ru
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала EEP Communication

Канал EEP Communication (@eepcommuication) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 533 подписчиков, занимая 8 368 место в категории Технологии и приложения и 2 174 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 533 подписчиков.

Согласно последним данным от 30 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 10, а за последние 24 часа — -6, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 24.86%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 16.87% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 862 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 620 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 9.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
EEP Communication

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 01 июля, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Технологии и приложения.

15 533
Подписчики
-624 часа
-207 дней
+1030 день
Архив постов
photo content
+5

የዳሰነች ወረዳ አርብቶ አደሮች በተደረገላቸው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ መደሰታቸውን ገለፁ ....///.... የደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ የሲኤስ ክላስተር አርብቶአደሮች በተደረገላቸው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ መደሰታቸውን ገለፁ። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ክትትል ኮሚቴ በወረዳው የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው የምግብ እጥረት ሳቢያ ድጋፍ የተደረገላቸውን የሲኤስ ክላስተር ባዮ ቀበሌ አርብቶ አደሮችን ጎብኝቷል። የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ አብርሃም ምነ እንደተናገሩት የአየር ንብረት ለውጡ በሰዎችና በቤት እንስሳት ላይ የከፋ አደጋ ደቅኖ መቆየቱን አውስተዋል። የተደረገላቸው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ወቅቱን ያማከለ በመሆኑም ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ሥርጭቱን ላከናወነው ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ ቦሀልባ ምነ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፉ መደረጉ ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው ህፃናት ለሚበዙባቸው ቤተሰቦች ጭምር ሥርጭቱ መከናወኑን ገልፀዋል። እንደ እርሳቸው ገለፃ በቀበሌው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ያላገኙ ነዋሪዎች ቢኖሩም በጋራ የመካፈል ባህላችንን ተጠቅመን ድርቁን ለመከላከል ተችሏል። እስካሁን ለተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ቦሀልባ በቀጣይም ዘላቂ ድጋፍ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ወ/ሮ ኦቾሎ ገልቴ በበኩላቸው የተደረገላቸው የበቆሎ ዱቄት ከዚህ በፊት እየፈጩ የሚጠቀሙበትን ጊዜና ጉልበት እንደቆጠበላቸው ተናግረዋል። በቀበሌው የተደረገው የአልሚ ምግቦች ድጋፍ የወለዱ እናቶችን ጤና  ከማሻሻሉም በላይ ልጆቻቸውን እንዲያጠቡ እንዳገዛቸውም ነው የገለፁት። በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ኮሚቴ ከዳሰነች ወረዳ አስተዳደር አመራሮች ጋር በሰብዓዊ እርዳታ ሥርጭቱ ላይ በቱርሚ ከተማ ውይይት አካሒዷል። በውይይቱ ላይ የሰብዓዊ እርዳታ ሥርጭቱን አፈፃፀም አስመልክቶ ገለፃ ያደረጉት የወረዳው ተወካይ አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ሎጎዲቴ እንደተናገሩት በወረዳው የሚገኙ 68 ሺህ 593 አርብቶአደሮች የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፉ ተጠቃሚ ሆነዋል። በወረዳው በሚገኙ 40 ቀበሌዎች የቀረበው የእርዳታ መጠንና  የተረጂ አርብቶ አደሮች ቁጥር አለመመጣጠን በሥርጭቱ ሥራ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩን አቶ ታደሰ ተናግረዋል።  እንደ ተወካይ አስተዳዳሪው ገለፃ በወረዳው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከሃያ ሺህ በላይ አርብቶአደሮች ይገኛሉ። በ40 ቀበሌዎች የተከናወነው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሥርጭት ፍትሐዊ በመሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የወረዳው ምክር ቤት የቅርብ ክትትል ሲያደርግበት መቆየቱን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በወረዳው ላደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ምስጋናቸውን የገለፁት አስተዳዳሪው በቀጣይም የወረዳው አርብቶ አደሮች በዘላቂነት ድጋፍ በሚያገኙበት ዙሪያ ላይ ከተቋሙ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጊዜያዊ የእርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ኮሚቴ አባላት በበኩላቸው ተቋሙ በወረዳው ለሚገኙ አርብቶ አደሮች የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል። ተቋሙ በወረዳው የሚገኙ አርብቶ አደሮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችል የማህበራዊ ልማት ዕቅድ ጥናት እያከናወነ መሆኑንም ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጊዜያዊ እርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ኮሚቴ በዛሬው ዕለትም በኛንጋቶም እና ሀመር ወረዳ የአስቸኳይ ጊዜ የእርዳታ ድጋፍ በተደረገላቸው አካባቢዎች የመስክ ምልከታ ያካሂዳል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+5

photo content
+6