en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Open in Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
912
Subscribers
-224 hours
-127 days
+5130 days
Posts Archive
የፍቅር ስቃይ.....! በኡስታዝ አቡ ሱፍያን አላህ ይጠብቀው! ስለ ቀልባችን☑️ ➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1

ሐዘን ልብን ያደክማል፤ የሰውን ልጅ ጽናትና ብርታት ያላላል ታላቁ ዓሊም የኢማም ኢብኑል ቀይም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "ያለፉ አሳዛኝ ትውስታዎችን ደጋግማችሁ ወደ ራሳችሁ አትጥሩ!" ሐዘን
ሐዘን ልብን ያደክማል፤ የሰውን ልጅ ጽናትና ብርታት ያላላል ታላቁ ዓሊም የኢማም ኢብኑል ቀይም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "ያለፉ አሳዛኝ ትውስታዎችን ደጋግማችሁ ወደ ራሳችሁ አትጥሩ!" ሐዘን ልብን ያደክማል፤ የሰውን ልጅ ጽናትና ብርታት ያላላል፤ እንዲሁም ጠንካራ የመሥራት ፍላጎትንና ውሳኔን (ኢራዳን) ይጎዳል። ለአማኝ ባሪያ ከሐዘንና ከተስፋ መቁረጥ ይበልጥ በሰይጣን ዘንድ የሚወደድ (የሚያስደስት) ምንም ዓይነት ነገር የለም። ምክንያቱም ሰይጣን አማኝን በሐዘን ሰንሰለት አስሮ ከጌታው መንገድና ከሕይወት ብርሃን ሊያርቀው ይፈልጋልና። ስለዚህ ወዳጄ ! ያለፈውን አሳዛኝ ታሪክህን እየቆሰቆስክ ዛሬህን አታጨልም። ሐዘን የሰይጣን ትልቁ መሣሪያ መሆኑን አውቀህ፤ ልብህን በጌታህ እዝነትና በተስፋ ብርሃን አስውበው። ጌታችን አላህ ከሐዘን፣ ከጭንቀትና ከሰይጣን ወስዋስ ይጠብቅን። https://t.me/Asselefiyah_Channel

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። የጀነት በር ጠባቂ መላዒካ ረድዋን  ይባላል፡፡

⚠️አስቸኳይ የነፍስ አድን ጥሪ 👉ያአህባብ እዪልኝ ይሄን በጭፈራ ላይ የተመሠረተ አምልኮ የልዕለ ሀያሉ ጌታችንን አላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ እንደት እንደተዳፈሩት እያያችሁ ነዉ የመኪና ብዛት  የህዝብ ስብስብ  ዶሪህ ለመለመን ችግራቸዉን ለጅን አቤቱታ የሚያቀርቡ  ከሙስሊሙ የወጡ ሰዎች ባሻገር ክሪስቲያኖች ጭምር ለአላህ በመናገር ፋንታ ግን እነሱ ምንም ለማያደርግላቸዉ ዶሪህ ተናግረዉ ይሄዳሉ በአመቱ ተመልሰዉ መተዉ ስለታቸዉን ለጅን ያርዳሉ!! የቦረናው ሸህዬ  የቦረናው ደግዬ እርዱን አባብዬ ይህ የሽርክ ግጥም የሚዘመርባት ከተማ ከ500ሺ ህዝብ በላይ ሽርክን ለማንገስ ከአድስ አበባ እስከ ባሌ ከወለጋ እስከ ሐረር ከወሎ እስከ ጎጃም  ከጎንደር እስከ ሸዋ ሳይቀር ሰው ስለቱን ይዞ ኮርማውን እየነዳ ሽቱውን ገዝቶ መጋረጃ ሸምቶ ልክ እንደ ግሸን ማርያም ክብረ_በዓል መንገድ በአይሱዚና በቅጥቅጥ እንድሁም በህዝብ ብዛት ጥቅምት 15 የዶሪኋን ታቦት በማነገስ ከተማዋ ትጨናነቃለች ። በዚያ ሌሊት  የሚጎራ ጉሪያ የሚወገር ድቤ የሚጮህ ጩኸት የሚለቀስ ለቅሶ የሚጨስ አድሩስ የሚታረድ በግና ፍየል ምን ልበልህ ባጭሩ ራሷ ከተማዋ ታብዳለች ።   ለወንድም እህቶቼ ፦ ወንድም እህቶቼ፣ በየዓመቱ ብዙ ሰዎች ችግራቸውን ይዘው ወደ እዚህ  ቦታዎች ይጓዛሉ። ብዙዎቹ በሕመም፣ በችግርና በጭንቀት የተጎዱ ናቸው።
ስለምንወዳቸው ነው የምናስታውሳቸው፤ ከአላህ ውጭ ሌላ አያድናቸውም።
1️⃣ አላህ ቅርብ ነው وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ «ባሮቼ ስለ እኔ ቢጠይቁህ እኔ ቅርብ ነኝ፤ ለማኙ ሲለምነኝ ልመናውን እቀበላለሁ።»
ሱረቱል -በቀራህ  ምዕራፍ 2:አንቀፅ 186
وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ «ጌታችሁም አለ፦ ለምኑኝ፣ እመልስላችኋለሁ።»
ሱረቱል ጋፊር ምዕራፍ 40:አንቀፅ 60
አላህ ከእኛ ጋር አማላጅ ሳያስፈልገው ቅርብ ነው። በሌሊት፣ በሱጁድ፣ በየትኛውም ቦታ ልንለምነው እንችላለን። 2️⃣ ዱዓ ኢባዳ ነው «الدُّعَاءُ هُوَ الْعِبَادَةُ» «ዱዓ (ልመና) ኢባዳ (አምልኮ) ነው።»
📚ቲርሚዚ፣ አቡ ዳውድ ዘግበውበታል
ኢባዳ ደግሞ ለአላህ ብቻ ይገባል፦ وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا «መስጊዶች የአላህ ናቸው፤ ስለዚህ ከአላህ ጋር ማንንም አትለምኑ።»
ሱረቱል አል-ጂን ምዕራፍ 72:አንቀፅ 18)
«إِذَا سَأَلْتَ فَاسْأَلِ اللَّهَ، وَإِذَا اسْتَعَنْتَ فَاسْتَعِنْ بِاللَّهِ» «ከጠየቅህ አላህን ጠይቅ፤ ርዳታ ከፈለግህ በአላህ ተረዳ።»
📚ቲርሚዚ ዘግበውታል
3️⃣ ከአላህ ሌላ የሚለመኑት ሊጠቅሙ አይችሉም وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ ۝ إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا دُعَاءَكُمْ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም:: ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም:: ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም
ሱረቱል ፋጢር ምዕራፍ 35:አንቀፅ 13-14
ምንም ሊያደርጉልን የማይችሉትን መለመን ጊዜና ተስፋ ማባከን ነው። 4️⃣ ማረድ ለአላህ ብቻ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ ۝ لَا شَرِيكَ لَهُ «በል፦ ሶላቴ፣ እርዶቼ (ሥርዓተ አምልኮዬ)፣ ሕይወቴና ሞቴ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው። አጋር የለውም።»
ሱረቱል አል-አንዐም ምዕራፍ 6:አንቀፅ 162-163
«لَعَنَ اللَّهُ مَنْ ذَبَحَ لِغَيْرِ اللَّهِ» «ለአላህ ላልሆነ ያረደን አላህ ረግሟል።»
📚(ሙስሊም) ዘግበውታል
5️⃣ ሽርክ ከሁሉ የከበደ ሐጢአትነው إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ «አላህ በእሱ ላይ ማጋራትን አይምርም፤ ከዚያ ሌላውን ለሚሻው ይምራል።»
ሱረቱል   አን-ኒሳእ አን ምዕራፍ 4:አንቀፅ 48
ስለዚህ ነው የምናስጠነቅቀው፤ ስለምንጠላችሁ ሳይሆን ስለምንወዳችሁ። ወደ አላህ መመለስ (ተውበት) በር ግን ዛሬም ክፍት ነው። 6️⃣ ምን እናድርግ❓ 🤲 ችግራችሁን በሌሊት ተነስታችሁ በሱጁድ ለአላህ አቅርቡ። 🩺 ሕመም ካለ ወደ ሐኪም ሂዱ፤ ከሕክምና ጋር ሩቅያ ሸርዒያን (በቁርኣንና በነቢያዊ ዱዓዎች መታከምን) ተጠቀሙ። 💝 ሰደቃ ስጡ፤ ለችግረኛ መርዳት ችግርን ያቀልላል። 📖 ተውሒድን ከታመኑ ዑለማ ተማሩ። 🌿 ቤተሰብና ጎረቤትን በፍቅር፣ በትዕግስትና በግል አነጋግሩ። አላህ ሁላችንንም ከሽርክ ይጠብቀን፣ ችግር ውስጥ ያሉትንም አውጣቸው፣ ወደ ቀጥተኛው መንገድም ይምራን። አሚን። የቴሌግራም ቻናል t.me/yedeger_selefioch_jemea የቴሌግራም ግሩፕ t.me/yedeger_muslim_Wetatoch_jemea

ከወንጀሎች ቅጣቶች መካከል አንዱ፦ የእድሜን በረካ፣ የርዝቅን በረካ፣ የእውቀትን በረካ፣ የመልካም ተግባርን በረካ እና የዒባዳን በረካ የሚያጠፉ መሆናቸው ነው።ባጠቃላይ፣ የሃይማኖትንም ሆነ የዱንያን በረካ ያጠፋሉ።
ابن القيم | الداء والدواء
t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie

↩من أعظم النعم على المؤمن .. أن يهبه بصيرة يميّز بها الحق من الباطل والطيب من الخبيث والخير من الشر.
↩من أعظم النعم على المؤمن .. أن يهبه بصيرة يميّز بها الحق من الباطل والطيب من الخبيث والخير من الشر.

"ኸይር ከሰራችሁለት ሰው ሸር ይጠብቃችሁ።"

Repost from N/a
ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  ብዙ  የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ። የሱና ቻናል ያላቹ👉 @Quran_mylife1 ጥያቄ 1 💎ተዉሂድ በስንት ይከፈላል?

ከመካከላችን አንዱ የዱንያን ዕድሉን ወዲያው ሊያገኝ ይችላል፤ የሚያስደስተውን ሥራ፣ ስሙን ከፍ የሚያደርግበትን ደረጃ፣ ኑሮውን የሚያሰፋበትን ሀብት ሊያገኝ ይችላል። ከመካከላችን ደግሞ የሚገባን የሚመስሉን ዕድሎች ሁሉ እድሜ ልካችንን ሳያገኙን የሚያልፉብን ይኖራሉ። ሌላው ሲመኘው የነበረውን ነገር ሲያገኝ፣ ሰዎች ሲያመሰግኑትና ሲያደንቁት ያያል። እሱም ፈገግ ይላል፣ ነገር ግን በልቡ ውስጥ የሆነ ነገር ይቀራል። ዕድላችን የዘገየብን የሚመስለን እኛ ሆይ፣ የእኛ ድርሻ የጠፋ አይምሰለን።ምናልባት አላህ ካመለጡን ነገሮች ሁሉ የሚበልጥን ነገር ለእኛ አስቀምጦልን ይሆናል። ረሱልን صلى الله عليه وسلم በጀነት መገናኘት፣ ከወደድናቸው ሰዎች ጋር በሽታም ሆነ ሞት በሌለበት ዓለም አብሮ መኖር፣ ነፍስ ካወቀቻቸው ጸጋዎች ሁሉ በላይ በሆነ ጸጋ መሸለም ሊጠብቀን ይችላል። ከሰዎች መካከል ዕድላቸውን በዱንያ የሚያገኙ ይኖራሉ። ከአላህ ባሮች መካከል ግን አንዳንዶቹ ዕድላቸው ለዱንያ አይደለም፤ አላህ የዘገየውን ዕድላቸውን አስቀምጦላቸዋል።ለእነርሱ ጀነት እንጂ ሌላ አትመጥናቸውም። #ማስታወሻ

🇾🇪የመኖችን ለማታውቋቸው -------------------------- ሐጃጅ ኢብን ዩሱፍ አል-ሠቃፊ 🇾🇪 ስለ የመን ሕዝብ ምን ብለዋል⁉️ አል-ሐጃጅ ኢብን ዩሱፍ አል-ሠቃፊ ስለ የመን ሕዝብ የተ
🇾🇪የመኖችን ለማታውቋቸው -------------------------- ሐጃጅ ኢብን ዩሱፍ አል-ሠቃፊ 🇾🇪 ስለ የመን ሕዝብ ምን ብለዋል⁉️ አል-ሐጃጅ ኢብን ዩሱፍ አል-ሠቃፊ ስለ የመን ሕዝብ የተነገረው ታዋቂ አባባል #ወንድሙን #ሙሐመድ_ኢብን_ዩሱፍን የየመን🇾🇪 ገዥ አድርጎ ሲሾም ለእሱ የሰጠው አደራና ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ይህን ይላል‼️ ♦️#ታዋቂው #የሐጃጅ አባባል‼️ .....የመኖች🇾🇪 “የመኖችን በትዕግሥታቸው አትታለሉ፣ በፍፁም ኃይላቸውንም አቅልላችሁ አትመልከቱት‼️ 🇾🇪#የመኖች ሰውን ለመደገፍ ከተነሱ የመሪነትን ዘውድ እስኪይዝ ድረስ አይተዉትም። 🇾🇪#የመኖች ሰውን ከጠሉትና ፊት ከነሡ ደግሞ ጭንቅላቱን እስኪ*ቆርጡት ድረስ አይተዉትም። እነሱ በምድር ላይ ምርጥ ወታደሮች ናቸውና ድልን ፈልጉባቸው። ♦️ከእነሱ ጋር በተያያዘ 🇾🇪❸ ነገሮችን ተጠንቀቁ‼️ ❶🇾🇪#ሴቶቻቸው፦ በክፉ ዓላማ አትቅረቧቸው፣ አለበለዚያ አንበሶች አድነው እንደሚበሉ ይውጧችኋል። ❷🇾🇪#መሬታቸው ትንኩ አለበለዚያ ሌላ ነገር ቢያጡ በተራራዎቻቸው ድንጋዮችም ቢሆን ይዋጉዋችኋል። ❸🇾🇪♦️#ሃይማኖታቸውን አትንኩ፦ በተውሒዳቸው፣በአቂዳቸው፣ #በእስልምናቸው ከመጣችሁባቸው #ዱንያችሁን ያጨልሙታል ይላል።” ሁሉንም ተመልክተናል በተጨባጭም እያየነው ነው። ...ኑረዲን...✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

እህቶቻችን በኒቃባቸው፣ በጂልባባቸው ብዙ ትንኮሳ ይደርስባቸዋል። ታዲያ አንዳንዴ ሙስሊም መሆናቸው የማያስታውቁ ወንድሞች ነብር ሆነው ሲከላከሉላቸው ስታይ ከነ ድክመታቸው ለእምነታቸው፣ ለእህቶቻቸው ያላቸው ተቆርቋሪነት ያስደስትሀል። ከዚህ በተቃራኒ ሙስሊም ሆነው ሳለ ነገር ግን እህቶቻችንን ልክ እንደ ካፊ^ ሮቹ በየመንገዱ በአለባበሳቸው የሚተነኩሱ ዘልዛላዎችን ማየት ሲበዛ የሚያም ነው። እባክህን! የራስህ ደካማነት በቂ ጥፋት ነው! ከዚያ አልፈህ የለየልህ ሙጅ ^ሪም አትሁን። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

➡         🌿🔥 ልዩ የዒልም ጥሪ! 🔥🌿 📖 ሸርሁ ሱንና ሊልበርበሃሪ شرح السنة للبربهاري ✨ የዒልም ፈላጊዎች የምስራች! ✨ 📚 በታላቁ የዐቂዳና የሱንና ኪታብ «ሸርሁ ሱንና ሊልበርበሃሪ» ላይ የሚደረገው የዒልም ደርስ ዛሬ ማታ ይጀምራል! 🔥 🎙️ በኡስታዝ አህመድ አማን (ሀፊዘሁሏህ) 📚 ኪታቡ በሸይኽ ሷሊሕ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ሸርህ መሠረት ይቀራል። ━━━━━━━━━━━━━━ 📍 ቦታ፦ መስጅደል አዝሀር 🗓️ ቀናት፦ ከማክሰኞ እስከ ሀሙስ 🕰️ ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ ━━━━━━━━━━━━━━ 🔥 ዛሬ ማታ አትቅር! የዒልም ማዕድ ተዘጋጅቷል፤ አንተስ/ሽ ትመጣለህ/ሽ? ━━━━━━━━━━━━━━ 📢 ይህን መልዕክት በተቻለዎት መጠን ሸር ያድርጉ! 🤍 👉 ለዒልም ፈላጊ ጓደኞቻችሁ 👉 ለተማሪዎች 👉 የዒልም ማዕድ ለሚወዱ ሁሉ 📞 ያላዩትን ወንድምበወንድሙ/እህትበእህቷ በስልክ ተጠራርታችሁ አሳውቁ። 🌱 አንተ በቻልከው ሸር አድርገው ይህን መልዕክት ለሌላ ሰው የዒልም መንገድ ሊከፍት ይችላል! 🔗 የደርሱን መረጃ ለመከታተል👇 https://t.me/abuabdelah123 🤲 አላህ ይቀበለን፣ በዒልም ያሳድገን እና የተማርነውን ለመተግበር ያግዘን። 🌿 የዒልም ማዕድ — ዛሬ ማታ በመስጅደል አዝሀር! 🌿

አህባቦች ለምንኖርለት ነገር #ትልቅ_ አላማ" ሊኖረን ይገባል።

ይሄ አሁን "ሙመይዕ ነው ወይንስ ኢኽዋኒ" ነው የሚያስብለው⁈ ﴿إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ ﴿  سورة البقرة 160﴾ ይሄ መርህ ነው። ጥፋተኞች ይቅር ይባልላቸው ዘንድ ከቀድሞው እኩይ ድርጊታቸው፡ መቶበት፣ ማስተካከልና ግልጽ ማድረግ አለባቸው ነው የሚለው መመሪያው። ለዛም ይመስለኛል አቡ ሙዓዝ ከቀጥተኛው የሰለፍያ መንሀጅ በቃኝ ብሎ ወደ እናንተ ሲመጣ መጀመሪያ ተውበትህን ኢዕላን አድርግ ብላችሁ ስትወተውቱት የነበረው። ስለዚህ እንዲያ ከሆነ ነገሩ ሽይኽ አቡ ዘር ከተምይዕ/ከኢኽዋንነት/ መንገድ ወደ ሰለፊያ መንሀጅ ሲቀላቀል የቶበተበትንና ግልጽ ያደረገበትን የድምጽ ቅጅ ስጡን። አበቃ!! አሁን ያለበት መንሀጅ ላይ ሁኖ ሰፊ ስራ መስራቱ የተውበቱ ማሳያ ነው ብላችሁ ልtሸውዱኝ እንዳትሞክሩ እኔ በዚህ የምታለል ህጻን አይደለሁም። የቢድዓ ባለቤት ዘንድ መማር ቀርቶ መቀማመጥ ሁክሙ ምንድን ነው? በሉ አሁን ቪድዮውን እዩና ፈትዋውን አያዩይዛችሁ መልሱልኝ። ይልቅስ ነገሮችን በልክ ካልተያያዝን እራሳችሁ የቦረቦራችሁት ቅርቃር ውስጥ የምትገቡበትን ነው እየበረበርኩ የምበትንላችሁ። *ለማንኛው ቪደዎዉ ለ Africa Tv በሚቀርብ ቀረጻ ላይ ሸይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጦፋ ላይ "ሲ*ራ" ሲቀራ የሚያሳይ ነው። *ከዚህ መንሀጅ የቶበተበትን ማስረጀ ከሰጣችሁኝ እኔ ጽሁፌን አነሳለሁ። እውነታን የመነጋገር እንጂ የእልህ አካሄድ የለብኝም። ይሄን የማትሰጡኝ ከሆነ ግን ሌላ ጨምሬ እመጣለ ኢንሻ አላህ። አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida

አንተ የሰው ልጅ ሆይ ከጌታህ ምን አታለለህ 👉ሰዎችን ወደ ደን የምንጠራበት መንገድ ምን መምሰል አለበት በሰፊው ተዳሷል 👉በተለይ እዚህ ወሎ አካባቢ ያሉ ቤተሰቦቻችንን እንደት ነው መጥራት ያለብን ? 👉በዳዕዋ ላይ እዝነት ማለት ምን ማለት ነው ተዳሷል 🎙 በሸህ ከማል መኪይ ሃፊዘሁላህ 🕌 ወረኢሉ ፉርቃን_መስጅድ 📝 ነሃሴ 15/2018 E.C https://t.me/YewereiluMuslimoch/6278 የሸህ ከማል መኪይ ሃፊዘሁላህ ወረኢሉ_ፉርቃን መስጅ ያደረጓቼውን ዳዕዋዎች ለማገኘት ከ1_4 1👇👇👇👇👇 https://t.me/YewereiluMuslimoch/6275 2👇👇👇👇 https://t.me/YewereiluMuslimoch/6276 3 👇👇👇👇👇 https://t.me/YewereiluMuslimoch/6277 4👇👇👇👇 https://t.me/YewereiluMuslimoch/6278

የመካነ ሰላምና የከላላ ወንድምና እህቶቻችን አዛኙ ጌታችን በእዝነቱ ይጠብቃችሁ እሱ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነውና 🤲✍️