EEP Communication
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览
频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 533 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 338,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 162 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 533 名订阅者。
根据 29 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 6,过去 24 小时变化为 -1,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.10%。内容发布后 24 小时内通常能获得 16.85% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 901 次浏览,首日通常累积 2 619 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 8。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“EEP Communication”
凭借高频更新(最新数据采集于 30 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。
15 533
订阅者
-124 小时
-167 天
+630 天
帖子存档
15 533
የዳሰነች ወረዳ አርብቶ አደሮች በተደረገላቸው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ መደሰታቸውን ገለፁ
....///....
የደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ የሲኤስ ክላስተር አርብቶአደሮች በተደረገላቸው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ መደሰታቸውን ገለፁ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ክትትል ኮሚቴ በወረዳው የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው የምግብ እጥረት ሳቢያ ድጋፍ የተደረገላቸውን የሲኤስ ክላስተር ባዮ ቀበሌ አርብቶ አደሮችን ጎብኝቷል።
የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ አብርሃም ምነ እንደተናገሩት የአየር ንብረት ለውጡ በሰዎችና በቤት እንስሳት ላይ የከፋ አደጋ ደቅኖ መቆየቱን አውስተዋል።
የተደረገላቸው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ወቅቱን ያማከለ በመሆኑም ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ሥርጭቱን ላከናወነው ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አቶ ቦሀልባ ምነ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፉ መደረጉ ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው ህፃናት ለሚበዙባቸው ቤተሰቦች ጭምር ሥርጭቱ መከናወኑን ገልፀዋል።
እንደ እርሳቸው ገለፃ በቀበሌው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ያላገኙ ነዋሪዎች ቢኖሩም በጋራ የመካፈል ባህላችንን ተጠቅመን ድርቁን ለመከላከል ተችሏል።
እስካሁን ለተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ቦሀልባ በቀጣይም ዘላቂ ድጋፍ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ወ/ሮ ኦቾሎ ገልቴ በበኩላቸው የተደረገላቸው የበቆሎ ዱቄት ከዚህ በፊት እየፈጩ የሚጠቀሙበትን ጊዜና ጉልበት እንደቆጠበላቸው ተናግረዋል።
በቀበሌው የተደረገው የአልሚ ምግቦች ድጋፍ የወለዱ እናቶችን ጤና ከማሻሻሉም በላይ ልጆቻቸውን እንዲያጠቡ እንዳገዛቸውም ነው የገለፁት።
በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ኮሚቴ ከዳሰነች ወረዳ አስተዳደር አመራሮች ጋር በሰብዓዊ እርዳታ ሥርጭቱ ላይ በቱርሚ ከተማ ውይይት አካሒዷል።
በውይይቱ ላይ የሰብዓዊ እርዳታ ሥርጭቱን አፈፃፀም አስመልክቶ ገለፃ ያደረጉት የወረዳው ተወካይ አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ሎጎዲቴ እንደተናገሩት በወረዳው የሚገኙ 68 ሺህ 593 አርብቶአደሮች የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፉ ተጠቃሚ ሆነዋል።
በወረዳው በሚገኙ 40 ቀበሌዎች የቀረበው የእርዳታ መጠንና የተረጂ አርብቶ አደሮች ቁጥር አለመመጣጠን በሥርጭቱ ሥራ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩን አቶ ታደሰ ተናግረዋል።
እንደ ተወካይ አስተዳዳሪው ገለፃ በወረዳው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከሃያ ሺህ በላይ አርብቶአደሮች ይገኛሉ።
በ40 ቀበሌዎች የተከናወነው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሥርጭት ፍትሐዊ በመሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የወረዳው ምክር ቤት የቅርብ ክትትል ሲያደርግበት መቆየቱን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በወረዳው ላደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ምስጋናቸውን የገለፁት አስተዳዳሪው በቀጣይም የወረዳው አርብቶ አደሮች በዘላቂነት ድጋፍ በሚያገኙበት ዙሪያ ላይ ከተቋሙ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጊዜያዊ የእርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ኮሚቴ አባላት በበኩላቸው ተቋሙ በወረዳው ለሚገኙ አርብቶ አደሮች የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ተቋሙ በወረዳው የሚገኙ አርብቶ አደሮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችል የማህበራዊ ልማት ዕቅድ ጥናት እያከናወነ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጊዜያዊ እርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ኮሚቴ በዛሬው ዕለትም በኛንጋቶም እና ሀመር ወረዳ የአስቸኳይ ጊዜ የእርዳታ ድጋፍ በተደረገላቸው አካባቢዎች የመስክ ምልከታ ያካሂዳል።
"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
