 channels
Get PRO
February '24
+61
in 6 channels
Get PRO
January '24
+33
in 5 channels
Get PRO
December '23
+47
in 3 channels
Get PRO
November '23
+82
in 4 channels
Get PRO
October '23
+54
in 4 channels
Get PRO
September '23
+64
in 0 channels
Get PRO
August '23
+38
in 0 channels
Get PRO
July '23
+18
in 0 channels
Get PRO
June '23
+20
in 0 channels
Get PRO
May '23
+17
in 0 channels
Get PRO
April '23
+28
in 0 channels
Get PRO
March '23
+21
in 0 channels
Get PRO
February '23
+36
in 0 channels
Get PRO
January '23
+66
in 0 channels
Get PRO
December '22
+79
in 0 channels
Get PRO
November '22
+53
in 0 channels
Get PRO
October '22
+21
in 0 channels
Get PRO
September '22
+10
in 0 channels
Get PRO
August '22
+4
in 0 channels
Get PRO
July '22
+12
in 0 channels
Get PRO
June '22
+8
in 0 channels
Get PRO
May '22
+10
in 0 channels
Get PRO
April '22
+8
in 0 channels
Get PRO
March '22
+7
in 0 channels
Get PRO
February '22
+22
in 0 channels
Get PRO
January '22
+31
in 0 channels
Get PRO
December '21
+56
in 0 channels
Get PRO
November '21
+6
in 0 channels
Get PRO
October '21
+8
in 0 channels
Get PRO
September '21
+205
in 0 channels
Date
Subscriber Growth
Mentions
Channels
06 September0
05 September+6
04 September0
03 September+8
02 September+6
01 September+4
Channel Posts
..........ዛሬ ጷግሜ አንድ ነዉ።ወቅቱ የአዲስ አመት መግቢያ እንደመሆኑ....... ሰዉ በለሊት ተነስቶ የጷግሜን ጠበል ከተጠበለ በኋላ አዲስ ተስፋን ሰንቆ በየፊናዉ በዓሉን ተደስቶ ለማክበር ይሯሯጣል። ገሚሱ ሰንጋተራ፤ ገሚሱ በግተራ የተቀረዉ ሰዉ ደግሞ ሾላ ገበያ ከትሟል። ታዲያ በእኛ ጊቢ ከግንቦት ልደታ ባልተናነሰ መልኩ ጷግሜ አንድ በደመቀ መልኩ ይከበራል። በተለምዶ አሮጌ ልደታ ተብሎ ይጠራል።ጎረቤት አንድ ላይ ተሰብስቦ በረንዳ ላይ ቡና ይፈላል።አናባበሮዉ እና ንፍሮዉ ይቀርባል። ጋሽ ተስፋዬ የሰባ አመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸዉ።ባለቤታቸዉ ወይዘሮ ሸዋዬ የአንገታቸዉ ንቅሳት ከሩቅ የሚታይ ዉበታቸዉ የማይደበዝዝ ድርብብ ያሉ እመቤት ናቸዉ።  ቡናዉ ካከተመ በኋላ ጋሽ ተስፋዬ የያዙትን ስኒ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠዉ ከመቀመጫቸዉ ተነስተዉ ጋቢያቸዉን አስተካክለዉ ሊመርቁን ቆሙ። ሁላችንም እጃችንን አሜን ለማለት አመቻችተን ቆም ቆም አልን። "የጎመን ምንቸት ይዉጣ።የገንፎ ምንቸት ይግባ።" "አሜን..........." "ሀገራችንን ዳሯን እሳት መሐሏን ገነት ያድርግልን።በዳር ድንበር በጦርነት  ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉትን ወደቤታቸዉ ያግባልን።ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።" "አሜን............." ለዛሬ መድረስ ያልቻሉትን፣በሞት ከእኛ የተለዩትን፤ ወዳጅ ዘመዶቻችንን  ነፍሳቸዉን ይማርልን። "አሜን............." ገበሬዉም ያረሰዉን የሚሰበስብበት የድካሙን ፍሬ የሚበላበት ያርግልን። "አሜን.........." ያላጨ የሚያጭበት፤ ያገባም የሚወልድበት፤ የወለደም የልጆቹን ወግ ማዕረግ የሚያይበት ዓመት ያድርግልን።" ለአዲሱ ዓመት በሰላም እንዳሁኑ ከቁጥሩ ሳያጎድል ያድርሰን።አይለየን!" "አሜን "በሉ ወዳጆቼ እኔ ባጎደልኩ እርሱ ይሙላበት።"ብለዉ ከወንበራቸው ላይ ተቀመጡ። ከአሜን ይቀራልና አሜን በሉ........... በዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn

2
መቃብር ምሰው አፈር አልብሰው ደረት ደልቀው ፍም ዕንባ አፍስሰው ደህና ሁን ብለው የመጡትን ሰው፤ ድንገት በር ላይ ጥላውን ቢያዩት - ድምፁን ቢሰሙት ፤ ምንድን ነው ሚሉት!? ጨርቁን አጣጥፈው ስንቁን አጥቅሰው አንገቱን አቅፈው ደረቱን ዳብሰው ከእንግዲህስ ቻው ያሉትን ፍቅር - ከልብ ቆርጠው የሸኙትን ሰው፤ ድንገት አልጋ ላይ ጋደም ብሎ ፤ እጅ እግሩን ሰቅሎ -  ሀሳቡን ጥሎ ሲስቅ ቢያገኙት፤ ምንድን ነው ሚሉት!? ይኸው እንግዲህ ዳግም ብቅ አለ ብቸኝነቴ፤ ቻው ተባብለን ከአንዴም ሁለቴ፤ ለካስ እንደ ልጅ አዲስ እንግዳ ከቤት ሲመጣ 'ጓዳ ሩጦ እንደሚገባው፤ እንግዳው ሂዶ እስከሚወጣ እያጮለቀ እንደሚያደባው፤ ይህ ብቸኝነት አይሄድም ጥሎ፤ ያደፍጣል እንጅ የሞተ መስሎ፤ By Tewodros kasa @topazionnn @topazionnn
280
3
ሰላም እንዴት ናቹ ✨ በመጀመሪያ ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን🙏 እናም ውድ ቤተሰቦች የራሴን ትንሽዬ የ T-Shirt Brand ጀምሪያለሁ " ሙሉወርቅ | Muluwerk Designs "😊 . እና+4
ሰላም እንዴት ናቹ ✨ በመጀመሪያ ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን🙏 እናም ውድ ቤተሰቦች የራሴን ትንሽዬ የ T-Shirt Brand ጀምሪያለሁ " ሙሉወርቅ | Muluwerk Designs "😊 . እና Channel ከፍቻለሁ ገባ ገባ እያላቹ ቤቴን መርቁ ORDER ማድረግ የምትፈልጉም ORDER አድርጉ ምትፈልጉት ሁሉ አለን CUSTOM ORDERም እንቀበላለን ✨ . ቤቴን መርቁ ጅማሬዬንም ፍፃሜንም አምላክ ይባርክ🙏 THIS IS THE CHANNEL : @muluwerkdesigns
307
4
ማዘን ሲገባኝ ፥ ስትጠፊ ካይኔ መጻፍ ሲገባኝ ፥ ሙሾ ወይ ቅኔ (እንጃልኝ እኔ ...) የጤና አይመስልም ፥ ደህና መሆኔ ። ትዝ አትዪኝም ወይ ለትንሽ ደቂቃ ? አትናፍቂኝም ወይ ሳዳምጥ ሙዚቃ ? ረሳሁሽ በቃ ? እንጃልኝ እንጃልኝ ናፍቆትሽ በኋላ ምን እንዳሰበልኝ ። ሰው ባይገባው እንጂ አዕምሮው ደንዘዞ እንዴት 'እፎይ' ይላል  ስንት ኮተት ይዞ ? እባክሽ አታዘግዪብኝ ፥ ስቃዬን ዛሬ ልወጣው አንቺስ ሄደሻል እሺ ናፍቆትሽ መች ነው ሚመጣው ? By Hab HD @topazionnn @topazionnn
533
5
. . .ናቅን መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን . . . ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
568
6
@ediwub @topazionnn @topazionnn
@ediwub @topazionnn @topazionnn
3 995
7
Check Out👇👇👇 https://vt.tiktok.com/ZSVWFjECK/
252
8
https://vt.tiktok.com/ZSVpRCwQo/
241
9
ጉድ እኮ ነው! በዘመን መሰልጠን በዝቶ ሽግግሩ ስፍራ ተዘጋጅቶ በሰው እያጠሩ ለአጉል ትግያ ሀገሬው ተምሞ በመቶ ሺ ያሲዛል እዚ ወገን ታሞ! @weyblann
1 001
10
፨፨፨፨፨ እሞታለሁኝ አይቀራትም ደርቄ አልቀርም እንደ በጋ፤ ግና ሳላሽት ፈቀቅ የለም ጓጉተው ሳይወስዱኝ ከማድጋ። .. ስማር ኖሪያለው ስንት አመታት ከሞት ተናንቆ ድል ማድረግን፡ እንኳን ለአንዱ ለሺህ አልሳሳም እያነባሁኝ አልምትም ግን!። #mikiyas_feyisa @topazionnn
255
11
No text...
1 115
12
የ ፯ ዓመት ስለት ፀሐፊ እና አንባቢ፦ ዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
4 826
13
ምንድነው ፍላጎትህ/ሽ ? ለነገሩ ምንም ቢሆን Don't worry .... ግጥም ...... ድርሰት ........ አዝናኝ ወግ...... አጫጭር የፍቅር ታሪክ...... ወይስ ገራሚ ጥቅስ.... የፈለጋችሁበትን አማርጣችሁ ምታገኙበት ድንቅ Channel ጀባ ልበላችሁ..... በደራሲ @sirius_black1212 የተፃፉ ውብ የ ብዕር አርማዎች እለት በእለት እሚታተምበት ምርጥ Channel ተቀላቀሉ አትፀፀቱም! Join us https://t.me/yebier_arbegna
205
14
ደብረ ታቦር . . ብርሃነ መለኮት ከተገለፀበት፤ መልኩ ተለዉጦ ፀዳል በሆነበት፤ አብም ስለ ልጁ እርሱን ስሙት ብሎ ከመሰከረበት፤ የጌታ አምላክነት የሥላሴ ምስጢር ከተሰበከበት፤ ልብን ከሚመስጥ ከዚህ
ደብረ ታቦር . . ብርሃነ መለኮት ከተገለፀበት፤ መልኩ ተለዉጦ ፀዳል በሆነበት፤ አብም ስለ ልጁ እርሱን ስሙት ብሎ ከመሰከረበት፤ የጌታ አምላክነት የሥላሴ ምስጢር ከተሰበከበት፤ ልብን ከሚመስጥ ከዚህ ድንቅ ስፍራ፤ መንፈስ ከሚያድስ ከታቦር ተራራ፤ በዚህ መኖር ለእኛ ....... እጅጉን መልካም ነዉ ከጌታችን ጋራ። እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ። ........................................................ በዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
5 734
15
እስቲ የቡሄ ትዝታችሁን አጋሩን እንኳን አደረሳችሁ።
250
16
ይህ ህይወት.... ለእናቴ ሆነ እንጂ ሰርክ የሚያስተክዘኝ፣ * እንደ ሀምሌ ጭጋግ የሚያደበዝዘኝ፣ * በንቃት አለም ውስጥ ሁሌ የሚያፈዘኝ.... * ለራሴስ ያልኩ 'ለት ማንም ነው ማይዘኝ! @Weybl
ይህ ህይወት.... ለእናቴ ሆነ እንጂ ሰርክ የሚያስተክዘኝ፣ * እንደ ሀምሌ ጭጋግ የሚያደበዝዘኝ፣ * በንቃት አለም ውስጥ ሁሌ የሚያፈዘኝ.... * ለራሴስ ያልኩ 'ለት ማንም ነው ማይዘኝ! @Weyblann ያቡ✍
5 868
17
🗒 . . ላይድን ቁስል፤ ጨዉ መነስነስ፤ ከድንጋይ ላይ፤ ዉሃ ማፍሰስ ፤ ለሟች ዘመድ ፤ ዳግም ማልቀስ፤ መኖር ካሉት፤ እንደዚህ ነው፤ ሳቅን ትቶ፤ መንሰቅሰቅ ነው። 🖊ዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
1 945
18
መውደዴን ለንፋስ ነግሬው - ይዞብኝ ሄደ መልክሽን በብራና ስዬው -  ተቀደደ ስስቴን ባሰፍረለት ለባህር ሳቀብኝ እንደክፉ መምህር ስላንቺ ሚሰማኝን ለሰማይ ብነግረው አመቱን በሙሉ - ክረምት አደረገው በነፍሴ ያመላለስኩት በአጥንቴ የታመምኩት ለሳር ለቅጠሉ ብለፍፍ ተቆጠረ እንደሴተኛ አዳሪ እድፍ! አየሽ ! ለዚህ ነው የምጎዳው - ለዚ ነው ምትጎጂው ለማይሰማኝ ነውና የማወራው ለማይሰማሽ ነውና የምታስረጂው! እወቁልን አያሻንም  ይቅር አንታይ ከጫፍ ጫፍ ብንታመም ዝም እንበል እንደሚጠረብ ዛፍ አንዳንድ ልክ አለ ቢነገረም የማይጠቅም - ቃልን ዝምታ ያሳከለ አንዳንድ እውነት አለ አንዳንድ ህመም አለ  - ብንለፋ ብንጥር እያነሰ ሚሄድ  ባስረዳነው ቁጥር! ኤልያስ ሽታኹን @topazionnn
1 994
19
No text...
1 288
20
የምትመለከቱዋት ወጣት ታዳጊ ኤልሮኢ ቅዱስ ትባላለች በአጥንት ካንሰርን ህክምና ላይ ትገኛለች በሽታው ከታወቀ አንድ አመት ሆኗታል በበሽታው ምክንያትም አንድ እጇ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል ሆኖም+2
የምትመለከቱዋት ወጣት ታዳጊ ኤልሮኢ ቅዱስ ትባላለች በአጥንት ካንሰርን ህክምና ላይ ትገኛለች  በሽታው ከታወቀ አንድ አመት ሆኗታል በበሽታው ምክንያትም አንድ እጇ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል  ሆኖም ግን ኤልሮኢ ተስፋ ሳትቆርጥ ህክምናዋን እየተከታተለች ነው  አሁን ግን በሽታው ወደ ሳንባዋ በመሠራጨቱ የመተንፈስ ችግር ስላጋጠማት በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ Heal Venture Medical and Surgical Center በ ICU ትገኛለች ሆኖም ግን በአሁን ሰአት ላይ የሆስፒታሉ ወጪ በቀን ከ50.000ብር ነው ከቤተሰብ አቅም በላይ ስለሆነ የኛን እርዳታ ትሻለች CBE - 1000487578828 TeleBirr - 0911179293 Awash Bank - 013471629151800 ሁሉም አካውንት ስም - Rahel Aregay እህታችን ትፈልገናለች እንድረስላት 🙏
1 866