cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن

#ሰለፍያ_ቀጥተኛ_የሀቅ_መንገድ_ብሎም_አይነኬ_ፅኑ_ተራራ_ነው ለአስተያዬትና እርማት @Nuredin_al_arebi_Bot

Show more
Advertising posts
20 920
Subscribers
-924 hours
-397 days
+6930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰማህ ወይ በል 🍃🕯 ˓٭˛ ،🌸 ٰ           قَالَ ابْنُ الْقَيِّمِ رَحِمَهُ اللهُ:    "وَكُلُّ مَعْصِيَةٍ عَيَّرْتَ بِهَا أخَاكَ فَهِيَ إلَيْكَ". ማንኛውም ወንድምህን ያነወርክበት ወንጀል እሱ ወደ አንተ ይመለሳል።
📚 [ مَدَارِجُ السَّالِكينَ (١/١٧٧) ]
               http://t.me/nuredinal_arebi
Show all...
👍 8
ጀነት በሚፈለግባቸው ስራዎች ከንቱ ዝናን እና መሪነትን መፈለግ ይብቃ! ሰሞኑን ከየመን የተላኩ ጥቂት ኪታቦች ደረሱኝ ። አላህ የዒልም እና የጀነትን መንገድ ያግራለትና አንድ የሱና ወንድሜ ነበር ኪታቦቹን የላከልኝ ። ከነዚህ ኪታቦች ውስጥ አይኔ አጠር ያለች አንዲት አጭር ሪሳላ ላይ አረፈ ። ርእሱ ልቤን ሳበው ! ሪሳላዋን ላነብ አለቅጥ ጓጓሁ ... ርእሱ በዘመናችን የተንሰራፉ ሁለት የልብ ነቀርሳዎችን መሰረት ያደረገ ነው - ዝናን ማንፍነፍ ! መሪነትን ማሰስ! ! حب الرئاسة والظهور يورث الشقاق والشرور ይላል ... ፀሃፊው ከየመን መሻይኽ ዉስጥ አንዱ የሆኑት الشيخ أنيس بن صالح المهندس اليافعي ናቸው ... ሪሳላዋ ውስጥ በርእሱ ዙሪያ ጠቃሚ እና ልብን የሚያክሙ ገሳጭ ምክሮችን በሰፊው እናገኛለን ወላሂ! ነገሩ ያሳስባል ! ርእሱ እጅጉን ያስጨንቃል ! ለመሆኑ ... ስንቶቻችን እንሆን እንዲህ አይነቱን በሽታ በልባችን አምቀን ከመልካሞች የምንታሰብ !? ስንቶቻችን እንሆን ... በመልካም ስራዎቻችን እና ንግግሮቻችን ዝናን እያነፈነፍን ውለን የምናድር? ስንቶቻችን እንሆን እነዚህን ሁለት የኢኽላስ ጠላቶች ተሸክመን ስለ ኢኽላስ የምንሰብከው ? ! ስንቶቻችን እንሆን ዝናን በማሰስና ፣ መሪነትን በማሰብ ሌሎች ወንድሞች በእኛ ቦታ የአላህ ቤቶች ውስጥ እንዳያስተምሩ እንቅፋት የምንሆነው ?!! ስንቶቻችን እንሆን ዝናን እና የበላይነትን ፍለጋ ሊትተቹ የማይገባቸው አማኞችን አለአግባብ የተቸን ?! ስንቶቻችን ... አላህ ይመልሰን ጀነት በሚፈለግባቸው ስራዎች ከንቱ ዝናን እና መሪነትን መፈለግ ይብቃ! https://t.me/Muhammedsirage
Show all...
MuhammedSirage M.NOOR

اتق الله حيثما كنت

👍 4
* ሰበብ እየፈለገ ሌሎችን ከሱና የሚያስወጣ አካል መጨረሻ ላይ ሌሎችን ባስወጣበት በር ራሱ ይወጣል። * እወቅ! ሌሎች ላይ የመዘዝከው የኢልዛም ሰይፍ ወዳንተም ይዞራል። እቆርጥበታለሁ ያልከው ይቆርጥሃል። * ሰለፊያ የወደድከውን የምታስገባበት፣ የጠላሀውን የምታስወጣበት ያ'ባትህ ግቢ አይደለም። ሰለፊያ ኢስላም ማለት እንጂ ሌላ ቡድን አይደለም። ይህንን ከቃላት ባሻገር በተግባር አስረግጥ። * በዚህ ዘመን በመንሀጅ ስም ተጠቅልሎ ያለው አብዛኛው ጩኸት የአመል ችግር ነው። ያለበለዚያ ሰው እንዴት እስ'ካፍንጫው በተነከረበት ጥፋት ሌሎችን ሊከስ ይደፍራል? * በሺርክና በቢድዐ መፈረጅ ከሺርክና ከቢድዐ የማስጠንቀቅ ያህል ቀላል አይደለም። ሁለተኛው ላይ ካለህ ትጋት ይልቅ የመጀመሪያውን መድፈርህ መታመምህን ነው የሚያሳየው። ሳይጠናብህ ታከመው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

👍 4
ወይ አዲስ አበባ!!
Show all...
👍 66
ጭፍራው ቅርቃር ውስጥ ገብቷል ~ ቅልጥ እንደ ቅቤ - ፍርስ እንደ ሸክላ ሁሉ ነገር እርቃን - እነ ሳይሞቅ ፈላ! ይሄ ሰካራም ጭፍራ ብዙ እንደማይራመድ በጣም እርግጠኛ ነበርኩ። በዚህ ፍጥነት ድንብርብሩ ሲወጣ፣ ጉዱ ሲዝረከረክ ማየት ግን የጠበቅኩት አልነበረም። የዛሬን ሁለት ዓመት መሰለኝ ወራቤ ላይ አንድ ወንድም ዐብዱልሐሚድ ለተሞ አንድ መንሀጅ ላይ ሁለት አመት ታግሶ መቆየት አይችልም ጠብቁ ሲል ሰምቼው ነበር። ምናልባት የሆነ ያክል ተጋኖ ይሆን? አላውቅም። ንግግሩ ግን በውስጡ የሆነ እውነት አዝሏል። አሁን ላይ አንዳንድ ነገሮች ጫፋቸው እየዘለቀ ነው። እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ ይሄው እየጠራ መጣ። በየጊዜው እየወጡ ካሉ በርካታ የቪዲዮ እና የፎቶ ማስረጃዎች ውስጥ ለጊዜው አንድ ማሳያ ልጥቀስ፦ ጠሃ ኸዲር የዚህ የተንቀዠቀዠ ጭፍራ አጫፋሪ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ሶሻል ሚዲያ ላይ እየዘለቀ ሁለት ሶስት መስመር ስድብ መፃፍን ቁም ነገር ያደረገ በተግባር ግን በተለያየ ቦታ የተለያየ ፊት የሚጠቀም ሰው ነው። * ሳዑዲ ውስጥ ጤነኛ ያልሆኑ ሰዎች ዘንድ ቁጭ ብሎ ለአመታት ይማራል። እዚህ ደግሞ እነ እከሌ ከእነ እከሌ ጋር ተቀመጡ እያለ ፎቶ ይለጥፋል። የሳዑዲ ኤምባሲ ሲጋብዛቸው ራሱም ጭፍራዎቹም ከነዚያው ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር አንድ ላይ ይጣዳሉ። በተለያዩ ቦታዎች የተለያየ ፊት ማሳየትን ተክኖበታል። * መሻይኾች ዘንድ ሌላ ሰው ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ደግሞ ሌላ። * ሳዑዲ ውስጥ ሌላ ሰው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ። * እንደ ባህሩና ሑሴን ያሉ ተናካሽ ጓዶቹ ጋር ሲሆን ሌላ ነው። አቃቂር እያወጡ፣ ቅጥፈት እየለጠፉ የሚናከሱ አውሬዎች ናቸው። እያደናነቀ የሚያስተዋውቃቸው የሀረር አካባቢ ጭፍራዎቹ ደግሞ እሱ በሚስላቸው 'ሙስተዋ' ላይ አይደሉም። ያያያዝኩት ቪዲዮ ለዚህ አንድ ምስክር ነው። በቪዲዮው ላይ የጠሀ ጭፍራ የሆኑት (የነበሩት ብለው ይሻል ይሆን?) እነ ኢልያስ ዐባስ እና አሕመድ ሙሐመድ (ጭሮ?) ከነ ዶክተር ጀይላን ጋር ተቀማምጠው የአንድነት መግለጫ ያወጡበት ጉባዔ ነው። ቪዲዮው ላይ ከሰፈረው ቃል ቀንጨብ ላድርግ፦ 1- የዶክተር ጀይላን ንግግር፦ "በሀረር ዑለማኦች መካከል ልዩነት እንደሌለ እንዲሁም በዑለማኦቹ መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚጥሩ አካላት በዑለማእ ስም የሚነግዱ እንደሆኑ፤ እኛ ሁላችንም አንድ እና የተሰማማን እንደሆንን፤ በመካከላችን ልዩነት እንደሌለ የሀረር እና የኢትዮጵያ መሻይኽ ጉባኤ ገልጿል።" 2- የኢልያስ ዐባስ ንግግር፦ "እኛ እንደ አሕመድ ሱኣላ እና እንደ ዶክተር ጀይላን ካሉ ታላላቅ ዑለማኦች ጋር ነን። ድሮም፣ አሁንም በመካከላችን ልዩነት የለም። እስከ ዘላለም ከነሱ አንለይም።" 3- የአሕመድ ሙሐመድ ንግግር:- "እኛ አሁን ከዑለማኦቻችን ጋር ነን። እነሱን ከሚሳደቡ አካላት ድሮም አሁንም የጠራን ነን። ፈፅሞ ከነሱ (እነሱን ከሚሳደቡ) ጋር አንሆንም።" ልብ በሉ! ጠሀ ኸዲር እነዚህን ሁለቱን ሰዎች (ማለትም ኢልያስ ዐባስ እና አሕመድ ሙሐመድ) ሞቅ አድርጎ ያወድሳል። ያሰራጭላቸዋልም፡፡ ለምሳሌ ያክል በቅርቡ እንዲህ ሲል ፅፏል:- أشد على أيديكم يا أبطال شرق هرر فضيلة الشيخ Sheek Iliyaas Abbaas وفضيلة الشيخ Shekh Ahmade Muhammed زادكم الله قوة إلى قوتكم فقد أقضت جهودكم المضاجع وألهبت المشاعر وأسهرت وهزت ولن يهنأ منهم أحد مهما كان بعدما التهبت الأحشاء واضطرمت! = እነዚህ የጠሀ ጀግኖች ግን፡ 1ኛ፦ ከነ ዶክተር ጀይላን ጋር እንደሆኑ ድሮም፣ አሁንም በመካከላቸው ልዩነት እንደሌለ ገልፀዋል። እስከ ዘላለም ከነሱ እንደማይለዩም አስረግጠው ተናግረዋል። 2ኛ:- እነሱን (እነ ዶክተር ጀይላንን) ከሚሳደቡ አካላት ድሮም አሁንም የጠራን ነን። ፈፅሞ እነሱን ከሚሳደቡ ጋር አንሆንም ማለታቸውን ያዙ። እዚህ ላይ ቁጥር አንድ ተጠቃሹ ጠሀ ኸዲር ነው። አሞሌው አልሰራም። ከዚህ በኋላ ያለው ምርጫ ሁለት ነው። 1ኛው ምርጫ፦ ወይ እንደ ግለቱ እያዩ ሲያሻቸው "እኛ ድሮም ጀምሮ መንሀጅ ገብቶናል፣ ለ 20፣ ለ30 አመታት ሰለፊያን (የነሱን ቨርዥን) ስናስተምር ነው የኖርነው፣ ከኢኽዋን የጠራን ነን፣ ..." እያሉ መሞገት፤ ሲላቸው ደግሞ ከነዚያው ኢኽዋን ከሚሏቸው ሰዎች "ድሮም አሁንም አንድ ነን፣ ዘላለም አንለያይም" እያሉ የጋራ መግለጫ እያወጡ መቀጠል ነው። በተለያየ መመዘኛ እየመዘኑ፣ የተለያየ ፊት እያሳዩ መሄድ ለጠሀ ከባድ አይመስለኝም። ይሄ ግን የሰለፊ መገለጫ አይደለም። ሸይኽ ሙቅቢል እንዲህ ይላሉ፦ فالحزبي مستعد أن يكون له خمسة أوجه. والنبي ﷺ يقول: إن من شر الناس ذا الوجهين الذي يأتي هـولاء بوجه وهؤلاء بوجه. أما السني فإنه متمسك بدينه سواء رضي فلان أو لم يرضَ بخلاف الحزبيين. "ቡድንተኛ ሰው አምስት ፊት ሊኖረው ዝግጁ ነው። ነብዩ ﷺ 'ከክፉ ሰዎች ውስጥ የሆነው ባለ ሁለት ፊት ነው። ያ እነዚያ ዘንድ በአንድ ፊት፣ ሌሎቹን ደግሞ በሌላ ፊት የሚቀርበው።' ሱኒይ የሆነ ሰው ግን እከሌ ቢወድም ሆነ ቢጠላ ዲኑን አጥብቆ የሚይዝ ነው። ከቡድንተኞች በተለየ።" [ቱሕፈቱል ሙጂብ፡ 290] 2ኛው ምርጫ፦ ከነዚህ ሲያወድሳቸው ከነበሩ አካላት መለያየቱን ማወጅ ነው። ሰውየው ተቃራኒ ነገሮችን የማስተናገድ ልምድ ቢኖረውም ይሄኛው ግን ለመሸፈን የሚመች አይደለም። "ግመል ሰርቆ አጎንብሶ" የማይሆን ነገር ነው። ስለዚህ መለያየትን ከማወጅ ውጭ ምርጫ አይኖርም። ካ'ህያ ቆዳ የተሰራ ቤት ይበታተናል ጅብ የጮኸ 'ለት! - የነዚህ ሰዎች ጉድ ይሄ ብቻ አይደለም። አለ ገና! ستُبْدي لكَ الأيّامُ ما كنتَ جاهلاً - ويأتِيكَ بالأخبارِ مَن لم تُزَوِّدِ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

👍 68
በሰው እጅ ቢሆንማ... لو كانت الأرزاق بيد البشر لمات الناس جوعا وعطشا ሪዝቃችን በሰወች እጅ ቢሆን ኖሮ የሰው ልጅ በውሀጥምና ቀረሀብ ይሞት ነበር። ولكن فضل الله ورحمه جعلها بيده ليتسنى لنا أن نعيش ونتنفس ونأكل من خيراته ግና የአሏህ እዝነትና ችሮታ ሆኖ እንድንኖር እንድንተነፍስና እንድንመገብ አድርጎ ሪዝቅን በእጁ አደረገልን። فلنحمد الله دائما على هذه النعمة العظيمه ስለሆነም ለዚህ ትልቅ ፀጋ ሁሉም ዘላለማችንን አሏህን ማመስገን አለብን። ✍️نورالدين العرب http://t.me/nuredinal_arebi
Show all...
👍 53
ሙስሊሞች ነና والله لسنا لأحد إنا لله وإنا إليه راجعون እኛ የማንም አይደለንም ይልቁንም እኛ የአሏህ ብቻ ነን። http://t.me/nuredinal_arebi
Show all...
👍 39
" إن فاتك أن تكون محبوباً فلا يفوتك أن تكون مُحباً ." "ተወዳጅነትን ካጣህ መወደድ እንዳያመልጥህ።" http://t.me/nuredinal_arebi
Show all...
👍 27
" إن فاتك أن تكون محبوباً فلا يفوتك أن تكون مُحباً ."
Show all...