ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Tikvah-University

Tikvah-University

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Tikvah-University

Канал Tikvah-University (@tikvahuniversity) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 393 769 подписчиков, занимая 107 место в категории Образование и 12 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 393 769 подписчиков.

Согласно последним данным от 01 ноября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 1 688, а за последние 24 часа — -78, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 12.23%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 7.22% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 48 173 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 28 444 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 83.

📝 Описание и контентная политика

Описание канала не предоставлено.

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 02 ноября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Образование.

393 769
Подписчики
-7824 часа
-4527 дней
+1 68830 дней
Архив постов
ራያ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በይፋ መጀመሩን ገልጿል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) የተቋሙን የመጀመሪያ ቀን፣ የመጀመሪያ ክፍል መርሐግብር ዛሬ ጥቅምት 23/20
+2
ራያ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በይፋ መጀመሩን ገልጿል፡፡   የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) የተቋሙን የመጀመሪያ ቀን፣ የመጀመሪያ ክፍል መርሐግብር ዛሬ ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም አስጀምረዋል።   ራያ ዩኒቨርሲቲ የነባር ተማሪዎች እንዲሁም ነባር የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባን ከጥቅምት 16-18/2019 ዓ.ም ማከናወኑ ይታወቃል፡፡   @tikvahuniversity

#KUE ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር (Alumni Association) ምስረታ እያደረገ ነው። ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ (በቀድሞ መጠሪያው ኮተቤ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ
#KUE ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር (Alumni Association) ምስረታ እያደረገ ነው። ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ (በቀድሞ መጠሪያው ኮተቤ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ) ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች በሰርተፊኬት፣ በዲፕሎማ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ እና በዶክተሬት ዲግሪ (PhD) አስመርቋል፡፡   በዚህም የተቋሙ የቀድሞ ተማሪዎች https://forms.cloud.microsoft/r/bmmpzyWkhz ላይ በመግባት ምዝገባ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲተው ጠይቋል፡፡   ‌‎@tikvahuniversity

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት (English Language Improvement Centers) በጉራጌ ዞን ሥራ አስጀምሯል፡፡ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፈ
+2
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት (English Language Improvement Centers) በጉራጌ ዞን ሥራ አስጀምሯል፡፡   የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፈቃዱ እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሀሰን (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ፣ ያኣበሩስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በእምድብር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተቋቋሙትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት መርቀዋል።   ማዕከላቱ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛሉ ተብሏል።   ‌‎@tikvahuniversity

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ መድኃኒት ቤት (ሞዴል ፋርማሲ) በኮምቦልቻ ከተማ በይፋ አስመርቋል፡፡ የፋርማሲው ሥራ መጀመር፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥራቱን የጠበቀ መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የሚ
+2
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ መድኃኒት ቤት (ሞዴል ፋርማሲ) በኮምቦልቻ ከተማ በይፋ አስመርቋል፡፡   የፋርማሲው ሥራ መጀመር፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥራቱን የጠበቀ መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያስችል ነው ተብሏል። ‎ ‎ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከሰባት ዓመት በፊት በደሴ ከተማ የመጀመሪያውን የማኅበረሰብ መድኃኒት ቤት መክፈቱ ይታወቃል፡፡   ‌‎@tikvahuniversity

#ሎርካን_ሜዲካል_ኮሌጅ የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ሐኪሞችና ምሁራን ባለቤትነት የሚመራው ሎርካን ሜዲካል ኮሌጅ ምዝገባ ላይ ነው❗️ BSc Fields of Study: → Doctor of Medici
#ሎርካን_ሜዲካል_ኮሌጅ የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ሐኪሞችና ምሁራን ባለቤትነት የሚመራው ሎርካን ሜዲካል ኮሌጅ ምዝገባ ላይ ነው❗️ BSc Fields of Study: → Doctor of Medicine → Doctor of Dental Medicine → Bachelor of Dental Science → Nursing TVET Programs: → Dental Therapy → Nursing → Medical Laboratory → Pharmacy → Radiography ⭐️ የ CPD ማዕከል አገልግሎት! ☎️ 0913398780 / 0911596059 አድራሻ፦ CMC አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ ከ ICMC ጠቅላላ ሆስፒታል አጠገብ 📍 Addis Ababa, CMC Square, Behind Tsehay Real Estate, next to ICMC General Hospital Facebook: https://www.facebook.com/Lorcanmedicalcollege Tiktok: https://www.tiktok.com/@lorcan.medical.co

66ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ቅዳሜ ህዳር 05/2019 ዓ.ም ይጀመራል። 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 የድርጅቶች ሒሳብ አያያ
66ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ቅዳሜ ህዳር 05/2019 ዓ.ም ይጀመራል። 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 የድርጅቶች ሒሳብ አያያዝ ስርዓት ስልጠና በፒስችሪ ተደግፎ የሚሰጥ 👉 VAT፣ Excise Tax፣ የትርፍ ግብር፣ ዓመታዊ ግብር አሰራር እና ሪፖርት አቀራረብ እንዲሁም ሌሎችም የግብር ዓይነቶችን በተግባር እየሰሩ የሚሰለጥኑበት 👉 በተግባራዊ ዶክመንቶች ታግዞ የሚሰጥ ስልጠና። የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 ☎️   0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute

#MoE በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቱ የመግቢ
#MoE በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቱ የመግቢያ ቀናት ህዳር 01 እና 02/2019 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ህዳር 03/2019 ዓ.ም አጠቃላይ ገለጻ እና ህዳር 04/2019 ዓ.ም የመማሪያ መጻሕፍት ስርጭት እንደሚከናወን ተገልጿል። @tikvahuniversity

#ጥቆማ የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በደረጃ እና በዲግሪ መርሐግብር ሰልጣኞችን በመቀበል ላይ ይገኛል። ኢንስቲትዩቱ በዘመናዊ ወርክሾፖች የተደገፈ ተግባር ተኮር ስልጠና ይሰጣል። የስልጠና
#ጥቆማ የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በደረጃ እና በዲግሪ መርሐግብር ሰልጣኞችን በመቀበል ላይ ይገኛል። ኢንስቲትዩቱ በዘመናዊ ወርክሾፖች የተደገፈ ተግባር ተኮር ስልጠና ይሰጣል። የስልጠና መርሐግብር በቀን (መደበኛ)፣ በማታ እና በእረፍት ቀናት የስልጠና ፕሮግራሞች ከደረጃ 3-5 ● Hospitality ● Culinary Art ● Food & Beverage Control ● Bakery and Pastry በዲግሪ ፕሮግራም ● Hotel Management ● Tourism Management ● Event Management ● Culinary Art አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ (ገነት ሆቴል) ለተጨማሪ መረጃ፦ 0994011793 / 0115301811 / 0115308106 @tikvahuniversity

#ጥቆማ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር ኢንስቲትዩት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ ባገኘባቸው ሦስት የቴክኒክና የሙያ ዘርፎች ለ2019 ዓ.ም የስልጠና መርሐግብር ምዝገባ ጀምሯል፡
#ጥቆማ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር ኢንስቲትዩት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ ባገኘባቸው ሦስት የቴክኒክና የሙያ ዘርፎች ለ2019 ዓ.ም የስልጠና መርሐግብር ምዝገባ ጀምሯል፡፡ የስልጠና ዘርፎች ● Train Driving (Level 2 to Level 5) ● Rolling Stock Electrical & Electronics System Maintenance (Level 2 to level 5) ● Railway Signal & Communication System Installation and Maintenance (Level 1 to 5) መስፈርቶች ● ሰልጣኞች በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መስፈርት መሠረት የ12ኛ ክፍል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የመግቢያ ውጤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ● ለባቡር ካፒቴንነት (Train Driving) ሙያ ስልጠና ለመመዝገብ ሰልጣኞች የተረጋገጠ የሕክምናና የአካላዊ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ● ለምዝገባ ሲሔዱ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ እና አራት ፓስፖርት መጠን የሆኑ ፎቶግራፍች ልትይዙ ይገባል፡፡ የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም አድራሻ፦ አያት ደራርቱ አደባባይ፣ የባቡር ኢንስቲትዩት የስልጠና ማዕከል። ለተጨማሪ መረጃ፦ 0116390409 / 0114702047 @tikvahuniversity

#የፌሎውሺፕ_ጥቆማ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሕክምና ኮሌጅ በየተለያዩ የትምህርት ክፍሎቹ ብቃት ያላቸው አመልካቾችን ለ2027 ትምህርት ዘመን የፌሎውሺፕ ፕሮግራም መቀበል ይፈልጋል፡፡ የፌሎው
#የፌሎውሺፕ_ጥቆማ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሕክምና ኮሌጅ በየተለያዩ የትምህርት ክፍሎቹ ብቃት ያላቸው አመልካቾችን ለ2027 ትምህርት ዘመን የፌሎውሺፕ ፕሮግራም መቀበል ይፈልጋል፡፡ የፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ ክፍት የሆነባሀቸው መስኮች፦ ● የ Neonatology ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ➻ 3 ● የ Pediatric Cardiology ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ➻ 2 ● የ Pediatric Emergency & Critical Care ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ➻ 3 ● የ Pediatric Pulmonary & Critical Care ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ➻ 1 የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም አመልካቾች የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትናችሁ ያለፋችሁ መሆን ይጠበቅባችኋል። ይህ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ሠልጣኞች ዘመናዊና ጥራት ያለው ሕክምና፣ ትምህርት እና ምርምር እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል። (መስፈርቶችና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን https://web.facebook.com/sphmmc ላይ በመግባት ይመልከቱ፡፡) @tikvahuniversity

10ኛ ዙር የህንፃ ኤሌክትሪክ እና ሶላር ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ (Building Electric and Solar Panel Electric Installation) ስልጠና ነገ ሰኞ ጥቅምት 23/2019
10ኛ ዙር የህንፃ ኤሌክትሪክ እና ሶላር ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ (Building Electric and Solar Panel Electric Installation) ስልጠና ነገ ሰኞ ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ይጀመራል። 👉 የህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ከንድፈ ሃሳብ እስከ ተግባራዊ ዝርጋታ በወርክሾፕ የሚሰለጥኑበት 👉 የኤሌክትሪክ ዲዛይን አሰራር፣ አነባበብ እና ትርጉም በ AutoCAD Software ተደግፎ የሚሰጥበት 👉 የኤሌክትሪክ ወጪ ግምት አሰራር እና የውድድር ሰነድ ዝግጅት ያካተተ 👉 የሶላር ሲስተም ዲዛይንና የጭነት ስሌት እስከ ሶላር ፓነል ተከላ ተግባራዊ ስልጠና ያካተተ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 ☎️  0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute

#UoK ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በሦስት የትምህርት መስኮች የኦንላይን ማስተርስ ፕሮግራም መስጠት ሊጀምር ነው። የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ አካዳሚያዊ ውሳኔዎች አሳልፏል። በ
#UoK ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በሦስት የትምህርት መስኮች የኦንላይን ማስተርስ ፕሮግራም መስጠት ሊጀምር ነው። የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ አካዳሚያዊ ውሳኔዎች አሳልፏል። በዚህም ሦስት ሙሉ በሙሉ የኦንላይን ማስተርስ ፕሮግራሞች እንዲጀመሩ ወስኗል። አዲስ የሚጀመሩ የኦንላይን ማስተርስ ፕሮግራሞች፦ ● MBA in Energy ● MA in Energy Project Management ● MSc in Petroleum and Energy Economics በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና ዶክትሬት የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እንዲጀመርም ሴኔቱ ወስኗል። የቀድሞው የቀብሪደሃር ሆስፒታል የዩኒቨርሲቲው የማስተማሪያ ሪፈራል ሆስፒታል ሆኖ እንዲያገለግል ተወስኗል። ሴኔቱ በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው በተቋቋመው የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ኢንስቲትዩት (EIPE) ስር የተከፈቱ 19 የመጀመሪያ ዲግሪ እና 24 የማስተርስ ፕሮግራሞችን አጽድቋል። @tikvahuniversity

#WachemoUniversity ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት ለፕሬዝዳንት የአመራርነት ሥራ መ
+3
#WachemoUniversity ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት ለፕሬዝዳንት የአመራርነት ሥራ መደብ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ልምድ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ መሰየም ይፈልጋል። በዚህም ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ የተቀመጠውን ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታና መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጥቅምት 14/2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 22 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስረጃችሁን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር አስፈፃሚ ቢሮ ቁ. 32 እንዲሁም አዲስ አበባ፣ ሽሮ ሜዳ አካባቢ በሚገኘው የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ግቢ ባለው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ማመልከቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ስካን የተደረጉ ፒዲኤፍ ፋይሎችና ሶፍት ኮፒ መረጃዎች በኢሜል አድራሻ jemmahaji@gmail.com መላክ ይኖርባችኋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ 👉 0913448421 (ዝርዝር መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።) @tikvahuniversity

33ኛ ዙር የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ይጀመ
33ኛ ዙር የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ይጀመራል። 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ 👉 በተግባር ድረ-ገፆችን እና የሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት 👉 UI እና UX ዲዛይንን በፊግማ ያካተተ ስልጠና የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 ☎️  0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute

#ETEI የኢትዮጵያ የቴክኒክ ልሕቀት ኢንስቲትዩት በ2ዐ19 ዓ.ም በዋናው ግቢ በሪሚዲያል ፕሮግራም፣ በደረጃ VII (ማስተርስ) እና በደረጃ VIII (ፒ.ኤች.ዲ.) ለመማር የተመለመላችሁ ሰልጣኞች የ
#ETEI የኢትዮጵያ የቴክኒክ ልሕቀት ኢንስቲትዩት በ2ዐ19 ዓ.ም በዋናው ግቢ በሪሚዲያል ፕሮግራም፣ በደረጃ VII (ማስተርስ) እና በደረጃ VIII (ፒ.ኤች.ዲ.) ለመማር የተመለመላችሁ ሰልጣኞች የቅበላ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑንና ጥሪ እስከሚደረግ ሰልጣኞች በትግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል። በዋናው ግቢ በደረጃ VI (የመጀመሪያ ዲግሪ) የተመለመላችሁ ሰልጣኞች ትምህርት ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል። (ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።) @tikvahuniversity

#AksumUniversity አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከተማሪዎች ጊዚያዊ ምደባ ጋር በተያያዘ አጠር ያለ ማብራሪያ በተቋሙ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አውጥቷል፡፡ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች
#AksumUniversity አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከተማሪዎች ጊዚያዊ ምደባ ጋር በተያያዘ አጠር ያለ ማብራሪያ በተቋሙ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አውጥቷል፡፡ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2019 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው አዲስ የተመደቡ ተማሪዎች፣ በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዚያዊነት መመደባቸው ይታወቃል። ከዚህ ጋር በተያያዘ “ተመልሰን በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችንን መቀጠል እንችላለን ወይ” የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች እየቀረቡለት እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ በዚህም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች፣ ትምህርታችሁን በአክሱም ዩኒቨርሲቲ "መቀጠል የምትችሉ መሆኑን" ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ጥቅምት 24 እና 25/2019 ዓ.ም ሁሉንም ነባር እና አዲስ ተማሪዎች ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል። @tikvahuniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ.ም የተመደቡለትን አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት መቀበል ጀምሯል። ለተያዘው ትምህርት ዘመን የተመደቡለትን ከ1,800 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በመቀበል ላይ እንደ
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ.ም የተመደቡለትን አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት መቀበል ጀምሯል። ለተያዘው ትምህርት ዘመን የተመደቡለትን ከ1,800 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በመቀበል ላይ እንደሚገኝ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። @tikvahuniversity

#MekdelaAmbaUniversity በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 03 እና 04/2019 ዓ.ም መሆኑን
#MekdelaAmbaUniversity በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 03 እና 04/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ● የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ (ጊምባ ካምፓስ) ● የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በመካነ-ሰላም ካምፓስ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ● የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ● የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ● መጠኑ 3×4 የሆነ አራት ፎቶግራፍ፣ ● የፋይዳ መታወቂያ (Digital ID) ፣ ● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ። @tikvahuniversity

#UoG በ2019 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለመከታተል በትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 01 እና 02/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው
#UoG በ2019 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለመከታተል በትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 01 እና 02/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት ህዳር 04/2019 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ የሁሉም የማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ምዝገባ በአጼ ፋሲል ግቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ● የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ● የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ● መጠኑ 3×4 የሆነ 2 ፎቶግራፍ፣ ● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ። @tikvahuniversity

#የፌሎውሺፕ_ጥቆማ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሕክምና ኮሌጅ በየተለያዩ የትምህርት ክፍሎቹ ብቃት ያላቸው አመልካቾችን ለ2027 ትምህርት ዘመን የፌሎውሺፕ ፕሮግራም መቀበል ይፈልጋል፡፡ የፌሎው
#የፌሎውሺፕ_ጥቆማ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሕክምና ኮሌጅ በየተለያዩ የትምህርት ክፍሎቹ ብቃት ያላቸው አመልካቾችን ለ2027 ትምህርት ዘመን የፌሎውሺፕ ፕሮግራም መቀበል ይፈልጋል፡፡ የፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ ክፍት የሆነባሀቸው መስኮች፦ ● የ Neonatology ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ➻ 3 ● የ Pediatric Cardiology ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ➻ 2 ● የ Pediatric Emergency & Critical Care ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ➻ 3 ● የ Pediatric Pulmonary & Critical Care ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ➻ 1 የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም አመልካቾች የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትናችሁ ያለፋችሁ መሆን ይጠበቅባችኋል። ይህ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ሠልጣኞች ዘመናዊና ጥራት ያለው ሕክምና፣ ትምህርት እና ምርምር እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል። (መስፈርቶችና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን https://web.facebook.com/sphmmc ላይ በመግባት ይመልከቱ፡፡) @tikvahuniversity