ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

前往频道在 Telegram

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

显示更多

📈 Telegram 频道 ከስነ-ፅሁፍ ዓለም 的分析概览

频道 ከስነ-ፅሁፍ ዓለም (@ethiobooks) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 10 339 名订阅者,在 书籍 类别中位列第 3 826,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 3 318 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 10 339 名订阅者。

根据 27 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 40,过去 24 小时变化为 3,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 9.92%。内容发布后 24 小时内通常能获得 3.05% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 026 次浏览,首日通常累积 315 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 5。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 28 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 书籍 类别中的关键影响点。

10 339
订阅者
+324 小时
+217 天
+4030 天
帖子存档
ተንኮለኛ / ነገረኛ 😏 😏 😏 ተንኮለኛ፣ ተሰባብሮ ተኛ። 😏 ነገረኛ ሰው፣ ከቤቱ አይሞትም። 😏 ከተንኮለኛ የዋህ አይወጣም። 😏 ነገረኛ፣ ታሞ አይተኛ። 😏 ተንኮለኛ ገደል፣ ዝንጀሮን ይጥላል
ተንኮለኛ / ነገረኛ 😏 😏 😏 ተንኮለኛ፣ ተሰባብሮ ተኛ። 😏 ነገረኛ ሰው፣ ከቤቱ አይሞትም። 😏 ከተንኮለኛ የዋህ አይወጣም። 😏 ነገረኛ፣ ታሞ አይተኛ። 😏 ተንኮለኛ ገደል፣ ዝንጀሮን ይጥላል፣ በሬን ያሳልፋል። 😏 ለነገረኛ ሰው፣ ጀርባህን ስጠው። 😏 አያስብ ቀበኛ፣ ተንኮለኛ። 😏 ነገረኛ ዝንጀሮ፣ ውሻ ታረባለች። 😏 ለተንኮለኛ ሲሉ ይሰበሰባሉ፣ ለቅን ይፈርዳሉ። 😏 ለነገረኛ ነገር ተውለት፣ ለሆዳም ምግብ አቅርብለት። 😏 ተንኮለኛ ሲጎዳ እየተራቀቀ፣ ጎርፍ ሲወስድ እያሳሳቀ። 😏 ከነገረኛ ሰው ስንቅ አይደባልቁም። 😏 ተንኮለኛ መበለት፣ በጦም ዶሮ፣ በፋሲካ እልበት። 😏 ነገረኛ ሰው ሲሞት፣ 'ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ' ይላል። 😏 ተንኮለኛ ናቸው፣ አርቃችሁ ቅበሯቸው። 😏 😏 ነገር በምሳሌ @ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

ቃል ኪዳን ━✦━ (ተረት ተረት) ✍ ካሕሳይ ገ/እግዚአብሔር ' ድኩላና ነብር በጓደኝነት ለመኖር ተስማሙ፤ ለዚህም የስምምነት ውል ተዋዋሉ (ቃል ኪዳን ተገባቡ)። በውሉ መሠረት ነብር ድኩላውን ላይበላውና ይልቁንም ከሌሎች ጠላቶች ሁሉ ሊከላከልለት ቃል ገባለት። በዚህ ውል መሠረት ቅጠል በረገፈና ኮሽታ በሰማ ቁጥር ነፍሱን እያስጨነቀ ይኖር የነበረው ድኩላ ያለ ስጋት በልቶ መተኛት ቻለ። ባጭር ጊዜ ውስጥም ሰውነቱ ወፍሮ ወዙ ከሩቅ ያብለጨልጭ ጀመር። ነብር ይህንን እያየ አላስችል አለው። አንድ ቀን ሁለቱ ጓደኛሞች ውኃ ለመጠጣት ወንዝ ወረዱ። ውኃ ጠጥተው ወንዝ ዳር አረፍ እንዳሉ ነብር ድኩላን «ስማ! ቃል ኪዳን ያፈረሰ ምን ይሆናል?» ብሎ ይጠይቀዋል። ድኩላም «እርሱ ምንም ላይሆን ይችላል። ውሎ አድሮ ግን የሠራው ግፍ በልጆቹ፣ ካልሆነም በልጅ ልጆቹ መድረሱ አይቀርም» ብሎ መለሰለት። ነብሩ ይህንን እንደሰማ በሆዱ "እኔ በልቼ ልጥገብ እንጂ ልጆቼ የራሳቸው ጉዳይ" አለና ዘሎ በድኩላው ላይ ተከመረበት። ያለ ምንም ስጋት ኃይሉን ያጠነከረው ድኩላ ከመቅጽበት በመፈናጠር በሹል ቀንዶቹ የነብሩን ሆድ እቃ ተረተረው። ባላሰበው ሁኔታ ከሞት አፋፍ ላይ የወደቀው ነብር በጣር ድምፅ «ምነው ድኩላ? ቃል ኪዳን ያፈረሰ በልጆቹ ካልሆነም በልጅ ልጆቹ ይደርሳል አላልከኝም ነበር?» ቢለው፤ ድኩላ «አባትህ፣ አያትህና ቅድመ አያቶችህ ቃል ኪዳን በማፍረስ ግፍ ሠርተው ይሆናላ!» ብሎት ወደ ሠፈሩ አመራ። ━━━━━━━━ 📔 ኅብረ - ብዕር አንደኛ መጽሐፍ 🗓 2009 ዓ.ም. 📄 59 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

💬 ❝በአእምሮህ ስትሠራ የሕዝብ ገዢ ትሆናለህ፤ በጉልበትህ ስትሠራ ደግሞ ሕዝብ ይገዛሃል።❞ ካህሊል ጂብራን 💬 ❝የሕይወት ብቸኛው መባቻ፣ ለመሆን የምንችለውን ነገር መሆን ነው።❞ ቤኔዲክት ስፒኖዛ
💬 ❝በአእምሮህ ስትሠራ የሕዝብ ገዢ ትሆናለህ፤ በጉልበትህ ስትሠራ ደግሞ ሕዝብ ይገዛሃል።❞ ካህሊል ጂብራን 💬 ❝የሕይወት ብቸኛው መባቻ፣ ለመሆን የምንችለውን ነገር መሆን ነው።❞ ቤኔዲክት ስፒኖዛ 💬 ❝የአንድ ሰው የወደፊት ዕጣ የሚወሰነው ስለ ራሱ በሚኖሩት ዕሳቤዎች ነው።❞ ሄንሪ ዴቪድ ቶሮ 💬 ❝የሕዝብ ገንዘብ እንደ ፀበል ነው፤ ማንም ሰው እየተነሳ ካልወሰድኩ ይላል።❞ የሕንድ አባባል 💬 ❝ለስኬታችንም ሆነ ለውድቀታችን ከፊት ለፊታችን ከተጋረጡ ማናቸውም ጉዳዮች ጋር ለንፅፅር በማይቀርብ መልኩ አመለካከታችን ወሳኙን ሚና ይጫወታል።❞ ኖርማን ቪንሰንት ፒል 💬 ❝የራስ ስብዕና ለሕይወት ዕጣ ወሳኝ ዳኛ ነው።❞ ሳይረስ 💬 ❝እስከ ጨረቃ ውልደት ድረስ ይተኛል፣ ቀን በፀሐይዋ ሙቀት ሊዝናና ይወጣል፣ ኑሮውን በሙሉ "ነገ እሠራዋለሁ" ሲል ያሳልፈዋል፤ ምንም ነገር ሳይሠራ ይሞታል።❞ ጀምስ አልበሪ 💬 ❝አንድ ሕዝብ እርስ በርሱ የሚተሳሰረው እርስ በርሱ በሚጋራቸው እምነቶችና አመለካከቶች ነው። በማኅበረሰብ ውስጥ እንደ ወረርሽኝ ከሚቀሰቀሱ ግጭቶች ለመዳን የሚያስችላቸውም ይኽ ትስስር ነው። አንድ ሕዝብ ለዛ፣ ጥሩ መንፈስ፣ ሀቅ፣ የሥነ-ምግባር ዘዬና የፅናት አቋም የሚያገኘውም በዚህ ነው።❞ ጆን ጋርድነር 💬 💬 ጥቅሶች @ethiobooks

💬 ❝በአእምሮህ ስትሠራ የሕዝብ ገዢ ትሆናለህ፤ በጉልበትህ ስትሠራ ደግሞ ሕዝብ ይገዛሃል።❞ ካህሊል ጂብራን 💬 ❝የሕይወት ብቸኛው መባቻ፣ ለመሆን የምንችለውን ነገር መሆን ነው።❞ ቤኔዲክት ስፒኖዛ
💬 ❝በአእምሮህ ስትሠራ የሕዝብ ገዢ ትሆናለህ፤ በጉልበትህ ስትሠራ ደግሞ ሕዝብ ይገዛሃል።❞ ካህሊል ጂብራን 💬 ❝የሕይወት ብቸኛው መባቻ፣ ለመሆን የምንችለውን ነገር መሆን ነው።❞ ቤኔዲክት ስፒኖዛ 💬 ❝የአንድ ሰው የወደፊት ዕጣ የሚወሰነው ስለ ራሱ በሚኖሩት ዕሳቤዎች ነው።❞ ሄንሪ ዴቪድ ቶሮ 💬 ❝የሕዝብ ገንዘብ እንደ ፀበል ነው፤ ማንም ሰው እየተነሳ ካልወሰድኩ ይላል።❞ የሕንድ አባባል 💬 ❝ለስኬታችንም ሆነ ለውድቀታችን ከፊት ለፊታችን ከተጋረጡ ማናቸውም ጉዳዮች ጋር ለንፅፅር በማይቀርብ መልኩ አመለካከታችን ወሳኙን ሚና ይጫወታል።❞ ኖርማን ቪንሰንት ፒል 💬 ❝የራስ ስብዕና ለሕይወት ዕጣ ወሳኝ ዳኛ ነው።❞ ሳይረስ 💬 ❝እስከ ጨረቃ ውልደት ድረስ ይተኛል፣ ቀን በፀሐይዋ ሙቀት ሊዝናና ይወጣል፣ ኑሮውን በሙሉ "ነገ እሠራዋለሁ" ሲል ያሳልፈዋል፤ ምንም ነገር ሳይሠራ ይሞታል።❞ ጀምስ አልበሪ 💬 ❝አንድ ሕዝብ እርስ በርሱ የሚተሳሰረው እርስ በርሱ በሚጋራቸው እምነቶችና አመለካከቶች ነው። በማኅበረሰብ ውስጥ እንደ ወረርሽኝ ከሚቀሰቀሱ ግጭቶች ለመዳን የሚያስችላቸውም ይኽ ትስስር ነው። አንድ ሕዝብ ለዛ፣ ጥሩ መንፈስ፣ ሀቅ፣ የሥነ-ምግባር ዘዬና የፅናት አቋም የሚያገኘውም በዚህ ነው።❞ ጆን ጋርድነር 💬 💬 ጥቅሶች @ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

ካህሊል ጂብራን - 2 የመጨረሻው!

ካህሊል ጂብራን - 1

▶ ካህሊል ጂብራን ━━━━━━ «ሊባኖሳዊው ባለቅኔ፣ ደራሲና ሰዓሊ» @ethiobooks
+1
▶   ካህሊል ጂብራን ━━━━━━ «ሊባኖሳዊው ባለቅኔ፣ ደራሲና ሰዓሊ»              @ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

ላንቺ ስል ═✦═ ✍አንዱዓለም ኪዳኔ ' "የተለየሽኝ 'ለት         እሞታለሁ ያልከው ውሸት ነበር እንዴ         የታለ የሞትከው?" ብለሽ የጠየቅሽኝ እኔስ ክልትው ባልኩኝ         ደሜ በፈሰሰ ፍቅርሽ ከልቤ አፀድ         መቼ ተፋለሰ ግና ከሞት አፋፍ         ተንጠልጥዬ ሳለሁ ለሰማይ ህይወትሽ         ላንቺ እጨነቃለሁ ታዲያ አትታዘቢኝ         አይግባሽ ቅያሜ በህይወት ስታዪኝ         ፊ'ለፊትሽ ቆሜ ሞትን ያልመረጥኩት         ደሜም ያልፈሰሰው ሲዖል እንዳትገቢ         ጦስ እንዳልሆንሽ ነው። ══════════ 📔 በዝናብ ቅጠሪኝ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

━ ፬ ━ >>> ከአፍታ በኋላ ከመንገዱ ጥግ ካለ ግቢ የነፍስ አባታቸው መምሬ ስብሀት ድንገት ወጥተው ከፊት ለፊታቸው ድቅን አሉ። መክሊት መብራቱን እያቻኮለች እንዳላየ ለመሄድ ስትጣደፍ መምሩ የክርስትና ስሟን እየጠሩ ተከተሏት። «እህተ ማርያም! ኧረ እህተ ማርያም!... ምንድነው የሚያስሮጣችሁ? እህተ ማርያም!! » መምሩ እየተጣሩ መጡ። «መምሩ...!!» ብሎ መብራቱ ወደሳቸው ዞረ። መክሊትም እየተሳቀቀች ወደሳቸው በግማሽ ዞረች። መምሩ መስቀል አውጥተው ካሳለሟቸው በኋላ ስለ መብራቱ ጤንነት እየጠየቁ አብረዋቸው ወደ ቤታቸው ማዝገም ጀመሩ። መክሊት መምሩን እንዴት አድርጋ እንዲለዩዋቸው ማድረግ እንደምትችል ግራ ገብቷት በጭንቀት ትከተላቸዋለች። «እኔ 'ምለው መምሩ...! ምነው በጠዋቱ ጋን ጋን ይሸታሉ? ትንሽ እንኳ ረፈድ ቢልልዎ ምን ነበረበት?» አለ መብራቱ በድንገት። መምሩ ድንግጥ አሉና፣ «ሀሀሀሀሀ አይ ልጄ! የክርስትና እኮ ነው። ጉሽ ጠላ ምናለው ብለህ ነው። ገብስ እኮ ነው። መጽሐፉም ቢሆን "ወይን ያስተፈስህ ልበ-ሰብ" አይደል የሚለው? ወይን እስኪገኝ ድረስ ጠላው ምን ይላል ብለህ ነው? ደሞ አልሰከርኩ!!» ዘላበዱ። «አይ መምሩ! ስንቴ ሰክረው ሲወላገዱ ሀገር ያይዎት የለ እንዴ? እዚህ ሰፈር እኮ "ከተማሩ እንደ ታምሩ፣ ከሰከሩ እንደ መምሩ!" እየተባለ ይቀለዳል፤ አልሰሙም ይሆን?» መብራቱ ልክ ተራ ወሬ እንደሚያወራቸው ረጋ ብሎ ነበር የሚያናግራቸው። መምሩ ድንገት ቱግ አሉ፤ «ደግ አደረኩ! ምን ይላል ይሄ... አጠጣኝ አልኩህ ታዲያ? ብጠጣስ ምን አለበት? አሹ አበጀሁ! እስቲ ምን ትሆን? ምን ያለው ነው አያ!... እርም ደጃችሁን ብረግጥ!» ብለው ጭራቸውን እየነሰነሱ ተቆናጥረው ሔዱ። መክሊት ይህ ሁሉ ሲሆን መግቢያ ቀዳዳው ጠፍቷት ትቅበዘበዝ ነበር። ሌላ ጦስ ይዞ ሳይመጣባት መብራቱን እያቻኮለች ወደ ቤታቸው አመሩ። መክሊት መጪው ጊዜ ፈታኝ እንደሚሆን ታውቋት ነበር። "እንዴት ብሎ ነው መብሬ ወደፊት ሥራውን የሚሠራው? እንዴት አድርጎስ ነው ከሰው ጋር የሚኖረው? ዶክተር ሙልተዘም 'ለሕይወት እጅግ አስፈላጊ' ያለውን ውሸት እንዴት አድርጎ መመለስ ይቻላል?" በሐሳብ ባከነች። እንደሁልጊዜው ተለባብሶ መኖርን እስኪለምድ - የውሸት መሳቅን፣ የውሸት ማልቀስን፣ የውሸት ሰላምታ መስጠትን፣ የውሸት 'ጀግና ነህ' ማለትን፣ የውሸት 'ገብቶኛል' ማለትን፣ የውሸት 'ታምሪያለሽ' ማለትን፤ መብራቱ እስኪለምድ፣ ጤንነቱ እስኪመለስ የቻለችውን ሁሉ ለማድረግ ለራሷ ቃል ገባች። የውሸት 'ግሩም ግብዣ ነው' ማለትን፣ የውሸት 'የሚደንቅ ሐሳብ ነው' ማለትን፣ የውሸት 'እንዴት ዓይነት ደግ ሰው ነህ' ማለትን እስኪለምድ . . . ስንት ዘመን ይፈጃል? ሐሳቡ ራሱ እንደ ጭራቅ አስፈራራት። ━━━━━━━━━━ 📔 በአራጣ የተያዘ ጭን 📄 5 - 10 🗓 2010 ዓ.ም. 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

━ ፫ ━ >>> አንድ ወፍራም ቦርጫም ሰውዬ ከተቀመጡበት ወንበር ጀርባ ሆኖ እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ፤ «እንዴ መብሬ! እንዴ መብሬ! እንኳን ለዚህ አበቃህ የኔ ጌታ!! መቼ ከሆስፒታል ወጣህ?» አለ። «ዛሬ መውጣቴ ነው!» አለ መብራቱ ረጋ ብሎ ሰውዬውን በትህትና እየጨበጠው። «እንኳን እግዜር አተረፈህ ወንድሜ። ሌላውን ቀስ ብለህ ትደርስበታለህ...» አለ ሰውዬው በማዳነቅ ዓይነት። «ኧረ ተመስገን ነው። በሕይወት መትረፉማ ነው ትልቁ ቁም ነገር!» አለ መብራቱ ረጋ ብሎ። መክሊት ደስ አላት። አነጋገሩ የተመጠነና የተረጋጋ በመሆኑ ቅድም የተከሰተው ዓይነት ችግር እንደማይደገም ተስፋ አደረገች። ነገሩ ሁልጊዜ የሚከሰት ላይሆን እንደሚችልም አሰበች። ከሰውዬው አነጋገር ከመብራቱ ጋር አንድ መሥሪያ ቤት እንደሚሠሩ ገምታለች። «ሥራ በቅርቡ ለመጀመር አሰብክ ታዲያ?» አለ ሰውዬው ወደ መብራቱ ጠጋ ብሎ። «እስቲ አንድ ሁለት ሳምንት ልረፍና አስብበታለሁ። አንተስ እየሠራህ ነው?» አለ መብራቱ። «አዎ! ይመስገን! መቼስ ኑሮ እንደምታየው ተወዷል። ዋናው ልጆቻችን አለመራባቸው ነው!» አለ ሰውዬው ተለሳልሶ። «እንዴ አንተማ ተመስገን በል እንጂ። ከአንድም ሁለት ሦስት ቤት አዲስ አበባ ውስጥ አለህ አይደል እንዴ? ለዚያውም ጂ-ፕላስ ቤቶች። በየቦታው የያዝከውስ መሬት?» «አይ ልጅ መብራቱ! የዘመድ ንብረት ያንተ ሊሆን አይችልም እኮ!» አለ ሰውዬው ሌላ የሚያውቀው ሰው በአካባቢው እንዳለ ለማረጋገጥ እየተገላመጠና ተጨናንቆ። «እንዴ ተው እንጂ! የዘመድማ አይደለም። ያንተ የራስህ ነው። ጉምሩክ ፍተሻ እየሠራህ 'ኤክስፓየር' ያደረገ ዘይት ለማስገባት ከነጋዴ ተስማምተህ 10 ሚሊዮን ነጭተህ የለም እንዴ?... ከዚያ ወዲህ እኮ ነው እንዲህ ቅልብ ፈረስ ያከልከው.. ሃሃሃሃሃሃ..» መብራቱ ዘለግ ላለ ጊዜ ሳቀ። የመብራቱን ንግግር በታክሲው ውስጥ ይሰሙ የነበሩ ሰዎች ወደ ሰውዬው ዞር እያሉ ገልመጥ አደረጉት። "አንተ ነህ ለካ በማይረባ ዘይት ሆዳችንን እያተራመስከን የምትገኝ! ቆይ ነብር ዐየኝ በል..፣ ደሞ እኛን መስሎ በታክሲ ይሳፈራል እንዴ? የሌባ ዓይነ ደረቅ..." የሚሉ ይመስላሉ ተሳፋሪዎቹ፣ በውስጣቸው። ሰውዬው ተጨነቀ። ሐሳብ ቢያስቀይርልኝ ብሎ፣ «ማነህ ረዳት! የሦስት ሰው ሒሳብ እንካ ተቀበል...!» ብሎ እጁን ሲዘረጋ ረዳቱ መከፈሉን ነገረው። «እንዴት ነው አሁንም ጉቦ እየበላህ ነው?» አለ መብራቱ ወደ ሰውዬው ዞሮ። ሰውዬው በድንጋጤ አመዱ ቡን ብሎ «ማነህ ረዳት..! ጫፍ ላይ ወራጅ! ወራጅ!» ብሎ ጮኸና መኪናው ሙሉ በሙሉ ሳይቆምለት ከታክሲው ዘሎ ወረደ። መክሊት የምትገባበት ጨንቋት ተሳቀቀች። ዶክተሩ የነገራት ችግር በፍፁም እስከዚህ ይደርሳል ብላ አልገመተችም ነበር። ሌላ ሰው እንዳያገኙ በሰቀቀን እየተገላመጠች እንዲሁ እንደተጨነቀች ከሰፈራቸው ደርሰው ወረዱ። ከታክሲው ቢወርዱም መክሊት ጭንቀቱ ከላይዋ ላይ አልወረደላትም። የሰፈራቸውን መግቢያ በሰቀቀን ቃኘች። በአጋጣሚ ብዙም የሚያውቁት ሰው አልነበረም። "እፎይ!" አለችና ከመብራቱ ጋር እጅ ለእጅ እንደተያያዙ በሰፈራቸው መግቢያ ወዳለው ድልድይ መሄድ ጀመሩ። >>> @ethiobooks

━ ፪ ━ >>> «እማማና አባባ እኮ ክበቡ ጋ እየጠበቁን ነው፤ እንዴት ናፍቀውኻል መሰለህ...? በተለይ ማማ በጣም ነው የናፈቀችህ...» አለች መክሊት በስስት እያየችው። «እናትሽን ተያቸው! እንደውም ዓይናቸውን ባላይ ደስ ይለኝ ነበር።..» አለ መብራቱ ክፍት ብሎት። «ለምን የኔ ጌታ? እንደልጇ እኮ ነው የምትወድህ...!» መክሊት የምትናገረው ጠፋባት። «እኔን እንደ ልጃቸው? አይምሰልሽ ተሳስተሻል! እንደውም ልንገርሽ? በጣም ባለጌ ናቸው!» መብራቱ ፍጹም ሳያመነታ በእርግጠኝነት ስሜት ነበር የተናገረው። «እ... ምን ማለትህ ነው?» መክሊት የሞት ሞቷን ጠየቀችው። «ኽም... ስንት ጊዜ መሰለሽ ያልሆነ ነገር እንድናረግ የጠየቁኝ። እኔማ "የልጅዎ ባል አይደለሁም ወይ...፣ እንዴት እንደዚህ ይጠይቁኛል?" ብዬ ስላቸው ምን እንዳሉ ታውቂያለሽ?" "እሷ የወጣችበትን ብትቀምሰው ምን አለበት? ቀረብህ!!" አይሉኝ መሰለች!! በጣም ነው ያስጠሉኝ!... አባትሽ ግን ደግና የዋህ ናቸው። አሁን እናትሽ ከዘበኛቸው ጋር ምን እንደሚያደርጉ ቢያውቁ ምን ይላሉ? ስል እጨነቃለሁ።» መክሊት ትንፋሽ አጠራት። ኡ! ኡ! ብላ መጮኽ አማራት። እናትና አባቷ ከክበቡ እነሱ ወዳሉበት ሲመጡ አስተዋለች። አባቷ መብራቱ የሚናገረውን ቢሰሙ የደም ብዛታቸው ተነስቶ እዚያው ፍግም እንደሚሉ ጥርጥር የለውም። ወደነሱ እየቀረቡ ሲመጡ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባት ቆረጠች። መብራቱን እያቻኮለች ከሕንፃው ኋላ ወሰደችው። በጓሮ በኩል አድርጋ ወደ ዋናው መንገድ ወጡ። አንድ ከርካሳ ሚኒባስ ታክሲ ሲመጣ ተመልክታ አስቆመችና መብራቱን እያቻኮለች ወደ ውስጥ አስገባችው። ደንግጣለች! ነገር ዓለሙ ተደበላልቆባታል! ዶክተር ሙልተዘም ያለው ነገር አሁን በደንብ ነው የገባት። በእናቷ ቅሌት ከማፈሯ የተነሳ ኢምንት ሆነች። መብራቱ ይኼን ሁሉ ችሎ መቀመጡ ለሱ ያላትን ክብር ከፍ ቢያደርገውም ሁልጊዜም ወጣትነት በሚሰማት እናቷ ላይ ቅናት አይሉት ቁጣ ብቻ የኾነ የብስጭት ችቦ በጭንቅላቷ ውስጥ ተቀጣጠለ። እቶን የተሸከመች ያህል አናቷ ነደደ። «እንዴት እንዲህ ታደርጋለች?!» ከእናቷ ጋር ያላት ግንኙነት እስከወዲያኛው ሲበጣጠስ ታወቃት። በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባት ስታስብ ከኋላ ወንበር ሞቅ ያለ ሰላምታ የሚያሰማ ድምፅ ሰምታ ዞር አለች። >>> @ethiobooks

ውሸትን ፍለጋ! ━━✦━━ ✍ ዮፍታሔ ካሳ ' ━ ፩ ━ «በጣም አዝናለሁ መክሊት! ባለቤትሽ በደረሰበት ግጭት በጣም የሚያሳዝን እና ምናልባትም የሚያስገርም ሊባል የሚችል የአንጎል ጉዳት እንዳጋጠመው ማረጋገጣችንን ስገልፅልሽ በእውነት በእውነት እያዘንኩ ነው።» አላት የእእምሮ ሊቀጠበብቱ ሐኪም ሙልተዘም አንገቱን ግራ ቀኝ እየነቀነቀ። «ማለት ዶክተር.. የ..የሚገርም ዓይነት ስትል?» መክሊት ግራ ገብቷት ተንተባተበች። «ላንቺ ቀለል ባለ ቋንቋ ለማስረዳት.. እ.. ምን ማለቴ መሰለሽ? እ.. ባለቤትሽ ከአሁን በኋላ እንደ ማንኛውም ጤነኛ ሰው የሚያስበውን ነገር ወይም ስሜቱን መደበቅ አይችልም። ይህ ማለት ደግሞ.. እም... ባጭሩ መዋሸት አይችልም ማለት ነው። ወይም ሁልጊዜ እውነተኛ ስሜቱን ብቻ ነው የሚያፀባርቀው።» «ዶክተር ይኼ ታዲያ... ምን ችግር አለው? ማለቴ እውነተኛ መሆንና ስሜትን በግልጽ መናገሩ ችግር አለው? ጤነኛ መሆን እንደውም ይኼ አይደለም እ..ን..ዴ..!» መክሊት ግራ ተጋብታ ንግግሯን አንጠልጥላ ተወችው። «እሱ ልክ ነሽ። ሁላችንም እውነተኛ መሆንና ግልጽነት እንፈልጋለን። ነገር ግን በሕይወታችን ው ስጥ የተወሰነ ውሸት.. ማለቴ ራሳችን ጋ የምናስቀራቸው ነገሮች ሊኖሩ ይገባል። የምናስበውን ሁሉ የምንናገር ከሆነ ትንሽ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። ያው ማኅበራዊ ሕይወት ለመኖር አለ አይደል...» ዶክተር ሙልተዘም እንዴት አድርጎ እንደሚያስረዳት እርግጠኛ አልነበረም። መክሊት በመኪና አደጋው ምክንያት ባለቤቷ ላይ ተፈጠረ የተባለው የአእምሮ ጉዳት ሊገባት አልቻለም። "ከእንግዲህ መዋሸት አይችልም" ብሎ ጉዳት እንዴት ያለ ነው? እውነተኛ መሆንን ማን ይጠላል? «ዶክተር ይቅርታ አድርግልኝና ያጋጠመውን ጉዳት እንደ ችግር ልወስደው አልቻልኩም። ምናልባት ስላልገባኝ ይሆናል። ግን እውነተኛ መሆን የሚበረታታ እንጂ የሚጠላ ነገር አልመሰለኝም።» አለች መክሊት ዶክተሩን ያስተባበለችው እንዳይመስለው ድምጿን ስጋት እየተጫነው። ዶክተር ሙልተዘም ከዚህ በላይ ሊያስጨንቃት አልፈለገም። በራሷ ጊዜ ሁኔታውን እንደምትደርስበት ገመተ። «አሁን ባለቤትሽን ለማግኘት ዝግጁ የሆንሽ ይመስለኛል። ብቻሽን ነው እንዴ ልትወስጂው የመጣሽው?» «አባቴና እናቴም አብረውኝ መጥተዋል። ውጪ ሆነው እየጠበቁን ነው...» አለችው መክሊት። ዶክተር ሙልተዘም የእናትና አባቷን መምጣት የወደደው አልመሰለም። ፊቱን ቅጭም አድርጎ ሲያስብ ከቆየ በኋላ ትከሻውን ሰብቆ ባለቤቷ ወደተኛበት ክፍል መክሊትን ይዟት ገባ። መብራቱ ውስጠኛው ክፍል ውስጥ ጋቢ ከላይ ደርቦ አንድ ወንበር ላይ ቁጭ ብሏል። መክሊት እንዳየችው ወደሱ ሮጣ አንገቱ ላይ ተጠመጠመችበት። ከጠበቀችው በላይ ተለውጧል። ጭንቅላቱን በመኪና አደጋ ሲገጭ ለሦስት ወራት ያህል ማንንም ለመለየት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። አሁን ግን ሙሉ በሙሉ የተሻለው ይመስላል። «መክሊትዬ በጣም ነበር የናፈቅኩሽ..» ብሎ አንገቷ ሥር ውሽቅ አለ። መክሊት የባለቤቷ ሁኔታ አንሰፈሰፋት። እሷም በጣም ናፍቃው ነበር። ተቃቅፈው ለደቂቃዎች ቆዩ። በዶክተሩ አስታዋሽነት ተላቀው ከሆስፒታሉ ወጡ። ዶክተር ሙልተዘም የመብራቱ ሁኔታ በጣም ያሳሰበው ይመስላል። የሆስፒታሉን ሕንፃ ለቀው ሲወጡ ከኋላ አተኩሮ ሲያስተውላቸው ቆየና አንገቱን እየነቀነቀ ወደ ቢሮው ገባ። ሆስፒታሉን ለቀው እንደወጡ መክሊት መብራቱን ከላይ እስከታች ቃኘችው። ትንሽ ጉስቁልቁል ብሏል፤ አንጀቷን በላት። የሆዷን በሆዷ ይዛ ልታጽናናው ፈለገች። «በጣም አምሮብኻል መብሬ...» አለችው። «አዎ! ተኝተን ይኼን ሾርባ እየጠጣን...።» አላት በግዴለሽነት። «እኔስ ተለወጥኩ?» አለችው። መብራቱ ከላይ እስከ ታች ቃኛትና፣ «ምንም አትዪም ግን ቦርጭ ጨመርሽ... በዚያ ላይ ቁመትሽ አጭር ስለሆነ እርጉዝ አይጥ መሰልሽ!» አላት ኮስተር ብሎ። መክሊት እየቀለደ መስሏት መጀመሪያ ፈገግ አለች። ፊቱ ላይ ቀልድ ስታጣ ግን ድንግጥ አለች። ይኼን አልነበረም የጠበቀችው። የዶክተር ሙልተዘም ማስጠንቀቂያ በጆሮዋ ማቃጨል የጀመረው በዚህ ጊዜ ነው። >>> @ethiobooks

sticker.webp0.08 KB

የሙሴ ዘመቻ - 2 የመጨረሻው!

የሙሴ ዘመቻ - 1