ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Открыть в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
900
Подписчики
-124 часа
-177 дней
+3530 дней
Архив постов
የራስዎንም ይሁን የልጆችዎን ስሞች ከሸሪዐህ ጋር የማይፃረሩ አለመሆናቸውን አስረግጠዋልን? በቤታችን ወይም በአካባቢያችን በተለያዩ ምክንያቶች በእምነታችን የማይፈቅዱ ስሞች በብዛት ያጋጥማሉ፡፡ በብዛት እነዚህ የተሳሳቱ ስሞች የሚወጡት ለጉዳዩ ኢስላም የሚሰጠውን ቦታ ስለማያውቁ በግዴለሽነት፣ ከጎረቤት፣ ከዜና ወይም ከፊልም ላይ ያዩትን እንዳመጣላቸው በመሰየም ሲሆን አንዳንዱ ደግሞ “አበጀሁ” ብሎ ጥፋት ላይ የሚወድቅ አለ፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን እርማት የሚሹ ስሞችን ልናርም ይገባናል፡፡ በተለይ ደግሞ ልጆቻችን ህጋዊ ማስረጃዎቻቸው (ዶክሜንቶቻቸው) ላይ አላስፈላጊ ስም ሰፍሮ ሁሌ ምቾት ከሚነሳቸው በጊዜ ልናርመው ይገባናል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተለያዩ ስሞችን በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረዋል፡፡ ለምሳሌ “ዓሲያህ” (በሷድ ፊደል) የሚለውን ስም በጀሚላህ ቀይረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] “አልዓስ” የሚባለውን “ሙጢዕ” ብለው ሰይመውታል፡፡ [ሙስሊም] እንዲሁም “ዐዚዝ” የሚለውን “ዐብዱርረሕማን” ብለው ቀይረውታል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 904] ሌሎችም አሉ፡፡ ለመሆኑ የማይፈቀዱ ስሞችን መለያ ጥቅል መርህ ይኖራልን? ከተለያዩ ምንጮች ያገኘሁት መረጃ ይህን ይመስላል፡- 1. እያንዳንዱ አስቀያሚ ወይም መጥፎ መልእክት ያዘለ ስም ሁሉ ክልክል ነው፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “አልዓሲ” (ወንጀለኛ)፣ “ዐትላህ” (አረመኔ)፣ “ሸይጧን”፣ “ጉራብ” (ቁራ)፣ “ሐርብ” (ጦርነት) እና መሰል ስሞችን ቀይረዋል፡፡ ከዚህም በመነሳት መጥፎ መልእክት ያላቸው ስሞች እንደማይፈቀዱ ዓሊሞች ይጠቅሳሉ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስቀያሚ ስም ሲሰሙ በጥሩ ስም ይቀይሩት ነበር፡፡ [ሶሒሑልጃሚዕ፡ 4743] 2. እንደ “አልቁዱስ”፣ “አርረሕማን”፣ “አልሙሀይሚን”፣ … ያሉ የአላህ ብቻ መጠሪያ የሆኑ ስሞችንም በምንም መልኩ ለፍጡር መጠሪያነት ልናውል አይገባም፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “አቡልሐከም” የሚለውን “ኩንያ” “አቡ ሹረይሕ” ሲሉ ቀይረውታል፡፡ [ኢርዋኡልገሊል፡ 2615] “ንጉሰ ነገስት” እና መሰል ስያሜዎችም ከዚሁ ስር ይካተታሉ፡፡ 3. ግብረ-ገብነትን የሚፃረሩ፣ ስሜት ቀስቃሽ ስሞችም አይፈቀዱም፡፡ ለምሳሌ፡- ኑሃድ (ጡቷ ወጣ ወጣ ያለች ሴት ለማለት ነው)፣ ጋዳህ (ለስላሳ እና ምቹ የሆነች ሴት ለማለት ነው)፣ ፊትናህ፣ ፋቲን፣ ዐቢር፡፡ በሀገራችንም ተቀራራቢ ወይም የከፋ መልእክት ያላቸው ስሞች አሉ፡፡ 4. ለፍጡር ባርነትን ወይም በደጋጎች ላይ ድንበር ማለፍን የሚያመላክቱ ስሞችን ማውጣትም እንዲሁ ተገቢ አይደለም፡፡ ለምሳሌ “ዐብዱርረሱል” (የረሱል ባሪያ)፣ “ዐብዱልከዕባህ”፣ “ዐብዱልሑሰይን”፣ …፡፡ እንዲህ አይነቱ ስም ሐራም በመሆኑ ላይ ኢጅማዕ እንዳለበት ኢብኑ ሐዝም ረሒመሁላህ ጠቅሰዋል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አይነት ስሞችን ቀይረዋል፡፡ 5. ውዳሴና ማጥራራት ያለባቸው ስሞችም እንዲሁ አይፈቀዱም፡፡ ለምሳሌ “ዒዘዲን”፣ “ናሲሩዲን”፣ “ሙሕዩዲን”፣ “ኢማን”፣ “ኢስላም”፣ “ተቅዋ”፣ “ሰይፈልኢስላም”፣ “ኸይረድዲን”፣ “ኑረላህ” እና የመሳሰሉት፡፡ እነዚህ ስያሜዎች ከእውነታ የራቀ ግነት የያዙ ናቸው፡፡ (በተለይ “ኑረላህ” የሚለው አላስፈላጊ መልእክት ሊያስተላልፍ ስለሚችል “ጥሩ አይደለም ሊቀየር ይገባል” ይላሉ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ፡፡) ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በርራህ” የምትባለዋን ሶሐቢያህ “ዘይነብ” ብለው መቀየራቸው ከግምት ይግባ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] እንዳውም በአንድ ወቅት ስሟን ከቀየሩ በኋላ አንዷ “በርራህ” ብላ ስትጣራ ሰምተው “እራሳችሁን አታጥራሩ!! ከናንተ ጋጠ-ወጧን ከክቡሯ ለይቶ የሚያውቀው አላህ ነው” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም] ጁወይሪያም እንዲሁ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀይረውት እንጂ “በርራህ” ነበር ስሟ፡፡ [ሙስሊም] ከዑለማዎች በነዚህ ቅፅሎች የሚታወቁ መኖራቸው እንዳይሸውደን፡፡ ለምሳሌ ነወዊ “ሙሕዩድዲን”፣ ኢብኑ ተይሚያም “ተቅይዩድዲን” በሚል ቅፅል ቢታወቁም እነሱ ግን ይጠሉት እንደነበር ተወስቷል፡፡ ሸይኹልአልባኒ ረሒመሁላህ “ዒዝዘዲን፣ ሙሕዩድዲን፣ ናሲሩድዲን እና መሰል ስሞችን መሰየም አይፈቀድም” ይላሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 216] 6. ካፊሮች የሚታወቁባቸው የሆኑ ስሞችን መጠቀምም አይፈቀድም፡፡ ለምሳሌ ዮሐንስ፣ ቴዎድሮስ፣ ሮናልዶ፣ ሜሲ፣… 7. የጋጠ-ወጦች፣ የዘፋኞች፣ የፊልም ሰዎችን ስያሜ ሆን ብሎ ለልጆች ማውጣት ተገቢ አይደለም፡፡ 8. “በቁርኣን ስሞች እና በቁርኣን ምእራፎች መሰየምም እንዲሁ ከሚከለከሉ ስሞች ውስጥ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ‘ጧሀ’፣ ‘ያሲን’፣ ‘ሐሚም’፣ …፡፡ (ኢማሙ) ማሊክ፡ ‘ያሲን’ ብሎ መሰየም የተጠላ እንደሆነ አስፍረዋል፡፡ ‘ያሲን’ እና ‘ጧሃ’ ከነብዩ ስሞች ነው እያሉ መሀይማን የሚያወሱት ልክ አይደለም፡፡ እነዚህ ፊደሎች ልክ እንደ ‘አሊፍ ላም ሚም’፣ ‘ሓ ሚም’ እና መሰሎቻቸው የሚመደቡ ናቸው፡፡” ይሄ (8ኛው) ነጥብ ሙሉ ለሙሉ ከኢብኑልቀይዪም የተወሰደ ነው፡፡ [ቱሕፈቱልመውዱድ፡ 127] 9. በቃላቱ ውበት ተመርኩዞ በረካ የሚሻትባቸው ወይም “ተፋኡል” የሚታሰብባቸው የሆኑ “ምን ይሄ እንትን ነው? እንትን ነው እንጂ!” እያሉ ሰዎች ገልብጠው መጥፎ ግምት (ተሻኡም) የሚያሳድሩባቸው ስሞችም ክልክል ናቸው፡፡ እናም እንደ “የሳር”፣ “ረባሕ”፣ “ነጂሕ”፣ “አፍለሕ”፣ “በረካህ”፣ “ናፊዕ” እና መሰል ስሞችን እንድንርቅ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አሳስበዋል፡፡ [ሙስሊም፡ 5722-5724] 10. የሚወጣው ስም የኋላ ኋላ የልጁን ስነ-ልቦና የሚጎዳ፣ በእኩዮቹ የሚሾፍበት፣ የሚሳለቁበት ሊሆንም አይገባም፡፡ በየቋንቋው እንዲህ አይነት ስሞች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ፡- “ዘገየ”፣ “ሞቅያለው”፣ “እርገጤ” … አማርኛ ውስጥ ከሚገኙ ለሹፈት ከሚያጋልጡ ስሞች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ የዐረብኛ ስሞች በራሳቸው ጥሩ ይሆኑና በአካባቢው ቋንቋ ግን መጥፎ መልእክት ኖሯቸው ለተጠሪው መቸገር ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የአካባቢያችንን እውነታ ከግምት ልናስገባ ይገባል፡፡ ሸይኽ ኢብኑልዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ሰው ለልጁ ትልቅ ሲሆን የሚነወርበት፣ የሚንቋሸሽበት ያልሆነን ስም የመምረጥ ግዴታ አለበት፡፡ ምናልባት አባት የሆነ ስም ሊመስጠው ይችላል፡፡ ነገር ግን የኋላ ኋላ ልጁ የሚቸገርበት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም ወላጁ ለልጁ መቸገር መንስኤ ሊሆን ነው ማለት ነው፡፡ ሙእሚንን ማስቸገር ደግሞ ክልክልነቱ የታወቀ ነው፡፡ ስለሆነም ውብ የሆኑ እና አላህ ዘንድ የተወደዱ ስሞችን ሊመርጥ ግድ ይለዋል፡፡” [አሽሸርሑልሙምቲዕ፡ 7/495] 11. ልጆችን “ጂብሪል”፣ “ሚካኢል” … እያሉ በመላእክት ስም መሰየምን በተመለከተ ዑለማዎች የተለያዩ ሀሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ ኢብኑልዑሠይሚን ረሒመሁላህ ከነዚህ ሀሳቦች ውስጥ “የተጠላ ነው” ወደሚለው በማዘንበል “በነዚህ ስያሜዎች ልንሰይም አይገባም” ይላሉ፡፡ [አሽሸርሑልሙምቲዕ፡ 7/495] ሐቁ ምንም ይሁን ምን ከውዝግብ መራቁ ጥሩ ብልሃት ነው፡፡ 12. የሚወጣው ስም ለጆሮ እንግዳ ለምላስ ከባድ ባይሆን ተመራጭ ነው፡፡ ያለበለዚያ በአቅራቢያው ባሉ ሰዎች ዘንድ ተንሻፎ የመጠራቱ እድል ሰፊ ነው፡፡ የሆነ ቦታ “ቁርረተልዐይን” ለማለት ከብዷቸው “ቁራ” እያሉ እንደሚጠሩ ሰምቻለሁ፡፡ ተጠሪው ላይ የሚፈጥረውን ስሜት አስቡት፡፡ 13. አንዳንዱ ቃሉ ቁርኣን ላይ ስለሚገኝ ብቻ ምንም ሳያስተውል፣ መልእክቱን በቅጡ ሳይረዳ የሚሰይም አለ፡፡ ሸይኽ ኢብኑልዑሠይሚን ረሒመሁላህ ከ

12🔹#ابتدائيات_في_علم_النحو_للصغيرات س: ما هي الأمثلة الخمسة؟ يفْعَلَانِ، وتفعلان، ويفعلون، وتفعلون، وَتفعلين. س: ما هي الأسماء الخمسة؟ أبوك وأخوك وحموك وفوك وذو مال. س: ما إعراب: يذهبان؟ فعل مضارع مرفوع وعلامة رفعه ثبوت النون، وألف الاثنين فاعل. س: ائتي بهذا المثال(تضربان) على نفس نمط الأفعال السابقة في أول سؤال، فقط غيِّريه من(يفعلان..) إلى هذا، الله يفتح عليك؟ ج: يضربان، تضربان، يضربون، تضربون، تضربين. س: إيش نعرب(ألف الاثنين والاثنتين، وواو الجماعة وياء المخاطبة) في هذه الأمثلة؟ كلها فاعل. س: (مخلص) ما نوع هذه الكلمة؟ ج: اسم. س: (منتسبٌ) ما نوع هذه الكلمة؟ ج: اسم. س: أعربي(يخرجان)؟ فعل مضارع مرفوع وعلامة رفعه ثبوت النون.
جميع روابط قنوات الشيخة أم عبدالله بنت الشيخ مقبل الوادعي حفظها الله تعالى وغفر لها ولوالديها: https://alwadeia.blogspot.com/p/blog-page.html ●✺┈┈┈┈📖┈┈┈┈✺●

በዐረበኛ ቋንቋ ማውራትን መለማመድ قال شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله تعالى-: «واعلم أن اعتياد اللغة يؤثر في العقل، والخلق، والدين تأثيرا قويا بينا، ويؤثر أيضا في مشابهة صدر هذه الأمة من الصحابة والتابعين، ومشابهتهم تزيد العقل والدين والخلق. ‏وأيضا فإن نفس اللغة العربية من الدين، ومعرفتها فرض واجب، فإن فهم الكتاب والسنة فرض، ولا يفهم إلا بفهم اللغة العربية، وما لا يتم الواجب إلا به فهو واجب.» ​« (በዐረበኛ) ቋንቋ የመናገር ልምድ በአእምሮ፣ በሥነ-ምግባርና በዲን ላይ ግልጽና ጠንካራ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር እወቅ ። እንዲሁም የዚህችን ኡማ ቀደምቶች (ሶሃቦችንና ታቢዒዮችን) በመምሰል ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፤ እነሱን መምሰል ደግሞ አእምሮን፣ ዲንን እና ሥነ-ምግባርን ይጨምራል። ​በተጨማሪም ራሷ የአረብኛ ቋንቋ የሃይማኖቱ አካል ናት፤ እሷን ማወቅም ግዴታ (ፈርድ) ነው። ቁርዓንን እና ሱናን መረዳት ግዴታ ነው፤ እነሱን ደግሞ የአረብኛን ቋንቋ በመረዳት እንጂ መረዳት አይቻልም። ግዴታ የሆነ ነገር ያለ እሱ እንጂ የማይሞላባት የሆነ ነገር ደግሞ ፣ ያ ነገር ራሱ ግዴታ ይሆናል።» ሸይኹል እስላም ኢብኑ ተይሚያህ (رحمه الله) المصدر: اقتضاء الصراط المستقيم، جـ١، صـ٥٢٧ https://t.me/durusuabihizam

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎች ➖➖➖➖➖➖➖ ↩️💎 ‏من سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿 ➊ 💎الغسل ➋💎 الطيب ➌ 💎السواك ➍💎 لبس الجميل ➎💎 قراءة سورة الكهف ➏💎 التبكير لصلاة الجمعة ➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➊ 🌺መታጠብ ➋ 🌺ሽቶ መቀባት ➌🌺 ሲዋክ መጠቀም ➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ ➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን ➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት መጣድ ➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰 اللهم صل وسلم على نبينا محمد اللهم صل وسلم على نبينا محمد اللهم صل وسلم على نبينا محمد اللهم صل وسلم على نبينا محمد اللهم صل وسلم على نبينا محمد اللهم صل وسلم على نبينا محمد اللهم صل وسلم على نبينا محمد اللهم صل وسلم على نبينا محمد اللهم صل وسلم على نبينا محمد اللهم صل وسلم على نبينا محمد   በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !! የቴሌግራም ቻናል፦ =                 https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

👉ለውርደትህ 👉ለዝቅጠትህ 👉 ለድህነትህ 👉ለሁለቱም ሀገር ኪሳራህ መንስኤእናት አባትህ ብቻ ችላ ማለትህ ላንተ በቂ ነው ! በተለይ ያቺ ጎስቋላዋ እናትህ

በደዕዋ ላይ የተሰማራ ሰው ትልቅ አማና ነው የተሸከመው። ስለዚህ በአማናው ላይ ሐቀኛ ሊሆን ይገባል። የተብሊግ ቡድን በርካታ የዐቂዳ ችግሮች አሉበት። ይህንን እያወቀ፣ አስገዳጅ ሁኔታ ሳይገጥመው ይህንን ቡድን የሚያወድስ አካል ለተሸከመው የደዕዋ አማና የማይታመን አደራ በላ ነው። በተመሳሳይ ማመሀኛ ነገ ደግሞ የባሱ አንጃዎችንና ግለሰቦችን ከማወደስ አይመለስም። ከእንዲህ አይነት ሰው ላይ መማር አይገባም። * ችግራቸውን ባያውቅ ዑዝር ነበረው። ግን እንደሚያውቅ እያስረገጠ፣ "እነሱን ከፊቴ ስላየሁ ነው ይህንን ያደረግኩት" የሚል ሰው ጥፋቱን በቀጥታ አምኖ ከመመለስ ውጭ ለመሸዋወድ መሞከር የሚያዋጣ ምክንያት አይደለም። ወጣቶች ሆይ! የሸሪዐ እውቀት የአካደሚ ትምህርት አይደለም። ዲን ነው። ከማን እንደምትወስዱት እያስተዋላችሁ። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

📔رسالة نافعة،أصلها محاضرة ألقاها الشيخ العلاّمة د. محمد بن عمر بازمول 🤎 تم تفريغها، تحوي على تأصيلات و نصائح منهجية تربوية، بعنوان: 🖊↗️ منهج السلف في كيفية التعامل مع الانحرافات العقديـــــــة و المنهجيـــــــــــــــــــــــــــــــة↗️🖊 🔅https://t.me/RadioOnInsght

Repost from Dr. Seid Musa
❐ ( مـــن الاعتقـــادات الخـــاطئــــة ) ▪️ اعتقاد أن كفارة الحلف بالله هي صيام ثلاثة أيام ، وهذا غير صحيح . ▫️قال ابن عثيمين - رحمه الله - : فإن كفارة الحلف هي أن يختار الإنسان أحد هذه الأمور الثلاثة وهي : 1) إطعــــام عشرة مساكين . 2) أو كسوة عشـرة مساكين . 3) أو عتـــق رقبــــــــــــة . فمن لم يستطع على واحد من هذه الأمور الثلاثة مثل الفقير فإنه : يصــوم ثــــلاثـــــة أيــــــام . ▪️فمن كان قادرًا على إطعام عشرة مساكين أو كسوتهم أو عتق رقبة ، وصـــام ثـــلاثـــــة أيـــــــام بنيــــة الكفـــــارة فإن ذلك لا يُجزئه". ( تفسير سورة المائدة ؛ آية : ٨٩ ). = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/AbulbukhariSeid

በተክፊር ጉዳይ ላይ ከመጠን በላይ መሄድና ቸኩሎ ፍርድ መስጠት የሚያሳዩ መገለጫዎች፦ 1. የተክፊርን መስፈርቶችና ሸሪዓዊ መርሆች አለማወቅ፦ በአጠቃላይ የኩፍር ፍርድ (التكفير المطلق) እና *በተወሰነ ግለሰብ ላይ የሚሰጥ የኩፍር ፍርድ (تكفير المعيّن) መካከል ያለውን ልዩነት አለመረዳት። 2. የተክፊር ሁኔታዎችንና ከፍርዱ የሚከለክሉ ነገሮችን አለማጤን፦ አንድን የተወሰነ ሰው በኩፍር ለመፍረድ በቅድሚያ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ እና ይህን ፍርድ የሚያስቀሩ ምክንያቶች እንዳሉ አለመመርመር። 3. ሊተረጎሙ የሚችሉ ንግግሮችንና ተግባራትን ያለ ማረጋገጥ በቀጥታ እንደ ኩፍር መቁጠር፦ ወደ ታላላቅ የዕውቀት ባለቤቶች ሳይመለሱ፣ ሳይመረምሩና ሳያጣሩ ከባድ ፍርድ መስጠት። 4. በኢጅቲሃድ ወይም በመለያየት የሚታወቁ የፍቅህ ጉዳዮች ላይ የሚለያዩ ሰዎችን የኩፍርና የጥመት ሰዎች ማድረግ። 5. ያለ ግልጽ ማስረጃ ሙስሊሞችን በቢድዓ፣ በፊስቅና በኩፍር ፍርድ ላይ መቸኮል፤ ይህም ከአህሉ ሱና ወል ጀማዓ የጥንቃቄና የፍትሕ መንገድን ጋር የሚቃረን ነው። 6. ከዕውቀትና ከጥበብ ይልቅ ስሜትንና ዝንባሌን ማስቀደም፦ ምክንያቱም የተክፊር ጉዳይ በዲን ውስጥ እጅግ አደገኛ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ነው። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (رحمه الله) እንዲህ ብለዋል፦ “ማንም ሙስሊም ቢሳሳትና ቢሳሳት እንኳን፣ ማስረጃ እስኪቆምበትና እውነት እስኪገለጽለት ድረስ በኩፍር ሊፈረድበት አይገባም።” የአህሉ ሱና ወል ጀማዓ መንገድ በዕውቀት፣ በፍትሕ፣ በርህራሄና በጥንቃቄ ላይ የተመሠረተ ነው። ሰዎችን ያለ መብት በከባድ ፍርዶች ለመወሰን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም ተክፊር የሸሪዓ ፍርድ ስለሆነ መመለሻው ቁርአን፣ ሱናና እይታ ውስጥ የሚገቡ ዑለማዎች ግንዛቤ ነው።

ራሳቸውን ወደ ሱና በሚያስጠጉ አካላት ላይ በሰፊው ከሚታዩ ነውረኛ ተግባራት ውስጥ አንዱ ሰዎችን በተመለሱበት ጉዳይ መክሰስ ነው። አንድ ሰው ከሆነ የተሳሳተ አቋም ወይም ጥፋት ከተመለሰ ያንን ጉዳይ #እያወቀ ሆነ ብሎ በሱ ላይ የሚለጥፍ ሰው 1ኛ፦ ዋሾ ነው። 2ኛ፦ ውሸትን የደዕዋው መንገድ አድርጎ የያዘ መጥፎ ሰው ነው። 3ኛ፦ ዓላማው ዲን ሳይሆን ቂም ማወራረድና ብሸሸቅ ነው። ይሄ ነገር የሰውየውን መመለስ #ሳናውቅ ሊገጥመን ይችላል። መመለሱን ካወቅን በኋላ በተመለሰበት ጉዳይ መወንጀል ግን ያለ ወንጀሉ ሰውን መክሰስ ነው። ቡድናዊ ሽኩቻ ላይ ያነጣጠሩ "ረዶች" በብዛት ይሄ ችግር ጎልቶ ይታይባቸዋል። ሰውን በተመለሰበት ጥፋት መክሰስ ባልፈፀመው ጥፋት እንደ መክሰስ ነው። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል:- { وَٱلَّذِینَ یُؤۡذُونَ ٱلۡمُؤۡمِنِینَ وَٱلۡمُؤۡمِنَـٰتِ بِغَیۡرِ مَا ٱكۡتَسَبُوا۟ فَقَدِ ٱحۡتَمَلُوا۟ بُهۡتَـٰنࣰا وَإِثۡمࣰا مُّبِینࣰا } "እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሰሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ፡፡" [አልአሕዛብ: 58] ነብያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ من قال في مؤمنٍ ما ليس فيه أسكنه اللهُ رَدْغَةَ الخَبالِ حتّى يخرُجَ ممّا قال "በአማኝ ላይ የሌለበትን የተናገረ ሰው አላህ የጥፋት ማጥ ውስጥ ያኖረዋል፣ ከተናገረው ነገር እስከሚወጣ ድረስ።" [ሶሒሑ ተርጊብ: 2845] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

"ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር!" ~ እንዲህ ዓይነቱ መጃጃል በዲን ስም መፈፀሙ ያሳዝናል። ተሶውፍ ሌላ ዓለም ነው። አሁን ይሄ ትልቅ ዒባዳ ነው በሱ ቤት። በሃገራችንም ያለው የመንዙማ ጭፈራ ከመጠነኛ ልዩነት ውጭ ይሄው ራሱ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን መጃጀል ነው እንግዲህ "ነባሩ እስልምና" የሚሉት። ይሄ ነባር ሳይሆን ነብራራ ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

መውደድ በልክ ነው፣ መጥላትም! ~ መዋደድና መጠላላት በዘመናት ውስጥ ሊፈራረቁ ይችላሉ፡። ዛሬ የጠሉት ነገ ወዳጅ ሊሆን ይችላል። በተቃራኒውም እንዲሁ። ሲጣሉ ልክ ማለፍ ሲታረቁ ያሳቅቃል። ሲዋደዱ አቅልን መሳት ሲራራቁ ይቆጫል። ሁሉም በልክ ሲሆን ያምራል። ይህንን ድንቅ ሐዲሥ እንመልከትማ፦ أحْبِبْ حبيبَكَ هوْنًا ما، عَسى أنْ يَكونَ بَغيضَكَ يومًا ما، و أبْغِضْ بغيضَكَ هوْنًا ما، عَسى أنْ يكونَ حبيبَكَ يومًا ما "ወዳጅህን በልክ ሆነህ ውደድ። ምናልባት የሆነ ቀን የምትጠላው ይሆናል። የምትጠላውንም በልክ ሆነህ ጥላ። ምናልባትም የሆነ ቀን ወዳጅህ ሊሆን ይችላል።" [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 178] ልክ ሲያልፍ ግን ውዴታም ፈተና ይሆናል። ጥላቻም ገዳይ ይሆናል። ስንቶች አሉ በሆነ መነሻ የጠሉትን አካል ሞቱን የሚመኙ! ዘይድ ብኑ አስለም - ረሒመሁላህ - እንዳስተላለፉት ዑመር ብኑል ኸጧብን - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ ብለዋል፦ لا يكُن حُبُّكَ كَلَفًا، ولا بُغضُكَ تَلَفًا "ውዴታህ ፈተና አይሁን፤ ጥላቻህም ጥፋት አይሁን።" "እንዴት ነው እሱ?" ስሏቸው ይህን አሉ፦ إذا أحبَبتَ كَلِفْتَ كَلَفَ الصَّبِيِّ، وإذا أبغضتَ أحببتَ لصاحبِك التَّلَفَ "ስትወድ የህፃን አይነት ሙጭጭ ማለትን ሙጭጭ ልትል ነው። ስትጠላም ለጠላሀው አካል ሞቱን ልትወድ ነው።" [ሶሒሑል አደቢል ሙፍረድ፡ ቁ. 1322] ልክ ባለፈ ፍቅር እና ጥላቻ ገደል የገቡ ብዙ አካላት አሉ። ሐሰኑል በስሪይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ "أحبوا هونًا، وأبغضوا هونًا، فقد أفرط أقوامٌ في حب أقوام فهلكوا، وأفرط أقوام في بغض أقوام فهلكوا؛ فلا تفرط في حبك، ولا تفرط في بغضك" "በልክ ውደዱ። በልክ ጥሉ። በውዴታ ልክ አልፈው የጠፉ ሰዎች አሉ። በጥላቻም ልክ አልፈው የጠፉ ሰዎች አሉ። በውዴታህ ድንበር አትለፍ። በጥላቻህም ድንበር አትለፍ።" [ሹዐቡል ኢማን፡ 5/261] ልከኝነት ለሁሉም ኸይር አለው። በልክ ስትሆን ራስህን አትጎዳም። ለሌሎችም እዳ አትሆንም። ዐብዱላህ ብኑ ዐውን - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ "كَانَ فِي بَعْضِ الْكُتُبِ الَّتِي كُنْتُ أَقْرَأُ عَلَى مُحَمَّدِ بْنِ سِيرِينَ : يا بُنَيَّ لَا تَكُنْ حُلْوًا فَتُبْتَلَعَ ، وَلَا مُرًّا فَتُلْفَظَ ، وَلَكِنْ بَيْنَ ذَلِكَ "ሙሐመድ ብኑ ሲሪን ላይ የምቀራው ኪታብ ላይ እንዲህ የሚል ነበር፦ 'ልጄ ሆይ! ጣፋጭ አትሁን ትዋጣለህ። መራራም አትሁን ትተፍፋለህ። ይልቁንም በዚህ መሀል ሁን።" [አልጃሚዕ፣ ኢብኑ ወህብ፡ 475] ስለዚህ ራሳችንንም ሌሎችንም እንዳንጎዳ፣ ኋላ ፀፀት እንዳይለበልበን ሁሉንም ነገር በልክ መያዝ ይገባል። ኢማሙ አሕመድ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ لا تغلـو فـي كـل شـيء، حـتى الحـبّ و البغـض "በየትኛውም ነገር ድንበር አትለፍ። በመውደድና በመጥላት እንኳ ቢሆን።" [አልኣዳቡ ሸርዒያህ፡ 1/98] #ከደጋጎቹ_ቀዬ = Ibnu Munewor ፣ ዙል ቀዕዳህ 09/1444 የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor

ሙሓደራ ቁጥር 239 ክፍል 3 ርዕስ= ረድ በ ሙስጠፋ አብደላህ ላይ "መስዓለቱ ዑዝር ቢል ጀሕል'' 🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም) https://t.me/UstazKedirAhmed

👉 ​በሟች ቤት ለመብላት፣ ለመጠጣት ፣ጫት መቃምና ካርታ መጫወት እና ቁርኣን ለማንበብ መሰብሰብ ቢድዐ (አዲስ ፈጠራ) ነው። ​በሟች ቤት ለመብላት፣ ለመጠጣት እና ቁርኣን ለማንበብ መሰብሰብ ቢድዐ ነው። እንዲሁም በቤት ውስጥ ሶላት መስገድ አይፈቀድም። ይልቁንም በወንዶች ላይ የተጣለው ግዴታ በ መስጂድ ከጀማዐ (ከህብረት) ጋር መስገድ ነው። ወደ ሟች ቤተሰቦች የሚኬደው ለማጽናናት ፣ መልካም ለመመኘት እና ለሟቹ እዝነትን (ተረሁም) ለመጠየቅ ብቻ ነው። ​ነገር ግን በልዩ ንባብ ወይም በልዩ ዱዓዎች ወይም በሌሎች መሰል ነገሮች የሐዘን ስብሰባ ለማቋቋም መሰብሰብ ቢድዐ ነው። ይህ ነገር መልካም ቢሆን ኖሮ ደጋግ አባቶቻችን (ሰለፎች) ይቀድሙን ነበር። መልእክተኛው (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ይህንን አላደረጉትም። ጃዕፈር ቢን አቢ ጣሊብ፣ ዐብዱላህ ቢን ረዋሐ እና ዘይድ ቢን ሓሪሣ (ረዲየላሁ ዐንሁም) በሙእታ ዘመቻ በተደደሉ ጊዜ ወሕይ (ራእይ) መጥቶላቸው የሞታቸውን ዜና ለሶሓቦች አበሰሩ፤ እርቅንም ወረደላቸው፣ ዱዓ አደረጉላቸው፤ ነገር ግን የሐዘን ስብሰባ አላዘጋጁላቸውም። ​ከእርሳቸው በኋላ የነበሩት ሶሓቦችም ቢሆኑ ከዚህ ውስጥ ምንም አላደረጉም። አቡ በክር አሥ-ሥዲቅ (ረዲየልላሁ ዐንሁ) ሲሞቱ የሐዘን ስብሰባ አላዘጋጁላቸውም። ኡመር (ረዲየልላሁ ዐንሁ) ሲገደሉ  አላደረጉላቸውም፣ ቁርኣን እንዲያነቡም ሰዎችን አላሰበሰቡም። ከእርሳቸው በኋላ ኡሥማን እና ዐሊይ (ረዲየልላሁ ዐንሁማ) ሲገደሉም ሶሓቦች ከነዚህ ነገሮች ምንም አላደረጉም። ​ትክክለኛው ሱና ግን ለሟች ቤተሰቦች ዘመዶቻቸው ወይም ጎረቤቶቻቸው ምግብ አዘጋጅተው መላክ ነው። ነቢዩ (ሶለልላሁ አለይሂ ወሰለም) የጃዕፈር የሞት ዜና በመጣ ጊዜ ለቤተሰቦቻቸው፡ «ለጃዕፈር ቤተሰቦች ምግብ አዘጋጁላቸው፤ የሚያስጨንቃቸው ነገር መጥቶባቸዋልና» እንዳሉት ማለት ነው (ከነሳኢ በስተቀር አምስቱ የሐዲስ ዘጋቢዎች ዘግበውታል)። ሕጋዊና የተወደደው አሠራር ይህ ነው። ​ነገር ግን ከደረሰባቸው መከራ በላይ ሌላ መከራ እንዲሸከሙ ማድረግ እና ለሰዎች ምግብ እንዲያዘጋጁ ማስገደድ ከሱና ያወጣና ቢድዐ ነው። ቀደም ሲል እንደጠቀስነው እና ጀሪር ቢን ዐብዲላህ አል-በጀሊይ (ረዲየልላሁ ዐንሁ) ባሉት መሠረት፡ «ከቀብር በኋላ በሟች ቤተሰብ ዘንድ መሰብሰብን እና ምግብ ማዘጋጀትን ከኒያሓ (ዋይታ/ሙሾ) እንቆጥረው ነበር» ብለዋል (ኢማም አሕመድ እና ኢብኑ ማጃህ በትክክለኛ የሐዲስ ሰንሰለት ዘግበውታል)። ​ኒያሓ ማለት፡ ድምፅን ከፍ አድርጎ በለቅሶ መጮህ (ሙሾ ማውጣት) ሲሆን እርሱም የተከለከለ (ሐራም) ነው። ሟችም በገደለው/በተላቀሰበት ሙሾ ምክንያት በቀብሩ ውስጥ ይቀጣል፤ ከነቢዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) በሶሒሕ ሐዲስ እንደተረጋገጠው። ስለዚህ ከዚህ ነገር ጥንቃቄ ማድረግ واجب (ግዴታ) ነው። ​ለቅሶን በተመለከተ ግን ያለ ኒያሓ (ያለ ሙሾና ጩኸት) በአይን እንባ ብቻ ከሆነ ምንም ችግር የለውም፤ ነቢዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልጃቸው ኢብራሂም ሲሞት፡ «አይን ታነባለች፣ ልብም ያዝናል፤ ጌታችንን የሚወደውን እንጂ አንናገርም። እኛ በአንተ መለየት ኢብራሂም ሆይ! እጅግ አዝናናል» ብለዋልና። የቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me/Deewaselefyya1448 http://t.me/Deewaselefyya1448

ሸርህ ነዋቂዱል ኢስላም 🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ አልኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ ክፍል 10 ተጠናቀቀ አልሀምዱ ሊላህ https://t.me/Eslamikkk https://t.me/Eslamikkk የፒዲኤፉ ሊንክ ከስር https://t.me/Eslamikkk/6 https://t.me/Eslamikkk/6

ሸርህ ነዋቂዱል ኢስላም 🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ አልኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ ክፍል 19 https://t.me/Eslamikkk https://t.me/Eslamikkk የፒዲኤፉ ሊንክ ከስር https://t.me/Eslamikkk/6 https://t.me/Eslamikkk/6

ሸርህ ነዋቂዱል ኢስላም 🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ አልኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ ክፍል 18 https://t.me/Eslamikkk https://t.me/Eslamikkk የፒዲኤፉ ሊንክ ከስር https://t.me/Eslamikkk/6 https://t.me/Eslamikkk/6

ሸርህ ነዋቂዱል ኢስላም 🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ አልኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ ክፍል 17 https://t.me/Eslamikkk https://t.me/Eslamikkk የፒዲኤፉ ሊንክ ከስር https://t.me/Eslamikkk/6 https://t.me/Eslamikkk/6