cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

Больше
Рекламные посты
77 397
Подписчики
+2024 часа
+957 дней
+90030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

00:40
Видео недоступноПоказать в Telegram
ፈገግ በሉ ~ የአናቱን አምስት ብር ያነሳው ልጅ "ማነው ብር የወሰደው?" ሲባል "እኔ አምስት ብር አላየሁም" አለ አሉ። አንዳንዶች ባልታሰበ ሰዓት ወንጀላቸውን ይናዘዛሉ። ያያያዝኩት በዒራቅ ላይ ወረራ የፈፀመ ጆርጅ ቡሽ የተሰኘው የአሜሪካ መሪ ነው። የዩክሬንን ወረራ ሊያወግዝ ፈልጎ ምላሱ አጋለጠው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
ደርስ ~ * ሪያዱ ሷሊሒን * ክፍል:- 1️⃣5️⃣6️⃣ * የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/3505 * የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 475፣ ሐዲሥ ቁ. 1376 * የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን * የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
ከመግሪብ በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

በለተሞ መንጋ የምርቃና ስብከት ለተጠለፋችሁ ሁሉ! ~ 1ኛ፦ እነዚህ ሰዎች የመንሀጅ ግንዛቤያቸው የተንሻፈፈ፣ የግል አመላቸውንና ሰለፊያን የሚያምታቱ ስለሆነ የሰለፊያን ግንዛቤ ከነዚህ ሰዎች አትውሰዱ። ይልቁንም ጊዜው የሚመች ነውና ከነ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድ፣ ... ኪታቦችና የድምፅ ቅጂዎች ተጠቀሙ። ከነሱም በላይ የቀደምት ዑለማዎችን አካሄድ በሚገባ ፈትሹ። እነዚህ ሰዎች ሰለፊያ ነው ብለው የሚያቀርቡላችሁ ከክፉ አመላቸውና ሸውራራ ግንዛቤያቸው ጋር የተቀላቀለ ቡድንተኛ አካሄድ ነው። የሱና ዑለማኦችን የሚያጣቅሱት ለሽፋን ያህል ነው። 2ኛ፦ ደዕዋችሁ የአካባቢያችሁን ተጨባጭ ያገናዘበ ይሁን። አዲስ ብሄርተኛ ይመስል መንሀጅ በተገነዘባችሁ ማግስት በትንሽ በትልቁ ሌሎች ጋር አትላተሙ። እነዚህ የሚያጋጯችሁ አካላት ከምትገቡበት አጣብቂኝ እንድትወጡ የሚያግዝ ይሄ ነው የሚባል ሃሳብ እንኳ ማቅረብ አይችሉም። እነሱ እንደሆኑ ለራሳቸው ጥቅም ሲሆን ካሜራ ውስጥ እንዳይገቡ እየተሹለከለኩ፣ ማስክ እያጠለቁ የሚጣዱ ናቸው። እነሱን ተከትላችሁ ደዕዋችሁ ቢሰናከል ብዙ ርቀት ወደ ኋላ ይመልሷችኋል። 3ኛ፦ ለፍረጃና ለተብዲዕ አትቸኩሉ። በቂ የመንሀጅ ግንዛቤ ያልያዘ ሰው ፈፅሞ ለተክ -ፊርና ለተብዲዕ ብቁ አይደለም። ነገሩ በሚገባ ተገልጦልናል ብላችሁ በምታምኑበት ጉዳይ ራሱ በመናገራችሁ የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ አስሉ። የደመ ነፍስ አካሄድ ማንንም አይጠቅምም። 4ኛ፦ የለተሞ ጭፍራዎች ጋር መጓዝ መስጂዶቻችሁን ያሳጣችኋል። ከማህበረሰብ ጋር ያጋጫችኋል። በሂደት ደዕዋችሁን ወይ ሙሉ ለሙሉ ያጠፋዋል። ወይ ደግሞ በእጅጉ ያቀጭጨዋል። ብዙ ካበላሻችሁ በኋላ ግራ ቀኝ አይታችሁ የተሻለ መስለሐ ያለበትን ውሳኔ ብትወስኑ ራሱ እነዚህ እባቦች ከማንም በላይ የሚናደፉት እናንተን ነው። የቻግኒው ሸይኽ ከማል አፍሪ ጉዳይ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። ቀድመው በነዚህ አካላት የተሳሳተ አቅጣጫ ይዘው ነበር። አሁንም ምን ያህል እንደነቁ አላውቅም። የተሻለ መስለሐ አይተው መስጂድ ገብተው ሲያስተምሩ እድሜያቸውንም፣ ውለታቸውንም በማይመጥን መልኩ እያብጠለጠሏቸው ነው። "ያሳደጉት ውሻ፣ ያሳጣል መድረሻ!" 5ኛ፦ የአካባቢያችሁን መስለሐ ራሳችሁ ወስኑ። በሩቅ ያለ ሰው ያላችሁበትን ተጨባጭ ላያውቅ ይችላል። በተለይ እነዚህ ከህሊናቸው የተጣሉ አካላትን ፈፅሞ አታማክሩ። እንኳን ለናንተ ለራሳቸውም የሚሆኑ አይደሉም። አስፈላጊ ሲሆንና ከተቻላችሁ ዑለማኦችን አማክሩ። እነዚህ የሚጮሁትን የማይኖሩ ደናቁራን እንዳያሳስቷችሁ። ለተሞ በራሱ ምስክርነት ከ10 አመት በላይ ኢኽዋንን ሲያደንቅና አብሮ ሲጓዝ የኖረ ሰው ነው። አሁንም ከተወሰኑት ጋር ያፋጠጠው የጥቅም ግጭት ነው። እንጂ የጥቅም ቃል ሲገባለት እንኳን ከነዚህ ጋር ይቅርና ቀድሞ ተብዲዕ ካደረጋቸው ሰዎች ጋር ራሱ ሊታረቅ እልል ሲል ነበር። አሁንም የተሻለ ካየ ለሌላ ይፈርማል። ባህሩም ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ ሲል ለዲን ተቆርቁሮ አይደለም። የራሱ አንዱ ጋሻጃግሬ ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር የመስጂድ ኮሚቴ አባል ነው። ኮሚቴው በመጅሊስ መዋቅር ስር እንደሆነ አስተውሉ። የባህርዳሩም ጭፍራ ዲን አይደለም ከመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ጋር ያፋጠጠው። "ለኛ የተላከ ኪታብ ወስደውብን ..." እያለ ነው የህፃን ለቅሶ የሚያለቅሰው። ራሳቸው በቡኻሪ መስጂድ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድን ፕሮግራም አስተዋውቀው ሲያበቁ እነዚህ ከህዝቡ ብር ሲሰበስቡ ጊዜ ጨርቃቸውን ጣሉ። በቀናት ልዩነት ውስጥ ተነስተው አስጠነቀቁ። ስሜታቸውን የማይቆጣጠሩ፣ ይሉኝታ የማያውቁ ጉዶች ናቸው። እንጂ ዛሬ ለተብዲዕ የሚመዙትንጉዳይ እየጠቀሱ ተብዲዕ ግን አናደርግም ሲሉ እንደነበር የድምፅ መረጃ አለ። 6ኛ፦ በደዕዋ ላይ ተመዩዝ አስፈላጊ ነው። ተመዩዝ ማለት ግን በራስ ላይ በር ዘግቶ መጮህ አይደለም። ከሆነላችሁ ያለ ንክኪ አስተምሩ። መድረክ ካገኛችሁ አቋማችሁ የተጠበቀ እስከሆነ ድረስ በሱፊዮች መስጂድ እንኳ ቢሆን አስተምሩ። ታላላቅ መሻይኾች በሱፊያ መስጂዶች ያስተማሩበት ተጨባጭ አለ። ለምሳሌ ሸይኽ ረቢዕ ሱዳን ውስጥ በሱፊያ መስጂድ አስተምረዋል። "በአቋም ቢገናኙ ነው ከነ እንትና መስጂድ የሚያስተምሩት" የሚለው የነዚህ ሰዎች ጩኸት ዝቅ ቢል ድንቁርናቸውን ከፍ ቢል አታላይነታቸውን ነው የሚያሳየው። ለአመታት ሂዝቢዮች ላይ ቁጭ ብለው ሲማሩ ነው የኖሩት። ባህሩ፣ ሁሴን ሲልጢ እና ጠሀ ኸዲር ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። ራሳቸው የሳዑዲ ጃሚ0ዎች በሒዝቢዮች የተጥለቀለቁ እንደሆኑ ይገልፃሉ። ራሳቸው በንዲህ አይነት ተቋማት ቁጭ ብለው እየተማሩ እኛ ጋር መጥተው እንትናን ከእንትና ጋር አየነው እያሉ አድብተው ይጠብቃሉ። በሰሜን ወሎ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ ዞኖች የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ የገቡ አሉ። ለተሞ በሚያብጠለጥላቸው የየመን መራኪዝ የሚማሩ የለተሞ መንጋዎች አሉ። የመን መዕበር ድረስ ሄደው ሙሐመድ አልኢማም ዘንድ የሚማሩ ሁሉ አሉ። እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ዐረብኛ ትምህርት በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሙመይዐ ከሚሏቸው እና ኢኽዋኒዮች ዘንድ ቁጭ ብለው የሚማሩ አሉ። ከዚህም የባሰ ሱፊዮች ዘንድ ሳይቀር ሉጋ የሚማሩ አሉ። ራሳቸው በሚሰሩት ጉዳይ ሌሎችን ተብዲዕ የሚያደርጉ የማፊያ ስብስብ ናቸው። ጩኸታቸው የእውነት መስሏችሁ እነሱን የተከተላችሁ በጊዜ ብትነቁ ይሻላችኋል። ጥሪዬ በተለይ መሬት የረገጠ ደዕዋ ላላችሁ ነው። ደዕዋችሁን ሳታጡት በፊት ደጋግማችሁ አስቡበት። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ደርስ ~ * ሪያዱ ሷሊሒን * ክፍል:- 1️⃣5️⃣5️⃣ * የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/3505 * የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 471፣ باب فضل المملوك الذي يؤدي حق الله * የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን * የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
ከመግሪብ በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

Фото недоступноПоказать в Telegram
ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም ~ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ህዝበ ሙስሊሙን ማግለሉን ተያይዞታል። ምንድነው ገና ብዙ ሳይራመድ ውልክፍክፍ ስራ መስራት? የነዚህን አካላት ሸፍጠኛ አካሄድ ሙስሊሙ አጥብቆ ሊኮንነው ይገባል። ጉዳዩን ብዙም ትኩረት የሰጠነው አይመስልም። ምናልባት ምክክሩ የእውነት ከልብ የተያዘ ሆኖ ተፅእኖ የሚኖረው ከሆነ ኋላ ነገራችን ጅብ ከሄደ እንዳይሆነ ዛሬ አጥብቆ መጋፈጥ ያስፈልጋል። ገና ከመነሻው በቅጡ አሳታፊ ካልሆነ እንቅስቃሴው ሳይወለድ የሞተ ሆኗል ማለት ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ግርንቢጥ ጭፍራ ~ በነገራችን ላይ እነዚህ ያለፈ ያገደመውን በመናከስ እና ቅጥ በሌለው የተብዲዕ ጥማት የተለከፉ የለተሞ መንጋዎች ከተለያዩ አካላት ጋር የሚጣጣዱባቸውን ፎቶዎችና ቪዲዮዎች የምለጥፈው ተብዲዕ ለማድረግ አይደለም። በጭራሽ! የተብዲዕ ጉዳይ ከባድ ነው። የተክ 'ፊር ደግሞ የባሰ ነው። እኔ ሌሎች ተጨባጭ እውነታዎችን ሳይመለከቱ እና ግራ ቀኝ ሳያዩ እከሌ በመጅሊስ መዋቅር ውስጥ ገባ፣ እከሌ ከእከሌ ጋር ተቀመጠ፣ እከሌ ከእንትና ላይ ተማረ በሚል መነሻ ብቻ ሰዎችን ከሱና ማስወጣት ላይ አልዳፈርም። ይህንን የማደርገው ለራሴ ስል ነው። ይልቁንም የነዚህን ሰዎች ምስሎች እና ተግባሮች የምጠቅሰው የተሸወደባቸው አካል አታላይነታቸውን እንዲያውቅ ነው። ሌሎችን ከሚያወግዙባቸው ተግባሮች እነሱ ራሳቸው ነፃ ቢሆኑ ኖሮ "ከተብዲዕ በፊት ሊፈተሹ የሚገባቸው ጥንቃቄዎችን ስለማያውቁ ነው የሚቸኩሉት" ብለን ዑዝር እንሰጣቸው ነበር። ሌሎችን የሚወነጅሉባቸውን ተግባራት ራሳቸው የሚያቦኳቸው ከሆኑ ግን ጉዳዩ ለዑዝርም አይመችም። የሚቀረው ምርጫ በሰለፊያ ስም የሚነግዱ ስሜት ያስከራቸው አታላዮች እንደሆኑ እንደመድማለን። እስኪ እነዚህን ነጥቦች ተመልከቱ:- 1- አብዛኞቹ የኡሙል ቁራ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች ከኢኽዋንና ከሱሩሪያ ቡድን የሆኑ ሒዝቢዮች ናቸው ይላል ሑሴን አሲልጢ። ይሄው ቃሉ፦ جامعة أم القرى وغالب المدرّسين حزبيون من الإخوان والسرورية በራሱ ምስክርነት ሒዝቢዮች ላይ ቁጭ ብሎ ለአመታት ሲማር ነው የቆየው ማለት ነው። ከሙብተዲዕ ላይ መማርና መቀማመጥ ሑክሙ ምን ነበር? ነው ይሄ ህግ ኢትዮጵያ ውስጥ እንጂ ሳዑዲ ውስጥ አይሰራም? ህጉ ሌሎችን ለማብጠልጠል እንጂ ለራስ ከሆነ ችግር የለውም ማለት ነው? ምናልባት እነ ሸይኽ እንትናም እዚያ አስተምረዋልኮ ይሉ ይሆናል። ይሄ ማስረጃ አይሆንም። የሰለፎችን አሣር ያለ ቅድመ ሁኔታ ለውግዘት እየተጠቀምክ ጉዳዩ ወዳንተ ሲዞር ጊዜ ራሴን ወገቤን ማለት አያዛልቅም። 2- "ልክ እንደዚሁ በሌሎችም የሳዑዲ ዩኒቨርሲቲዎች ሰለፊዮች አናሳ ናቸው" ይላል ሑሴን። ይሄው ቃሉ፦ وكذلك الجامعات الأخرى في السعودية وغيرها فالسلفيون فيها قلة فهذا لا ينكره إلا من أعمى الله بصره وبصيرته ጓደኛው ጠሀ ኸዲር የሚማረው ጃሚዐቱል ኢማም ነው። ማን ላይ እየተማረ እንደሆነ ተመልከቱ። ይሄ ተግባር ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን ግን ተብዲዕ ያደርጉበታል። ተግባሩ የራሳቸው ሲሆን ግን ሰበብ ይደረደርበታል። "ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ይሏታል።" 3- እነዚህ ሰዎች ዘንድ አንድ ሰው ሐለቢን ቢያደንቅ ከጥይት የፈጠነ ተብዲዕ ይከተለዋል። "ችግሩ" የነሱ ሲሆንስ? ይሄው ጠሀ ኸዲር ሐለቢን ሞቅ አድርጎ የሚያደንቀውን ሪያድ አሰዒድ "ሸይኻችን" እያለ የሚገልፅበትን ተመልከቱ። ሌላ ሰው ቢያደርገው አስቡት። ይሄ ታዲያ አጭበርባሪነት ካልሆነ ሌላ ምን ስም አለው? 4- እነ እከሌ ከመጅሊስ ሰዎች ጋር ታዩ እያሉ ለማራገብ አንደኛ ናቸው። ራሳቸው ግን አብረው የሚጣዱባቸው ፎቶዎችና ቪዲዮዎች ወጥተዋል። ማስክ እየለበሱ ሊያደፍጡ ቢሞክሩም ተለይተዋል። አብረው አፍጥረዋል። ሁሉም በተካፈሉበት መድረክ ላይ ወጥቶ ንግግር ያደረገም አለ። (ነዚፍ ጂሃድ።) ከአሕባሽ ጋር ተቀምጦ የሚበላ ታይቷል። መሰል ጉዳዮችን እነሱ የሚይዙበት አያያዝ ጋር አገናዝቡት። 5- ከዚህም በላይ የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ የገቡባቸው አካባቢዎች አሉ። ሰሜን ወሎ ሀራ ከተማ ያሉት መጅሊስ ውስጥ ገብተው የነበረ ቢሆንም አባረዋቸዋል። አስቂኙ ነገር "ለምን እንባረራለን?" ብለው ግርግር ፈጥረው የነበረ መሆኑ ነው። ደግመው እስከ ዞን ድረስ ደብዳቤ ቢፅፉም አልተቀበሏቸውም። በዚያው ዞን በሌሎች ቀበሌዎች መጅሊስ ውስጥ የገቡት ግን ዛሬም አሉ። በጉራጌና በስልጤ ዞን መጅሊስ ውስጥ የገቡም አሉ። ዐብዱልሐሚድ ለተሞም ስሙ ተካቶ ቢወጣም ያ መታገስ የማይችል ሰው ያለወትሮው ዝም ጭጭ ብሏል። እነዚህ ሁሉ ተግባሮች የሌሎች ቢሆኑ ብላችሁ አስቡ። እና ይሄ ዲን ነው? 6- በቅርቡ የኛ ሲሏቸው የነበሩ መሻይኾች ከመጅሊስ ዑለማኦች ጋር ድሮም፣ አሁንም፣ እስከዘላለም አንድ ነን። እነሱን ከሚነካ ንፁህ ነን" የሚል መግለጫ አውጥተው አይተናል። ይሄ ጉዳይ ሲወጣ ጠሀ ኸዲር "ተገደው ነው እንደዚያ ያሉት" የሚል ፅሁፍ አጋርቶ ነበር። ባህሩ ተካ ደግሞ "እነዚህ ሁለት ሰዎች ድሮም ከኢኽዋን ጋር ነበሩ አሁንም ከኢኽዋኖች ጋር ናቸው እንላለን" ይላል። የሚገርመው ጠሀ ኸዲር ይህንንም ያጋራ መሆኑ ነው። "ተገደው ነው እንጂ ሰለፊዮች ናቸው" ሲባልም ያሰራጫል። "አይ ድሮም ከኢኽዋን ጋር ነበሩ አሁንም ከኢኽዋኖች ጋር ናቸው" ሲባልም ያሰራጫል። ሰዎቹ የአቋም ብቻ ሳይሆን የዐቅልም ችግር ያለባቸው ይመስላሉ። ምንም አይነት ተቃርኖ አይጎረብጣቸውም። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور