قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Відкрити в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
899
Підписники
-224 години
-167 днів
+2730 днів
Архів дописів
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ጧሊበል ዒልም እና ኪታብ
~
1- ኪታብ ስንገዛ አቅም በፈቀደ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀውን እንግዛ። በተለይ የሚታወቅ አታሚ ወይም የሚታወቅ ሰው ያዘጋጀው ቢሆን መልካም ነው። ወይም ሰው ብናማክር ጥሩ ነው።
2- በጥንቃቄ እንያዝ። በጥንቃቄ ስለማንይዛቸው ስንት ኪታቦቻችን የሽፋን ፅሁፋቸው ደብዝዟል ወይም ጠፍቷል?! ስንቱ ወረቀታቸው ተነቃቅሏል?! ስንቱ ተቀዳደዋል?! ስለዚህ ውስጣቸው እርሳስና እስኪርቢቶ ማስቀመጥ፣ ወረቀት እያጥጠፉ ምልክት ማድረግ፣ ስርአት በሌለው መልኩ ላያቸው ላይ መለቅለቅ እና መሰል ልማዶችን መተው ይገባል። ይልቁንም ሽፋናቸውን በላስቲክ ወይም በፕላስተር መለጠፍ ይገባል። የምናስቀምጥበት ቦታም ጥሩ ቦታ ሊሆን ይገባል።
3- ሌላኛው ጥንቃቄ የሚፈልገው ማዋስ ላይ ነው። በጥንቃቄ በመያዝ፣ በጊዜ በመመለስ ለምታውቁት ካልሆነ በስተቀር ኪታብ አታውሱ። ብዙ ሰው የረባ የንባብ ልማድ ሳይኖረው እንዲሁ ጓጉቶ ይዋስና ወስዶ የትም ይጥለዋል። መጨረሻ ከማን እንደተዋሰው እንኳን አያስታውስም። በዚህ መልኩ ስንት ኪታብ ጠፍቶብናል? ስንት ኪታብ ጥለናል? አሁንም ይህንን ፅሁፍ የምታነቡ ሁሉ ኪታቦቻችሁን ፈትሹ። የተዋሳችኋቸውን ኪታቦች መልሱ። አማና ላይ አትዘናጉ። የምታውሱ ደግሞ የተዋሹን እና የኪታቡን ስም የተዋሰበት ቀን ጋር መዝግቡ።
4- ኪታቦች ላይ ወሳኝ ማስታወሻ ወይም እርምት ስትፅፉ ኪታቡን በማያበላሽ መልኩ ይሁን። በመጀመሪያ የረባ ዋጋ የሌለው ነገር መፃፍ አይገባም። ሁለተኛ ቢቻል እርሳስ ብንጠቀም ጥሩ ነው። ሶስተኛ በተቻለ መጠን ስርአት ባለው በሚነበብ መልኩ እንፃፈው። በችኮላ ፅፈነው ኋላ የራሳችንን ፅሁፍ ማንበብ የምንቸገር እንኖራለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኪታብ በማስተማር ላይ ለተሰማራችሁ
~
1- ለተማሪዎችህ የሚማሩትን ኪታብ መምረጥ። አቅማቸውን፣ የጎደላቸውን፣ የሚያስፈልጋቸውን እንጂ እንዲሁ የጠየቁትን ሁሉ አትጀምር። ተማሪ ያላቅሙ ትልቅ ኪታብ መጀመር ሊፈልግ ይችላል። ተማሪው በጥሩ ደረጃ ላይ ካለ የጠየቀውን ብትቀበልም ችግር የለውም።
2- የምታቀርበው ትምህርት፣ የምትመልሰው ጥያቄ ታዳሚህን ያገናዘበ ይሁን። ሰፊ ህዝብ የሚታደምበት ደርስ ላይ የሚኖርህ አቀራረብ በ'ቂራአት' ገፋ ካደረጉ ተማሪዎች ጋር ከሚኖርህ ጋር በይዘቱም፣ በቋንቋውም፣ በመጠኑም ሊለይ ይገባል። ለምሳሌ ከመግሪብ እስከ ዒሻ መስጂድ ውስጥ የሚሰጥ ደርስ ላይ ጠለቅ ያለ ኺላፍ አትተንትን። ይሄ ማስተማር ሳይሆን ማደናገር ነው። ኺላፍ ጆሯቸውን ከመታቸው ተማሪዎች ጋር ስትሆን ደግሞ በተቻለ መጠን 'ራጂሕ' እና 'መርጁሑን' ባቅማቸው መጠን ለይተህ አቅርብ። ብዥታዎችን ግፈፍ። የምታቀርበው ነገር ግልብ ከሆነ ደርስህን ጣዕም ያጡበታል። ባጭሩ ትምህርት ታዳሚዎችህን ያገናዘበ ይሁን።
3- ተዘጋጅተህ ቅረብ። ቢያንስ ገረፍረፍ አድርገው። ተማሪዎችህ ፊት አትደናበር። በቅጡ ሳትይዝ ቀርበህ ሸርሕ ላይ በፍለጋ አትባዝን። የቀለም ትምህርት ላይ እንኳ አስተማሪዎች ተዘጋጅተው ነው የሚቀርቡት። የዲን ጉዳይ የበለጠ ጥንቃቄ ይፈልጋል።
4- ካ'ቅምህ በላይ ካልሆነ በስተቀር ቀሪ አታብዛ። ደርስ አታቆራርጥ። ይሄ የተማሪዎችን ሞራል በጣም ያቀዘቅዛል።
5- ተማሪዎችን አታሸማቅ። አንዳንዱ አስተማሪ ጥያቄዎችን በቅንነት አይረዳም። ሁሉ ነገር መፈታተን ይመስለዋል። ይሄ መሆን የለበትም። መፈታተን የሚፈልግ፣ ልታይ ልታይ የሚል፣ መጥፎ አቀራረብ ያለው ተማሪ ካለ እንዳስፈላጊነቱ በጥቅል ወይም በተናጠል ለይተህ ምከር። ካልሆነ ጠንከር አድርገህ ገስፀው። ነገር ግን ቁጣችን የራሳችን ድክመት መሸፈኛ ሊሆን አይገባም። በአስተማሪዎች ከባድ ባህሪ የተነሳ ስንት ደርስ ተበትኗል! ስንት ተማሪ ተሰናክሏል! ስንት የደዕዋ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል!
6- ድንገት ያልገባህ ነገር ከገጠመህ ወይም የማታውቀው ጥያቄ ከተጠየቅክ አትደንግጥ። አንተ ሁሉን እንደማታውቅ ይታወቃል። አይቼ እመጣለሁ፣ አላውቀውም በል። እንጂ እርግጠኛ ባልሆንክበት በግምት እንዳትመልስ። አደራ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from N/a
🌆ለቁርዓን ያላችሁን ፍቅር በሚገርም ሁኔታ የሚጨምርና ጣሪያ እንዲነካ የሚያደርግ አጂብ የሚያሰኝ የቁርዓን ቻናል ተወዳጅነትን አትርፏል🔋
🗳ወላሂ ሐቂቃ ማስታወቂያ ነው ተቀላቀሉ🗳
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ሁሉን ማመን አለቀኝ ያለ በሽታ ሆነብኝና....ብዙ ነገሬ.......
«ሰው አምናለሁ»
ወዳጅ መስለው ለቀረቡኝ፡
ወንድም ብለው ለሚያስቡኝ፡
ለሁሉም ሰው እባባለሁ ሁሉም ደግሞ ያጠቃኛል፡
ንፁህ ሆኘ የቀረብኩት ቀን ጠብቆ ይጎዳኛል፡
እኔ ያው ነኝ ምንም ብሆን አልቀየር፡
መሬት ለቆ ቢሄድ ባየር፡
ስንቱ መጥቶ ወግቶኝ ሔዷል፡
ንፁህ ልቤ ብዙ ነጉዷል፡
ግን አሁንም እንደዛው ነው፡
ነገ እንደት ነው የምሆነው!?
ይህ ባህሪዬ እየሳበኝ፡
የነግ ህልሜ አሳሰበኝ፡
የማይሻል ህመም አለኝ፡
አንድ እሱ ነው የጎደለኝ፡
በሩቃ ኬዝ የማይወጣ፡
እጂግ በጣም የሚቀጣ፡
ልብ ላለው የሚያስቆጣ፡
ልብ አዕምሮን የሚሰብር፡
ህያው አርጎ የሚቀብር፡
ደም የሚመጥ እንደ ነብር፡
የታሸገ በፈገግታ፡
አብሮኝ ያለ ጧትም ማታ፡
የሚሰጠኝ ለበሽታ፡
አለኝ ሰይጣን አለኝ ልምሻ፡
ጫፍ የሌለው መዳረሻ፡
ሰው አምናለሁ… እንደ ውሻ!
...ይህን ባህሪ መቀየር አልቻልኩም ወዳጆቼ እስኪ ምክር ስጡኝ ..በአሏህ...⁉️
...ኑር....✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
لا تكُن إِمَّعَةً
تميل مع النَّاس حيثُ مالُوا
كُن صاحِبَ عقِيدة
كُنْ مع الحَقِّ فِي كُلِّ زمَانٍ ومَكَان
- أنتَ الجَمَاعَةُ وَلَو كُنتَ وَحْدَكَ!.
Repost from قناة أبي ماهر الأثري الحبشي𝐀bu Mahir )
እነ ሙስጦፍና ግብረ አበሩ ኡዙር የለም ኡዙር አለ የሚል ሙርጅአ ነው ካፊር ነው ይላሉ ያለምንም ማስረጃ ቁጭብለው ከኹዝ ጀምረው መቅራት ሲገባቸው አዋቂነን ብለው ተነስተዋል ለመሆኑ መቼ መቼ ዳአዋ አድርገው ነው ሰውን ለማክፈር የዘመቱት አጅብነው ሲጀመር ዳአዋተ ሰለፍያን አካሄድ መቼ ሲያዉቁት እውቀት ያለውኮነው የዳአዋን ሲስተም የመሚያውቀው በጩኸትና በስድብ የተሞላ ዳአዋ መሆኑ ግልፅነው እኛንም እያከፈሩነው ሁሉንም አክፍረው እስልምናን እራቁቱን ለማስቀረት የተነሱ አካላቶች ናቸው ስለዚህ ሸይኸ ኡሰይሚንንም ይህን ታላቅ የሱና አሊም ሊያከፍሩነው በቃል ባይደፍሩትም በተግባር አክፍረዋል ይህ ታላቅ የሱና አሊም ሸይኸ ኡሰይሚን ስለኡዙር ቢል ጀህል ተጠይቀው በግልፅ ኡዙር እንደሰጡ በግልፅ ቋንቋ
ጠያቂ: አንድ ሴት በአውሮፖ ወይም በአፍሪካ ትኖር ነበር ከዚያ ሞተች በመቃብር ጦዋፍ ታድርግ ነበር ለመቃብር ታርድ ነበር እዚያ አካባቢ ተወሂድ የሚያስተምር እና ለሷ ስለ ተወሂድ ሽርክ የሚያብራራላት አካል አልነበረም ይች ሴት ምክንያት (ኡዙር ) ይሰጣታልን ልጆቿ ዱአን ማድረግ እና ዱአ ማድረግ የሚፈልግ አካል ለእሷ ዱአ ማድረግ ይቻላልን ?
ምላሽ : በእስለምና ውስጥ ገብታ ከዚያ ሽርክን ቋጠረች ማንም አካል ሽርክ መሆኑን የነገራት ያብራራላት (ሁጃ ያቆመባት) የለም ይች ሙስሊምናት !!!
እንደማንኛውም ሙስሊም ትታያለች ከሞተች ይሰገድባታል ሙስሊሞች መቃብር ትቀበራለች ልጆቿ ዱአ ያደርጉላታል ምክንያቱም አላዋቂ ናት ሽርክ መሆኑን አላወቀችም ለእሷ የሚያብራሩ ኡለማዎች (ሁጃ የሚያቆሙ) የሉም ይች ጃሂል ናት አላህ በተከበረው ቃሉ ( እኛ መልእክተኛን እስክንልክ ድረስ አንቀጣም ) ብሏል ።
Repost from قناة أبي ماهر الأثري الحبشي𝐀bu Mahir )
[ بين المذنب والمبتدع ]
ومعلوم أن المذنب إنما ضرره على نفسه، وأما المبتدع فضرره على النوع.
وفتنة المبتدع في أصل الدين، وفتنة المذنب في الشهوة.
والمبتدع قد قعد للناس على صراط الله المستقيم يصدَّهم عنه، والمذنب ليس كذلك.
والمبتدع قادح في أوصاف الرب وكماله، والمذنب ليس كذلك.
والمبتدع مناقض لما جاء به الرسول ﷺ، والعاصي ليس كذلك.
والمبتدع يقطع على الناس طريقَ الآخرة، والعاصي بطيء السير بسبب ذنوبه.
• ابن القيم | الداء والدواء صـ (٣٣١-٣٣٢)
=
https://t.me/A2mnt
የእውቀት ባለቤቶች እና የስሜት ባለቤቶች ልዩነት
