የጥበብ ማዕድ
📈 Telegram kanali የጥበብ ማዕድ analitikasi
የጥበብ ማዕድ (@alazartewodros1) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 14 617 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 876-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 435-o'rinni egallagan.
📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika
невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 14 617 obunachiga ega bo‘ldi.
02 Noyabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -363 ga, so‘nggi 24 soatda esa -11 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.
- Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
- Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 5.06% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 1.86% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
- Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 740 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 272 ta ko‘rish yig‘iladi.
- Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 8 ta reaksiya keladi.
📝 Tavsif va kontent siyosati
Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!
@Alazartewodros1
የጥበብ”
Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 03 Noyabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.
Ma'lumotlar yuklanmoqda
| Sana | Obunachilarni jalb qilish | Esdaliklar | Kanallar | |
| 03 Noyabr | 0 | |||
| 02 Noyabr | 0 | |||
| 01 Noyabr | 0 |
| 2 | ፡
እግዜር ለበደሌ
በምድር ሲሰጠኝ
ምህረት ያጣ ቅጣት
ካንቺ ጣለኝና
ሰማንያ ፈረምኩኝ
በመከረኛው ጣት
እና አሁን
እንዴት ነው ሚሰረዝ
እንዴት ነው ሚረሳ ታሪክ እንደ'ድሮ
ህመም ለሸመተ
ላሳደገ ወላጅ ሰላም አበ'ድሮ።
ለቀልድ ነው ጨጓራዬን ስል ባንቺ ምክንያት አይደለም።
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ) | 297 |
| 3 | ቀበሌና ብዙ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች ግን መሶብ ገብተው ለአመት ያህል ልምድ ቢወስዱ ጥሩ ነበር። ትንሽ ትህትናና ስራ ምን እንደሆነ ገብቷቸው እንዲመጡ!
#መሶብ_ሁርሶ! | 340 |
| 4 | ለሚያደርግልህ ነገሮች ሁሉ ጥፋተኝነት ከሚሰማው ሰው ራቅ መጨረሻው የበዛ ወቀሳ ነው። | 341 |
| 5 | ቃል ቀልጦ ተቀርፆ
ካስነሳ አንድ ሙት፡
ዝም ብሎ ያለውን
ተናገር አትበሉት....
ተግባር እርቃለች
ማን ይድረስ ተጉዞ፡
ሁሉ መካሪ ሆኗል
ዲስኩር ጢባጢቤ
ይመታል ጠልዞ፡
ስኬት ይመስለናል
ሱፍ መሀል መደበቅ፡
ሲያምረን አይን አናቅም
ሀሉን መነካካት...
ሁሉን ማጨማለቅ...
ደርሰን የት እንረፍ
ከአለም አዲስ አልቋል፡
መመሳሰል ብቻ
ጥሬው ከብስሉ
አንድ ላይ ታጭቋል፡
እውቀት አመለጠች
በቀዳዳ ወጥታ፡
መስከን መንናለች
በሀገሬው ሁካታ።
@dagi1u✍ገጣሚ ዳግም ግርማ
(ግርማዊ ዳግም) | 382 |
| 6 | በስተመጨረሻ መልካም ቀኖችና ብዙ ውለታዎች ይረሱና ጨካኝና መጥፎ ተብለህ ትጠራለህ። | 345 |
| 7 | ፡
የተዋቀረ እልፍኝ
በካስማ ምሶሶ
እንዳይሆን ፍርስራሽ
ድጋፍ ለቁመናው
የሰዎችን መኖር
ይፈልጋል ትንፋሽ!!!
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ) | 344 |
| 8 | "ከደሞዝ ቀን በቀር ሁሉ ነገር ይረሳል"!
"እንቅልፍ እና እድሜ" በእውቀቱ ስዩም | 388 |
| 9 | አቅመ ደካማው አጠገብ የተወጠሩ ጅማቶቹን በተደለደለ ሰውነት ላይ አሳየ! ይህ ግን ትልቅነቱ ከአዛውንቱ አንፃር ነበር። ሱ አንድ ሰዓት የስፖርት ስራ ከሚበልጡት ሚግ ተዋጊዎች ሚያስጥሉት መስሎታል። | 42 |
| 10 | መኖሩን ነበረን
ይተርፋል ለአዳም፡
ግን...ስብአዊነትን
ፍፁም አያስከዳም፡
በጦርነት ውሀ
መርከብ ለማንሳፈፍ፡
ሟቹ በዝቷል እና
ያመጣል መቀሰፍ፡
ሰላም ይሁንልን
አንፈልግም ወደብ፡
አንሙት ይቅርበን
ጊዜ መጥቷልና
የሚያሳጣን አደብ...
ለሞቱትስ ?...😭
@dagi1u | 459 |
| 11 | ከስር ወደ ላይ ነው
ደረጃ የሚካብ፡
ሲደባበቁብህ ተደብቀህ እለፍ
ልብ በል እንደ እባብ፡
ልክ እንደ መዶሻ
ልክ እንደ ሚስማር ጫፍ፡
ዝም በል ታገሰው
ያነቀህን መዳፍ፡
ከአለም አብልጠህ
ፈጣሪህን ካድም፡
ግርግር አታብዛ
ከፈረሱ በፊት ጋሪው እንዳይቀድም፡
ልጎሙን ጨብጠው
መሪህ ይሁን እምነት፡
ፍላጎትህ ታይቶ ይጨመራልና
የንሰሀ አመት...
ጎማውን አጠንክር
ህሊናህን ቅጣ፡
ብቻ ግን አደራ
ለመን-ገንዘብ-ብለህ
ከመስመር አትውጣ!።
@dagi1u✍ገጣሚ ዳግም ግርማ
(ግርማዊ ዳግም) | 411 |
| 12 | እጅግ ንፁህ ውሃ ህይወት የለበትም ለአሳዎችም አልተተወም! ለተለያዩ ሰዎች ግን መዝናኛ ነው። | 67 |
| 13 | ጫካውን ማቋረጥ የግድ ከሆነ አውሬውን ማላመድ ትልቁ ስራህ ነው። | 389 |
| 14 | :
ባለው ሰው ሲኮራ
ወደብ ባህር ጠቅሶ
እኛ ከማን አንሰን
ቀይ ደም ባህር አለን
ያልተገታ ለቅሶ!
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ) | 414 |
| 15 | ከባድ ሸክም ተሸክማቹ ታውቃላቹ? ሸክሙን ሚያሸክማቹ ሰው ከመሬት አንስቶ ትከሻቹ ላይ ካኖረ በኋላ የራሱን መንገድ ይጓዛል። ሸክም የተሸከመ ሰው Ultimate goalኡ ሸክሙን ሚጥልበት ቦታ ነው። ሸክሙ ከብዶት ወደ ሰማይ ማየት ተስኖት አቀርቅሮ መሬት መሬት እያየ እንኳን በምናቡ የሚያስበው የመጨረሻዋን ቦታ ነው።
ደሞም የሆነ ሰዓት አለ መጓዝ የሚያቅትህ፣ ላበት አይንህ ውስጥ ገብቶ የሚያቃጥልህ፣ መንገድ ማየት ተስኖህ ከሰው ጋ ስትጋጭ ያሰውም እያየ ገጭቶህ አንተን ጥፋተኛ አድርጎ የሚሰድብህ፣ ከሰውዬው ግጭት ተንገዳግደህ ሃይል የምትሰበስብበት፣ ምትጓዘውን energy በመንገዳገድ የሚያልቅብህ፣ ........
ደሞም ከሸክም የሚያስጠላው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ? «ሸክም ሲበዛብህ ህመምህ ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ መሆኑ ነው።»የሸክምህን ክብደትና የመጣህበት ሩቅ መንገድ ሳያውቁ የሚሳለቁብህን ችላ በላቸው፤ እነሱን ለማየት ስትዞር የዛለው አንገትህ ሊቀጭ ይችላል።
ሸክም የተሸከመ ሰው የሰው ብዛት ባለበት ቦታ አይጓዝም ምክኒያቱም መድረሻው ሩቅ ይሆንበታል። በመሃል እየተጓዝክ ሸክሙ ሲያስጨንቅህ ለማልቀስ ትፈልጋለህ.... ግን ለቅሶም energy ይፈልጋል ከአፍህና ከአፍንጫህ የሚወጣው ቁና ሚያሰፍር ትንፋሽ እንጂ የማልቀስ አቅም አይደለም።
አንድ ቀን ታርፋለህ አይዞህ መንገድህን ቀጥል።
✍️ Henok | 455 |
| 16 | ሀዘን የቤት ወገን
ደስታ መንገደኛ፡
እንግዳ ነው ለሀገር
ከሁሉ የሚተኛ፡
አለምን ግርግር
ገብስሶ ሲያምሳት፡
ታስተናግዳለች አዬ ልብ
ምስኪን ናት...
ደስታ የፋታ ወሬ
ሆያ ሆዬ ቁስል፡
ለካስ የሀዘን ፋታ ነው
እረፍትን የሚስል፡
በከንቱ መደለቅ
እንደ ዘለአለም ድል፡
እውነቱ...ሀዘን እየመራ
ደስታን ሊደብቅ ነው
የተሰጠው እድል።
@dagi1u✍ ገጣሚ ዳግም ግርማ
(ግርማዊ ዳግም) | 448 |
| 17 | በዚህ ዘመን ቁምነገርህ ቀልድ እንዳይሆን ቁምነገር አድርገህ አታውራው!
ቀልድህ ግን ተመልካች ካገኝ ቁምነገር ሆኖ ካንተ በላይ ታዋቂ ሆኖ ታገኘዋለህ። | 443 |
| 18 | 📚 ጥሪ ወደ ሞት 📚
📝ደራሲ:- አህመድ ሁስ ( ሻድ )
📜ይዘት:- እውነተኛ ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 141
📆 ዓ.ም :- 2018
🖨 ዕትም :- 13.9MB
💭Type :- #pdf #ጥሪ_ወደ_ሞት | 520 |
| 19 | ደገስኩልሽ
በደም እንባ ለቅሶ ወይን...
ተመልከቺው የእኔን አይን...
አልወደድሽልኝም ልፋቴን
ያጣፈጥኩትን ድግሴን፡
ልቤን ነበረ የቀቀልኩት
አላየሽም በእግር ማንከሴን?
አላየሸም መተናነሴን ?
ድር ማጌን ነካካው ትራፊ
የለበስኩትን ፈትለ በርኖስ፡
በራሴ ድግስ ጎዳ ዘግቼ
አልወጣም ድንበር ልክ እንደ ዋኖስ፡
የለሽም ቀርተሻል ለግብዣው
ድፍን ሀገር ተገኝቶ፡
ሀገሬ አንቺ ነሽ ቀልቤ ተሰቀለ
አንድ ሀገሩን አጥቶ፡
ጠምቄ ነበረ መጣሽ ብዬ
በደም እንባ ለቅሶ ወይን....
ግን አላየሽው የኔን አይን....
የለሽም በቦታው
ጀግና ነሽ እውነትም...
እንዳልድን... አቆሰልሽኝ አደል
አልሞ ተኳሽ ሰው አይሞትበትም።
@dagi1u✍ ገጣሚ ዳግም ግርማ
(ግርማዊ ዳግም) | 538 |
| 20 | ፡
እንዲ በላቸውማ…
የገፈተርነው ሰው
እንዴት ጸና ቢሉ
ለሰዎች ተረፈ
ከድጥ ጭቃ መሐል
ስለተረገጠ
ጉብታ ሆኖ ነው
ተመርጦ ያለፈ!
ገና አናበራለን አትገረምም!!!
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ | 494 |
