ru
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала EEP Communication

Канал EEP Communication (@eepcommuication) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 533 подписчиков, занимая 8 368 место в категории Технологии и приложения и 2 174 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 533 подписчиков.

Согласно последним данным от 30 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 10, а за последние 24 часа — -6, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 24.86%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 16.87% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 862 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 620 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 9.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
EEP Communication

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 01 июля, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Технологии и приложения.

15 533
Подписчики
-624 часа
-207 дней
+1030 день
Архив постов
photo content
+2

በዞኑ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሥርጭት 97 በመቶ ተጠናቋል ……...///…….. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በደቡብ ኦሞ ዞን በአየር ንብረት ለውጥ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ አራት ወረዳዎች ያደረገው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሥርጭት 97 በመቶ መከናወኑን በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኦሞ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኦሞ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በሰብዓዊ እርዳታ ሥርጭቱ ላይ በጂንካ ከተማ ውይይት አካሒዷል። በውይይቱ ላይ የሰብዓዊ እርዳታ ሥርጭቱን አፈፃፀም አስመልክቶ ገለፃ ያደረጉት በማህበሩ የደቡብ ኦሞ ዞን የአደጋ ስጋትና ቅነሳ ቡድን መሪ ወ/ሮ ባህረወሰን ወ/አረጋይ እንደተናገሩት ድጋፉ በደቡብ ኦሞ ዞን በሐመር፣ ዳሰነች፣ ኛንጋቶም እና ሰላማጎ ወረዳዎች በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተከሰተውን የምግብ እጥረት በጊዜያዊነት ለመቅረፍ ያለመ ነው። በአራቱም ወረዳዎች በዕቅድ ከተለዩት 1 መቶ 54 ሺህ 512 ነዋሪዎች ውስጥ 1 መቶ 50 ሺህ 134ቱ የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፉ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። በወረዳዎቹ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን የምግብ እጥረት በጊዜያዊነት ለመቅረፍ ከተመረጡት 68 ቀበሌዎች ውስጥ በ67 ቀበሌዎች የሰብዓዊ እርዳታ ሥርጭቱ መከናወኑን የገለፁት ቡድን መሪዋ ቀሪው አንድ ቀበሌ በፀጥታ ችግር ምክንያት ሳይካተት መቅረቱን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዞኑ ያደረገው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንፃር ውጤታማ ሥራ መስራቱንም ጠቅሰዋል። እንደ ወ/ሮ ባህረወሰን ገለፃ የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የዞኑ አራት ወረዳ አርብቶ አደሮች 22 ሺህ 232 ነጥብ 5 ኩንታል በቆሎ፣ 149 ሺህ 723 ሊትር ዘይት፣ 22 ሺህ 264 ነጥብ 75 ኩንታል ባቄላ እንዲሁም 2 ሺህ 392 ነጥብ 73 አልሚ ምግቦች ተሰራጭቷል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከዚህ በፊት የሰብዓዊ እርዳታ ሥራዎች ተደራሽ አድርጎ በማያውቅባቸው እንደ መርሲና ባጫ ቀበሌዎች ላይ መድረስ የቻለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባደረገው የእርዳታ ድጋፍ አማካኝነት መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። የተበታተነ የሥርጭት ጣቢያ መኖር፣ የመንገድ ተደራሽነት ማነስ፣ ዝርፊያ ማጋጠሙ፣ የፀጥታ ችግር እና የተመረጡ ተጠቃሚዎች አለመገኘት በሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሥርጭቱ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዞኑ ላደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ምስጋናቸውን የገለፁት ወ/ሮ ባህረወሰን በቀጣይም በርካታ ሥራዎችን በጋራ ለመስራት ማህበራቸው ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጊዜያዊ የእርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ኮሚቴ አባላት በተመረጡት ዞኖች ማህበሩ ላከናወነው የሰብዓዊነት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል። በዞኖቹ የተከሰተውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ በተደረገው የሥርጭት ሥራ ላይ የነበሩትን የግልፀኝነት፣ ከስምምነት ማዕቀፉ ጋር ተያይዞም በአተገባበሩ ላይ የታዩ ችግሮችና የመረጃ ልውውጥ ክፍተቶች መታረም እንዳለባቸው አፅዕኖት ሰጥተው አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በደቡብ ኦሞ ዞን በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለተከሰተው የምግብ እጥረት ከሩብ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ማድረጉን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content

ከ90 በመቶ በላይ የተቋሙ ቋሚ ይዞታዎች ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አግኝተዋል ……..///….. በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ የተቋሙ ቋሚ ንብረቶች መካከል ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንዲያገኙ መደረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፋሲሊቲ መምሪያ ገለፀ፡፡ የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሺፋ እንደተናገሩት አብዛኛዎቹ የተቋሙ የኃይል ማመንጫዎች እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አልነበራቸውም፡፡ ባለፉት አራት ዓመታት በተከናወኑ ጠንካራ ሥራዎች ከ145 በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል፡፡ አቶ ከሊል እንደገለፁት የተቋሙን ንብረት በዘመነ መንገድ መያዝ እና መጠቀም እንዲቻል በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ማድረጊያ ሥርዓት ወይም በእንግሊዝኛ ምዕፃሩ IFRS መሰረት የንብረት ምዝገባ ተከናውኗል፡፡ ከኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ያልተጠናቀቁ የንብረት ክፍፍሎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ ንብረቶቹ ለሁለቱም ተቋማት ካላቸው ጠቀሜታ አንፃር እየተመዘኑ እንዲከፋፈል በተቋማቱ የበላይ አመራሮች አቅጣጫ መሰጠቱን አብራርተዋል፡፡ በሌላ በኩል በተቋሙ ገቢ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጫና እያሳደረ የመጣውን የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ስርቆት ለመከላከል ከክልል እስከ ቀበሌ ባሉ መዋቅሮች በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+2

በፕሮጀክቱ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ስርቆት ለመከላከል በትብብር መስራት ይገባል ……...///……... ለአዋሽ- ወልዲያ - ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየተገነባ ባለው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ እየተፈፀመ ያለውን ስርቆት በጋራ ለመከላከል ህብረተሰቡና የፀጥታ አካላት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ፕሮግራም-2 የፕሮጀክት አስተዳደር-1 ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ አባዲ እንደገለፁት ለአዋሽ- ወልዲያ - ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየተገነባ ባለው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ እየተፈፀመ ያለውን ስርቆት ለመከላከል በትብብር መስራት ይገባል፡፡ ሥራ አስኪያጁ በፕሮጀክቱ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ስርቆት መከላከል በሚቻልበት መንገድ እና እና በግንባታው ላይ እያሳደረ ስለሚገኘው ተፅዕኖ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዞን ሦስት ዋና አስተዳዳሪ ጋር ውይይት አካሂደዋል። ፕሮጀክቱ እንደተጀመረ ከካሳ ክፍያና ከአንዳንድ ግለሰቦች የግል ጥቅም ፍላጎት ጋር በተያያዘ የግንባታ ሥራውን የማስተጓጎል ሁኔታ ከመስተዋሉ ውጭ የስርቆት ወንጀሎች እንዳልነበሩ ነው አቶ ዮናስ ያስታወሱት። ከዚህ በፊት ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ከአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመመካከር መፍታት እንደተቻለ የጠቆሙት አቶ ዮናስ እየተስፋፋ የመጣውን የስርቆት ወንጀል በዚሁ አግባብ እልባት ሊሰጠው እንደሚገባም ተናግረዋል። በፕሮጀክቱ ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶችን ለመከላከል የአካባቢው ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት፣ ከሥራ ተቋራጩና ከተቋሙ ጋር በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ የዞኑ አስተዳደር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት ማከናወን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ በበኩላቸው ለህዝቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ለማከናወን አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራውን በአካባቢው ተሰሚነት ያላቸው የሀገር ሽማግሌዎች ከቀጣዩ እሁድ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ችግሩ በስፋት በሚስተዋልባቸው ቀበሌዎች በመዘዋወር ግንዛቤ እንዲሰጡ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+4

የድሬዳዋ ቁጥር 1 የማከፋፈያ ጣቢያ ለከተማዋ የኃይል አቅርቦት ቁልፍ ድርሻ እያበረከተ ነው ……..///……… የድሬዳዋ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያ ለከተማዋ እና በከተማዋ ለሚገኙ ፋብሪካዎች እስከ 56 ሜጋ ዋት ኃይል በማቅረብ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የጣቢያው ኃላፊ አቶ ሚካኤል አልይ ገለፁ፡፡ ኃላፊው እንደተናገሩት በ1952 ዓ.ም. ተገንብቶ እስከ 26 ሜጋ ዋት ኃይል መጠን ሲያቀርብ የቆየው ማከፋፈያ ጣቢያው የአቅም ማሳደግ ሥራ ከተከናወነለት በኋላ እስከ 56 ሜጋ ዋት ኃይል ማስተናገድ ችሏል፡፡ ይህም የድሬዳዋ ከተማና በከተማዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን የኃይል ፍላጎትን እንዲያሟላ አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ በኃይል ማስተላለፊያ መስመርና በማከፋፈያ ጣቢያ ኦፕሬሽን ዘርፍ የምስራቅ 1 ሪጅን የሰብስቴሽን ጥገና ባለሙያ ግርማ ደቻሳ በበኩላቸው እንደተናገሩት የድሬዳዋ ቁጥር 3 ማከፋፈያ ጣቢያ በ1987 ከተገነባና የድሬዳዋ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያ አቅም ማሳደግ ከተሰራለት ከ 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በከተማዋ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት የማስተናገድ አቅም ተፈጥሯል፡፡ የጣቢያው አቅም ማደግ የድሬዳዋ ከተማንና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን የኃይል ፍላጎት በመመለስ የምስራቅ ኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኔትወርክ እንዲሻሻል ማድረጉንም ባለሙያው ገልፀዋል፡፡ 23 ሠራተኞች ያሉት የድሬዳዋ ቁጥር 1 የማከፋፈያ ጣቢያ 22 ሜጋ ዋት ኃይል ለናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ እንዲሁም 34 ሜጋ ዋት ኃይል ለድሬዳዋ ከተማ በማቅረብ ላይ ይገኛል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+3