قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
الذهاب إلى القناة على Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
913
المشتركون
-324 ساعات
-177 أيام
+5330 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from الــــســــنـــةسفــــينة نــــــــوح🖊
የፍቅር ስቃይ.....!
በኡስታዝ አቡ ሱፍያን አላህ ይጠብቀው!
ስለ ቀልባችን☑️
➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
ሐዘን ልብን ያደክማል፤ የሰውን ልጅ ጽናትና ብርታት ያላላል
ታላቁ ዓሊም የኢማም ኢብኑል ቀይም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "ያለፉ አሳዛኝ ትውስታዎችን ደጋግማችሁ ወደ ራሳችሁ
አትጥሩ!"
ሐዘን ልብን ያደክማል፤ የሰውን ልጅ ጽናትና ብርታት ያላላል፤ እንዲሁም ጠንካራ የመሥራት ፍላጎትንና ውሳኔን (ኢራዳን) ይጎዳል።
ለአማኝ ባሪያ ከሐዘንና ከተስፋ መቁረጥ ይበልጥ በሰይጣን ዘንድ የሚወደድ (የሚያስደስት) ምንም ዓይነት ነገር የለም። ምክንያቱም ሰይጣን አማኝን በሐዘን ሰንሰለት አስሮ ከጌታው መንገድና ከሕይወት ብርሃን ሊያርቀው ይፈልጋልና።
ስለዚህ ወዳጄ ! ያለፈውን አሳዛኝ ታሪክህን እየቆሰቆስክ ዛሬህን አታጨልም። ሐዘን የሰይጣን ትልቁ መሣሪያ መሆኑን
አውቀህ፤ ልብህን በጌታህ እዝነትና በተስፋ ብርሃን አስውበው። ጌታችን አላህ ከሐዘን፣ ከጭንቀትና ከሰይጣን ወስዋስ ይጠብቅን።
https://t.me/Asselefiyah_Channel
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
የጀነት በር ጠባቂ መላዒካ ረድዋን ይባላል፡፡
⚠️አስቸኳይ የነፍስ አድን ጥሪ
👉ያአህባብ እዪልኝ ይሄን በጭፈራ ላይ የተመሠረተ አምልኮ የልዕለ ሀያሉ ጌታችንን አላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ እንደት እንደተዳፈሩት እያያችሁ ነዉ የመኪና ብዛት የህዝብ ስብስብ ዶሪህ ለመለመን ችግራቸዉን ለጅን አቤቱታ የሚያቀርቡ ከሙስሊሙ የወጡ ሰዎች ባሻገር ክሪስቲያኖች ጭምር ለአላህ በመናገር ፋንታ ግን እነሱ ምንም ለማያደርግላቸዉ ዶሪህ ተናግረዉ ይሄዳሉ በአመቱ ተመልሰዉ መተዉ ስለታቸዉን ለጅን ያርዳሉ!!
የቦረናው ሸህዬ
የቦረናው ደግዬ
እርዱን አባብዬ
ይህ የሽርክ ግጥም የሚዘመርባት ከተማ ከ500ሺ ህዝብ በላይ ሽርክን ለማንገስ ከአድስ አበባ እስከ ባሌ ከወለጋ እስከ ሐረር ከወሎ እስከ ጎጃም ከጎንደር እስከ ሸዋ ሳይቀር ሰው ስለቱን ይዞ ኮርማውን እየነዳ ሽቱውን ገዝቶ መጋረጃ ሸምቶ ልክ እንደ ግሸን ማርያም ክብረ_በዓል መንገድ በአይሱዚና በቅጥቅጥ እንድሁም በህዝብ ብዛት ጥቅምት 15 የዶሪኋን ታቦት በማነገስ ከተማዋ ትጨናነቃለች ። በዚያ ሌሊት የሚጎራ ጉሪያ የሚወገር ድቤ የሚጮህ ጩኸት የሚለቀስ ለቅሶ የሚጨስ አድሩስ የሚታረድ በግና ፍየል ምን ልበልህ ባጭሩ ራሷ ከተማዋ ታብዳለች ።
ለወንድም እህቶቼ ፦
ወንድም እህቶቼ፣ በየዓመቱ ብዙ ሰዎች ችግራቸውን ይዘው ወደ እዚህ ቦታዎች ይጓዛሉ። ብዙዎቹ በሕመም፣ በችግርና በጭንቀት የተጎዱ ናቸው።
ስለምንወዳቸው ነው የምናስታውሳቸው፤ ከአላህ ውጭ ሌላ አያድናቸውም።1️⃣ አላህ ቅርብ ነው وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ «ባሮቼ ስለ እኔ ቢጠይቁህ እኔ ቅርብ ነኝ፤ ለማኙ ሲለምነኝ ልመናውን እቀበላለሁ።»
ሱረቱል -በቀራህ ምዕራፍ 2:አንቀፅ 186وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ «ጌታችሁም አለ፦ ለምኑኝ፣ እመልስላችኋለሁ።»
ሱረቱል ጋፊር ምዕራፍ 40:አንቀፅ 60አላህ ከእኛ ጋር አማላጅ ሳያስፈልገው ቅርብ ነው። በሌሊት፣ በሱጁድ፣ በየትኛውም ቦታ ልንለምነው እንችላለን። 2️⃣ ዱዓ ኢባዳ ነው «الدُّعَاءُ هُوَ الْعِبَادَةُ» «ዱዓ (ልመና) ኢባዳ (አምልኮ) ነው።»
📚ቲርሚዚ፣ አቡ ዳውድ ዘግበውበታልኢባዳ ደግሞ ለአላህ ብቻ ይገባል፦ وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا «መስጊዶች የአላህ ናቸው፤ ስለዚህ ከአላህ ጋር ማንንም አትለምኑ።»
ሱረቱል አል-ጂን ምዕራፍ 72:አንቀፅ 18)«إِذَا سَأَلْتَ فَاسْأَلِ اللَّهَ، وَإِذَا اسْتَعَنْتَ فَاسْتَعِنْ بِاللَّهِ» «ከጠየቅህ አላህን ጠይቅ፤ ርዳታ ከፈለግህ በአላህ ተረዳ።»
📚ቲርሚዚ ዘግበውታል3️⃣ ከአላህ ሌላ የሚለመኑት ሊጠቅሙ አይችሉም وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا دُعَاءَكُمْ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም:: ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም:: ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም
ሱረቱል ፋጢር ምዕራፍ 35:አንቀፅ 13-14ምንም ሊያደርጉልን የማይችሉትን መለመን ጊዜና ተስፋ ማባከን ነው። 4️⃣ ማረድ ለአላህ ብቻ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ لَا شَرِيكَ لَهُ «በል፦ ሶላቴ፣ እርዶቼ (ሥርዓተ አምልኮዬ)፣ ሕይወቴና ሞቴ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው። አጋር የለውም።»
ሱረቱል አል-አንዐም ምዕራፍ 6:አንቀፅ 162-163«لَعَنَ اللَّهُ مَنْ ذَبَحَ لِغَيْرِ اللَّهِ» «ለአላህ ላልሆነ ያረደን አላህ ረግሟል።»
📚(ሙስሊም) ዘግበውታል5️⃣ ሽርክ ከሁሉ የከበደ ሐጢአትነው إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ «አላህ በእሱ ላይ ማጋራትን አይምርም፤ ከዚያ ሌላውን ለሚሻው ይምራል።»
ሱረቱል አን-ኒሳእ አን ምዕራፍ 4:አንቀፅ 48ስለዚህ ነው የምናስጠነቅቀው፤ ስለምንጠላችሁ ሳይሆን ስለምንወዳችሁ። ወደ አላህ መመለስ (ተውበት) በር ግን ዛሬም ክፍት ነው። 6️⃣ ምን እናድርግ❓ 🤲 ችግራችሁን በሌሊት ተነስታችሁ በሱጁድ ለአላህ አቅርቡ። 🩺 ሕመም ካለ ወደ ሐኪም ሂዱ፤ ከሕክምና ጋር ሩቅያ ሸርዒያን (በቁርኣንና በነቢያዊ ዱዓዎች መታከምን) ተጠቀሙ። 💝 ሰደቃ ስጡ፤ ለችግረኛ መርዳት ችግርን ያቀልላል። 📖 ተውሒድን ከታመኑ ዑለማ ተማሩ። 🌿 ቤተሰብና ጎረቤትን በፍቅር፣ በትዕግስትና በግል አነጋግሩ። አላህ ሁላችንንም ከሽርክ ይጠብቀን፣ ችግር ውስጥ ያሉትንም አውጣቸው፣ ወደ ቀጥተኛው መንገድም ይምራን። አሚን። የቴሌግራም ቻናል t.me/yedeger_selefioch_jemea የቴሌግራም ግሩፕ t.me/yedeger_muslim_Wetatoch_jemea
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
ከወንጀሎች ቅጣቶች መካከል አንዱ፦ የእድሜን በረካ፣ የርዝቅን በረካ፣ የእውቀትን በረካ፣ የመልካም ተግባርን በረካ እና የዒባዳን በረካ የሚያጠፉ መሆናቸው ነው።ባጠቃላይ፣ የሃይማኖትንም ሆነ የዱንያን በረካ ያጠፋሉ።
ابن القيم | الداء والدواءt.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
↩من أعظم النعم على المؤمن .. أن يهبه بصيرة يميّز بها الحق من الباطل والطيب من الخبيث والخير من الشر.
Repost from N/a
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው ብዙ
የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን
ያገኛል ።
የሱና ቻናል ያላቹ👉 @Quran_mylife1
ጥያቄ 1
💎ተዉሂድ በስንት ይከፈላል?
Repost from ከ ደጋጎቹ ዓለም
ከመካከላችን አንዱ የዱንያን ዕድሉን ወዲያው ሊያገኝ ይችላል፤ የሚያስደስተውን ሥራ፣ ስሙን ከፍ የሚያደርግበትን ደረጃ፣ ኑሮውን የሚያሰፋበትን ሀብት ሊያገኝ ይችላል።
ከመካከላችን ደግሞ የሚገባን የሚመስሉን ዕድሎች ሁሉ እድሜ ልካችንን ሳያገኙን የሚያልፉብን ይኖራሉ። ሌላው ሲመኘው የነበረውን ነገር ሲያገኝ፣ ሰዎች ሲያመሰግኑትና ሲያደንቁት ያያል። እሱም ፈገግ ይላል፣ ነገር ግን በልቡ ውስጥ የሆነ ነገር ይቀራል።
ዕድላችን የዘገየብን የሚመስለን እኛ ሆይ፣ የእኛ ድርሻ የጠፋ አይምሰለን።ምናልባት አላህ ካመለጡን ነገሮች ሁሉ የሚበልጥን ነገር ለእኛ አስቀምጦልን ይሆናል።
ረሱልን صلى الله عليه وسلم በጀነት መገናኘት፣ ከወደድናቸው ሰዎች ጋር በሽታም ሆነ ሞት በሌለበት ዓለም አብሮ መኖር፣ ነፍስ ካወቀቻቸው ጸጋዎች ሁሉ በላይ በሆነ ጸጋ መሸለም ሊጠብቀን ይችላል።
ከሰዎች መካከል ዕድላቸውን በዱንያ የሚያገኙ ይኖራሉ። ከአላህ ባሮች መካከል ግን አንዳንዶቹ ዕድላቸው ለዱንያ አይደለም፤ አላህ የዘገየውን ዕድላቸውን አስቀምጦላቸዋል።ለእነርሱ ጀነት እንጂ ሌላ አትመጥናቸውም።
#ማስታወሻ
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
🇾🇪የመኖችን ለማታውቋቸው
--------------------------
ሐጃጅ ኢብን ዩሱፍ አል-ሠቃፊ
🇾🇪 ስለ የመን ሕዝብ ምን ብለዋል⁉️
አል-ሐጃጅ ኢብን ዩሱፍ አል-ሠቃፊ ስለ የመን ሕዝብ የተነገረው ታዋቂ አባባል #ወንድሙን
#ሙሐመድ_ኢብን_ዩሱፍን የየመን🇾🇪 ገዥ አድርጎ ሲሾም ለእሱ የሰጠው አደራና ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ይህን ይላል‼️
♦️#ታዋቂው #የሐጃጅ አባባል‼️
.....የመኖች🇾🇪
“የመኖችን በትዕግሥታቸው አትታለሉ፣
በፍፁም ኃይላቸውንም አቅልላችሁ አትመልከቱት‼️
🇾🇪#የመኖች
ሰውን ለመደገፍ ከተነሱ የመሪነትን ዘውድ እስኪይዝ ድረስ አይተዉትም።
🇾🇪#የመኖች
ሰውን ከጠሉትና ፊት ከነሡ ደግሞ ጭንቅላቱን እስኪ*ቆርጡት ድረስ አይተዉትም።
እነሱ በምድር ላይ ምርጥ ወታደሮች ናቸውና ድልን ፈልጉባቸው።
♦️ከእነሱ ጋር በተያያዘ 🇾🇪❸ ነገሮችን ተጠንቀቁ‼️
❶🇾🇪#ሴቶቻቸው፦
በክፉ ዓላማ አትቅረቧቸው፣ አለበለዚያ አንበሶች አድነው እንደሚበሉ ይውጧችኋል።
❷🇾🇪#መሬታቸው ትንኩ
አለበለዚያ ሌላ ነገር ቢያጡ በተራራዎቻቸው ድንጋዮችም ቢሆን ይዋጉዋችኋል።
❸🇾🇪♦️#ሃይማኖታቸውን አትንኩ፦
በተውሒዳቸው፣በአቂዳቸው፣ #በእስልምናቸው ከመጣችሁባቸው #ዱንያችሁን ያጨልሙታል ይላል።”
ሁሉንም ተመልክተናል በተጨባጭም እያየነው ነው።
...ኑረዲን...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እህቶቻችን በኒቃባቸው፣ በጂልባባቸው ብዙ ትንኮሳ ይደርስባቸዋል። ታዲያ አንዳንዴ ሙስሊም መሆናቸው የማያስታውቁ ወንድሞች ነብር ሆነው ሲከላከሉላቸው ስታይ ከነ ድክመታቸው ለእምነታቸው፣ ለእህቶቻቸው ያላቸው ተቆርቋሪነት ያስደስትሀል።
ከዚህ በተቃራኒ ሙስሊም ሆነው ሳለ ነገር ግን እህቶቻችንን ልክ እንደ ካፊ^ ሮቹ በየመንገዱ በአለባበሳቸው የሚተነኩሱ ዘልዛላዎችን ማየት ሲበዛ የሚያም ነው። እባክህን! የራስህ ደካማነት በቂ ጥፋት ነው! ከዚያ አልፈህ የለየልህ ሙጅ ^ሪም አትሁን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from አቡ ዓብደሏህ(أبو عبد الله الولوي)🇸🇦
➡
🌿🔥 ልዩ የዒልም ጥሪ! 🔥🌿
📖 ሸርሁ ሱንና ሊልበርበሃሪ
شرح السنة للبربهاري
✨ የዒልም ፈላጊዎች የምስራች! ✨
📚 በታላቁ የዐቂዳና የሱንና ኪታብ «ሸርሁ ሱንና ሊልበርበሃሪ» ላይ የሚደረገው የዒልም ደርስ ዛሬ ማታ ይጀምራል! 🔥
🎙️ በኡስታዝ አህመድ አማን (ሀፊዘሁሏህ)
📚 ኪታቡ በሸይኽ ሷሊሕ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ሸርህ መሠረት ይቀራል።
━━━━━━━━━━━━━━
📍 ቦታ፦ መስጅደል አዝሀር
🗓️ ቀናት፦ ከማክሰኞ እስከ ሀሙስ
🕰️ ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
━━━━━━━━━━━━━━
🔥 ዛሬ ማታ አትቅር!
የዒልም ማዕድ ተዘጋጅቷል፤ አንተስ/ሽ ትመጣለህ/ሽ?
━━━━━━━━━━━━━━
📢 ይህን መልዕክት በተቻለዎት መጠን ሸር ያድርጉ! 🤍
👉 ለዒልም ፈላጊ ጓደኞቻችሁ
👉 ለተማሪዎች
👉 የዒልም ማዕድ ለሚወዱ ሁሉ
📞 ያላዩትን ወንድምበወንድሙ/እህትበእህቷ በስልክ ተጠራርታችሁ አሳውቁ።
🌱 አንተ በቻልከው ሸር አድርገው ይህን መልዕክት ለሌላ ሰው የዒልም መንገድ ሊከፍት ይችላል!
🔗 የደርሱን መረጃ ለመከታተል👇
https://t.me/abuabdelah123
🤲 አላህ ይቀበለን፣ በዒልም ያሳድገን እና የተማርነውን ለመተግበር ያግዘን።
🌿 የዒልም ማዕድ — ዛሬ ማታ በመስጅደል አዝሀር! 🌿
አህባቦች ለምንኖርለት ነገር #ትልቅ_ አላማ" ሊኖረን ይገባል።
Repost from Abu_Oubeida~channel
ይሄ አሁን "ሙመይዕ ነው ወይንስ ኢኽዋኒ" ነው የሚያስብለው⁈
﴿إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ ﴿ سورة البقرة 160﴾
ይሄ መርህ ነው። ጥፋተኞች ይቅር ይባልላቸው ዘንድ ከቀድሞው እኩይ ድርጊታቸው፡ መቶበት፣ ማስተካከልና ግልጽ ማድረግ አለባቸው ነው የሚለው መመሪያው። ለዛም ይመስለኛል አቡ ሙዓዝ ከቀጥተኛው የሰለፍያ መንሀጅ በቃኝ ብሎ ወደ እናንተ ሲመጣ መጀመሪያ ተውበትህን ኢዕላን አድርግ ብላችሁ ስትወተውቱት የነበረው። ስለዚህ እንዲያ ከሆነ ነገሩ ሽይኽ አቡ ዘር ከተምይዕ/ከኢኽዋንነት/ መንገድ ወደ ሰለፊያ መንሀጅ ሲቀላቀል የቶበተበትንና ግልጽ ያደረገበትን የድምጽ ቅጅ ስጡን። አበቃ!! አሁን ያለበት መንሀጅ ላይ ሁኖ ሰፊ ስራ መስራቱ የተውበቱ ማሳያ ነው ብላችሁ ልtሸውዱኝ እንዳትሞክሩ እኔ በዚህ የምታለል ህጻን አይደለሁም። የቢድዓ ባለቤት ዘንድ መማር ቀርቶ መቀማመጥ ሁክሙ ምንድን ነው? በሉ አሁን ቪድዮውን እዩና ፈትዋውን አያዩይዛችሁ መልሱልኝ። ይልቅስ ነገሮችን በልክ ካልተያያዝን እራሳችሁ የቦረቦራችሁት ቅርቃር ውስጥ የምትገቡበትን ነው እየበረበርኩ የምበትንላችሁ።
*ለማንኛው ቪደዎዉ ለ Africa Tv በሚቀርብ ቀረጻ ላይ ሸይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጦፋ ላይ "ሲ*ራ" ሲቀራ የሚያሳይ ነው።
*ከዚህ መንሀጅ የቶበተበትን ማስረጀ ከሰጣችሁኝ እኔ ጽሁፌን አነሳለሁ። እውነታን የመነጋገር እንጂ የእልህ አካሄድ የለብኝም። ይሄን የማትሰጡኝ ከሆነ ግን ሌላ ጨምሬ እመጣለ ኢንሻ አላህ።
አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
➤ ❝ግጥም ❞
በከላላ መስጂደ-ሰላም ላይ የቀረበ!!
✔️ ❝ቦረና” ይለያል❞,,,,,,።✔️
ሐጃዊራን ያንጫጫው ግጥም
🎙 ❝በኑረዲን አል አረቢ❞
t.me/nuredinal_arebi/16051
t.me/nuredinal_arebi/16051
Repost from የወረኢሉ ሙስሊም ወጣቶች ድምፅ
አንተ የሰው ልጅ ሆይ ከጌታህ ምን አታለለህ
👉ሰዎችን ወደ ደን የምንጠራበት መንገድ ምን መምሰል አለበት በሰፊው ተዳሷል
👉በተለይ እዚህ ወሎ አካባቢ ያሉ ቤተሰቦቻችንን እንደት ነው መጥራት ያለብን ?
👉በዳዕዋ ላይ እዝነት ማለት ምን ማለት ነው ተዳሷል
🎙 በሸህ ከማል መኪይ ሃፊዘሁላህ
🕌 ወረኢሉ ፉርቃን_መስጅድ
📝 ነሃሴ 15/2018 E.C
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6278
የሸህ ከማል መኪይ ሃፊዘሁላህ
ወረኢሉ_ፉርቃን መስጅ ያደረጓቼውን ዳዕዋዎች ለማገኘት ከ1_4
1👇👇👇👇👇
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6275
2👇👇👇👇
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6276
3 👇👇👇👇👇
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6277
4👇👇👇👇
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6278
Repost from የወረኢሉ ሙስሊም ወጣቶች ድምፅ
የመካነ ሰላምና የከላላ ወንድምና እህቶቻችን አዛኙ ጌታችን በእዝነቱ ይጠብቃችሁ እሱ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነውና 🤲✍️
