قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Открыть в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
901
Подписчики
-424 часа
-167 дней
+4030 дней
Архив постов
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ጧሊበል ዒልም እና ኪታብ
~
1- ኪታብ ስንገዛ አቅም በፈቀደ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀውን እንግዛ። በተለይ የሚታወቅ አታሚ ወይም የሚታወቅ ሰው ያዘጋጀው ቢሆን መልካም ነው። ወይም ሰው ብናማክር ጥሩ ነው።
2- በጥንቃቄ እንያዝ። በጥንቃቄ ስለማንይዛቸው ስንት ኪታቦቻችን የሽፋን ፅሁፋቸው ደብዝዟል ወይም ጠፍቷል?! ስንቱ ወረቀታቸው ተነቃቅሏል?! ስንቱ ተቀዳደዋል?! ስለዚህ ውስጣቸው እርሳስና እስኪርቢቶ ማስቀመጥ፣ ወረቀት እያጥጠፉ ምልክት ማድረግ፣ ስርአት በሌለው መልኩ ላያቸው ላይ መለቅለቅ እና መሰል ልማዶችን መተው ይገባል። ይልቁንም ሽፋናቸውን በላስቲክ ወይም በፕላስተር መለጠፍ ይገባል። የምናስቀምጥበት ቦታም ጥሩ ቦታ ሊሆን ይገባል።
3- ሌላኛው ጥንቃቄ የሚፈልገው ማዋስ ላይ ነው። በጥንቃቄ በመያዝ፣ በጊዜ በመመለስ ለምታውቁት ካልሆነ በስተቀር ኪታብ አታውሱ። ብዙ ሰው የረባ የንባብ ልማድ ሳይኖረው እንዲሁ ጓጉቶ ይዋስና ወስዶ የትም ይጥለዋል። መጨረሻ ከማን እንደተዋሰው እንኳን አያስታውስም። በዚህ መልኩ ስንት ኪታብ ጠፍቶብናል? ስንት ኪታብ ጥለናል? አሁንም ይህንን ፅሁፍ የምታነቡ ሁሉ ኪታቦቻችሁን ፈትሹ። የተዋሳችኋቸውን ኪታቦች መልሱ። አማና ላይ አትዘናጉ። የምታውሱ ደግሞ የተዋሹን እና የኪታቡን ስም የተዋሰበት ቀን ጋር መዝግቡ።
4- ኪታቦች ላይ ወሳኝ ማስታወሻ ወይም እርምት ስትፅፉ ኪታቡን በማያበላሽ መልኩ ይሁን። በመጀመሪያ የረባ ዋጋ የሌለው ነገር መፃፍ አይገባም። ሁለተኛ ቢቻል እርሳስ ብንጠቀም ጥሩ ነው። ሶስተኛ በተቻለ መጠን ስርአት ባለው በሚነበብ መልኩ እንፃፈው። በችኮላ ፅፈነው ኋላ የራሳችንን ፅሁፍ ማንበብ የምንቸገር እንኖራለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኪታብ በማስተማር ላይ ለተሰማራችሁ
~
1- ለተማሪዎችህ የሚማሩትን ኪታብ መምረጥ። አቅማቸውን፣ የጎደላቸውን፣ የሚያስፈልጋቸውን እንጂ እንዲሁ የጠየቁትን ሁሉ አትጀምር። ተማሪ ያላቅሙ ትልቅ ኪታብ መጀመር ሊፈልግ ይችላል። ተማሪው በጥሩ ደረጃ ላይ ካለ የጠየቀውን ብትቀበልም ችግር የለውም።
2- የምታቀርበው ትምህርት፣ የምትመልሰው ጥያቄ ታዳሚህን ያገናዘበ ይሁን። ሰፊ ህዝብ የሚታደምበት ደርስ ላይ የሚኖርህ አቀራረብ በ'ቂራአት' ገፋ ካደረጉ ተማሪዎች ጋር ከሚኖርህ ጋር በይዘቱም፣ በቋንቋውም፣ በመጠኑም ሊለይ ይገባል። ለምሳሌ ከመግሪብ እስከ ዒሻ መስጂድ ውስጥ የሚሰጥ ደርስ ላይ ጠለቅ ያለ ኺላፍ አትተንትን። ይሄ ማስተማር ሳይሆን ማደናገር ነው። ኺላፍ ጆሯቸውን ከመታቸው ተማሪዎች ጋር ስትሆን ደግሞ በተቻለ መጠን 'ራጂሕ' እና 'መርጁሑን' ባቅማቸው መጠን ለይተህ አቅርብ። ብዥታዎችን ግፈፍ። የምታቀርበው ነገር ግልብ ከሆነ ደርስህን ጣዕም ያጡበታል። ባጭሩ ትምህርት ታዳሚዎችህን ያገናዘበ ይሁን።
3- ተዘጋጅተህ ቅረብ። ቢያንስ ገረፍረፍ አድርገው። ተማሪዎችህ ፊት አትደናበር። በቅጡ ሳትይዝ ቀርበህ ሸርሕ ላይ በፍለጋ አትባዝን። የቀለም ትምህርት ላይ እንኳ አስተማሪዎች ተዘጋጅተው ነው የሚቀርቡት። የዲን ጉዳይ የበለጠ ጥንቃቄ ይፈልጋል።
4- ካ'ቅምህ በላይ ካልሆነ በስተቀር ቀሪ አታብዛ። ደርስ አታቆራርጥ። ይሄ የተማሪዎችን ሞራል በጣም ያቀዘቅዛል።
5- ተማሪዎችን አታሸማቅ። አንዳንዱ አስተማሪ ጥያቄዎችን በቅንነት አይረዳም። ሁሉ ነገር መፈታተን ይመስለዋል። ይሄ መሆን የለበትም። መፈታተን የሚፈልግ፣ ልታይ ልታይ የሚል፣ መጥፎ አቀራረብ ያለው ተማሪ ካለ እንዳስፈላጊነቱ በጥቅል ወይም በተናጠል ለይተህ ምከር። ካልሆነ ጠንከር አድርገህ ገስፀው። ነገር ግን ቁጣችን የራሳችን ድክመት መሸፈኛ ሊሆን አይገባም። በአስተማሪዎች ከባድ ባህሪ የተነሳ ስንት ደርስ ተበትኗል! ስንት ተማሪ ተሰናክሏል! ስንት የደዕዋ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል!
6- ድንገት ያልገባህ ነገር ከገጠመህ ወይም የማታውቀው ጥያቄ ከተጠየቅክ አትደንግጥ። አንተ ሁሉን እንደማታውቅ ይታወቃል። አይቼ እመጣለሁ፣ አላውቀውም በል። እንጂ እርግጠኛ ባልሆንክበት በግምት እንዳትመልስ። አደራ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from N/a
🌆ለቁርዓን ያላችሁን ፍቅር በሚገርም ሁኔታ የሚጨምርና ጣሪያ እንዲነካ የሚያደርግ አጂብ የሚያሰኝ የቁርዓን ቻናል ተወዳጅነትን አትርፏል🔋
🗳ወላሂ ሐቂቃ ማስታወቂያ ነው ተቀላቀሉ🗳
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ሁሉን ማመን አለቀኝ ያለ በሽታ ሆነብኝና....ብዙ ነገሬ.......
«ሰው አምናለሁ»
ወዳጅ መስለው ለቀረቡኝ፡
ወንድም ብለው ለሚያስቡኝ፡
ለሁሉም ሰው እባባለሁ ሁሉም ደግሞ ያጠቃኛል፡
ንፁህ ሆኘ የቀረብኩት ቀን ጠብቆ ይጎዳኛል፡
እኔ ያው ነኝ ምንም ብሆን አልቀየር፡
መሬት ለቆ ቢሄድ ባየር፡
ስንቱ መጥቶ ወግቶኝ ሔዷል፡
ንፁህ ልቤ ብዙ ነጉዷል፡
ግን አሁንም እንደዛው ነው፡
ነገ እንደት ነው የምሆነው!?
ይህ ባህሪዬ እየሳበኝ፡
የነግ ህልሜ አሳሰበኝ፡
የማይሻል ህመም አለኝ፡
አንድ እሱ ነው የጎደለኝ፡
በሩቃ ኬዝ የማይወጣ፡
እጂግ በጣም የሚቀጣ፡
ልብ ላለው የሚያስቆጣ፡
ልብ አዕምሮን የሚሰብር፡
ህያው አርጎ የሚቀብር፡
ደም የሚመጥ እንደ ነብር፡
የታሸገ በፈገግታ፡
አብሮኝ ያለ ጧትም ማታ፡
የሚሰጠኝ ለበሽታ፡
አለኝ ሰይጣን አለኝ ልምሻ፡
ጫፍ የሌለው መዳረሻ፡
ሰው አምናለሁ… እንደ ውሻ!
...ይህን ባህሪ መቀየር አልቻልኩም ወዳጆቼ እስኪ ምክር ስጡኝ ..በአሏህ...⁉️
...ኑር....✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
لا تكُن إِمَّعَةً
تميل مع النَّاس حيثُ مالُوا
كُن صاحِبَ عقِيدة
كُنْ مع الحَقِّ فِي كُلِّ زمَانٍ ومَكَان
- أنتَ الجَمَاعَةُ وَلَو كُنتَ وَحْدَكَ!.
Repost from قناة أبي ماهر الأثري الحبشي𝐀bu Mahir )
እነ ሙስጦፍና ግብረ አበሩ ኡዙር የለም ኡዙር አለ የሚል ሙርጅአ ነው ካፊር ነው ይላሉ ያለምንም ማስረጃ ቁጭብለው ከኹዝ ጀምረው መቅራት ሲገባቸው አዋቂነን ብለው ተነስተዋል ለመሆኑ መቼ መቼ ዳአዋ አድርገው ነው ሰውን ለማክፈር የዘመቱት አጅብነው ሲጀመር ዳአዋተ ሰለፍያን አካሄድ መቼ ሲያዉቁት እውቀት ያለውኮነው የዳአዋን ሲስተም የመሚያውቀው በጩኸትና በስድብ የተሞላ ዳአዋ መሆኑ ግልፅነው እኛንም እያከፈሩነው ሁሉንም አክፍረው እስልምናን እራቁቱን ለማስቀረት የተነሱ አካላቶች ናቸው ስለዚህ ሸይኸ ኡሰይሚንንም ይህን ታላቅ የሱና አሊም ሊያከፍሩነው በቃል ባይደፍሩትም በተግባር አክፍረዋል ይህ ታላቅ የሱና አሊም ሸይኸ ኡሰይሚን ስለኡዙር ቢል ጀህል ተጠይቀው በግልፅ ኡዙር እንደሰጡ በግልፅ ቋንቋ
ጠያቂ: አንድ ሴት በአውሮፖ ወይም በአፍሪካ ትኖር ነበር ከዚያ ሞተች በመቃብር ጦዋፍ ታድርግ ነበር ለመቃብር ታርድ ነበር እዚያ አካባቢ ተወሂድ የሚያስተምር እና ለሷ ስለ ተወሂድ ሽርክ የሚያብራራላት አካል አልነበረም ይች ሴት ምክንያት (ኡዙር ) ይሰጣታልን ልጆቿ ዱአን ማድረግ እና ዱአ ማድረግ የሚፈልግ አካል ለእሷ ዱአ ማድረግ ይቻላልን ?
ምላሽ : በእስለምና ውስጥ ገብታ ከዚያ ሽርክን ቋጠረች ማንም አካል ሽርክ መሆኑን የነገራት ያብራራላት (ሁጃ ያቆመባት) የለም ይች ሙስሊምናት !!!
እንደማንኛውም ሙስሊም ትታያለች ከሞተች ይሰገድባታል ሙስሊሞች መቃብር ትቀበራለች ልጆቿ ዱአ ያደርጉላታል ምክንያቱም አላዋቂ ናት ሽርክ መሆኑን አላወቀችም ለእሷ የሚያብራሩ ኡለማዎች (ሁጃ የሚያቆሙ) የሉም ይች ጃሂል ናት አላህ በተከበረው ቃሉ ( እኛ መልእክተኛን እስክንልክ ድረስ አንቀጣም ) ብሏል ።
Repost from قناة أبي ماهر الأثري الحبشي𝐀bu Mahir )
[ بين المذنب والمبتدع ]
ومعلوم أن المذنب إنما ضرره على نفسه، وأما المبتدع فضرره على النوع.
وفتنة المبتدع في أصل الدين، وفتنة المذنب في الشهوة.
والمبتدع قد قعد للناس على صراط الله المستقيم يصدَّهم عنه، والمذنب ليس كذلك.
والمبتدع قادح في أوصاف الرب وكماله، والمذنب ليس كذلك.
والمبتدع مناقض لما جاء به الرسول ﷺ، والعاصي ليس كذلك.
والمبتدع يقطع على الناس طريقَ الآخرة، والعاصي بطيء السير بسبب ذنوبه.
• ابن القيم | الداء والدواء صـ (٣٣١-٣٣٢)
=
https://t.me/A2mnt
የእውቀት ባለቤቶች እና የስሜት ባለቤቶች ልዩነት
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
ሙስጦፋ አብደላህ ሆይ ⁉️
ስለ ሸይኽ ረቢዕ ማንን እንስማ⁉️
አንተን እንስማ ወይስ ሸይኽ ሷሊሁል ፈውዛንን⁉️
አንተን እንስማ ወይስ ሸይኽ ኢብኑ ኡሠይሚንን⁉️
አንተን እንስማ ወይስ ኢማሙል አልባኒን⁉️
አንተን እንስማ ወይስ ሸይኽ ሙቅቢልን⁉️
አንተን እንስማህ ወይንስ የሌሎችን ታላላቅ አኢማወችን ንግግር⁉️
ለመሆኑ አንተ ምነው አፍህ ገደብ አጣ በታላላቅ ኡለማወች ላይ⁉️
ተው ባይ የለህም⁉️
መካሪ የለህም⁉️
ተቆጭ የለህም⁉️
ቡድንህን ለመርዳት ብለህ እንደት እንደዚህ በስሜት ከኡለማወች ላይ ትናገራለህ⁉️
ተው አሏህን ፍራ ወደ አሏህ ተመለስ
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid
Repost from N/a
🚨ፈጥኖ ማን ይመልስ ‼️🏃➡️🏃➡️
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው ብዙ ጠቃሚ ኢስላማዊ ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ።
Wave 👉 @selluhi
👉ጥያቄ፦ ቁርዓን ስንት ምዕራፍ አለው⁉
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
👉ሞት ቅርብ ነው።
ለምትወዱትን ሰው ፍቅራችሁን ሳትገልፁለት ፣ ሞት እንዳይቀድማችሁ!
ነገሮችን ለነገ አታሳድሩ
ማድረግ የምትፈልጉትን ዛሬ አድርጉለት መናገር የምትፈልጉትንም ዛሬ ተናገሩ።
ከሞተ በኋላ ቁጭት አይጠቅምም።
ዛሬ እንተሳሰብ፣
ዛሬ እንደማመጥ፣
ዛሬ እንከባበር፣
ዛሬ እንተዋወቅ...ወዳጃችሁን በወረትና በተረት አትቀይሩት #ውደታ የአካል ጥምረት ሳይሆን የመንፈስ ውህደት ነው።
...ኑር...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
«ከውጭ መልዓክ እየመሰልክ ቤት ውስጥ ሰይጣን አትሁን።»
«ሚስትህ ቤት ውስጥ መልካም ንግግርን ትፈልጋለች...»
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
የማይቋረጥ ደስታን የፈለገ ቁርዓንን አጥብቆ ይያዝ!
የማይከዳን፣የሚያፅናናን፣የሚያስደስተን፣ሳንከፍል እየተከፈለን የምንደሰትበት ነገር ቢኖር ቁርዓንን መሀፈዝና ለመሀፈዝ የምናደርገው ድግግሞሽ ላይ የሚሸልመንን ሽልማት በአይናችን አሁኑኑ ብናይ ኑሮ አንድም ሰው ጓደኛ ዘመድ ቤተሰብ እያለ ግዜውን ባላባከነ ነበር።
ነገር ግን የኛ የአማኞች ዋናውና ትልቁ እምነታችን በሩቅ በገይብ ማመናችን ነው የምንመነዳውን ካላየን ሳይሆን እምንለው ምንዳችን ወደር የለውና ልጣር ልልፋ መልካምን ልከስብ፣የሚል የአማኞች እምነት ነው።አልሀምዱሊላህ!
ስለዚህ ነገ እድለኛ መሆን የፈለገ ቁርዓንን ጓደኛው ያድርግ። ወላሂ ርካታውን የሚያውቀው ያየው ሰው ነው ሞክሩት ትርፋማ ንግድ ነው።
የተወሰደ
Repost from Hussein Ali (Durus & Fewa'id)
የጥንቃቄ መልእክት
ውድ ወንድሞችና እህቶች ዛሬ ዛሬ ሌቦች ይበልጥ በማያሰነቃ ሁኔታ የሱናን አለባበስ ተላብሰው ሰዎች ዘንድ በጣም አሏህን ፈሪ በመምሰል ሞባይል እየሰረቁ ስለሆነ ማንነቱን የማተውቁትን ግለሰብ ባለባበሱ ተማርካችሁ ሙሉ እምነት ልትሰጡ አይገባም ። ይህ ምስሉን የምታዩት ግለሰብ በአወሊያ መስጅድ ግቢ አስደውሉኝ በማለት ሞባይል አታሎ ይዞ የሄደ ሰው ነው። ሲያደርጋቸው የነበሩት ተግባሮች ሁሉ በካሜራ ተቀርፆ ተቀምጧል። እሱም ከዚህ ሰራው ይታቀብ ዘንድ ሌሎች ወንድምና እህቶች እንዳይታለሉ በማሰብ ፎቶውን አያይዣለሁ
http://t.me/husseinali210
እኛ አህሉ ሱናዎች ለ «ሱና ዑለማዎች» ለየት ያለ ውዴታ አለን።ቀለል ያለ ስህተት ቢኖርባቸው እንኳን እናከብራቸዋለን።እንወዳቸዋለን። ከስህተታቸው እንድመለሱም ዱዓ እናደርግላቸዋለን።በእነርሱም ላይ የሚቀጥፍ አካል ካለ ከእነርሱ እንከላከላለን። በዚህም ከአላህ ምንዳ እንፈልግበታለን። ኢንሻአላህ።
Repost from የለተሞ መንጋን በመረጃ ማፈራረስ
▣ ኢልዛምን የሚመለከት ዳሰሳ
🎙 ኡስታዝ ሙሀመድ አህመድ (ኢብኑ ሙነወር)
https://t.me/Menhaje_Selef/5
https://t.me/Menhaje_Selef/
Repost from قَناةُ وفَوا ئِد أبي فَوزان الْحَبَشِيِّ
የተውሒድ ፍሬዎች!
ثَمَرَات التوحيد
🎙;-በሸይኽ ዐብዱል'ዐዚዝ አልቡረዒይ حفظه الله
🔷👉https://t.me/abujemila25
🔷👉https://t.me/abujemila25
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ለዚህ ቪዲዮ እኔም ህያው ምስክር ነኝ! ሀቂቃ… ትዳር የሪዝቅና የበረካ በራፍ ነው።
ሰራተኞች አሉኝ፤ ያገቡትም፣ ያላገቡትም፣ ልጆች ያላቸውም አሉ። የሁሉንም ወርሃዊ ደመወዝ እኔው ነኝ የምከፍለው፤ ክፍያቸውም በጣም ተቀራራቢ ነው። ነገር ግን እውነተኛው ልዩነት የሚታየው ደመወዝ ከተከፈለ በኋላ ባለው ህይወት
ነው!
ያገቡት ሰራተኞቼ ያቺኑ የምከፍላቸውን ደመወዝ አብቃቅተው፣ ቤታቸውን መርተው፣ የልጆቻቸውን ፍላጎት አሟልተው በሰላም ሲኖሩበት፤ ላጤዎቹ ሰራተኞቼ ግን ገና ወሩ አጋማሽ ሳይደርስ «እባክህ የቀጣይ ወር ደመወዝ ቅድሚያ ስጠኝ» እያሉ ማንኳኳት ይጀምራሉ!--ሀሀ--
እናላችሁ… በትዳር ውስጥ ያለው ሚስጥር የገንዘቡ ብዛት ሳይሆን የበረካው ስፋት ነው ወላሂ! ትዳር ትንሹን አብዝቶ፣ ጎደሎውን
ሞልቶ ያሳያል። ስለዚህ ያላገባችሁ… ከመበደር ወደ ማብቃቃት፣ ከላጤነት ወደ በረካው ጎጆ ተሻገሩ ለማለት ነው! 😉
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
سُئِلَ أبو داود السجستاني فقيل له:
من تأمرنا أن نُجالِس بعدك؟
قال: الكتب!
[ الفوائد المنتخبة لابن بشكوال - ١/ ٤١٣ ]
