📢📢 ጮክ ብለህ አንብበው 🎤🎤
👉 የት ነህ? ምን እየሰራህ ነው? ምን ገጠመህ? ምንድነው ነው ጭንቅላትህ የተቆጣጠረው? እነማን ምን አሉህ? ከማን ምን አጣህ? ምንስ ነው ልብህን ያደማው?
🖐🖐🖐🖐🖐 በቃ አሁን ካለህበት ሁሉ ጥያቄ ውስጥ ሆነህ ስማኝ። 😄የተወደድክ ምርጥ ዘር፣ 😆ትንሹ የፍሬ ዛፍ፣ 😄ህልመኛው የሀገር ተስፋ፣
🦵ወድቀሃል? ተነሳ። የወደቀ ይነሳል ለዛውም መውደቁን በመቆም እንዲተካ በሚረዳ ፀጋ እየተረዳ።
✍️✍️ "ሰባት ጊዜ የወደቀ ሰባት ጊዜ ይነሳል።" ልክ እንደ ቃሉ። 👉
#እኔም_ደግሜ_እልሃለው። ሰባት ጊዜ ከወደክ
#ስምንት ጊዜ ተነሳ። መነሳት እንጂ መውደቅ አይከብድምና መነሳ ከበደኝ ብለህ አትተወው።
👍ከወደክበት ለመነሳት ከእጅህ እና ከእግርህ በላይ በልብህ
#ቅዱሱን_መንፈስ የተሸለምክ
#የእግዜአብሔር_ፀጋ የበዛልህ ትውልድ መሆንህን አስብ።
👉ስተሃል? ደክሞሃል? አይዞኝ ወንድም አለም። አሁንም ጊዜ አለ።
#ገና_ነው_አልመሸም። የሳተ ይመለሳል። ተመለስ። እንዴት? አቅቶኝ እኮ ነው አትበል❗️
🧣መሳትህ የሚያሳሳው መጥፋትህ የሚያንገበግበው
#አባት አለህ።
#አባ ብለህ ጩህ እመነኝ እሱ
#ዘንበል ይልልሃል።
ስማኝ 📢📢
👂አንተን ለመጣል የተወረወረውን ድንጋይ ራስህን ገንባበት። የጣሉህ እስኪያነሱህ፣ የሰደቡህ እስኪመርቁህ፣ መሳትህን የሚያውቁ እስኪመልሱህ
#አትጠብቅ።
#ይልቅ📌ሲጠሩት አቤት ለሚለው፤ ሲሰጥሙ እጃቸውን የዘረጉለትን እጁን ልኮ ለሚታደገው፤ ንገረው። ንገረው። እመነኝ እሱ
#እጁን_ሰዶ ይታደግሃል።
😭😭እያለቀስክ ነው? ነገሮች ተዘጋግተውብሃል? አንተ የአባቴ ብሩክ ከአይንህ ላይ እንባህ አብስ።
😁አንተ ለራስህ ከምታስበው በላይ፤ ከከበቡህ አዳማቂዎች በላይ
#ከነ_ገበናህ የሚወድህና የሚሳሳልህ አባት አለህ። ከሚያስፈልግህ ማያጎድልብህ ከሚስፈልግህ ማያስቀርበህ ከሞትህ ውስጥ ህይወትን ሊያወጣ የሚቻለው
#አባት አለህ።
😂😂የደስታህ ጊዜ
#ሁልጊዜ ይሆን ዘንድ የታወጀልህ፤ የደስታህ ምንጭ ክርስቶስ ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መርገምህን በመስቀል፤
#ተፈፀመ ብሎ አድራሻህን በትንሳኤው ጉልበት በዘላለማዊው የእረፍት ስፍራ ያደረገልህ
የእግዚአብሔር ወራሽ የአዲስ ኪዳን ፍሬ ነህ።
🤣🤣🤣🤣🤣😂😂😂
ይህ ደግሞ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ሳቅን ይጭራል። ከልብ የእውነት ያስፈነድቃል። ሳቅ። 😂😂😂😂😂 ለዛውም ከሁኔታዎች በላይ የሆነ ሳቅ። ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበልህ።😂😂😂😂
#ልብ_በል።
የገጠመህን ሁሉ ለመልካም መንዝረው። በዚህ ዓለም ለዓለም ዕንቆቅልሽ የሆኑና አበቃላቸው ሲባሉ የሚቀጥሉት ሁሉ፥
👉ከስድብ ውስጥ ምርቃት
👉ከምርቃት ውስጥ ምክር
👉ከምክር ውስጥ መራመድን የሚወልዱ
ናቸው።
አዕምሮህ በተመላለሱ አሳቦች ተወጥሮ በቃ ሁሉም አከተም እስክትል ወዳጅ መሳይ ሸንጋዮች ረብ የለሽ አሳቦችን ያቀበሉህ ውድቀትህን ሊዘግቡ ደጅ አፍህ ላይ ተቀምጠው ይሆናል።
እመነኝ አይሳካላቸውም።
👍👍አንተ እኮ ስብርባሪም ላይ ሆነህም ቢሆን የምትሻገር፣ እንደ ወጣህ መንገድ ላይ የማትቀር፣ መንገድህ በዘይት የታጠበ፣ አብ በልጁ የባረከህ፣ የክርስቶስ ልብ የተሰጠህ ድንቅ ልጅ ነህ።
🙏🙏የት ነህ? ያለህበት ጠበበህ? አልተመቸህም? በቃ፤ በአለህበት ሆነህ
#የማይመስልን ነገር አስብ። አስብ። አስበህ አልሆነም ነበረ? ግዴለም አሁንም አስብ። የልብ መዘጋጀት ከሰው የምላስ መልስ ደግሞ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነውና አሁንም አስብ። በአንተ ያለ አንድ ፍሬ
#ነገ_ዛፍ ይሆናል። ማድረግና ማከናወኑን ለአባትህ ተውለት። እመነኝ ድምዳሜህ የሳቅ የደስታ ይሆናል፤ በጌታ። ሁሉም በጌታ።
👉በተመሳሳይ መንገድ እየሄድክ መንገዱን ሳትቀይር በረከትን፣ ከንውንንና ስኬትን ፍለጋ ሳትባክን ከታመንከው የዘላለም አባት ዘንድ ያ
#ጥቂቱ ከተባረከ
#ትጋት ጋራ ይበዛልሃል።
🙏🙏እመነኝ ወንድም ዓለም
#ሁሉን_በሚችለው #በክርስቶስ_ሁሉን ትችላለህ። 💯ፀጋው ሁሉን በልኩ ያቀናጀዋል።
🤜🤛🤜🤛🤜🤛🤜🤛🤜🤛🤜🤛🤜🤛
ጠፋ ሲሉህ የምትበዛ
አከተመለት ሲሉ የምታብብ
በሚናወጥ ማዕበል
ፅናት የሚያበራ
የነደፈህ ዕፉኝት የማይገድልህ፤
አራግፈህ የምትቀጥል 👇👇
በሰማይ ቤት ያለህ
የተወደድክ
#ምርጥ_ዘር_ነህ።
[ አንተ ጎበዝ ይልሃለሁ ተነሣ ]
( ሉቃ 7፡14)
Join & Share 👇👇
✓
@lightoflamb ✓
✓
@lightoflamb ✓
Show more ...